cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ALL ETHIO CONTRACTOR & ENGINEER STATION

ከጨረታ እና ስራ ማስታወቂያ በተጨማሪ ለሁሉንም ምህንድስና ነክ ጉዳዮች መፍትሄ የሚሰጥ ፡፡

Show more
Advertising posts
1 753
Subscribers
+824 hours
+377 days
+14630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

_@etconp_የኮንስትራክሽን_ኢንዱስትሪ_ጥራትና_ብቃት_አፈጻጸም.pdf6.56 KB
የሀምሌ_ወር_2016_ዓ_ም_የሀራጅ_ሽያጭ_ማስታወቂያ_1.PDF3.01 MB
Photo unavailableShow in Telegram
#News የኢትዮ ጂብቲ ባቡር ዳንኤል ኃ/ሚካኤል (ኢንጅነር) ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር ( ኢዲአር) ቺፍ ቴክኒካል በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ኢንጂነር ዳንኤል ኃ/ሚካኤል ከሰኔ 21፤2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዉ መሾማቸዉ ተነግሯል ። የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ለኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ በነበሩት አብዲ ዘነበ ( ዶ/ር ) ምትክ ዳንኤልን (ኢንጅነር ) ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንዲሆኑ መመደባቸው ተሰምቷል ።
Show all...
Dear all, The Young Engineers Committee is calling for volunteers to assist in implementation of various proposed committee activities. If you are interested to volunteer please express your interest by filling the following google form.   https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfCiuJrNGfm5KKyQbE2gow9DeM6vyG4XWavM_FszSOjMEmgeQ/viewform
Show all...
Call for Volunteers>>>Shaping the Future of Engineering in Africa!

The FAEO Young Engineers Forum is seeking passionate young engineers from across Africa to join our dynamic volunteer committees. We offer a unique opportunity to develop your skills, network with fellow engineers, and contribute to shaping the future of the engineering profession in Africa. To express your interest, please enter your details.

Photo unavailableShow in Telegram
👉ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ሁለቱን አገሮች የሚያገናኝ 220 ኪሜ ርዝመት ያለው መንገድ ሊገነቡ ነው። 🚧738 ሚሊዮን ዳላር የሚያወጣውን መንገድ ለመገንባት የተስማሙት በ ግንቦት 2023 እኤአ ነበር። ✳️የ ደቡብ ሱዳኑ Transitional National Legislative Assembly (TNLA) የኢትዮ ሱዳኑን የድንበር አቋራጭ መንገድ ግንባታ ስምምነት በ June 25 ያጸደቀው ሲሆን ስምምነቱን ለማጽደቅ ለአገሪቱ መሪ ለፕሬዚደንት ሳልቫኪር  አቅርቦታል። Via የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 👈👈
Show all...
📌 የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ካሣ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁ. 1161/2011
Show all...
የመሬት ካሳ አዋጅ .pdf7.31 KB
ለሕዝብ_ጥቅም_ሲባል_የመሬት_ይዞታ_የሚለቀቅበትን፣_ካሣ_የሚከፈል_ዎች_መ_አዋጅ_ቁጥር_1161_2011ን.pdf8.12 KB
NEW VACANCY UNICEF Position: Construction Specialist    Employment: #FullTime | #Contract Place of Work: #AddisAbaba Deadline Date: July, 09/2024  Summary The incumbent will be responsible for planning, managing, monitoring, reporting and quality assuring all re/construction related activities supported by GPE funded STEP for Girls and Learning Programme and providing technical support to UNICEF Programmes/Operations on construction and rehabilitation activities. Qualification - An advanced university degree in civil engineering, construction engineering, architecture, or other relevant area. - A first-level university degree (Bachelor's) in a relevant technical field (as identified above), in conjunction with an additional two (2) years of relevant work experience may be accepted in lieu of an advanced university degree. To applay and see Detai https://www.geezjobs.com/job-detail/22826/construction-specialist
Show all...
Construction Specialist job at UNICEF | GeezJobs

View job detail for construction specialist job at UNICEF and apply on Geezjobs

ለመሬት ረገጥ ሀብት ግዢ አንዳንድ ጥንቃቄዎች (Precautions in Real Estate Purchase) መሬት ረገጥ ሀብትን (Real Estate) ስንገዛ ማሰብና መከወን ያሉብን ቴክኒካዊ ጉዳዮች በ22 ዝርዝሮች ተቀምጠዋል።  በብዙ ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ስናደርግ እንደዚህ በጥልቀት ማየት የሚኖርብን ሲሆን፣ እነዚህ ዝርዝሮች ከአሻሻጮቹም ሆነ ከነጋዴዎቹ እውቀት በላይ በመሆናቸው ልፋት አከል ሥራዎች ሊሆኑ ይችላሉ። በተጨማሪም አብዛኞቹ መሬት ረገጥ ሀብቶች የሚሸጡት በአካል በአገር ውስጥ ለሌሉ ደንበኞች ሲሆን፣ ባለሀብቶቹ ከማከራየት ባለፈ እንደ ኢንቨስትመንት ስለሚያዩዋቸው እንደተዘረዘሩት የሚጨነቅ ገዢም ሆነ ገንቢ እንዲሁም ተከራይ አይገጥሙንም። (ያከራየኝ ሰው ቤቱንም አይቶት አያቅም ሲባል አልሰማችሁም) በቅርቡ ግን ሁላችንም በሰማይ ላይ ተንጠልጥለን መኖራችን ስለማይቀር ሁሉም ቴክኒካዊ ዝርዝሮች ሁላችንንም አንድ በአንድ እንደሚያገቡን እሙን ነው። ስለዚህ እነዚህን ጥያቄዎች ለማወቅ አልሚዎችን ስንጠይቅ እንደደፋር ተቆጥረን  "ትገዛ እንደሆነ ግዛ አንተ ምን ስለሆንክ ነው የምትጠይቀው?" አይነት መልስ ልናገኝ እንደምንችል ይገመታል። ወደ ዝርዝሩ፦ 1. የአልሚ እና የገዢ ውሉን ህግ፣ ለህግ አዋቂ ከፍሎ ማስመርመር፤ 2. የአልሚውን የበፊት የማልማት ዝናን መፈተሽ፤ 3. ከተቻለ የተገነባን  ሀብት መግዛት፤ 4. የተገነባም ሆነ ሊገነባ ያለ ከሆነ የቤቱን ፕላን በህንጻ ነዳፊ ማስመርመር፤ ( የእሳት ማጥፍያ የውሀ ስርአት ፣ የእሳት አደጋ ግዜ ማንቅያ፣ በእሳት አደጋ ጊዜ የአደጋ ማምለጫ ደረጃ እሳትና ጭስ የመቋቋም ስርዓት፣ የምግብ ማብሰያ እና መታጠብያ ቤት ሽታ ማስወገጃ፣ በቂ ተሽከርካሪ ማቆሚያ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረግያ ወዘተርፈ መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።) 5. የህንጻ አስተዳደር (facility management) ተገማች ወርሀዊ ወጪ ስንት እንደሆነ መጠየቅ፤ 6. የመነሻ አፈር ምርመራን፣ የግንባታ ወቅት ተከታታይ የብረት እና አርማታ ምርመራ ምስክር ወረቀትን ጠይቆ ማየት፤ 7. የኤሌክትሪክ ገመዶችና ስርዓቶችን በባለሙያ ማስመርመር፣ ተጠባባቂ ኃይል አመንጪ መኖሩን እና አቅሙን መጠየቅ፤ ቁመተ ረጅም ህንጻ ከሆነ ስለመብረቅ መከላከያ ስርአት መጠየቅ፤ 8. የፍሳሽ መስመር ላይ በተጓዳኝ የሚዘረጋ የማስተንፈሻ ቱቦ እና ስርዓት መኖሩን ማረጋገጥ (የፍሳሽ ሽታ ማስወገጃ ዘዴ) 9. ህንጻው የከተማ የፍሳሽ መስመር አጠገቡ መኖሩን ማጣራት (አለበለዝያ በየወቅቱ የፍሳሽ ማስመጠጫ ተሽከርካሪ አዋኪነትን መቀበል) 10. በቂ የውሀ ማከማቻ እና አቅርቦት ስርአት እንዳለው በባለሙያ ማጣራት። 11. የፍሳሽ ማስወገጃ የቁመት ትቦዎች የሚያልፉበት ድምጽ በማያሳልፍ  በተከለለ ቀዳዳ እንደሚያልፍ ማረጋገጥ፤ (እነዚህ ቱቦዎች በድምጽ ስለሚረብሹ በየመታጠብያ ክፍሉ ተጋልጠው መገኘት የለባቸውም) 12. ለተሽከርካሪ መንገድ ቀረቤታ ካለው የድምጽ መከላከያ እርምጃዎች ምን እንደሆኑ ማጣራት፤ 13. ለሳተላይት ርቀት ማያ (TV) ወይም ለበይነመረብ ፕሮቶኮል ርቀት ማያ (IPTV) የተዘጋጀ መስመር እንዳለው ማረጋገጥ (አለበለዝያ ሁሉም ሰው የሳተላይት ሰሃኑን ሰገነት ላይ ሰቅሎ የህንጻው መልክ እንደሚበላሽ መቀበል) 14. የተጣራ እና ያልተጣራ የሚሸጥ የቤት ስፋትን ማጣራት፣ (መተላለፍያ፣ ደረጃ፣ ተሽከርካሪ ማቆምያ ወዘተርፈ.... በነዚህ ስፋቶች መካተት አለመካተታቸውን ማጣራት) 15. የከፍታ ተሽከርካሪን (lift) የሰው የመጫን አቅምን፣  ብዛትን  እና ፍጥነትን ማጣራት። 16. የጥያራ  ማረፍያ (airport) በአካባቢው ካለ ጥያራው የሚያስነሳውን አዋኪ ድምጽ ዴሲቤል በተንቀሰቃሽ ስልክ መለካት፤ 17. አካባቢው ከቤተ እምነቶች በድምጽ ማጉልያ የሚወጡ ድምጾች እንዳሉ ማረጋገጥ፤ 18. የሚገዛው ቤት ዋና ዋና ክፍሎች አቅጣጫን ማወቅ (ለምሳሌ ወደ ሰሜን የሚከፈት ክፍል በፍጹም ፀሐይ የማያገኝ ከመሆኑ የተነሳ በአርማታ በተሰራ ህንጻ ውስጥ፣ በአዲስአበባ ከተማ አውድ እጅግ ቀዝቃዛና የሚደብት መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል) 19. የሚቻል ከሆነ አልሚው የመስኮቶች ክፍተት ላይ ትንኝ-ከላ ወንፊትን ከመስታወቶች አዳብሎ እንዲሰራ ማመላከት፤ 20. አካባቢው በቋሚነት ከሚከሰት መጥፎ ሽታ ነፃ እንደሆነ ማረጋገጥ፤ 21. ልማቱ ላይ እጅግ የበዛ አባወራ እንዲኖርበት የተነደፈ ከሆነ ወደልማቱ የሚወስዱ ተመጣጣኝ ስፋት ያላቸው መጋቢ መንገዶች እንዳሉ ማረጋገጥ፤ 22. በመጨረሻም ባለብዙ ወለል ባለብዙ መኖርያ  የጋራ መኖርያ ቤት የሚሰራ ከሆነ እና እንደ ባህላችን በቀስታ ተቁላልተው የሚሰሩ ምግቦች የሚበስሉባቸው ማብሰያ ክፍሎች የሚኖሩ ከሆነ ማብሰያ ክፍሎች ውስጥ ያለውን የሽታ ማስወገጃ ስርአት በጥልቅ መመርመር ያስፈልጋል። አንደኛ ካንዱ ቤት ወደ አንዱ ቡና እና ወጥ ሽታ እንዳንቀባበል፣ ሁለተኛው ደግሞ ሽታዎች  ከምግብ ማብሰያ ወደ መኝታ እና እንግዳ መቀበያ እንዳይገቡ ሲባል ነው። (ዳዊት በንቲ፣ መምህር እና ሕንፃ ነዳፊ)

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.