en
Feedback
TeddyAfroFans Officialወደፍቅር

TeddyAfroFans Officialወደፍቅር

Open in Telegram

እንኳን ወደዚህ ግዙፍ ወደ ሆነው ''ወደ ፍቅር . . .'' ቻናል በደህና መጡ ይህ ቻናል በቴዲ አፍሮ ወዳጅ ቤተሰቦች የተመሰረተ ሲሆን ባለቤትነቱም በቴዲ አፍሮ #Teddy_Afro እውቅና ባለው ''ወደ ፍቅር . . . ''ማህበር አባላትና መስራቾች ነው ፡፡ ፍቅር ያሸንፍል !!

Show more
536
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-130 days
Posts Archive
ካራማራ የካቲት 26 / 1970 ዓ.ም "ይህ ነው ምኞቴ እኔ በህይወቴ ከራሴ በፊት ለኢትዮጵያ እናቴ " ክብር የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ላስከበሩ ጀግኖች አርበኞቻችን 💚💛❤️🙏 #የካራማራ_ድል_47
+1
ካራማራ የካቲት 26 / 1970 ዓ.ም "ይህ ነው ምኞቴ እኔ በህይወቴ ከራሴ በፊት ለኢትዮጵያ እናቴ " ክብር የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ላስከበሩ ጀግኖች አርበኞቻችን 💚💛❤️🙏 #የካራማራ_ድል_47ኛው_ዓመት #የካቲት_26__1970_ዓም_የተገኝ_ድል #የካራማራ_ድል #ኢትዮጲያ #Ethiopian #victory Teddy Afro Teddy Afro Fans #ወደፍቅር . . . #ክብር_ለውዲቷ_የኢትዮጵያ_ልጆች 🟩🟨🟥🙏 የካቲት 26/2017ዓ.ም

ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ 🚨 ይህ የ ተወዳጆ አርቲስት Adanech Weldgebriel (አዲ)መልዕክት ነው❗️ ሰላም ሰላም ወንድም እህቶቼ 🙏በጣም የረበሸኝን ነገር ለመግለፅ ነው የ ቴሌግራም አካዉ
+3
ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ 🚨 ይህ የ ተወዳጆ አርቲስት Adanech Weldgebriel (አዲ)መልዕክት ነው❗️ ሰላም ሰላም ወንድም እህቶቼ 🙏በጣም የረበሸኝን ነገር ለመግለፅ ነው የ ቴሌግራም አካዉንቴ ሀክ ተደርጎ በስሜ ገንዘብ ልመና እያደረጉ ስለሆነ እኔ አለመሆኔን እንድታዉቁልኝ ለመግለፅነዉ በኔ የደረሰዉ አይድረስባችሁ ተጠንቀቁ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ተመልከቱት 🙏🙏🙏 Teddy Afro Fans #ወደፍቅር . . . #followers #helight

በቀደምት ጀግኖች አያቶቻችን ታላቅ ተጋድሎ እና መስዋዕትነት እንዲሁም በታላቁ ታሪክ የማይረሳው ንጉሳችን ዳግማዊ አጤ ምንሊክ እና በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ብልህ አመራር እና አስተባባሪነት ለተቀዳጀነው አ
በቀደምት ጀግኖች አያቶቻችን ታላቅ ተጋድሎ እና መስዋዕትነት እንዲሁም በታላቁ ታሪክ የማይረሳው ንጉሳችን ዳግማዊ አጤ ምንሊክ እና በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ብልህ አመራር እና አስተባባሪነት ለተቀዳጀነው አንፀባራቂው የ፻፳ ወ፱ኛው የአድዋ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን ሳስተላልፍ በታላቅ ብሔራዊ ኩራት ነው:: ይህ በታሪክ ተመዝግቦ በየአመቱ የምንዘክረው አድዋ ላይ የተቀዳጀነው ድል የኢትዮጵያን ነፃነት ያስከበረ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ የቅኝ ግዛት ቀንበር ተጭኗቸው ሲሰቃዩ ለነበሩ አፍሪካዊያን ወንድም እና እህቶቻችን እንዲሁም በመላው አለም በጭቆና ውስጥ የነበሩትን ጥቁር ህዝቦች ቀና ብለው እንዲሄዱ እና ነፃ እንዲወጡ በወቅቱ ታላቅ መነቃቃትን የፈጠረ ገናና የጥቁር ህዝቦች ድል ነው። የዘንድሮውን የ፻፳ ወ፱ ኛው የአድዋ ድል በአል ስናከብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ቀላል ለማይባሉ አመታት አንድነቷን አስጠብቃ ወደ ፊት እንዳትራመድ ሰቅዞ የያዛትን ተከታታይ የብሔር ፖለቲካ አዙሪት እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ ያስከፈለንን እና እያስከፈለን ያለውን ዋጋ ግምት ውስጥ በማስገባት ካለንበት ውስብስብ እና እጅግ ኋላቀር የዘር ፖለቲካ ለመውጣት ከመቼውም ጊዜ በላቀ አንድነታችንን አስተባብረን የህልውናችን መሰረት የሆነችው እናት ሀገራችንን ለማዳን በንቃት መቆም ይጠበቅብናል። <<ምንሊክ ጥቁር ሰው!>> ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

1,457,000.00 ( አንድ ሚልየን አራት መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ ) ብር ለመቄዶንያ በለንደን ከተማ በተካሄደው የንጉሱ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ከታዳሚዎች እና ከአስተባባሪዎች የተገኘውን 8,300 ፓውንድ (1,457,000.00 ብር) አዘጋጆቹ ወደ መቄዶንያ አካውንት ገቢ አድርገዋል። ክብር ይገባቹሃል እናመሰግናለን!! 💚💛❤️🙏 Teddy Afro Amleset Muchie #ወደፍቅር Teddy Afro Fans #መቄዶንያ #seifufantahunonebs

Tonight London, England 🇬🇧 Ethiopia ,Gonder Gonder , Mar Eske Tuwaf , Tikur Sew, TamTaram, Africaye, Feran, Janehoye, Bashaw, JiJino......Don't miss it❗️ Teddy Afro Amleset Muchie Teddy Afro Fans #ወደፍቅር . . .

ንጉሱ በሰላም London, England 🇬🇧 ገብቶል February 15/2025 በፍፁም አይቀርም ❗️ Teddy Afro Teddy Afro Fans #ወደፍቅር Amleset Muchie

እንደ ቴዲ አፍሮ የተሳረ ፣እንደ ቴዲ አፍሮ ብዙ የመንግስት ጫና የተደረገበት ፣እንደ ቴዲ አፍሮ የህዝብ ብሶትን በአደባባይ ያወጣ ፣እንደ ቴዲ አፍሮ ስለ ሀገር ፍቅር ፣ስለ ባንድራ ክብር እና በገሀድ መንግስት የሚያደርገው የአፈና እና የጭቆና መረብ የተቃወመ ዘፈኛ በኢትዮጵያ ታሪክ የለም።እሱ በእዚህ ረገድ ፈር ቀዳጅ ነው። ቴዲ አፍሮ ዘፋኝ ብቻ ሳይሆን የሰበዓው መብት ተከራካሪ ነው ይሉታል ነጮቹ።ሌላው እንደ ቴዲ አፍሮ በኢትዮጳያ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ተወዳጅ አርቲስት የለም።ስራ በመደመጥ ፣አልበም ሽያጭ ፣ትላልቅ የአለማችን ሚዲያዎች እና መላዊ ኢትዮጳያን የሚያንቀጠቅጥ ሰው አይተን አናውቅም። ሙዚቃ ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን መልዕክቱ እና ቅድሚያ ለሚስጠው ቅድሚያ መስጠቱ ነው ብለን ካመንን ቴዲ አፍሮ ቀዳሚ ነው። ለእኔ ከአንዲት የሴት ልጅ ውበት ከማዜም ስለ ሀገር ወቅታው ሆኔታ መዝፈን ጋር አላወዳድረውም።ጨርቅሽ ፣ቁመናሽ ፣አለባበስሽ ፣አካሄድሽ ከሚለው የሚቀድመው ይቺ ሴት የምትኖርበት ሀገር ነው።ሀገር እየፈረስ ስለ ምንትስ መዝፈን በሀገር እና እናት ላይ ቀልድ ነው።በአፓርታይድ ጊዜ ስለ ፍቅር አይዘፈንም ስለ ሀገር እንጂ ፣ዮጎዥላቪያ ስትፈርስ አፍቅርሻለው የሚል ዘፈን አይሰማም ከተሰማ ግን ቀልድ ነው። ሀይማኖት እኩል በልሆነበት ፣የገዢ መደብ ባለበት ፣እኩልነት እና ፍትህ ብዙ ባልተረጋገተበት በ50 ዎቹ የኖሩ ኮከብ አርቲስቶቻችን ምን አሉ? ምንም… … መልሱ ይሄ ነው።ታዲያ በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ ቢያንስ እንካን አንድ ዘፈን ይጠፋል።አንድ አርቲስት አልተቃወመም። የያኔው ስርዓትን የሚተች አልነበረም? አንድም ዘፋኝ ንጉሱን አልተናገረም? በአንድ ዜማም የህዝብ ስሜት አልተገለፀም? ወይስ ዘፋኝ ከሀገር እና ፖለቲካ ነፃ ነው! በጭራሽ ጥበብ ጊዜን ካላሳየች ጥበብ ጥበብ አትባልም።ለዚህም ነው የያነው ዘፈኖች ድንቆችም ቢሆኑ ሁሉን ያማከለ አይደለም የምለው።ሀገር ስታለቅስ ዘፋኝ ይስቃል ፤ ገበሬ ይረገጣል ጨፍሪ የሚል ሙዚቃ ይለቀቃል።የደርግ ስርዓት ላይ መንግስቱ ስለ ሀገር ፍቅር ስለሚሞት አንዳንዶች በጉልበት ይዘፍኑ ነበር ።ሰውየውን ስለሚፈሩት በስራቸው ወደው ተገደቀወ ሀገሬ ብለዋል ።ግን መንግስቱ የሰራው ሰራ ከበዓሉ ግርማ ውጪ የተናገረ አለ? የለም… …ለዚህ ነው ዘፋኝ ማለት ከሙዚቃ በላይ ሲሆን አፄ ነው የምለው። ቴዲ አፍሮ አፄ ነው ቴዲ አፍሮም በሙዚቃ ቃና ስለ ሀገር ፍቅር ፣ስለ ሀገር አንድነት ፣ስለ ባንድራ ፣ስለ አብሮ መኖር ፣ስለ መንግስታት ድክመት ፣ስለ ህዝብ የፍትህ እና ሁለንተናዎ ቀውስ ተናግሯል።በሙዚቃ የትኛውም መሪ ሆነ ገዢ ሀገሩ ላይ ግፍ ሲሰራ አልፈራም።ለሀገሩ የማይሆነው ስርዓት በተወዳጅ ድምፁ እና ዜማው ነግሮናል።በኢትዮጵያ ማንንም አይፈራም።ናገሩም አይደራደርም።ታዲያ ሌላ ዘፋኝ አለ እንደ እሱ የሆነ? እንደ እሱ ስለ ሀገር ምንነት እና የታሪክ አዋቂ አለ እንዴ! አይታሰብም።እሱ የሚያደርገውን አንዱ ለማድረግ የደፈረ ዘፋኝ የለም። ኦላን ይዞ እያለ ኦራል ይዞ የሚዞር መንግስት ተችታል ፤ ያስተስርያል እያለ ለውጥ ያለመኖሩን ተናግራል ፣ ሼመንደፍር ብሎ የሀይማኖት ጣልቃ ገብነት ይቁም አለ ፣ አኛናቱ ብሎ ለኦሮሞ የኖረ ፣ዶርዜ ፣አፋር ፣ናት ባሮ ጋንቤላ ፣አደይ ትግራይ ፣ዳክላክ ኤርትራ……እረ ብዙ አለ።ለሀገር ዋልታ የሆኑት ቴዎድሮስ ፣ሚኒልክ ፣ጃንሆን እና የሀገር ታሪክን የበረበረ እና ለገዢው መንግስት ወቀሳን ተው ያሰኘ……ብላቴማው በፍቅር ግጥሙ እንኳን ሀገሩን አይረሳም። ታዲያ አንድም ዘፋን ያለው ዘፋኝ ከተባለ ቴዲ አፍሮም ዘፋኝ ከተባለ የሚያስቅ እና የማያሳምን ጨወታ ይሆናል ። # ሀገሬ ቲዮብ

ቴዲ አፍሮ ዘፋኝ ብቻ ሳይሆን የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ነው ይሉታል ነጮቹ ❗️ ሙዚቃ በድምጸቱ ልዩ ዉበት ያለውና በስው ልቡና ውስጥ ሰርስሮ ሊገባ የሚችል ኃይል እንዳለው በርካቶች ይስማሙበታል ። በ
ቴዲ አፍሮ ዘፋኝ ብቻ ሳይሆን የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ነው ይሉታል ነጮቹ ❗️ ሙዚቃ በድምጸቱ ልዩ ዉበት ያለውና በስው ልቡና ውስጥ ሰርስሮ ሊገባ የሚችል ኃይል እንዳለው በርካቶች ይስማሙበታል ። በጥቂት ምጥን ቃላት ብዙ ነገሮችን አምቆ በመያዝ ለሰዉ ልጅ ቅርብ በሆነና የስሜት ሕዋሳትን በቶሎ የሚደርስ ቃናዉ በሚነካ የሚመስጥ ምቱ ስልቱ የትውልዶችን ፍስሃ እና ምሾ አትሞ እና ቀርጾ የሚያሻግር የሰው ልጅ ሁለንተናውን የሚነድፍበት፣ ስሜቱንና አመለካከቱን የሚቀርጽበት ኪነጥበብ ዘርፍ መሆኑን ምሁራን ያብራራሉ ይህን መሰረታዊ ሀሳብ በዜማዎቻቸዉ እንድናይ ካደረጉት መካከል ቴዲ ቀዳሚዉ ነዉ ። ቴዲ አፍሮ ብቻ ያለው! ቴዲ አፍሮ የሙዚቃው አለም ከተቀላቀለበት የመጀመሪያ አልበሙ አቦጊዳ እስከ አሁን ድረስ ስለ አንድ ኢትዮጳያ ፣ስለ ባንድራ ፣ስለ ፍቅር እና ወቅታዊ ሀገራዊ ማንነት ላይ በሙዚቃ ያለቅሳል ፤ ያስደምጠናል።ቴዲ አፍሮ የኢትዮጳያን ታሪክ ለመጪው ትውልድ በሙዚቃ ያስተማ እያስተማረ ያለ ብቸኛ ዘፋኝ ነው። ለስሩ ነገስታት ያዜመ… የሀገር ጀግኖችን ክብር የሰጠ እና አንድ ኢትዮጳያ ላይ ፅኑ አላማ ያለው ወጣት አቀንቃኝ ነዉ ቢባል ማጋነን አይሆንም። አረንጓዴ ፣ብጫ እና ቀይ አርማ ከእጁ ያልተለየው ፣ለባንድራው ዘፍኖ የማይጠግብ ነው።በጥንታዊ ኢትዮጰያ ያሉ አፄዎች እና ስራዎቻቸው የሚያነሳ ብቸኛ እሱ ነው።ዘመናዊ ሙዚቃ ጨፍሪ … ነይልኝ …ሙቺልኝ ፣…አበድኩልሽ ከሚሉ የዘፈን ግጥሞች ውጪ የሆነ አርቲስት ነው። ስለ ሀገሩ በዘፈነ ፣ስለ ባንድራው ስለዘፈነ አስከፊ እንግልት ፣እስር እና በሀገሩ የፈለገው ማድረግ እንዳይችል ቢደረግም ፍቅር ያሸንፋል ብሎ ሆዱ እየከፋው እኛን ያስደስታል። በግል ህይወቱ የመጣበት ፈተና ለሀገሩ ሲል የተሸከመ ያሳለፈ ነዉ።

ለገንቢ፣ አስተማሪና አወያይ ሐሳብ መድረኩ ክፍት ነው። ጥላቻ፣ ከንቱ ንግግርና እንቶ ፈንቶ እስከ ወዲያኛው ብሎክ ያስከትላል። #ሙሼ_ሰሙ ቴዲ አፍሮ ለሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የተደረጉና የሚደረ
ለገንቢ፣ አስተማሪና አወያይ ሐሳብ መድረኩ ክፍት ነው። ጥላቻ፣ ከንቱ ንግግርና እንቶ ፈንቶ እስከ ወዲያኛው ብሎክ ያስከትላል። #ሙሼ_ሰሙ ቴዲ አፍሮ ለሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የተደረጉና የሚደረጉ ትግሎችን በማገዝ ትልቅ ሚና የነበረውና እምቅ አቅም የፈጠረ አንጋፋ አርቲስት ነው። ሙዚቃዎቹ ፍቅርና ሰላምን የሚቀኙትን ያህል ጀግንነትን አወድሰዋል፣ ታሪክን ከትበዋል፣ ግፈኞችን አውግዘዋል፣ ከስልጣን ፊት ቆመውም ስልጣንን ፊት ለፊት ተጋፍጠዋል። የአማራ ሕዝብ መከራና ስቃይ፣ ስደትና መፈናቀል የሁላችንም ሕመምና ስቃይ ነው። ሰላም ሰፍኖ መከራውና ስቃዩ እንዲቆም ከልብ እንመኛለን። ይህም ሆኖ ግን ሌ'ት ተቀን አስረሽ ምቺው በሚደለቅበትና ሃያ አራት ሰዓት እሽኮለሌ በሚባልበት ሀገር ቴዲ አፍሮ ስራውን ስለ ሰራ ብቻ በተለይ ተመርጦ የሚወገዝበት አንዳችም ምክንያት የለም። ምክንያት አለ ከተባለም መወገዝ ያለብን አውጋዦቹን ጭምር የእለት ከእለት ስራችንን የምንሰራ ሁላችንም መሆን አለብን። ቴዲ አፍሮ ሙዚቀኛ እንጂ የእለት ከእለት ፓለቲከኛም ሆነ ታጋይ አይደለም። ቴዲ አፍሮን በሙያውና በስራው መደገፍም ሆነ አለመደገፍ መብት ነው። አይመለከተኝም። ነገር ግን ፣ የእለት ከእለት ስራውን በትጋትና በንቃት እንደሚሰራ ማንኛውም ዜጋ ቴዲ አፍሮ ስራውን ስለሰራ፣ ስራህን አትስራ ማለት ግን ፖለቲካ ሊሆን አይችልም። Teddy Afro Amleset Muchie #ወደፍቅር Teddy Afro Fans

ከ Amleset Muchie የካቲት 1 ለሚጀመረው የገቢ ማሰባሰቢያ የመጀመሪያውን የ ማስጀመሪያ ድጋፍ በእኔና በቤተሰቤ ስም አበርክተናል እናንተም የበኩላችሁን አስተዋጻኦ እንድታደርጉ ጥሪዬን አስተላል
ከ Amleset Muchie የካቲት 1 ለሚጀመረው የገቢ ማሰባሰቢያ የመጀመሪያውን የ ማስጀመሪያ ድጋፍ በእኔና በቤተሰቤ ስም አበርክተናል እናንተም የበኩላችሁን አስተዋጻኦ እንድታደርጉ ጥሪዬን አስተላልፍለሁ::የካቲት 1 በሰይፉ በ ebs youtube Channel ይጠብቁን:: #amlesetmuchie #mekedoniya Teddy Afro #ወደፍቅር Teddy Afro Fans

ንጉሱ ትናንት ምሽት በትዝታው ንጉሥ ማህሙድ አህመድ መኖሪያ ቤት ከባለቤቱና ከወዳጆቹ ጋር በመገኘት፣ በወርቅ የተጻፈ የማህሙድ የስሙ የመጀምሪያ ፌደል (M) ያለበትና መተጣጠፊያዎቹ ላይ በወርቅ ቀለበቶች የተጌጠ ከዘራ አበርክቶለታል ሁሌም ታላላቆቹን የሚያከበር ይከበራል ይሄ ደግሞ ለንጉሱ የህይወት መመሪያው የሁልጊዜም ተግባሩ ነው ። ክበርልን🙏 https://vm.tiktok.com/ZMkgQY8Wc/

#ሜሪ እና #ጥሌ በድጋሚ መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ ከ ወደፍቅር ማህበር Teddy Afro Fans "ቤትና ባለጠግነት ከአባቶች ዘንድ ይወርሳሉ ፥ አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት" ምሳሌ
#ሜሪ እና #ጥሌ በድጋሚ መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ ከ ወደፍቅር ማህበር Teddy Afro Fans "ቤትና ባለጠግነት ከአባቶች ዘንድ ይወርሳሉ ፥ አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት" ምሳሌ 19፥14 ➠ ጋብቻችሁ የተባረከ ፣ የሰመረ ፣ በፍቅር የተሞላ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን። ሙሽራዎች ውለዱ ፥ ክበዱ 💞። ቀሪው ዘመናችሁ የተባረከ ይሁን። የሙሽራው እና የሙሽሪት ቤተሰቦችም እንኳን ደስ አላችሁ። መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ 💞🙏💞 Teddy Afro Amleset Muchie Meron Daniel Adanech Weldgebriel

በዛሬው ዕለት በደማቅ የጋብቻ ስነ-ስርዓት ትዳራቸውን እየፈፀሙ ለሚገኙት ልበቀናዋ፣የንጉሱ የልብ ወዳጅ ለሆነችው እና ለወደ ፍቅር ማህበር አባል ጎደኛችን Meron Daniel እና ለባለቤቶ አቶ ጥላሁ
በዛሬው ዕለት በደማቅ የጋብቻ ስነ-ስርዓት ትዳራቸውን እየፈፀሙ ለሚገኙት ልበቀናዋ፣የንጉሱ የልብ ወዳጅ ለሆነችው እና ለወደ ፍቅር ማህበር አባል ጎደኛችን Meron Daniel እና ለባለቤቶ አቶ ጥላሁን መልካም ጋብቻ እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን 🙏 የአብርሃም እና የሳራ ትዳር ይሁንላችሁ ትዳራችሁን እግዚያብሄር ይጠብቅላችሁ መልካም ጋብቻ 🎂🍾 Teddy Afro #ወደፍቅር Teddy Afro Fans

የንጉሱ ወላጅ እናት ጥላዬ አራጌ (ራዬ)እና ባለ ደግ ልቧ አርቲስት ገጣሚ እና ፕሮሞተር አዳነች ወ/ገብርኤል (አዲ)የንጉሱ የሙያ እናት ለመጀመሪያ ጊዜ አቅሙን ችሎታውን ተገንዝባ አቅጣጫ ያሳየችው ።
የንጉሱ ወላጅ እናት ጥላዬ አራጌ (ራዬ)እና ባለ ደግ ልቧ አርቲስት ገጣሚ እና ፕሮሞተር አዳነች ወ/ገብርኤል (አዲ)የንጉሱ የሙያ እናት ለመጀመሪያ ጊዜ አቅሙን ችሎታውን ተገንዝባ አቅጣጫ ያሳየችው ። ሁለቱ ፈርጦች ከብዙ ያልተሰሙ ታሪኮቻቸው ጋር የልብ ወግ ላይ የ ጥምቀት እለት እሁድ ከ ቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በ Maya Media ይጠብቋቹሃል እንዳያመልጦ። Teddy Afro Amleset Muchie Teddy Afro Fans #ወደፍቅር . . .