en
Feedback
Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Open in Telegram

Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Chat us! Buy ads: https://telega.io/c/consite

Show more
3 597
Subscribers
+224 hours
+97 days
-2030 days
Posts Archive
#የቅድሚያ_ክፍያ ( #Advance_Payment) ------------- ------------- ------------ በዚህ ፅሁፍ ቅድሚያ ክፍያ ምንድ ነው? አላማውስ? አቅራቢውና ተጠቃሚውስ ማን ነው? ያለባቸው ግዴታስ ምን ይመስላል? የሚሉትን ነጥቦች እንዳስሳለን፡፡ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና በኮንስትራክሽን ዉሎች ከሚዘወተሩ የዋስትና አይነቶች አንዱና የተለመደዉ ነው፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያ የቅድሚያ ክፍያ ምንድ ነው የሚለውን እንይ፡፡ በመንግስት ግዢ አዋጁ አንቀፅ 48 ላይ በመንግስት ገዥ አፈፃፀም ጊዚ አቅራቢዎች ከክፍያው ጋር እኩል የሆነ ዋስትና ሲያቅርቡ የቅድሚያ ክፍያ እንደሚስጥ ይገልፃል፡፡ ይህ የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ከጠቅላላው የውሉ ዋጋ ሰላሳ ፐርሰንት (30%) መብለጥ እንደለለበትና ሊከፈል የሚችለው የገንዘብ መጠንም በጨረታ መመሪያው ላይ መገለፅ እንደሚገባው የመንግስት ግዢ መመሪያ አንቀፅ 16.26.1 ያስገድዳል፡፡ ተዋዋይ ተቋራጮችም ይህንን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ለማግኘት ከማመልከቻ ጋር የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም በሁኔታዎች ያልተገደበ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሐገር ውስጥ ተቋራጮች ሲሆኑ በሁኔታዎች የተገደበ ዋስትና ከኢንሹራንስ ተቋማት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ የሚያቀርቡትም ዋስትና ከሚጠይቁት የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ጋር እኩል መሆን አለበት፡፡ ይሁን እንጂ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በዋስትናው ምትክ ከመሰረታቸውና ከሚከታተላቸው ባለሰልጣን መስሪያ ቤት የሚያቀርቡት ደብዳቤ እንደ ዋስትና ተቀባይነት ይኖረዋል ሲል የመመሪያው አንቀፅ 16.20.5(ሐ) ይደነግጋል፡፡ ከዚህም በፊት ግን ተቋራጩ በግዢ ስነ-ስርዓቱ ያሸነፈውን ዉል መፈረምና የውል ማስከበሪያ ገንዘብ ወይም ዋስትና ያቀረበ መሆን አለበት (አዋጅ ቁ.649/2001፣ አንቀፅ 48/2/)፡፡ በአዋጁ አንቀፅ 78(3) መሰረት የመንግስት ግዢ ኤጀንሲ አዋጁንና መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ ያወጣው መደበኛ የውል ሠነድ ጠቅላላ ሁኔታ [The Public Procurement Agency Standard Bidding Document: General Condition of Contracts: PPA-2011] ክሎስ 60(1) ላይ የቅድሚያ ክፍያው ለተቋራጩ መከፈል ያለበት ተቋራጩ ስራውን ለመጀመር የሚያወጣውን ወጪ ለመሸፈን እነዲረዳው ታስቦ ሲሆን ይህም የሚከፈለው ተቋራጩ ለግንባታ ስራው የሚያገለግሉ ማሽኖችን ዕቃዎችንና መሳሪያዎችን መግዛቱን ወይም ማዘዙን የሚያሳይ መረጃ ሲያቀርብ መሆኑን ያስቀምጣል፡፡ በስራው ጊዜያትም ገንዘቡን እነዚህን ዕቃዎችና ማሽኖችን ለመግዛትና ወደ ግንባታ ቦታው ለማንቀሳቀስ/ለማዘዋወር የተጠቀመበት መሆኑን የሚያሳይ ፋክቱር/Invoices ለኢንጂነሩ በማቅረብ ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በተጨባጭ የሚስተዋለው ችግር ብዙ ጊዜ ተቋራጮች የቅድሚያ ክፍያውን ለታለመለት አላማ አያውሉም የሚል ሲሆን ይህም ችግር በተለይ በግንባታው ዘርፍ በተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ ይህም ትልቁ ችግር መነሻው እነዚህ ተቋማት ምንም የሚያቀርቡት ዋስትና ሳይኖር ባቋቋማቸው መስሪያ ቤት ደብዳቤ ላይ ብቻ ተማምኖ ክፍያው ስለሚሰጣቸው ነው፡፡ ለዚህም ሲባል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ወይም በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ የኢንሹራንስ ዋስትና ያቀረቡ ተቋራጮችን አሰሪው/ተዋዋዩ የመንግስት አካል አስፈላጊ ሲሆን፡ የቅድሚያ ክፍያው ገቢ የሚደረግበትና ከውሉ ጋር ለተያያዙ ወጪዎች ብቻ በመንግስትና በኢንተረፕራይዙ ወይም በኮንትራክተሩ ተወካዮች በጋራ ፊርማ ወጪ የሚደረግ የተለየ የባንክ አካውንት እንዲከፈት ሊያዝ ይችላል፤ ገንዘቡም ለታሰበለት አላማ ብቻ እንዲውል የተለየ ስምምነት መፈራረም አለበት፡፡ ስለዚህ የቅድሚያ ክፍያ ማለት ተቋራጩ ለስራው ማስጀመሪያ የሚሆኑትን የተለያዩ የግንባታ መሳሪያዎች መግዢያነት የሚውል በአሰሪው የመንግስት መስሪያ ቤት በቅድሚያ የሚከፈለው ገንዘብ ነው፡፡ ይህም ምንም ስራ ሳይሰራ የሚከፈል ገንዘብ ስለሆነ ለተቋራጩ ዕዳ ወይም ብድር ነው፡፡ ስለሆነም ተቋራጩ ብድሩን እንዲምልስ ይገደዳል ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ተቋራጩ ይህንን ብድር እንዴት ይመልሳል የሚለው አንዳንድ ጊዜ በግንባታ ውሎች ላይ አለመግባባት ያስነሳል፡፡ በግዢ መመሪያው አንቀፅ 16.26.9 ላይ እንደተገለፀው ለተቋራጮችና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተከፈለ የቅድሚያ ክፍያ በውሉ አፈፃፀም የተለያዩ ደረጃዎች ላይ በክፍያ ሰርተፍኬት ፀድቀው ከሚከፈሏቸው እያንዳንዱ ክፍያዎች ላይ እየተቀነሰ ሙሉ የቅድሚያ ክፍያው እስኪመልስ ድረስ የመንግስት መስሪያ ቤቱ ያስቅራል፡፡ ይህም ማለት ተቋራጩ የወሰደውን የቅድሚያ ክፍያ ሙሉውን ከአንድ ወይም ከሁለት ክፍያዎች ላይ የመክፈል ግዴታ የለበትም፡ አሰሪ መስሪያ ቤቱም ሙሉ ክፍያውን አንዴ ቀንሶ ማስቀረት አይችልም ማለት ነው፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አንዳድ ጊዜ ሙሉ ቅድሚያ ክፍያውን በአንዴ ቀንሰው በማስቀረት ከተቋራጮች ጋ እሰጣገባ ሲገጥሙ ይስተዋላል፡፡ ይህ ከህጉ አግባብ ውጭ ነው፡፡ የቅድሚያ ክፍያ ገንዘቡ ሙሉውን ሳይመለስ በተለያዩ ምክንያቶች ውሉ ቢቋረጥ የአሰሪ መስሪያ ቤቱ የከፈለውን ገንዘብ ማስመለስ እንዲያስችለው ተቋራጩ የሚያቀርበው ዋስትና ክፍያው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስገዳጅነት እንደሚኖውም መመሪያው ይገልፃል፡፡ ውሉ ቢቋረጥ እንኳን ያልተከፈለውን የቅድሚያ ክፍያ ዋስትናው ወዲያውኑ ካለምንም መቃወሚያ እንዲከፍል ይገደዳል ይላል የመደበኛ የውል ሠነድ ጠቅላላ ሁኔታ ክሎስ 60.7፡፡ By: Girum Getu LL.M Candidate in Construction

Share General Registration Requirement and Procedure for Contractors.docx

Share የኮንስትራክሽን መብቶች ምንነት እና የሚስተዋሉ ችግሮች.pdf

ጥልቅ ሀዘን! ገዜ ጎፋ ወረዳ #ኬንቾ_ሻቻ_ጎዝዲ ቀበሌ ትላንት ረፋድ አካባቢ የተከሰተው የመሬት ናዳ ብዙ ሰዎችን ጎድቷል። ሁላችንም በምንችለው አቅም ትብብር እናድርግ ወንድማችን ኮንትራክተር አንዷለ
+1
ጥልቅ ሀዘን!
ገዜ ጎፋ ወረዳ #ኬንቾ_ሻቻ_ጎዝዲ ቀበሌ ትላንት ረፋድ አካባቢ የተከሰተው የመሬት ናዳ ብዙ ሰዎችን ጎድቷል። ሁላችንም በምንችለው አቅም ትብብር እናድርግ ወንድማችን ኮንትራክተር አንዷለም ገብሩ ድጋፍ አድርገዋል እባካችሁ ሌሎቻችንም ድጋፍ በማድረግ ከጎናቸው እንሁን!

ለማህበሩ አባላት በሙሉ! 7ኛው ዙር ስልጠና ምዝገባ
ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በኮንስትራክሽን የሙያ ደህነትና ጤንነት በተመለከተ እየተሰጠ ያለው ስልጠና አሁንም እንደቀጠለ ነው ። በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር  መሰብሰቢያ አዳራሽ የተካሄደው 6ተኛው ዙር 81 ሰልጣኞች የተሳተፉበት  ስልጠና ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናቋል። 👩‍👩‍👧‍👦 ሰባተኛው ዙር ስልጠና ምዝገባ በመካሄድ ላይ በመሆኑ የማህበሩ አባላቶች የስልጠናው ተሳታፊ እንድትሆኑ ማህበሩ ጥሪውን ያስተላልፉል። የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ ማህበር

ጠቃሚና ወቅታዊ መረጃዎችን ስለምንለቅ ቻናሉን join አድርጉት
http://t.me/ConSiteCatalogue 👈👈🚧🏗
ለሌሎችም ተያያዥ ስራ ላላቸው ባልደረቦቻችሁ አጋሩ በተለይ ኮንትራክተሮች እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ላላችሁ ባለሞያዎች ይጠቅማችኃል መልካም ጊዜ!🤚

የሀምሌ_ወር_2016_ዓ_ም_የሀራጅ_ሽያጭ_ማስታወቂያ_1.PDF3.01 MB

Share ደረጃ 8 ኮንትራክተሮች ሊስት.pdf

Share ደረጃ 8 ኮንትራክተሮች ሊስት.pdf

የስራ ማስታወቂያ
የስራው መጠሪያ: Office engineers የስራው አይነት: ባሉበት የሚሰራ - ቋሚ የስራው ዘርፍ: #ሲቪል_ምህንድስና_እና_ኮንስትራክሽን የስራው ቦታ: አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ የትምህርት ደረጃ: የመጀመሪያ ዲግሪ የልምድ ደረጃ: ከፍተኛ የተፈላጊ ሰው ብዛት: 3 የአመልካቾች ጾታ: ወንድ ደሞዝ/ክፍያ: ወርሃዊ የማመልከቻ ማብቂያ ቀን: August 2nd, 2024 የስራው ዝርዝር: የስራ አድራሻ: ተከስተ ዘሪሁን ጠቅ/ስ/ተ - የስራ መደብ መጠሪያ : office engineer -የስራ ቦታ : አ.አ ፆታ: ወንድ -የትምህርት ደረጃ : በengineering degree - የስራ ልምድ : 5አመት እና ከዚያ በላይ ጨረታ ላይ የሰራ
ስልክ : 0912663267 Tekesete zerihun General contractor