cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ድንቃ ድንቅ ኢስላማዊ ወጎች👌👌

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች በዚህ ቻናል ድንቅ ኢስላማዊ ወጎችን እንዲሁም ለናንተ ይጠቅማሉ ያልናቸውን ኢስላማዊ ታሪኮች እናቀርብላችኋለን

Show more
Advertising posts
198
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-630 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
✅ ደስተኛ መሆን ከፈለግክ ለሌሎች ደስታ ምክንያት ሁን። ✅ ጥሩ ሰው ማገኘት ከፈለግክ አንተ ለሌሎች ጥሩ ሁን። ✅ ትልቅ ሰው መሆን ከፈለክ ትህትናን የራስህ አድርግ። መልካም ቀን
90Loading...
02
ቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ 7 ከንቱ ምኞቶች‼ ============================= ①) «ዋ ምኞቴ! ምነው አፈር በሆንኩ!» [አ-ን'ነበእ: 40] ②) «ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ!» [አል-ፈጅር: 24] ③) «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ!» [አል-ሐቀህ: 25] ④) «ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ!» [አል-ፉርቃን: 28] ⑤) «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን፤ መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ!» [አል-አሕዛብ: 66] ⑥) «ዋ ምኞቴ! ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ!» [አል-ፉርቃን: 27] ⑦) «ወይ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ!» [አ-ን'ኒሳእ: 73] ሁሉም የሟቾች ምኞቶ ናቸው። ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ምኞታቸው ወደ ዱንያ አንዴ መጥተው ለአኺራቸው ጥሩን ነገር መስራት ነው። ግን ምን ዋጋ አለው! አልፏል ተቀድሟል! ቀብር ገብተህ አንተም ይህን ከምትመኝ ነፍስህ አካልህ ውስጥ እስካለች ድረስ ለአኺራህ አስቀድም። ብልህ የሆነ ሰው ከመጸጸቱ በፊት ሥራውን ይሥራ አላህ ሆይ! ከነዚህ ከንቱ ምኞቶች በእዝነትህ ጠብቀን።
190Loading...
03
የፈጅር (የሱብሕ) ሶላት ትሩፋቶች እና ፈጅርን አለመስገድ ያለው አደጋ ~ ~ ~~ ~ ~ 1. ፈጅርን ስገድና በአላህ ጥበቃ ስር ሁን፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ሱብሕን የሰገደ በአላህ ጥበቃ ስር ነው” ብለዋል፡፡ [ሙስሊም] 2. ፈጅርን ስገድ ሌሊቱን በሶላት እንደቆምክ ይቆጠርልሃልና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ዒሻእን በጀማዐህ የሰገደ ግማሽ ሌሊትን በሶላት እንደቆመ ነው፡፡ ሱብሕን በጀማዐህ የሰገደ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ እንደቆመ ነው”  ይላሉ፡፡ [ሙስሊም] 3. ሱብሕን ስገድ እራስህን ከሙናፊቆች መገለጫ አፅዳ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በሙናፊቆች ላይ እንደፈጀር እና ዒሻእ ሶላት የሚከብድ የለም” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 4. ፈጅርን ስገድ ለጭንቅ ቀን ብርሃን ይሆንሃልና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በጨለማዎች ወደ መስጂዶች የሚጓዙትን በቂያማህ ቀን ሙሉ በሆነ ብርሃን አብስራቸው”  ይላሉ፡፡ [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 570] 5. ሱብሕን ስገድ መላእክት ይመሰክሩልሃል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “በናንተ ውስጥ የሌሊት መላእክትና የቀን መላእክት ይተካካሉ፡፡ በፈጅር ሶላት እና በዐስር ሶላት ላይ ይሰባሰባሉ፡፡ ከዚያም እነዚያ በናንተ ዘንድ ያደሩት (ወደ ሰማይ) ይወጣሉ፡፡ ይህኔም ጌታቸው በነሱ ሁኔታ አዋቂ ሆኖ ሳለ “ባሪያዎቼን በምን ሁኔታ ላይ ተዋቸኋቸው?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ “እነሱ እየሰገዱ ነው የተውናቸው፡፡ እየሰገዱም ነው የመጣናቸው” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 6. ሱብሕን ስገድ ሙሉ የሐጅና የዑምራን አጅር እፈስ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የማለዳን ሶላት በጀማዐ የሰገደ ከዚያም ፀሀይ እስከሚወጣ ድረስ አላህን እያወሳ የተቀመጠ እና ከዚያም ሁለት ረከዐ ሶላት የሰገደ ልክ እንደ ሐጅና ዑምራ አጅር አለው፡፡ ሙሉ! ሙሉ ! ሙሉ!”  ይላሉ፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 3403] 7. ፈጅርን ስገድ በአለም ላይ ካሉ ፀጋዎች ሁሉ በላጭ የሆነ ፀጋ የምትጎናፀፍበት እድል ታገኛለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የፈጅር ሱንናህ (ከፈርዱ በፊት የምትሰገደዋ ትርፍ 2 ረከዐ ሶላት) ከዱንያ እና በውስጧ ካለ ሁሉ በላጭ ነች” ይላሉ፡፡ [ሙስሊም] 8. ፈጅርን ስገድ ከጀሀነም መትረፊያ ጀነትን መጎናፀፊያ ብስራትን ታገኛለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም  “ፀሀይ ከመውጣቷ እና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም” ይላሉ፡፡[ሙስሊም] እነዚህ ሶላቶች ፈጅርና ዐስር ናቸው፡፡ በሌላም ሐዲሥ “ሁለት ብርዳማ ሶላቶችን የሰገደ ጀነትን ይገባል” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 9. ፈጅርን ስገድ ከፀጋዎች ሁሉ በላጭ ፀጋ የሆነውን የላቀውን ጌታ መመልከትን ትታደላለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “እናንተ ይህን ጨረቃ እንደምታዩት ጌታችሁን ታያላችሁ፡ እሱን በማየትም አትቸጋገሩም፡፡ ፀሀይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት ባለ ሶላት አለመረታት ከቻላችሁ አድርጉት (ስገዱ)”  ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 10. ፈጅርን ስገድ ጥሩ ነፍስ ይዘህ አንግተህ ንቁ ሆነህ ትውላለህ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] ተጠንቀቅ! 1. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ከፈጅር ሶላት መሳነፍ አደገኛ የሆነ የሙናፊቆች ምልክት ነውና!! [ቡኻሪና ሙስሊም] 2. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ የሸይጣን መፀዳጃ አትሁን፡፡ በአንድ ወቅት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ እስከሚነጋ ድረስ ሌሊቱን ስለሚተኛ ሰው ተወራ፡፡ ይህኔ እሳቸው እንዲህ አሉ፡- “ያ በጆሮዎቹ ውስጥ ሸይጣን ሽንቱን የሸናበት ሰው ነው!” አሉ፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 644] 3. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ያለበለዚያ የሸይጣን ወጥመድ ሲሳይ ትሆናለህ፡፡ ቀንህን ሙሉ ድብርት ይጫጫንሃል፣ ንቃት ይቀልሃል፡፡ ፈጅር ላይ ተነስቶ ውዱእ አድርጎ ያልሰገደ ሰው ቆሻሻ ነፍስ ይዞ እንደሚያነጋና ስንፍና እንደሚጫጫነው ተናግረዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 4. ፈጅርን ስገድ ያለበለዚያ በቀብርህ ውስጥ እስከ እለተ ቂያማ የሚዘልቅ ዘግናኝ ስቃይ ትሰቃያላህ፡፡ ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተላለፈው አንድ ሰው ተንጋሎ ሌላው ካጠገቡ ቋጥኝ ይዞ በመቆም እራሱን ይደቁሰዋል፡፡ ድንጋዩ ተንከባሎ ሲሄድም እሱን አምጥቶ እስከሚመለስ ድረስ እራሱ እንደነበር ይመለሳል፡፡ ከዚያም እንደ መጀመሪያው ይሰራበታል፡፡ ቂያማ እስከሚቆም ድረስም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል፡፡ ይህን በዚህ መልኩ የሚሰቃየውን ሰውየ ምንነት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጂብሪል ሲጠይቁት “ይሄ ቁርኣንን ይዞ ፊት የሚነሳው ከግዴታ ሶላትም የሚተኛ ነው” አላቸው፡፡ ወንድሜ ሆይ! ከፈጅር ሶላት አትዘናጋ፡፡ ወቅቱን ጠብቀህ እንድትሰግድ የሚያግዝህን ብልሃትም ተጠቀም፡፡ 1. በጊዜ ተኛ፡፡ የምሽት ወሬ ይቅር፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዒሻ በፊት እንቅልፍ፣ (ከዒሻ) በኋላ ደግሞ ወሬ ይጠሉ ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 2. ቀኑን በወንጀል ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ወንጀል ከኸይር ስራ ያቅባል፡፡ በሌላ በኩል ለኸይር ስራ ትጋ፡፡ ኢስላማዊ የመኝታ ስርኣቱን ጠብቅ፡፡ የኸይር ስራ አንድ ሽልማቱ ለሌላ ኸይር ስራ መታደል ነውና፡፡ 3. ማታ ከመተኛትህ በፊት ለፈጅር ለመነሳት ቁርጠኛ ውሳኔ አድርግ፡፡ ረጅም ጉዞ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ ቢኖርብህ ያለ ማንም አጋዥ ምናልባትም ያለአላርም እየነቃህ ለሶላት ሲሆን መዘናጋትህ ስለእውነት ከባድ የሞራል ልሽቀት ነው፡፡ 4. ማንቂያ ደወል (አላርም) ተጠቀም፡፡ ምናልባት ሳይታወቅህ አጥፍቶ የመተኛት አጉል ባህሪ ካለብህ ትንሽ ራቅ አድርገህ አስቀምጠው፡፡ 5. በሰአቱ ነቅተህ ከተጫጫነህ “ትንሽ ተኛ” ለሚሉ ሸይጣን እና ነፍስያ ሸንጋይ ጉትጎታ እድል አትስጥ፡፡ መነሳትህ ያለውን ዋጋ፣ መተኛትህ ያለውን አደጋ ላፍታ አስብ፡፡ ብትነሳ 50 ዶላር ይሰጣል ቢባል የሚኖርህን ንቃት ቃኝና እራስህን ታዘብ፡፡ ፈርዱ ቀርቶ ትርፍ የሆነችዋ የፈጅር 2 ረከዐ እንኳን ከዱንያ ፀጋ ሁሉ በላጭ እንደሆነች እራስህን አስታውስ፡፡ 6. በመልካም የሚያግዝ ጓደኛ ወይም የህይወት አጋር ካለህም እሰየው፣ ተጠቀምበት፡፡ @yasin_nuru @yasin_nuru
170Loading...
04
የአላህን እዝነት ተመልከቱ!! 🍂ከቁርኣን አንድ ሀርፍ የቀራ ሰው 10 አጅር ያገኛል። «አሊፍ፣ ላም፣ ሚም» ያለ ሰው 30 አጅር ያገኛል። 🍂«ቁል ሁወ‘ላሁ አሀድ»ን የቀራ ሰው የቁራኣንን 1/3 እንደቀራ ይፃፍለታል። 🍂ሰላሳ አያዎችን ያላትን «ሱረቱል ሙልክ»ን የቀራ ሰው… ታማልድለታለች፣ ወንጀሉም ይማራል። 🍃አላህን ሚያስታውስ ሰው አላህ ያስታውሰዋል። 🍃በአላህ መንገድ ከመግደልና ከመገደል በላይ ዚክር ማድረግ በላጭ ነው። 🌴ሱብሀነላህ፣ አልሀምዱሊላህ፣ ክኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር… ፀሀይ ከወጣባቸው ቦታዎች ባጠቃላይ በላጭ ናቸው። የጀነት ተክሎችም ናቸው። 🍃100 ጊዜ ሱብሀነላሂ ወቢሀምዲሂ ያለ ሰው… ወንጀሉ የበህር አረፋ ቢያህል እንኳን ይማርለታል። 🍃100 ጊዜ ‘ላ ኢላሀ ኢለላህ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሀምዱ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይዒን ቀዲር’ ያለ ሰው… 10 ባሪያ ነፃ እንዳወጣ ይያዝለታል። 100 ወንጀል ይማርለታል፣ 100 ምንዳ ያገኛል፣ ከሸይጣን ይጠበቃል፣ ማንም የሱን ያህል ምንዳ አያገኝም እሱ ያለውን ያህል ያለ ወይም ከሱ በላይ ያለ ሰው ሲቀር። 🌴‘ላሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ’ የጀነት ተክል ነው። በነቢዩ ላይ አንዲትን ሰለዋት ያወረድ አላህ በሱ ላይ 10 ያወርዳበታል። 🌼ውዱእን አስውቦ ያደረገ ሰው ወንጀሉ ይማርለታል። ፊቱን ሲታጠብ በአይኑ ያየው ወንጀሉ ይገርፋል። እጁን ሲታጠብ በጁ የሰራው ይወጣል፣ እግሩን ሲታጠብ በእግሩ ወደ ወንጀል የሄደበት ወንጀሉ ይጠራል። (ከወንጀል ጠርቶ እስኪወጣ ድረስ።) 🌼ቤቱ ውድዕ አድርጎ ወደ መስጂድ የሚሄድ ሰው በአንድኛው እርምጃው ወንጀሉ ይታበሳል፣ በሌላኛው አጅር ይፃፍለታል። ውዱኧን፣ ኩሹኧን፣ ሩኩኣን አስተካክሎ ዋጂብ ሰላትን የሰገደ ሰው ያለፈው ወንጀሉ እንዳለ ይማርለታል። (ከባኢሮች ሲቀሩ።) 🌼ውዱእ ሳይፈታ እዛው የሰገደበት ቦታ ላይ የዘወተረ ሰው… መላኢካዎች ምህረትን ይጠይቁለታል። ‘አላህ ሆይ! ማረው፣ አላህ ሆይ! እዘንለት!’ ይላሉ። 🌼ኢሻን በጀመኣ የሰገደ ሰው ሌሉትን ግማሽ እንደቆመ ይፃፍለታል፣ ፈጅርን በጀመኣ የሰገደ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ እንደሰገደ ይፃፍለታል። በፈጅርና በኢሻ ውስጥ ያለን ምንዳ ሰዎች ቢያውቁ ኖሮ በእንብርክካቸውም ቢሆን ይመጡ ነበር። 🌼የፈጅር ሱና ከዱንያን ውስጡ ካለው ነገር ባጠቃላይ በላጭ ናት። 🌼በአላህ ላይ ምንዳውን ተሳስቦ ለይልን የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ እንዳል ይሰረያል። ⚡️ፆመኛን ያስፈጠረ ሰው… የፆሚን ምንዳ ያገኛል። @anbeb_islamic
190Loading...
05
ኢና ሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ! በማእከላዊ ጎንደር ደንቢያ ወረዳ አየንባ ቀበሌ የመስጅድ ኢማም የሆኑት ሸኽ ሲራጅ ተገደሉ! ... በማእከላዊ ጎንደር ደንቢያ ወረዳ አየንባ ቀበሌ የመስጂድ ኢማም የሆኑት ሸኽ ሲራጅ መግሪብ ሰላት ሰግደዉ ከመስጂድ ሲወጡ በታጣቂዎች ተይዘዉ ከሄዱ በሃላ በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ደብድበዉ መገደላቸውን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ገልፀዋል። ... ሸኽ ሲራጅ በዛዉ መስጅ ለረጅም አመት ደረሳዎችን እስከዛሬዋ እለት ያቀሩ የነበሩ ሲሆን መግሪብን አሰግደዉ ሲወጡ ታጣቂዎቹ እየጎተቱ የወሰዷቸዉ መሆኑና ይህን የሀገር ሽማግሌ የሁሉ አባት የሆኑት የመስጅድ ታላቁን ሸኽ ገድለዉ ጥለዋቸዉ እንደሄዱ የክልሉ መጅሊስ ዋና ፀሀፊ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል። .. ©ሀሩን ሚዲያ
230Loading...
06
አስኳላቸው 🏵 💡:ኢስላም ዐቂዳ ነው ፤ #አስኳሉ ተውሒድ ነው። 💡:ዒባዳ ነው ፤ #አስኳሉ ኢኽላስ ነው። 💡:መኗኗር ነው ፤ #አስኳሉ እውነተኝነት ነው። 💡:ስነ - ምግባር ነው ፤ #አስኳሉ እዝነት ነው። 💡:ህግ ነው ፤ #አስኳሉ ፍትህ ነው። 💡:ሥራ ነው ፤ #አስኳሉ ጥራት ነው። 💡:አደብ ነው ፤ #አስኳሉ ትህትና ነው። 💡:መስተጋብር ነው ፤ #አስኳሉ ወንድማማችነት ነው። 💡:ሥልጣኔ ነው ፤ #አስኳሉ ሚዛናዊነት ነው። ┊  ┊  ┊  ┊ ┊  ┊  ┊  ✿ ┊  ┊  ❀ 📗 ┊  ✿ 🔗 ❀ Muslimchannel2.t.me
230Loading...
07
ይህንን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ‼ ================== ✍ ይህንን ባለ 15 ገፅ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለትን አዲሱን ረቂቅ አዋጅ ሶፍት ኮፒ በስልካችሁ ላይ ላለ ሰው ሁሉ፣ በምታገኙት ግሩፕና ቻነል እንዲሁም በማንኛውም ገፅ ላይ በማሰራጨት መረጃው በእያንዳንዱ ሙስሊም እጅ ላይ ደርሶ እንዲያነበው እናድርግ። ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት ማንበብ ለሚፈልግም ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35708 * ሰው ጽሑፉን ዝም ብሎ ቢያነበውም ከላይ ሲመለከታቸው አንቀፆቹ ጤነኛ ሊመስሉት ስለሚችሉ፤ ፍንጭ ይሰጠው ዘንድ ረቂቅ አዋጁ ከኛ ከሙስሊሞች ጋር የሚያጋጩትንና ጥያቄ የሚያጭሩ 15+ ነጥቦች የተጠቀሱበትን ይህንን ጽሑፍም ጨምሩለት። https://t.me/MuradTadesse/35742 ይህንን የአዲሱን ረቂቅ አዋጅ PDF ለሁሉም በማሰራጨት መረጃው እንዲደርሰው እናድርግ። የላ ቻሌንጃችን ይጀመር! አብዛሃኛው ሰው ከጀርባ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረጃው የለውም። ጭራሽ አዲስ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ራሱ እንኳን ከመረጃው የራቀው ማኅበረሰብ ሚዲያ ላይ አለን የሚለው ራሱ በበቂ ሁኔታ የሰማ አይመስለኝም። ወሬውን ቢሰማም ዶክመንቱ በተጨባጭ ያልደረሰው ብዙ ነውና ይህንን በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር። የፌዴራሉ መጅሊስም በዚህ ጉዳይ ተቃውሞ ያወጣውን ባለ 4 ገፅ መግለጫ አያይዘን እናሰራጨው። መግለጫው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35632?single ከተቋማችንም ጎን እንቁም። የላ! ከአሁኑ ይጀመርና ያሰራጨ ሰው ለማነቃቂያ ስክሪን ሹቱን ኮመንት ላይ አስቀምጡት!
410Loading...
08
✍️#በሕይወትህ_ዘመን_ይህን_አስብ!" #ደስታና_መከራ ባገኘህ ጊዜ ሁለቱም በመጠንና በእርጋታ ተቀበላቸው እንጂ በደስታ ጊዜ ፈንጠዝያ በመከራ ጊዜ ደግሞ መጨነቅ አታብዛ። #ደስተኛ_ሆነህ መኖር ከፈለግክ ልብህን ከጥላቻ እንዲሁም አእምሮህን ከጭንቀት ነፃ አድርግ። #ኑሮ_እንድታለቅስ_መቶ ምክንያቶችን ከሰጠችህ፤ አንተ ደግሞ ፈገግ ለማለት ሺህ ምክንያቶችን ደርድርላት። #በዚህ_ዓለም ጥድፊያና ሁካታ ሳትበገር በእርጋታ ኑር፤ ከፀጥታ ሰላምና እረፍት የሚገኝ መሆኑን አትዘንጋ። #አሁን_እያለፍክበት_ያለው_ፈተና እና የኑሮ ጦርነት እድልህን እንድታማርር እያደረገህ ይሆናል፤ ☞ነገ የሚመጣውን ግን አታውቅም፤ ☞የአንተ ችሎታና ጥበብ መሆን ያለበት ሁሉንም እንደአመጣጡ መቀበል እና ነገን ለአላህ መተዉ ነው። #ቻናላችንን_ሼር_ያድርጉ 👇👇 @Alif_islamic_posts @Alif_islamic_posts
320Loading...
09
ክብር ለሴቶች . 1⃣. ባል በሚስቱ ላይ ከወሰለተ ቅጣቱ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ መወገር ነው፡፡ 2⃣. 2ኛ ሚስት አግብቶ እኩል ካላስተዳደር የትንሳኤ ቀን ወደ ጎን ተጣሞ ይቀሰቀሳል፡፡ 3⃣.ጥሎሽ ይህን ያህል እሠጣታለሁ ብሎ ቃል ገብቶ ካልሠጠ እሱ ሌባ ነው፡፡ 4⃣. የፈታት አንደሆነ ከሠጣት ነገር ዉስጥ አንዳችም ነገር መውሰድ የለበትም፡፡ አሳፋሪ ነው አትውሰዱ ይላል ቁርኣን፡፡ 5⃣. የዉርስ መብቷን የማይሠጣት ከሆነ የአላህን ድንበር ተላለፈ፡፡ የአላህን ድንበር የሚተላለፍ ራሱን ምንኛ በደለ!፡፡ 6⃣ ሴትን ልጅ በመምታት ይሁን በሌላ ነገር ያዋረዳትና ዝቅ ያደረጋት እሱ የተዋረደ ነው፡፡ 7⃣. ከአራትወር በላይ ጥሏት የጠፋ እንደሆነ የመለያየት መብት አላት፡፡ 8⃣. እንደ እናቱ ሊያያት አይገባም፤ ጀርባውን መስጠትና ፍራሹን መለየትም የለበትም፡፡ 9⃣. ‹አልቀርብሽም አንቺ ለኔ እንደ እናቴ ነሽ› ካላት በኋላ ቃሉን ማጠፍ ከሳበ ለቅጣቱ ስልሳ ቀናትን መፆም ይኖርበታል፡፡ 🔟. የጠላት እንደሆነም ይታገስ፡፡ በጠሉት ነገር ዉስጥ ብዙ መልካም ነገር ሊኖር ይችላልና ይላል ቁርአን ፡፡ 1⃣1⃣. አንደኛውን ባህሪዋን ቢጠላ ሌላውን ይውደድላት፡፡ ሰው ሆኖ ሙሉ የለምና፡፡ 1⃣2⃣ የፈታት እንደሆነም መልካምነቷን አይርሳ፡፡ ትዝታ አያረጅም፡፡ ምንም እንኳ የሆነ ጊዜ ጥሩ ትንፋሽ ተለዋውጠዋልና፡፡ 1⃣3⃣. በፍቺ ከተለያዩ ልጆቿን አይከልክላት፡፡ ቀለባቸውንም በትክክል ይስጣት ፡፡ 1⃣4⃣. ሴት ልጅ በሀብት ንብረቷ ሙሉ ባለመብት ናት፡፡ መፀወተች፣ ነገደችበት መብቷ ነው፡፡ በሷ ገንዘብ ባሏ አያገባውም፡፡ 1⃣5⃣ ድንበር ያለፈባት ሰው በተመሳሳይ መልኩ መቀጣት ይኖርበታል፡፡ 1⃣6⃣. ባሏን የምትታዘዘው በመልካም ነገር ያዘዛት እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ፈጣሪን በማመፅ ፍጡርን መታዘዝ የለም፡፡ 1⃣7⃣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የበኑ ቀይኑቃዕ ጎሣዎች ላይ የዘመቱት በሴት ልጅ ክብር ምክንያት ነው፡፡ 1⃣8⃣. ከሷ መከላከል የመስዋእትነት ደረጃ አለው፡፡ 1⃣9⃣. ኸሊፋ አል-ሙዕተሲም ዐሙሪያ ድረስ ጦራቸውን ያዘመቱት ስለሷ መነካት እልህ ብለህ ነው፡፡ (ይህን ታሪክ ፈልጋችሁ አንብቡ፡፡) 2⃣0⃣. በዉሸት በዝሙት የወነጀላት የሰማኒያ ጅራፍ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ 2⃣1⃣. እሷን ማስተማር ግዴታ ነው፡፡ በመልካም ሁኔታ ማሳድግ የጀነት መግቢያ መንገድ ነው፡፡ 2⃣2⃣ ከእናቶች እግር ሥር አትነሱ፡፡ ጀነት በእግራቸው ሥር ነውና፡፡ 2⃣3⃣. እናት ከአባት በሦስት ደረጃዎች የበለጠች ናት፡፡ አል-ዐሪፊ እንደፃፉት… ራሳችሁ በድላችሁ፣ መብቶቻቸውን ሰርቃችሁ እስልምና ሴቶችን ይበድላል አትበሉ።💞💞💞 @yasin_nuru @yasin_nuru
362Loading...
10
ሴቶች.... ና ዕድሜ      ሰውየው አራት ሚስቶች አሉት ፤ ሚስቶቹ ቅሬታ ነበራቸውና ተመካክረው ፍርድ ቤት ከሰሱት ፤ በቀጠሮውም መሰረት ፍርድ ቤት ቀረቡ። ዳኛው ክሳቸውን ለመስማት ከአራታችሁ በእድሜ ታላቅ የሆነችዋ ቀድማ ቅሬታዋን ታሰማ አላቸው። ሆኖም ፍርድ ቤቱ በፀጥታ ተዋጠ ፤ ክሱን የሚያሰማ ጠፋ ፤ ፋይሉም ተዘጋ ።
380Loading...
11
❌Mother's Day❌      ➲ «ቀን የላትም እናት» ⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻ የእዝነት የደግነት የፍቅር ተምሳሌት፡ የማማ ውለታ መች ይረሳል ቀን ሌት፡ ምን አይነት ቅዠት ነው እንደት አይነት ስሌት፡ 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ አንድ ቀን አስቦ አመት ሙሉ መርሳት፡ ከእውነት መሸሽ ነው ሰወችን ማሳሳት፡ የአሏህን አደራ ትዕዛዙን አራክሰን፡ የእናትን ትውስታ በአንድ ቀን መወሰን፡ አጉል ፍልስፍናን ከነጮች ተውሰን፡ ይህ አይነቱ ቅዠት የት ነው የሚያደርሰን!? 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ በስልጣኔ ስም ጠልፎን መጥፎ ንዝረት፡ ጀነት በእግሮቿ ስር ለሆነላት ፍጥረት፡ ለርሷ ማስታወሻ አንድ ቀን መመስረት፡ አያዋጣም ተውት ፍፃሜው ነው ክስረት፡ 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ ሐቋን እያሟላህ ታዘዛት ይልቅስ፡ ከቀብር ስትገባ ነገ እንዳታለቅስ፡ በድሎኛል ብላ እማዬ እንዳትወቅስ፡ 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ ራስክን አዘጋጅ ለመልካም ትብብር፡ በማንኛውም ቀን እናትህን አክብር፡ ስሜት ተከትለህ ለሸይጧን አትገብር፡ 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ የደስታ የፍቅር የፅናት መልክ ናት፡ ማዕረጓን ከፍ አርጎ አሏህ ያገነናት፡ ታስቦ የሚውል ቀን የላትም እናት፡ 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ ✍️በኑረዲን አል አረቢ➊❹❹❹
511Loading...
12
Media files
480Loading...
13
ጀሀነም የሚገባው ወደ ጀሀነም ጀነት የሚገባውም ወደ ጀነት ከገባ በኋላ አንድ ተጣሪ እንዲህ ሲል ይጣራል! አንተ ሙሐመድ! ተደሰተክ ወይ? እርሳቸው እንዲህ ይለሉ«ጌታዬ! ወላሂ አልተደሰትኩም። ከኡመቶቼ እሳት ውስጥ የቀረ አለ» አላህም ለመላኢኮች «ቅንጣት ታክል ኢማን በቀልቡ ያለውን ሁሉ ከእሳት አውጡ» በማለት ያዛቸዋል። ከዚያም ጀሀነም በሯ ይከፈትና የተወሰነው የሙስሊሙ ክፍል ወጥቶ ወደ ጀነት ይተማል። አላህ በድጋሚ «ሙሐመድ ሆይ! ተደሰትክ?» ይላቸዋል። «ጌታዬ ባንተ እምላለሁ! አሁንም ከህዝቦቼ የቀሩ አሉ» ብለው ያለቅሳሉ! አላህም ለመላእክቱ «አይኑ የትንኝ ራስ የምታክል እንባም ብትሆን እኔን ፈርታ ያነባችን ሁሉ አውጡ» በማለት ያዛል። ከዚያም «ያ ሙሐመድ! አሁንስ ተደሰትክ?» ይላቸዋል። «ወላሂ አልተደሰትኩም። አሁንም ከኡመቴ የቀሩ ሰዎች አሉ። ይላሉ ረሱላችን ﷺ » አላህ ለመላኢኮች «ላኢላሀ ኢለላህ፣ ሙሐመዱን ረሱሉላህ ያለውን በጠቅላላ ከጀሀነም አውጧቸው» በማለት ያዛል። ጀሀነም በሮቿ ተከፍተው ሁሉም ወደ መስካሪዎች ጎራ ይነጉዳሉ። ከወርቅና ከሉል በተሰራ ግንብ ውስጥ ይነዳሉ። ባማረ መዓዛ ይታወዳሉ። ውስጥ የነበሩት የጀነት ሰዎች የተበለጡ እስኪመስላቸው ድረስ እነዚህ ሰዎች ውብ ይሆናሉ። ከዚያም ወደ ጀናህ እንዲገቡ ይደረጋል። ይሄኔ ለመጨረሻ ጊዜና ለዘልዓለም ጀሀነም ትዘጋለች!! በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ፦ « ﺭُّﺑَﻤَﺎ ﻳَﻮَﺩُّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ ﻟَﻮْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﻣُﺴْﻠِﻤِﻴﻦَ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡ (ሱረቱ አል-ሒጅር- 2) አላህ የርሳቸውን ሸፈዓ የምናገኝ ያድርገን!! ሰሉ ዐለል ሐቢብ!! @yasin_nuru @yasin_nuru
470Loading...
14
ዱዐችን ለምን ምላሽ አጣ ሰዎች ተሰብስበው ኢብራሂም ኢብኑ አድሀም ዘንድ መጡና <<ለምንድነው ዱዐችን ምላሽ ያጣው?>> ሲሉ ጠየቁ ኢብራሒም ሲመልሱ. .... ቀልባችሁ ውስጥ ባለው 10 በሽታዎች ምክንያት ነው አሉ።      1) በአላህ መኖር ታምናላቹ ትዕዛዙን ግን አትፈፅሙም   2) ረሱል (ሰ.0.ወ) እንወዳለን ትላላቹ ሱናቸውን ግን አትፈፅሙም   3) ቁርዐንን ታነባላችሁ ነገር ግን በተግባር ላይ ስታውሉት አትታዩም   4) የአላህን ፀጋ ትሻማላችሁ ነገር ግን ተገቢው ምስጋና አታደርሱም   5) ሸይጣን ጠላታችሁ እንደሆነ ታውቃላችሁ ነገር ግን ጠላታችሁ አድርጋችሁ አትጠነቀቁትም   6) ጀነትን ለመግባት ትመኛላችሁ ነገር ግን ለጀነት አትዘጋጁም   7) ወደ ጀሀነም መወርወር አትፈልጉም ነገር ግን ከጀሀነም ለመዳን አትጥሩም   8) ሁሉም ፍጥረት ሞትን እንደሚቀምስ ታምናላችሁ ግን ለሞት አትዘጋጁም   9) ሰውን ታማላችሁ የሰውን ነውር ትከታተላላችሁ ነገር ግን የራሳችሁን ስህተትና መጥፎ ፀባይ ትረሳላችሁ 10) ሙታንን ትቀብራላችሁ ነገር ግን ከሟች ትምህርትን አቶስዱም ። @yasin_nuru @yasin_nuru
831Loading...
15
✍አዕምሮን መጠቀም የአንደሉስ ገዢ የነበሩት ሐሪስ ኢብኑ ዐብባድ ዐዲይ ኢብኑ አቢረቢዓን ለመበቀል አሰቡ። የእሳቸውም ሆነ የጠባቂዎቻቸው ብቸኛ ችግር የነበረው አንዳቸውም ኢብኑ አቢ ረቢዓን በአካል አለማወቃቸው ነበር። ችግራቸውን የተገነዘበ አንድ እስረኛ ከጠባቂዎቹ ወደ አንዱ ቀርቦ "እኔ ዐዲይ ኢብኑ አቢ ረቢዓን ባሳያችሁ ከእስር ነፃ ልታደርጉኝ ቃል ትገባላችሁ?" አለው። ጠባቂውም " ይህን አድርግ እንጂ ከእስር እንደምንለቅህ ቃል እገባልሀለው" አለው። ከጠባቂው ቃል የተገባለት እስረኛ "ዐዲይ ኢብኑ አቢ ረቢዓ ማለት እኔ ነኝ" ሲለው ጠባቂው ቢናደድም ለእስረኛው የገባለትን ቃል ማክበር ስለነበረበት ከእስር ለቀቀው። ================== https://t.me/dnqadnqwegoch
1592Loading...
16
☞ ይህ ለኡማው መርህ ሊሆን የሚገባ  የረሱል ሰ.ዐ.ወ ታላቅ ምክር ነው። . * አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መጣና <<ለዱንያም ሆነ ለአኼራ የሚጠቅም ንግግር ለመጠየቅ ነው የመጣሁት>> አላቸው ። እሳቸውም (ሰዐወ) ደግሞ <<የመጣልህን ጠይቅ>> አሉት። . ☞ <<ከሰው ሁሉ አዋቂ ለመሆን እፈልጋለው?>> ✔ እሳቸውም "አላህን ፍራ" አሉት ☞ <<ከሰው ሁሉ ሀብታም ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው። ✔ <<ባለህ ነገር ተብቃቅተህ አላህን አመስግን" አሉት ☞ <<ትክክለኛ ፈራጅ እና ታማኝ ሰው ለመሆን እፈልጋለው?>> ሲል፣ ✔ << ለራስህ የምትወደውን ለሰዎች ውደድ>> አሉት። ☞ <<ከሰው ሁሉ ብርቱ ለመሆን እፈልጋለው?>> ሲል ✔ << በአላህ ተወከል>> አሉት ☞ << በአላህ ዘንድ ብቸኛ ተመራጭ ለመሆን እፈልጋለው? >> ፣ ሲላቸው ✔ << ዚክር አብዛ>> ፣ አሉት። ☞ << ከሰው ሁሉ በላጭ ለመሆን እና ጥሩ ሰው ለመሆን እፈልጋለው?>> ፣ ሲል ✔ << ለሰው ጠቃሚ ሁን>> ፣  አሉት። ☞ << የተከበረና ቸር ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው ደግሞ ✔ << ችግርህን ለፍጡር አትንገር>> አሉት። ☞ << ረሱል እና አላህ እንዲወዱኝ እፈልጋለው?" ባላቸውም ጊዜ ✔ << አንተም እነሱ የወደዱትን ውደድ>>፣ አሉት:: ☞ ከወንጀል የጠራው ሁኜ አላህን መገናኘት እፈልጋለው" ሲል ደግሞ፦ ✔ << ጀናባህን በደንብ ታጥበህ እስቲግፋር አብዛ ፣ ማልቀስ መተናነስ መታመም አለብህ>>፣ አሉት። ☞ << ከበጎ ሰሪወች ለመሆን እፈልጋለው?>>፣ ሲላቸውም፦ ✔ << አላህን ልክ እንደምታየው ሁነክ ተገዛው>> ÷ አሉት። ☞ << ኢማኔ እንዲሞላ እፈልጋለው>> ፣ሲል ✔ << ፀባይህን አሳምር" አሉት። ☞ << እርዝቄ እንዲሰፋ እፈልጋለው>> ፣ ሲል፦ ✔ << ተዋዱዕ አዘውትር>> ፣ አሉት። ☞ << ዱዓዬ ሙስተጃብ እንዲሆንልኝ እፈልጋለው?>> ሲላቸው፦ ✔ << ሀራም አትብላ>> አሉት:: ☞ << አላህን ከሚታዘዙ ሰዎች ለመሆን እፈልጋለው?>>  ፣ ሲል፦ ✔ << ግዴታዎችህን ፈፅም>> አሉት። ☞ << በአላህ ዘንድ ትልቁ ሀሠና ወይም ደግ ሥራ የቱ ነው?>> ፣ ብሎ ሲጠይቃቸው፦ ✔ << መልካም ፀባይ መተናነስ እና በበላዕ ላይ ሰብር ማድረግ ነው>> አሉት። ☞ << በአላህ ዘንድ የትኛው ስርዓት ነው መጥፎ ሥራ?>>፣ ሲል ሲጠይቃቸው፦ ✔ << መጥፎ ፀባይና ፍላጎትን መከተል ናቸው>> ፣ አሉት፦ ☞ << በዱንያም ሆነ በአኼራ የአላህን ቁጣ የሚያበርድ ምንድነው?>>  ሲል ጠየቃቸው፦ ✔ << ድብቅ ሰደቃ እና ዘርን መቀጠል ናቸው>> አሉት። ☞ <<የቂያማ ቀን በአላህ ኑር ለመሰብሰብ እፈልጋለው?>> ፦ ሲል ☞ << ሰውን አትበድል>> ፣ አሉት ☞ << የቂያማ እለት አላህ እንዲያዝንልኝ እፈልጋለው?>> ✔ << ለአላህ ባርያዎች እዘን>>  አሉት። ☞ << የቂያማ ቀን የጀሀነም እሳት የሚያጠፋው ምንድነው?>>  ብሎ ሲጠይቃቸው፦ ✔ << በችግር ላይ ወይም በሙሲባ ላይ ትዕግስት ማድረግ ነው>> ፣  አሉት። ☞ << የቂያማ እለት ነውሬ እንዲሸፈንልኝ እፈልጋለው?>> ሲልም፦ ✔ << የወንድምህን አይብ ሸፍን>>፣  አሉት። ☞ << የቂያማ ቀን ከአላህ ቁጣ ሰላም ለመሆን እፈልጋለው?>> ሲል፦ ✔ << በአንድም ፍጡር አትቆጣ>> ፣አሉት። . ☞ አላህ(ሱ.ወ) ባወቅነው በሰማነው የምንስራ ያድርገን አሚን!!!! =================== https://t.me/dnqadnqwegoch
541Loading...
17
ጊዜ🥀 ወፎች በህይወት እያሉ...ጉንዳኖችን ይበላሉ።ወፎች ሲሞቱ...ጉንዳኖች በተራቸው ወፎችን ይበላሉ። ከአንድ ዛፍ ሚሊዮን የክብሪት እንጨቶች ይሰራሉ።በአንድ የክብሪት እንጨት ሚሊዮን ዛፎች ይነዳሉ። ዛሬ አንተ ሐይለኛ ስለሆንክ ደካማ ሰዎችን አትናቅ አታጥቃ! ጊዜ ከአንተ በላይ ሐይለኛ እና ሐቀኛ ነው። ቀንህ ሲደርስ አንተም ደካማ መሆንህ እማይቀር ነው። መልካም ለይል❤️‍🩹 @anbeb_islamic
420Loading...
18
#ሱብሃንአላህ => ጂንን የሚፈራው ቀበሮ ሳይሆን፤ ጂን ቀበሮን እንደሚፈራ ያውቃሉ?!! => ግመል የበደለውን እንደማይረሳ ያውቃሉ?!! => ንስር አሞራ በህመም ምክንያት እራሱን በማጥፋት እንጂ በኖርማል ሁኔታ እንደማይሞት ያውቃሉ?!! => ቀጭኔ በቀን ሶስት ጊዜ፤ በጥቅሉ ለ9 ደቂቃዎች ያህል ብቻ እንደምትተኛ ያውቃሉ?!! => ዝሆን ሀዘን ሲሰማው እንደሚያለቅስ ያውቃሉ?!! => ፈረስ ጅራቱ ከተቆረጠ እንደሚሞት ያውቃሉ?!! => ዶልፊን ሲተኛ አንድ አይኑን ብቻ እንደሚጨፍን ያውቃሉ?!! => አዞ ሲደሰት እንደሚያለቅስ ያውቃሉ?!! => አንበሳ የአውራ ዶሮ ጩኸትን እንደሚፈራ ያውቃሉ?!! => ጉንዳን ስታስነጥስ እራሷን እንደምትስት ያውቃሉ?!! በመጨረሻም ኀያሉ ጌታችን አላህ (ሱ.ወ) ጥራት ይገባው ማለት ይገባናል፡፡ #ሱብሃነላህ!! @yasin_nuru @yasin_nuru @yasin_nuru
470Loading...
19
ልቦናን ከሚያበላሹ 5 ነገሮች ራቁ! 1) ገደብ አልባ መደበላለቅ፣ 2) ጥጋብ፣ 3) እንቅልፍ ማብዛት፣ 4) ከአላህ ውጭ በሆነ ነገር ተስፋ ማድረግ፣ 5) የቅዠት ተስፋ። ኢብኑ-ል-ቀ-ይ'ዩም አል-ጀውዚ-ይ'ያህ
460Loading...
20
ለመንገድ..... 🦋 አስታውሳለሁ አትበል በወረቀት ላይ ፃፈው። 🦋ስራውን ሳይጨርስ ሙሉ ክፍያ አትስጠው። 🦋የደስታህ ዘጠና  በመቶ ምንጭ ናትና ሚስትህን በጥንቃቄ ምረጥ። 🦋የነገው ቀንህ ጥሩ እንዲሆን በጊዜ ተኛ። 🦋ሌላ ስራ ማግኘትህ እርግጠኛ ሳትሆን ያለህበትን ስራ አትልቀቅ። 🦋የጓደኛህ መኪና ከተዋስክ ነዳጅ ሞልተህ መልስ። 🦋እናትህ ይቆጭሀል ካለችህ ተጠንቀቅ። 🦋ባታነበውም ቆንጆ መፅሀፍ ግዛ። 🦋አንድን ነገር ከአንድ ጊዜ በላይ የምትዋስ ከሆነ ገበያ ወጥተህ ግዛው። 🦋ሁሉም ትላልቅ ሰዎች ከ24 ሰዓት በላይ አልነበራቸውም ጊዜ ኤለኝም አትበል። 🦋ከልጆችህ ጋር ስትጫወት ተሸነፍላቸው። 🦋ከአላህ ቀጥሎ ስኬትህ ስራህ ላይ ጥገኛ ነው። 🦋እንዴት አይሆንም ማለት እንደምትችል እወቅበት። 🦋ለተቺዎችህ ምለሽ ለመስጠት ጊዜ አታባክን። 🦋ለጤናህ ስትል ክርክር ተው። 🦋በፊት የማትበላውን ውድ ነገር ተጋበዝኩ ብለህ አትዘዝ። ከንባብ መንደር የተገኘ የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎበታል ። @anbeb_islamic
582Loading...
21
ሰው እንዴት ራሱን ያጃጅላል? ------ በአንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ይህን የልጅ ተግባር ስመለከት እንደ ተቋምነታቸው በጣም አዘንኩላቸው። እርግጥ ነው ሀይማኖቷ ብዙ ኋላ ቀርና ዘመኑን ያልዋጀ አጉል እምነቶችን ያጨቀች እንደመሆኗ ምእመኖቿ ከቀን ወደቀን እየሸሹ ወደ እስልምናና ጴንጤነት እየገቡባት ተቸግራ ሊሆን ይችላል። ሆኖም የእምነቷን ህልውና ለማስቀጠል አሁንም የልጅ ተግባር ይዞ መቅረብ መፍትሄ ይሆናል ብዬ ግን አላስብም!! እንዴት በአንድ የሀይማኖት ተቋም እንዲህ ያለ ድራማ ይሰራል? ያውም የሌላን እምነት እሴት እንዲህ በሰይጣን እየመሰሉና ድራማ እየሰሩ ልክ ሰይጣን ከቤተ ክርስቲያኒቱ እንደተባረረ አስመስሎ አሯሩጦ በማውጣት ድራማ 😂😂 ይህ እኮ ተውኔት እንጂ እምነት አይደለም!!🤔 እና እምነታችን እንዲህ ነው እያላችሁን ነው?? ለማንኛውም 1 ነገር ቆም ብዬ ልምከራችሁ 1, የሌላን እንመት በማንቋሸሽና ሰይጣን አስመስሎ ለምእመናችሁ በማቅረብ ፈፅሞ የምእመናችሁን ፍልሰት አታስቀሩትም። ምእመኑ አእምሮውን የተጠቀመ እለት በቤተ እምነታችሁ ድራማ እየተሰራ መሆኑንና ልብ ወለድ ደግሞ ከሰው ሰራሽነት ያልዘለለ የሰው ፈጠራ መሆኑን ያወቀ እለት ስለ እስልምና እውነታ ለማወቅ እንዲጥር በር ትከፍቱለታላችሁ!! ስለ እስልምና ካወቀ ደግሞ በቀጥታ እንደሚሰልም እኛም እናንተም የምናውቀው እውነታ ነው!! ትልቅ ተቋም ያለው ሀይማኖት እንደመሆናችሁ ተቋማዊ ስራ ስሩ! የልጅ ስራ በሰራችሁ ቁጥር ባለ አእምሮዎቻችሁን ታሸሻላችሁ እንጂ ምእመን እንጨምራለን ብላችሁ ታስቡ ይሆን??? ለማንኛውም ጠቅላይ ወቃሽ አይደለንምና ይህ ፅሁፍ የሚመለከተው አካል ቪዲዮው ላይ ያለውን ስራ በመስራት ለተሳተፉ ሰዎች ሁሉ ነው!!
630Loading...
22
ትንሽ ፈገግ በሉ‼ ============ ✍ «… ወሎ ውስጥ ነው አሉ። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። ክርስቲያኑ ሙስሊሙን ግብዣ ጠራው። የገና በአል ነበር። ሙስሊሙ ሲመጣ  ምግቡ፣ መጠጡ፣ ሁሉ ነገር ተትረፍርፏል። ሰዎቹ ፌሽታ በፌሽታ፣ ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል። * ሙስሊሙ:– "ድግሱ ምንን ምክንያት በማድረግ ነው?" ብሎ ጠየቀ። "ጌታ ተወልዶ ነው" አሉት። ለሙስሊሙ ይሄ አስደንጋጭ ነበር። ጌታ ይወለዳል?! ግን ከሰው ቤት ነው ያለው ምን ይላል? "ህምምም" ብሎ የሆዱብ በሆዱ አድርጎ ዝም ይላል። ይህን ጉድ አይቶ ተመለሰ። ሌላ ጊዜ ተጠራ። ጥምቀት ነበር። ሲመጣ ድግሱ አሁንም እንደባለፈው የደመቀ ነው። ሰዎቹም ደስታ በደስታ ናቸው። "ይሄስ በአል ምንድን ነው ምክንያቱ?" ብሎ ጠየቀ። "ጌታ ተጠምቆ ነው" አሉት። ዘንድሮ ጉድ ተአምር እያየ ነው። እንዲያም ነው፤ እንዲህም ነው ሳይል ወደ ቤቱ ተመለሰ። አሁንም ተጠራ። ስቅለት ነበር። ሲመጣ ከወትሮው የተለየ ነገር አየ። ሰዎቹ የባለፈው አይነት ደስታ አይታይባቸውም። አዝነዋል። በባዶ እግር ይሄዳሉ። የሚበሉት ንፍሮ ነው። ግንባራቸውን በሳር መሳይ ነገር አስረዋል። ምን ጉድ ነው?! ቆለኛው ግራ ገብቶታል። * "ምንድን ነው የሆናችሁት?" አላቸው። "ጌታ ሞቶ ነው" አሉት። * "ያ ባለፈው የተወለደው?" ሲል ጠየቀ። "አዎ" አሉት። · ከዚያ ምን ቢል ጥሩ ነው:– "እኔኮ ቀድሞም ፌሽታ ስታበዙ እንደማያድግ አውቄያለሁ!" ©: የታሪኩ ምንጭ አንድ የደሴ ክርስቲያን ነው። @yasin_nuru @yasin_nuru
490Loading...
23
✏️ከድቅድቅ ጨለማ ቀጥሎ ብርሃናማ ቀን እንደሚመጣ ሁሉ ከችግር በኋላ እፎይታ እንደሚመጣ የሰው ልጅ አሳምሮ ያውቃል። ሆኖም ችግር በሚገጥመው ጊዜ የተፈጥሮው ደካማው ክፍል ያይልና ብሩህ ነገር መምጣቱን ያስረሳዋል። በችግር ላይ ያለ ሰው ችግሩን ለመቅረፍ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ አለበት። አሊያ ተስፋ ቢስነት ይጠናወተዋል። ከዚህ በፊት ሰዎች በከበባድ ችግሮች ሲፈተኑ ያሳዩትን ታጋሽነት ማስታወስ አንድ ሰው ቁርጠኝነቱን የሚያጠነክርበት ዘዴ ነው። ከምቾት በፊት ያለ ችግር፤ ከምግብ በፊት እንዳለ ረሃብ ነው። ምግብ ጥፍጥናው የሚታወቀው ከረሃብ በኋላ ሲመገቡት ነው። ✍አህመድ ኢብኑ ዩሱፍ ▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭ https://t.me/dnqadnqwegoch
440Loading...
24
✍አላህ ላንተ በመደበልህ ነገር ተብቃቃ፤ ከሰዎች ሁሉ ሀብታም ትሆናለህ። ▭▭▭▭▭▭▭▭▭ https://t.me/dnqadnqwegoch
530Loading...
25
ወላሂ ወዳጄ ብዙ አትከፋ፤ ችግር አላፊ ነው ቢተልቅ ቢሰፋ ። ዛሬ ቢወርድብህ መከራ ሰቀቀን፤ አዳልጦህ ብትወድቅ አምርረህ አትዘን። ስንት ክቡር ሰዎች ዝናን የጨበጡ፤ ኖረዋል አደጋን ችግርን ሲጠጡ። ግና ትዕግስታቸው ሃያል ስለነበር፤ ከገቡበት ችግር መውጣት ችለው ነበር። ➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳ https://t.me/dnqadnqwegoch
550Loading...
26
✍በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆንህን ስትረዳ መጥፎ ነገርን ፍራ። በመጥፎ ሁኔታ ላይ መሆንህን ስትረዳ ጥሩ ነገርን ተስፋ አድርግ። ብዙ ሰዎች ሞትን እየፈለጉ ኖረዋል። መኖርን እየፈለጉ ሞተዋል። ብዙ ጊዜ አንድ ሠው ደህንነትን የሚያገኘው የፍርሀትን መንገድ ከተጓዘ በኋላ ነው። ▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭ https://t.me/dnqadnqwegoch
470Loading...
27
✍      ንጉሶቹ የሚወረወሩበት ጫካ!! ልብ ላለው ልብ የሚነካ ታሪክ   አንዲት ጉደኛ ሀገር አለች። በዚች ሀገር ውስጥ ከሚደረጉ አስገራሚ ነገሮች አንዱ፦ በሀገሪቷ ላይ የሚነግሰው የትኛውም ንጉስ መንገስና መምራት የሚችለው እስከ ተገደበለት ጊዜ ድረስ ብቻ ነው። ልክ ያንን ጊዜ ሲጨርስ በሀገሪቷ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ወደ ለንጉሶች መጣያ የተዘጋጀ ጫካ ይወሰድና ይጣላል።    ጫካው የሚገኘው ከሀገሪቷ ራቅ ያለ ቦታ በመሆኑ የሀገሪቷ ህዝቦች ስለ ጫካው ብዙም ጠንቅቀው አያውቁም። ብቻ ግን የንጉሱ ጊዜ ሲያበቃ ለዚህ ተግባር የተመደቡ ሰዎች ወስደው ጥለዉት ይመለሳሉ።   ንጉሱ ከዝያ በኋላ ተመልሶ አይመጣም። በምን ሁኔታ እንደ ሚኖር? በምን ሁኔታ እንደ ሚሞት የሚታወቅ ነገር የለም።   ንጉሱም ምንም እንኳ በንግስናው ዘመን የፈለገውን ማድረግ የመቻል መብት ቢኖረውም ጫካውን የሚያየው ግን ተወስዶ በሚጣልበት ቀን ነው።   ነገሩ በዚህ መልኩ እየሄደ ሳለ በሀገሪቷ ላይ ተራው ይደርሰውና አንድ ንጉስ ይነግሳል።   ይህ ንጉስ በጣም አዋቂና በሳል ስለ ነበር በስልጣን ዘመኑ እንደ ፈለገ ተመቻችቶ በመጨረሻም በማያውቀው ጫካ መጣል አልፈለገም።      "ታድያ ምን አደረገ❓"    ከዕለታት አንድ ቀን አገልጋዮቹን በማስከተል ንጉሶች የሚጣሉበት ጫካ ምን ዐይነት እንደ ሆነ እንየው ብሏቸው ይሄዳሉ። [በንግስና ዘመኑ የፈለገውን ማድረግ ስለ ሚፈቀድለት] ወደ ጫካው ሄደው ሲያዩ; ጫካው፦   በአስፈሪ አራዊቶች የተሞላ፣    እሾሃማ እና የሚያቆስሉ ዛፎች የበዙበት፣ አየሩ በመጥፎ ጠረን የተበከለ እና   በአጠቃላይ በጣም የሚያስፈራ ጫካ ሆኖ አገኙት።    በዚህ ጊዜ ይህ አስተዋዩ ንጉስ ነገ ወደዚህ ጫካ ከመጣሉ በፊት የቤት ስራውን መስራት ጀመረ። በስልጣኑ ከሚያገኘው ገቢ አብዛኛውን ወደዚህ ጫካ ወጪ በማድረግ ጫካው እንዲመነጠር፣    አስፈሪ አውሬዎቹ እንዲታደኑ፣      እሾሃማ ዛፎች እንዲወገዱ፣        ማራኪና ጥሩ ማዕዛ ያላቸው ተክሎች እንዲተከሉ በማድረግ ያ አስፈሪ የነበረው ጫካ ወደ ውብ መናፈሻነት ቀየረው።   የማይደርስ የለምና የንግስና ማብቂያ ቀኑ ደርሶ ወደ ጫካው ሲጣልም እንደ ቀደምት ነገስታቶች ስቃይና እንግልት ሳይሆን ውብና ማራኪ የሆነ ህይወት መኖር ጀመረ። ♻️እዚህ ጋ ቆም በልና ታሪኩን በምናብህ ቃኘው!! ናልኝማ ወዳጄ👇 እስከ አሁን ታሪኳን የነገርኩህ ሀገር፦ 👉የምስራቅ አውሮፓዋ …… ሀገር አይደለችም። እስከ አሁን ታሪኩን የነገርኩህ ንጉስ፦ 👉ከላይ የተጠቀሰቿ ሀገር ንጉስም አይደለም። ሀገሪቷ………     ያለንባት ዱንያ ናት። ንጉሶቹ………     እኔና አንተ ነን። ንግስናው………    የዱንያ ሕይወት ነው። ንግስናችን (ሕይወታችን) ሲያልቅ የምንጣልበት ጫካ………     ቀብራችን ነው። ንጉሶቹ ወስደው የሚጥሉት………      ቀባሪዎቻችን ናቸው። ጫካው ውስጥ ያሉ አስፈሪዎች………   የቀብር ውስጥ ጠያቂዎች ናቸው። ንጉሱ ወደ ጫካው ግንባታ ወጪ ያደረገው………   መልካም ስራው ነው። ♻️ጥያቄው👇 በዱንያ ሕይወታችን (ንግስናችን)፦ 💫አስፈሪው ቀብራችን እየገነባንና እያስዋብን ነን?? ወይንስ………… 💫በአስፈሪው ቀብር ተወስደን እስከ ምንጣል ቸላ ብለነዋል?? https://t.me/AbuReyan_3030    https://t.me/AbuReyan_3030
1051Loading...
28
ኢማሙ ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለት እና እንዲህ ብሏል :- ምድር ያለዝናብ ሀያት ( እድሜ) እደሌላት ሁሉ : ቀልብም ሀያት (እድሜ )የላትም በእውቀት ቢሆን እንጂ ✍ መፋቲህ ዳር አስሰአዳ (508/ 1) ▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭ https://t.me/dnqadnqwegoch
360Loading...
29
✍ኢብኑል ቀዪም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል። አብዛኛው ሰው ለጀነት ያለው አመለካከት የተሳሳተ ነው፣ ጀነት ማለት ዛፎች ያሉባት፣የተለያዩ ፍራፍሬዎች፣ምግብ፣መጠጥ፣ሑረልዒን፣ወንዞችና ህንፃዎች ለነዚህ ለዛዎች ብቻ የዋለ ስም አይደለም። ጀነት ማለት ሙሉና ልቅ የሆነች የመጠቃቀሚያ አገር ናት፣ ከመጠቃቀሚያዎች በሙሉ በላጩ ፀጋ፦ የቸሩ አላህን ፊት መመልከት ፣ንግግሩን መስማት፣የጀነት ሰዎች የአይን ማረፊያቸው ከርሱ መቅረብና ውዴታው መሆኑ። የዚህ ፀጋ (ለዛ)ከመብላት ከመጠጣት ከመልበስ ለዛ ጋር ፈፅሞ ሊነፃፀር አይገባም። 【መዳሪጁ ሳሊኪን፤2/80】 አላህ ሆይ በራህመትህ ጀነትን ከሚገቡ ሰዎች አድረገን! ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ https://t.me/dnqadnqwegoch
480Loading...
30
🌼ኢማሙ ኢብነል ቀዩም አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ 🌴 የልብ በሽታ ከሰውነት/አካል በሽታ የበለጠ አስቸጋሪ ነው። የሰውነት ህመም ቢበዛ ታማሚውን ለሞት ቢዳርግ ነው። 👉የልብ ህመም ግን ሰውዬውን ለዘላለም እድለቢስነት ይዳርገዋል። ለልብ ህመም ደግሞ በዕውቀት እንጂ ሌላ ህክምና/መድሀኒት የለውም። 🌼እውቀት ለልብ: ልክ ውሀ ለአሳ እንደሚያስፈልገው ነው። ባጣው ጊዜ ይሞታል። አላህ ዲናችንን የምንገነዘብ እና በተገነዘብነው ደግሞ ለአላህ ብለን በኢኽላስ የምንሰራ ያድርገን @islam_in_school
400Loading...
31
እነዚያ ትላንት የሞቱት ለዛሬ ጠዋት እቅድ ነበራቸው ..... እነዚያ ጠዋት የሞቱት ደግሞ ለምሽት እቅድ ነበራቸው ....... ስለመኖርህ እርግጠኛ አትሁን በአይን እርግብግቢት ቅፅበት ሁሉም ነገር ሊቀየር ይችላል።ስለዚህ ሞትህን ሞተህ አትጠብቀው። ሁሌም ቢሆን ተውበት ማድረግን እና ለሞት መዘጋጀትን አትዘንጋ ያረብ ከሞት በፊት ተውበትን በሞት ጊዜ ሸሀዳን ከሞት በኋላ ጀነትን ስጠን🤲🤲 ▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭ https://t.me/dnqadnqwegoch
320Loading...
32
📌ያስቸገረኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር! ተወልዶ ካደገበት ሃገሩ በተፈጠሩ ማሕበራዊ ቀውሶች ምክንያት ወደሌላ ሃገር በስደት ለመሄድ የቆረጠ አንድ ሰው ረጅም፣ አድካሚና አስፈሪ የሆነን በረሃ ለቀናት በእግሩ በመሄድ ካቋረጠ በኋላ እጅግ ደክሞና ዝሎ መድረስ የፈለገበት ከተማ ገባ። እንደደረሰም በከተማው ውስጥም በተለገሰው አንዳንድ እርዳታ እራሱን ትንሽ አገገመ፡፡ የዚህን ሰው የጉዞ ጀብድ የሰማና ለሕብረተሰቡ ለመዘገብ የፈለገ አንድ ጋዜጠኛ አገኘውና አንድን ጥያቄ ጠየቀው፡፡ “ተጉዘህ የመጣኸው በረሃ ብዙ ሰው የማይደፍረው በረሃ ነው! ለመሆኑ በመንገድህ ላይ በጣም የጎዳህና ያስቸገረህ ውኃ ጥም ፣ምግብ ማጣት፣ አውሬ ፣ ሽፍቶች ነበሩ ሲል ጠየቀው? የዚህ ስደተኛ መልስ ለጋዜጤኛው ያልተጠበቀ ነበር፡፡ በዚህ አደገኛ በረሃ አቋርጬ ስመጣ በጣም ያስቸገሩኝ የጠቀስካቸው ትልልቅ ነገሮች አልነበሩም፡፡ ጉዞየን በጣም አድካሚና አስቸጋሪ ያደረገብኝ በእርምጃዬ ወቅት ጫማዬ ውስጥ እየገባ የሚቆረቁረኝና አላራምድ ያለኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር አለው፡፡ ================= የሕይወት ጉዞም እንዲሁ ነው! አብዛኛውን ጊዜ የሚያስቸግረን፣ የሚቆረቁረን፣ አላራምድ የሚለንና ከዓላማችን የሚጎትተን ችግር ትልልቁ አይደለም፡፡ በየቀኑ የሚያጋጥሙን ጥቃቅን “አሸዋዎች” ናቸው፡፡ ትንንሽ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ባህሪይ፣ ትንንሽና አናሳ ወሬን የሚያወሩ ሰዎች ሁኔታ፣ ትንንሽና ስሜትን የሚነካኩ የየቀን ገጠመኞች . . . ጉዟችንን አዳጋችና አድካሚ ያደርጉታል፡፡ “በትንንሽ” ሰዎችና ሁኔታዎች ሳትበገሩ ትልቁ የሕይወት ስእልና ዓላማችሁ ላይ በማተኮር ወደፊት መገስገስን ያወቃችሁበት ጊዜ ዋናውን የሕይወት ድል የተጎናጸፋችሁበት ጊዜ ነው፡፡ እናም በርቱ!
390Loading...
33
አንድ አባት ሴት ልጁን ውድ በሆነ ሆቴል ራት ጋበዛት.... ከሆቴሉ ባልተቤት ጋር በመነጋገር  ከፊት ለፊታቸው የተለያዩ  ያማሩና ጣፍጭ ምግቦች እንዲያስቀምጥ ነገረው ። ከትንሽ ደይቃ ብኋላ የሆቴሉ ባልተቤት የተለያዩ ጣፍጭ ምግቦችንና የተሸፈነ ምግብ ይዞ መጣ.. ልጂቱም ከፊት ለፊቶ የተቀመጡትን ምግቦች መመልከት ጀመረች  በእቃ የተሸፈነው  ምግብ ይበልጥ ሳባትና ልትከፍተው ስትል አባቷ ከለከላት ....! አባቷም ከፊት ለፊትሽ በርካታ ጣፍጭና የሚያማምሩ ምግቦች እያሉ የተሸፈነውን ለምን መክፈት ፈለግሽ ሲል ጠየቃት...? ልጂቱም የተሸፈነ ስለሆነ በውስጥ ያለው ያማረና የተሻለ ጥፍጥና ይኖረዋል  ብየ ስላሰብኩ ነው ስትል መለሰች አባቷም ፈገግ አለና እንዲህ አላት በሒጃብ ለምን እንደምሸፍንሽ አወቅሽ! ልጂቱም ወደ መሬት እየተመለከተች አባቷ ያላት ገባት ! ከዛ ብኋላ ምርጥ የተሸፈነ ምግብ ሆነች! ሒጃብ ነገራቶች ለማክበድ ሳይሆን በአጭሩ መደበቅ ያለበት ተደብቆ ማየት ያለበት እንዲያይ ነው ። 🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
621Loading...
34
Sheikh Mishary Rashid Al-Afasy😍😍
430Loading...
35
🛑👉ወንድም አስተውለሀል? ~ ☞ አድካሚውና አሰልቺው ስራህ፦ የብዙ ስራ አጦች ምኞት ነው !! ☞ ዘወትር የሚያናድህ ልጅህ፦ የብዙ መሀኖች ህልም ነው!! ☞ ትንሿ ጎጆህ ፦ የሁሉም ተፈናቃዮች ምኞት ናት !! ☞ ጤናህ ፦የብዙ ህመምተኞች ህልም ነው!! ☞ፈገግታህ፦ የብዙ ጭንቀታም ጭምቶች ምኞት ነው! ☞አንተ ብቻ የምታውቀው ገመናህ፦ውርደት አንገት ያስደፋቸው ሁሉ የቁጭት ምኞት ነው! ☞ ከሀራም ርቀህ በዲንህ መፅናትህ፦የአንዳንድ ወንጀለኞች የሩቅ ምኞት ነው !! ታድያ ምን አጣህ!? የአላህን ፀጋዎች ቆጥረህ ስለማትዘልቅ አመስግን እንጂ አታማር!!             وَآتَاكُمْ مِنْ كُلِّ مَا سَأَلْتُمُوهُ ۚ وَإِنْ تَعُدُّوا نِعْمَتَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ إِنَّ الْإِنْسَانَ لَظَلُومٌ كَفَّارٌ «ከለመናችሁትም ሁሉ የሰጣችሁ ነው፡የአላህንም ጻጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ ሰው በጣም በደለኛ ከሓዲ ነው!» ኢብራሂም 34 አላህ ሆይ! ስለ ፀጋዎችህ ሁሉ እናመሰግንሀለን!!   = 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
431Loading...
36
ቢስሚላሂ ረሕማኒ ረሒም - መልካም ምክሮች 1- ቀንህን ከምትጀምርባቸው ነገሮች ሁሉ ዚክር እና ሶላት ምርጦቹ ናቸው!! 2- ወንጀል ብትሰራም ባትሰራም ምላስህ ሌት ተቀን አላህን እስቲግፋር ከመጠየቅ አይቦዝን! 3- በዱዐ አትዘናጋ ለመዳን ወሳኙ መሳሪያ እሱ ነውና!! 4- ከመናገርህ በፊት ቃላቶችህን የሚፅፉ መላኢካዎች አጠገብህ እንዳሉ አትዘንጋ!! 5- ትልቅ ማእበል ቢያጋጥምህ እንኳ አሁንም መውጫ እንዳለህ አስብ!! 6- አለንጋ ጣቶችህ የበለጠ የሚያምሩት ዚክር ላይ ሲሳተፉ ነው!! 7- ለዱዐ ምላሽ የምታገኝበትን እድል ሐራም በመብላት አትዝጋው!! 8- የመጥፎ ጥርጣሬ አባዜ ከሌለብህ ደስተኛ ሁነህ ትኖራለህ!! 9- በጋዜጣና በሞባይል ፍቅር ከመውደቅህ በፊት በቁርአን ፍቅር ውደቅ!! 10- የሰው ልጅ ነፍሱ አመፀኛ ናትና በአላህ ትዛዝ ላይ አስገድዳት!! 11- ያንተ አሮጌ ልብሶች ለድሃ አዳድሶች ናቸው!! 12- ምድርን ስትሰናበት ካንተ ጋራ መቃብር የሚገባ ስራ ይኑርህ!! 13- ሀሜተኛ ሰው ካጋጠመህ 'አላህን ፍራ' ለማለት አትፍራ!! 14- ህይወት በተፈጥሮ ውብ ናት፣ ከኢማንና ከተስፋ ጋር ደግሞ እጅግ ውብ ናት!! 15- የምትቸኩልለት ነገር ሁሉ ከሶላት የሚበልጥ አይደለምና ተረጋግተህ ስገድ!! 16- ህይወት እኛ ከምንገምተው በላይ በጣም አጭር ናትና ከዚህም ከዚያም ጋር አትጋጭ!! 17- የጭንቀት ሁሉ መንስኤው ከአላህ ﷻ መራቅ ነውና በተቻለህ አቅም ከአላህ ላለመራቅ ሞክር!! @yasin_nuru @yasin_nuru
391Loading...
37
✍የመርሳት ሱጁድ የሱጁድ አስ'ሰህው ትርጓሜ የመርሳት ሱጁድ በመርሳት ምክንያት ሶላቱ ውስጥ የተከሰተውን ጉድለት ለማካካስ ሰጋጁ የሚያደርጋቸው ሁለት ሱጁዶች ናቸው፡፡ የመርሳት ሱጁድ ምክንያቶች የመርሳት ሱጁድ ምክንያቶች ሦስት ናቸው ፡- ጥርጣሬ፣ ጭማሬና ጉድለት 1 - ጥርጣሬ ጥርጣሬ ከሁለት ነገሮች መካከል የትኛው ይሆን የተከሰተው ብሎ ማመንታት ነው፡፡ ሶላትን በተመለከተ ጥርጣሬ በሁለት ይከፈላል ፡- 1 - ሶላቱ ካበቃ በኋላ የሚሆን ጥርጣሬ ለዚህ ዓይነቱ ጥርጣሬ ትኩረት አይሰጥም፡፡ ምሣሌው ፡- አንድ ሰው ከፈጅር ሶላት በኋላ ሁለት ረክዓ ነው ወይስ ሦስት ነው? ብሎ መጠራጠር ነው፡፡ እርግጠኛ ሆኖ በተረጋገጠለት ነገር ከመስራት ውጭ ለዚህ ጥርጣሬ ግምት አይሰጥም፡፡ 2 - ሶላቱ ውስጥ እያሉ የሚፈጠር ጥርጣሬ ይህ ጥርጣሬ ከሁለት ሁኔታዎች አንዱ ነው ፡- ሀ- ከሁለት ነገሮች ውስጥ አንዱን አመዛኝ ሆኖ ማግኘት በዚህ ሁኔታ አመዛኝ ሆኖ በተገኘው መሰረት በመፈጸም ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ምሣሌው ፡- አንድ ሰጋጅ ዙህር በመስገድ ላይ እያለ ሁለተኛው ረክዓ ነው ወይስ ሦስተኛው ነው? ብሎ ተጠራጥሮ ሦስት ነው የሚለውን አመዛኝ ሆኖ አገኘው፡፡ በዚህ ሁኔታ ሦስት ነው ብሎ ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው የነቢዩ ﷺ ቃል ነው ፡- ‹‹አንዳችሁ በሶላቱ ከተጠራጠረ ትክክለኛውን ለማወቅ ጥረት ያድርግ፤ከዚያም ሰላምታ ይበልና ሁለት ሱጁድ ይውረድ፡፡›› [በእብን ሒባን የተዘገበ] ሰላምታ ይላል የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል ለ- ከሁለት አንዱም አመዛኝ ሆኖ አለመገኘት በዚህ ሁኔታ በአነስተኛው ቁጥር ላይ ተሞርክዞ ሶላቱን በማጠናቀቅ የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ምሣሌው ፡- አንድ ሰጋጅ ዙህር በመስገድ ላይ እያለ ሁለተኛው ረክዓ ነው ወይስ ሦስተኛው ነው ብሎ ተጠራጥሮ ሁለቱም አመዛኝ ሳይሆኑ ይቀራሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ በአነስተኛው ቁጥር ላይ ተመስርቶ ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በፊት የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው የነቢዩ ﷺ ቃል ነው፡- ‹‹አንዳችሁ በሶላቱ ከተጠራጠረና ሶስት ይሆን አራት ስንት እንደ ሰገደ ካላወቀ፣ ጥርጣሬውን ወደ ጎን ያድርግ፣ አመዛኝ ሆኖ ባገኘው ላይ ይመስርት፤ከዚያ ከሰላምታ በፊት ሁለት ሱጁድ ያድርግ፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ] የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል ሰላምታ ይላል 2 - ጭማሬ ይህ ሰጋጁ በሶላቱ ውስጥ ሩኩዕ ወይም ሱጁድ፣ . . ወዘተ. የመጨመር ሁኔታ ነው፡፡ ጭማሬው ከሚከተሉት ሁለት ሁኔታዎች አንዱ ከመሆን አያልፍም ፡- ሀ- ሰጋጁ በማድረግ ላይ እያለ ጭማሪውን የሚያስታውስበት ሁኔታ፡፡ ይህ ከሆነ ከድርጊቱ መታቀብ ግዴታ ይሆንበታል፡፡ ከዚያ ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ምሣሌው ፡- አንድ ሰጋጅ ዙህር በመስገድ ላይ እያለ አምስተኛ ረክዓ ለመስገድ ተነስቶ ከቆመ በኋላ ጭማሪ መሆኑን ያስታውሳል፡፡ በዚህ ሁኔታ ወዲያውኑ ተመልሶ በመቀመጥ ሶላቱን ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡ ከሰላምታ በኋላ የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ለ- ሰጋጁ በመጨመር ላይ እያለ ጭማሪውን የሚያስታውስበት ሁኔታ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ያደርጋል፡፡ ለዚህ ማስረጃው ከእብን መስዑድ (ረዐ) የተላለፈው የሚከተለው ሐዲስ ነው ፡- ‹‹ነቢዩ ﷺ ዙህርን አምስት ረክዓ ሰገዱና ‹በሶላቱ ጭማሬ ተደረገ ወይ?› ተብለው ተጠየቁ፡፡ ምን ተደረገ? ሲሉ ‹‹አምስት ነው የሰገዱት›› ተባሉና ከሰላምታ በኋላ ሁለት ሱጁድ ወረዱ፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ] 3 - ጉድለት ይህ ሰጋጁ ከሶላት ማእዘናት ወይም ከግዴታዎቹ አንዱን ማእዘን ወይም አንዱን ግዴታ የማጓደል ሁኔታ ነው፡፡ 1 - የማእዘን ጉድለት ይህ ማእዘን የእሕራም ተክቢራ ከሆነ ሶላቱ ውድቅ ነው፣ ሶላቱ ከነአካቴው አልተመሰረተምና፡፡ ጉድለቱ ከእሕራም ተክቢራ ውጭ ካሉት ማእዘናት አንዱ ከሆነ ሁኔታው ከሚከተሉት ሁለት ሁኔታዎች አንዱ ከመሆን አይዘልም ፡- ሀ- ሰጋጁ በቀጣዩ ረክዓ ላይ በተረሳው ማእዘን ላይ ከደረሰ በኋላ ያስታወሰ መሆን፡፡ ሁኔታው ይህ ከሆነ ማእዘኑ የጎደለበትን ረክዓ ውድቅ አድርጎ በቀጣዩ ረክዓ ይተከዋል፡፡ ምሣሌው ፡- አንድ ሰጋጅ በመጀመሪያው ረክዓ ሩኩዕ ረስቶ በሁለተኛው ረክዓ ሩኩዕ ላይ መርሳቱን ያስታውሳል፡፡ በዚህ ሁኔታ አሁን ያለበትን ረክዓ የመጀመሪያው ረክዓ አድርጎ በመውሰድ የበፊተኛውን ረክዓ ውድቅ አድርጎ ሶላቱን ያሟላል፤ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ሰላምታ ይላል የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል ለ- ሰጋጁ በቀጣዩ ረክዓ ላይ በተረሳው ማእዘን ላይ ከመድረሱ በፊት ያስታወሰ መሆን፡፡ እዚህ ላይ ወደ ተተወው ማእዘን ተመልሶ በማከናወን ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በኋላ የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ምሣሌው ፡- በመጀመሪያው ረክዓ ላይ ሁለተኛውን ሱጁድና ከርሱ በፊት ያለውን መቀመጥ ረስቶ ከሁለተኛው ረክዓ ሩኩዕ ቀና ካለ በኋላ ያስታወሰ ሰው ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ተመልሶ በመቀመጥ ሱጁድ ይወርድና ሶላቱን በማሟላት ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ 2 - የዋጅብ ጉድለት አንድ ሰጋጅ ከሶላት ዋጅቦች ውስጥ አንዱን ዋጅብ ከረሳ ሁኔታው ከሚከተሉት ሦስት ሁኔታዎች አንዱ ከመሆን አያልፍም ፡- ሀ- የተረሳውን ዋጅብ ቦታ ለቆ ወደ ሌላ ሳይተላለፍ ያስታወሰው መሆን፡፡ በዚህ ሁኔታ ዋጅቡን መፈጸም ነው፤ሌላ ነገር አይኖርበትም፡፡ ለ- ሰጋጁ በሶላቱ ውስጥ የተረሳውን ዋጅብ ቦታ ለቆ ወደ ሌላ ከተላለፈ በኋላ ወደ ቀጣዩ ማእዘን ከመድረሱ በፊት ያስታወሰው መሆን፡፡ በዚህ ሁኔታ ወደ ተወው ተመልሶ በመፈጸም ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በኋላ የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ሐ- ወደ ቀጣዩ ማእዘን ከደረሰ በኋላ ያስታወሰው መሆን፡፡ እዚህ ላይ ሶላቱን ይቀጥላል፤ወደዚያ ተመልሶ አይሄድም፡፡ ከሰላምታ በፊት የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ምሣሌው ፡- በሁለተኛው ረክዓ ከሁለተኛው ሱጁድ ተሸሁድን ረስቶ ለሦስተኛው ረክዓ ተነስቶ ቀጥ ብሎ ከመቆሙ በፊት መርሳቱን ያስታወሰ ሰጋጅ ነው፡፡ ይህ ለተሸሁድ ተቀምጦ ሶላቱን ያሟላል፣ ማካካሻ የለበትም፡፡ ተነስቶ ከቆመ በኋላና ቀጥ ብሎ ሙሉ በሙሉ ከመረጋጋቱ በፊት ካስታወሰ ለተሸሁድ ተመልሶ ይቀመጥና ሶላቱን ያሟላል፤ ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ሙሉ በሙሉ ተረጋግቶ ከቆመ በኋላ ካስታወሰ ግን ተመልሶ አይቀመጥም፡፡ ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በፊት የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ለዚህ ማስረጃው ከዐብዱላህ ብን ቡሐይና (ረዐ) የተላለፈው የሚከተለው ሐዲስ ነው ፡- ‹‹ነቢዩ ﷺ ዙህርን አሰገዷቸውና በመጀመሪያዎቹ ሁለት ረክዓዎች ሳይቀመጡ ተነስተው ቆሙ፤ሰውም አብሯቸው ተነስቶ ቆመ፡፡ ሶላቱ ሲያበቃ ሰው ሰላምታ ይላሉ ብሎ ሲጠብቅ አል’ሏሁ አክበር ብለው ሁለት ሱጁድ ወረዱና ሰላምታ አሉ፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ] ካለፈው የምንረዳው የመርሳት ሱጁድ ከሰላምታ በፊትና ከሰላምታ በኋላም የሚደረግ መሆኑን ነው፡፡ የመርሳት ሱጁድ አደራረግ የመርሳት ሱጁድ (ሱጁድ አስ’ሰህው) ከመደበኛው የሶላት ሱጁድ ጋር አንድ ነው፡ ሲወርዱና ቀና ሲሉም ተክቢራ ይደረግበታል፡ በሱጁዱ ውስጥና በሁለቱ ሱጁዶች መካከከል የሚደረገው ዝክርም አንድ ዓይነት ነው፡፡ ▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬ https://t.me/dnqadnqwegoch
410Loading...
38
✍የትራፊዎች (ኣሳር) ትርጓሜ ፈሳሽ ትራፊዎች ሌላ ጠጪ ጠጥቶለት እቃ ውስጥ ያስቀረው ትራፊ ጭላጭ ነው፡፡ ለነጃሳነቱ ማስረጃ ካልቀረበበት በስተቀር ፈሳሽ ትራፊዎች (ኣሳር) በመሰረቱ ንጹሕ (ጣህር) ናቸው፡፡ ዝርዝሩ ይቀጥላል፡- ንጹሕ የሆኑ ትራፊዎች ሀ- የሰው ልጅ ጠጥቶ ያስቀረው ትራፊ ነቢዩ ﷺ፣ ዓእሻ (ረዐ) የወር አበባ እያለባቸው ጠጥተው ያስቀሩትን ትራፊ ይጠጡ እንደ ነበርና አፋቸውንም የዓእሻ አፍ አርፎ በነበረበት ቦታ ላይ ያደርጉ እንደ ነበር በሐዲስ ተረጋግጧል፡፡ [በሙስሊም የተዘገበ] ለ - የድመት ትራፊ (ሱእር) ከእቃ የጠጣችውን ድመት አስመልክተው ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ነጃሳ አይደለችም፣ በዙሪያችሁ ከሚሆኑ ገርና ጥንቁቅ አገልጋዮች ናት፡፡›› ብለዋል፡፡ [በትርምዚ የተዘገበ] የድመት ትራፊ ሐ- ሥጋቸው የሚበላ እንስሳት፣ የበቅሎ፣ የአህያ፣ ሥጋ በል አዳኝ አራዊት፣ አዳኝ አሞራዎችና የመሳሰሉት እንስሳት ትራፊ፡- የነዚህ እንስሳት ትራፊ ንጹሕ ነው፡፡ ነጃሳ ስለመሆናቸው ማስረጃ ባለመኖሩና ነገሮች ተቃራኒው ካልተረጋገጠ በመሰረቱ ንጹሕ በመሆናቸው የነዚህ እንስሳት ትራፊ ንጹሕ ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ በአህያ ይቀመጡ ነበር፡፡ በዘመናቸው አህያ ለማጓጓዣነት ታገለግል ነበር፡፡ የአዳኝ አሞራ (አዕዋፍ) ትራፊ የአህያ ትራፊ የአዳኝ አውሬ ትራፊ ሥጋው የሚበላ እንስሳ ትራፊ ውሃ ነጃሳ የሆኑ ትራፊዎች ሀ - የውሻ ትራፊ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ያንዳችሁን ዕቃ ውሻ በአፉ (ምላሱን በማስገባት) ከለከፈው የሚጸዳው (ዕቃውን) ሰባት ጊዜ አንደኛውን ዙር በአፈር በማጠብ ነው፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ለ- የአሳማ ትራፊ የአሳማ ትራፊ (ሱእር) ነጃሳ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እርሱ ርኩስ ነውና . . . ›› [አል-አንዓም፡145] ከርሱ የወጣ ነገርም ነጃሳ ነው፡፡ የአሳማ ትራፊ የሰው ልጅ ንጹሕ (ጣህር) መሆኑ የሰው ልጅ፣ ነቢዩ ﷺ፡- ‹‹ሙእምን ሰው አይነጅስም፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ባሉት መሰረት ሙስሊም በራሱ ንጹሕ (ጣህር) ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ ሙሽሪክ ከሆነች ሴት የውሃ ስልቻ ዉዱእ ማድረጋቸው የተረጋገጠ [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] በመሆኑ ሆነ ካፍርም በራሱ ንጹሕ (ጣህር) ነው፡፡ ‹‹አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፤›› [አል-ተውባህ፡28] የሚለው የአላህ ቃል ሕሊናዊ ርክሰት ማለትም የእምነታቸውን ነጃሳነት የሚመለከት ነው፡፡ ▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬ https://t.me/dnqadnqwegoch
400Loading...
39
أذكار الصباح ولمساء
400Loading...
40
ታላቁ የዘመናችን ዓሊም ኢማም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦ «እውቀትን ስታሰራጭ የአላህን ሀይማኖት እያሰራጨህ ነው ስለዚህም በአላህ መንገድ ከሚታገሉት ታጋዮች ትሆናለህ! ምክንያቱም ታጋዩ በሰይፍና በኢማን ሀገርን እንደሚከፍት ሁሉ አንተም በእውቀት የሰዎችን ልብ ትከፍታለህና» [ሸርህ ዱዓዑ ቁኑቲል ዊትር /(ገፅ)12]
370Loading...
00:46
Video unavailableShow in Telegram
ቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ 7 ከንቱ ምኞቶች‼ ============================= ①) «ዋ ምኞቴ! ምነው አፈር በሆንኩ!» [አ-ን'ነበእ: 40] ②) «ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ!» [አል-ፈጅር: 24] ③) «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ!» [አል-ሐቀህ: 25] ④) «ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ!» [አል-ፉርቃን: 28] ⑤) «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን፤ መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ!» [አል-አሕዛብ: 66] ⑥) «ዋ ምኞቴ! ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ!» [አል-ፉርቃን: 27] ⑦) «ወይ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ!» [አ-ን'ኒሳእ: 73] ሁሉም የሟቾች ምኞቶ ናቸው። ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ምኞታቸው ወደ ዱንያ አንዴ መጥተው ለአኺራቸው ጥሩን ነገር መስራት ነው። ግን ምን ዋጋ አለው! አልፏል ተቀድሟል! ቀብር ገብተህ አንተም ይህን ከምትመኝ ነፍስህ አካልህ ውስጥ እስካለች ድረስ ለአኺራህ አስቀድም። ብልህ የሆነ ሰው ከመጸጸቱ በፊት ሥራውን ይሥራ አላህ ሆይ! ከነዚህ ከንቱ ምኞቶች በእዝነትህ ጠብቀን።
Show all...
የፈጅር (የሱብሕ) ሶላት ትሩፋቶች እና ፈጅርን አለመስገድ ያለው አደጋ ~ ~ ~~ ~ ~ 1. ፈጅርን ስገድና በአላህ ጥበቃ ስር ሁን፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ሱብሕን የሰገደ በአላህ ጥበቃ ስር ነው” ብለዋል፡፡ [ሙስሊም] 2. ፈጅርን ስገድ ሌሊቱን በሶላት እንደቆምክ ይቆጠርልሃልና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ዒሻእን በጀማዐህ የሰገደ ግማሽ ሌሊትን በሶላት እንደቆመ ነው፡፡ ሱብሕን በጀማዐህ የሰገደ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ እንደቆመ ነው”  ይላሉ፡፡ [ሙስሊም] 3. ሱብሕን ስገድ እራስህን ከሙናፊቆች መገለጫ አፅዳ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በሙናፊቆች ላይ እንደፈጀር እና ዒሻእ ሶላት የሚከብድ የለም” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 4. ፈጅርን ስገድ ለጭንቅ ቀን ብርሃን ይሆንሃልና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በጨለማዎች ወደ መስጂዶች የሚጓዙትን በቂያማህ ቀን ሙሉ በሆነ ብርሃን አብስራቸው”  ይላሉ፡፡ [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 570] 5. ሱብሕን ስገድ መላእክት ይመሰክሩልሃል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “በናንተ ውስጥ የሌሊት መላእክትና የቀን መላእክት ይተካካሉ፡፡ በፈጅር ሶላት እና በዐስር ሶላት ላይ ይሰባሰባሉ፡፡ ከዚያም እነዚያ በናንተ ዘንድ ያደሩት (ወደ ሰማይ) ይወጣሉ፡፡ ይህኔም ጌታቸው በነሱ ሁኔታ አዋቂ ሆኖ ሳለ “ባሪያዎቼን በምን ሁኔታ ላይ ተዋቸኋቸው?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ “እነሱ እየሰገዱ ነው የተውናቸው፡፡ እየሰገዱም ነው የመጣናቸው” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 6. ሱብሕን ስገድ ሙሉ የሐጅና የዑምራን አጅር እፈስ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የማለዳን ሶላት በጀማዐ የሰገደ ከዚያም ፀሀይ እስከሚወጣ ድረስ አላህን እያወሳ የተቀመጠ እና ከዚያም ሁለት ረከዐ ሶላት የሰገደ ልክ እንደ ሐጅና ዑምራ አጅር አለው፡፡ ሙሉ! ሙሉ ! ሙሉ!”  ይላሉ፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 3403] 7. ፈጅርን ስገድ በአለም ላይ ካሉ ፀጋዎች ሁሉ በላጭ የሆነ ፀጋ የምትጎናፀፍበት እድል ታገኛለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የፈጅር ሱንናህ (ከፈርዱ በፊት የምትሰገደዋ ትርፍ 2 ረከዐ ሶላት) ከዱንያ እና በውስጧ ካለ ሁሉ በላጭ ነች” ይላሉ፡፡ [ሙስሊም] 8. ፈጅርን ስገድ ከጀሀነም መትረፊያ ጀነትን መጎናፀፊያ ብስራትን ታገኛለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም  “ፀሀይ ከመውጣቷ እና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም” ይላሉ፡፡[ሙስሊም] እነዚህ ሶላቶች ፈጅርና ዐስር ናቸው፡፡ በሌላም ሐዲሥ “ሁለት ብርዳማ ሶላቶችን የሰገደ ጀነትን ይገባል” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 9. ፈጅርን ስገድ ከፀጋዎች ሁሉ በላጭ ፀጋ የሆነውን የላቀውን ጌታ መመልከትን ትታደላለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “እናንተ ይህን ጨረቃ እንደምታዩት ጌታችሁን ታያላችሁ፡ እሱን በማየትም አትቸጋገሩም፡፡ ፀሀይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት ባለ ሶላት አለመረታት ከቻላችሁ አድርጉት (ስገዱ)”  ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 10. ፈጅርን ስገድ ጥሩ ነፍስ ይዘህ አንግተህ ንቁ ሆነህ ትውላለህ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] ተጠንቀቅ! 1. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ከፈጅር ሶላት መሳነፍ አደገኛ የሆነ የሙናፊቆች ምልክት ነውና!! [ቡኻሪና ሙስሊም] 2. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ የሸይጣን መፀዳጃ አትሁን፡፡ በአንድ ወቅት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ እስከሚነጋ ድረስ ሌሊቱን ስለሚተኛ ሰው ተወራ፡፡ ይህኔ እሳቸው እንዲህ አሉ፡- “ያ በጆሮዎቹ ውስጥ ሸይጣን ሽንቱን የሸናበት ሰው ነው!” አሉ፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 644] 3. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ያለበለዚያ የሸይጣን ወጥመድ ሲሳይ ትሆናለህ፡፡ ቀንህን ሙሉ ድብርት ይጫጫንሃል፣ ንቃት ይቀልሃል፡፡ ፈጅር ላይ ተነስቶ ውዱእ አድርጎ ያልሰገደ ሰው ቆሻሻ ነፍስ ይዞ እንደሚያነጋና ስንፍና እንደሚጫጫነው ተናግረዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 4. ፈጅርን ስገድ ያለበለዚያ በቀብርህ ውስጥ እስከ እለተ ቂያማ የሚዘልቅ ዘግናኝ ስቃይ ትሰቃያላህ፡፡ ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተላለፈው አንድ ሰው ተንጋሎ ሌላው ካጠገቡ ቋጥኝ ይዞ በመቆም እራሱን ይደቁሰዋል፡፡ ድንጋዩ ተንከባሎ ሲሄድም እሱን አምጥቶ እስከሚመለስ ድረስ እራሱ እንደነበር ይመለሳል፡፡ ከዚያም እንደ መጀመሪያው ይሰራበታል፡፡ ቂያማ እስከሚቆም ድረስም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል፡፡ ይህን በዚህ መልኩ የሚሰቃየውን ሰውየ ምንነት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጂብሪል ሲጠይቁት “ይሄ ቁርኣንን ይዞ ፊት የሚነሳው ከግዴታ ሶላትም የሚተኛ ነው” አላቸው፡፡ ወንድሜ ሆይ! ከፈጅር ሶላት አትዘናጋ፡፡ ወቅቱን ጠብቀህ እንድትሰግድ የሚያግዝህን ብልሃትም ተጠቀም፡፡ 1. በጊዜ ተኛ፡፡ የምሽት ወሬ ይቅር፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዒሻ በፊት እንቅልፍ፣ (ከዒሻ) በኋላ ደግሞ ወሬ ይጠሉ ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 2. ቀኑን በወንጀል ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ወንጀል ከኸይር ስራ ያቅባል፡፡ በሌላ በኩል ለኸይር ስራ ትጋ፡፡ ኢስላማዊ የመኝታ ስርኣቱን ጠብቅ፡፡ የኸይር ስራ አንድ ሽልማቱ ለሌላ ኸይር ስራ መታደል ነውና፡፡ 3. ማታ ከመተኛትህ በፊት ለፈጅር ለመነሳት ቁርጠኛ ውሳኔ አድርግ፡፡ ረጅም ጉዞ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ ቢኖርብህ ያለ ማንም አጋዥ ምናልባትም ያለአላርም እየነቃህ ለሶላት ሲሆን መዘናጋትህ ስለእውነት ከባድ የሞራል ልሽቀት ነው፡፡ 4. ማንቂያ ደወል (አላርም) ተጠቀም፡፡ ምናልባት ሳይታወቅህ አጥፍቶ የመተኛት አጉል ባህሪ ካለብህ ትንሽ ራቅ አድርገህ አስቀምጠው፡፡ 5. በሰአቱ ነቅተህ ከተጫጫነህ “ትንሽ ተኛ” ለሚሉ ሸይጣን እና ነፍስያ ሸንጋይ ጉትጎታ እድል አትስጥ፡፡ መነሳትህ ያለውን ዋጋ፣ መተኛትህ ያለውን አደጋ ላፍታ አስብ፡፡ ብትነሳ 50 ዶላር ይሰጣል ቢባል የሚኖርህን ንቃት ቃኝና እራስህን ታዘብ፡፡ ፈርዱ ቀርቶ ትርፍ የሆነችዋ የፈጅር 2 ረከዐ እንኳን ከዱንያ ፀጋ ሁሉ በላጭ እንደሆነች እራስህን አስታውስ፡፡ 6. በመልካም የሚያግዝ ጓደኛ ወይም የህይወት አጋር ካለህም እሰየው፣ ተጠቀምበት፡፡ @yasin_nuru @yasin_nuru
Show all...
የአላህን እዝነት ተመልከቱ!! 🍂ከቁርኣን አንድ ሀርፍ የቀራ ሰው 10 አጅር ያገኛል። «አሊፍ፣ ላም፣ ሚም» ያለ ሰው 30 አጅር ያገኛል። 🍂«ቁል ሁወ‘ላሁ አሀድ»ን የቀራ ሰው የቁራኣንን 1/3 እንደቀራ ይፃፍለታል። 🍂ሰላሳ አያዎችን ያላትን «ሱረቱል ሙልክ»ን የቀራ ሰው… ታማልድለታለች፣ ወንጀሉም ይማራል። 🍃አላህን ሚያስታውስ ሰው አላህ ያስታውሰዋል። 🍃በአላህ መንገድ ከመግደልና ከመገደል በላይ ዚክር ማድረግ በላጭ ነው። 🌴ሱብሀነላህ፣ አልሀምዱሊላህ፣ ክኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር… ፀሀይ ከወጣባቸው ቦታዎች ባጠቃላይ በላጭ ናቸው። የጀነት ተክሎችም ናቸው። 🍃100 ጊዜ ሱብሀነላሂ ወቢሀምዲሂ ያለ ሰው… ወንጀሉ የበህር አረፋ ቢያህል እንኳን ይማርለታል። 🍃100 ጊዜ ‘ላ ኢላሀ ኢለላህ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሀምዱ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይዒን ቀዲር’ ያለ ሰው… 10 ባሪያ ነፃ እንዳወጣ ይያዝለታል። 100 ወንጀል ይማርለታል፣ 100 ምንዳ ያገኛል፣ ከሸይጣን ይጠበቃል፣ ማንም የሱን ያህል ምንዳ አያገኝም እሱ ያለውን ያህል ያለ ወይም ከሱ በላይ ያለ ሰው ሲቀር። 🌴‘ላሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ’ የጀነት ተክል ነው። በነቢዩ ላይ አንዲትን ሰለዋት ያወረድ አላህ በሱ ላይ 10 ያወርዳበታል። 🌼ውዱእን አስውቦ ያደረገ ሰው ወንጀሉ ይማርለታል። ፊቱን ሲታጠብ በአይኑ ያየው ወንጀሉ ይገርፋል። እጁን ሲታጠብ በጁ የሰራው ይወጣል፣ እግሩን ሲታጠብ በእግሩ ወደ ወንጀል የሄደበት ወንጀሉ ይጠራል። (ከወንጀል ጠርቶ እስኪወጣ ድረስ።) 🌼ቤቱ ውድዕ አድርጎ ወደ መስጂድ የሚሄድ ሰው በአንድኛው እርምጃው ወንጀሉ ይታበሳል፣ በሌላኛው አጅር ይፃፍለታል። ውዱኧን፣ ኩሹኧን፣ ሩኩኣን አስተካክሎ ዋጂብ ሰላትን የሰገደ ሰው ያለፈው ወንጀሉ እንዳለ ይማርለታል። (ከባኢሮች ሲቀሩ።) 🌼ውዱእ ሳይፈታ እዛው የሰገደበት ቦታ ላይ የዘወተረ ሰው… መላኢካዎች ምህረትን ይጠይቁለታል። ‘አላህ ሆይ! ማረው፣ አላህ ሆይ! እዘንለት!’ ይላሉ። 🌼ኢሻን በጀመኣ የሰገደ ሰው ሌሉትን ግማሽ እንደቆመ ይፃፍለታል፣ ፈጅርን በጀመኣ የሰገደ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ እንደሰገደ ይፃፍለታል። በፈጅርና በኢሻ ውስጥ ያለን ምንዳ ሰዎች ቢያውቁ ኖሮ በእንብርክካቸውም ቢሆን ይመጡ ነበር። 🌼የፈጅር ሱና ከዱንያን ውስጡ ካለው ነገር ባጠቃላይ በላጭ ናት። 🌼በአላህ ላይ ምንዳውን ተሳስቦ ለይልን የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ እንዳል ይሰረያል። ⚡️ፆመኛን ያስፈጠረ ሰው… የፆሚን ምንዳ ያገኛል። @anbeb_islamic
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram