cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

𝐔𝐦𝐮 r𝐞𝐲𝐲𝐚𝐧 a𝐬 s𝐞𝐥𝐞𝐟𝐲𝐚𝐚𝐡

✍ﻭَﻗُﻞ ﺭَّﺏِّ ﺯِﺩْﻧِﻲ ﻋِﻠْﻤًﺎ «ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ በል!

Show more
Ethiopia11 073The language is not specifiedReligion & Spirituality99 815
Advertising posts
190
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-1030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
➴"ኡሙ ሰለማ  رضي الله عنها" ~በጣም የምታፈቅረው  በሏ ሸሂድ በሆነ ሰዓት በጣም ልቧ ተሰብሮ ነበር! #ከዛም_ረሱል  صل الله عليه وسلم ሊያፅናኗት እንዲህ ብለሽ ዱአ አድርጊ አሏት " አሏህ ሆይ ከደረሰብኝ  ችግር ካታጣሁት የተሻለውን ተካልኝ " ብለሽ ዱአ አድርጊ አሏት ኡሙ ሰለማም ከ አቡ ሰለማ የተሻለ ባል የት ሊገኝ አለች 🔹ዱአውን አደረገች አሏህ ደግሞ ከሁሉም የ አደም ልጆች በላጭ የሆኑትን ረሱልን ተካላት።* ➴አያቹ  መተኪያ የላቸውም ብለን ያልናቸው ውድ ነገሮች ሁሉ አሏህ ዘንድ በላጭ በሆኑ  ነገሮች ይተካሉ  ከእኛ የሚጠበቀው #ዱዓእና_ሶብር_ነው..!! አሏህ ከምናስበው በላይ የተሻሉና ያማሩ ውብ ኒዕማዎች (ስጦታዎች) አሉት።         ↷⇣🌹⇣↷ ""
Show all...
Audio from يااااااااااارب
Show all...
AUD-20231006-WA0040.mp35.94 MB
ቆየት ካለ #ሙሐደራ ርዕስ ⤵️ #ይህ_ነው_እውነታው 🎙 በኡስታዝ #ሳዳት_ከማል ሀፊዘሁሏህ እውነታው #የተፍረጠረጠበት ምርጥ #ዳዕዋ ነው ብዙ #ነጥቦች ተዳሰውበታል። ያድሞጡት!!! ⚘
Show all...
4_5778614880265308062.mp318.60 MB
Photo unavailableShow in Telegram
የዛሬ ቀን ረቢአል አወል 12 ነብዩ ﷺ የሞቱበት ነው። ይህን ቀን አመታዊ የደስታ ቀን አድርጎ መያዝ ሰይጣናዊ መንገድ ነው። በኢስላም የሙት አመት የሚባልም ነገርም የለም። በኢስላም የታዘዝነውን ብቻ እንስራ። ከክስረት እንጠበቃለንና። ነብዩ ﷺ "ቢድአ ሁሉ ጥመት ነው" ብለዋል።
Show all...
“መውሊድ”፣ “ክሪስማስ”፣ አሹራ….? *** ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው በላይ አውቀው ነው ወይ? ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ነብይ ተደርገው በተላኩ ጊዜ ነሷራዎችም (ክርስትያኖች) ይሁዳዎችም ነበሩ፡፡ ነሷራዎች የኢሳንም ልደት ሲያከብሩ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የወንድማቸውን ኢሳ ልደት አንድም ቀን አክብረው አያውቁም፡፡ ምክንያቱም በአላህ አልታዘዙምና፡፡ የነብይም ይሁን የሌላ ግለሰብ የልደት በዓል ማክበር የነብያቶች እምነት እስልምና በፍፁም የሚያውቀው አይደለም፡፡ ልደት ማክበር የእስልምና አካልም አይደለም፡፡በሌላ በኩል ሌላኛው ወንድማቸው ነብየላህ ሙሳን (አለይሂ ሰላም) አስመልክቶ የሁዳዎች አሹራን ሲፆሙ አዩ፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሁዳዎችን ለምን እንደሚፆሙ ጠየቁ “አላህ ሙሳን እና የእስራኢል ልጆችን ከፊርዐውን ነፃ ያወጣበት ቀን ነው” ሲሉ መለሱላቸው፡፡ ነብዩም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “እኛ በሙሳ ጉዳይ ከናንተ የበለጠ የተገባን ነን” ብለው አሹራን ፆሙ እንዲፆምም አዘዙ፡፡ እንዲያውም ረመዳን ከመደንገጉ በፊት አሹራ በሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነበር፡፡ ከረመዳን በኋላ ይሀው እኛም የሳቸውን ፈለግ በመከተል እንፆመዋለን፡፡ ልክ እንደዚሁ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ሰኞ ለምን እንደሚፆሙ” ሲጠየቁ “የተወለድኩበት ቀን ስለሆነ እና ቁርዐን እኔ ላይ የወረደበት ቀን ስለሆነ ነው” ብለዋል፡፡ ታድያ ግዴታ ያልሆነ የሱና ፆም አሹራን በአመት አንዴ እንድንፆመው፣ እሳቸው የተወለዱበትን ቀን እና ቁርዓን የወረደበትን ቀን ሰኞ እንዲሁ በሳምንትን አንዴ ሱና ፆም እንድንፆም ነግረውናል፡፡ የሚያሳዝነው አብዛኛው “መውሊድን” አከብራለሁ የሚል ሰው የታዘዘውን በየሳምንቱ የሚፆመውን ሱና ሲፆም አይታይም፡፡ ይልቁንስ ለምሳሌ “የኢስነይን ሰዎች ነን” እያሉ ሰኞ ሰኞ ጉንጫቸውን በአንደንዛዡ ቅጠል ጫት ወጥረው ሲቅሙ እና ሲጨፍሩ የሚውሉ ሸይጧን የተጫወተባቸው አሉ፡፡ በአመት አንዴ ግን ያልታዘዙትን “መውሊድ” ብለው በማክበር “የኢሳ ልደት” ብለው ከሚያከብሩት ሰዎች ጋር ተመሳስለዋል፡፡ የታዘዙትን ትተው ያልታዘዙትን በመስራት ወደ አላህ እዝነት ሳይሆን ቁጣውን ወደሚያከናንባቸው የሰይጣን መንገድ የሚንደረደሩ ሰዎች ምን አለ ቆም ብለው ቢያስቡ? አላህ እኮ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) በመከተል እንጂ ውዴታውን እና ምህረቱን ቃል የገባልን ያላዘዙትን በመስራት አይደለም፡፡ ሸይጧን ደግሞ እንዲህ አሳቢ መስሎ ነው ከጥንት እስከዛሬ ሰዎችን ሲያጠም የነበረው፡፡ አላህ ከተንኮሉ ይጠብቀን፡፡ ሌላው ሰሃባዎች አላህ አማኝ፣ እውነተኞች፣ ወድጃቸዋለሁ እያለ ያወደሳቸው….. ከነሱ መንገድ ውጭ ያለን የሚከተል መንገድ የሳተ፣ ጀሀነምም እንደሚገባ አላህ እና መልክተኛው ነግረውን ሲያበቁ፡፡ ለምን ይሆን መውሊድንም ይሁን ሌሎች ተግባራትን በተመለከተ ሰሃባዎች የቆሙበት ቦታ የማንቆመው? ሰሃባዎች ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በህይወት በነበሩ ግዜም ይሁን ሞተው አንድም ቀን የማንንም ነብይ ይሁን የረሱልን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልደት አክብረው አያውቁም፡፡ ታድያ እኛ ማን ሆነን ነው ሰሃባዎች ያልሰሩትን የምንሰራው? የአላህን ዲን፣ ንፁሁን የነብዩ ሱና በቢድዐ ለማቆሸሽ፣ የሰይጣንን ተልኮ “ነብዩን መውደድ” በሚል ስም ለማሳካት ደፋ ቀና የሚባለው? እውነት ሰሃባዎች ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሳይወዱ ቀርተው ነው የነብዩን መውሊድ ያላከበሩት? ወይንስ እነሱ ለነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላቸው ውዴታ ሸሪዐ በደነገገው መልኩ በገንዘብ፣ በህይወት መስዋትነት እና በሌላም ስለገለፁ ነው? እውነታው እነሱ ስለስርዐት አላቸው፡፡ ይህንን ከሰማይ የወረደ ዲን “እኔ እንደሚመስለኝ” እያሉ ሳይዳፈሩ ያንን ንፁህ ምንም ጭማሪ የማይፈልግ ዲን ለእኛ በሰላም አድርሰዋል፡፡ አላህም ወዷቸዋል፡፡ ዛሬ አላህ ዘንድ ገና ፍርድ ያልተሰጠባቸው ሰዎች ይህን ዲን መጥተው በፈለጉ ጊዜ በቀያየሩት ቁጥር እኛ አብረን የምንቀያየረው አላህን ነው የምናመልከው ወይንስ እነዚህ አላህ ያልደነገገውን የሚደነግጉ ዲን አፍራሾች? መውሊድ የሸሮች ሁሉ መጠራቀሚያ፣ የሙስሊሞችን አንድነት ማፍረሻ፣ የድሆችብ ንብረት መብያ….. እርኩስ ተግባር ነው፡፡ ሙስሊሞች ሆይ! ራቁት፡፡ አይ ሸይጧን በየዘመኑ መጥፎውን ነገር ጥሩ አስመስሎ ስም እየቀያየረ የአደም ልጆችን ያጠማቸዋል፡፡ ወደ እሳትም ይመራቸዋል፡፡ ተመልከቱ አደም እና ሀዋን ያቺን ዛፍ ስሟን አሳምሮ እንዳትበሉ የተባሉትን አስበላቸው ከዛም ስህተት ውስጥ ጣላቸው፡፡ የኑሕን (አለይሂ ሰላም) ህዝቦች በሞቱት 5 ደጋግ ሰዎች ያዘነ መስሎ መቀማመጫቸው ላይ ሀውልት አሰርቶ ገደል ከተታቸው፡፡ የጠፉበትን እርኩስ ተግባር ሽርክ ውስጥ ዘፈቃቸው፡፡ አሁንም ይህን ኡመት “ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላችሁን ውዴት ልደቱን አክብሩለት” የሚመስል የሰይጣን ሹክታ እዚህ ኡማ ላይ ተሰራጭቶ የሽርክ መነሃርያ የሆነውን መውሊድ እያከበሩ ወደ እሳት ሲነዱ ይታያሉ፡፡ መውሊድ ላይ ከባባድ የሽርክ ቃላትን ከእስልምና አስፈንጥረው የሚያስወጡ የሽርክ ተግባራት ይታያሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ አላህን ትቶ ፍጡራንን መለመን፣ እነሱን ድረሱልን ብሎ መጣራት፣ አላህን ትቶ ለፍጡራን ስለት መግባት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ አሳዛኙ ደግሞ ጥመቱን እንደሃቅ፣ ሃቁን እንደ ጥመት ቆጥረው “ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ ሰሀባዎቻቸው፣ ታቢኢኖች፣ አትባኡታቢኢን፣ 4 አኢማዎች፣ ሙሐዲሶች፣ 3 ምርጥ ክፍለ ዘመን እና ትውልድ አላከበረውም” ሲባሉ ሃቁን ከመቀበል ይልቅ ያልታዘዝነውን አንሰራም ያሉትን “ነብዩን የማይወዱ፣ የነብዩ ጠላቶች፣ ወሃብዬች እና ሌላም” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ከድጡ ወደ ማጡ ይሉሃል ይህ ነው፡፡ ሸይጧን ግን ዛሬ ጥፋታቸውን እያሸበረቀላቸው ዲንን በዲን ስም እንዲንዱ እየገፋፋቸው ነው፡፡ ነሷራችን በነብየላህ ኢሳ (አለይሂ ወሰለም) ላይ ድንበር አልፈው “የአላህ ልጅ ነው” እንዲሉ ያደረጋቸው የሰው እና የጂን ሰይጣናት ናቸው፡፡ ነሷራች ኢሳን ድንበር ያለፉበት ጠልተውት ሳይሆን ወደውት ነው፡፡ ግን ድንበር አለፉ፡፡ ከልክ በላይ ከፍ ከፍ አደረጉት፣ ያላታዘዙትን ልደቱን አከበሩለት፡፡ ከዚህም ኡማ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመውደድ ስም ሸይጧን መንገድ አስቷቸው ልክ እንደነሷራች ያልታዘዙትን ልደት ማክበር፣ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “መጣ ያለፈው ወንጀላችንን ማረ”፣ “የሁሉ ቀላቢ”፣ “ልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ” እና የመሳሰሉትን የብቸኛ ፈጣሪና ተመላኪ አላህ መብት አሳልፈው ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመስጠት ታላቁን ማጋራት እና ቢድዐ ሲሰሩ ይታያል፡፡ ሸይጧን መቼም ለሰው ልጎች ከባድ ጠላታቸው ነው፡፡ አላህ ድንበር ከማለፍ፣ ከሽርክ፣ ከቢድዐ እና አላህ ከጠላው ሁሉ ይጠብቀን፡፡ አላህ ወደ ተውሒድ፣ ሱና፣ የሰለፉነ ሷሊሂን አረዳድ፣ እሱ መልካም ወዳለው ሁሉ ይምራን፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ https://t.me/SadatTe
Show all...
Sadatte