cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

#ገጣሚ_ኤልያስ_ሽታሁን ከሁሉም በላይ በዚህ ቻናል ይነግሳል ! ሌሎችም ድንቅ እና እውቅ ገጣምያን ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ፣ ኤፍሬም ስዩም ፣ ገብረክርስቶስ ደስታ ፣ መስፍን ወንድወሰን አስታወሰኝ ረጋሳ እና ሌሎች ገጣሚያን ስራቸው በዚህ ቻናል ይለቀቃል ! እናንተ ቻናሉን ተቀላቀሉ #Share በማድረግ ቤተሰባዊ ሀላፊነታችሁን ተወጡ🙏 እኔ @Henilogy ነኝ 🥰🥰🥰🥰🥰 ኢትዮጵያዊ

Show more
Advertising posts
10 167
Subscribers
-124 hours
+1037 days
+44230 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
Check out ስሜትን በግጥም😘😢😄: https://t.me/semetnbegtm
4560Loading...
02
​​┈◦◎●◉አልሞትም!◉●◎◦┈ ስሚ! እኔ በዚህ ዐለም ፤ብዙ ብሰቃይም አንድ ሀሙስ የቀረው፤ መስየ ብታይም አምሮቴን ሳላገኝ፤ሱሴን ሳላከትም በመሬት ከርስ ውስጥ ፤ገላየን አልከትም አልሞትም! ማንም ባልደፈረው፤ መንገድ ሳልገሰግስ እንደ ንጉስ አይዙር፤ግማሽ ቀን ሳልነግስ በጠገበው ሳልስቅ፤ ለራበው ሳልደግስ አልሞትም! ዝማሜን ሳላወልቅ፤ ያንድበቴን ግድብ ዙፋን ላይ ሳልሸና፤ ጌቶቼን ሳልሰድብ ከድሃ ሳላብር፤ ከገባር ሳልወግን ከምድር በረከት፤ ድርሻየን ሳልዘግን አልሞትም፤ ስሚ! ልቤ እንደምኞቱ፤ ቢያገኝ እንደምርጫው ያላማየ ማብቂያ፤ አንቺ ነሽ መቁዋጫው እና አገሬን ለቅቄ፤ ልብሽህ ላይ ሳልከትም በውብ ከንፈርሽ ላይ፤ ከንፈሬን ሳላትም አልሞትም! ➢ገጣሚ ፦በእውቀቱ ስዩም ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢ @eliyasshitahun @eliyasshitahun     ➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟
1 34025Loading...
03
Media files
1 1400Loading...
04
ብቸኝነት! ቀኑ ተሰናብቷል ጨለማው በርትቷል ጨረቃ የት ጠፋች? ምን ሆኑ ኮከቦች? ጅቦች አይፈነጩ ውሾች አይንጫጩ፡፡ ጨለማው ፍጹም ነው ነፋስ ጭራሽ አይነፍስ ዛፍ አይወዛወዝ አንድ ወፍ አይላወስ ሁሉም ፀጥ በያለበት ለጥ፡፡ ሰው ሁሉ ምን ነካው? ድምፁ እንዲህ የጠፋው? እኔንስ ምን ነካኝ? እንቅልፍ የማይወስደኝ? እኔ ብቻዬን ነኝ በዚህ ደረቅ ውድቅት፤ ልቤ እየቃተተ ጠልቶ ብቸኝነት፡፡ ሰው አለወይ ባገር? ማረፊያ ለፍቅር? ፈላጊና፤ ተፈላጊ ሁሉ ቀናው ወይ በሙሉ? የቀረ የለም ወይ በዓለም አለኔ በምኞት ኩነኔ? እኔ እንደዚህ ስዋኝ ባሳብ በትካዜ የት ይሆን ያለሽው አንቺ ይህን ግዜ ምን ታደርጊ ይሆን? እንገናኝ ይሆን? መች ይሆን ዕለቱ? መች ይሆን ሰዓቱ? የትስ ይሆን ቦታው? እንዴት ይሆን እውቂያው? እጠብቅሻለሁ ልቤን እየታዘዝሁ፤ አትቅሪ፤ ፈልጊኝ፤ እፈልግሻለሁ፡፡ ©ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም @eliyasshitahun
1 46928Loading...
05
@eliyasshitahun የተክልዬዋ
1 6687Loading...
06
@eliyasshitahun የተክልዬዋ
1 9134Loading...
07
በጉም የታፈነ ሰማይ ስር ደመናዉ ጎልቶ ከደመናዉ በታች ንስር አይኑን ያጣ ወጣት የማያያዉ ታምር ይከወናል ሁሌ በዚች ምድር በታመመ ፊደል ህመሙን ሊደብቅ እንደሚተጋ ፀሃፊ ሌት ከቀን እንደሚጨነቅ የማያይ ግን እዉር ነዉ አላልንም በአሳማሚ ፊደል ልቡን አልሰበርንም ይልቅስ ቅስም በሚሰብር      ቅጥ ባጣ አንደበት እዉር ነዉ የሚል ቃል      እኛ የጣልንበት ብኩን ምድርን ላያይ እግዜር የመረጠዉ የአይኑን ብረሃን ያጣ ማየት የተሳነዉ እኔ ግን... በልብ ፊደል ቋንቋ ለመግባባት ማየት የተሳነዉን መርጣለዉ ያን ወጣት ገላዬን በሸፈነዉ ጨርቅ ላልመሰለኝ መልኬን ገጼን አይቶ የማይሸሸኝ ልቡን ብቻ ከፍቶ የዉስጤን ሚረዳ የሰማዩን መጥቆር የኑሮን ቀዳዳ ባያይም ተረድቶ ጥላ የሚፈልግ ራሱን የሚመስል ሁሌ የሚል ፈገግ እሱን እመርጣለዉ ወዳጄ ላደርገዉ አዎ ያንን ወጣት ማየት የተሳነዉ። ✍️ዳዊት 📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌 @eliyasshitahun @eliyasshitahun @betagitim
1 8739Loading...
08
መቼ ትመጫለሽ?? በዔደን ታደሰ እና ኤልሻዳይ(ኤል ቶ) ተፅፎ እንደቀረበ✍🎤 @ediwub & @elshaday_23 @topazionnn @topazionnn
1 92710Loading...
09
ሞትና ህይወት ህይወት ማለት ፤ተጓዥ ሂደት 'ምትሰጥህ ፤ነፃ ትምህርት ሁለት ቀለም ፤ጥቁርናነጭ ምታሲዝህ ፤አንድ አማራጭ ብርቱ ውጊያ ፤ባለ ትግል ከጊዜጋ ምታነሳ ፤ወይ የምትጥል አንዴ ጣፋጭ ፤ወይ መራራ ስትደቁስ የማትራራ ግማሽ ባንተ ፤ግማሽ ላንተ እየሆነች ተለዋዋጭ ሂደት፤ 'ማትሰለች ትልቅ ሀሰት፤ ምትክድህ በአንድ እለት ምትሞሽርህ ለቁርጥ ቀን፤ ምትድርህ ለሞት ሞት ማለት ፤የማይፋቅ እውነት በሰከንዶች ውስጥ ፤ከአለም መለየት ጣዕም አልባ ፤ባዶ ስሜት ለዱንያ ጥፋት ፤መክፈያ ሰዓት የምድር ሩጫን ፤የጉዞ ማብቂያ ነብስን መከተል፤ ስጋን መልቀቂያ አንዴ ከሄዱ ፤የማይመጡበት ነፃ መውጫ ነው፤  ከዓለም ሰንሰለት እንዳመጣጥህ፤ ጠርቶ የሚወስድህ አፈር 'ሚያለብስክ፤ ለራቁት ገላህ ደባል ማይጠራ ፤ገንዘብ ወይም ሌላ  ጊዜ የማይሰጥ ፤ከመጣ ሗላ ይዘህ ምትሄደው፤ የኖርከው ግብርህ ክፋና መልካም ፤ያረከው ስራህ እንዲነው እልፈት ፤ቸኳይ እንግዳ ከተፍ የሚለው ፤ሳትሰናዳ ወስዶ ይከትሀል፤ ከዘመን ምርጫህ ሲኦል ወይ ገነት፤ ልክ እንደ ስራህ። ✍️የተክልዬዋ @semetenbegtm @eliyasshitahun share&comment እንዳይረሳ😊
2 54821Loading...
10
@eliyasshitahun @semetnbegtm የተክልዬዋ
2 75015Loading...
11
ለኔ እኮ አንቺ፣    ከ 10 ቱ ትዕዛዛት ልክ እንዱ ትእዛዝ እንደ ሙሴ የእስራኤልን ህዝብ    ይዞ እንደመጓዝ ለኔ እኮ የሆንሺብኝ፣ እንደ ቤተክርስቲያን ደዉል፣ አዛን ማዉጣት መካ ላይ ከ ቢላል  እኩል፥ ምን ስሆን ትወጂኛለሽ..?!!? ራስ ዳሽን ወጥቼ ያንቺን ምስል ልስቀል ከዛ ላይ ወደ ታች በአፍጢሜ ልተከል የቱን ሀገር---በስምሽ ላሰይም...!? የልቤ ሀገር ባንቺ ስም ነዉ ለአንቺ ባይታይም ምን አድርጌ ምን ሰርቼ ነዉ ምታፈቅሪኝ..? እንደ ነቢያቱ ላንቺ እየፃፍኩኝ እንደ እየሩሳሌም አንቺን አመለኩኝ አንቺ እንድቶጂኝ... ሁሉንም ሁኛለዉ ያልሆንኩት የለኝም አንቺን ስል ያልሄድኩበት ቦታ አይገኝም ስምሽን አምልኬ ስጋዬን በጾም ቀጣዉ፥ ጸሎቴም አንቺ ሁነሽ መጀመሪያዉ..ማሳረጊያዉ። አንቺ እንድቶጂኝ... ጨረቃ ላይ ልዉጣ ኮከብ ላዉርድልሽ እንደ ዶክተር አብይ መግለጫ ላዉጣልሽ ቴዲ አፍሮን ወይስ ጥላሁንን ሁኜ ላዚምልሽ ወይስ እንደ ባዓሉ ግርማ መጽሃፍ ልፃፍልሽ ንገሪኛ ...የኔ ፊያሜታ🇪🇷 ምን ስሆን ነዉ ባንቺ የምፈቀር?? የኤርትራን ባህር ዋኝቼ ልሻገር   ያንቺን  ምስል ልስቀል አዉርጄ ባንዲራ 🇪🇷 ወይስ በእግሬ ልምጣ ከመቀሌ አስመራ?!! ንገሪኛ መልሺልኝ...ምን ስሆን ነዉ ምታፈቅሪኝ     ''ካህን ሁኜ ተቀምጬ ገዳም ደሃ ሁኜ ወይስ ሀብታም ዳኛ ሁኜ አያስታራቅኩ..." ወይስ እንደ ዮሃንስ ህዝቡን እያጠመኩ' እንደ ጳዉሎስ አንቺን እየሰበኩ''። እያፈቀርኩ ልጠብቅሽ...ልፈልግሽ ለልቤ ዕረፍትን ትሰጪያለሽ...?   ግን መቼ ትመጪያለሽ...?!! ✍️ከዳዊት @eliyasshitahun @betagitim @betagitim
3 08255Loading...
12
ክርስቶስ በገብረ ክርስቶስ ደስታ ገጣሚ ቴዲ_አፍሮ አንባቢ ቴዳ እዩት ኢሄን ጠቢብ ሸራው እስኪደማ በቀይ እየወጋ በደም እየሳለው እንጨት እየወጋ ዳግም ክርስቶስን ጨርቁ ለይ ሰቀለው ቀራንዮ ሆነ የወጠረው ሸራ ጎሎጎታ ሆነ የወጠረው ሸራ አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ ብሩሹን አሹሎት እንደ ጎኑ ጦር ገብረ ክርስቶስም ክርስቶስ ላይ ከፍ የቆዳው አይነቱ በደም ተከልሎ ዘሩ እስከሚጠፋ እየወጋ ሳለው እየሳለ ወጋው ዘሩ እስከማይለይ መልኩ ዝም ብሎ ደሙ እስከሚናገር የትም ያለ ፍቅር እንዳይኖረው አገር እንዳለው ፈረንጅ እንዳለው ጥቁር እንዳለው ቀይ በመስቀል ላይ ሞቶ ያለው ስቃይ በቆዳ በቀለም እንዳናሳንሰው በደሙ ተሰቅሎ ሰው ያዳነውን ሰው ከቀናት ባንዱ ለት ሰዎች ሲሟገቱ በቀለሙ ጉዳይ ሲከራከሩለት በተመፃዳቂ የሙህር አንደበት በአንዱ አፍ ሲጠቁር በአንዱ አፍ ሲነጣ መታገስ አቃተው ሰአሊው ተቆጣ ስሜቱ ገንፍሎ በብሩሽ ጫፍ ወጣ ሀሳቡን የሚገልፅ ቀለም እስከሚያጣ ሸራ ላይ ሰቀለው እንጨት አመሳቅሎ አሎጣልህ አለው ፍቅርን ስሎ ስሎ በሳለው እየወጋ በደሙ እነቀባ ክርስቶስ ደሙ እንጂ ዘሩ አልተሰቀለም እንጨቱ ላይ ያለው እውነት ይህ አደለም እያለ እስኪናገር የስፅሉ አንደበት ገብረ ክርስቶስም ለክርስቶስ ቢሆን ቀለም እስኪያልቅበት በነጩ  ሸራ ላይ እስካሁን የሚወርድ ደም አፈሰሰበት ቀለም ቀይ ቀለም የደም ቀለም የጥላ ቀለም ፍቅር ዘር አደለም
2 36022Loading...
13
@eliyasshitahun
2 29411Loading...
14
ክፉ ቃል ......ያን ጊዜ ያን ጊዜ ልንተወው ልባችን ያልቻለው ፍቅርን አልነበረም ጥል ፀባችንን ነው ..........እኔም እኔም ስትሄጂ ቃላትን አውጥቼ መንገድ ሰርቻለው .....አንቺም አንቺም ፈቅደሽ እንደተውሺኝ አስታውሰዋለው ......ልሂድ ስትይኝ እሺ ያልኩት የራሴ ልብ ላይ ክደት የፈፀምኩት ለምን ነበር ተይ ያላልኩት? ......ለምን? አሁን ከሰማሺኝ ጆሮ ከሰጠሺኝ ትንሽዬ ጠጠር ችግር ተሰንቅራ አለያይታናለች ክፋት ተንኮል ጭራ እያልኩኝ ለምክንያት አልደረድርም ቃል ያኔ ያወጣሁት ክፉ ቃል ይበቃል ክፉ ቃል   ✍ቴዳ
2 66720Loading...
15
#ወለም_ያለው_ዘመን😏😏 #መስፍን_ወንድወሰን ለወዳጆ ያጋሩ Share... እሁድ እንደዚህ አይነት ግጥም ካልተሰማ አትመሽም👏👏 https://t.me/eliyasshitahun https://t.me/eliyasshitahun
2 83614Loading...
16
እሷን መልሱልኝ እግዜር ከሰዉ ለይቶ እንደሰራት እንደ ማህተብ ከልቤ ያነጻት በፍቅር ደቂቃ ሰኮንዶች የሆነችኝ ሀሁ በላ ፍቅርን ያስቆጠረችኝ ሀገር ምድሩ የመረቃት ከእኔም ልብ ዘመናት ያቆያት ጠፊ ሁና የዉሃ ሽታ ሁለመነዋ ሊቀር በትዝታ ልቤ ሳይደፈን ሳይዘጋ ማንም ላይገባበት እሷን መልሱልኝ የልቤን ነገር ዳግም ታስብበት ✍️ዳዊት ============================ @eliyasshitahun @eliyasshitahun @betagitim @betagitim
2 58719Loading...
17
የጠቢባን እውቀት አስገራሚነቱ፣ አላዋቂን ሁሉ በጥበብ መርታቱ። @Henilogy
2 2604Loading...
18
............አንድ ሰው አለ...........   ✍ገጣሚ ➖በውቀቱ ስዩም አንባቢ ቴዲ እርጅና ሲጫንሽ እድሜ ተጠራቅሞ እንደ አስም ሲያፍንሽ ሽበት እንደሙዳይ በጭንቅላትሽ ላይ በድንገት ሲፈላ ያይንሽ ከረጢቱ በንቅልፍሽ ሲሞላ ምድጃ ዳር ሆነሽ መፃፍሽን ከፈተሽ ያለፈውን ዘመን ገልጥ ስታነቢ የኔን ቃል አስቢ እወድሻለው ያልኩሽን ከልብሽ አንብቢ ስንቶአፈቀሩት በሀይቅ በይስሙላ የገጽሽን አቦል የውበትሽን አፍላ ግን አንድ ሰው አለ ከሌሎች ወንዶች ጋ ያልተመሳሰለ በዕጽብ ድንቅ ፍቅርሽ የነደደ የመልክሽ ፀደይ ሲያልፍ ልክእንደመስቀል ወፍ ጥሎሽ ያልነጎደ። 〰〰〰〰〰〰〰
2 49319Loading...
19
➿➿➿➿➿➿➿➿➿➿➿ ፍቅሬን ሳልገፅላት!! ------------------------------ ያቺ! ውብ ከፍጡራን በላይ፤ የውቅያስ ጥበብ የዓይን አማላይ፤ የምሽት ጨረቃ የመዓልቱ ጮራ ፤ ውበቷን ሊያነፁ ቢተጉ በተራ፤ ምስሏን ሊቀርፁ ጠቢባን ቢለፉ፤ በምናብ ሀዲድ ቢከንፉ፤ ብዕር ብትተፋ !ለዛች ዓይነ-ግቡ፤ ይሄድ ይሄዱና መባቻ ጠፍቶአቸው፤ አንክሮ ይላሉ ውበቷ ደንቋቸው። ያኔ በለጋነት ስንሄድ በአደባባይ ፤ ሽርፍራፊ ቅኔ በሚያፍር ዓይን ላይ፤ ማዕቀብ ወርዶበት ላይወጣ በገሃድ ፤ ዘመን በበረረ በትግስት መንገድ፤ የኑዛዜ ወኔ ድፍረት ሲያጣጥር፤ ዝንተዓለም ወድጄያት ፍቅሬን ሳልናገር፤ እሷስ ሄደች አሉኝ ወደ ትዳር ህይወት፤ በብዙ ባስባት አሳቅፋኝ ናፍቆት። ** በ dt (dtvote12) 9/6/2013E.C እንደተፃፈ
2 60716Loading...
20
#በዚህ_ጊዜ እሬሳ ቀለለ ሞትም እረከሰ፣ የሰው ልጅ ክብር ከእንስሳ አነሰ። ወንድም ወንድሙ ላይ ጦር እየሰበቀ፣ መኖር ብርቅ ሆነ ጥል እየደመቀ።     @Henilogy [ገጣሚ ሄኖክ ፀጋዬ] ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @eliyasshitahun
2 5112Loading...
21
❗❗ የጅራፍ ንቅሳት ❗❗ ኤፍሬም ስዩም በዚህ ግጥም ምስጥ እያላችሁ ተኙ..... መልካም ምሰጣ $$$$$$ JOIN US $$$$$ https://t.me/eliyasshitahun https://t.me/eliyasshitahun
2 58529Loading...
22
#ትውስታ #ትውስታ #ትውስታ
1 9790Loading...
23
ገጣሚ ኤልያስ ሽታኹን አንባቢ ቴዲ "ወንበሩ ሰው አለው?" *    *    *     *     *     *    * እሷ "ወንበሩ ሰው አለው?" እኔ "ነበረው" (የለም የለም ውሸቴን ነው) እመጣለሁ ካለች ዘመን ያስቆጠረች፡፡ ደርሻለሁ ብላኝ መጠበቅ የበላኝ አይሃለሁ ያለች ልክ ነሽ ሰው አለች፡፡ (ነበረች) እሷ "ወንበሩ ሰው አለው?" እኔ ነበረው እንዳልል አለውም እንዳልል ቁጭ በይ እንዳልል ያንገበግበኛል ቃሏን እንደመጣስ ግራ ገባኝ እኮ ግን ደሞ ብትመጣስ ግን ደግሞ የለችም መጣለሁ ብላኝ ይኸው አልመጣችም.... ወንበሩ ሰው አለው እንጃ ቀርታለች እላለው እንጃ መንገድ ሰነከላት እንጃ ወይ ሌላ ከጀላት እንጃ መስከረሟ ጠባ እንጃ እግዜር መሀል ገባ እንጃ ብቻ ወንበሩ ሰው...አለው ብቻ ወንበሩ ሰው...የለው፡፡ መቀመጥ ያውም ወንበር ይዞ ትመጣለች ብሎ ሽንት እንኳ ቀዝቅዞ መናፈቅ ሳቅን ሲጠብቁ ስትቀር መነፍረቅ መጎለት ለመጣ ሰው ሁሉ ትመጣለች ማለት መጠበቅ እንደድሮ ፅሁፍ ሳይታዩ መድመቅ ነብዝዞ  ደብዝዞ መገኘት ሰውን ለመቀበል ራስን መሸኘት... "ወንበሩ ሰው አለው?" እንጃ.
2 31745Loading...
24
#አይ_መርካቶ አገር ከየጐራው ወጥቶ አንቺን ብሎ ነቅሎ መጥቶ ግሣንጉሡን ጓዙን ሞልቶ ኁልቁ መሣፍርትሽ ፈልቶ ባንቺ ባዝኖ ተንከራትቶ እንዴባዘቶ ተባዝቶ ተንጠራውዞ ዋትቶ ዋትቶ #አይ መርካቶ የምድር ዓለም የእንጀራ እናት ላንዱ ርካሸ ለሌላ እሳት ላንዱ ፍትሃት ላንዱ ምትሃት ላንዱ ሲሳይ ላንዱ ፍርሃት ላንዱ ተስፋ ላንዱ ሥጋት የግርግር የሆይታ ቋት #አይ መርካቶ ያንዱን ወስዶ ላንዱ ስጥቶ ያንዱን ገፍፎ ላንዱ አብልቶ አንዱን ነስቶ ላንዱ አድልቶ ስንቱን ፈርቶ ስንቱን ሸሽቶ ባፌጮሌ ተሸልቶ.. #አይ መርካቶ ቢያዋጣ ወይ ባያዋጣ ከስንቱ ተንጣጥቶ ጣጣ ተነታርኮ ተገዛግዞ ተብለጥልጦ ተበዛብዞ #መርካቶ ያገር ድግሱ የገጠር ስንቅ አግበስብሱ ለከተሜው ለአባ ከርሱ በትሬንታው በአውቶቡሱ በቁሳቁስ ግሣንጉሱ ለቱጃር የጥጋብ ቅርሱ ለኔ ብጤም የቀን ጉርሱ አባ መስጠት እጦት ቢሱ አይ መርካቶ፥ ተሻምቶ ተገበያይቶ ወይ ተፈራርሶ ተጣልቶ በእንካ ስላንቲያ ተማትቶ አንዳንዴም ተፊነካክቶ ወይ ተመራርቆ ተስማምቶ #አይ መርካቶ የኤስፔራንቶ የቋንቋ አገር ያ ሲነገር ያ ሲሰበር የስንቱ ልሣን ሲቀመር ያንዱን ሲያከር ያንዱን ሲያቀር ያንዱን ሲያውስ ያንዱን ሲያስቀር ያ ሲደቀል ያ ሲፈጠር የልሣን ሸማች ለብቻ ከዕቃው ጭምር በስልቻ ሲመዠርጥ እንደግቻ ቶሎ በል ቶሎ በል ብቻ ዝግ በለ እማይባልበት መርካቶ የአንደበት ፍላት ግርግር እማይባልበት ክርክር እሚሞቅባት ወዝ እሚንጠፈጠፍባት ሸቀጥ እሚታመቅባት ደላላ የሚያውጅባት ቸርቻሪ እሚተምምባት ሌባ ላብከን የሚያልብባት #አይ መርካቶ መርካቶ የገበያ ጎራ ላንዱ ምድር ላንዱ ጣራ #ያ ሲዘረፍ ያ ሲደራ ያ ሲወስን ያ ሲፈራ ያ ሲሸሽግ ያ ሲያወራ የንግድን ጠፍ ወይ የአዝመራ የነጋዴን ምጥ መከራ የከበረ እንደመረዋ ረብጣ፣ አፍኖት ሲያስገመግም የከሰረ አንደ ፈላስፋ፣ በቁም ቅዠት ሲያልጐመጉም የኔብጤም ጠብሻን መቶት፣ በየጥሻው ሲያስስመልም ቸርቻሪ ዝርዝሩን ቋጥሮ ፣ ቅንጣቢውን ሲቃርም የወር ሸማች ስንቁን ጭኖ፣ ሲመርቅና ሲረገም ማጅራት መቺ ከጀርባው፣ ጥሻውን ዘሎ ሲያዘግም ከዚህ በርሮ እዚያ ሰብሮ፣ ያዝ ሲባል ሲሸሽ ሲጣጣር ከአማኑኤል እራጉኤል ሾልኮ፣ ዶሮ ማንቂያ ዳር ከመስጊድ እስከበረንዳ፣ ከአራተኛ እስከነፍስ ይማር የኡኡታው የጡሩምባው ፣የጩኽቱ የፊሸካው ሳግ የሰው የመኪና የከብት ፣የፍግ የቁሳቁስ ትንፋግ ሲገፋተር ሲመዣረጥ፣ ላቦት ለላቦት ሲላላግ ትንፋሽ ለትንፋሸ ሲማማግ አባ ሽብሩ መርካቶ ፣ ያለውን በገፍ አጣጥቶ የሌለውን ከሌለበት ፣አስጐልጉሎ አስወጥቶ ስንቱን ከዳር ዳር አዛምቶ በግድም በውድም አስማምቶ አገርን ካገር አስማምቶ ሁሉን አቅፍ ባይ መርካቶ ያቻችለዋል አሻምቶ። #አይ መርካቶ ©✍ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን @eliyasshitahun
2 64017Loading...
25
​​➢➢ላ’ንዲት የገጠር ሴት➢➢ ስትፈጭ የኖረች ሴት፣ መጁ በመጠኗ፣ ወፍጮውም በልኳ፣ ጓያ ትፈጫለች ጓያ ሽሮ ሲሆን ያበቃል ታሪኳ !!    አስባው አታውቅም… ወደ ኦናው ምድር ለምን እንደመጣች፣ ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ከና’ቷ ሆድ ወጣች፣ ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ጡት አጎጠጎጠች፣ ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ለባሏ ተሰጠች…… ተዚያን ቀን ጀምራ፣ ተዚያን ቀን ጀምሮ፣ ድንግል ድንጋይ ወቅራ፣ ትፈጫለች ሽሮ…… አታውቅም፣ ማን እንደሚባሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አታውቅም፣ ሹማምንት በ’ሷ ስም፣ ምን እንደሚሠሩ፣ አነሳኹት ‘ንጂ፣ እኔም ለነገሩ፣ ፖለቲካ ጥበብ ራስን ማራቀቅ፣ ምን ይጠቅማትና ጓያዋን ለማድቀቅ ከቶ ማንም የለ, አበባ ‘ሚሰጣት፣ ከቶ ማንም የለ፣ ከተማ ‘ሚያወጣት፣ ከቶ ማንም የለ ፣ በዳንኪራ መላ፣ ወገቧን የሚያቅፋት፣ ልፋቷም፣ ዕረፍቷም፣ ወደዚህ መጅ መሳብ ወደዚያ መጅ መግፋት…… እንደ ዓባይ ፏፏቴ፣ ሽህ ዓመት ቢንጣለል፣ ቢጎርፍም ዱቄቱ፣ እንደ ሲኦል ወለል፣ ጫፍ የለውም ቋቱ!     ከዘመናት ባንዱ መስተዋት ፊት ቆማ፣ በተወለወለው፣ ራሷን ለማየት፣ ከጸጉራ ላይ ያለው ዱቄት ይኹን ሽበት ሲያቅታት መለየት፣ ያኔ ይገባታል የተሰጣት ዕጣ፣ ከማድቀቅ ቀጥሎ፣ መድቀቅ እንዲመጣ…     የመጅ አጋፋፏ - አምሳለ ሲሲፈስ፣ ከቋት ሥስት እንጅ፣ ሢሳይ አይታፈስ፣ ትቢያ ‘ሚተነብይ ዱቄት በዙሪያዋ፣ ከባርኔጣ አይሰፋም፣ የኑሮ ጣሪያዋ፣ "ስትፈጭ የኖረች ሴት" ይህ ነው መጠሪያዋ! ➛➛ገጣሚ ፦ በእውቀቱ ስዩም @eliyasshitahun                          ➛ሼር ያድርጉ!  ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━━
2 69633Loading...
26
አንተ እስክትገባበት "ለሁሉም ግዜ አለው⏳"        ያልከኝን ሰምቼ እራሴን በራሴ በትዝብት አምቼ   አለው ሁሉን ትቼ.... የትላንቱ ማዕበል🌪              ከወደቡ እስኪጋጭ እሳተገሞራው             ውሀውን እስኪያጭ የት አለኝ አማራጭ🤷‍♀️ ? የእልሁ ንዳድ ከቁጭት ተባብሮ🥺 የአሸናፊው ሽንፈት ተስፋዬን ሰባብሮ💔 ከስቃይ ሲያጋጨኝ ከድሌ ገፍትሮ ምን ይሁን ዘንድሮ😥? ታዲያ እንዳገኘሁህ ደረብኩኝ መግላሊት ተስፋዬን ቆርጬ እያየሁ የኋሊት ግና በአካሌ ሽንቁር አልጠፋበት በሬማ ክፍት ነው ................አንተ እስክትገባበት! ✍ihsuu እንደፃፈችው https://t.me/melody1212
2 46714Loading...
27
እድል ወይስ እጣ ዋጋ ቢሱን ዋጋ ለኑሮ እየቸረ ነገውን በትላንት እያመሳከረ ለሚኖር በምድር ሁሌ እንደዳከረ😒 እድል ወይስ እጣ ተጠያቂው ማነው ወርዶ እንዲወጣ የኑሮን ቁልቁለት የኑሮን አቀበት ሲወርደው በበጋ ሲወጣው በክረምት እድሉን ያማራል ይረግማል በድፍረት.. እጣ ፋንታ እድል እድል እጣ ፋንታ የእድል ግልባጭ ነው ህይወት ወይስ የእጣ መንታ🤔 እንዲያውም..... አጋጣሚ ይቀድማል ሀሳብ ከተምታታ Ihsuu✍ https://t.me/melody1212
2 3648Loading...
28
ኑሮ በጣም መሮኝ ማደርገዉን ሳጣ፣ ገመድ ለመግዛት ወደ ሱቅ ብ'ወጣ በባለሱቁ ምክር ሀሳቤን ቀይሬ በአንዴ ላለመሞት ሳልቃጠል አርሬ   በቀላል አልሞትም እንዲዉ እንደዋዛ   ብያለዉ...እንግዲህ ሚስት አግብቼ ስቃዬ ሳይበዛ። ✍️ዳዊት @betagitim @betagitim
2 5239Loading...
29
እኔና አንቺማ   አመላችን ገጥሞ ባያዉቅም   ተራርቀን እንኳን ባንነፋፈቅም የተሳብንበት ቀለም ሁለታችንን የሚያፈካ የወደድነዉ መጠጥ ሁለታችንን የሚያረካ   አለ..የከነፍንለት ህልም              ለሌላዉ ቅጀት የሆነ የምንድክመልት ህይወት     ፍሬ አፍርቶ ትዉልድን ያዳነ አለ...ያ'ካፋ ለት ጉም ወርሶት ሰማዩን    እኔና አንቺ እንጠርጋለን ላይ ላዩን ጥሪት ተርፎት ሁሉ ሰዉ ምድሩን ሲያስዉበዉ እኔና አንቺ ግን ሰማዩን ነበር ምናስበዉ ምድር ሁሌ እንድትርስ     እንድታፈራ ዘላለም ብሩክ ትሁን እያልን     ምድረ ለምለም ይህ ሁሉ ቢሆንም እኔ እና አንቺ ግን አልተገናኘንም። ✍️ዳዊት @betagitim @eliyasshitahun @eliyasshitahun
2 88721Loading...
Check out ስሜትን በግጥም😘😢😄: https://t.me/semetnbegtm
Show all...
ስሜትን በግጥም😘😢😄

እንኳን ደህና መጡ ወደዚህ ቻናል የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ግጥምና ስነፅሁፎች ከእራሳችንና ከገጣምያን ተሰብስበው የምናደርስበት ስሜታችንን የምንገልፅበት አውድ ነው። ግጥማቹን ሌላ ችሎታቹን @sg2124ለማጋራት የምትፈልጉ

​​┈◦◎●◉አልሞትም!◉●◎◦┈ ስሚ! እኔ በዚህ ዐለም ፤ብዙ ብሰቃይም አንድ ሀሙስ የቀረው፤ መስየ ብታይም አምሮቴን ሳላገኝ፤ሱሴን ሳላከትም በመሬት ከርስ ውስጥ ፤ገላየን አልከትም አልሞትም! ማንም ባልደፈረው፤ መንገድ ሳልገሰግስ እንደ ንጉስ አይዙር፤ግማሽ ቀን ሳልነግስ በጠገበው ሳልስቅ፤ ለራበው ሳልደግስ አልሞትም! ዝማሜን ሳላወልቅ፤ ያንድበቴን ግድብ ዙፋን ላይ ሳልሸና፤ ጌቶቼን ሳልሰድብ ከድሃ ሳላብር፤ ከገባር ሳልወግን ከምድር በረከት፤ ድርሻየን ሳልዘግን አልሞትም፤ ስሚ! ልቤ እንደምኞቱ፤ ቢያገኝ እንደምርጫው ያላማየ ማብቂያ፤ አንቺ ነሽ መቁዋጫው እና አገሬን ለቅቄ፤ ልብሽህ ላይ ሳልከትም በውብ ከንፈርሽ ላይ፤ ከንፈሬን ሳላትም አልሞትም! ➢ገጣሚ ፦በእውቀቱ ስዩም ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢ @eliyasshitahun @eliyasshitahun     ➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟
Show all...
😁 10👍 2❤‍🔥 1🔥 1
ብቸኝነት! ቀኑ ተሰናብቷል ጨለማው በርትቷል ጨረቃ የት ጠፋች? ምን ሆኑ ኮከቦች? ጅቦች አይፈነጩ ውሾች አይንጫጩ፡፡ ጨለማው ፍጹም ነው ነፋስ ጭራሽ አይነፍስ ዛፍ አይወዛወዝ አንድ ወፍ አይላወስ ሁሉም ፀጥ በያለበት ለጥ፡፡ ሰው ሁሉ ምን ነካው? ድምፁ እንዲህ የጠፋው? እኔንስ ምን ነካኝ? እንቅልፍ የማይወስደኝ? እኔ ብቻዬን ነኝ በዚህ ደረቅ ውድቅት፤ ልቤ እየቃተተ ጠልቶ ብቸኝነት፡፡ ሰው አለወይ ባገር? ማረፊያ ለፍቅር? ፈላጊና፤ ተፈላጊ ሁሉ ቀናው ወይ በሙሉ? የቀረ የለም ወይ በዓለም አለኔ በምኞት ኩነኔ? እኔ እንደዚህ ስዋኝ ባሳብ በትካዜ የት ይሆን ያለሽው አንቺ ይህን ግዜ ምን ታደርጊ ይሆን? እንገናኝ ይሆን? መች ይሆን ዕለቱ? መች ይሆን ሰዓቱ? የትስ ይሆን ቦታው? እንዴት ይሆን እውቂያው? እጠብቅሻለሁ ልቤን እየታዘዝሁ፤ አትቅሪ፤ ፈልጊኝ፤ እፈልግሻለሁ፡፡ ©ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም @eliyasshitahun
Show all...
👏 13👍 4 4❤‍🔥 3
በጉም የታፈነ ሰማይ ስር ደመናዉ ጎልቶ ከደመናዉ በታች ንስር አይኑን ያጣ ወጣት የማያያዉ ታምር ይከወናል ሁሌ በዚች ምድር በታመመ ፊደል ህመሙን ሊደብቅ እንደሚተጋ ፀሃፊ ሌት ከቀን እንደሚጨነቅ የማያይ ግን እዉር ነዉ አላልንም በአሳማሚ ፊደል ልቡን አልሰበርንም ይልቅስ ቅስም በሚሰብር      ቅጥ ባጣ አንደበት እዉር ነዉ የሚል ቃል      እኛ የጣልንበት ብኩን ምድርን ላያይ እግዜር የመረጠዉ የአይኑን ብረሃን ያጣ ማየት የተሳነዉ እኔ ግን... በልብ ፊደል ቋንቋ ለመግባባት ማየት የተሳነዉን መርጣለዉ ያን ወጣት ገላዬን በሸፈነዉ ጨርቅ ላልመሰለኝ መልኬን ገጼን አይቶ የማይሸሸኝ ልቡን ብቻ ከፍቶ የዉስጤን ሚረዳ የሰማዩን መጥቆር የኑሮን ቀዳዳ ባያይም ተረድቶ ጥላ የሚፈልግ ራሱን የሚመስል ሁሌ የሚል ፈገግ እሱን እመርጣለዉ ወዳጄ ላደርገዉ አዎ ያንን ወጣት ማየት የተሳነዉ። ✍️ዳዊት 📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌 @eliyasshitahun @eliyasshitahun @betagitim
Show all...
👍 15 1
መቼ ትመጫለሽ?? በዔደን ታደሰ እና ኤልሻዳይ(ኤል ቶ) ተፅፎ እንደቀረበ✍🎤 @ediwub & @elshaday_23 @topazionnn @topazionnn
Show all...
መቼ ትመጫለሽ .mp33.46 MB
7👍 3❤‍🔥 1

👍 14👏 9 1😭 1