cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መዝሙር ከነ ግጥሙ

የብዙ ክርስቲያኖች ችግር መዝሙር ማግኘት ሳይሆን የመዝሙሩን ግጥም ጠንቅቆ ማወቁ ነው። ይህ ቻናል አዳዲስ እና ቆየት ያሉ መዝሙሮችን ከነ ሙሉ ግጥማቸው ያደርሳቹሃል። ከእኛ ጋር ይሁኑ ለ ወዳጆም ዝማሬዎቹን ይጋብዙ subscribe On Youtube👇👇 https://www.youtube.com/@AGAPE178 ተባረኩ https://t.me/mezemur_lyrics

Show more
Advertising posts
11 862
Subscribers
+5924 hours
+2717 days
+1 33130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ዘማሪ :- ቤተልሔም ወልዴ "ባለውለታዬ " አዝ:- ባለውለታዬ ጌታዬ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ መድህኔ ቅዱስ ስምህን እባርካለሁ ውለታህን አስታውሰዋለሁ (2x) ለኔ ነው መንከራተትህ መስቀል ተሸክመህ መውረድህ ለኔ የደም ላብ ያላበህ ፍቅር ነው እንዲህ ያስጨነቀህ ውለታህን አስታውሳለሁ ፈቅጄም አመልክሃለሁ ውለታህን አስታውሳለሁ ወድጄም አመልክሃለሁ አዝ:- ባለውለታዬ ጌታዬ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ መድህኔ ቅዱስ ስምህን እባርካለሁ ውለታህን አስታውሰዋለሁ ከአብ ዘንድ ለኔ የተሰጠ ትልቁ ስጦታዬ አንተ ነህ ይህ ሚስጥር ለኔ ተገልጾ መዳን ከአንተ ዘንድ ሆኖልኛል ውለታህን አስታውሳለሁ ፈቅጄም አመልክሃለሁ ውለታህን አስታውሳለሁ ወድጄም አመልክሃለሁ አዝ:- ባለውለታዬ ጌታዬ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ መድህኔ ቅዱስ ስምህን እባርካለሁ ውለታህን አስታውሰዋለሁ (2x) ልከፍለው አልችልም ውለታህን ያኔ ያረከውን በጐልጐታ ምስጋናን ሙገሳን ይዤ ላክብርህ ኢየሱስ ወዳጄ ውለታህን አስታውሳለሁ ፈቅጄም አመልክሃለሁ ውለታህን አስታውሳለሁ ወድጄም አመልክሃለሁ አዝ:- ባለውለታዬ ጌታዬ የእግዚአብ ሔር ልጅ ኢየሱስ መድህኔ ቅዱስ ስምህን እባርካለሁ ውለታህን አስታውሰዋለሁ (2x) share♻️share♻️share♻️
🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ
   🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Show all...
8❤‍🔥 2👍 1😍 1
"ደሙ በመቃኔ" ዘማሪት ምህረት ኢተፋ በአንተ ፡ ነው ፡ ሕይወቴ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ ክብሬ (፯x) ሞገሴ ደሙ ፡ በመቃኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ ደሙ ፡ በጉበኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ ሞት ፡ አለፈ ፡ ሄደ ፡ እራቀ ፡ ከእኔ ፡ ጋር የጌታዬን ፡ ደም ፡ አይቶ የኢየሱሴን ፡ ደም ፡ አይቶ (፪x) ሞት ፡ አለፈ ፣ ሞት ፡ አለፈ ሄደ ፡ ከእኔ ፡ ርቆ የሞት ፡ መልአክት ፡ አያስፈራኝ ተሸፍኛለሁ ፡ አያገኘኝ (፪x) ዙሪያዬ ፡ ከደሙ ፡ ታጥሯል ያን ፡ ቅጥር ፡ አልፎ ፡ እንዴት ፡ ይገባል (፪x) ለጠላቴ ፡ የሃዘን ፡ ለእኔ ፡ የደስታ ፡ ቀን ፡ ነው ሞት ፡ እየገባ ፡ ያለው ፡ በጠላቴ ፡ መንደር ፡ ነው ይዙር ፡ እንጂ ፡ ዙሪያዬን ፡ እንደሚያገሳ ፡ አንበሳ ፍፁም ፡ አይቀናም ፡ አይችልም ፡ ከደሙ ፡ የተነሳ (፪x) ደሙ ፡ በመቃኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ ደሙ ፡ በጉበኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ ሞት ፡ አለፈ ፡ ሄደ ፡ እራቀ ፡ ከእኔ ፡ ጋር የጌታዬን ፡ ደም ፡ አይቶ የኢየሱሴን ፡ ደም ፡ አይቶ (፪x) ሞት ፡ አለፈ ፣ ሞት ፡ አለፈ ሄደ ፡ ከእኔ ፡ ርቆ በአንተ ፡ ነው ፡ ሕይወቴ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ ክብሬ (፯x) ሞገሴ share♻️share♻️share♻️    ✝️መልካም የፋሲካ በዓል✝️      ➖➖➖➖➖➖➖
🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ
    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics      ❖ ───✝️─── ❖
Show all...
9👍 2🙏 2❤‍🔥 1🥰 1🤩 1
``ተነስቷል''     °°°°°° ዘማሪዎች በአዲስ ኪዳን ካህናት                 ቤተክርስቲያን ኳየር °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ሰማያዊ ደስታ የትንሣኤው ክብር አምላክ ለሰው ልጆች ሰው ሆነ በፍቅር /2×/ ጌታ እየሱስ ሞቶ መቀበሩ በሦስተኛውም ቀን ተነስቶ መክበሩ የማይሻረው ቃል የወንጌሉ እውነት ህያው ተስፋ ሆኗል ለሚታመኑበት /2×/ ተነስቷል ሞትን አሸንፏል በረከትን ሊቀበል ይገባዋል መንግስትና ካህን ላደረገን የድል ዜማ እንዘምራለን /2×/ የምህረት ዘመን ተስፋ የሞላበት ጌታ እየሱስ ነው ትንሳኤና ሕይወት ሞትን ላሸነፈው ክብርና ምስጋና ለነገስታት ንጉሥ ይገባዋልና /2×/ ተነስቷል ሞትን አሸንፏል በረከትን ሊቀበል ይገባዋል መንግስትና ካህን ላደረገን የድል ዜማ እንዘምራለን /2×/ ፅድቃችን እየሱስ ሕይወት የሆንከን ሞትን አሸንፈህ ከሞት ያዳንከን አሮጌው ተሻረ አዲስ ተተክቶ ብርሀን በራልን ጨለማው አብቅቶ ለትንሳኤው ጌታ ተነሱ እንዘምር ክብር ይገባዋል በሰማይ በምድር /2×/ ተነስቷል ሞትን አሸንፏል በረከትን ሊቀበል ይገባዋል መንግስትና ካህን ላደረገን የድል ዜማ እንዘምራለን /2×/ የዛሬው ቀኑ ደስ ይላል ልናመሰግን መተናል ከጥላት እጅ ያዳነን (ቸሩ ጌታችን ይመስገን (3×) (ደጉ ጌታችን ይመስገን (2×) /2×/ share♻️share♻️share♻️ ✝️መልካም የፋሲካ በዓል✝️      ➖➖➖➖➖➖➖
🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ
   🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Show all...
15👍 12❤‍🔥 2🥰 2🤩 1🙏 1😍 1
"በፀጋ" ኢሎራ መዘምራን ያደረኩት የለም ስለመዳኔ(x2) የከፈልኩት የለም ስለመዳነ(x2) እንዲው በነፃ የዳንኩት እንዲው በነፃ እንዲው በነፃ ነው እንዲው በነፃ እንዲው በፀጋ የዳንኩት እንዲው በፀጋ እንዲው በፀጋ ነው እንዲው በፀጋ ጌታ እየሱስ ነው ለኔ የሞተልኝ ከሃጥያት እርግማን ነፃ ያወጣን እራሱን ስለኔ በርግጥ ሰውቶታል ነፍሴን ሊያድናት ደም ከፍሎላታል ወዶኝ ስላዳነኝ የለብኝ ኩነኔ እዳዬ ተከፍሎልኛል ነፃ ነኝ እኔ ስራዬ መስቀል ላይ ሰርቶ ጨርሶታል በሞቱ ሂወቴ በሞቱ ዋጅቷቷል ያደረኩት የለም ስለመዳኔ(x2) የከፈልኩት የለም ስለመዳነ(x2) እንዲው በነፃ የዳንኩት እንዲው በነፃ እንዲው በነፃ ነው እንዲው በነፃ እንዲው በፀጋ የዳንኩት እንዲው በፀጋ እንዲው በፀጋ ነው እንዲው በፀጋ ግራ አልተጋባሁም አልተቅበዘበዝኩም ድነትን ፍለጋ እየዞርኩ ወጥቼ አሎረድኩም በማምኔ ብቻ በልጁ በእየሱስ እኔን አድርጎኛል በአብ ቀኝ ከርሱ ጋር እንድወርስ ቤቴን በሰማይ እርሱ ሰርቶልኛል መኖሪያዬን በላይ አዘጋጅቶልኛል አርፊያለው በርሱ በነፍስ በስጋዬ የዘላለም ሂወት ሰቶኝ እየሱስ ጌታዬ እንዲው በነፃ እንዲው በነፃ እንዲው በነፃ እንዲው በነፃ(x2) እንዲው በፀጋ እንዲው በፀጋ እንዲው በፀጋ እንዲው በፀጋ(x2) share♻️share♻️share♻️    ✝️መልካም የፋሲካ በዓል✝️      ➖➖➖➖➖➖➖
🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ
    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics      ❖ ───✝️─── ❖
Show all...
❤‍🔥 9🥰 7👍 5 5😍 3🤩 1
ደሙ ዘማሪት ሰላም ደስታ ደሙ ደሙ ደሙ ደሙ ደሙ ደሙ /2×/ የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያነፃል የልጁ የኢየሱስ ደም ከበደል ሁሉ ያፀድቃል /2×/ አሜን ያነጻል ያፀድቃል በመመላለሻ ባደባባይ እርቃኑን ተሰቅሎ ለሰው ልጅ ሲታይ በግፍ እየተገፋ ተራራን ነጎደ በቀራኒዮ ስፍራ በመስቀል ሞተ አይተው እንዳይወዱት ደም ግባት የለውም እጅግ የተጠላ ቁስለኛ ነዉ ታዲያ ይሄማ እንዴት መድኃኒት ይሆናል ያለ ሁሉ ይስማ ደሙ ያነፃል የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያነፃል የልጁ የኢየሱስ ደም ከበደል ሁሉ ያፀድቃል /2×/ አሜን ያነጻል ያፀድቃል እንደ አሮን ልጆች ክህነት እንደ ሌዊ ዘር ስርዓት (አይደለም የውዴ)/ 2×/ የኮርማና የዋኖስን ደም መች ይዞ ገባ እኔን ለማፅደቅ /2×/ ስጋውን አንዴ አቅርቦ ዘላለም ያማረ ደሙ የፈሰሰና ኃጥያቴ ተሻረ በቀራንዮ ሞቱ ዳግም ወለደና አብን አባ አልኩት ልጅነሽ ተባልኩና /2×/ የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያነፃል የልጁ የኢየሱስ ደም ከበደል ሁሉ ያፀድቃል /2×/ አሜን ያነጻል ያፀድቃል share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Show all...
24🙏 5👍 4❤‍🔥 2🥰 1😍 1
"አንበሳ ነው " ዘማሪ ተከስተ ጌትነት አዝ : - አንበሳ ነው የ ይሁዳ አንበሳ የሞትን ጣር አጥፍቶ ተነሳ መቃብሩን የፈነቃቀ ለው ይሄ ጌታ የጌቶች ጌታ ነው x2 ለብዙዎች መቃብር ይሰራል በጌጥ ይታደሳል ጀግና የተባለው ሺ ገዳይ ስንት ሰው ተረስቷል ሞትን ድል አድርጎ የወጣ መቃብር ፈንቅሎ አሸንፎ ወደ አባቱ ሄደ በሞት ላይ አይሎ አዝ :- አንበሳ ነው የ ይሁዳ አንበሳ የሞትን ጣር አጥፍቶ ተነሳ መቃብሩን የፈነቃቀ ለው ይሄ ጌታ የጌቶች ጌታ ነው x2 ያ እየሱስ ገና በህይወት በኛ ዘንድ እያለ በ ሶስተኛው ቀን ከሙታን እነሳለው እነሳለው እንዳለ ከፊተኛው ስተት ኅለኛው እንዳይብስ እያሉ በዘብ እንዲጠበቅ መቃብሩ ብለው ተማማሉ ግን አልቻለም መቃብር ሊይዘው እንደስጋታቸው ጀግና ነው እየሱስ ተነሳ በርግጥም ታማኝ ነው አዝ :- አንበሳ ነው የ ይሁዳ አንበሳ የሞትን ጣር አጥፍቶ ተነሳ መቃብሩን የፈነቃቀ ለው ይሄ ጌታ የጌቶች ጌታ ነው x2 የሚያለቀሱ ዳግም ላያለቅሱ በጠላት ሊስቁ የተራቡም እንጀራን ሊጠግቡ በ ሞት ሊሳለቁ ያስለቀሳቸውን ማህተም እየሱስ ፈታታው ጀግና የተባለው ስመ ጥር እንዲ ነው አንበሳው አዝ :- አንበሳ ነው የ ይሁዳ አንበሳ የሞትን ጣር አጥፍቶ ተነሳ መቃብሩን የፈነቃቀለው ይሄ ነው ይሄ ነው     x2 share♻️share♻️share♻️    ✝️መልካም የፋሲካ በዓል✝️      ➖➖➖➖➖➖➖ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ     🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics      ❖ ───✝️─── ❖
Show all...
15❤‍🔥 2🙏 2👍 1🥰 1🤩 1😍 1
ታግሶታል ዘማሪት ቤተልሔም ተዘራ ተጨነቀ ተሰቃየ አፉን አልከፈተም ዝም አለ ታረደ እንደ በግ የኔን ነብስ ሊታደግ የኔን ነብስ ሊታደግ /2×/ ሁሌ አስባለው ፍቅሩን/2×/ የእየሱሴን የእውነተኛውን /2×/ የህማም ሰው ሆነ በደዌ ተመታ ፍቅር ነው እንደ በግ ተነድቶ እንዳልሆነ ጌታ ለኔ ነው እሾሁን ጅራፉን ዘለፉውን ቻለ ፍቅር ነው መስቀል ተሸክሞ ደፋቀና እያለ ለኔ ነው የእግዚአብሔር ፈቃድ በእጁ ሊከውን ከነፍሱ ድካም ሊያይ ብርሀን ታግሶታል አቤት ኢየሱሴ በፀሎት በእንባዬ ታክብረው ነፍሴ ጌታ እስከ ሞቱ ሰው ወደደ ጌታ እስከ መስቀል ሞቱ ሰው ወደደ ይቅር በላቸው ብሎ እየማለደ /2×/ ኤሎሄ ኤሎሄ እያለ ተጣራ ፍቅር ነው እንደማይችል ራሱን ባዶ አደረገና ለኔ ነው እንደወንጀለኛ እየተዘለፈ ፍቅር ነው ስለ ሀጥያተኞች ነፍሱን አሳለፈ ለኔ ነው የእግዚአብሔር ፈቃድ በእጁ ሊከውን ከነፍሱ ድካም ሊያይ ብርሀን ታግሶታል አቤት ኢየሱሴ በፀሎት በእንባዬ ታክብረው ነፍሴ share♻️share♻️share♻️
🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ
   🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Show all...
❤‍🔥 15👍 3🥰 2😍 2👏 1🙏 1
ኮብልላ ነበረች ነፍሴ ከእግዚአብሔር መንገድ በጣም የበደልኩኝ ኀጢአተኛም ነበርኩ ግን አዳኜ ከላይ ፍቅሩን ሰጠኝ ሰላም ልጁን ለእኔ ልኮ አወጣኝ ደሙን ለእኔ አፍሶ አዳነኝ /2x/ የማልረባም ብሆን አምላኬን የማላውቅ ልጁ ለእኔ ወርዶ አወጣኝ ተስፋ ቢስ ነበርኩኝ ሊያወጣኝ ሲመጣ ግን እርሱ ነገረኝ ነጻ እንደምወጣ ከዚያማ አነሳና ክብሩን አቀናጀኝ ልጁን ለእኔ ልኮ አወጣኝ ደሙን ለእኔ አፍሶ አዳነኝ /2x/ የማልረባም ብሆን አምላኬን የማላውቅ ልጁ ለእኔ ወርዶ አወጣኝ ልቤን ደስ ይለዋል ከመረጥኩት ወዲህ ከማዕበሉ አሁን ወዴርሱ ሸሻለሁ ክንዱን ከተደገፍኩ አልፈራም መከራን ልጁን ለእኔ ልኮ አወጣኝ ደሙን ለእኔ አፍሶ አዳነኝ /2x/ የማልረባም ብሆን አምላኬን የማላውቅ ልጁ ለእኔ ወርዶ አወጣኝ ሰማያዊ ደስታን ሰላምን ከሰጠኝ ጌታ ሆይ ሕይወቴን ለአንተ ሰጣለሁኝ እንግዲህ እጄን እየያዝክ ከአንተም ጋር አቁመኝ ልጁን ለእኔ ልኮ አወጣኝ ደሙን ለእኔ አፍሶ አዳነኝ /2x/ የማልረባም ብሆን አምላኬን የማላውቅ ልጁ ለእኔ ወርዶ አወጣኝ share♻️share♻️share♻️
🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ
   🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Show all...
11👍 5❤‍🔥 3👏 2🙏 2😍 1
" ተነስቷል" የመሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ መዘምራን ህብረት ተነስቷል ተነስቷል የመቃብር ደጃፍ ተከፍቷል ድንጋዩም በሩቅ ተንከባሏል ከፈኑ ብቻ ነው አስከሬኑ የታል በእውነትም የሱስ ድል ነስቷል 1. የሱስ ማሸነፉን ይስማ የሩሳሌም ይውጣ ምስራቹ ከዓለም እስከ ዓለም ይስማ እንጂ ጠላትም መርዶውን አልቅሶ ጌታ እንደው ተነስቷል ላይሞት ተመልሶ 2. ይወቀር ድንጋዩ ጠባቂውም ይምጣ የሱስን ካቃተው ጌታ መውጫ ካጣ የትኛው ጠባቂ ነው የከለከለው ጌታ መቃብሩን ሲፈነቃቅለው 3. ይነገር ለዓለም ምስራች ይሰማ ሞትን አሸንፏል ጀግናው የሱስማ ይህ ሃሰት አይደለም ዘላለም እውነት ነው ይታይ የጌታችን መቃብር ባዶ ነው 4. ይኼ ነው እንግዲህ የጎልጎታው ሚስጢር ወንጌላችን የሱስ ከሙታንም በኩር ሙትን አናመልክም መቃብር የዋጠው ያሸነፈን እንጂ ሞትን ድል የነሳው share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Show all...
❤‍🔥 13👍 8🥰 4 3🤩 2👏 1🙏 1
ቤዛዬ ዘማሪ መስከረም ጌቱ ይህ ነው ቤዛዬ ይህ ነው /2×/ በሰራነው ኃጢአት የተገባን ነን እንድንሞት ክርስቶስ ነብሱን ከፈለ በመስቀል ስለኛ ዋለ ከክብሩ አነሰ ስለኛ ስጋለበሰ መስዋዕት ሆነ በእኛ ፋንታ ተኮነነ ይህ ነው ቤዛዬ ይህ ነው መብቱን ተወልን እኛን በህይወት አቆየን የፋሲካው በግ ሲታረድ የሰው ልጅ ተረፈ ከፍርድ ተገረፈልን እየሱስ ፍርዳችንን ሊደመስስ ደም እስኪያልበው ደከመ ህመማችንን ታመመ ይህ ነው ቤዛችን share♻️share♻️share♻️
🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ
   🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Show all...
10👍 2🥰 2🙏 2😍 2❤‍🔥 1🤩 1