cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የፍቅር ቃል

እንኳን በሰላም ወደ ቤታችሁ ማለቴ ወደ ቻነላቹ መጣችሁ። የፍቅር ቃል ሁሉም ውስጥ አለ ከምንም በላይ ልቤ ውስጥ በሰፊው አለ ። መመሰጥ ሙዱ ለሆነ ሰው ተመራጭ ቻናል አፍቅር ቃል። 😂 ሃሳብ ሃስተያየት ካላቹ👉 @Kokeeet ደሞ #no ጅንጀና ዋ

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
189
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

-- 🌼 🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ቀን ቀረው ። #እንኳን_አደረሳችሁ_መልካም_አዲስ_ዓመት
Show all...
ሰላም ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች እንዴት ከረማችሁ እንዴትስ አደራቹ። ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን እያለን ወጣቶች ተደራጅተው ስለከፈቱት ስለ አንድ ድርጅት በትንሹ ላውጋቹ። EYODA ብለው ሰይመውታል ቃሉ ሲፈታ (Ethiopia youth opportunity) ነው። ይህ አዲስ ድርጅት ወጣቶች ለወጣቶች ጥሩ እድሎችን የሚከፍቱበት በሮች እንደሆኑ ተረድቻለሁ። ለዚህ አዲስ ድርጅት አዲስ እንደመሆኔ መጠን ስለድርጅቱ የምለው ይህን ያህል ነው። ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው እና ከፍተኛ ፍላጎት ለፈያላቸውን ወጣቶች የሚደግፍ እን።ሆነም ተረድቻለሁ። በኢኮኖሚው በማህበራዊው እና በፋይናንሽ ዘርፍ ትልቅ እድል የሚሰጥ Company ነው። ይህን ወጣቶች ለወጣቶች company ለመቀላቀል እና የለውጡን ውጤት መቋደስ ለምትፈልጉ ወጣቶች @yanealemyihenew በዚ ያግኙኝ። መልካም እድል።
Show all...
የሌት ማሕሌት (በእውቀቱ ስዩም) ትንሽ ቆየት ብሎ ፥ ኮረንቲው ይጠፋል እሱን ተከትሎ፥ደምኖ ያካፋል ከናፍቆትሽ በቀር፥ ሁሉ ነገር ያልፋል :: አሁን መብራት ጠፋ ፥ ተረኛ ነን አይደል ቁና ይዠ ቀረብሁ፥ ጨለማ ሲታደል ፤ እያገላበጠ ብቻነት አመሰኝ፥ “ ዝናቡ እየጣለ ጋራ ጋራውን ጎርፍ ያመጣሽ ‘ንደሁ ልጠብቅ ጎርፉን “ የሚል እንጉርጉሮ፥ በድንገት ታወሰኝ :: ግን ይሄ ትውስታ አራራይ ትዝታ ለቆሰለው ልቤ፥ መዳኒት አልሆነም ያባቶቼ ዘፈን፤ ለኔ አልተዘፈነም፤ ማዶ ዝናብ ዘንቧል፤ ዶፉን ተከናንቧል- -እንጦጦ-ዲልዲላ በገፈጅ ይመስል ፥ቀበናም ቢሞላ ምንም አያመጣም፤ ከ’ድፍ ውሀ ሌላ እሳት ነው ፍጥረትሽ፥ ከውሃ ጋ አትኖሪም አንቺ መብረቅ እንጂ፥ ጎርፍ አትሳፈሪም:: ( አዳምኤል) ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! @AdamuReta @AdamuReta
Show all...
አንዷ በ Inbox ይህን post አይታ "ዘመናዊ እስር ቤት መባሉን ሰምተው ይሆን" 😂😂😂😂 አይ ዲያብሎስ ተጫወተብን ኮ
Show all...
ለፍልሰታ ፆም ሱባኤ የገባቹ ወገኖቼ ሆይ ግን በማርያም ምን አስባችሁ ነው online እየገባቹ ስልክ እያወራቹ እና ቲክስት እየተላላካቹ ያላችሁት?? እዛ መግባታችሁ ኮ ከአለም ሸሽታችሁ ከፈጣሪ ጋር መሆን በመፈለጋችሁ ነው። ማርያምን ልቦናውን ይስጣችሁ።
Show all...
Ewyyyyyyy🥺💋🥰 @mahinaqueen 🦋🦋
Show all...
መጣና ባመቱ ኧረ አንደምን ሰነበቱ ክፈት በለው ተነሳ ይህን አንበሳ ክፈት በለው በሩን የጌታዬን ሆያ ሆዬ ሆ ሆያ ሆዬ ሆ ኧረ እዚህ ቤቶች ሆ እንደምን ናችሁ ሆ በአመት አንድ ቀን ሆ መጣንላችሁ ሆ በአመት አንድ ቀን ሆ ለመጣ እንግዳ ሆ ምሳው ሙክት ነው ሆ እራቱ ፍሪዳ ሆ ሆያ ሆዬ ጉዴ ጨዋታ ነው ልማዴ 👇👇👇 @yefikrbet33✨✨🥀
Show all...
አረጀው መሰል ቀንም ጠፍቶብኛል። የሆኑ የሰፈር ታዳጊዎች በዛ ብለው ከቤታችን በራፍ ላይ የያዙትን እንጨት እና ቆሮኬ እያንካኩ በመሪያቸው አማካይነት ይዘምራሉ። በሩን ከፍቼላቸው ገብተው እናቴ የሰጠቻቸውን ሙልሙል በልተው ከኔ 10 ብር ተቀብለውኝ በደንብ መርቀውኝ ሄዱ። መስጠት ልማዴ ሆኖ እንጂ ልጆቹ የመጡት ለቡሄ ይሁን ለመስቀል ይሁን እንጃ ብቻ ምርቃታቸውን ተቀብዬ ወደ ቤቴ ስመለስ ትዝ ሲለኝ . . . ለካ ነገ ቡሄ ነው😂😂 እንኳን አደረሳችሁ
Show all...
#ለመኖር_የተከፈለ_ዋጋ ከላይ በምስሉ ላይ የምትታየው ሴት ማሪ አን ቢቫን ትባላለች። እንስቷ በዘመኗ በተደረገ ውድድር ተወዳድራ ቁጥር አንድ አስቀያሚ ሴት የሚል 'ክብር' አግኝታለች። ወዳጆቼ የዚችን ሴት የታሪክ ድርሳን ስትመረምሩ ውብ የሆነ ስብዕና ይታያችኋል። እስኪ ታሪኳን አብረን እንየው። ማሪ አን አክሮመጋሊ በሚባል በአጋጣሚ በጣም በጥቂት ሰዎች ላይ በሚከሰት 'ህመም' ተጠቂ ሆነች። አክሮመጋሊ የአካል ክፍልን የተዛባ ዕድገት የሚፈጥር እና የፊትን ቅርፅ የሚያበላሽ ነው። 'በዕንቅርት ላይ ጆሮ ገድፍ' እንዲሉ የማሪ ህይወት ውስብስብነት ባሏን በሞት ስታጣ እየባሰ መጣ። የማሪ ባል ሲሞት በቤት ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ ጠፋ። የብድር ዕዳ ቁልል በየዕለቱ እየጨመረባት ከመምጣቱም በተጨማሪ ብቻዋን ማሳደግ ያለባትን አራት ልጆቿን ዳቦ ለማብላት ኑሮ ሲዖል ሆነባት። ማሪ ግን በድሏ ማማረርና ማልቀስ ለልጆቿ ዳሞ ስለማይገዛላት ቆም ብላ በማሰብ አማራጮችን ፈተሸች። በወቅቱ በሚካሄደው "የአስቀያሚዎች ውድድር" ለመወዳደር ወሰነች። ይታያችሁ በዛ ዘመን በዚህ ውድድር የሚሳተፉት ለሰዎች መሳቂያና መሳለቂያ ከመሆን ባሻገር በማህበረሰቡ የሚደርሰው ማህበራዊ ተፅዕኖ ከባድ ነበር። ግን የልጆቿን ፍላጎት ማሟላት ግቧ አድርጋ ለተነሳችው ማሪ ሁሉንም በፅናት ለመቋቋም አልከበዳትም። በውድድሩም "የዓለማችን አስቀያሚዋ ሴት" አሸናፊ ሆና የገንዘብ ሽልማት ከማግኘቷም ባሻገር በአንድ የሰርከስ ክለብ ተቀጥራ በየከተማው በመዞር ሰርታለች፡ የሰዎች ስላቅ፣ ትችት፣ ስድብና ወዘተ ተቋቁማ ፈጣሪ የሰጣትን "አስቀያሚነት" በፀጋ መንገድ ቀይራ ልጆቿን አሳደገች። ማሪ በፈረንጆቹ 1933 ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች። #መውጫ የሰው ልጅ ሰውን በቅርፁ፣ በአቋሙና በመልኩ መገምገሙን ትቶ በአፉ እንደሚለው "ውስጣዊ" ውበትን ቢያይ.... የማሪን አካል ትተን ነፍሷን፣ ስብዕናዋን፣ ፅናቷን እና እናትነቷን ካየን ከሷ የበለጠ ማን ቆንጆ አለና...... ❤️❤️❤️ via Good Lives መልካም ምሽት Tsita neng https://t.me/abakiyak
Show all...
የፍቅር ቃል

እንኳን በሰላም ወደ ቤታችሁ ማለቴ ወደ ቻነላቹ መጣችሁ። የፍቅር ቃል ሁሉም ውስጥ አለ ከምንም በላይ ልቤ ውስጥ በሰፊው አለ ። መመሰጥ ሙዱ ለሆነ ሰው ተመራጭ ቻናል አፍቅር ቃል። 😂 ሃሳብ ሃስተያየት ካላቹ👉 @Kokeeet ደሞ #no ጅንጀና ዋ

#ለመኖር_የተከፈለ_ዋጋ 👇👇👇👇👇👇👇👇
Show all...