Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗
Ir al canal en Telegram
Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Comments Construction Solution Official Service
Mostrar más3 589
Suscriptores
+224 horas
-17 días
+4230 días
Archivo de publicaciones
ከግንቦት_13_ቀን_2016_ዓ_ም_እስከ_ግንቦት_30_ቀን_2016_ዓ_ም_የሀራጅ_ሽያጭ_ማስታወቂያ1.PDF3.62 MB
የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሳምንትከግንቦት 15 – 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል።
የግንባታ ፍቃድ አጠያየቅ እና የወሰንተኛ ጉዳይ:-የማሻሻያ፣ የመጠቀሚያ ፈቃድ፣ ጊዜያዊ ግንባታ ወይም የማፍረስ ሥራ ለማከናወን የሚቀርብ የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ ሲኖር በተናጠል በተዘጋጀላቸው (ማለትም ለአዲስ ለማስፋፊያ ወይም ለማሻሻያ ግንባታ ቅፅ፣ ለግንባታ እድሳት ፈቃድ ቅፅ፣ ለግንባታ ማፍረስ ፈቃድ ቅጽ፣ ለአገልግልት ለውጥ ቅጽ፣ ለጊዜያዊ ግንባታ ቅጽ) በመሙላት የግለሰብ ከሆነ በአመልካቹ ተፈርሞ፣ በመንግስታዊ፣ በሕዝባዊ እና የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተያዘ ወይም የሚተዳደር ከሆነ በኃላፊው ተፊርሞ እና የድርጅቱ ማህተም አርፎበት ጥያቄው መቅረብ ይኖርበታል። ማንኛውም የግንባታ ፈቃድ ጠያቂ ስለወሰንተኞቹ ትክክለኛ መረጃ በወሰንተኛ ግንባታ መግለጫ ቅጽ ላይ ወሰንተኛውን በማስሞላትና በማስፈረም ማቅረብ አለበት፣ ቅፁን ለመሙላት ፈቃደኛ በማይሆን ወሰንተኛ የከተማ አስተዳደሩ ቅፁን የማስሞላት ሃላፊነት አለበት። ወሰን ላይ የሚገነባ የምግብ ማብሰያና መሰል አገልግሎት ሰጪ ክፍሎች ግድግዳ የእሳት ቃጠሎን በተሻለ ሁኔታ መከላከል በሚችል ድፍን የግድግዳ ቁሳቁስ መገንባት አለበት። ጭስ እና እንፋልት ወደወሰነተኛ መውጣት የለበትም። በተለያዩ አካባቢዎች የሚገነቡ አንድ ዓይነት ስታንዳርድ ፕላኖች ያላቸው ግንባታዎች የየራሳቸው የግንባታ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል። ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማካተት ይኖርበታል፣ ወለልና በላይ ያለው ማንኛውም ግንባታ (የምድር በታች ወለል ቢኖረውም ባይኖረውም) ከወሰን ሁለት ሜትርና ከዚያ በታች ተጠግቶ የሚሰራ ከሆነ በቅድሚያ የወሰን ላይ ግንባታ ቅጽ መሙላትና ስምምነት ማግኘት ይኖርበታል፣ ለፈቃድ የሚቀርበው ስትራክቸራል ዲዛይን የወሰንተኛውን ነባር ህንፃ መዋቅር ይዘት ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት፤ የሚቀርበው የዲዛይን ሠነድ የወሰንተኛውን ነባር ህንፃ መጠን ለምሳሌ የኃይል ሚዛን (Load) ከግምት ያስገባበት አግባብ ማመልከት አለበት፣ በወሰንተኛ ነባር ግንባታ ደህንነት ላይ ምንም አይነት መናጋት እንዳይፈጠር በቁፋሮና በግንባታ ሂደት መወሰድ የሚኖርበትን የሚያሳይ የጥንቃቄ ንድፍ ለፍቃድ ከሚቀርበው ሰነድ ጋር መቅረብ አለበት። አየር ማስገቢያ ሳይኖረው ብርሃን ብቻ የሚያስገባ ግንባታ ወሰን ላይ ለመሥራት ለዚሁ ተብለው በተዘጋጁና አሳልፈው በማያሳዩ ውፍረታቸው ከ5 ሳ.ሜ የማያንስ የመስታወት ግርግዳ መጠቀም ይቻላል። ይህም በሚቀርበው ዲዛይን ላይ በግልጽ መጠቀስ ሲኖርበት ወሰን ላይ የተሰራ ከሆነ ወሰንተኛው እንደማንኛውም ድፍን የግድግዳ አካል አስጠግቶ ሊሰራበት ስለማይከለከል የብርሃን ማስገቢያ መስፈርት ለሚጠየቅበት ተጨማሪ ወይም አማራጭ የብርሃን ምንጭ ማመልከት አለበት። ማንኛውም ሰው ግንባታውን እስከ ወሠን አስጠግቶ ማከናወን ይችላል ሆኖም ወሠን ላይ ለመገንባት ያቀደ ሰው በአዋሳኙ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚያደርገውን የመከላከያ ዘዴዎች ለአጎራባቹ ማሳወቅ ይኖርበታል። ግንባታው ተጀምሮ እስኪጠናቀቀ ድረስ በአጎራባቹ አደጋና ችግር በማያስከትል ሁኔታ መከናወን አለበት። በማንኛውም ጊዜ ወሰንተኛው ግንባታውን እንዲከታተል መፍቀድ አለበት። በማንኛውም የግንባታ ወቅት ለሚፈጠር ችግር ገንቢው ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል። በአዋጁ፣ በደንቡ እና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ባረቀቀው የሕንጻ መመሪያ (Building Directives) እና በሌሎች የማስፈጸሚያ ሰነድች ላይ የተገለፁትን መስፈርቶች ያላሟላ የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ በግንባታ መጠየቂያ ቅጽ ላይ በተመለከተው ቦታ ያልተሟላበትን ምክንያት በመግለፅ ተመላሽ መደረግ ይኖርበታል።
¡Ya disponible! Investigación de Telegram 2025 — los principales insights del año 
