cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ተድባበ ጽዮን እናቴ

የምናስተላልፋቸው ፕሮግራሞች ፦ ነገረ ቅዱሳን /ዝክረ ቅዱሳን ፦ ባሕረ ሐሳብ ፦ ዜና ቤተ ክርስቲያን (ለተቸገሩ አብያተ ክርስቲያናት ገቢ ማሰባሰብ) ፦ ገንዘብ በማሰባሰብ ለተቸገሩ ሰዎች መርዳት ናቸው ። https://www.youtube.com/@yirehmiel

Show more
Advertising posts
407
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-1230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ልያነቡት የሚገባ ጽሑፍ
Show all...
📖ጽሑፉን ለማንበብ 📖
💵 just crypto ✅
#ታሪክ_አለን። በርእሰ አድባራት፤ወገዳማት፤መንበረ ፓትርያርክ፤ተድባበ፤ጽዮን ማርያም፤ያስተዳድሩ የነበሩ ፓትርያርኮች፤ስም ዝርዝር። በታሪክ የማውቃቸውን ብቻ በዝርዝር ላስቀምጥ።ከአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን ጀምሮ የሁሉም ፓትርያርኮች ስማቸው በታሪክ መዝገብ በገዳሙ ሊኖር ይችላል።እርሱን ወደፊት በሰፊው የምመለስበት ሲሆን ለዛሬ በስም የማውቃቸውን ላስታውሳችሁ። 1ኛ. ፓትርያርክ መርሃ-ጽዮን፤ 2ኛ. ፓትርያርክ ዘሙሴ 3ኛ. ፓትርያርክ አፈወ ድምግል በዓፄ ገላዴውስ ዘመነ መንግሥት የነበሩ፤ 4ኛ. ፓትርያርክ ወልደ ገብርኤል፤ 5ኛ.ፓትርያርክ አፈወርቅ፤ሲሆኑ፦ ፕትርክናው አራት ኪሎ ከገባ በኋላ፤ ለማታለያ የፓትረያርኩ ተጠሪ እየተባሉ የተጠሩ ሁለት አባቶች አሉ። እነሱም፦1ኛ. መምህር በትረ ጽዮን ሙላት የፓትርያርኩ ተጠሪ፤ 2ኛ.መምህር ወልደ ትንሣኤ ዘለቀ ( አባ ጥላሁን ዘለቀ) የርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪና የፓትረያርኩ ተጠሪ እየተባሉ ከቆዩ በኋላ፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲሾሙ የአሁኑ "መንበረ ሰላማ" ተብሎ የተሰየመው የረጅም ጊዜ እቅድ የተጠነሰሰው ያኔ ነው መሰል፤ የፓትርያርኩ ተጠሪ ተብሎ ይጠራ የነበረው የመንበረ ፓትርያርክ ተድባበ ማርያም አስተዳዳሪ የፓትርያርኩ ተጠሪ ተብሎ እንዳይጠራ ታገደ። ከዚያ በኋላ ፓትርያርክ የሚባለው የገዳሟ መጠሪያ ስም ቀርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ የገዳሟ የድጓ መምህር የነበሩት ባሕታዊውና ሊቁ መምህር ጊራ ወርቅ ጸምሩ መምህር ተብለው የገዳሟ አስተዳዳሪ ሆነው ተመደቡ።የገዳሟ አስተዳዳሪ ሆነው የተመደቡት ሊቁ መምህር ጌራ ወርቅ ጸምሩም ፓትርያርክ የሚለው የገዳሟ ስምና ማዕርግ ይመለስልን።እርሱ ባይቻል እንኳን፤የፓትርያርኩ ተጠሪ የሚለው ስም እንኳን ይመለስልን በማለት በተደጋጋሚ ቢጠይቁ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ። በመሆኑም አሁን መንበረ ሰላማ ሲኖዶስ፤ ብሔር ብሔረ ሰብእ ሲኖዶስ፤እያሉ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚከፋፍሏት ፖለቲከኞች የበዙት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ ታሪኳና ልዕልናዋ፤ አንደነቷና ሰላሟ እየተናጋ የመጣው በየዘመኑ በተነሱ በቤተ መቅደሱ ሆነው የግል አጀንዳ በሚያራምዱ የፖለቲካ ሰዎች ምክነያት ነው። በመሆኑም፦ወደ ቀደመው ታሪካች መመለስ አለብን። የመንበረ ፓትርያርክ ተድባበ ማርያም አበው ሲጠይቁት የነበረው የዘመናት ጥያቄ " ፓትርያርክ" የሚለው ስም ይመለስ ዘንድ አሁን ምቹ ጊዜ ነው። ፓትርያርኩ ወደ ቦታው ይመለስልን። "ካልደፈረሰ አይጠራም"እንዲሉ አበው ቀጣዩ ፓትርያርክ፤መንበረ ፓትርያርክ በሆነችው ርእሰ አድባራት ወገዳማት መንበረ ፓትርያርክ ተድባበ ማርያም ተሹሞ፤ በአፄ ዘርዓ ያእቆብ ከተማ ደብረ ብርሃን ላይ አዲሱ ሲኖዶስ መቋቋም አለበት። ምክንያቱም የኢትዮጵያን አንድነት ፈልገን እንጅ ክብራችንንና ስልጣናችንን የተውነው፤ "መንበረ ሰላማ"ከሚለው የተውሶ ስም ይልቅ መንበረ ፓትርያርክ የሚል እውነተኛ ታሪክ አለን። ማሳሰቢያ፦ ለፕትርክናም ለኤጲስ ቆጶስነትም ክብር የበቁ እውቀትን ከትሕትና አስተዳደራዊ ፈሊጥን ከመንፈሳዊነት ጋር አስተባብረው የያዙ እልፍ አእላፋት የሆኑ ቆሞሳት አባቶች አሉን #ሐምሌ.14/2015.ዓ.ም አድስ አበባ/ኢትዮጵያ መ/ር_የማነብርሃን ጥላሁን! 👉👉 share
Show all...
ብሔረ ሕያዋን ገብቶ ያስተማረ ሐዋርያAnonymous voting
  • ቅዱስ ዮሐንስ
  • ቅዱስ ማቲያስ
  • ቅዱስ ሉቃስ
  • ቅዱስ ማቴዎስ
0 votes
የኢኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፱ ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመች። ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለዘጠኝ አህጉረ ስብከት የተመረጡት ፱ ቆሞሳት ዛሬ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተፈጸመ ሥርዓት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አንብሮተ እድ በኤጲስ ቆጶስነት ተሹመዋል። ከሌሊቱ ፱ ስዓት ጀምሮ በተከናወነው ሥርዓተ ሢመት ላይ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች።፣ ግብዣ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች፣ ከየአህጉረ ስብከቱ የመጡ ሊቃውንት፣ የሥራ ኃላፊዎች እና ምእመናን ተገኝተዋል። በዚህም መሠረት የሚከተሉት አባቶች በቅድስት ቤተክርስቲያን የተሰጣቸውን ሥያሜ ይዘው ለተጠቀሱት አህጉረ ስብከት ተመድበዋል። ፩- ቆሞስ አባ ክንፈገብርኤል ተክለማርያም ብፁዕ አቡነ ገሪማ ተብለው ተሠይመው ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ፪- ቆሞስ አባ ሣህለማርያም ቶላ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ተብለው ተሠይመው ለምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ፫- ቆሞስ አባ ስብሐትለአብ ኃይለማርያም ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ተብለው ተሠይመው ዳውሮና ኮንታ ሀገረ ስብከት ፬- ቆሞስ አባ አምደሚካኤል ኃይሌ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ተብለው ተሠይመው ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ፭- ቆሞስ አባ ኃይለማርያም ጌታቸው ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስም ተብለው ተሠይመው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
Show all...
፮- ቆሞስ አባ ጥላሁን ወርቁ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ተብለው ተሠይመው በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ፯-  ቆሞስ አባ ዘተክለሃይማኖት ገብሬ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ተብለው ተሠይመው በሆሮ ጉድሩ ሀገረ ስብከት ፰-  ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ገብሬ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ተብለው ተሠይመው በምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ፱-  ቆሞስ አባ ወልደገብርኤል አበበ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ ተብለው ተሠይመው በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ተመድበዋል። ምንጭ: ሕዝብ ግንኘነት መምሪያ
Show all...
✝✝በስመ  አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ እዌጥን በረድኤተ እግዚአብሔር ጽሒፈ ግሥ+( አንድ አምላክ በሚሆኑ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እግዚአብሔርን ረዳት በማድረግ ግሥ መጻፍን እጀምራለሁ፡፡ ሃልሀ....ወደረ ለሕሐ....ቀዳ (የውኃ) ላሕልሐ፡፡፡።።ራሰ ለስሐ።።።።።አልጫ ሆነ ለቅሐ(ጥ)።።።።አበደረ ለብሐ(ጥ)።።።።ሠራ(የሸክላ ብቻ) ለትሐ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ተጎነጨ(የመጠጥ) ሎሐ፡፡፡፡፡፡፡ጻፈ ማሕምሐ፡፡፡፡፡አፈረሰ መልኀ(ላ)፡፡፡፡መዘዘ መልሐ(ጥ)፡፡፡፡አጣፈጠ መስሐ(ላ)፡፡፡፡፡ምሳ አደረገ መርሐ፡፡፡፡፡፡፡፡፡መራ ሞርቅሐ፡፡፡፡፡፡፡ላጠ ሞቅሐ፡፡፡፡፡አሰረ(የሰው ብቻ) መትሐ፡፡፡፡፡፡ሣሣ፣ ቀጠነ፣ ረቀቀ መንዝሐ፡፡፡፡፡ተደላደለ መድሐ፡፡፡፡፡፡ፈጨ ሞጥሐ፡፡፡፡ለበሰ ሰርሐ(ላ)፡፡፡፡ሠራ ሠርሐ(ጥ)፡፡፡አቅናና፣ አብራራ ሰብሐ(ጥ)፡፡፡፡አመሰገነ ሠብሐ(ላ)፡፡፡፡፡፡ስብ ኾነ ሰንሐ(ላ)፡፡፡፡፡፡፡በራ ሆነ(የጸጉር) ሰይሐ(ጥ)፡።ታመመ ሴሐ።።።።።ወቀጠ ሰጥሐ።።።አሰጣ ዘረጋ ሰፍሐ።።።።።ሰፋ፣ሰፊ ሆነ ረምሐ።።።።።ወጋ(የጦር) ረስሐ።።።።።።።ጎሰቆለ ረቅሐ።።።።።።።።ጋረጠ ረብሐ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ረባ ረውሐ(ጥ)።።።።።።ቀደደ ሮሐ።።።።።።።ወለወለ፣ አናፈሰ ቃሕቅሐ።።።።።።ተንቆራቆሰ ቆልሐ።።።።።።።ፍሬ ያዘ ቀምሐ።።።።።።።አፈራ ቀርሐ።፡፡።ጨለጠ፣ ላጨ፣ነጨ ቃርሐ።።።።።ተኮሰ ቄቅሐ።።።።።ፈተገ ቄሐ።።።።።።ቀላ(ቀዪሕ፡ቀይ) ቀድሐ።።።ቀዳ(የመጽሐፍ፡የውሃ) ባኅብኃ።።።።ከረፋ፣ቀረና፣ቦነቸ በኁበኆ።።።።ሸተተ፣በሰበሰ በልኀ።።።።።።።ተሳለ ባልሐ።።።።።አዳነ በርሀ።።።።።ብርሃን ኾነ በዝሐ።።።።በዛ በጥሐ።።።በጣ(በጢሕ፡ዱባ) በጽሐ።።።።ደረሰ ታሕትሐ።።።።ፈላ ተመክሐ።።።ተመካ፣ኮራ፣ታበየ ቶስሐ።።።።ጨመረ ተራኅርኃ።።።።ቸር ኾነ ተቃድሐ።።።።ተደነባበረ(የድንበር) ተበውሐ።።ሠለጠነ፣ፈቃድ ተቀበለ ተንሀ(ጥ)።።፡፡አገመ ተዋፅኀ።።።ተፈጨ፣ተቆላ(የመከራ) ተዋህውሀ።።።።ተመላለሰ ተየዉሀ።።።።።የዋህ ኾነ፣ ተሞኘ ተይሀ(ጥ፡ቀላወጠ(ትያህ፡ቀላዋጭ ተጋውሐ።።።ጎረቤት ኾነ ተግሀ።።።።።ተጋ ተጻብሐ፡፡፡፡፡እንዴት አደርክ ተባባለ ተፈሥሐ።።።ደስ ተሰኘ(ፍስሐ፡ደስታ ናሕንሐ።።።።ትርፍርፍ አለ ነስሐ(ጥ)።።።ተጸጸተ(ንስሐ፡ጸጸት) ነስኀ(ላ)።።።።ሸተተ ከረፋ ነቅሀ(ላ)።።።።።።ነቃ ነብሐ(ላ)።።።።ጮኸ (የውሻ) ኖኀ፣ነውሐ።።።ረዘመ(ኖኅ፡ረዝም) ነዝሀ።።።።። ረጨ ነድሐ።።።።ነዳ ነግሀ።።።ነጋ ነጽሐ።።፣ንጹሕ ኾነ ነፍኀ።።።ነፋ       ✝✝ ክፍል✝✝ አምኀ።።።።እጅ ነሣ አመልትሐ።።።።አመሳቀለ አመርግሐ።።።።አንከባለለ አመድቅሐ።።።።ሠራ(የቤት) አመብኩሐ።አናፋ(የእሳት፣ የትንፋሽ አስተማዝሐ።አቀቀጠ፣ አቀማጠለ አርሳሕስሐ።።አረሳሳ፣ አስነወረ አቅየሐይሐ።።አቅላላ አብሐ(ላ)።።።አሰናቀተ፣ ፈቀደ አንሳሕስሐ።።።።አነሳሳ፣ተነሳሳ አንቆቅሐ።።ቋቋ(አንቆቅሖ፡እንቁላል አንባሕብሐ።።።ዱብ ዱብ አደረገ አንካሕክሐ።።።ፈተፈተ አንግሀ።።።ማለደ(የመገስገስ) አውጽሐ።።።አቀረበ፣ቀዳ ኤኀ።።።።ጠፋ አጸንሕሐ።።።አሻተተ አጽናሕንሐ።።።ወዘወዘ(የጽና) ከልሐ።።።።ጮኸ(የሰው፣የከብት) ከልትሐ።።።አሰረ(የነዶ) ኮስሐ።።።።ተናጻ ኮርሀ(ላ)።።።ግድ አለ ወክሐ(ጥ)።።።ደነፋ፣ ፎከረ ወጥሐ(ጥ)።።።ከመረ፣ደረደረ ዛሕዝሐ።።።።ትርፍርፍአለ ዘልሐ(ጥ)።።።ጠመቀ(የጠላ) ዘብሐ(ላ)።።።አረደ ዘግሐ።።።ዘጋ የውሀ(ጥ)።።።።አታለለ ደኅኀ።።።።።ጸና ደምሐ።።።።ጠለቀ ደርገሐ።።።ደረተ፣ሰፋ ደቅሐ።።።።ደቃ፣ቀጠቀጠ ገህሀ።።።።አበራ ጋህግሀ።።።ክፍት ክፍት አደረገ ገምሀ፡፡፡ነጨ፣አለፋ፣መለጠ(የቆዳ ገርሀ(ላ)።።ገራገርኾነ(የእርሻ፣የጠ             ባይ(ገራህት፡እርሻ) ጎርሐ(ጥ)።።።ተተነኳኮለ ገንሐ(ጥ)።።።ተቆጣ ጎሐ።።።።።ጠባ፣ነጋ(ጎሕ፡ ንጋት) ጠብሐ።።።አረደ ጠፋልሐ።።።መዘነ ጠፍሐ።።።።አጨበጨበ ጸሕጽሐ።።።አጎረፈ ጸርሐ፡።።።።ጮኽ ጸብሐ(ላ)።።።ጠባ(የጥባት) ጸብሐ(ጥ)።።።ገበረ ጸንሐ።።።።።።ቆየ ጼሐ።።።።።።ጠረገ ጸፍሐ።።።።።ገለበጠ ፈልሐ።።።።።ፈላ ፈርሀ።።።።።ፈራ ፈትሐ።።።።።ፈታ ፎሐ።።።።።።።ገመሰ ፈጽሐ።።።።።።ሰነጠቀ ✝የ "ሀ" ግስ ተፈጸመ✝ የ " ለ" ግስ ይቀጥላል ማሳሰቢያ፡፡ ይህን አንቀጽ ብትፈልጉ በማስታወሻ እየጻፋችሁ ብትፈልጉ ደግሞ በቃላችሁ አጥኑ፡፡ ይህን ግስ አጥንታችሁ ወደ አእመረ እርባታ ስንገባ በራሳችን ሌላውን ግስም እናረባለን፡፡ የሚጠብቀውን ፤ የሚላላውን እንዴት እናጠናለን ካላችሁ በድምጽ እልክላችኀለው፡፡አስተያየታችሁን ጻፋልኝ፡፡
Show all...
ሉተር ማነው(2).pdf5.20 KB
ማርቲን ሉተር የ ፕሮቴስታንት እምነት መስራች ማን ነው ? እና ምን አይነት ሰው ነው ? ለሚሉ ጥያቄዎች ሙሉ መልስ ።
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.