en
Feedback
Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Open in Telegram

Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Chat us! Buy ads: https://telega.io/c/consite

Show more
3 611
Subscribers
-224 hours
No data7 days
+930 days
Posts Archive
🏗️ ከስራ ተቋራጮች ጋር ሲሰሩ ማወቅ የሚገቡዎት 10 ወሳኝ ነጥቦች:- - ​በግንባታው ዓለም ስኬታማ ጉዞ ለማድረግ እና ገንዘብዎን ከብክነት ለመታደግ ከስራ ተቋራጮች (Contractors) ጋር ሲያደርጉት የሚገባውን ውልና ጥንቃቄዎች በዝርዝር ተመልከቱ፦ ​1. ህጋዊ ፈቃድ እና ምዝገባ 📄 ሥራ ከመጀመራቸው በፊት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ማረጋገጫ መጠየቅ የመጀመሪያው እና ትልቁ የጥንቃቄ እርምጃ ነው። ​2. የብቃት ማረጋገጫ (Grade) ተቋራጮች በምን ያህል አቅም እና ካፒታል እንደሚሰሩ የሚገልጽ ደረጃ (ከደረጃ 1 እስከ 10) አላቸው። ለሚሰሩት ፕሮጀክት የሚመጥን ደረጃ ያለው መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ​3. የስራ ልምድ (Portfolio) 🏢 ከዚህ በፊት የሰሩዋቸውን ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች፣ የተጠናቀቁ ህንፃዎች ወይም ሌሎች ግንባታዎች በአካል በመሄድ ወይም በምስል ማየት የብቃታቸው ትልቁ ማሳያ ነው። ​4. ውል እና ስምምነት (Contract) ✍️ በቃል የሚደረግ ንግግር በግንባታ ላይ ቦታ የለውም። የዋጋ ዝርዝር፣ የቁሳቁስ ጥራት፣ የሚጠናቀቅበት ጊዜ እና የክፍያ ሁኔታ በግልጽ የሰፈረበት ውል በህግ ባለሙያ መዘጋጀት አለበት። ​5. የዋጋ ግምት እና ክፍያ (Budget) 💰 ክፍያዎች በሂደት (በደረጃ) እንጂ በአንዴ መፈጸም የለባቸውም። ስራው ሲሰራ እና የጥራት ምርመራ ሲያልፍ ብቻ ክፍያ እንዲለቀቅ ማድረግ ገንዘብን ከብክነት ይታደጋል። ​6. የጊዜ ሰሌዳ (Timeline) ⏳ ግንባታው የሚጀምርበትን እና የሚጠናቀቅበትን ቀን በግልጽ የሚያሳይ የጊዜ ሰሌዳ (Schedule) ከውሉ ጋር መያያዝ አለበት። ዘግይቶ የሚጠናቀቅ ስራ ከፍተኛ ተጨማሪ ወጪ ያስከትላል። ​7. የቁሳቁስ ጥራት (Quality Control) 🧱 በውሉ ላይ የተስማሙባቸውን የኮንክሪት መጠን፣ የብረት ዓይነት እና ሌሎች የግንባታ እቃዎች ጥራት በባለሙያ ማስመረመር ለህንፃው ጽናት ዋስትና ነው። ​8. የሰራተኞች ዋስትና እና ደህንነት (Safety) 🦺 በግንባታ ቦታ ላይ ለሚደርሱ አደጋዎች ተቋራጩ ኃላፊነት አለበት። የኢንሹራንስ ሽፋን ያላቸው እና የደህንነት እቃዎች (Safety materials) የሚጠቀሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው። ​9. የባለሙያ ቁጥጥር (Supervision) 📐 እርስዎ ራስዎ ኢንጂነር ካልሆኑ፣ የስራውን ሂደት የሚከታተል ገለልተኛ አማካሪ (Consultant) ወይም መሐንዲስ መቅጠር ተቋራጩ ጥራቱን የጠበቀ ስራ እንዲሰራ ይገፋፋል። ​10. የዋስትና ጊዜ (Defect Liability Period) 🔑 ስራው ተጠናቆ ከተረከቡ በኋላም እንኳ ለተወሰነ ጊዜ የሚፈጠሩ ስንጥቆች ወይም ጉድለቶች በባለቤቱ ወጪ ሳይሆን በተቋራጩ እንዲስተካከሉ በውሉ ላይ መካተት አለበት።

🏠 አሁን ላይ 94 ካሬ ሜትር ቤት ለመስራት ስንት ብር ያስፈልጋል? ቤት ለመስራት ሲያስቡ እነዚህ ጥያቄዎች ያጋጥሙዎታል፡ እነዚህን ካዎቁ ግምቱን ያውቃሉ፡፡ 📍 የት ነው የሚገነባው? (አዲስ አበባ
🏠 አሁን ላይ 94 ካሬ ሜትር ቤት ለመስራት ስንት ብር ያስፈልጋል? ቤት ለመስራት ሲያስቡ እነዚህ ጥያቄዎች ያጋጥሙዎታል፡ እነዚህን ካዎቁ ግምቱን ያውቃሉ፡፡ 📍 የት ነው የሚገነባው? (አዲስ አበባ ወይስ ከከተማ ውጪ?) 🏗 በምን አይነት ማቴሪያል ይሰራል? (ጂ+0፣ ጂ+1፣ በHCB 15 ወይስ?) ውጤቱስ 📋 ምን ያህል የቁሳቁስ እና የገንዘብ ወጪ ያወጣል? ምን ምን ያስፈልጋል? ምን ያክል ጊዜ ? እነዚህን ጥያቄዎች በትክክለኛ መረጃ እና በአጭር ጊዜ ለመመለስ 👉 https://estimator.et/ ላይ በመግባት በነጻ ይሞክሩት! 🎁 የዚህ ገጽ ተከታዮች ልዩ ስጦታ! የፕሮሞ ኮድ CONPROXY26 በመጠቀም 100% በነጻ፡ ✅ ሙሉ የ BOQ Excel ፋይል ማውረድ ✅ ዝርዝር Material Requirement (የሲሚንቶ፣ የብረት፣ የባላስት ወዘተ ፍላጎት) ማግኘት ይችላሉ!

+2
የሳይት መሃንዲስ ሆናቹ ስትሰሩ ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት ማረጋገጥ ያለብን ነገሮችን inspect ለማድረግ የሚረዳን ቼክ ማድረጊያ ቼክሊስት ነው በዚህ ቴሌግራም ቻናል ገብታቹ አውርዱት ትወዱታላቹ። 👇👇👇👇👇

የ G+4 Slab ዲዛይን ሙሉ ቴምፕሌት አሁኑነ አውርደው ይጠቀሙበት

📶 ኮንትራክተሮች የቢሮ መሃንዲሶች ዲዛይን መሃንዲሶች ኮንትራክተር ለመሆን ያሰባቹ እንዲሁም በግንባታ በግዢ አስተዳደርና በማማከር ዙርያ ያላቹ በሙሉ እስከመጨረሻው አድምጣቹ ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር አድርጉላቸው‼️

👉የዋጋ ማሻሻያ (Price Adjustment) – አስፈላጊነቱ እና ተግባራዊነቱ የዋጋ ማሻሻያ በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከፍተኛ ሚና ያለው የኮንትራት መርህ ሲሆን፣ በፕሮጀክት አፈጻጸም ወቅት የሚከሰቱ የዋጋ ግሽበቶች፣ የገንዘብ ዋጋ መቀነስ እና የግብዓት ዋጋ ለውጦች ተፅዕኖ እንዳያስከትሉ የሚረዳ መንገድ ነው። ዓላማው ኮንትራክተሩን እና አሠሪውን ከልክ ያልፈ የፋይናንስ አደጋ መጠበቅ እና ፍትሃዊ ክፍያ ማረጋገጥ ነው። በኢትዮጵያ፣ በተለይም በመንገድ እና በትልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች፣ የነዳጅ፣ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ቢቱመን፣ የሰራተኛ ኃይል እና የመሳሪያ ዋጋ ፈጣን መለዋወጥ የዋጋ ማሻሻያን የማይተካ አስፈላጊ መሆኑን አሳይቷል። ይህ መርህ በትክክል ሲተገበር፣ ፕሮጀክቶች እንዳይዘገዩ፣ ኮንትራክተሮች እንዳይጎዱ እና የህዝብ ገንዘብ በአግባቡ እንዲውል ያግዛል። 📎 ለተግባራዊ አጠቃቀም፣ የዋጋ ማሻሻያ ሂሳብ ማስላት የሚያግዝ Excel ፎርማት አብረን አያይዘናል፤ ለወደፊት አጠቃቀምዎ እንዲረዳ ተዘጋጅቶ ቀርቧል። @etconp

✅ የአዲስ አበባ መሬት አስተዳደር ቢሮ እግድ ተነስቶል።
✅ የአዲስ አበባ መሬት አስተዳደር ቢሮ እግድ ተነስቶል።

የደረጃ 5 ጨረታ ምዝገባ ቅድመ ምዘና ዉጤት ማሳወቅን ይመለከታል:: አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ፍላጎት ለማሟላትና የከተማዋን እድገት ለማፋጠን በልዩ ትኩረት እየተገበረ
+9
የደረጃ 5 ጨረታ ምዝገባ ቅድመ ምዘና ዉጤት ማሳወቅን ይመለከታል:: አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ፍላጎት ለማሟላትና የከተማዋን እድገት ለማፋጠን በልዩ ትኩረት እየተገበረ ለሚገኘው መጠነ ሰፊ የቤት ልማት ፕሮግራም በግንባታው ዘርፍ የተሰማሩ እና አስፈላጊውን መስፈርት የሚያሟሉ በደንብ ቁጥር 199/2018 መሰረት ሥራ ተቋራጮችን ለመመዝገብ ከቅዳሜ 09/12/2018 ዓ.ም እስከ ሐሙስ 14/12/2018 ዓ.ም ድረስ ጥሪ ማድረጉና የምዝገባ ሂደቱ በስኬት መጠናቀቁ ይታወቃል። በዚሁ መሠረት የቀረቡትን ሰነዶች የማጣራት ሥራ ተከናውኖ የመጀመሪያ ደረጃ የምዝገባ ሂደቱን ሙሉ በሙሉ ላሟላችሁ እና ስማችሁ ከዚህ በታች ለተዘረዘራችሁ ሥራ ተቋራጮች በሙሉ የቴክኒክ ሰነዳችሁን (Technical Proposal) በቴክኒክ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የጊዜ ገደብ እና መስፈርት መሠረት እንድታስገቡ እናሳዉቃለን፡፡ ነሀሴ 15 ቀን 2018 ዓ/ም የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የደረጃ 1 ጨረታ ምዝገባ ቅድመ ምዘና ዉጤት ማሳወቅን ይመለከታል:: አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ፍላጎት ለማሟላትና የከተማዋን እድገት ለማፋጠን በልዩ ትኩረት እየተገበረ
+3
የደረጃ 1 ጨረታ ምዝገባ ቅድመ ምዘና ዉጤት ማሳወቅን ይመለከታል:: አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ፍላጎት ለማሟላትና የከተማዋን እድገት ለማፋጠን በልዩ ትኩረት እየተገበረ ለሚገኘው መጠነ ሰፊ የቤት ልማት ፕሮግራም በግንባታው ዘርፍ የተሰማሩ እና አስፈላጊውን መስፈርት የሚያሟሉ በደንብ ቁጥር 199/2018 መሰረት ሥራ ተቋራጮችን ለመመዝገብ ከቅዳሜ 09/12/2018 ዓ.ም እስከ ሐሙስ 14/12/2018 ዓ.ም ድረስ ጥሪ ማድረጉና የምዝገባ ሂደቱ በስኬት መጠናቀቁ ይታወቃል። በዚሁ መሠረት የቀረቡትን ሰነዶች የማጣራት ሥራ ተከናውኖ የመጀመሪያ ደረጃ የምዝገባ ሂደቱን ሙሉ በሙሉ ላሟላችሁ እና ስማችሁ ከዚህ በታች ለተዘረዘራችሁ ሥራ ተቋራጮች በሙሉ የቴክኒክ ሰነዳችሁን (Technical Proposal) በቴክኒክ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የጊዜ ገደብ እና መስፈርት መሠረት እንድታስገቡ እናሳዉቃለን፡፡ ነሀሴ 15 ቀን 2018 ዓ/ም የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የግንባታ ስራ ጨረታ ማስታወቂያ፡ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን "ከ ኮካ -ገዳመ እየሱስ መሳለሚያ የአስፋልት መንገድ ግንባታ የግንባታ ሥራዎች " በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
+9
የግንባታ ስራ ጨረታ ማስታወቂያ፡ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን "ከ ኮካ -ገዳመ እየሱስ መሳለሚያ የአስፋልት መንገድ ግንባታ የግንባታ ሥራዎች " በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ፍላጎት ያላቸው ተቋራጮች በሙሉ ከታች ባለው የeGP system ሊንክ በመግባትና አስፈላጊውን መረጃ በመሙላት መሳተፍ ይችላሉ። Construction Works Tender Notice: The Addis Ababa City Roads Authority invites eligible contractors through an Open Tender for the Construction Works of Coca - Gedame Eyesus - Mesalemia Asphalt Road Project. Qualified firms can participate by registering and submitting all required information through the official eGP System link below. Procurement Reference No.: AACRA-ICB-W-0007-2019-BID-Open eGP System Link: https://production.egp.gov.et/egp/bids/report/tendering/fea30a5e-b8f7-4e3a-8bff-a88fac1684fb/open

በአገራችን የግንባታ ኮንትራት ስርዓት መሠረት (በተለምዶ በ Public Procurement and Property Authority መመሪያዎች እና በ Ethiopian Public Procurement Proclamation No. 649/2009 የመሠረተ ልማት) በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ የስራ መጠን ለውጦች፣ ክፍያዎች እና የኮንትራክተር አፈፃፀምን ለመቆጣጠር ብዙ የኮንትራት ቃላት ይጠቀማል። ከእነዚህ ዋና ዋና ቃላት የሚከተሉት ናቸው። 1. ኦሚሽን (Omission) ትርጉም:- ኦሚሽን ማለት በኮንትራቱ ውስጥ የተጠቀሰ አንድ የስራ ክፍል ወይም እቃ ከፕሮጀክቱ ውስጥ መወገድ ማለት ነው። ዓላማ:- - የፕሮጀክቱ ዲዛይን ሲቀየር - የበጀት ጉዳይ ሲኖር - አንዳንድ ስራዎች አስፈላጊ ካልሆኑ ባህሪያት:- - በ Variation Order ይፈፀማል - ኮንትራክተሩ ለተወገደው  ስራ ክፍያ አይጠይቅም - የኮንትራት ዋጋ ይቀንሳል ምሳሌ:- 10 km የውሃ መስመር ለመጫን ተወስኖ ነበር። በኋላ 2 km አስፈላጊ አይደለም ተብሎ ከፕሮጀክቱ ተወገደ። 2. አዲሽን (Addition / Extra Work) ትርጉም:- አዲሽን ማለት ከመጀመሪያ ኮንትራት በኋላ የሚጨመር አዲስ ስራ ወይም የስራ መጠን መጨመር ነው። ዓላማ - ዲዛይን እንዲሟላ ያደርጋል - የፕሮጀክቱ ጥራት እንዲሻሻል ይጠቅማል ባህሪያት - በኢንጅነር ወይም በባለቤት ይፀድቃል - በ Variation Order ይመዘገባል - ኮንትራክተሩ ተጨማሪ ክፍያ ይቀበላል የክፍያ መንገዶች:- - የኮንትራቱን ዋጋ መጠቀም - አዲስ ዋጋ መወሰን - Daywork መጠቀም 3. ቫሪዬሽን ኦርደር (Variation Order) ትርጉም:- ቫሪዬሽን ኦርደር ማለት በኮንትራቱ ውስጥ ያለውን የስራ መጠን ወይም ዲዛይን ለመቀየር የሚሰጥ መደበኛ ትእዛዝ ነው። ዓይነቶች:- - ስራ መጨመር - ስራ መቀነስ - ዲዛይን መቀየር - የእቃ አይነት መቀየር ዋና ነጥቦች:- - በመደበኛ ሁኔታ መፀደቅ አለበት - የኮንትራቱ ዋጋ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል - የጊዜ ማራዘሚያ ሊያስፈልግ ይችላል ፎርሙላ:- New Contract Price = Original Price ± Variation Value 4. ቦነስ (Bonus) ትርጉም:- ቦነስ ማለት ኮንትራክተሩ ፕሮጀክቱን ከተወሰነው ጊዜ በፊት ካጠናቀቀ የሚሰጥ ተጨማሪ ክፍያ ነው። ዓላማ:- - ፕሮጀክቱ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ - የመዘግየት አደጋ እንዲቀንስ ምሳሌ:- Bonus = 40,000 Birr / day ቀደም ብሎ 10 ቀን ካጠናቀቀ Bonus = 40,000 × 10 = 400,000 Birr 5. ፔናልቲ (Penalty / Liquidated Damage) ትርጉም ፔናልቲ ማለት ኮንትራክተሩ ፕሮጀክቱን በተወሰነው ጊዜ ካልጨረሰ የሚቀነስ ገንዘብ ነው። ዓላማ:- - የባለቤቱን ኪሳራ ለመከላከል - ኮንትራክተሮች በጊዜ እንዲጨርሱ ፎርሙላ:- Penalty = Contract Price × Penalty Rate × Delay Days ምሳሌ:- Contract Price = 50,000,000 Birr Penalty Rate = 0.1% Delay = 20 days Penalty = 50,000,000 × 0.001 × 20 Penalty = 1,000,000 Birr 6. የጊዜ ማራዘሚያ (Extension of Time – EOT) ትርጉም:- የጊዜ ማራዘሚያ ማለት ኮንትራክተሩ በማይቆጣጠሩ ምክንያቶች ሲዘገይ ተጨማሪ ጊዜ መስጠት ነው። ምክንያቶች:- - ከባድ ዝናብ - ጎርፍ - የዲዛይን ለውጥ - የክፍያ መዘግየት - የጥሬ እቃዎች እጥረት 7. የዋጋ ለውጥ (Price Escalation) ትርጉም:- የዋጋ ለውጥ ማለት የስራ እቃ፣ ሰራተኛ ወይም ነዳጅ ዋጋ ሲጨምር የኮንትራቱ ክፍያ መቀየር ነው። ፎርሙላ:- Pn = Po × (a + b(Ln/Lo) + c(Mn/Mo) + d(Fn/Fo)) 8. ሪቴንሽን ገንዘብ (Retention Money) ትርጉም:- ሪቴንሽን ገንዘብ ማለት ከኮንትራክተሩ ክፍያ ውስጥ የሚቀነስ ገንዘብ ሲሆን የስራ ጥራት ለማረጋገጥ ይጠቀማል። በተለምዶ:- - 5% – 10% ይቀነሳል መመለሻ - 50% ስራ ሲጠናቀቅ - 50% ከ Defects Liability Period በኋላ 9. የጉድለት ኃላፊነት ጊዜ (Defects Liability Period) ትርጉም:- ፕሮጀክቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ኮንትራክተሩ የሚታዩ ጉድለቶችን በራሱ ወጪ የሚያስተካክልበት ጊዜ ነው። የተለመደ ጊዜ:- - 6 ወር - 12 ወር ምሳሌ ጉድለቶች:- - የኮንክሪት ስንጥቅ - የውሃ ፍሳሽ - የመንገድ መውደቅ 10. ፐርፎርማንስ ቦንድ (Performance Bond) ትርጉም ፐርፎርማንስ ቦንድ ማለት ኮንትራክተሩ ስራውን እንደሚፈጽም የሚሰጥ የገንዘብ ዋስትና ነው። በተለምዶ:- - 10% የኮንትራት ዋጋ 11. አድቫንስ ክፍያ (Advance Payment) ትርጉም:- አድቫንስ ክፍያ ማለት ስራ ከመጀመሩ በፊት ለኮንትራክተሩ የሚሰጥ የመጀመሪያ ክፍያ ነው። በተለምዶ - 10% – 20% የኮንትራት ዋጋ ዓላማ:- - መሳሪያ ለመግዛት - ሰራተኞችን ለመከፈል - ስራ ለመጀመር 12. ኢንተሪም ክፍያ (Interim Payment Certificate – IPC) ትርጉም ኢንተሪም ክፍያ ማለት በፕሮጀክት ሂደት ውስጥ ለተጠናቀቀ ስራ በየወሩ የሚሰጥ ክፍያ ነው። ፎርሙላ:- Payment = Work Done − Retention − Previous Payments 13. የመጨረሻ ክፍያ (Final Payment Certificate)

👉 የተሻሻለዉ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ ውሏል።