cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሩዋድ የበጎ አድራጎት እና መረዳጃ ማሀበር®

ጉዞ ወደ ከፍታ ☆መረጃ ለማግኘት telegram:- @buki1453 @Esoo_017 @Abunehyan1

Show more
Advertising posts
394
Subscribers
No data24 hours
+27 days
-130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

( ﺍللَّهُمَّ ﺻَﻞِّ ﻋَﻠَﻰ ﺳَﻴِّﺪِﻧَﺎ مُحَمَّدٍ ﻋَﺒْﺪِﻙَ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟِﻚَ ﺍلنَّبِيِّ ﺍﻷُﻣِّﻲ ﻭَﻋَﻠَﻰ ﺁﻟِﻪِ ﻭَﺻَﺤْﺒِﻪِ وَسَلِّمْ تَسْلِيماً ) Selewat to be said 80 or 100 times on Friday after asr. ጁሙዐ ከአስር ቡሀላ 80 ወይም 100 ጊዜ የሚደረግ ሰለዋት
Show all...
ክብር ለሴቶች . 1⃣. ባል በሚስቱ ላይ ከወሰለተ ቅጣቱ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ መወገር ነው፡፡ 2⃣. 2ኛ ሚስት አግብቶ እኩል ካላስተዳደር የትንሳኤ ቀን ወደ ጎን ተጣሞ ይቀሰቀሳል፡፡ 3⃣.ጥሎሽ ይህን ያህል እሠጣታለሁ ብሎ ቃል ገብቶ ካልሠጠ እሱ ሌባ ነው፡፡ 4⃣. የፈታት አንደሆነ ከሠጣት ነገር ዉስጥ አንዳችም ነገር መውሰድ የለበትም፡፡ አሳፋሪ ነው አትውሰዱ ይላል ቁርኣን፡፡ 5⃣. የዉርስ መብቷን የማይሠጣት ከሆነ የአላህን ድንበር ተላለፈ፡፡ የአላህን ድንበር የሚተላለፍ ራሱን ምንኛ በደለ!፡፡ 6⃣ ሴትን ልጅ በመምታት ይሁን በሌላ ነገር ያዋረዳትና ዝቅ ያደረጋት እሱ የተዋረደ ነው፡፡ 7⃣. ከአራትወር በላይ ጥሏት የጠፋ እንደሆነ የመለያየት መብት አላት፡፡ 8⃣. እንደ እናቱ ሊያያት አይገባም፤ ጀርባውን መስጠትና ፍራሹን መለየትም የለበትም፡፡ 9⃣. ‹አልቀርብሽም አንቺ ለኔ እንደ እናቴ ነሽ› ካላት በኋላ ቃሉን ማጠፍ ከሳበ ለቅጣቱ ስልሳ ቀናትን መፆም ይኖርበታል፡፡ 🔟. የጠላት እንደሆነም ይታገስ፡፡ በጠሉት ነገር ዉስጥ ብዙ መልካም ነገር ሊኖር ይችላልና ይላል ቁርአን ፡፡ 1⃣1⃣. አንደኛውን ባህሪዋን ቢጠላ ሌላውን ይውደድላት፡፡ ሰው ሆኖ ሙሉ የለምና፡፡ 1⃣2⃣ የፈታት እንደሆነም መልካምነቷን አይርሳ፡፡ ትዝታ አያረጅም፡፡ ምንም እንኳ የሆነ ጊዜ ጥሩ ትንፋሽ ተለዋውጠዋልና፡፡ 1⃣3⃣. በፍቺ ከተለያዩ ልጆቿን አይከልክላት፡፡ ቀለባቸውንም በትክክል ይስጣት ፡፡ 1⃣4⃣. ሴት ልጅ በሀብት ንብረቷ ሙሉ ባለመብት ናት፡፡ መፀወተች፣ ነገደችበት መብቷ ነው፡፡ በሷ ገንዘብ ባሏ አያገባውም፡፡ 1⃣5⃣ ድንበር ያለፈባት ሰው በተመሳሳይ መልኩ መቀጣት ይኖርበታል፡፡ 1⃣6⃣. ባሏን የምትታዘዘው በመልካም ነገር ያዘዛት እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ፈጣሪን በማመፅ ፍጡርን መታዘዝ የለም፡፡ 1⃣7⃣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የበኑ ቀይኑቃዕ ጎሣዎች ላይ የዘመቱት በሴት ልጅ ክብር ምክንያት ነው፡፡ 1⃣8⃣. ከሷ መከላከል የመስዋእትነት ደረጃ አለው፡፡ 1⃣9⃣. ኸሊፋ አል-ሙዕተሲም ዐሙሪያ ድረስ ጦራቸውን ያዘመቱት ስለሷ መነካት እልህ ብለህ ነው፡፡ (ይህን ታሪክ ፈልጋችሁ አንብቡ፡፡) 2⃣0⃣. በዉሸት በዝሙት የወነጀላት የሰማኒያ ጅራፍ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ 2⃣1⃣. እሷን ማስተማር ግዴታ ነው፡፡ በመልካም ሁኔታ ማሳድግ የጀነት መግቢያ መንገድ ነው፡፡ 2⃣2⃣ ከእናቶች እግር ሥር አትነሱ፡፡ ጀነት በእግራቸው ሥር ነውና፡፡ 2⃣3⃣. እናት ከአባት በሦስት ደረጃዎች የበለጠች ናት፡፡ አል-ዐሪፊ እንደፃፉት… ራሳችሁ በድላችሁ፣ መብቶቻቸውን ሰርቃችሁ እስልምና ሴቶችን ይበድላል አትበሉ።💞💞💞
Show all...
👍 1
💛ያ አላህ እኔ በጣም ታምሜያለሁ ስልህ”ከአላህ እዝነት ተስፋን አትቁረጡ” አልከኝ 💛ልቤ ውስጥ ጭንቀት አለ ስልህ” አላህን በማስታወስ ትረጋጋለች” አልከኝ» 💛ሰዎች አዛ ያድርጉኛል / ያሰቃዪኛል / ስልህ” አላህ እነዛ በዳዬችን በሚሰሩት ስራ ዘንጊ አይደለም” አለከኝ 💛ብቸኝነት ይሰማኛል ስልህ” እኛ ከደምሰሮቻቸው የበለጥ ቅርብ ነን” አልከኝ 💛 እኔ ወንጀለኛ ነኝ ተሳስቻለሁ ስልህ” ከአላህውጭ ወንጀልን የሚምር ማን አለና? “አለከኝ 💛ጌታየ አትተወኝ ስልህ” አስታውሱኝ አስታውሳቹሀለሁ » አልከኝ 💛 ህይወቴ በጭንቀት ተሞልቷል ስልህ “አላህን የሚፈራ መውጫውን የበጅለታለ “አልከኝ 💛ብዙ ነገር እፈልጋለሁ ስልህ” ለምኑኝ እቀበላቹሀለሁ”አልከኝ። -------------------------------- አዎ አላህ ካንተ ውጭ ማንም የለንም ጌታችን ሆይ እባክህን ዱአችንን ተቀበለን ወንጀላችንን ማረን
Show all...
👍 3
ትንሽ ፈገግ በሉ‼ ============ ✍ «… ወሎ ውስጥ ነው አሉ። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። ክርስቲያኑ ሙስሊሙን ግብዣ ጠራው። የገና በአል ነበር። ሙስሊሙ ሲመጣ  ምግቡ፣ መጠጡ፣ ሁሉ ነገር ተትረፍርፏል። ሰዎቹ ፌሽታ በፌሽታ፣ ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል። * ሙስሊሙ:– "ድግሱ ምንን ምክንያት በማድረግ ነው?" ብሎ ጠየቀ። "ጌታ ተወልዶ ነው" አሉት። ለሙስሊሙ ይሄ አስደንጋጭ ነበር። ጌታ ይወለዳል?! ግን ከሰው ቤት ነው ያለው ምን ይላል? "ህምምም" ብሎ የሆዱብ በሆዱ አድርጎ ዝም ይላል። ይህን ጉድ አይቶ ተመለሰ። ሌላ ጊዜ ተጠራ። ጥምቀት ነበር። ሲመጣ ድግሱ አሁንም እንደባለፈው የደመቀ ነው። ሰዎቹም ደስታ በደስታ ናቸው። "ይሄስ በአል ምንድን ነው ምክንያቱ?" ብሎ ጠየቀ። "ጌታ ተጠምቆ ነው" አሉት። ዘንድሮ ጉድ ተአምር እያየ ነው። እንዲያም ነው፤ እንዲህም ነው ሳይል ወደ ቤቱ ተመለሰ። አሁንም ተጠራ። ስቅለት ነበር። ሲመጣ ከወትሮው የተለየ ነገር አየ። ሰዎቹ የባለፈው አይነት ደስታ አይታይባቸውም። አዝነዋል። በባዶ እግር ይሄዳሉ። የሚበሉት ንፍሮ ነው። ግንባራቸውን በሳር መሳይ ነገር አስረዋል። ምን ጉድ ነው?! ቆለኛው ግራ ገብቶታል። * "ምንድን ነው የሆናችሁት?" አላቸው። "ጌታ ሞቶ ነው" አሉት። * "ያ ባለፈው የተወለደው?" ሲል ጠየቀ። "አዎ" አሉት። · ከዚያ ምን ቢል ጥሩ ነው:– "እኔኮ ቀድሞም ፌሽታ ስታበዙ እንደማያድግ አውቄያለሁ!" ©: የታሪኩ ምንጭ አንድ የደሴ ክርስቲያን ነው።
Show all...
( ﺍللَّهُمَّ ﺻَﻞِّ ﻋَﻠَﻰ ﺳَﻴِّﺪِﻧَﺎ مُحَمَّدٍ ﻋَﺒْﺪِﻙَ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟِﻚَ ﺍلنَّبِيِّ ﺍﻷُﻣِّﻲ ﻭَﻋَﻠَﻰ ﺁﻟِﻪِ ﻭَﺻَﺤْﺒِﻪِ وَسَلِّمْ تَسْلِيماً ) Selewat to be said 80 or 100 times on Friday after asr. ጁሙዐ ከአስር ቡሀላ 80 ወይም 100 ጊዜ የሚደረግ ሰለዋት
Show all...
አቡ ነዎስ ማነዉ ? - አቡ ነዋስ ማለት በኢማም አሽ'ሻፊዒይ ዘመን የነበረ ሰዉ ሲሆን በጣም በመጥፎነት እና ኸምር (አስካሪ መጠጥ) በመጠጣት የታወቀ ነበረ። ከእለታት አንድ ቀንም ወደ መስጅድ እንሂድ ሲባል እንዲህ በማለት ግጥም እየገጠመ መልስ ሰጠ: ”مَاقالَ ربُكَ ويلٌ لِلذِينَ سَكِرُوا ولَكِن قالَ ويلٌ لِلمُصَلينَ“ ”دَعِ الْمَسَاجِدَ لِلعُبَادِ تَسْكُنُهَا وَطِفْ بِنَا حَولَ خَماّرٍ ليَسقِيناَ“ “መስጅዶችን ለአምላኪዎች ተዉላቸዉ ይቆዩበት  መጠጥ አጠጪ ቤት ዉሰደን እኛን ያጠጣበት” “ጌታህኮ ለሚሰክሩት ሰዎች ወየዉላቸሁ አላለም ነገር ግን እኮ ለሰላት ሰጋጆች ብሏል ወየዉላቸዉ” ከዛም ይህንን መጥፎ እና አፀያፊ ግጥም የሰማዉ የዘመኑ ኸሊፋ ሀሩን አራ'ሺድ በመቆጣት የአቡ'ነዋስን አንገት መምታት ፈለገ። አንድ ግለሰብም ገጣሚዎች እኮ የማይተገብሩትን ነዉ የሚናገሩት በማለት ኸሊፋዉን አረጋጋና ይቅርታ ተደረገለትበስተ መጨረሻም አቡ ነዋስ ሞተ፣ ጀናዛዉ ሲታጠብም በልብሱ ዉስጥ እንዲህ የሚል ግጥም ተፅፎ አገኙ : ”يَاربِ وإِن عَظُمَتْ ذُنوبِي كثْرةً فَلقَد علِمتُ بأن عَفوَك أعْظَمٌ إنْ كانَ لاَ يرْجُوكَ إِلاَّ مُحسِنٌ فَبِمنْ يَلوذُ ويَستَجيرُ المُجرِمُ“ “ጌታዬ ሆይ ወንጀሎቼ ቢሆኑ በብዛታቸዉ ግዙፍ በእርግጥም አወኩ ያንተ መሀርታ መሆኑን ግዙፍ አንተን ደግ እንጂ ሌላ ማንም የማይከጅል ከሆነ ታዲያ በዳዩ በማን ይጠበቃል በማን ይማራል” ”أَدعوكَ رَبِّ كَما أَمَرتَ تَضَرُّعاً فَإِذا رَدَدتَ يَدي فَمَن ذا يَرحَمُ ما لي إِلَيكَ وَسيلَةٌ إِلا الرَجا وَجَميلُ عَفوِكَ ثُمَّ أَنّي مُسلِمُ“ “ጌታዬ ሆይ በፍራቻ እጣራሀለዉ እንደዘዝከኝ እጄን በከንቱ ከመለስከዉ ታዲያ ማን ይማረኝ ወዳንተ ለመቃረብ ከመመፀን ዉጪ ምን አለኝ ይቅርባይነትህ ሲቀር ቀጥሎም ሙስሊም ነኝ” ይህንን ግጥምም ኢማም አሽ'ሻፊዒይ ካነበቡት በኋላ እሳቸዉ ከሙስሊሞች ጋር ሆነዉ ሰላተል ጀናዛን በአቡ ነዋስ ላይ ሰገዱት። 𝐓𝐞 ▸  https://t.me/Halal_post ♡ㅤ   ❍ㅤ     ⎙ㅤ     ⌲  ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ     ˢʰᵃʳᵉ
Show all...
👍 1
ቀይ ቀለም ያለዉ ወተት ¡ አቡ ጃዕፈር ሀሩን አር'ረሺድ የምዕመናን መሪ፣ እንዲሁም አምስተኛዉ የዓባሲዬች ኸሊፋ፣ ከረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በኋላም 24ኛ ኸሊፋ ነበረ። አቡ ነዎስ ማለት ደግሞ በመጠጥ የታወቀ ነገር ግን ወደ አኺራ ሳይሄድ በፊት ተዉበት ያደረገ ሰዉ ነበረ። ከዕለታት አንድ ቀንም አቡ ነዋስ የተባለዉን ሰዉ መካ ከተማ ዉስጥ ኸምር (አስካሪ መጠጥ) ይዞ ተመለከተዉ፣ ኸሊፋዉ ሀሩን እንዲ ሲል ጠየቀ : ያ አቡ ነዎስ በእጅክ ምንድን የያዝከዉ? አለ አቡ ነዋስ : ወተት ነዉ አለ ኸሊፋዉ ሀሩን  : ወተት ቀይ ነዉ እንዴ ? አለ አቡ ነዋስም : "አንቱ አሚረል-ሙዕሚኒን ሆይ እርሶን ሲመለከት ነዉ ከእፍረቱ የተነሳ ወተቱ ቀይ የሆነዉ" አላቸዉ👌 (💣BOOM) 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 https://t.me/Halal_post ♡ㅤ   ❍ㅤ     ⎙ㅤ     ⌲  ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ     ˢʰᵃʳᵉ
Show all...
❤️‍🩹❤️‍🩹
Show all...
📖      በቁርኣን ታሪኮች ለምን ይወሱልናል??!! ከብዙ ጥበቦቹ ውስጥ አንዱ……    ታሪኮቹ በምታነብ ጊዜ ከምታውቀው ጠባቡ ዐለም ወደ የረሳኸው ሰፊው ዐለም ይዘውህ ይሻገራሉ። ያ………    የረሳኸው ሰፊው ዐለም ላይ የአንተው ዐይነት ሰዎች ነበሩ; እንደቆሰልከው የቆሰሉ; እንደታመምከው የታመሙ; እንደተበደልከው የተበደሉ።    ታግሰው; ተሸክመው; ችለው… አልፈዋል!! 🧿ብትዋሽ………     ከአንተ በፊት ኑሕ ተዋሽቷል። 🧿ብትታመጽ………      ከአንተ በፊት ሙሳ ታምጿል። 🧿ብትበደል………      ከአንተ በፊት ዩሱፍ ተበድሏል። 🧿ብትቸገር………      ከአንተ በፊት ዒሳ ተቸጋግሯል። 🧿ብትባረር………     ከአንተ በፊት ሙሐመድ ተባሯል። 🧿እምቢተኛ ልጅ ቢኖርብህ………     የኑሕ ልጅ ከአንተ ልጅ ቀድሞ እምቢ ብሏል። 🧿አመጸኛ ሚስት ብትኖርብህ………      የሉጥ ሚስት ከአንተዋ ቀድማ አምጻለች። 🧿አመጸኛ ባል ቢኖርብሽ………     የዐሲያ ባል ከአንቺ ባል ቀድሞ አምጿል። 🧿አጓጉል ዘመዶች ቢገጥሙህ………     የሙሐመድ ዘመዶች በዚህ ተግባር ቀድመዋል። ብቻህን አይደለህምና <> ቀለል አርገው!! እነርዚህ ታላላቆች መከራውን ለማለፍ በተሳፈሩበት መርከብ ከተሳፈርክ;    የደረሱበት ደረጃ ትደርሳለህ!! ታገስ……ታገስ……ታገስ ወንድሜ!! ✏️          ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
Show all...
00:45
Video unavailableShow in Telegram
❤️‍🩹❤️‍🩹
Show all...