cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Hasen Manzuma Official

@ ብስራታን ነገራት አርግዘሻል አላት ተደሰቺ አላት አብሽሪአሚና ሰይዲና ኑረል አለሚና

Show more
Advertising posts
202
Subscribers
No data24 hours
-37 days
+330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ጀሀነም የሚገባው ወደ ጀሀነም ጀነት የሚገባውም ወደ ጀነት ከገባ በኋላ አንድ ተጣሪ እንዲህ ሲል ይጣራል! አንተ ሙሐመድ! ተደሰተክ ወይ? እርሳቸው እንዲህ ይለሉ«ጌታዬ! ወላሂ አልተደሰትኩም። ከኡመቶቼ እሳት ውስጥ የቀረ አለ» አላህም ለመላኢኮች «ቅንጣት ታክል ኢማን በቀልቡ ያለውን ሁሉ ከእሳት አውጡ» በማለት ያዛቸዋል። ከዚያም ጀሀነም በሯ ይከፈትና የተወሰነው የሙስሊሙ ክፍል ወጥቶ ወደ ጀነት ይተማል። አላህ በድጋሚ «ሙሐመድ ሆይ! ተደሰትክ?» ይላቸዋል። «ጌታዬ ባንተ እምላለሁ! አሁንም ከህዝቦቼ የቀሩ አሉ» ብለው ያለቅሳሉ! አላህም ለመላእክቱ «አይኑ የትንኝ ራስ የምታክል እንባም ብትሆን እኔን ፈርታ ያነባችን ሁሉ አውጡ» በማለት ያዛል። ከዚያም «ያ ሙሐመድ! አሁንስ ተደሰትክ?» ይላቸዋል። «ወላሂ አልተደሰትኩም። አሁንም ከኡመቴ የቀሩ ሰዎች አሉ። ይላሉ ረሱላችን ﷺ » አላህ ለመላኢኮች «ላኢላሀ ኢለላህ፣ ሙሐመዱን ረሱሉላህ ያለውን በጠቅላላ ከጀሀነም አውጧቸው» በማለት ያዛል። ጀሀነም በሮቿ ተከፍተው ሁሉም ወደ መስካሪዎች ጎራ ይነጉዳሉ። ከወርቅና ከሉል በተሰራ ግንብ ውስጥ ይነዳሉ። ባማረ መዓዛ ይታወዳሉ። ውስጥ የነበሩት የጀነት ሰዎች የተበለጡ እስኪመስላቸው ድረስ እነዚህ ሰዎች ውብ ይሆናሉ። ከዚያም ወደ ጀናህ እንዲገቡ ይደረጋል። ይሄኔ ለመጨረሻ ጊዜና ለዘልዓለም ጀሀነም ትዘጋለች!! በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ፦ « ﺭُّﺑَﻤَﺎ ﻳَﻮَﺩُّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ ﻟَﻮْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﻣُﺴْﻠِﻤِﻴﻦَ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡ (ሱረቱ አል-ሒጅር- 2) አላህ የርሳቸውን ሸፈዓ የምናገኝ ያድርገን!! ሰሉ ዐለል ሐቢብ!! ✍ HASEN MANZUMA OFFICIAL
Show all...
አዲስ የሰርግ መንዙማ//ሙዓዝ ሀቢብ// new wedding neshida #MUAZ HABIB MEDINA||TUBE https://t.me/medina_tube
Show all...
መደድ መደድ መደድ
Show all...
* * * * * * * * * ** * * * * * * * * * አሏሁ መርሃም ኑር ሁሰይን አሏሁ መርሃም ኑር ሁሰይን ሸፊዑል ወራ ፊዳረይን 💚 💕 💚 💕 💚 💕 ================== * ኑር ሁሰይን ቁጥቡል ሀበሻ የአይታም ምስኪን መሸሻ የታረዘውን መልበሻ አሽራር በላዕ መመለሻ ማበሻ ሲቃ ሀዘኔን ሸፊዑል ወራ ፊዳረይን... * ኑር ሁሰይን የከውኑ አባት ዙህድ ነው የሱ ሚለት ፆም ውሎ ያድራል ሶላት ላጣው እናት ነው አባት ለሰው ለእንስሳ አሳቢ ሸፊዑል ወራ ፊዳረይን... * በአናጂናው ሰፈር ይፋ ወጥቷል ያንቱ ሲር አያልቀው ሲመነዘር እንደው ገና በኸበር ላቤን ቆረጠልኝ ጥሜን ሸፊዑል ወራ ፊዳረይን... * ከቁረይሽ የሆነው ዘሩ ሲወለድ የታየው ኑሩ አዛኝ ለምስኪን ፈቂሩ ደርሶ ተበልቷል ሰመሩ ተከውኑ ዋርካ ኑር ሁሰይን ሸፊዑል ወራ ፊዳረይን... * ሰላም አለይኩም ነጋሲ ሰላም አለይኩም አባባ ገሩ ኢላላ ዱቢኒ ዬ ገሪፍ ገሌ መሌ ኬሰን ሒክማዳ ዱቢኒ አሏሁ መርሃም ኑር ሁሰይን * * * * * * * * * * 🥁 🥁 👏 👏 🥁 🥁 አሏሁ መርሃም ኑር ሁሰይን ሸፊዑል ወራ ፊዳረይን አሏሁ መርሃም ኑር ሁሰይን ሸፊዑል ወራ ፊዳረይን * ኑር ሁሰይን የአላህ ገበር የአውልዬቹ ስመጥር ከራማው ላይቆጠር አንጠፈጠፈው ቀለሜን * ኑር ሁሰይን የሌት ንጋቱ ድልቡን ተግቶት በጠዋቱ ፈሰሰ ብትከጅሉ አንቱ ከታች ወደ ላይ ጅረቱ * ምላሱ ኢልምን ያንቧቧል አይኑ ለጌታው ያነባል ሌላን አጥግቦ ይራባል ያስባል ዳኢም ለከውነይን * ደማም የደማም ወለድ - ቁረይሺይ ናቸው የነቢ ቤተሰብ - ከአቂል ነው ዘራቸው በመሪነት ሰም ወርቅ - ቢቀኘው ኑራቸው የሰቀለይን ሼህ - ነበር ስያሜያቸው ✍ HASEN MANZUMA OFFICIAL
Show all...
አባት ከልጁ ጋር ፊልም እያዩ አስጠያfee ቦታዎች ጋር ሲደርስ አባት ያው ልጁ እንዳይባልግbut ቶሎ ብሎ ያሳልፈዋል:: ተመስጠው ቀጥለው እያለ አባት ተጠራጥሮ ሊያሳልፈው ሪሞት ሲይዝ ልጅየው <<ተወው እሱ ጋር ሴ** የለውም>> አለው ይባላል🤭 እና መንዙማ ሀላል/ሀራም እያሉ የሚ-ያካ-ብዱ ኡስታዞች ጭራሽ ግጥምና ዜማው ከየትኛው ዘፈን እንደተወሰደ ይተነትኑልናል😂 ግዴላችሁም ሁላችንም አስመሳዮች ነን አለ:: ዑነቴን ነው እኮ:: ሰው መሰሉህ! ✍ HASEN MANZUMA OFFICIAL
Show all...
ጀነት ውስጥ በውብ የአትክልት ስፍራዎቿ  ፈታ እያልክ ድንገት ቀና ስትል ከነቢ ጋር አይን ለአይን ተገጣጥማቹ ስትተያዩ አስበኸዋል??       ሰሉ ዐለ ነቢ💛 ✍#HASENMANZUMAOFFICIAL
Show all...
ከካምፓስ ተማሪዎች ጋር የ24 ሰአት ኹሩጅ
Show all...
➦ በሸኾች ሐረም ሙሉ ረመዳን በአደብ ፥ በተርቲብ ፥ በአውራድ ፥ በአዝካር እጅግ ባማረ መልኩ ፆመው... ከዒድ በሁዋላ ስድቱን ጥብቅ ሱና የሸዋል ፆም አስከትለው ፥ በሸዋል ፆም ፍቺ ማግስት የሲልሲላ የነጃት ዱዓ ይቀመጣሉ:: ➦ ይህ የአምር ዱዓ እጅግ ብዙ ኸይር የሚከጀልበት ሸኾች "አንድ ሰው ስሙኒ ብቻ ቢኖረውና ይህንን ሳንቲም በምን ኸይር ስራ ላውለው ብሎ ቢጠይቅ በዚህ ቀን በሚደረገው ዱዓ አውለው ተብሎ ይባል ነበር" ያሉለት ፥ ለሀገር ሰላም ሚመመኙበት ፥ የረመዳን በረካውን እድያውን የሚታደሉበት ፥ የሢልሢላው መሻኢኾች ሩሕ የሚሀደርበት ፥ የጠሪቃው መሻይኾች የሚወሱበት እጅግ በዐደብ የተሞላ የስኩት ዱዓ ነው:: ➦ ሲልሲላውን አብሬቶች ጋር ላደረሱት ስምንቱ የሀበሻ ቃዲርይ ጦሪቃ መሻኢኾች 💖ከቁባ ጌታ እስከ ሠይድ ከቢር ሀሺም ድረስ ላሉ የሲልሲለተል ቃድሪያ ኸሊፋዎች በአብሬትዩ ሳኒ የተመደኸ(ሺሊላት) 👇 ✦ ✧ ✦ ✧ ✦ ✧ ✦ ✧ ✦ ✧ 1💕ሺሊላ ሺሊላ ያገ(غ)ውሱል አብሬዲ ሰላሙን አለይኩም ቢኩሊ መዚዲ * 2💕ሺሊላ ሺሊላ ያአባ ዘኪዪ አሽአኑል ሙሚዱ ሀድረተል ቁድሲዪ * 3💕ሺሊላ ሺሊላ ያአባ አሲያ ጧሂሩል ሙጠሀር ሐድረተል አሊያ * 4💕ሺሊላ ሺሊላ  ያአባ ሙሐመድ መደዱል ሐደራት ጀማሉል ሙአበድ * 5💕ሺሊላ ሺሊላ  ሰይድ ሙሐመደ ሻፊ ኸበሩኩ ደዋ ዊዳዱኩም ሻፊ * 6💕ሺሊላ ሺሊላ ያ ቁጥቡል ዳኢሪ ፈቂሁል ሙቀደም ደሊሉ ሐኢሪ * 7💕ሺሊላ ሺሊላ  መዝሀሩል ዓጃኢብ አሕመድ ኢብኑ ሷሊህ አስራሩል ገ(غ)ራኢብ * 8💕ሺሊላ ሺሊላ ሳሒቡ ሀረሪ ረምዙ በሕረል ሀኢ ቁበቱል ጀውሃሪ ✍ HASEN MANZUMA OFFICIAL
Show all...
በስሜት አይንህ ስታይ ቀልብህ ይታወራል። (ልብህ መጨረሻውን ማየት ይሳነዋል) ከልክ በላይ ለሚፈነጥዙና ለሚያዝኑ የኳስ ደጋፊዎች ይድረስልኝ አንዳንዴ ግራ ይገባኛል የኛ ጂልነት ።  ለራሳችን ዘይት መግዣ አጥተን ለአንዲት ድቡልቡል ኳስ ሲራገጡ ማየት ያስደስተናል ። ፈረንጆች የኢስላም ጠላት ናቸው ግን በቀኝ ግዛት በእግር ኳስ ዛሬም ገዝተውናል 4 ነገሮችን ተጠንቀቅ ሸይጧንን ነፍስያን #ስሜትንና መጥፎ ጓደኛን። ኢማኑ ያላስለቀሰው ብዙ ሰው ዛሬ በኳስ የመጣ ግማሹ ሲያለቅስ ሌላው ሲጨፍር ማደሩ ያሳዝናል ✍ HASEN MANZUMA OFFICIAL
Show all...