cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

THIKVAH-ETHIOPIA

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Show more
The country is not specifiedAmharic6 206The category is not specified
Advertising posts
1 209
Subscribers
+224 hours
+257 days
+17430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" የኦንላይን ፈተናው በተመረጡ 25 ከተሞች ይሰጣል " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ 25 ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ገልጿል። ተፈታኝ ተማሪዎች በኦንላይን ለሚሰጠው ፈተና እንዲዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከሁሉም ክልሎች በተመረጡ 25 ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል። በወረቀት ከሚሰጠው ፈተና ጎን ለጎን የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው #ቤተሰቦቻቸው_ጋር_እያደሩ ፈተናውን ይወስዳሉ ሲሉ አሳውቀዋል። ወ/ሮ አየለች ፤ ተማሪዎች ለፈተናው እንዲዘጋጁ፣ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ፣ ወላጆችንም ልጆቻቸውን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል። ትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ፈተናው በኦንላይን የሚሰጥባቸውን 25 ከተሞች በዝርዝር ይፋ አላደረገም። የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው ተብሏል። @tikvahethiopia
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ለጥንቃቄ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ በተለያየ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የመኪና ስፖኪዮ በመስረቅ ወንጀል የተጠረጠሩ 3 ግለሰቦች (ልጆች) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ ሚያዚያ 23 እና 24 ቀን 2016 ዓ.ም ወረዳ 2 ጋዜቦ አደባባይ እና ወረዳ 9 አካባቢ ነው የተያዙት ተብሏል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ የትራፊክ መብራቶች እና ተሽከርካሪ በሚቆምባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ በመንቀሳቀስ ስፖኪዮ ሲሰርቁ እንደነበር አመልክቷል። በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳትፈው የተገኙ ህፃናቶች መሆናቸውም ተመላክቷል። ይህ መነሻ በማድረግ በተደረገ ምርመራ ለህፃናቱ ስምሪት የሚሰጡ የተደራጁ ወንጀለኞች መኖራቸውን ፖሊስ ማረጋገጡን ገልጿል። አንዳንድ ህፃናት መኪና የሚጠብቁ  እንዲሁም እርዳታ የሚፈልጉ መስለው በመቅረብ ወንጀል እንደሚፈፅሙ አሽከርካሪዎች ተገንዝበው   በትራፊክ  መብራቶችም ሆነ የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ ሲቆሙና በዝግታ ሲያሽከረክሩ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል። #AddisAbabaPolice @tikvahethiopia
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#LionInternationalBank አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኙ የጥያቄና መልስ ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል፡፡ እርስዎም የሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያሉትን የባንኩን ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች በመቀላቀል እና ጥያቄውን ቀድመው በመመለስ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉl ጥያቄው የሚካሄዳው እሁድ ሚያዚያ 27 ከቀኑ 5:00 ሰዓት ሲሆን ጥያቄውን ቀድመው ለመለሱ 3 ሰዎች ሊሸልም ዝግጅቱን ጨርሷል። 1ኛ ለሚወጣ ተሸላሚ የበግ ሽልማት 2ኛ ለሚወጣ  የ5000 ብር ሽልማት  3ኛ ለሚወጣ የ3000 ብር ሽልማት      ያበረክትላችኋል። እርስዎም ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የውድድሩ ተሳታፊ ይሁኑ!! አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ          የስኬትዎ አጋር!    [Telegram]  [Facebook] https://t.me/LionBankSC #LIB #lioninternationalbank #anbesabank #keytosuccess
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#DV2025 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2025 አሸናፊዎች ነገ ይፋ ይደረጋሉ። ለዲቪ (Diversity Visa) 2025 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov/ESC/ ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ። NB. የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ነው። ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot Confirmation Number በማለት አስፈለጊ መረጃ በመሙላት በኢሜል አዲስ ቁጥር ማግኘት ይቻላል። ውጤቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽት 1 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይሆናል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል ፣ ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው ምንደውለው / ይህን ኢሜል / ቴክስት የምንልከው " በማለት #የሚያጭበረብሩ_አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ አሳስቧል። አንድ አመልካች ዲቪ 2025 ደርሶት እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማወቅ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ከላይ የተጠቀሰው ድረገጽ መሆኑን አስገንዝቧል። አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ (ኢትዮጵያ ጨምሮ) ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 55 ሺህ ሰዎችን በዲቪ (DV) ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች። @tikvahethiopia
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" በየቤቱ የቁም እንስሳት ማረድ / በየአካባቢው ቅርጫ አድርጎ መከፋፈል አልተከለከለም " - የአዲስ አበባ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ፥ ከትንሳዔ በዓል ጋር በተያያዘ " ህብረተሰቡ በየቤቱ የቁም እንስሳት እርድ በማካሄድ ወይም በየአካባቢው ቅርጫ በማድረግ የሚከፋፈልበት አሰራር ተከልክሏል " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ #ሐሰተኛ መሆኑ አሳወቀ። ከዚህም ጋር በተያያዘ #ምንም_ዓይነት_ክልከላ ያልተደረገ መሆኑን አረጋግጧል። ነገር ግን በየአካባቢው #በሕገወጥ_መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ድርጊቱ በከተማው ነዋሪዎች ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ብሏል። የከተማዋ ነዋሪዎችም ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። @tikvahethiopia
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት ለአደጋ መንሰዔ የሚሆኑ የአሰራርና የአጠቃቀም ግድፈቶችን በማሰወገድ ዘወትር ህይወትንና ንብረትን ከጉዳት መታደግ እንደሚያስፈልግ የእሣት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መልዕክቱን አስተላልፏል። ለበዓሉ መደረግ ያለባቸዉ ጥንቃቄዎች ምንድናቸው ? ➡️ በምግብ ማብሰያ / ማዕድቤት/አካባቢ የኤሌክትሪክ፣ የቡታጋዝ፣ የጧፍና የከሰል ምድጃዎችን በአግባቡና በጥንታቄ ይጠቀሙ። ➡️ በገበያ ማዕከላት የገበያተኛውን ቀልብ ለመሳብ የሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክስ ዲኮሬሸኖች ቃጠሎ እንዲያስነሱ ይጠንቀቁ። ➡️ ሻማና ጧፍ በሚጠቀሙበት ወቅት ከተቀጣጣይ ነገር ያርቁት። ➡️ ካምፋዬር የሚያዘጋጁ ከሆነ ከአካባቢው ከመራቅዎ በፊት በደንብ መጥፋቱን ያረጋግጡ። ➡️ በፍጹም ጠጥተው አያሸከርክሩ። ➡️ ለመዝናናትዎ ገደብ ይስጡት። ኮሚሽኑ ፤ " በመጨረሻም የበኩልዎን ሁሉ ጥረት አድርገው ከአቅም በላይ ለሚገጥምዎ ችግር እርሶን ለማገልገል 24 ሰዓት ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን " ሲል አሳውቋል። ለማናቸውም የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም የአምቡላንስ አገልግሎት በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች መዝግበው እንዲይዙ መልዕክት አስተላልፏል። 1.ማዕከል - 0111555300/ 0111568601 2. አራዳ - 0111567004/ 0111560249 3. ቂርቆስ - 0114663420/21 4. አዲስ ከተማ - 0112769145/46 5. ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 0114425563/64 6. አቃቂ ቃሊቲ - 0114340096 / 0114343063 7. ቦሌ - 0116630373/74 8. ኮልፌ ቀራንዮ- 0113696085/ 0113696104 9. ጉለሌ - 0112730731/ 0112730653 10. ቦሌ ሰሚት - 0116680846/ 0116680760 11. ልደታ - 0115589043/ 0115589533 @tikvahethiopia
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
“ ... ለኩራዝ የሚጠቀሙበት ነዳጅ በግልጽ ሁኔታ በችርቻሮ፣ የአረቄ በርሜል በከፍተኛ መጠን የሚሸጥበት ቦታ ነው ” - አቶ ንጋቱ ማሞ በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አቃቂ ገበያ ማዕከል ትላንት ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ የእሳት አደጋ አጋጥሞ ነበር። በሰዎች ላይ ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን 6 ሙሉ ለሙሉ፣ 10 በከፊል፣ በድምሩ 16 ሱቆች እንደተቃጠሉ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። የአደጋው መንስኤ ታውቋል? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ “ ፓሊስ ምርመራ እያደረገ ነው። በንብረት ላይ የደረሰን ጉዳትም ባለንብረቶቹን ፓሊስ አጣርቶ ምርመራ እያደረገ ነው ” ብለዋል። ገበያ ማዕከሉ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብሎ የተለዬ እንደሆነ ፣ ለአደጋ የተጋለጠባቸውን ጉዳዮች ለሚመለከታቸው አካላት ቢያቀርብም የማስተካከያ እንዳልተደረገ ኮሚሽኑ ያስታወቀ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ተሰጥቶ የነበረው ማስጠንቀቂያ ምን እንደነበር ኮሚሽኑን ጠይቋል። አቶ ንጋቱ በሰጡት ምላሽ፣ “ ለገበያ ማዕከሉ አክሲዮን ማኅበራት አደጋ ውስጥ ናችሁ። ገበያ ማዕከሉ በዘመናዊ መልክ ይገንባ ንብረታችሁ ለአደጋ ሰለባ እንዳይሆን የሚል ምክረ ሀሳብ አቅርበናል። በግልባጭ ደግሞ ለወረዳውም ” ብለዋል። “ ቤቶቹ በቀላሉ ሊቀጣጠሉ ከሚችሉ ግብዓቶች (ቆርቆሮ በቆርቆሮ) የተገነቡ ናቸው። መፍትሄ ብለን ያቀረብነው ገበያ ማዕከሉ ዘመናዊ ሆኖ እንዲገነባ ነው። ዘመናዊ ስንል እሳትን ሊቋቋም ከሚችል እንደ ድንጋይ ከመሳሰሉ ግብዓቶች እንዲሰራ ነው ” ሲሉ አስረድተዋል። አቶ ንጋቱ፣ “ ከገጠር የሚመጡ ሰዎች ለኩራዝ የሚጠቀሙበት ነዳጅ በግልጽ በችርቻሮ፣ የአረቄ በርሜል በከፍተኛ መጠን የሚሸጥበት ቦታ ነው” ብለዋል። “ ንግዱ ዘርፍ፤ ዘርፍ ያስፈልገዋል። በጎን ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እየተሸጡ፣ በጎን ደግሞ የካቲካላ ንግድ በፍጹም ምንም አይነት ህብረት የላቸውም ” ነው ያሉት። የገበያ ማዕከሉ በተደጋጋሚ አደጋ እንደደረሰበት አስታውሰው፣ አደጋ ቢያጋጥም እንኳ የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ለማስገባት ምቹ ባለመሆኑ፣ በውስጡ የሚከናወኑ የንግድ ዘርፎች የተደበላለቁ በመሆናቸው የሚመለከታቸው አካላት አሁንም ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ከዘመናዊ የATM ማሽኖቻችን ብር ለማውጣት ካርድዎን ወደ ማሽኑ በማስጠጋት እና የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት መገልገል ይችላሉ። አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ! #BoAATM #ATM #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #contactless #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኅን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ ትላንት በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ ተገልጾ ነበር። ዛሬ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ማኅበረ ቅዱሳን አሳውቋል። ምንም እንኳን አመራሮቹ በምን ምክንያት ተይዘው እነደነበር  ያብራራው ነገር ባይኖርም ፥ " በሂደቱ ጉዳዩን በመረዳት #አፋጣኝ_ምላሽ የሰጡንን የመንግሥት የጸጥታ አካላት እናመሰግናለን " ብሏል። @tikvahethiopia
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኅን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ ትላንት በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ ተገልጾ ነበር። ዛሬ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ማኅበሩ አሳውቋል። ምንም እንኳን ማህበሩ አመራሮቹ ለምን ተይዘው እነደነበር  ያብራራው ነገር ባይኖርም ፤ " በሂደቱ ጉዳዩን በመረዳት #አፋጣኝ_ምላሽ የሰጡንን የመንግሥት የጸጥታ አካላት እናመሰግናለን " ብሏል። @tikvahethiopia
Show all...