en
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Open in Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Show more
1 161
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መደበኛ ምልዓተ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ በተለያዩ ምክንያቶች ብፁዓን አባቶች በተጓደሉባቸው አራት አህጉረ ስብከት የብፁዓን አባቶችን ምደባ አከናወነ !!! ❤ ግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም (ተሚማ/አዲስ አበባ) ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ ❤ መደበኛ ምልዓተ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ በተለያዩ ምክንያቶች አባቶች ባልተመደቡባቸው አራት አህጉረ ስብከት የብፁዓን አባቶችን ምደባ አከናወነ። ❤ ላለፉት ቀናት በበዓላትና በዕረፍት ቀናት ምክንያት ሳይካሄድ የቆየው ምልዓተ ጉባኤው በዛሬው ዕለት ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በዛሬው ውሎው በተለያዩ አህጉረ ስብከት የብፁዓን አባቶችን ምደባ አከናውኗል። ❤ የብፁዓን አባቶች ምደባ የተከናወነባቸው አህጉረ ስብከት ኢሉአባቦራ ፣ አፋር ፣ ከሚሴ እና ምዕራብ ካናዳ አህጉረ ስብከት ሲሆኑ በዚህም መሠረት 1.ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከትን እንደያዙ የከሚሴ ሀገረ ስብከትን እንዲመሩ። 2.ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ኤዎስጣቴዎስ የሚኒሶታ ሀገረ ስብከትን እንደያዙ የኢሉአባቦራ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ ። 3.ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከትን እንደያዙ የአፋር ሀገረ ስብከትን እንዲመሩ። 4.ብፁዕ አቡነ አብርሃም የኤድመንተን ሀገረ ስብከትን እንደያዙ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከትን እንዲመሩ የተወሰነ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ❤ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እየተወያየ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ውይይቱን እንደቀጠለ ሲሆን በወቅታዊ ሀገራዊና የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል። ምንጭ፦ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰባኬ ወንጌል ሐዋርያት ትንቢት ለቤተክርስቲያን ዘይደምጽ ቀርን ነባቤ ለቤተክርስቲያን፡፡ ዮሐንስ ኮከብ ዘኤፊሶን አምደ ብርሃን ዘፍጥሞ መልአክ (ዘበምድር) ፪ መልአክ"። ትርጉም፦ ለቤተክርስቲን ድምጽ የሚያሰማ ቀርን ወንጌልን የሚሰብክ ከሐዋርያት ትንቢት የተናገረ፡፡ የኤፊሶን ኮከብ የፍጥሞ የብርሃን ምሰሶ ዮሐንስ በምድር ያለ መልአክ ነው። የቅዱስ ዮሐንስ መዝሙር። https://t.me/Eotcw

❤ ዮሴፍንም እርሱን የመሰለ ደግ ሰው እንዳልተወለደ። ኖኅና ሴምንም ክብራቸው ከሰው ሁሉ እንደሚበልጥ። አዳምንም በፍጥረት ሁሉ ላይ ንጉሥ እንደ ሆነ። ሰምዖንን በዘመኑ ቤተ መቅደስ እንደ ታነፀ በሕዝቡ ከምርኮ መመለስም እንደ ተመሰገነ በመጽሐፋ መጨረሻም "በሁሉ ቦታ ታላላቅ ሥራ የሚሠራና ዕድሜያችንን የሚያስረዝም እግዚአብሔር አምላክን አመስግኑት" አለ። ይህንንም ተናግሮ በፍቅር አንድነት ግንቦት16 ቀን ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የቅዱስ ሢራክ በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት16 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ዕብል ለሲራክ ፍጹም። ወልደ አልዓዛር ዘኢየሩሳሌም። ቈሪር ማይ ከመ ያጠፍኦ ለፍሕም። ያጠፍእ ይቤ መጽዊቶ ብእሲ ድኩም። ኃጣውኢሆሙ ለሥጋ ወደም"፡፡ ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 16። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አመ ትሠምር መሥዋዕተ ጽድቅ። መባዓኒ ወቊርባነኒ። አሜሃ ያዐርጉ ውስተ ምሥዋዒከ አልሕምተ"። መዝ 50፥19። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 14፥29-ፍ.ም። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወአርመመ ማዕበል። ወተፈስሥሑ እስመ አዕረፋ። ወመርሆሙ ውስተ ምርሶ ኀበ ፈቀዱ"። መዝ 106፥29-30። የሚነበቡት መልዕክታት ቈላ 2፥1-6፣ ራእ.ዮሐ 1፥1-12 ወይም 1ኛ ዮሐ 1፥1-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 8፥14-26። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 21፥20-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ የወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ የመታሰቢያ በዓልና የቅዱስ ሢራክ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፲፮ (16) ቀን። ❤ እንኳን ለሐዋርያው ወልደ ነጐድጓድ ለቅዱስ ዮሐንስ በእስክድርያ ቅዳሴ ቤቱ፣ በኤፊሶን መከራና ስብከቱ፣ በደሴተ ፍጥሞ ግዞቱ ለሚታሰብበት ዓመታዊ በዓልና ዕውቀትን ከልቡ ላፈለቀ ለኢየሩሳሌሙ ሰው ለአልዓዛር ልጅ ለቅዱስ ኢያሱ ሢራክ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ከሚታሰበው፦ በሰማዕትነት ከዐረፉ ኤጲስ ቆጶሳት ከዮሴፍ ልጅ ይምንዋስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ በዚች ቀን ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያው ነው። በእስያና በኤፌሶን በዙሪያቸው በአሉ አገሮች ሁሉ ስለ መስበኩና ከባሕር በመስጠምም ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር እስከ መለሳቸውና የክብር ባለቤት ጌታችን በእጆቹ ላይ በሚያደርገው ተአምራት በትምህርቶቹም ከሰይጣን ወጥመድ እስከ አዳናቸው ድረስ ጣዖታትን ከሚያመልኩ ከክፉዎች ሰዎች ስለደረሰበት መከራ ነው። ❤ በሸመገለም ጊዜ ወንጌልን ጻፈላቸው ሦስቱ ወንጌላውያን ያስቀሩትን እስከሚጽፍ መንፈስ ቅዱስ አነሣሥቶታልና የወልድንም አኗኗሩንና ሰው መሆኑን ዓለም የማይወስነውንም ተአምራትን። ❤ ከዚህ በኋላም ወደ ሰማይ እንደ ወጣና በሰማይ የሚኖሩ መላእክት ሠራዊት ሥርዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ። ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ሊሆን ግብጻውያን ይህን ሠሩ ዳግመኛም በእስክንድርያ አገር ውስጥ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ቀን ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ ሐዋርያ በቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የአልዓዛር ልጅ ቅዱስ ኢያሱ ሢራክ፦ እርሱም ጥንተ ትንቢት "የባሕር አሸዋን የዝናም ጠብታን የዘመንን ቁጥር ማን ቈጠረ" አለ። ከአብ ጋራ ስለ አለው አንድነት "የጥበብ ምክሯንስ ማን አወቀ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ የምትቀመጥ እጅግ የምታስፈራ ናት" አለ። ሁለተኛም "እኔ ከልዑል አፍ ወጥቼ ምድርን እንደ ጉም ሸፈንኋት በሰማያትም እኖራለሁ ዙፋኔንም በደመና ምሰሶ ላይ ዘረጋሁ ብቻዬን በሰማይ ዳርቻ ዞርኩ በውቅያኖስም ጥልቅ ውስጥ ማረፊያ እየፈለግሁ በባሕሩ ውኃ ላይ ሁሉ ተመላለስኩ" አለች አለ። ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን እንዲህ አለ "እግዚአብሔር በያዕቆብ ዘንድ እደሪ በእስራኤልም ዘንድ ተዋረሺ አለኝ አለች"። ❤ ደግሞ ስለ መድኃኒታችን ሞትና ስለ አይሁድ መጥፋት "በወጥመዱ ይጠመዳሉ የመሞቻቸው ጊዜም ሳይደርስ ይሠጥማሉ" አለ። ስለ ንስሓና ከንስሓ በኋላ ወደ ኃጢአት ስለ መመለስ እንዲህ አለ "ከታጠቡ በኋላ ቆሻሻን መዳሰስ ምን ይጠቅማል"። ❤ ደግሞ ስለ ቤተ ክርስቲያን መታነፅና ስለ ሕዝቡ እንዲህ አለ "አቤቱ በስምህ የተጠሩና በበረከት ያባዛኃቸውን ወገኖችህን ይቅር በል መመስገኛህና ማደሪያህ የሆነች አገርህ ኢየሩሳሌምንም ይቅር በል። የቃልህንም በረከት በጽዮንና በልጆቿ ላይ ምላ"። ❤ ስለ ሹማምንትና ስለ ሰባቱ መዐርጋት ሲናገር እንዲህ አለ "ሰባቱን ኃይሎች የተቀበለች የሰው ሰውነቱ ጉበኛ ናት። ከዚህም ሁሉ ጋር መንገድህን ያቀናልህ ዘንድ ወደ ልዑል እግዚአብሔር ጸልይ"። ❤ ስለ ጻድቃንም እንዲህ አለ "የጻድቃን ልጆች በዱር ጠል የዱር አበባ እንዲአብብ እንዲሁ ብቀሉ አብቡም እንደ ሊባኖስም መዓዛ መዓዛቹ እንዲሁ የጣፈጠ ይሁን" ዳግመኛም የእግዚአብሔር ሥራ ሲያስቡ እንዲህ "የሰማይ ንጽሕናውንና ጽናቱን ብርሃኑንም ያሳይ ዘንድ በሰማይ ገጽ ላይ ፀሓይን ማውጣቱን በቀትርም ጊዜ አገሩን ማቃጠሉን አስቦ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድ ላቦቱን ማን ይቀወመዋል የፀሐይ ዋዕይ" ሦስተኛውም "ተራራችን ያቃጥላቸዋል ከእርሱም የእሳት ወላፈን ይወጣል" አለ። "ጨረቃም ለዓለም ምልክቱ ነው በእርሱም ዘመናት የበዓላት ምልክት ይታወቃል"። ስለ ከዋክብትም "የሰማይ ጌጦቿ የከዋክብት ብርሃናቸው ነው በእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ እንዲሁ ያበራሉና በሥርዓታቸውም ጸንተው ከልካቸውም ሳይፋለሱ ሳይሳሳቱ ጸንተው ይኖራሉና" አለ። ስለ ቀስተ ደመናም ተናገረ "ቀስቱን አየሁ ፈጣሪውንም አከበረ ብርሃኑ መልካም ነውና የልዑል ሥልጣንም ያዘጋጀዋል"። ❤ ስለ በረድና መብረቅም ተናገረ ስለ እርሱ "ትዕዛዝም በረድ ይዘንማል በቃሉም መብረቅ ይፈጥናል ደመናትም እንደ አዕዋፍ ይበራሉ ነፋስም በእርሱ ፈቃድ ይነፍሳል የነጐድጓዱ ድምፅና ብልጭልጭታም ምድርን ያስፈራታል ዐውሎውና ውርጩ ነፍስን ያስጨንቃታል። ሰማይን እንደ ብረት ልብስ የሚሸፍነው እንደ ስለታም የብርጭቆ ስባሪ ይብለጨለጫል" አለ። ❤ ስለ ዝናምም ተናገረ "ዝናም የወረደ እንደሆነ ምድርን ደስ ያሰኛታል በትዕዛዙም ባሕር ይደርቃል" አለ። አባቶችንም በተሰጣቸው ሀብት ሲያመሰግናቸው "ኄኖክ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘው። ኖኅም ጻድቅ ሁኖ እንደተገኘ። አብርሃም ታማኝ እንደሆነ ይስሐቅም ለሰው ሁሉ የሚጠቅም በረከት እንደተሰጠው ለያዕቆብም በቸርነቱ እንደ ተገለጠለት ዐሥራ ሁለቱንም ነገድ እንደወለዳቸው በሰውና በእግዚአብሔርም ዘንድ እንደ ተወደዱ። ❤ ሙሴንም ስም አጠራሩ የከበረ የመላእክትም ብርሃን መልኩና ስም አጠራሩ የሆነ" አለ። ወንድሙ አሮንንም "የዘላለም ሕግን እንደ ሠራለት በልብሰ ተክህኖና በወርቅ አክሊል እንዳስደነቀው" አለ። ሹመቱ ሦስተኛ የሚሆን የአልዓዛር ልጅ ፊንሐንስም ወደሰ። ❤ የነዌ ልጅ ኢያሱን ለእስራኤል ልጆች የርስታቸውን ምድር እንዳወረሳቸው እጁንም በአነሣ ጊዜ እንደተመሰገነ። ሳሙኤልንም በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ እንደሆነ ናታንንም በዳዊት ዘመን ትንቢት እንደተናገረ። ዳዊትንም ታናሽ ሁኖ ሳለ አርበኛውን ጎልያድን እንደገደለው አመስግኖታል ሰሎሞንንም በሰላም ወራት እንደነገሠ። ❤ ኤልያስንም ሙት እንዳስነሣ እሳትንም ከሰማይ እንዳወረደ ራሱም በእሳት ሠረገላና በእሳት ፈረሶች እንደዐረገ ኤልሳዕንም በዘመኑ ጠላቶች እንዳስደነገጡት ሁለት ሙታኖችንም እንዳስነሣ አንዱን በሕይወት ሳለ አንዱን ከሞተ በኋላ ። ❤ ሕዝቅያስንም አገሩን አጽንቶ እንደጠበቀ የፋርስንም ሠራዊት በጸሎቱ አጥፍቶ ስለ አገራቸው ጽዮን የሚያለቅሱትን ደስ እንዳሰኛቸው ርኵሰትንና ኃጢአትንም እንደ አስወገደ። ኢዮስያስንም የኢዮስያስ ስም አጠራሩ መልካም ነው እንዳለው። ❤ ኤርምያስንም ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ እንዳከበረው። ሕዝቅኤልም የእግዚአብሔርን ጌትነቱን እንዳየ። ዘሩባቤልንም በቀኝ እጅ እንዳ ኀቲም ቀለበት ነው እንዳለው። ዐሥራ ሁለቱ ነቢያትንም በየቦታቸው ዐፅማቸው እንደሚለመልም። ሆሴዕና ነህምያንም የወደቀች ቅጽርን አንሥተው ጠቃሚ ሥራ እንደሠሩ።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፲፮ (16) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለአቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ከዚህ ዓለም ከሞት ለተሰወሩበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ፦ የትውልድ አገራቸው ሸዋ መርሐ ቤቴ ነው። ጻድቁ ተሰውረዋል እንጂ አልሞቱም ገና ወደፊት መጥተው በሰማዕትነት ይሞታሉ። የነበሩበት ዘመንም በጻድቁ ንጉሥ በዐፄ ገብረ ማርያም ሐርበይ ዘመን ነው። ጻድቁን መልአኩ ከሚያገለግሉበት ከወሎ የህላ ሚካኤል ወደ ደብረ በንኰል ገዳም ወስዷቸው እንዲመነኵሱ አድርጓቸዋል። የቆረቆሩት "አቡነ ሐዋርያት ክርስቶስ ገዳም" ወሎ መሐል ተከዜ ውስጥ ይገኛል። ከአቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን! ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፲፭ (15) ቀን። ❤ እንኳን ለሐዋርያው ስምዖን ለተባለው ለቅዱስ ናትናኤል ለዕረፍት በዓል፣ በላይኛው ግብጽ ውስጥ በደንደራ ከተማ በሰማዕትነት ለዐረፉ ለአራት መቶ ሰዎች ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ ከባሕታዊ ሚናስ፣ ከዲያቆንና ከአባ ሐርበጥላክያ ሰማዕታት ከሆኑ ከኤስድሮስም ማኅበር ከሆኑ ቀርጢኖስና ሚስቱ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ሐዋርያው ስምዖን የተባለው ቅዱስ ናትናኤል፦ እርሱም ናትናኤል ተብሎ ይጠራል በገሊላ አውራጃ የቃና ሰው ነው የኦሪትና የነቢያትንም መጻሕፍት ተምሮ ያወቀ ነው። መንፈሳዊ ቅንዓትም በውስጡ አለበት ስለዚህም ቀናዒ ተባለ እርሱም ንጹሕ ፊት አይቶ የማያደላ በሃይማኖቱ ዕውነተኛ ነው። ስለዚህ ፊልጶስ "ስለርሱ ሙሴ የጻፈለትን የዮሴፍ ልጅ የሚሉት የናዝሬቱን ኢየሱስ ክርስቶስን አገኘነው" ባለው ጊዜ "ከናዝሬት ደግ ሰው ሊወጣ ይችላልን?" አለው እንጂ አላደላለትም ፊልጶስም "ታይ ዘንድ ና" አለው። በመጣም ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን "ይህ በልቡ ሽንገላ የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ ነው" አለው። አሁንም ምስጋና ወደመቀበል አልተመለሰም "በየት ታውቀኛለህ" አለው እንጂ ልብንና ኵላሊትን የሚመረምር ጌታችንም "ፊልጶስ ሳይጠራህ በፊት በበለስ ዕንጨት ሥር አየሁህ" አለው። ያን ጊዜም የተሠወረውን የሚያውቅ አምላክ መሆኑን ተረድቶ "ጌታዬና ፈጣሪዬ በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ" አለው እንደ አይሁድ መምህራንም አልተቃወመም እርነሱ ከዚህ የሚበልጥ ድንቅ ተአምራትንና ኃይሎችን አይተው በእውነት አልተገዙምና። ❤ ስርሱ እንዲህ ተብሏል ጐልማሳ ሁኖ ሳለ ከአሕዛብ ወገን ከሆነ ጐልማሳ ጋራ ተጣልቶ አንዲት አመታትን መትቶ ገደለው በቤቱ ዐፀድም በአለ ዕፅ በለስ በሥሩ ቀበረው ይህንንም ማንም አላወቀበትም። ሁለተኛም በሕፃናት ዕልቂት ጊዜ እናቱ በአገልግል ውስጥ አድርጋ በበለስ ዕንጨት ላይ ሰቅላ ትሸሽገው እንደ ነበር በጭልታም አውርዳ አጥብታ መልሳ ትሰቅለዋለች የመከራውም ጊዜ ጸጥ እስከ አለ ድረስ እንዲህ ታደርግ ነበር። መድኃኒታችንም በምልክት ከእርሱ የሆነውን በገለጠለት ጊዜ የተሠወረውን የሚያውቅ ሁሉንም የሚመረምር በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ተረዳ። ያንጊዜም ራሱን ዝቅ አድርጎ ለመድኃኒታችን ተገዛለት። ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ ተከተለው ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያትም ጋራ ተቈጠረ። ❤ አጽናኝ የሆነ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በተቀበለ ጊዜ የአገሩ ሁሉ ቋንቋ ተገለጠለት መለኮታዊ ምሥጢርንም አወቀ ወደ ኵርጅ አገርና ወደ እልብጅህ ከተማ በሀድያን በድንቁርና ወደሚኖሩበት ሁሉ ገብቶ የሃይማኖትን ብርሃን አበራላቸው። ከተራቃቂዎችና ከሰነፎችም ብዙዎችን መልሶ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ሃይማኖት ልባቸውን አበራላቸው። የክርስትና ጥምቀትንም አጥምቆ ነጣቂዎች ተኵላ የነበሩትን የዋሃን በጎች አደረጋቸው። ❤ ሁለተኛም ወደሌሎች የከሀድያን አገሮች ወደ በራንጥያ ደሴትም ሒዶ በውስጣቸው ሰበከ። ይዘውም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃዩት እርሱ ግን ኃይልና ብርታትን ተጨመረ በእግዚአብሔርም ኃይል ሙታንን አስነሣ እንዲአጠምቃቸውም ለመኑት የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ብዙ ዘመንም ኖረ። ከዚያም በኋላ ከሀድያን ይዘው በዕንጨት ላይ ሰቀሉት በዚህም ምስክርነቱን ፈጽሞ ከወንድሞቹ ሐዋርያት ጋራ የማይጠፋ መንግሥት ወረሰ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ናትናኤል ጸሎት ይማረን ለሁላችን የክርስቲያን ወገኖችም በረከቱ ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አራት መቶ ሰማዕታት፦ ብዙ ሥቃንም ሲያሠቃዩአቸው ከኖሩ በኋላ የምስክርነታቸው ፍጻሜ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግሥት መጨረሻ ራስን በመቆረጥ ሆነ። በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 15 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ዕብል ብእሴ ምሁር። ዘመጽሐፈ ኦሪት ሕገ ወዘነቢያት መዝሙረ። አመ ውእቱ ወሬዛ ታሕተ ዕፀ በለስ ዘገብረ። ወልደ ማርያም አምላክ ሶበ ኅቡአቶ አእመረ። ለትእዛዘ ጽድቁ ናትናኤል ገረረ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 15። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ ብፁዕ ብእሲ ዘኢኈለቈ ሎቱ እግዚአብሔር ኃጢአቶ። ወዘአልቦ ጽልሑት ውስተ ልቡ። እስመ አርመምኩ በልያ አዕፅምትየ"። መዝ 31፥2-3። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 1፥44-ፍ.ም። + + + ❤ የዕለቱ ቅዳሴ ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 8፥24-35፣ ይሁ 1፥17-23 የሐዋ ሥራ 1፥12-15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥1-16። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ነው። መልካም የሐዋርያው ስምዖን የተባለው የቅዱስ ናትናኤል የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

መዝ.አርአየ ዝማሬ-1621913183537.mp34.06 MB

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለገብረ ክርስቶስ ብእሴ እግዚአብሔር ለነፍሱ ዘኮነ ኬንያ ዘአብዕዎ መላእክት ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ እንዘ ይብሉ፡ሃሌ ሉያ"። ትርጉም፦ ሃሌ ሉያ እያሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት መላእክት ያስገቡት ለነፍሱም ጠቢብ የእግዚአብሔር ሰው ለኾነ ለገብረ ክርስቶስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለአባ ጳኵሚስ ዘኮነ ማኅደሮ ለቅዱስ መንፈስ፤ ዘአጥረየ ብዙኃነ ደቂቀ እለ ይትጌበሩ ጽድቀ"። ትርጉም፦ የጽድቅ ሥራን የሚሠሩ ብዙዎች ልጆችን የሰበሰበ ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ለኾነ ለአባ ጳኵሚስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ እንኳን ለትንሣኤ አምስተኛ ሳምንት ዕለተ ጥብርያዶስ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። + + + ❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፮ "አርአየ ሥልጣኖ ላዕለ ሞት አርአየ ሥልጣኖ ላዕለ ሞት ንጉሠ ነገሥት እግዚአ አጋግእዝት፤ አዝ፣ ዘይቤብሕዎ ሊቃነ መላእክት ይሰግዱ ሎቱ ቅድሜሁ በፍርሃት፤ አዝ፣ ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአይሁድ አመ ይእኅዝዎ በይእቲ ሌሊት፤ አዝ፣ ተናግሮሙ ወይቤሎሙ ከመ ሠራቂ መጻእክሙ ተአኀዙኒ በመጥባሕት፤ አዝ፣ ኦ ትዕግሥት ወአርምሞት በፍቅረ ዚአነ በጽሐ እስከ ለሞት፤ አዝ፣ ወንህነኒ ንግበር ቅድስት ፋሲካ በሐሤት አርአየ ሥልጣኖ ላዕለ ሞት ገባሬ ሕይወት ክርስቶስ። ትርጉም፦ ሊቃነ መላእክት የሚያመሰግኑት በፊቱም በፍርሃት የሚሰግዱለት፤ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶች ጌታ ክርስቶስ በሞት ላይ ሥልጣኑን አሳየ። ኢየሱስ በተያዘባት በዚያች ሌሊት አይሁድን እንዲህ አላቸው፤ በሰይፍ ልትይዙኝ እንደ ሌባ ድንገት መጣችሁ አላቸው፤ በእኛ ፍቅር እስከ ሞት ደረሰ፤ ይህ ትዕግሥትና አርምሞ ከሃሊነት ምን ይረቅ ምን ይደንቅ ምን ይጠልቅ ኦ ወዮ እንደምን ያለ ረቂቅ ነው ለዚህ አንክሮ ይገባል፤ እኛም በታላቅ ደስታ የተለየች ፋሲካን እናድርግ፤ የሕይወት ፈጣሪ ክርስቶስ ሥልጣኑን (ኀይሉን) በሞት ላይ ገለጧልና። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር። እግዚኦ አነ ገብርከ። ገብርከ ወልደ አመትከ"። መዝ 115፥15-16 ወይም መዝ 30፥16-17። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥6-6 ወይም ማር 14፥26-ፍ.ም። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "በልዑ ወጸግቡ ጥቀ። ወወሀቦሙ ለፍትወቶሙ። ወኢያኅጥዖሙ እምዘፈቀዱ። መዝ 77፥29-30 ወይም 106፥16-17። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 4፥14-ፍ.ም ወይም 6፥1-15፣ ራዕ 20፥1-ፍ.ም ወይም 1ኛ ጴጥ 4፥4-12 እና የሐዋ ሥራ 10፥39-44 ወይም 23፥15-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ያሳይና የአቡነ ጳኵሚስ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ። ሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፲፬ (14) ቀን። ❤ እንኳን ከመንፈሳውያን ሐዋርያት ጋር አንድነት ላላቸው ለከበሩ አባት የገዳማውያን የአንድነት ማኅበር ለመሰረቱ ለአባ ጳኵሚስ ለዕረፍት በዓልና በምስር ገዢ በሆነ በቡላሚስ ዘመን ከአገረ ፈርማ ሰማዕት ከሆነ ለአባ ሲማኮስ ለዕረፍት በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ ከሚታሰቡ፦ ከአባ ሲማኮስ ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበሉ ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ አባ ጳኵሚስ፦ ይህም ቅዱስ ከአባ ጰላሞን ዘንድ መንኵሶ ሲያገለግለው የምንኵስናንም በጎ ሥራ እየሠራ ብዙ ዘመናት ኖረ። ከዚያም በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገልጾለት እንደ አባቶቻችን ሐዋርያት የአንድነትን ማኅበር ለመሥራት መነኰሳትን እንዲሰበስብ አዘዘው። ከዚህም በኋላ ብዙዎችን ሰዎችን ሰብስቦ በየቦታው ብዙ ገዳማትን ሠራላቸው። ለሁሉም በእጃቸው ሠርተው የሚአገኙትና በምግባቸው አንድነት እንዲሆኑ በጸሎት ጊዜ በመብልም የሚሠሩትን ሥርዓት ሠራላቸው እርሱ ከሁሉም በላይ አበ ምኔት ሁኖ ከበታቹ በገዳማት ለየአንዳንዱ አበ ምኔት ሾመላቸው። በአገረ እስዋን ወሰን ከአትፉ ከአክሚም ከተናዱስ እስከ ላዕላይ ግብጽ መጨረሻ ከደቡብም ከባሕራውያን የተመሳቀለ መንገድ ድረስ ሁሉንም ገዳማት በመዞር ይጐበኛቸዋል። ❤ ይህም አባት ስለዚህ ዓለም ከንቱ ውዳሴና በመካከላቸውም ጥል እንዳይኖር ከልጆቹ ክህነትን እንዲሾሙ አያሰናብትም ግን ለየአንዳንዱ ገዳም የሚቀድሱላቸውን ቀሳውስት ከዓለም አደረገ። ሊቀ ጳጳሳት ሐዋርያዊ አትናቴዎስ ወደ ላዕላይ ግብጽ በመጣ ጊዜ ይህን አባት ጳኵሚስን ቅስና ሊሾመው ወደደ። ከእርሱም ሸሸ። የከበረ አትናቴዎስም ልጆቹን "የማይናወጽ ቤትን የሠራህ ሆይ ከከንቱ ውዳሴ የራቅህ አንተ ብፁዕ ነህ ልጆችህም ብፁዓን ናቸው ብሎሃል በሉት አባታችሁን" አላቸው። ❤ አንድ ጊዜም ሲዖልን ያይ ዘንድ ወደደ እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ አውጥቶ በገነት የጻድቃንን ማደሪያ እንዲሁም በሲዖል የሥቃይን ቦታ አሳየው። ይህም አባት በአንድ ማኅበር ላይ እያጽናናቸውና ሥርዓትንም እየሠራላቸው አበ ምኔት ሁኖ አርባ ዓመት ኖረ። ከዚያም በኋላ በእርሱ ፈንታ ደመ መዝሙሩን ቴዎድሮስን ሹሙላቸው ግንቦት 14 ቀን በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጳኵሚስ በአማላጅነቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባ ሲማኮስ፦ ይህ ቅዱስ ቀጭን ልብሶችንና የከበሩ የሐር ልብሶችን የሚሠራ ነው። ወላጆችም አሉት እነርሱም ቴዎድሮስና ሲሲኮስ ናቸው። ቡላሚስ የሚባለው ከሃዲ መኰንን ክርስቲያኖችን ሊያሠቃይና ሊገድል እንደመጣ በሰማ ጊዜ አባ ሲማኮስ ሰማዕት ይሆን ዘንድ ወደደና ቤተሰቦቹን ተሰናብቶ ወደ ሰማዕትነት አደባባይ ወጣ፡፡ ወደ ሀገረ ድሜራ ቅርብ ወደሆነ ወደ ሀገረ በክሩዝ ሄዶ ከሃዲውን መኰንን አገኘው፡፡ እርሱም አንዲቷን ሰማዕት ይዞ ሲያሠቃያትና ወደ እሳቱ ምድጃ ሲጨምራት እሳቱም በተአምራት ሲቀዘቅስ ተመለከተ፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ሲማኮስ በፊቱ ቆሞ የጌታችንን ክብር መሰከረ፡፡ ❤ መኰንኑም አባ ሲማኮስን ይዞ ብዙ አሠቃየው፡፡ በዚህ ጊዜም አባ ሲማኮስ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበር፡፡ በመጀመሪያ ሰቀሉት፤ ቀጥለውም ከመንኰራኩር ውስጥ ጨምረው አበራዩት፡፡ ከእርሱም ብዙ ደም ፈሰሰ፡፡ አንዲትም ዐይኗ ሥውር የነበረች ሴት ደሙ ፈሶ ዐይኗን በነካት ጊዜ ዐይኗ ዳነ፡፡ ❤ ከዚኽም በኋላ ደግመው በእንጨት ላይ ሰቅለው አሠቃየው፡፡ በሥቃይም ላይ ሆኖ ወደ ጌታችን በለመነ ጊዜ አዳነው፡፡ መኰንኑም የአባ ሲማኮስን ራስ በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ፡፡ ሰያፊውም ይቆርጠው ዘንድ ሰይፉን መዘዘ ነገር ግን ኃይል ተነሥቶት ማነቀሳቀስ አቃተው፡፡ እንዲሁም ሁለተኛው፣ ሦስተኛው … እስከ ዐሥራ አራት ሰይፈኞች ኃይላቸው ደከመ፡፡ እነርሱም በምድር ላይ ወደቁ፡፡ ከዚህም በኋላ በአንገቱ ገመድ አስገብተው እስከ ረጅም ተራራ አናት ድረስ ጎተቱት፡፡ ነፍሱንም በክብር ባለቤት በጌታችን እጅ አሳልፎ ሰጥቶ የምስክርነት አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ከወታደሮቹም ውስጥ ዲዳና ደንቆሮ የነበረ የቅዱሱን ሥጋ ባየጊዜ ጆሮዎቹ ሰሙ፣ አንደበቱም መናገር ጀመረ፡፡ ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ ብዙ አረማውያንም የቅዱስ አባ ሲማኮስን ተአምራት አይተው በጌታችን አምነው ተጠመቁ፡፡ የጌታችንንም ክብር መስከረው በሰማዕት ዐረፉ፡፡ ቁጥራቸውም አንድ ሺህ ሰባት መቶ ኃምሳ ሆነ ወንዶችና ሴቶች ወጣቶችም፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሲማኮስ ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘዘላሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 14 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለአባ ጳኵሚስ ዘደቂቆ ባረከ ወረሰዮሙ ይኩኑ ከመ እምሰብእ አምላከ። ለመልእክተ ተስፋ ይትቀነይ ዘኢኮነ በከ። ኢገብረ አሣዕነ ለእራኀ እግሩ ተውሳከ፡፡ እንዘ በገዳም ይከይድ አሥዋከ"። ትርጉም፦ ልጆቹን የባረከ ለኾነና ከሰው ወገንም አምላክ ዘበጸጋ ይባሉ ዘንድ ያደረጋቸው ለኾነ ለአባ ጳኵሚስ ሰላምታ ይገባል፤ ከንቱ ላልኾነ ለተስፋ መልእክት ለወንጌል ይገዛ ዘንድ በገዳም እሾኽን እየረገጠ ለውስጥ እግሩ ጫማን አላደረገም። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 14። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

በቶሎ ይነበብ ልንነቃ ይገባል ለማንበብ 15 ደቅቃ ብቻ ስጥ ህይወትን ይቀየራል አትሳሳት share አድርገው ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ዓለም ወዴት እየሄደች ነው? 1. - መጽሐፍ ቅዱስን ማቃጠል በኡጋንዳ በይፋ ተረጋግጦአል * በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ፣ ወንድ ወይም ሴት በዝሙት ምክንያት ሌላውን የመክሰስ መብት የለውም *በአሜሪካ እየታየ ያለው የወንድ ለወንድና የሴት ለሴት ጋብቻ *ጀርመን ወንድም እህቱን ማግባት እንደሚችል ፣ አባት ልጁን:እናት ልጆአን የማግባት ፍቃድን መስጠቱ ፡፡ *የmiami ከተማበመንገድ ላይ ፣ በቤተ ክርስቲያን ፣ በገቢያ ፣ በእግር ኳስ ሜዳ ወዘተ ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነት በማንኛውም መንገድ ማግኘት እንዲችሉ መፍቀዶአ .*ካናዳ (ከእንስሳት ጋር የ sexታ ግንኙነትን መፍቀዶአ * በስፔን ውስጥ-የወሲብ ፊልሞች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በዩኒቨርሲቲዎች መፈቀዱ *- ለአካለ መጠን ያልደረሱ ዝሙት አዳሪዎች ፈቃድ ማሪ ሉክ በህግ መፈቀዱ *በመጨረሻም ዩኤስ አሜሪካ የሰይጣንን ቤተ ክርስቲያን ከፍታለች ፡፡ በይፋ። የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች ፣ መጨረሻው ተቃርቧል ፣ ጌታ ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል! ማርታናታ!!! ክርስትያኖች ትኩረታቸው እየተከፋፈሉ ሲሆን ዲያቢሎስ መለኮታዊውን ምህረት ለማስቆም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ነፍሳት ከእርሱ ጋር ሊወስድ ይፈልጋል ፡፡ ደቂቃ ካለዎት ... ይህንን መልእክት ያጋሩ ፡፡ ለምን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንተኛለን ? ስለ እግዚአብሔር ማውራት ከባድ የሆነው ለምንድነው ሐሜት ለመናገር በጣም ቀላል የሆነው ለምንድነው? የእግዚአብሔርን መልእክት ችላ ማለት ለምን ቀላል ሆነ? ይህንን መልእክት ለጓደኞችዎ ይልካሉ ወይም ችላ ይላሉ? እግዚያበሔር “በሰዎች ፊት ብትክዱኝ በአባቴ ፊት እክድዳችሁአለሁ” አለ ፡፡ እግዚያበሔር ከወደዱ ይህንን መልእክት ለምርጥ ጓደኞችዎ እና በቡድን በ 60 ሴኮንድ ውስጥ ያጋሩ ፡፡ እግዚአብሔር ይባርኮት. ኣሜን የአለም መጨረሻ ተቃርቧል አትዘናጉ አሁን ያለንበት 2013 ዓም + 5500 ዘመን=7513 ስለዚህ ከ 8ኛው ሽ ላይ ቀንሱት ። 8000 – 7513= 487 ዓም ይቀራል። ነገር ግን ሰምታችሁ ከሆነ ዘንዶ 400 ዓመት ገዝቷል ይባላል እስኪ ጠይቁ። እና የዘንዶው ሲቆጠር 487 – 400 =87 አመት ቀረው።ትንቢቱም እየተፈፀመ ነው። ሌላው ይህ በንዲህ እንዳለ ደሞ 666 አሁን እዚህ በደጃችን ነው፡፡ አጠንክረን እንፀልይ፡፡ የአውሬው ቁጥር 6 6 6 የሚፈፀምበት የትንቢት ጊዜ አልቋል/ተፈፅሟል፡፡ የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ባስተላለፈው የኦባማን የጤና ሽፋን ረቂቅ በህግ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ የህግ ተግባሩ በቅርቡ ይጀምራል፡፡ ይህን የጤና ሽፋን ረቂቅ በእያንዳንዱ የአሜሪካ ዜጋ የሰውነት ክፍል ላይ ግላዊ የሬዲዬ ፍሪኩዌንሲ ቺፕስ መልክ (RFID CHIPS) እንዲተከል ታዟል፡፡ ይህ ቺፕስ በግንባር ወይም በክንድ ላይ ይደረጋል፡፡ ይህ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው በራዕይ 13 : 15 -18 የተቀመጠውን የአውሬው ምልክት ይፈፀም ዘንድ ነው፡፡ እና አሁንም ስለ ፍፃሜው ትጠራጠራለህ? ታውቃለህ ለኦባማ የተለየ መኪና እንደተሰራ አውሬው የሚባል? ተዘጋጅ ንጥቀት አሁን ይጀምራል፡፡ ራዕይ 13ን ቀድመው ተጫውተውታል፡፡ ብዙዎች ግን ይህን አልተገነዘቡትም፡፡ 1. ለምንድን ነው ይህ ችፕስ ከባንክ አካውንት ጋር የተቆራኘው ወይም የተገናኘው? አስታውሱ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ካለ አውሬው ቁጥር 666 ልትገዙም ወይም ልትሸጡም አትችሉም ስለሚል፡፡ እስኪ ገምቱ ይህ ቺፕስ ከገንዘብ ዝርዝር መረጃ ጋር ለምን ተገናኘ? እንዲያውም በጣም ያሳዘነኝ በቤተክርስቲያን ያሉ ብዙዎች ሰዎች ጌታ ሲመጣ ይህን ሁኔታ ሊያልፉት አይችሉም፡፡ ደግሞም ብዙዎቹ መጨረሻው እንደቀረበ አያውቁም፡፡ የቴክኖሎጂ በጣም መራቀቅ ምክንያት ነው ብላችሁ መልስ እንዳትሰጡኝ፡፡ በማንኛውም የህይወት ጎዳናችሁ ከእግዚአብሔር ጋር ካልተስማማ አሁኑኑ ንሰሀ ግቡና ተለወጡ፡፡ ካለበለዚያ መንግስተ ሰማያትን ካጣችሁት ገሀነምን አታጡትም፡፡ ስለዚህ አስቡበት፡፡ ገሀነም መልካም ስፍራ አይደለም በጣም አስከፊው ክፍሉ እንደ መንግስተ ሰማያት ዘላለማዊነት እንዳለበት እዚህም እንደዛው ነው፡፡ ጆሮ ያለው ይስማ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ይስማ፡፡ ጠቃሚ ያልሆነ ነገር ከምትልኩ ይህን ለሌላው ብታስተላልፉ መልካም ነው፡፡ ለምታውቋቸው ቅርብ ለሆኗችሁ ሰዎች ላኩላቸው፡፡ እስኪ የወንጌላዊ ስራ እንስራ፡፡ እባካችሁ ለምታውቋቸው ለእያንዳንዳቸው በየስማቸው ላኩላቸው፡፡ ለሞባይል እንደምንጠነቀቅ ያክል ለእግዚአብሔር ቃል ብንጠነቀቅ ምን እንደሚሆን ልትገምቱ ትችላላችሁ፡፡ ከዚህ ደግሞ በጭራሽ ልንላቀቅ ነፃ ልንሆን አንችል፡፡ ስለዚህ የቻልነውን ያክል እንትጋ እንጋደል፡፡ 7% የሚሆኑቱ ናቸው መልዕክቱን የላኩት በድጋሚ 93%ቱ ግን አልላኩም አላወቁም ስለዚህ ጠንክረን እንስራ፡፡ ሰይጣን እንዲህ ይላል፡- " የሚገርመኝ ሰው እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ አይታዘዝም እኔን ይጠላኛል ግን ይታዘዘኛል፡፡" ይህን መልዕክት በኋላ እንዳትልኩት አሁኑኑ ላኩት!!! ባቢ ለ #15 ሰው እባካችሁ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏