cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Show more
Advertising posts
42 217
Subscribers
+1524 hours
+1557 days
+58430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
🕊እንኳን አደረሳችኹ ወርሃ ሐምሌን በሰላም ያስፈጽመን የንስሐ ልብ ይሰጠን:: 🕊"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/ 💥ስለ ንስሐ💥 ✝ከቅዱስ ሙሴ ጸሊም የምንማራቸው 7 ነገሮች። ፩, 🌿ቅዱስ አብርሃምን መምሰል( ፈጣሪውን ተመራምሮ አገኘ):: ፪,  🌿ዓለምንና የዓለምን ነገሮች መታው። ፫, 🌿የንስሐ ሕይወት( ንስሐን በትጋት መፈጸም)። ፬, 🌿መታዘዝ (የሚታዘዘውን ሳያጓድል መስራትን)። ፭, 🌿ለሌሎች መኖርን። ፮, 🌿በሰው አለመፍረድን። ፯, 🌿ትሕትናን።            🌿ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!! 1,💥ጥሩ ክርስትና ፈጥኖ የሚገኝ አይደለም፡፡ ትእግስትን ይጠይቃል፡፡ 2,💥ሰይጣን እኛን ኃጢአት በማሠራት አይረካም፡፡ የሚፈልገው ተስፋ ማስቆረጥ ነው፡፡ 3, 💥በእምነት የሚደረግ የትኛውም ጸሎት መፍትሔ አለው፡፡ 4,💥የበጎ ለውጥ እናት ዓላማና ቁርጥ ውሳኔ ናቸው ✝ 4 ነገሮችን በደንብ ልብ እንበል!     1, ✨አላማ     2 ,✨እምነት     3,✨ጥረት     4 ✨ጥንቃቄ =>እነዚኽን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው። 🌿እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤ እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን። ✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት 🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል) 🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር) 🔗https://t.me/zikirekdusn ▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
Show all...
2. St. Theodore the Martyr (Bishop of Pentapolis - the five cities) 3. St. Theodore the Martyr (Bishop of Corinth) 4. The Martyrs Lucianus and Dagnanius (Officers that reached honor through repentance) ✞✞✞ Monthly Feasts 1. Abba Barsauma the Syrian (Father to all Syrian Monks) 2. Abune Estenfase Kirstos (Ethiopian) 3. The “318” Holy Scholars (Fathers assembled at the Council of Nicaea) 4. Saints of the Realm of the Blessed 5. Abba Melchizedek of Mida (Ethiopian) 6. St. Zosimus (Zocima), Righteous (A father who saw the Realm of the Blessed) ✞✞✞ “He saith unto him, Which? Jesus said, Thou shalt do no murder, Thou shalt not commit adultery, Thou shalt not steal, Thou shalt not bear false witness, Honour thy father and thy mother: and, Thou shalt love thy neighbour as thyself. The young man saith unto him, All these things have I kept from my youth up: what lack I yet? Jesus said unto him, If thou wilt be perfect, go and sell that thou hast, and give to the poor, and thou shalt have treasure in heaven: and come and follow me.”✞✞✞ Matt. 19:18-21 ✞✞✞ Salutation to God ✞✞✞ (Translated by Mhr. Esuendale Shemeles with the permission of Dn. Yordanos Abebe)
Show all...
Feasts of Hamle 9 ✞✞✞On this day we commemorate the departure of Abba Helian✞✞✞ ✞✞✞In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, one God. Amen!✞✞✞ ✞✞✞ Abba Helian the Ascetic✞✞✞ =>The Saint was born and raised in a province of Egypt which was called the “Eye of the sun” (Heliopolis?). His parents were called Dista and Kalmona. Because they were good Christians, they taught him this strictly, when he was a child. St. Helian was not only known for his fasting and prayer, but he was also acclaimed for his temporal vocation, metalsmithing as a jeweler. ✞He had wealth, which he earned with his sweat. Particularly, he made his living from making gold and silver ornaments. And he helped the needy from his earnings. While he lived in such a manner, one day, he was tried. One Arabian woman came, asked him to make her earrings and he made her the jewelry from gold. However, after he gave her the earrings, she said, “I will not pay you.” ✞And when he responded saying, “Why my sister?! Why won’t you pay me my labors worth?”, she revealed her figure saying, “Let me give you my womanhood” inviting him for adultery. The Virgin Helian was very much socked by her speech and deed. He made the sign of the Cross before her and went to his home. He spent all night in sadness and when dawn broke, he resolved from his heart and decided to leave this temporal world. ✞The wealth, property, house, land, gold and silver, which he accumulated with his youthful vigor, did not make him hesitant. He called all the destitute to his home and distributed all his property. Because he only was left with the cloth that he was wearing, he filled in jubilation left the city and went to the desert. And since the Lord, Who knows the heart, wished to guide him, He sent him 3 holy anchorites (sowah/invisible fathers). ✞All three appeared before him crowned in luminous diadems, wearing luminous copes and holding luminous staffs. They led him to a wilderness which was scenic to the eyes that had water flowing on its right and left. There were no wild animals let alone people. And when the 3 Saints entered that habitation, gave him a staff which had a gem on top of it and said, “Let us prostrate to God”. ✞After he prostrated, when he looked up, all 3 were gone because they had disappeared [as they were spirit-borne]. Abba Helian wept because he was separated from the Saints. ✞But he strengthened his strife with prayer, fasting and prostrations. The Saint wore and ate leaves. He did not know night because that staff which he received used to emit great light. ✞And when he wanted to travel, it led him and shortened the distance. He lived in such a manner for many years separated from people. Demons tempted him in several ways but they could not resist him. When they were lacking in strength, they went to a city in the likeness of men and made a deal with bandits to kill him. But the bandits while seeing him before them, were not able to reach him as they walking towards him. ✞God in His wisdom lengthened their path. Later, when the bandits were about to perish from weariness and thirst, the Saint though they came to kill him had compassion for them and went to them walking on the water and without using a boat. He fed them from wild berries/fruits, gave them to drink from clean water, and sent them on their way. ✞One day, when he was of old age, those 3 Saints that disappeared from him revealed themselves to him again. And after they had spent the night conversing joyfully, when dawn broke, Abba Helian prostrated towards the east and departed. Thereafter, the 3 Saints shrouded and buried him in his cell. They wrote his accounts, placed it there and disappeared again. ✞✞✞ May the God of the Saints also send us the aid of the Fathers. And may He grant us from the Saint’s blessing.✞✞✞ Annual feasts celebrated on the 9th of Hamle1. Abba Helian the Ascetic
Show all...
✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ✞✞✞ ✝እንኩዋን ለጻድቅ #አባ_ኅልያን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ ✞✞✞ ✝አባ ኅልያን ገዳማዊ✝ ✞✞✞ =>ጻድቁ ተወልዶ ያደገው ዐይነ ፀሐይ በምትባል የቀድሞ የግብፅ ክፍለ ሃገር ሲሆን ወላጆቹ ዲስጣና ካልሞና ይባላሉ:: እነርሱ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩና ገና በልጅነት ይህንኑ አጥብቀው አስተምረውታል:: ቅዱሱ #ኅልያን ጾምን: ጸሎትን ብቻ ያይደለ በሥጋዊ ሙያውም የተመሰገነ አንጥረኛ ነበር:: +በወዙ በላቡ ሠርቶ ያገኘው ሃብት ነበረው:: በተለይ ወርቅና ብር እየሠራ ይተዳደር: ከገቢውም ነዳያንን ያስብ ነበር:: እንዲህ ባለ ግብር ሳለ አንድ ቀን ፈተና መጣበት:: አንዲት ዐረባዊት ሴት መጥታ የጀሮ ጌጥ (ጉትቻ) እንዲሠራላት ትጠይቀውና እርሱም ከወርቅ ይሠራላታል:: የጀሮ ጌጡን ከሰጣት በሁዋላ ግን "ዋጋውን አልሠጥህም" ትለዋለች:: +እርሱም "ምነው እህቴ! የደከምኩበትን ለምን አትከፍይኝም?" ሲላት ገላዋን አጋልጣ "ሴትነቴን ልስጥህ" ብላ ለዝሙት ጠየቀችው:: ድንግሉ ኅልያን ከአነጋገሯና ከድርጊቷ የተነሳ በጣም ደነገጠ:: ከፊቷ ላይ አማትቦ: ገስጿት ወደ ቤቱ ሔደ:: ሙሉ ሌሊት ሲያዝን አደረ:: ሊነጋጋ ሲል በልቡ ወሰነ:: ይሕችን ዓለም ሊተዋትም ቆረጠ:: +በወጣት ጉልበቱ ደክሞ ያፈራው ሃብቱ: ንብረቱ: ቤቱ: መሬቱ: ወርቁ: ብሩ አላሳሳውም:: ነዳያንን ሁሉ ወደ ቤቱ ጠርቶ ሙሉ ንብረቱን አካፈላቸው:: የተረፈችው የለበሳት ልብስ ብቻ ነበረችና ፈጽሞ ደስ እያለው ከተማውን ጥሎ ወደ በርሃ ተሰደደ:: ልቡናን የሚመረምር ጌታ ሊመራው ወዷልና 3 #ቅዱሳን ስውራንን ሰደደለት:: +ሦስቱም የብርሃን አክሊል ደፍተው: የብርሃን ካባ ላንቃ ለብሰው: የብርሃን ዘንግ ይዘው ተገለጡለት:: እየመሩም ወስደው በግራና በቀኝ ውሃ ከሚፈስባት: ደኗ ለዐይን ደስ ከምታሰኝ ዱር አደረሱት:: አካባቢው እንኩዋን ሰው እንስሳትም አልነበሩበትም:: 3ቱ ቅዱሳን ከቦታዋ እንደ ገቡ በላዩዋ ላይ ዕንቁ ያለባት የብርሃን ዘንግ ሰጥተውት "ወደ ፈጣሪ እንስገድ" አሉት:: +ሰግዶ ቀና ሲል ግን 3ቱም በአካባቢው አልነበሩም:: ተሠውረዋልና:: #አባ_ኅልያን ከቅዱሳኑ በመለየቱ ፈጽሞ አለቀሰ:: +ተጋድሎውን ግን በጾምና በጸሎት: በስግደትም አጠነከረ:: ቅዱሱ የሚመገበው: የሚለብሰውም ቅጠል ነበር:: በእርሱ ዘንድ ሌሊት የሚባል አልነበረም:: ምክንያቱም ያቺ ዘንግ ሲመሽ ግሩም የሆነ ብርሃን ታወጣ ነበርና ነው:: +መንገድ መሔድ በፈለገ ጊዜም ትመራው: ጐዳናውንም ታሳጥርለት ነበር:: እንዲህ ባለ ግብር ለበርካታ ዓመታት ከሰው ተለይቶ ኖረ:: አጋንንት በተለያየ መንገድ ፈተኑት:: ግን አልቻሉትም:: አቅም ሲያጥራቸው ወደ ከተማ ሔደው: በሰው አርአያ ሽፍቶችን አናግረው ሊያስገድሉት ሞከሩ:: ነገር ግን ከፊት ለፊት እያዩት ሽፍቶቹ ሲራመዱ ቢውሉም ሊደርሱበት አልቻሉም:: +#እግዚአብሔር በኪነ ጥበቡ መንገዱን ያረዝምባቸው ነበር:: በሁዋላ ግን ሽፍቶቹ በድካምና በውሃ ጥም ሊያልቁ ሆነ:: ጻድቁ ምንም እርሱን ለመግደል ቢመጡም አዘነላቸው:: ባሕሩን ያለ ታንኩዋ እየረገጠ ደረሰላቸው:: ከዱር ፍሬ አብልቶ: ንጹሕ ውሃም አጠጥቶ ሸኛቸው:: +እድሜው እየገፋ ሲሔድ አንድ ቀን እነዛ በፊት የተሠወሩ 3 ቅዱሳን እንደ ገና ተገለጡለት:: በደስታ ሲጨዋወቱ አድረው ሲነጋ አባ ኅልያን ወደ ምሥራቅ ሰግዶ ዐረፈ:: 3ቱ ቅዱሳንም ሥጋውን ገንዘው በበዓቱ ቀበሩት:: ዜና ሕይወቱንም ጽፈው አስቀመጡትና እንደ ገና ተሠወሩ:: =>የቅዱሳን አምላክ ለእኛም የአባቶችን ረድኤት ይላክልን:: ከጻድቁም በረከትን ይክፈለን:: =>ሐምሌ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አባ ኅልያን ገዳማዊ 2.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት (ዘሐምስቱ አሕጉር) 3.ቅዱስ ታውድሮስ ሰማዕት 4.ሰማዕታት ሉክዮስና ድግናንዮስ (በንስሃ ለክብር የበቁ የጦር አለቆች) =>ወርሐዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮዽያዊ) 3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) =>+"+ ጌታ ኢየሱስም "አትግደል: አታመንዝር: አትስረቅ: በሐሰት አትመስክር: አባትህንና እናትህን አክብር: ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ" አለው:: ጐበዙም "ይህንማ ሁሉ ከሕጻንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ:: ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?" አለው:: ጌታ ኢየሱስም "ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሒድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ:: መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ:: መጥተህም ተከተለኝ" አለው:: +"+ (ማቴ. 19:18) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
Show all...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

✞እንኳን አደረሰን ! •ብጹዕ አባ #ኪሮስ፥ ዘአንደየ ርዕሶ በእንተ መንግሥተ ሰማያት፤ •ብጹዕ አባ ኪሮስ፥ ዘአጥረየ ንዴተ ከመ ሐዋርያት፤ ወትረ ትጋሃ ከመ መላእክት፤ መዓልተ ጸሎታተ፤ ወሌሊተ ስግደታተ፤ ፈጸመ ሥርዓተ መነኮሳት፤ አዕረፈ በክብር ወበስብሐት! •ቅዱስ ወክቡር፤ ብእሴ እግዚአብሔር፤ ለአሕዛብ መምህር፤ አባ ብሶይ ኮከበ ገዳም፤ ዘደብረ አባ መቃርስ ወዘኲሉ ዓለም! ቸሩ መድኀኔ ዓለም ከበረከታቸው ይክፈለን! https://t.me/zikirekdusn
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.