cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Event Addis/ሁነት አዲስ

https://eventaddis.com ለአስተያየትና ማስታወቂያ: @Tmanaye

Show more
Advertising posts
7 004
Subscribers
+2024 hours
+1107 days
+57830 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
የወንዲ ማክ አልበም ሰኔ 14 ይለቀቃል የድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) "ይንጋልሽ" የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። ድምጻዊው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁም "እነሆ አርብ ሠኔ 14 ቁርጥ ቀን ሆነ "ይንጋልሽ " ብለን ከንጋት የተቃጠርንበት አልበማችንን ወደ እናንተ የምናደርስበት ሠላም ያቆየን" ብሏል። ይህም አልበም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
2541Loading...
02
እማዬ እንዳለች ኑ ቡና ጠጡ ብላለች! በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ከዛሬ ሰኔ 8 እስከ ነገ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ህዝብ ቡና በነፃ እየተጋበዘ ነው። ይህ አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት ነፃ ቡና ዝግጅት ሙዚቃ ፣ፋሽን ሾዎችን መዝናኛዎችን እና የተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶችን ማሰናዳታቸውን እና ህብረተሰቡ በነጻ ቡና እየጠጣ እንዲዝናና አዘጋጆቹ ታሜሶል ኮሚዩኒኬሽን አሴቲክስ ሶሉሽን እና ከሊያን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። #Ads ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
6859Loading...
03
የድምጻዊ ዘሩባቤል ሞላ ታናሽ ወንድም የሆነው ድምጻዊ ኤርሚያስ ሞላ አዲስ የቅብብል ነጠላ ሙዚቃውን አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ለአድማጮች አድርሷል። ሙዚቃው በኤርምያስ ሞላ እና የኢትዮጵያን አይዶል ምርጥ አምስት ተወዳዳሪ በነበረችው በእርገት ሰለሞን(ናኒ) በቅብብል የተሰራ ነው። "እስከወዲያኛው " የሚል ርዕስ የተሰጠው ሙዚቃው በዳዊት ተስፋዬ (ደጃፍ ፖድካስት) ግጥሙ ተጽፎለታል። የሙዚቃው ዜማ እና ቅንብሩ በራሱ በኤርሚያስ ሞላ ተሰርቷል። ከጀርባ በርካታ ሰዎች ተሳትፈውበታል። የሙዚቃ ቪድዮውን በኤርምያስ ሞላ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ታገኙታላችሁ ተብላችኋል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
601Loading...
04
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት በዚህ ወር ይካሄዳል የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት የፊታችን ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል። ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ የሚካሄደው የሃጫሉ ሽልማት በ11 የሽልማት ዘርፎች፤ በአፋን ኦሮሞ የተሰሩ የዓመቱ ምርጥ አልበም፣ የአመቱ ምርጥ ግጥምና ዜማ ደራሲ፣ የዓመቱ ምርጥ አቀናባሪ፣ ምርጥ የባህል ዘፈን፣ ምርጥ ዘመናዊ ሙዚቃ፣ የዓመቱ ምርጥ ወንድ እና ሴት አርትስቶች፣ የኣመቱ ምርጥ አዲስ ሙዚቀኛ (ሴት እና ወንድ)፣ ምርጥ የአመቱ የሙዚቃ ቪዲዮ፣ ሲኒማቶግራፊ እና ምርጥ ባህላዊ ውዝዋዜ በሚሉ ዘርፎች እንደሚሸለሙ ታውቋል፡፡ በሽልማት ውድድሩ ውስጥ ሚካተቱ የሙዚቃ ስራዎች ከመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የወጡ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡ ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
9723Loading...
05
"የአባቶች የአእምሮ ጤና:የቤተሰብ ብርታት" የተሰኘ ተከታታይ የሥነልቦና ውይይት ከእሁድ ጀምሮ ይካሄዳል የአእምሮ ጤና ተሟጋች የሆነው እና የቤተሰብ የአእምሮ ደህንነት ላይ በመስራት የሚገኘው ሜንታል ሄልዝ አዲስ “የአባቶች የአእምሮ ጤና፡ የቤተሰብ ብርታት” በሚል መሪ ቃል ተከታታይ  መርሐግብር ለማሰናዳት እየተዘጋጀ እንደሆነ አስታውቋል። ይህም አባቶች ጤናማ እና ብርቱ ቤተሰብ በማጎልበት ረገድ ስለሚጫወቱት ወሳኝ ሚና አፅንዖት ለመስጠትም ያለመ ነው ተብሏል። ዝግጅቱን በዓለም አቀፍ የአባቶች ቀን እሁድ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል በርካታ አባቶች በተገኙበት አባትነትን በመዘከር የመክፈቻ ፕሮግራም እንደሚደረግ ኤቨንት አዲስ ደስታ ድረገፅ ሰምቷል። የዚህ መርሐግብር መግቢያ ሁለት መቶ ብር ነው። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
9892Loading...
06
"ሜላድ"አውደርዕይ ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል ሜላድ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዝግጅት ማዕከል"ሜላድ የብራና ማዕድ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 8 እና ነገ እሁድ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም አዘጋጅቷል። ይህ አውደርዕይ ከዛሬ ቅዳሜ ከጠዋት 3፡00 ላይ ተከፍቶ እስከ እሁድ ምሽት ድረስ በቦሌ ደብረ ሳሌም ካቴድራል ትልቁ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
8653Loading...
07
የሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ የሥዕል አውደርዕይ ተከፈተ የእውቁ ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ "የይቅርታ ጉዞ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ቦሌ አትላስ መብራት አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሜትሮፖሊታን የሥዕል ማሳያ ውስጥ የሥዕል ወዳጆች በተገኙበት ለእይታ እንደበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። ይህ የሥዕል አውደርዕይ የፊታችን ሰኔ 23 2016 ዓ.ም ለሳምንታት በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 14911Loading...
08
ድምጻዊ ጉቱ አበራ "ጋፊኮ" የተሰኘ አልበሙን በሚቀጥለው ሳምንት ለአድማጮች ያደርሳል ድምፃዊ ጉቱ አበራ “ጋፊኮ” የተሰኘ የመጀመሪያው አልበሙን ማጠናቀቁን አስታወቀ። ድምፃዊ ጉቱ አበራ በለቀቃቸው ነጠላ ዜማዎች በርካታ አድናቂዎችን አፍርቷል። ከ15 ቀን በፊት ኢዮሌ የተሰኘ ቪዲዮ ክሊፕ የተሰራለት ነጠላ ዜማ ለቆ ተወዶለታል። አልበሙ በሚቀጥለው ሳምንት አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ፋስት መረጃ ከድምፃዊው ያገኘው መረጃ ያሳያል። አልበሙ የራሱን የዩቲዩብ ቻናልን ጨምሮ በሌሎችም ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በላይ ይለቀቃል ተብሏል። 📍መረጃው የፋስት መረጃ ነው። ቴሌግራም: @EventAddis1
1 0391Loading...
09
የድምጻዊ ጉቱ አበራ "ጋፊኮ" የተሰኘ አልበሙን በሚቀጥለው ሳምንት ለአድማጮች ያደርሳል ድምፃዊ ጉቱ አበራ “ጋፊኮ” የተሰኘ የመጀመሪያው አልበሙን ማጠናቀቁን አስታወቀ። ድምፃዊ ጉቱ አበራ በለቀቃቸው ነጠላ ዜማዎች በርካታ አድናቂዎችን አፍርቷል። ከ15 ቀን በፊት ኢዮሌ የተሰኘ ቪዲዮ ክሊፕ የተሰራለት ነጠላ ዜማ ለቆ ተወዶለታል። አልበሙ በሚቀጥለው ሳምንት አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ፋስት መረጃ ከድምፃዊው ያገኘው መረጃ ያሳያል። አልበሙ የራሱን የዩቲዩብ ቻናልን ጨምሮ በሌሎችም ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በላይ ይለቀቃል ተብሏል። 📍መረጃው የፋስት መረጃ ነው። ቴሌግራም: @EventAddis1
10Loading...
10
የኔ መኪና እና የኔ ዴልቨሪ አገልግሎቶች ይፋ ሆኑ ቲዎስ ቴክኖሎጂ "የኔ መኪና" እና "የኔ ዴልቨሪ" የተሰኙ ሶፍትዌሮችን በማበልጸግ ወደ ስራ ማስገባቱን ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል በተሰናዳ ፕሮግራም ይፋ አድርጓል። "የኔ መኪና" የትራንስፖርት ዘርፉን ከማዘመን አኳያ በርካታ ጥቅሞች እንደሚሰጥ የተነገረ ሲሆን በተለይም በመንገድ እና ትራንስፖርት ባለስልጣንና በተሽከርካሪ ባለንብረቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ያለምንም ክፍተት በመናበብ ስራቸውን ምቹ እና ቀልጣፋ እንዲሆን ከማድረግም በላይ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችን ማሳደስ ያለባቸውን ነገሮች በማስታወስ ከቅጣት እና አላስፈላጊ እንግልት የሚያድን ሶፍትዌር እንደሆነ ተገልጿል። ሌላኛው "የኔ ዴሊቨሪ" ሶፍትዌር ሲሆን የተለያዩ ዶክመንቶችን፣ ሰነዶችን፣ እቃዎችን እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን ቴከኖሎጂ በመጠቀም ለግለሰቦች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለሆስፒታሎች ለማድረስ የበለጸገ ሶፍትዌር እንደሆነ ተነግሯል። ቲዎስ ቴክኖሎጂ ሶልሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ሶፍትዌር መተግበሪያዎችን በማበልጽግ እየሰራ የሚገኘ ድርጅት ነው። ቴሌግራም: @EventAddis1
9824Loading...
11
ካውሰር ( ሻሊና ሄልዝ ኬር)የተሰኘ ድርጅት አራት የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶችን ያስተዋውቀበትን ኩነት አካሄድ ካውሰር PLC( ሻሊና ሄልዝ ኬር) በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተቀባይነትን ያተረፈ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያ ይዟቸው የመጣቸውን አዳዲስ ምርቶች ሰኔ 6 2016 ዓ.ም አስተዋውቋል። ከነዚህ ምርቶች ውስጥ አንዱ ሞናሊሳ ሲባል ይህም የቆዳ እንክብካቤን ለመጠበቅ የሚያስችል ሎሽንና ክሬም ነው። ኤፒግሎው የተሰኘው ደግሞ ለአፍሪካ ቆዳ የተዘጋጀ ሲሆን እንደ ጥቁር ነጠብጣቦች እና ዥንጉርጉር ፊትን እና የተለመዱ የቆዳ ስጋቶችን በ28 ቀናት ውስጥ በመቀነስ ብቻ የሚታይ ለውጥ የሚሰጥ የቆዳ መንከባከቢያ እንደሆነ ተገልጿል። ሌላው ፍሎደንት የተባለው የጥርስ ሳሙና ምርት ሲሆን በፍሎራይድ ለተጠቃ ጥርስ፣ ለአፍ ጤንነት፣ የጥርስ መቦርቦርን የሚታደግ እንደሆነ ተነግሯል። የመጨረሻው ምርት ጀርሞል የተሰኘ ሳሙና ሲሆን  ሰውነትን ከጀርሞች ለመከላከል የሚረዳ ነው ተብሏል። ሻሊና ሄልዝ ኬር 40 አመትን ያስቆጠረ ድርጅት ሲሆን እስካሁን በ22  የአፍሪካ ሀገራት ላይ ሰርቷል። ድርጅቱ በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ ላይ 6 ክፍለ ከተሞች ላይ ስራ የጀመረ ሲሆን 1000 ለሚደርሱ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል። ቴሌግራም: @EventAddis1
9424Loading...
12
በኢትዮጵያዊው የዜማ ሊቅ በቅዱስ ያሬድ ስም የተሰየመ የድረገጽ አገልግሎት ይፋ ተደረገ ታሪካዊው በሆነው የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ የአንድነት ገዳም ስያሜ የተሰራው ድረገጽ  ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ የምሥራቅ ካናዳ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በራማዳ ሆቴል በተከናወነው መርሐግብር ይፋ ተደርጓል። በሰሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ የሚገኘውን ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም  እየተከናወነ ያለውን የግንባታ ኘሮጀክት ያስተዋውቃል የተባለው ድረገጹ በገዳሙ እየተሰራ ያለውን የአብነት ትምህርት ጥንታዊነቱን ጠብቆ የሚያስተምር የልህቀት ማዕከል ማድረግና ምዕመናን ወደ ገዳሙ እየሔዱ በረከት የሚያገኙበት ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ጎብኚዎች የቤተክርስቲያኗንና የሀገራችን ቀደምትነት ገናና ባለታሪክ መሆናቸውን የሚረዱበትና ሀገራችንም የውጭ ምንዛሪ የምታገኝበት ማድረግን ዓላማ አድርጎ እየሠራ ይገኛል ተብሏል። www.kidusyaredzedebrehawi.com በገዳሙ እየተከናወነ ያለውን ፕሮጀክት አስመልክቶ ዝርዝር ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን ገዳሙን በገንዘብ በቀጥታ ማገዝ እንድችሉ ተደርጎ እንደበለጸገ በመድረኩ ላይ ተገልጿል። ቅዱስ ያሬድ ከ1500 አመታት በፊት የኖረ፣ የመጀመሪያው የአለማችን  የዜማ አውጭ፣ የመጀመሪያው የመፃሕፍት ደራሲ፣ ታላቅ የፍልስፍና ሰው፣ የብዙ ነገሮች ሊቅ፣ ባለቅኔ የሆነ፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው ግዙፍ ባለጸጋ ነው። ቅዱስ ያሬድ ባስተማረበት በመጨረሻም በተሰወረበት ስፍራ፣ በሰሜን ተራራ ላይ በደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም በርካታ ልማቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ማህበሩ አስታውቋል። ቴሌግራም: @EventAddis1
1 0421Loading...
13
በኢትዮያዊያው የዜማ ሊቅ በቅዱስ ያሬድ ስም የተሰየመ የድረገጽ አገልግሎት ይፋ ተደረገ ታሪካዊው በሆነው የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ የአንድነት ገዳም ስያሜ የተሰራው ድረገጽ  ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ የምሥራቅ ካናዳ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በራማዳ ሆቴል በተከናወነው መርሐግብር ይፋ ተደርጓል። በሰሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ የሚገኘውን ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም  እየተከናወነ ያለውን የግንባታ ኘሮጀክት ያስተዋውቃል የተባለው ድረገጹ በገዳሙ እየተሰራ ያለውን የአብነት ትምህርት ጥንታዊነቱን ጠብቆ የሚያስተምር የልህቀት ማዕከል ማድረግና ምዕመናን ወደ ገዳሙ እየሔዱ በረከት የሚያገኙበት ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ጎብኚዎች የቤተክርስቲያኗንና የሀገራችን ቀደምትነት ገናና ባለታሪክ መሆናቸውን የሚረዱበትና ሀገራችንም የውጭ ምንዛሪ የምታገኝበት ማድረግን ዓላማ አድርጎ እየሠራ ይገኛል ተብሏል። www.kidusyaredzedebrehawi.com በገዳሙ እየተከናወነ ያለውን ፕሮጀክት አስመልክቶ ዝርዝር ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን ገዳሙን በገንዘብ በቀጥታ ማገዝ እንድችሉ ተደርጎ እንደበለጸገ በመድረኩ ላይ ተገልጿል። ቅዱስ ያሬድ ከ1500 አመታት በፊት የኖረ፣ የመጀመሪያው የአለማችን  የዜማ አውጭ፣ የመጀመሪያው የመፃሕፍት ደራሲ፣ ታላቅ የፍልስፍና ሰው፣ የብዙ ነገሮች ሊቅ፣ ባለቅኔ የሆነ፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው ግዙፍ ባለጸጋ ነው። ቅዱስ ያሬድ ባስተማረበት በመጨረሻም በተሰወረበት ስፍራ፣ በሰሜን ተራራ ላይ በደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም በርካታ ልማቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ማህበሩ አስታውቋል። ቴሌግራም: @EventAddis1
10Loading...
14
ኮሜዲያን ቤቲ ዋኖስ የማይ ሶሮባን ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር የበጎ ፍቃድ አምባሳደር ሆና ተሾመች ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር “ሒሳብ ትምህርት ይከብዳል” የሚል የተሳሳተ አመለካከት በማስወገድ ጉብዝና ያሽልማል › በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት እና የስሌት ውድድር በሀገራችን በሚገኙ ሁለም ትምህርት ቤቶች ለማከናወን የተቋቋመ በኢትዮጵያ ብቸኛው የሒሳብ ትምህርት አወዳዳሪ ተቋም ነው፡፡ በማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ የ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር ከ50 ከተሞች የተውጣጡ ከ2ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች እና ከ3መቶ ሺ በላይ ተማሪዎችን አሳትፏል፡፡ ውድድሩ በአጠቃላይ ስድስት ዙሮች ሲኖሩት አምስቱ ዙሮች በየከተሞቹ የተከናወኑ ሲሆን የመጨረሻው ወይም ስድስተኛው ዙር የፍጻሜ ውድድር ከሁሉም ከተሞች የየከተማው አሸናፊ ተማሪዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሚሊኒየም አዳራሽ የመጨረሻውን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ለከፍተኛ ሽልማት ይወዳደራሉ፡፡ የዚህ ውድድር አሸናፊ ተማሪዎች በጠቅላላ አራት ሚሊዮን ብር የሚፈጅ የገንዘብና የአይነት ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል ተብሏል። በዳኝነት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የኮተቤ መምህራን ዩኒቨርስቲ መምህራን ሲሳተፉ የየከተማ ተወካዮቻቸውም በታዛቢነት እንደሚሳተፉ ተገልጿል። የመዝጊያው መርሃግብር በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ከሐምሌ 28 እስከ ነሐሴ 1 2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል። ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ዛሬ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ኮሜዲያን ቤቲ ዋኖስ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አድርጎ እንደሾመ አስታውቋል። ቴሌግራም: @EventAddis1
1 3994Loading...
15
መጻሕፍትን አሳትሞ ለአንባቢያን የማቅረብ ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ነው ተባለ ከዚህ ቀደም በዓመት እስከ አምስት መጻሕፍት የማሳተም ስራ ሲሰሩ የነበሩ አሳታሚ ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙሉ ለሙሉ የህትመት ስራ ማቆማቸውን ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ ሸገር ይህንን የሰማው በአንድ የመፀሀፍ ኤግዚቢሽን ላይ ተገኝቶ ደራሲያንን እና መፀሀፍ ሻጮችን ባነጋገረበት ወቅት ነው፡፡ የወረቀት ዋጋ መወደድን ተከትሎ አሳታሚዎች መፀሀፍቶቻቸውን እንዳያሳትሙ አድርጓቸዋል የተባለ ሲሆን በዚህ ሁሉ ችግር ታትሞ ለገበያ ቢቀርብም አንባቢ አይኖረውም ይላል ኤዞፕ መፀሀፍት መደብር፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ መፀሀፍቱ የሚሸጡበት ዋጋ ውድ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡ ሸገር ያነጋገራቸው ደራሲ ኩሪ አየለ በበኩላቸው መፀሀፍ ማሳተም አስቸጋሪ እየሆነብን መጥቷል ያሉ ሲሆን ይህ ችግር በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ነባር ደራሲያንን ብቻ ሳይሆን ወደ ዘርፉ የሚመጡ ጀማሪ ደራሲያንንም ያሳጣናል ብለውናል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአንባቢያን ቁጥር መቀነስ ደግሞ ሌላኛው ዘርፉን ወደኋላ የሚያስቀር ችግር ነው ይላሉ፡፡ ሸገር ከዚህ በፊት በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው ፀሀፊያን እና ደራሲያን እንዳሉት መንግስት ከቀረጥ ነፃ ወረቀት እንዲገባ እና በህትመት ስራዎች ላይ እንዲሳተፍ ሲሉ ይመክራሉ፡፡ በተጨማሪም ባለሀብቶች የህትመት ኢንዱስትሪው ላይ እና የወረቀት ማምረት ስራ ላይ ሊሳተፉ ይገባል ይላሉ፡፡ ይህ የሚሆን ከሆነ ደግሞ በደራሲያንም ሆነ በአንባቢያን ላይ የሚታየው ችግር ይስተካከላል ይላሉ፡፡ 📍መረጃው የፋሲካ ሙሉወርቅ( ሸገሬ ሬድዮ) ነው ቴሌግራም: @EventAddis1
1 4232Loading...
16
የሐሙስ መረጃዎች የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባሉ! ሚዲያዎች መረጃውን ስትጠቀሙ ምንጭ ጥቀሱ 📍መጽሐፍ - የገጣሚ ኤፍሬም ስዩም አንድ መጽሐፍ በአንድ ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ለህትመት ሊበቃ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። "ቡና እና ምልኪ" የተሰኘውና ከዓመት በፊት ለንባብ ይበቃል ተብሎ የዘገየው መጽሐፍ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በማህበራዊ ትስስር ገፅ በሚደረግ ቅድም ክፍያ እንደሚታተም ገጣሚው አስታውቋል። ገጣሚው በማህበራዊ ትስስር ገፁ"በሀርድ ኮፒ ያጌጠ ምልኪና ቡና ከቅዳሜ ጀምሮ 1000 ኮፒ ህትመት በ1000 ብር ብቻ እጃችሁና የመጻሕፍት ሼልፋችሁ ላይ ለማኖር ዝግጅት አድርጉ" ብሏል። -የገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ። መጽሐፉ "የጊዜ ሠሌዳ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ነው።በ103 ገፆች ተቀንብቡ በ250 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን የቀረበ ሲሆን ዛሬ በሚካሄደው የመቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ላይ በገጣሚዋ ተፈረሞ ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል። ገጣሚዋ ከዚህ ቀደም "የቃል ሠሌዳ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል። -የገጣሚና የህግ ባለሞያው ደሱ ፍቅርኤል "እስከ መቅደስ " የተሰኘ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።ገጣሚ ደሱ ከዚህ ቀደም "ሀገሬን ሰቀሏት" እና "ተይው ፖለቲካን ዝም ብለሽ ሳሚኝ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል። መጽሐፉን በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ታገናላችሁ ተብላችኋል። -የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ለአንባቢያን ይደርሳል።ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አዲስ መጽሐፍ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ቀናት ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል።መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። 📍ሙዚቃ -የድምጻዊት ሔዋን ገብረወልድ "ያንተን" የተሰኘ ሙዚቃ ነገ አርብ  ለአድማጮች ይደርሳል። በዚህ የሙዚቃ ስራዋ ላይ ገጣሚ ምልእቲ ኪሮስ በግጥም ምረታብ ደስታ በዜማ ተሳትፈዋል።ሙዚቃ ቅንብርና ማስተሪንጉን ስማአገኘሁ ሳሙኤል ሰርቷል። -የድምጻዊት ሜላት ቀለመወርቅ "ዋይ" የተሰኘ ሙዚቃ ነገ አርብ በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ይደርሳል ተብሏል።በዚህ የሙዚቃ ስራዋ ላይ በግጥምና ዜማ ምህረትአብ ደስታ ሲሳተፍ ቅንብር፣ሚክሲንግ፣እና ማስተሪጉን ደግሞ ሔኖክ ድለቃ ሰርቷል። -ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ "የኔ ትውልድ" በተሰኘ የአሜሪካ ጉዞ የሙዚቃ ዝግጅቱን እንደሚያካሄድ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል። የሙዚቃ ዝግጅቱን በቅርቡ በአሜሪካ አትላንታ ግዛትን ጨምሮ በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ እንደሚያቀርብ ገልጿል። ሮፍናና ከወራት በፊት ዘጠኝ በሚል ርዕስ "ሀራንቤ" እና "ኖር" የተሰኙ ሁለት አልበሞችን በአንድ ቀን ለአድማጮች ማድረሱ ይታወሳል። 📍 ቴአትር -የ"እያዩ ፈንገስ" 10ኛ ዓመት በዓልን አስመልክቶ  ረቡዕ ሰኔ 5 እና አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም በራስ ሆቴል ሊቀርብ የነበረው ዝግጅት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት  እንደማይቀርብ አዘጋጆቹ ማሳወቃቸው የተሰማው በዚህ ሳምንት ነበር።የተወኔቱ አዘጋጆች ወደፊት ተለዋጭ ፕሮግራም ሲኖር ለተመልካቹ እንደሚያሳውቁ ጨምረው ገልፀዋል። - "እሳት ወይ አበባ" ተውኔት ወደ መድረክ ሊመለስ ነው። በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ የተመሰረተው "እሳት ወይ አበባ" ግጥማዊ ዳንስ ተውኔት በብሔራዊ ቴአትር ከሰኔ 14 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መድረክ እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።ይህ ሙከራዊ ተውኔት ባሳለፍነው ጥቅምት 2 2016 ዓ.ም ነበር ዘወትር አርብ ሲቀረብበት ከነበረው የአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የተሰናበተው። በምትኩም "የሁለት ጌቶች አሽከር" የተሰኘ ተውኔት ሲቀርብም ቆይቷል። 📍ኪነጥበብ ዝግጅት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል። አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ሀሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በዕለቱም አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ በክብር እንግድነት ትገኛላች ተብሏል። 📍የሥነጥበብ አውደርዕይ (ሥዕል) - የሠዓሊ ዮናታን ወንደሰን ሥዕል ስራዎች የሚቀርቡበት "ከአጥሮች ባሻገር" የሥዕል አውደርዕይ ነገ አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ ይበቃል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ይቆያል ተብሏል። -የሠዓሊ ኃይለገብርኤል ንጉሴ የሥዕል ስራዎች የሚቀረበብት "The light Path" የሥዕል አውደርዕይ ቅዳሜ ሰኔ 8 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ላይ ለእይታ ይበቃል።ይህም የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል። 📍ፊልም "ጃንሞራ" የተሰኘ ፊልም በቅርቡ ለተመልካች ይቀርባል። በኪም ፊልምስ ተዘጋጅቶ በከአብ መልቲሚዲያ የቀረበው የያለው ደስታ (ራስ) "ጃንሞራ" የተሰኘ ፊልም ከሰኔ 21 ጀምሮ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ለተመልካች እንደሚቀረብ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።በዚህ ሀገርኛ ፊልም ማርታ ጎይቶም፣ ነብዩ እንድሪስ ፣ እንግዳሰው ሀብቴ እና ሌሎችም በተዋናይነት ተሳትፈውበታል። አዘጋጅ: ናቲ ማናዬ ቀን: ሰኔ 6 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በድረገጻችን በተሻለ አቀራረብ ያንብቡ: https://eventaddis.com ቴሌግራም: @EventAddis1
1 37510Loading...
17
ኢትዮ የምግብ እና መጠጥ ፌስቲቫል ተከፈተ የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ማዕከል ከአሜዚንግ ፕሮሞሽንና ኢቨንት እና ከዳብ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ከዛሬ ሰኔ 5 እስከ የፊታችን 9 2016 ዓ.ም የሚቆይ ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፍቷል። ለ5 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው "ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል" በምግብ፣ በመጠጥ፣ በፓኬጂንግ እና ተዛማጅ መስኮች ላይ የተሰማሩ ግብዓት አቅራቢዎች፣ አምራቾች፣ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ ከዘርፉ ጋር የተገናኙ አምራች እና አስመጪዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሏል። በፌስቲቫሉ ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም፣ ሽልማት የሚያስገኙ ልዩ ልዩ ውድድሮች እና የመዝናኛ ፕሮግራሞች መካተታቸው ተገልጿል። ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል የውጪ ሀገራት ዲፕሎማቶችን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሀገራችን በምግብና መጠጥ ረገድ ያላትን የቱሪዝም አቅም በቅርበት እንዲያውቁት የሚያደርግ ፌስቲቫል እንደሆነ ተነግሯል፡፡ የፊስቲቫሉ መግቢያ በነፃ መሆኑን እና ሁሉም ህብረተሰብ መካፈል እንደሚችሉ ተነግሯል ። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 4246Loading...
18
የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ ተከፈተ አራተኛው የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ ከዛሬ ሰኔ 05 እስከ ፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 08 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል። የዘንድሮው አራተኛው የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ"ኃይል ቁጠባ፣ አረንጓዴ አፍሪካ"በሚል መሪ ቃል የሚከናውን ሲሆን በዚህ አውደርዕይ ላይ አምራቾች ምርቶቻቸውንና አቅርቦቶቻቸውን ይዘው ይገኛል ተብሏል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 4215Loading...
19
የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ አራተኛው የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ ከዛሬ ሰኔ 05 እስከ ፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 08 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል። የዘንድሮው አራተኛው የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ"ኃይል ቁጠባ፣ አረንጓዴ አፍሪካ"በሚል መሪ ቃል የሚከናውን ሲሆን በዚህ አውደርዕይ ላይ አምራቾች ምርቶቻቸውንና አቅርቦቶቻቸውን ይዘው ይገኛል ተብሏል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
10Loading...
20
እያዩ ፈንገስ ተውኔት አይቀርብም ተባለ የእያዩ ፈንገስ 10ኛ ዓመት በዓልን አስመልክቶ ነገ ረቡዕ ሰኔ 5 እና አርብ ሰኔ 7 2016 በራስ ሆቴል ሊቀርብ የነበረው ዝግጅት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በነገው እለት እንደማይቀርብ አዘጋጆቹ ስለማሳወቃቸው ኤቨንት ድረገፅ ሰምቷል። የተወኔቱ አዘጋጆች ወደፊት ተለዋጭ ፕሮግራም ሲኖር ለተመልካቹ እንደሚያሳውቁ ጨምረው ገልፀዋል። በተጨማሪም "ለ10ኛ ዓመት በዓላችን መልካሙን ሁሉ ለተመኛችሁልንና በጠመዝማዛው መንገዳችን አብራችሁን ለነበራችሁ ወገኖቻችን ምስጋናችን ወሰን የለውም" በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። "እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው ተውኔት "አጀንዳዬ"  "ፌስታሌ" እና በቅርቡ ከመድረክ በታገደው "ቧልቲካ" በሚሉ ርዕሶች በተለያዩ መድረኮች ለታደሚያን ሲቀረብ ቆይቷል። ዘወትር ሐሙስ በዓለም ሲኒማ ሲቀረብ የነበረው የእያዩ ፈንገስ "ቧለቲካ" ቴአትር ባሳለፍነው ጥር 2 2016 ዓ.ም ለህዝብ እንዳይታይ እንደተከለከለ ይታወሳል። 📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ ! ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 80817Loading...
21
በነፃ የተዘጋጀው የሮፍናን ማስተር ክላስ ሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ በሐዋሳና አካባቢ ለሚገኙ ወጣት የሙዚቃ ባለሞያዎች እና ተያያዥ የስራ መስክ ውስጥ ለሚገኙ ሁሉ "የሮፍናን ማስተር ክላስ" ስልጠና ጥሪ አስተላልፏል። ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ ለሚመለከተው ሁሉ ተከታዩን መልዕክት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስተላልፏል: "በሐዋሳ እና አካባቢው ምትገኙ የማስተር ክላሱን የትምህርት እና በተግባር የታገዘ ልምድ ልውውጥ ለመካፈል የምትፈልጉ ወጣት ጀማሪ ሙዚቀኞች: አቀናባሪዎች : ድምፃዊያን : የግጥም እና ዜማ ደራሲዎች : ዲጄዎች : የድምፅ ቅጂ እና ማስተሪንግ ኢንጂነሮች : እንዲሁም በኢንተርቴመንት ማርኬቲንግ ስራ ላይ ለተሰማራችሁ የማርኬቲንግ ባለሙያዎች እድሉ ለሚፈቅደው የ150 ሰው ምርጫ ውስጥ ለመግባት ለአጭር ጊዜ ምዝገባ ክፍት ነው:: ይህንንም ስናገር ለሀገራችን የሙዚቃ እና ኪነጥበብ ሚያበረክተውን በጎ አስተዋፆ በማሰብ ትልቅ ደስታ እና እድለኝነት ይሰማኛል:: ምስጋናዬ ለሚመለከተው ሁሉ ይድረስ:: ሊንኩን በመጫን መመዝገብ ትችላላችሁ:: https://rophnanmasterclass.et/ " ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1 https://t.me/EventAddis1 https://t.me/EventAddis1
1 9587Loading...
22
"እሳት ወይ አበባ" ተውኔት ወደ መድረክ ሊመለስ ነው በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ የተመሰረተው "እሳት ወይ አበባ" ግጥማዊ ዳንስ ተውኔት በብሔራዊ ቴአትር ከሰኔ 14 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መድረክ እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። "እሳት ወይ አበባ" የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ መሰረት ያደረገ የግጥማዊ ዳንስ የሙከራ (Experimental) ቴአትር ነው። ይህ ሙከራዊ ተውኔት ባሳለፍነው ጥቅምት 2 2016 ዓ.ም ነበር ዘወትር አርብ ሲቀረብበት ከነበረው የአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የተሰናበትው።በምትኩም "የሁለት አሽከር ጌቶች" የተሰኘ ተውኔት ሲቀርብም ቆይቷል። ኤቨንት አዲስ ድረገፅ እንዳረጋገጠው በሚቀጥለው ሳምንት ሰኔ 14 2016 ዓ.ም "እሳት ወይ አበባ " ተውኔት ወደ መድረክ ተመልሶ በቋሚነት ዘወትር አርብ በ11:30 መቅረብ ይጀምራል ተብሏል። ይህ ግጥማዊ ድራማ ከዚህ ቀደም በሀገር ፍቅር ቴአትር ትንሿ አዳራሽ ለታደሚያን ይቀርብ እንደነበር ይታወሳል። 📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ ! ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 58414Loading...
23
"ዱባይ እንደምን ሠለጠነች?" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ከሰሞኑ ለንባብ በቅቷል በዱባዮ ገዢ ሼኽ መሀመድ ቢን ረሺድ አል መክቱም ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥነው"My Story"መጽሐፍ በጋዜጠኛ ናትናኤል ከበደ "ዱባይ እንደምን ሠለጠነች" በሚል ርዕስ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል። መፅሀፉ የዱባዩ ገዢ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬት ጠቅላይ ሚኒስትር ህይወት ዙሪያ የተፃፈ ቢሆንም ከ ሼኽ መሀመድ ህይወት ባሻገር በውስጡ ብዙ ርዕሰ ጉዳዮች እንደያዘ የሚናገረው ተርጓሚው አያይዞም መፅሀፉ በዋናነት ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ትምህርት ሊሆን የሚችል የዱባይ የሀገር ምስረታ ፣አለም ላይ ታዋቂ የሆኑት ተቋማቸውን እንዴት እንደገነቡ ፣ዲፕሎማሲ፣ከነዳጅ ባሻገር ስላለው የአመራር ክህሎት እና ልህቀት እንደሚያወሳ ተናግሯል። 50 ምዕራፎች የያዘው መጽሐፉ በ400 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል። መጻሐፉም ሜክሲኮ ጃፈር መፅሀፍት መደብር እና 4 ኪሎ እነሆ መፅሀፍት መደብር ይገኛል። Telegram:https://t.me/EventAddis1
1 7337Loading...
24
"እውቀትን ፍለጋ መጻሕፍት መደብር" እውቀትን ፍለጋ መጻሕፍት መደብር አዳዲስና ቆየት ያሉ የአማርኛ እና እንግሊዝኛ መጻሕፍትን አቅርቦላቸዋል። የፍልስፍና ፣ የታሪክ ፣ የልቦለድ ፣ የትምህርት መማሪያ ፣የልጆች እና የሙያ መጻሕፍትን በብዛትና እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ ታገኛላችሁ። አድራሻቸው: ገርጂ ታክሲ ተራ (ዓለም ጋለሪ አካባቢ ) ስልክ : 0913624488 ወይም :0913825404 የቴሌግራም ገጻቸው: https://t.me/book1219
1 5381Loading...
25
በእስር ላይ የሚገኘው መራሔ ተውኔት ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ በጽኑ ስለመታመሙ ተሰምቷል ከመጋረጃ ጀርባ ፣እብድት በህብረት  የተሰኙ ተውኔቶችን ጨምሮ የተለያዩ ተውኔቶች ሲያዘጋጅ የምናውቀው መራሔ ተውኔት ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ከሰሞኑ በታሰረበት ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በፅኑ ህመም ላይ እንደሚገኝ እና ዛሬ ሰኔ 2 2016 ዓ.ም ወደ ህክምና ቦታ እንደተወሰደ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ከቅርብ ምንጮች ሰምቷል። አንጋፋው ከያኒ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ለረጅም ጊዜ የስኳር ህመምተኛ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ክሱን ከእስር ቤት ውጪ ሆኖ እንዲከታተል ቤተሰቦቹ ለፖሊስ ጥያቄ ማቅረባቸው ተነግሯል። በቅርቡ በፖሊስ ተይዞ ለእስር የበቃው የ"እብደት በሕብረት" ቴአትር አዘጋጅ አንጋፋው ከያኒ ዳግማዊ ፈይሳ ባለፈው ሳምንት ግንቦት 28 2016 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረብ ሲሆን አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙን ጨምሮ ሌሎች 20 ሰዎችን በአንድ መዝገብ ለፌደራል መደበኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ  ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ቀርበው ሁሉም ለሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ይታወሳል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 8547Loading...
26
"ምን ሆኛለሁ?" መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል የሥነልቦና ባለሞያዋ ትዕግስት ዋልተንጉስ እና ጋዜጠኛና ደራሲ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ የተጣመሩበት 'ምን ሆኛለሁ?' መፅሀፍ በጣም በቅርቡ ታትሞ ይወጣል ተብሏል። "የምታደርጉት ድርጊት ግራ አጋብቷችሁ 'ምን ሆኛለሁ?' ብላችሁ ከጠየቃችሁ ይሄ መፅሀፍ ልጅነታችሁን በመመርመር ራሳችሁን በተሻለ እንድትረዱ ያግዛችኋል"። በተጨማሪም "በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ወይም በቲቪ የምታውቋቸው ነጋዴዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎች የሚያደርጉት ድርጊት አልገባ ብሏችሁ 'ምን ሆኖ ነው?' ወይም 'ምን ሆና ነው?' የሚል ጥያቄ ከፈጠረባችሁ ይሄ መፅሀፍ ጥሩ የፅንሰ ሀሳብ መነፅር ይሰጣችኋል " ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። "ምን ሆኛለሁ" የተሰኘውን መጽሐፍ ብዙዎች መፅሀፉን ቀድመው እየገዙ እንደሆነም ተመልክተናል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 69815Loading...
27
"እያዩ ፈንገስ" ለሁለት ቀናት ብቻ ሊታይ ነው በበረከት በላይነህ ተደርሶ በግሩም ዘነበ የሚተውነው "እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው  ተውኔት መድረክ ላይ መቅረብ ከጀመረ ዘንድሮ አስር ዓመት እንደሚሞላው አዘጋጆቹ አስታውቀዋል። ይህንን የአስርኛ ዓመት ክብረበዓል በማሰብ ረቡዕ ሰኔ 5 እና አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ በራስ ሆቴል ለሁለት ቀናት ብቻ "እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው ተውኔት ለታዳሚያን እንደሚቀረብ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ሰምቷል። "እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው ተውኔት "አጀንዳዬ"  "ፌስታሌ" እና በቅርቡ ከመድረክ በታገደው "ቧልቲካ" በሚሉ ርዕሶች በተለያዩ መድረኮች ለታደሚያን ሲቀረብ ቆይቷል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 61716Loading...
28
የያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት የመጀመሪያው ዳይሬክተር በሆኑት ፕ/ር አሸናፊ ከበደ ስም የተሰየመው የጥበብ ማዕከል ተመረቀ ፕ/ር አሸናፊ ከበደ በመጀመርያ ዳሬክተርነት ባገለገሉበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚገኘው የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት  በስማቸው የተሰየመው ፕሮፌሰር "አሸናፊ ከበደ የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል" ባሳለፍነው ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ይህም የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል በርካታ ሙዚቀኞችን እና የሙዚቃ ታዳሚያንን መያዝ የሚችል ሲሆን በሀገራችን ለሙዚቃ ማቅረቢያ የተሰራ ግዙፍና የመጀመሪያው ማዕከል እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። የሙዚቃ ሊቁ ፕ/ር አሸናፊ ከበደ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ውስጥ ትልቅ አሻራ ያሳረፉ እና ዘመን አይሽሬ የሙዚቃ ሥራዎችን ያበረከቱ የሙዚቃ ሊቅ እንደነበሩ ይነገራል። እረኛው ባለዋሽንት፣ የኢትዮጵያ ሰላም፣ የፍቅር አንሰር ፣ የእሳት እራት፣ የተማሪ ፍቅር ፣ የሀገራችን ሕይወት ፣ ኒርቫኒክ ፋንታሲ የተሰኙ ረቂቅ ሙዚቃዎችን ለአድማጭ ጆሮ  ያደረሱ የሙዚቃ ደራሲ አቀናባሪና ኮንዳክተር ናቸው። በተጨማሪም የሙዚቃ ሰዋሰው የመማርያ መፅሀፍ በአማርኛ፣ ኮንፌንሽን ልቦለድ እንዲሁም Root of Black Music የተሰኙ መጽሐፍትም ለአንባቢያን አድርሰዋል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 7357Loading...
29
አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ የክብር እንግዳ የሆነችበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ይካሄዳል አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ሀሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በዕለቱም እረኛዬን ጨምሮ በተለያዩ ፊልሞቿና ድራማዎቿ የምናውቃት አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ የክብር እንግዳ ሆና የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና  የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 54614Loading...
30
የተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረበዓል የመዝጊያ ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት ይካሄዳል የተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረበዓል የመዝጊያ ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተር ሌግዤሪ ሆቴል በልዩ ልዩ ሥነሥርዓት ይካሄዳል። በመዝጊያ ዝግጅቱም አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራዝ ይሸለማሉ።ከተስፋ ጋር አብረው የሰሩ ድርጅቶችም እውቅና ይሰጣቸዋል ተብሏል። ተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረ በዓሉን አስመልክቶ በጎ ስራዎችን የጀመረው ከታህሳስ 1-29 ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር “በሊፍት ከፍዬ እሳፈራለሁ የጎዳና ልጅ አነሳለሁ” በሚል የገቢ ማሰባሰቢያ ስራ ነበር። ጥር 10  ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ በብሔራዊ ቴአትር “ቤርሙዳ” የተሰኘውን ቴአትር፤ ሚያዚያ 28  ቀን “ሀሁ ወይም ፐፑ” ቴአትርን በልዩ ፕሮግራም ለኪነ-ጥበብ አፍቃሪው አቅርቧል፡፡ ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 5796Loading...
31
የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ይበቃል ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ያበቃል። ጋዜጠኛ መኮንን ወልደአረጋይ ስለመጽሐፉ በመግቢያው "በተለይም በራዲዮና በቴሌቪዥን የቀረበ መሰናዶዎቹን ያደመጡና የተመለከቱ ወዳጆቼ ይህ ቁም ነገር ተሰንዶ በህትመት ቢቀርብ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሳያስገነዘበ ቦዝነው አያውቁም፡፡ እናም ዛሬ ጊዜው ደርሶ የመጀመሪያውን ቅጽና ለሌሎች ሥራዎቹ ዓይን ገላጭ የሆነውን "እነሆ ሟሟሻ" እያካችሁ ብያለሁ" ብሏል። መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
2 2608Loading...
32
Media files
10Loading...
33
የድምፃዊ መሳይ ተፈራ "የልቤን" አልበም ተለቀቀ የድምፃዊ መሳይ ተፈራ ካሣ "የልቤን "የተሰኘ የመጀመሪያ አዲስ አልበም ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም በራሱ Mesay Tefera የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለማቀፍ መተግበሪያዎች ላይ ተለቋል። በሙዚቃ አልበሙ ላይ ወጣትና አንጋፋ የግጥምና ዜማ ደራሲያን የተሳተፉበት ሲሆን ከእነዚህ መካከል ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ ሞገስ ተካ ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ ናትናኤል ግርማቸዉ ፣ አቡዲ ፣ምህረታብ ደስታ፣ አንተነህ ምናሉ ፣ወንድወሰን ይሁብ ይገኙበታል። በቅንብር ሚክሲንግና ማስተሪንግ የሙዚቃ ባለሙያዎች ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ታምሩ አማረ (ቶሚ) አቤል ጳውሎስና ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል። ኤቨንት ድረገፅ እንደተመለከተው አምስት ዓመታት የፈጀው  አልበሙ በውስጡ ቻል ቻል ፣የብቻዬ ፣ቆንጆ ነሽ፤ደህና ይግጠምሽ፤ ማካሪና ፤ ከአባይ ማዶ ፤ውረጅ ካናቴ ፤ የልቤን ፤ግድ የለሽም፤ ኸረ ተይ፤አይ አለማወቋ፤ አወሰድማዬ፤ እሳቱ የተሰኙ ርዕሰ ያላቸው የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ 12 የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል። ድምጻዊ መሳይ ተፈራ ካሣ ከዚህ ቀደም  አሰብኩት ፣ ፋሽን፣ብርቄ ነሽ፣ ደግዬ ፣ በጣም እንጂ በጣም እና ሌሎችንም ነጠላ ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሷል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 9683Loading...
34
Media files
10Loading...
35
Media files
10Loading...
36
ወጣቷ ድምጻዊት ሀና ግርማ ''ባንተ ላይ'' በተሰኘ ስራዋ የናሆም ሪከርድስን ሪከርድ ሰብራለች ድምፃዊት ሀና ግርማ ከ9 ወራት በፊት በሰራችው ስራ ከሰሞኑ የናሆም ሪከርድስን ሪከርድ ሰብራለች ። የተለያዩ ቪዲዮ ክሊፖችን እና ፊልሞችን ዳይሬክት እያደረገች የምትገኘው አዩ ግርማ ቪድዮውን ሰርተዋለች። አቡዱ ግጥምና ዜማውን ሰርቶ ታምሩ አማረ  ሙዚቃውን አቀናብሮታል ። ሃና ግርማ ደግሞ በነሀሴ ወር 2015 ላይ አቀንቅናው በአንድ ግዜ በሙዚቃ አፍቃሪው ተወዳጅነትን አግኝቶላታል ። ''ባንተ ላይ''ሙዚቃው በናሆም ሪከርድስ በተለቀቀ 9 ወሩ 20 ሚሊዮን እይታ አግኝቷል።ይህም ኩባንያው ቪድዮዎችን መልቀቅ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተመልካች በማግኘት ቀዳሚ ሆኗል። ናሆም ሪከርድስ በዩቲዩብ ከለቀቃቸው ስራዎች በቀዳሚነት ላይ የሚገኘው የታሪኩ ጋንኪሳ ዲሽታ ጊና ሲሆን 35 ሚሊዮን ጊዜ ታይቷል። ይህ ስራ በዚህ ቁጥር የታየው በ3 አመት ውስጥ ነው። የሃና ግን በ9 ወራት ነው 20,000,000 የታየው። የቬሮኒካ አዳነ "ጥፍጥ አለኝ" ከሁለት አመት በፊት ተለቆ 18 ሚሊየን ጊዜ ታይቶ ናሆም ከለቀቃቸው ስራዎች ብዙ እይታ በማግኘት 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 📍መረጃው የሁሉ አዲስ ነው። ለተጨማሪው: @EventAddis1
2 05310Loading...
37
"ጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት" በድምቀት ተካሄደ በጣፋጭ ህይወት መልቲሚዲያ በየዓመቱ የሚዘጋጅው "የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት" ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ  ግንቦት 30 2016 ዓ.ም በስካይላት ሆቴል ተካሄዷል። አርብ አመሻሽ ላይ የተካሄደው"የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት" በስድስት ዘርፎች ልዩ ልዩ ተሸላሚዎችን ሸልሟል። የዘንድሮው የአራተኛው የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት የተሸላሚዎች ዝርዝር የሚከተለውን እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ተመልክቷል። 1.ስራ ፈጠራን ተግባር ዘርፍ ተሸላሚ: ኢ/ር ቢጃይ ናይከር 2. ተስፋ የሚጣልበት/የሚጣልባት ስራ ፈጣሪ ዘርፍ ተሸላሚ: ቤተልሔም ደሴ 3.በበጎ አድራጎት ተቋማት ዘርፍ ተሸላሚ: ይመለከተኛል የበጎ አድራጎት ተቋም 4. በበጎ አድራጎት ተቋማት ዘርፍ (በግል): ሚኪያስ ለገሰ 5.የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ (በተግባር ዘርፍ ) ተሸላሚ: ሔኖክ ሐ/ማርያም (ኒው ላይፍ ) 6.ተስፋ የሚጣልበት/የሚጣልባት የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ ተሸላሚ: ሰላም አታላይ (ቡና ፖድካስት) 7.ዝናን ለመልካም ምግባር በመጠቀም ዘርፍ ተሸላሚ: አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ 8.ሚዲያውን ለሥነልቦና ግንባታ ዘርፍ ተሸላሚ: መጽሔተጥበብ የሬድዮ ፕሮግራም 9.ማህበራዊ ሚዲያውን ለበጎ ምግባር በመጠቀም  በቲክቶክ ዘርፍ ተሸላሚ : መምህርት ዙፋን ታምር (ሚስ ዙፋን) 10.ማህበራዊ ሚዲያን በበጎ በመጠቀም በዩቲዩብ ዘርፍ ተሸላሚ: መሪ ፖድካስት 11. ልዩ ተሸላሚ: ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ለተጨማሪው: @EventAddis1
1 93210Loading...
38
ሔሎ ኢትዮጵያ የሬድዮ ፕሮግራም እውቅና ተሰጠው በዳጉ ኮምኒኬሽን ፒኤልሲ እየተዘጋጀ በአንጋፋው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የሚተላለፈው "ሔሎ ኢትዮጵያ" የሬድዮ ፕሮግራም ከአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት እውቅና ተሰጥቶታል። 54 ዓመታትን ያስቆጠረው አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት በርካታ የምርምር ውጤቶችን በማውጣትና ለሀገራችን ብሎም ለዓለም አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ ተቋም ነው። ግንቦት 29 እና 30 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ አህሪ አለርት የጤና መንደር እና በአዳማ በሚገኘው የወባና ትኩረት የሚሹ ቆላማ በሽታዎች የምርምርና ስልጠና ማዕከል ውስጥ በተካሄደው ጉባኤ ላይ የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) ላለፉት 54 ዓመታት በጤናው ዘርፍ የምርምር ልማትን ለማሳደግ እንዲያስችል በርካታ የምርምር ውጤቶችን በማውጣትና ለሀገራችን ብሎም ለአለም አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። በኢንስቲትዩቱ መድኃኒት የተላመደ የቲቢ ሕክምናን ከ24 ወራት ወደ 9 ወራት ዝቅ የሚያደርግ የምርምር ውጤት መገኘቱ የተገለፀ ሲሆን የምርምር ውጤቱ በዓለም ጤና ድርጅት እውቅና ተሰጥቶታል። በዚህ ጉባኤ ላይ ለሚዲያ ተቋማት እውቅና የተሰጠ ሲሆን ከእነዚህም የሚዲያ ተቋማት መካከል ሔሎ ኢትዮጵያ የሬድዮ ፕሮግራም አንደኛው ነው። እውቅናውን በቦታው በመገኘት የሔሎ ኢትዮጵያ ባልደረባ ጋዜጠኛ ናትናኤል ደበና በክብር ተቀብሏል። Telegram:https://t.me/EventAddis1
1 8902Loading...
39
ኤም ኤን ጂ ፊልም ፕሮዳክሽንና ኢንቨስትመንት የአፍሪካ ጽህፈት ቤቱን ሰኞ ያስመርቃል ከቴክኖሎጂ ጋር ዝምድና የፈጠረ፣ ዓለም አቀፍ  የፊልም ማህበረሰብን የመፍጠር ግብ የሰነቀው  ኤም ኤን ጂ የፊልም ኩባንያ በኢትዮጵያ ሥራውን በይፋ ሊጀምር ነው። ኤም  ኤን ጂ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቁ የፊልም አምራቾች የተወሰነውን ገበያ በመግዛት መልሶ በስቶክ ማርኬት የሚሸጥ ኩባንያ ነው፡፡  ይህ የፊልም ኩባንያ፣ ሲኒማቶግራፊን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር እንዴት ማቆራኘት እንደሚቻልና  የፊልም ኢንዱስትሪንም ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘዴዎችን የሚቀይስ ነው ተብሏል። ኤም ኤን ጂ ኩባንያ በአፍሪካ በይፋ የከፈተውን የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤቱን ሰኞ ሰኔ 3 2016 ከቀኑ 6:30  ጀምሮ በማዶ ሆቴል ያስመርቃል፡፡ በዚህ ዕለትም ከፊልም ሙያ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ባለሙያዎችና የሚዲያ ሰዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተወዳጅ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ከፓፓራዚ ማስታወቂያ ጋር በትብብር ያዘጋጁት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 📍መረጃው የተወዳጅ ሚዲያ ነው Telegram:https://t.me/EventAddis1
2 0998Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
የወንዲ ማክ አልበም ሰኔ 14 ይለቀቃል የድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) "ይንጋልሽ" የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። ድምጻዊው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁም "እነሆ አርብ ሠኔ 14 ቁርጥ ቀን ሆነ "ይንጋልሽ " ብለን ከንጋት የተቃጠርንበት አልበማችንን ወደ እናንተ የምናደርስበት ሠላም ያቆየን" ብሏል። ይህም አልበም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
እማዬ እንዳለች ኑ ቡና ጠጡ ብላለች! በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ከዛሬ ሰኔ 8 እስከ ነገ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ህዝብ ቡና በነፃ እየተጋበዘ ነው። ይህ አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት ነፃ ቡና ዝግጅት ሙዚቃ ፣ፋሽን ሾዎችን መዝናኛዎችን እና የተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶችን ማሰናዳታቸውን እና ህብረተሰቡ በነጻ ቡና እየጠጣ እንዲዝናና አዘጋጆቹ ታሜሶል ኮሚዩኒኬሽን አሴቲክስ ሶሉሽን እና ከሊያን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። #Ads ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የድምጻዊ ዘሩባቤል ሞላ ታናሽ ወንድም የሆነው ድምጻዊ ኤርሚያስ ሞላ አዲስ የቅብብል ነጠላ ሙዚቃውን አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ለአድማጮች አድርሷል። ሙዚቃው በኤርምያስ ሞላ እና የኢትዮጵያን አይዶል ምርጥ አምስት ተወዳዳሪ በነበረችው በእርገት ሰለሞን(ናኒ) በቅብብል የተሰራ ነው። "እስከወዲያኛው " የሚል ርዕስ የተሰጠው ሙዚቃው በዳዊት ተስፋዬ (ደጃፍ ፖድካስት) ግጥሙ ተጽፎለታል። የሙዚቃው ዜማ እና ቅንብሩ በራሱ በኤርሚያስ ሞላ ተሰርቷል። ከጀርባ በርካታ ሰዎች ተሳትፈውበታል። የሙዚቃ ቪድዮውን በኤርምያስ ሞላ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ታገኙታላችሁ ተብላችኋል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት በዚህ ወር ይካሄዳል የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት የፊታችን ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል። ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ የሚካሄደው የሃጫሉ ሽልማት በ11 የሽልማት ዘርፎች፤ በአፋን ኦሮሞ የተሰሩ የዓመቱ ምርጥ አልበም፣ የአመቱ ምርጥ ግጥምና ዜማ ደራሲ፣ የዓመቱ ምርጥ አቀናባሪ፣ ምርጥ የባህል ዘፈን፣ ምርጥ ዘመናዊ ሙዚቃ፣ የዓመቱ ምርጥ ወንድ እና ሴት አርትስቶች፣ የኣመቱ ምርጥ አዲስ ሙዚቀኛ (ሴት እና ወንድ)፣ ምርጥ የአመቱ የሙዚቃ ቪዲዮ፣ ሲኒማቶግራፊ እና ምርጥ ባህላዊ ውዝዋዜ በሚሉ ዘርፎች እንደሚሸለሙ ታውቋል፡፡ በሽልማት ውድድሩ ውስጥ ሚካተቱ የሙዚቃ ስራዎች ከመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የወጡ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡ ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
"የአባቶች የአእምሮ ጤና:የቤተሰብ ብርታት" የተሰኘ ተከታታይ የሥነልቦና ውይይት ከእሁድ ጀምሮ ይካሄዳል የአእምሮ ጤና ተሟጋች የሆነው እና የቤተሰብ የአእምሮ ደህንነት ላይ በመስራት የሚገኘው ሜንታል ሄልዝ አዲስ “የአባቶች የአእምሮ ጤና፡ የቤተሰብ ብርታት” በሚል መሪ ቃል ተከታታይ  መርሐግብር ለማሰናዳት እየተዘጋጀ እንደሆነ አስታውቋል። ይህም አባቶች ጤናማ እና ብርቱ ቤተሰብ በማጎልበት ረገድ ስለሚጫወቱት ወሳኝ ሚና አፅንዖት ለመስጠትም ያለመ ነው ተብሏል። ዝግጅቱን በዓለም አቀፍ የአባቶች ቀን እሁድ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል በርካታ አባቶች በተገኙበት አባትነትን በመዘከር የመክፈቻ ፕሮግራም እንደሚደረግ ኤቨንት አዲስ ደስታ ድረገፅ ሰምቷል። የዚህ መርሐግብር መግቢያ ሁለት መቶ ብር ነው። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
"ሜላድ"አውደርዕይ ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል ሜላድ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዝግጅት ማዕከል"ሜላድ የብራና ማዕድ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 8 እና ነገ እሁድ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም አዘጋጅቷል። ይህ አውደርዕይ ከዛሬ ቅዳሜ ከጠዋት 3፡00 ላይ ተከፍቶ እስከ እሁድ ምሽት ድረስ በቦሌ ደብረ ሳሌም ካቴድራል ትልቁ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ የሥዕል አውደርዕይ ተከፈተ የእውቁ ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ "የይቅርታ ጉዞ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ቦሌ አትላስ መብራት አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሜትሮፖሊታን የሥዕል ማሳያ ውስጥ የሥዕል ወዳጆች በተገኙበት ለእይታ እንደበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። ይህ የሥዕል አውደርዕይ የፊታችን ሰኔ 23 2016 ዓ.ም ለሳምንታት በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ድምጻዊ ጉቱ አበራ "ጋፊኮ" የተሰኘ አልበሙን በሚቀጥለው ሳምንት ለአድማጮች ያደርሳል ድምፃዊ ጉቱ አበራ “ጋፊኮ” የተሰኘ የመጀመሪያው አልበሙን ማጠናቀቁን አስታወቀ። ድምፃዊ ጉቱ አበራ በለቀቃቸው ነጠላ ዜማዎች በርካታ አድናቂዎችን አፍርቷል። ከ15 ቀን በፊት ኢዮሌ የተሰኘ ቪዲዮ ክሊፕ የተሰራለት ነጠላ ዜማ ለቆ ተወዶለታል። አልበሙ በሚቀጥለው ሳምንት አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ፋስት መረጃ ከድምፃዊው ያገኘው መረጃ ያሳያል። አልበሙ የራሱን የዩቲዩብ ቻናልን ጨምሮ በሌሎችም ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በላይ ይለቀቃል ተብሏል። 📍መረጃው የፋስት መረጃ ነው። ቴሌግራም: @EventAddis1
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የድምጻዊ ጉቱ አበራ "ጋፊኮ" የተሰኘ አልበሙን በሚቀጥለው ሳምንት ለአድማጮች ያደርሳል ድምፃዊ ጉቱ አበራ “ጋፊኮ” የተሰኘ የመጀመሪያው አልበሙን ማጠናቀቁን አስታወቀ። ድምፃዊ ጉቱ አበራ በለቀቃቸው ነጠላ ዜማዎች በርካታ አድናቂዎችን አፍርቷል። ከ15 ቀን በፊት ኢዮሌ የተሰኘ ቪዲዮ ክሊፕ የተሰራለት ነጠላ ዜማ ለቆ ተወዶለታል። አልበሙ በሚቀጥለው ሳምንት አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ፋስት መረጃ ከድምፃዊው ያገኘው መረጃ ያሳያል። አልበሙ የራሱን የዩቲዩብ ቻናልን ጨምሮ በሌሎችም ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በላይ ይለቀቃል ተብሏል። 📍መረጃው የፋስት መረጃ ነው። ቴሌግራም: @EventAddis1
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የኔ መኪና እና የኔ ዴልቨሪ አገልግሎቶች ይፋ ሆኑ ቲዎስ ቴክኖሎጂ "የኔ መኪና" እና "የኔ ዴልቨሪ" የተሰኙ ሶፍትዌሮችን በማበልጸግ ወደ ስራ ማስገባቱን ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል በተሰናዳ ፕሮግራም ይፋ አድርጓል። "የኔ መኪና" የትራንስፖርት ዘርፉን ከማዘመን አኳያ በርካታ ጥቅሞች እንደሚሰጥ የተነገረ ሲሆን በተለይም በመንገድ እና ትራንስፖርት ባለስልጣንና በተሽከርካሪ ባለንብረቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ያለምንም ክፍተት በመናበብ ስራቸውን ምቹ እና ቀልጣፋ እንዲሆን ከማድረግም በላይ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችን ማሳደስ ያለባቸውን ነገሮች በማስታወስ ከቅጣት እና አላስፈላጊ እንግልት የሚያድን ሶፍትዌር እንደሆነ ተገልጿል። ሌላኛው "የኔ ዴሊቨሪ" ሶፍትዌር ሲሆን የተለያዩ ዶክመንቶችን፣ ሰነዶችን፣ እቃዎችን እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን ቴከኖሎጂ በመጠቀም ለግለሰቦች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለሆስፒታሎች ለማድረስ የበለጸገ ሶፍትዌር እንደሆነ ተነግሯል። ቲዎስ ቴክኖሎጂ ሶልሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ሶፍትዌር መተግበሪያዎችን በማበልጽግ እየሰራ የሚገኘ ድርጅት ነው። ቴሌግራም: @EventAddis1
Show all...