👉 የነሲሐዎች ማንነት በመረጃ ሲረጋገጥ
ክፍል ሁለት
ነሲሐዎች ድሮ በተለይ ናጂያ ኢስላማዊ ማህበር በነበረበት ጊዜ ዐቂዳቸው የሰለፎች ዐቂዳ ነበር። ዳዕዋቸውም የሰለፍያ ዳዕዋ ነበር በወቅቱ ከኢኽዋንና ሱፍይ ጋር ሲደረግ በነበረው ትግል ትልቁን ድርሻ ይወጡ ስለነበር ሱና ወዳዱ ማህበረሰብ በተለይ ወጣቱ ባጠቃላይ ከጎናቸው ነበር።
በኪራይ ቤት የነበረው የናጂያ ማህበር ስሙን ወደ ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር በመቀየር ሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያለው የሱና ተከታይ ይህን ብቸኛ የሰለፍይ ተቋም ወደራሱ ማእከል ለማሸጋገር የቻለውን ዋጋ ከፍሎ ህልሙን እውን አደረገው።
ይህ ሁሉ ሲሆን በተለይ ናጂያ በነበረበት ጊዜ ያለ ምንም ልዩነት ዳዒዮች በሙሉ ወደ ሰለፍያ ነበር የሚጣሩት። ለዚህም ትልቁ ማረጋገጫ ኢኽዋኖች በዶ/ር ጀይላን መሪነት ከሱፍዮች ጋር የአንድነት ስምምነት ባደረጉበት ጊዜ በአዩብ ደርባቸው ይመራ የነበረው ናጂያ ስምምነቱ ባጢል መሆኑን ትልቅ የረድ ፕሮግራም አዘጋጅቶ በሚገርም መልኩ ረድ ማድረጋቸው ነው። ረዱን የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ያዳምጡ : –
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/bahruteka/2012
ይህ እንግዲህ ያኔ የነበሩበት አቋም ነው። ነገር ግን በዶ/ር ጀይላን የተዘረጋው ናጂያዎችን ከዚህ አቋማቸው የማለዘብ መረብ ቀስ በቀስ ኢልያስ አሕመድን በዶ/ሩ እውቀት እንዲሸነገልና የሱ አድናቂ እንዲሆን በማድረግ ስራውን ጀመረ። በአጭር ጊዜ ውጤታማ ሆነ። ኢልያስ አሕመድም የዶክተሩ አድናቂ ሆነ።
በወቅቱ የነበረው የአሕባሽ ዘመቻ ወርቃማ እድል የሰጠው የሀገራችን የኢኽዋን አንጃ ድምፃችን ይሰማ የሚል ንቅናቄ ጀመረ። ኢልያስ አሕመድና ሳሊሕ አሕመድ በድምፃችን ይሰማ ንቅናቄ ውስጥ ለመስላሓ በሚል ስም ገቡ ንቅናቄውን ይመራው የነበረው የኢኽዋን አንጃ በኮሚቴ ካካተታቸው የናጂያ ዱዓቶች አንዱ የነበረው ኢልያስ አሕመድ ፊት ለፊት ሳይቀርብ በውስጥ ስራውን ይሰራ ጀመር።
በወቅቱ አብዛኛ በገንዘብ ሲደግፋቸው የነበረው ነጋዴና ብዙ ዳዒዎች በድምፃችን ይሰማ መረብ እንዲገቡ ሰበብ ሆነ። ሳሊሕ አሕመድም የተለያዩ መረጃዎችን ለአል ጀዚያ በማቀበል ከኢኽዋን መሪዮች ጋር ግልፅ ያሆነ ግንኙነት ነበረው ። ኢኽዋኖች አጋጣሚውን በደንብ ተጠቀሙበት። ናጂያ አካባቢ የኢኽዋንን ስም ማንሳትና ከእነርሱ ማስጠንቀቅ የናጂያ ሰዎችም ዘንድ እንደወንጀል ይታይ ጀመር ።
የናጂያ መሪ የነበሩት አዩብ ደርባቸው፣ ኢልያስ አወልና ሳሊሕ አሕመድ በግልፅ በዚህ ሳአት ተሕዚር ከተደረገ በአሕባሽም፣ በመንግስትና ኢኽዋን ላይ ነው መደረግ ያለበት እንጂ ኢኽዋንን ነጥሎ ማድረጉ ትክክል አይደለም የሚል ከእንጀራ አባቶቻቸው የተሰጣቸውን የእንቅልፍ ክኒን ለተከታዩ መስጠት ጀምሩ ።
ይህ በሸይኻቸው ኢልያስ አሕመድ የተሰጠ ተልእኮ እንደነበር ኡማ ሆቴል ላይ ከተጠቀሱት መሪዮች ጋር ረዥም ውይይት ባደግንበት ጊዜ ቃበቃል ሲደግሙልኝ ነበር ያወቅሁት።
በጣም የሚገርመው ውይይቱን ጨርሰን ልንለያይ ስንቆም ለሳሊሕና ኢልያስ አወል" አሹሙ ፊኩማ ራኢኸተል ኢኽዋን" በሁለታችሁ ላይ የኢኽዋንይነት ሽታ አሸትባችኋለሁ ብያቸው መለያየታችን ነው ። በዚህ መልኩ የመርከዙ ሰዎች ወደ ኢኽዋንይነት ጉዞ ቀጠሉ
የናጂያ ማህበር ወደ ኢብኑ መስዑድ ተቀይሮ 18 ተዘዋወረ። ከዚህ በኋላ የኢልያስ አሕመድ ቀስ በቀስ ከኢኽዋኖች መሪ ደ/ር ጀይላን የተሰጠው የቤት ስራ በተከታዮቻቸው ላይ መስራት ተጀመረ።
ከየክፍለሀገሩ ዱዓቶች ይጠራሉ ሰፊና እንዲቀሩ ተደርጎ ስለጠሀራ ይጠየቁና መመለስ ሲያቅታቸው ይህን ሳታውቁ እገሌ እንዲህ ነው እያላችሁ ሑክም ትሰጣላችሁ በሚል ከኢኽዋን እንዳያስጠነቅቁ ተደረጉ። በዚህ መልኩ የተለያየ ሙሓደራና ኮርስ ተጠናክሮ ቀጠለ። ኢኽዋኖች ከመርከዙ ሰዎች ስጋት ነፃ ሆኑ። ከመሪዮቹ አልፎ ተከታዩም ወደኢኽዋን ሚንሀጅ እንደሚመለስ እርግጠኛ ወደ መሆን ደረሱ።
የመርከዙ ሰዎች ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ ሰላሳ ምክሮች ለወሰን አላፊዮች በሚል ሰለፍያን ያንኮታኮተ የኢኽዋንን አንጀት ያራሰ ኮርስ ሰጠ። በወቅቱ ወሰን አላፊ የተባሉት በዋነኝነት እነኢብኑ ሙነወር ነበሩ።
የዶ/ር አብይ ስርኣት ሙስሊሞች አንድ ሆነው መጅሊሳቸው በአዋጅ ህጋዊ እውቅና እንዲያገኝ እንደሚፈልግ ለኢኽዋን መሪዮች ነገራቸው። የኢኽዋን መሪዮች ወርቃማ እድል አገኙና ለመርከዙ ሰዎች ሚናቸውን እንዲለዩ ጥሪ አቀረበላቸው። መጀመሪያውኑ የተደመሩት የኢብኑ መስዑድ መሪዮች ይህን እንደጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው ከየክፍለሀገሩ ዱዓቶችን ጠርተው ተደምረን መጅሊሱ ላይ ካልገባን የበይ ተመልካች ነው የምንሆነው አሉ። አብዛኛው ከክፍለሀገር የመጡ ዱዓቶች ይህ ማለት ትላንት ስታወግዙት ወደነበረው የኢኽዋንና ሱፍይ አንድነት መግባት ነው ብሎ ኢንካር አደረገባቸው። ነገር ግን የመርከዙ መሪዮች እኛ የጠራናችሁ ልናሳውቃችሁ እንጂ እናንተ አይሆንም ስላላችሁ ልንተወው አይደለም የሚል ተስፋ አስቆራጭ ውሳኔ አስተላለፉላቸው። መጅሊስ ውስጥ ስለመግባት ስለመደመሩ የነበረው ውይይት ሳሊሕ አሕመድ ምን እንደ ተናገረ የሚከተለውን ሊንክ ተጭነው ያዳምጡ፦
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://drive.google.com/file/d/125XMYNitElGDvV5oAxdBN4xVXVWL26xM/view?usp=drivesdk
በዚህ መልኩ የመርከዙ መሪዎች ነፃነታቸውን አውጀው ከኢኽዋን፣ ከአሕባሽና ሱፍይ ጋር ተደመሩ። ለዚህ ተልእኮ መርከዙን ወክለው የተሳተፉት አዩብ ደርባቸውና ቡሽራ ነበሩ። በምን መልኩ ቃል ኪዳን ገብተው እንደተደመሩ በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ይመልከቱ፦
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️➡️⤵️
https://drive.google.com/file/d/10Mq2oeszIhe4o5FvYmGG612OjQlImwOR/view?usp=drivesdk
ይህን ቃል ኪዳን እነካሚል ሸምሹ በምን መልኩ እንደመሩት አሁንም በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ይመልከቱ፦
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://drive.google.com/file/d/109n8FkxP66G15bepsKDlHw-Ug-EWv7do/view?usp=drivesdk
የመርከዙ ሰዎች የተደመሩበት አንድነት መርህ ኢትዮዽያ ውስጥ ሱፍይ ሰለፍይ ኢኽዋንይ የሚባል እንደሌለና ሁሉም የኢትዮዽያ ሙስሊም እንደሆነ በአደባባይ ተነግሮ በተክቢራ አዳራሹ ተናውጦ ነበር የነአዩብ እጅ ለእጅ ተጨባብጦ ቃል ኪዳን መግባት የቀጠለው። ይህን መርህ ዶ/ር አብደላ በግልፅ ሲያስቀምጥ በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ያዳምጡ፦
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://drive.google.com/file/d/12cX-QYGbQxq4ZYIUsQb3J8k-F69nVXIs/view?usp=drivesdk
በዚህ የግፍና የሰለፍያን ዳዕዋ ገሎ ለነኢብራሂም ቱፋ የቀብሩን ስርኣት ለማስፈፀም ለመስጠት የተደረገ ስምምነት በደስታ በሰከረው ኣደም ካሚል ሶስት ኡሉል ዐዝሞች ይዘውት የመጡት ወሕይና ለአማኞች ያጎናፀፈው እድል ዶክተር አብይ ይዞት ከመጣው ዲሞክራሲ በታች ሲደረግና ዑሉል ዐዝሞቹን ደግሞ ከዶክተር አብይ ያሳነሰ የኩፍር ንግግር ሲያደርግ የመርከዙ ሰዎች በታደሙበት ነበር። የኣደም ካሚልን የኩፍር ንግግር በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ያዳምጡ፦
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://drive.google.com/file/d/12QoyaSsJMOdA-hb2EuVcEF6B-I82GNdy/view?usp=drivesdk
አላህ ካለ ገና ጉድ ይወጣል ጠብቁ።
https://t.me/bahruteka