cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ድንቃ ድንቅ ኢስላማዊ ወጎች👌👌

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች በዚህ ቻናል ድንቅ ኢስላማዊ ወጎችን እንዲሁም ለናንተ ይጠቅማሉ ያልናቸውን ኢስላማዊ ታሪኮች እናቀርብላችኋለን

Show more
Advertising posts
204
Subscribers
-124 hours
-27 days
-530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Sheikh Mishary Rashid Al-Afasy😍😍
Show all...
🛑👉ወንድም አስተውለሀል? ~ ☞ አድካሚውና አሰልቺው ስራህ፦ የብዙ ስራ አጦች ምኞት ነው !!ዘወትር የሚያናድህ ልጅህ፦ የብዙ መሀኖች ህልም ነው!!ትንሿ ጎጆህ ፦ የሁሉም ተፈናቃዮች ምኞት ናት !! ☞ ጤናህ ፦የብዙ ህመምተኞች ህልም ነው!! ፈገግታህ፦ የብዙ ጭንቀታም ጭምቶች ምኞት ነው!አንተ ብቻ የምታውቀው ገመናህ፦ውርደት አንገት ያስደፋቸው ሁሉ የቁጭት ምኞት ነው!ከሀራም ርቀህ በዲንህ መፅናትህ፦የአንዳንድ ወንጀለኞች የሩቅ ምኞት ነው !! ታድያ ምን አጣህ!? የአላህን ፀጋዎች ቆጥረህ ስለማትዘልቅ አመስግን እንጂ አታማር!!             وَآتَاكُمْ مِنْ كُلِّ مَا سَأَلْتُمُوهُ ۚ وَإِنْ تَعُدُّوا نِعْمَتَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ إِنَّ الْإِنْسَانَ لَظَلُومٌ كَفَّارٌ «ከለመናችሁትም ሁሉ የሰጣችሁ ነው፡የአላህንም ጻጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ ሰው በጣም በደለኛ ከሓዲ ነው!» ኢብራሂም 34 አላህ ሆይ! ስለ ፀጋዎችህ ሁሉ እናመሰግንሀለን!!   = 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
Show all...
ቢስሚላሂ ረሕማኒ ረሒም - መልካም ምክሮች 1- ቀንህን ከምትጀምርባቸው ነገሮች ሁሉ ዚክር እና ሶላት ምርጦቹ ናቸው!! 2- ወንጀል ብትሰራም ባትሰራም ምላስህ ሌት ተቀን አላህን እስቲግፋር ከመጠየቅ አይቦዝን! 3- በዱዐ አትዘናጋ ለመዳን ወሳኙ መሳሪያ እሱ ነውና!! 4- ከመናገርህ በፊት ቃላቶችህን የሚፅፉ መላኢካዎች አጠገብህ እንዳሉ አትዘንጋ!! 5- ትልቅ ማእበል ቢያጋጥምህ እንኳ አሁንም መውጫ እንዳለህ አስብ!! 6- አለንጋ ጣቶችህ የበለጠ የሚያምሩት ዚክር ላይ ሲሳተፉ ነው!! 7- ለዱዐ ምላሽ የምታገኝበትን እድል ሐራም በመብላት አትዝጋው!! 8- የመጥፎ ጥርጣሬ አባዜ ከሌለብህ ደስተኛ ሁነህ ትኖራለህ!! 9- በጋዜጣና በሞባይል ፍቅር ከመውደቅህ በፊት በቁርአን ፍቅር ውደቅ!! 10- የሰው ልጅ ነፍሱ አመፀኛ ናትና በአላህ ትዛዝ ላይ አስገድዳት!! 11- ያንተ አሮጌ ልብሶች ለድሃ አዳድሶች ናቸው!! 12- ምድርን ስትሰናበት ካንተ ጋራ መቃብር የሚገባ ስራ ይኑርህ!! 13- ሀሜተኛ ሰው ካጋጠመህ 'አላህን ፍራ' ለማለት አትፍራ!! 14- ህይወት በተፈጥሮ ውብ ናት፣ ከኢማንና ከተስፋ ጋር ደግሞ እጅግ ውብ ናት!! 15- የምትቸኩልለት ነገር ሁሉ ከሶላት የሚበልጥ አይደለምና ተረጋግተህ ስገድ!! 16- ህይወት እኛ ከምንገምተው በላይ በጣም አጭር ናትና ከዚህም ከዚያም ጋር አትጋጭ!! 17- የጭንቀት ሁሉ መንስኤው ከአላህ ﷻ መራቅ ነውና በተቻለህ አቅም ከአላህ ላለመራቅ ሞክር!! @yasin_nuru @yasin_nuru
Show all...
የመርሳት ሱጁድ የሱጁድ አስ'ሰህው ትርጓሜ የመርሳት ሱጁድ በመርሳት ምክንያት ሶላቱ ውስጥ የተከሰተውን ጉድለት ለማካካስ ሰጋጁ የሚያደርጋቸው ሁለት ሱጁዶች ናቸው፡፡ የመርሳት ሱጁድ ምክንያቶች የመርሳት ሱጁድ ምክንያቶች ሦስት ናቸው ፡- ጥርጣሬ፣ ጭማሬና ጉድለት 1 - ጥርጣሬ ጥርጣሬ ከሁለት ነገሮች መካከል የትኛው ይሆን የተከሰተው ብሎ ማመንታት ነው፡፡ ሶላትን በተመለከተ ጥርጣሬ በሁለት ይከፈላል ፡- 1 - ሶላቱ ካበቃ በኋላ የሚሆን ጥርጣሬ ለዚህ ዓይነቱ ጥርጣሬ ትኩረት አይሰጥም፡፡ ምሣሌው ፡- አንድ ሰው ከፈጅር ሶላት በኋላ ሁለት ረክዓ ነው ወይስ ሦስት ነው? ብሎ መጠራጠር ነው፡፡ እርግጠኛ ሆኖ በተረጋገጠለት ነገር ከመስራት ውጭ ለዚህ ጥርጣሬ ግምት አይሰጥም፡፡ 2 - ሶላቱ ውስጥ እያሉ የሚፈጠር ጥርጣሬ ይህ ጥርጣሬ ከሁለት ሁኔታዎች አንዱ ነው ፡- ሀ- ከሁለት ነገሮች ውስጥ አንዱን አመዛኝ ሆኖ ማግኘት በዚህ ሁኔታ አመዛኝ ሆኖ በተገኘው መሰረት በመፈጸም ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ምሣሌው ፡- አንድ ሰጋጅ ዙህር በመስገድ ላይ እያለ ሁለተኛው ረክዓ ነው ወይስ ሦስተኛው ነው? ብሎ ተጠራጥሮ ሦስት ነው የሚለውን አመዛኝ ሆኖ አገኘው፡፡ በዚህ ሁኔታ ሦስት ነው ብሎ ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው የነቢዩ ﷺ ቃል ነው ፡- ‹‹አንዳችሁ በሶላቱ ከተጠራጠረ ትክክለኛውን ለማወቅ ጥረት ያድርግ፤ከዚያም ሰላምታ ይበልና ሁለት ሱጁድ ይውረድ፡፡›› [በእብን ሒባን የተዘገበ] ሰላምታ ይላል የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል ለ- ከሁለት አንዱም አመዛኝ ሆኖ አለመገኘት በዚህ ሁኔታ በአነስተኛው ቁጥር ላይ ተሞርክዞ ሶላቱን በማጠናቀቅ የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ምሣሌው ፡- አንድ ሰጋጅ ዙህር በመስገድ ላይ እያለ ሁለተኛው ረክዓ ነው ወይስ ሦስተኛው ነው ብሎ ተጠራጥሮ ሁለቱም አመዛኝ ሳይሆኑ ይቀራሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ በአነስተኛው ቁጥር ላይ ተመስርቶ ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በፊት የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው የነቢዩ ﷺ ቃል ነው፡- ‹‹አንዳችሁ በሶላቱ ከተጠራጠረና ሶስት ይሆን አራት ስንት እንደ ሰገደ ካላወቀ፣ ጥርጣሬውን ወደ ጎን ያድርግ፣ አመዛኝ ሆኖ ባገኘው ላይ ይመስርት፤ከዚያ ከሰላምታ በፊት ሁለት ሱጁድ ያድርግ፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ] የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል ሰላምታ ይላል 2 - ጭማሬ ይህ ሰጋጁ በሶላቱ ውስጥ ሩኩዕ ወይም ሱጁድ፣ . . ወዘተ. የመጨመር ሁኔታ ነው፡፡ ጭማሬው ከሚከተሉት ሁለት ሁኔታዎች አንዱ ከመሆን አያልፍም ፡- ሀ- ሰጋጁ በማድረግ ላይ እያለ ጭማሪውን የሚያስታውስበት ሁኔታ፡፡ ይህ ከሆነ ከድርጊቱ መታቀብ ግዴታ ይሆንበታል፡፡ ከዚያ ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ምሣሌው ፡- አንድ ሰጋጅ ዙህር በመስገድ ላይ እያለ አምስተኛ ረክዓ ለመስገድ ተነስቶ ከቆመ በኋላ ጭማሪ መሆኑን ያስታውሳል፡፡ በዚህ ሁኔታ ወዲያውኑ ተመልሶ በመቀመጥ ሶላቱን ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡ ከሰላምታ በኋላ የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ለ- ሰጋጁ በመጨመር ላይ እያለ ጭማሪውን የሚያስታውስበት ሁኔታ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ያደርጋል፡፡ ለዚህ ማስረጃው ከእብን መስዑድ (ረዐ) የተላለፈው የሚከተለው ሐዲስ ነው ፡- ‹‹ነቢዩ ﷺ ዙህርን አምስት ረክዓ ሰገዱና ‹በሶላቱ ጭማሬ ተደረገ ወይ?› ተብለው ተጠየቁ፡፡ ምን ተደረገ? ሲሉ ‹‹አምስት ነው የሰገዱት›› ተባሉና ከሰላምታ በኋላ ሁለት ሱጁድ ወረዱ፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ] 3 - ጉድለት ይህ ሰጋጁ ከሶላት ማእዘናት ወይም ከግዴታዎቹ አንዱን ማእዘን ወይም አንዱን ግዴታ የማጓደል ሁኔታ ነው፡፡ 1 - የማእዘን ጉድለት ይህ ማእዘን የእሕራም ተክቢራ ከሆነ ሶላቱ ውድቅ ነው፣ ሶላቱ ከነአካቴው አልተመሰረተምና፡፡ ጉድለቱ ከእሕራም ተክቢራ ውጭ ካሉት ማእዘናት አንዱ ከሆነ ሁኔታው ከሚከተሉት ሁለት ሁኔታዎች አንዱ ከመሆን አይዘልም ፡- ሀ- ሰጋጁ በቀጣዩ ረክዓ ላይ በተረሳው ማእዘን ላይ ከደረሰ በኋላ ያስታወሰ መሆን፡፡ ሁኔታው ይህ ከሆነ ማእዘኑ የጎደለበትን ረክዓ ውድቅ አድርጎ በቀጣዩ ረክዓ ይተከዋል፡፡ ምሣሌው ፡- አንድ ሰጋጅ በመጀመሪያው ረክዓ ሩኩዕ ረስቶ በሁለተኛው ረክዓ ሩኩዕ ላይ መርሳቱን ያስታውሳል፡፡ በዚህ ሁኔታ አሁን ያለበትን ረክዓ የመጀመሪያው ረክዓ አድርጎ በመውሰድ የበፊተኛውን ረክዓ ውድቅ አድርጎ ሶላቱን ያሟላል፤ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ሰላምታ ይላል የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል ለ- ሰጋጁ በቀጣዩ ረክዓ ላይ በተረሳው ማእዘን ላይ ከመድረሱ በፊት ያስታወሰ መሆን፡፡ እዚህ ላይ ወደ ተተወው ማእዘን ተመልሶ በማከናወን ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በኋላ የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ምሣሌው ፡- በመጀመሪያው ረክዓ ላይ ሁለተኛውን ሱጁድና ከርሱ በፊት ያለውን መቀመጥ ረስቶ ከሁለተኛው ረክዓ ሩኩዕ ቀና ካለ በኋላ ያስታወሰ ሰው ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ተመልሶ በመቀመጥ ሱጁድ ይወርድና ሶላቱን በማሟላት ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ 2 - የዋጅብ ጉድለት አንድ ሰጋጅ ከሶላት ዋጅቦች ውስጥ አንዱን ዋጅብ ከረሳ ሁኔታው ከሚከተሉት ሦስት ሁኔታዎች አንዱ ከመሆን አያልፍም ፡- ሀ- የተረሳውን ዋጅብ ቦታ ለቆ ወደ ሌላ ሳይተላለፍ ያስታወሰው መሆን፡፡ በዚህ ሁኔታ ዋጅቡን መፈጸም ነው፤ሌላ ነገር አይኖርበትም፡፡ ለ- ሰጋጁ በሶላቱ ውስጥ የተረሳውን ዋጅብ ቦታ ለቆ ወደ ሌላ ከተላለፈ በኋላ ወደ ቀጣዩ ማእዘን ከመድረሱ በፊት ያስታወሰው መሆን፡፡ በዚህ ሁኔታ ወደ ተወው ተመልሶ በመፈጸም ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በኋላ የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ሐ- ወደ ቀጣዩ ማእዘን ከደረሰ በኋላ ያስታወሰው መሆን፡፡ እዚህ ላይ ሶላቱን ይቀጥላል፤ወደዚያ ተመልሶ አይሄድም፡፡ ከሰላምታ በፊት የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ምሣሌው ፡- በሁለተኛው ረክዓ ከሁለተኛው ሱጁድ ተሸሁድን ረስቶ ለሦስተኛው ረክዓ ተነስቶ ቀጥ ብሎ ከመቆሙ በፊት መርሳቱን ያስታወሰ ሰጋጅ ነው፡፡ ይህ ለተሸሁድ ተቀምጦ ሶላቱን ያሟላል፣ ማካካሻ የለበትም፡፡ ተነስቶ ከቆመ በኋላና ቀጥ ብሎ ሙሉ በሙሉ ከመረጋጋቱ በፊት ካስታወሰ ለተሸሁድ ተመልሶ ይቀመጥና ሶላቱን ያሟላል፤ ከሰላምታ በኋላ የማካካሻ ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ሙሉ በሙሉ ተረጋግቶ ከቆመ በኋላ ካስታወሰ ግን ተመልሶ አይቀመጥም፡፡ ሶላቱን ያሟላና ከሰላምታ በፊት የመርሳት ሱጁድ ይወርዳል፡፡ ለዚህ ማስረጃው ከዐብዱላህ ብን ቡሐይና (ረዐ) የተላለፈው የሚከተለው ሐዲስ ነው ፡- ‹‹ነቢዩ ﷺ ዙህርን አሰገዷቸውና በመጀመሪያዎቹ ሁለት ረክዓዎች ሳይቀመጡ ተነስተው ቆሙ፤ሰውም አብሯቸው ተነስቶ ቆመ፡፡ ሶላቱ ሲያበቃ ሰው ሰላምታ ይላሉ ብሎ ሲጠብቅ አል’ሏሁ አክበር ብለው ሁለት ሱጁድ ወረዱና ሰላምታ አሉ፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ] ካለፈው የምንረዳው የመርሳት ሱጁድ ከሰላምታ በፊትና ከሰላምታ በኋላም የሚደረግ መሆኑን ነው፡፡ የመርሳት ሱጁድ አደራረግ የመርሳት ሱጁድ (ሱጁድ አስ’ሰህው) ከመደበኛው የሶላት ሱጁድ ጋር አንድ ነው፡ ሲወርዱና ቀና ሲሉም ተክቢራ ይደረግበታል፡ በሱጁዱ ውስጥና በሁለቱ ሱጁዶች መካከከል የሚደረገው ዝክርም አንድ ዓይነት ነው፡፡ ▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬ https://t.me/dnqadnqwegoch
Show all...
የትራፊዎች (ኣሳር) ትርጓሜ ፈሳሽ ትራፊዎች ሌላ ጠጪ ጠጥቶለት እቃ ውስጥ ያስቀረው ትራፊ ጭላጭ ነው፡፡ ለነጃሳነቱ ማስረጃ ካልቀረበበት በስተቀር ፈሳሽ ትራፊዎች (ኣሳር) በመሰረቱ ንጹሕ (ጣህር) ናቸው፡፡ ዝርዝሩ ይቀጥላል፡- ንጹሕ የሆኑ ትራፊዎች ሀ- የሰው ልጅ ጠጥቶ ያስቀረው ትራፊ ነቢዩ ﷺ፣ ዓእሻ (ረዐ) የወር አበባ እያለባቸው ጠጥተው ያስቀሩትን ትራፊ ይጠጡ እንደ ነበርና አፋቸውንም የዓእሻ አፍ አርፎ በነበረበት ቦታ ላይ ያደርጉ እንደ ነበር በሐዲስ ተረጋግጧል፡፡ [በሙስሊም የተዘገበ] ለ - የድመት ትራፊ (ሱእር) ከእቃ የጠጣችውን ድመት አስመልክተው ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ነጃሳ አይደለችም፣ በዙሪያችሁ ከሚሆኑ ገርና ጥንቁቅ አገልጋዮች ናት፡፡›› ብለዋል፡፡ [በትርምዚ የተዘገበ] የድመት ትራፊ ሐ- ሥጋቸው የሚበላ እንስሳት፣ የበቅሎ፣ የአህያ፣ ሥጋ በል አዳኝ አራዊት፣ አዳኝ አሞራዎችና የመሳሰሉት እንስሳት ትራፊ፡- የነዚህ እንስሳት ትራፊ ንጹሕ ነው፡፡ ነጃሳ ስለመሆናቸው ማስረጃ ባለመኖሩና ነገሮች ተቃራኒው ካልተረጋገጠ በመሰረቱ ንጹሕ በመሆናቸው የነዚህ እንስሳት ትራፊ ንጹሕ ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ በአህያ ይቀመጡ ነበር፡፡ በዘመናቸው አህያ ለማጓጓዣነት ታገለግል ነበር፡፡ የአዳኝ አሞራ (አዕዋፍ) ትራፊ የአህያ ትራፊ የአዳኝ አውሬ ትራፊ ሥጋው የሚበላ እንስሳ ትራፊ ውሃ ነጃሳ የሆኑ ትራፊዎች ሀ - የውሻ ትራፊ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ያንዳችሁን ዕቃ ውሻ በአፉ (ምላሱን በማስገባት) ከለከፈው የሚጸዳው (ዕቃውን) ሰባት ጊዜ አንደኛውን ዙር በአፈር በማጠብ ነው፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ለ- የአሳማ ትራፊ የአሳማ ትራፊ (ሱእር) ነጃሳ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እርሱ ርኩስ ነውና . . . ›› [አል-አንዓም፡145] ከርሱ የወጣ ነገርም ነጃሳ ነው፡፡ የአሳማ ትራፊ የሰው ልጅ ንጹሕ (ጣህር) መሆኑ የሰው ልጅ፣ ነቢዩ ﷺ፡- ‹‹ሙእምን ሰው አይነጅስም፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ባሉት መሰረት ሙስሊም በራሱ ንጹሕ (ጣህር) ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ ሙሽሪክ ከሆነች ሴት የውሃ ስልቻ ዉዱእ ማድረጋቸው የተረጋገጠ [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] በመሆኑ ሆነ ካፍርም በራሱ ንጹሕ (ጣህር) ነው፡፡ ‹‹አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፤›› [አል-ተውባህ፡28] የሚለው የአላህ ቃል ሕሊናዊ ርክሰት ማለትም የእምነታቸውን ነጃሳነት የሚመለከት ነው፡፡ ▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬ https://t.me/dnqadnqwegoch
Show all...
أذكار الصباح ولمساء
Show all...
ታላቁ የዘመናችን ዓሊም ኢማም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦ «እውቀትን ስታሰራጭ የአላህን ሀይማኖት እያሰራጨህ ነው ስለዚህም በአላህ መንገድ ከሚታገሉት ታጋዮች ትሆናለህ! ምክንያቱም ታጋዩ በሰይፍና በኢማን ሀገርን እንደሚከፍት ሁሉ አንተም በእውቀት የሰዎችን ልብ ትከፍታለህና» [ሸርህ ዱዓዑ ቁኑቲል ዊትር /(ገፅ)12]
Show all...
ሀቲመል አሰም እንዲህ ይላል ድህነትን አትፍራ አላህ በእሳት አስፈራርቶሀል; በድህነት ግን አላስፈራራህም [አልፈዋኢድ ወልአኽባር ሊብኒ ሀመካን ▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬ https://t.me/dnqadnqwegoch
Show all...
ድንቃ ድንቅ ኢስላማዊ ወጎች👌👌

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች በዚህ ቻናል ድንቅ ኢስላማዊ ወጎችን እንዲሁም ለናንተ ይጠቅማሉ ያልናቸውን ኢስላማዊ ታሪኮች እናቀርብላችኋለን

ሸሪአዊ እውቀት ሸይኽ ዑሰይሚን እንዲህ ይላሉ፦ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ እንኳ ቢሆን መስኣላዎችን ለማወቅ ብሎ ኩቱቦችን ያነበበ፤ ልክ ሸሪኣዊ እወቀት ለማግኘት ብሎ ጉዞ እንዳደረገ ይቆጠርለታል ። 【ሸርሑ ሪያዱ ሳሊሂን (5/434 )】 ኢማሙ ሻፊኢይ(ረሂመሁላህ) ለዕውቀት የነበራቸውን ጉጉት እና ፍቅር ሲገልፁ፦ የሰውነት ክፍሎቼ በሙሉ ጆሮዬ ዒልም ሳደምጥ የማገኘውን ለዛ ቢጋሩኝ ስል እመኛለሁ። ይላሉ። አላህ በሸሪኣዊ ዕወቀት ላይ ያበርታን! የሸይጣን ምክትል ማን እነደሆነ ታውቃላችሁን?! ኢብኑል ቀዪም(ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ በምድር ላይ የሽይጣን ምትኮች ማለት:- ሰዎችን ሸሪዓዊ ከሆኑ ዕወቀት እንዳይገበዩ ዐቀበት የሚሆኑ ሰዎች ናቸው። እንደነዚህ አይነት ሰዎች ከጂን ሸይጣኖች የበለጠ ሰዎችን ይጎዳሉ፣ምክንያቱም በልቦናዎች እና ቅን በሆኑ በአላህ መንገዶች መካከል ጋሬጣዎች ናቸውና። ፨ 【ሚፍታሑ ዳሩ ሰዓዳ(1/170)】 ▬▭▬▭▬▭▬-▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭ https://t.me/dnqadnqwegoch
Show all...
ከፈጅር በኋላ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦  “የፈጅርን ሶላት በጀማዐ የሰገደ ከዚያም ፀሀይ እስከሚወጣ ድረስ አላህን እያወሳ የተቀመጠ እና ከዚያም ሁለት ረከዐ ሶላት የሰገደ። ልክ እንደ ሐጅና ዑምራ አጅር አለው፡፡ 📚 ሶሂህ አልጃሚዕ: 6346 🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
Show all...