cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopia Meteorology Institute

World-class meteorological services in Ethiopia.

Show more
Advertising posts
453
Subscribers
No data24 hours
+107 days
+7230 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በሚዲያ ኮምዩኒኬሽን ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ሰነድ ተፈራረመ ////////////////////////////////// የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ የሚቲዎሮሎጂ መረጃን ለህብረተሰቡ ከማሰራጨት አንፃር የሚዲያ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያነሱ ሲሆን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት /ኢዜአ/ ደግሞ አንጋፋና በተደራሽነቱም ተመራጭ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ምክትል ስራ አስፈፃሚዋ ቤተልሄም አበባውም የሚቲዎሮሎጂ መረጃ ለህብረተሰቡ እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ ኢዜአ በአገሪቱ ውስጥ ባሉት 38 ቅርንጫፎች በመጠቀም ተደራሽ በማድረግ አገራዊ ግዴታውን እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡
1000Loading...
02
እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2024 የሚኖረው የአየር ሁኔታ አዝማሚያ በእርሻ ሥራ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ /////////////////////////////////// በሚቀጥሉት አስር ቀናት በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የእርጥበት ሁኔታ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡ ይህም ሁኔታ አስቀድመው ተዘርተው በተለያየ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ የበልግ ሰብሎች፣ ለቋሚ ተክሎችና ለጓሮ አትክልቶች የውሃ ፍላጎትን ከማሟላት አኳያ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋ፡፡ በተጨማሪም በጁን ወር ለሚዘሩ የመኽር ሰብሎች የማሳ ዝግጅት ለማከናወንም ሆነ የተዘጋጁ ማሳዎችን በሰብል የመሸፈን ተግባራትን ለማከናወን አዎንታዊ ሚና ስለሚኖረው አርሶ አደሮች ይህንኑ መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም የሚያስችል ዝግጅት ከወዲሁ ማከናወን ያስፈልጋል፡፡
1091Loading...
03
እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 30/2024 የሚኖረው የአየር ጠባይ ///////////////////////////////////////// በመደበኛው ሁኔታ ወቅታዊው የክረምት ዝናብ ቀደም ብሎ በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የሚጀምር ሲሆን፤ በሂደትም እየተጠናከሩ ከሚሄዱ የክረምት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ጋር ተያይዞ በጁን ወር አብዛኛው የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ያዳርሳል :: በመጪው የጁን ወር ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ላይ አንጻራዊ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው የአሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በተለይም በምዕራብ አጋማሽ ኢትዮጵያ ዝናቡ በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተሻለ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም ላይ አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩ ደመናዎች ላይ በመነሳት ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአጠቃላይ በጁን ወር ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ዞኖች፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ፤አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና ሀረር፤ ከአማራ ክልል ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፤ ከትግራይ ክልል ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ከፋ፣ ሸካ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ፣ አማሮ፣ አሌ፣ ቡርጂ፣ ደራሼ፣ ባስኬቶ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ እና ጌዲዮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ፣ ሃዲያ፣ ጠምባሮ እና የየም ልዩ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል ማዣንግ፣ አኝዋክ፣ የኢታንግ ልዩ ዞን እና ንዌር ዞኖች፣ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
1020Loading...
04
እ.ኤ.አ ጁን 11 እስከ 20/2024 የሚኖረው የአየር ሁኔታ ////////////////////////////////////////// በጁን ሁለተኛው አሥር ቀናት በመደበኛ ሁኔታ በደቡብ ምዕራብ" በምዕራብ" በሰሜን ምዕራብና በመካከለኛው አካባቢዎች ላይ ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች እየተጠናከሩ የሚሄዱ ሲሆን፤ በአንጻሩ በሰሜንና በሰሜን ምሥራቅ ላይ አልፎ አልፎ ከሚኖረው መጠነኛ ዝናብ በስተቀር ደረቅና ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ያመዝናል፡፡ በመጪው የጁን ሁለተኛው አስር ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከቀን ወደ ቀን እየተሻሻሉ ከመሄዳቸውጋር ተያይዞ፤ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
860Loading...
05
እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2024 የሚኖረው የአየር ሁኔታ //////////////////////////////// በመደበኛ ሁኔታ የክረምት ዝናብ በጁን በመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት የደቡብ ምዕራብና የምዕራብ የሀገሪቱን አካባቢዎች ጨምሮ ቀስ በቀስ የሰሜን ምዕራብ ክፍሎችን የሚያዳርስበት ጊዜ ነው ። በሚቀጥለው አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በአጠቃላይ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፤ ከአማራ ክልል ማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ፣ ካማሺ፣ መተከል እና የማኦ ኮሞ ልዩ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ከፋ፣ ሸካ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባስኬቶ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ እና ጌዲዮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ፣ ሃዲያ፣ ጠምባሮ እና የየም ልዩ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል ማዣንግ፣ አኝዋክ፣ የኢታንግ ልዩ ዞን እና ንዌር ዞኖች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ስርጭት ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም ከኦሮሚያ ክልል ባሌ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ዞኖች፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ፤አዲስ አበባ፣ ድሬ ዳዋ እና ሃረር ከአማራ ክልል ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፤ ከትግራይ ክልል ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ፣ አማሮ፣ አሌ፣ ቡርጂ፣ ደራሼ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፤ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በሰሜን ምሥራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ላይ ከ35 እስከ 35 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ ትንበያዎች ያመላክታሉ፡፡
920Loading...
06
ለሁለት ቀን በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይትና ውሳኔ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ በውጤታማነት ተጠናቀቀ
1040Loading...
07
Media files
1500Loading...
08
በአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ 4ኛው የአየር ንብረት አገልግሎቶችና ተዛማጅ መተግበሪያዎች ፕሮግራም /ClimSA/ አህጉራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሄደ //////////////////////// 4ኛው በአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ የአየር ንብረት አገልግሎቶችና ተዛማጅ መተግበሪያዎች ፕሮግራም /ClimSA/ አህጉራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል ተካሄደ፡፡ ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጀት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ፈጠነ ተሾመ ኢትዮጵያን ለስብሰባቸው በመምረጣቸው በማመስገን አዲስ አበባ ሁለተኛ ቤታቸው እንደሆነና የሚያደርጉት ቆይታም የተሳካ እንዲሆን በመመኘት የአየር ንብረትና ጠባይ ድንበር የማይገድበው መሆኑን በመግለፅ ሁሉም በሳይንሱ ዙሪያ ያሉ ተመራማሪዎች በጋራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ዶ/ር አንድሬ ካምጋ የአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልእክት የአየር ንብረት ለውጥን መዋጋት በአለም አቀፍ፣ በአህጉር፣ በብሔራዊ እና በአካባቢያዊ ደረጃ እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን የገለፁ ሲሆን አያይዘውም ተቋማቸው የአየር ንብረት መረጃን ለግብርና፣ ለውሃ፣ ለጤና እንዲሁም ለአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፅ/ቤት የዳይሬክተሯ ተወካይ ዶ/ር ማሪያ የአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ከአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ ጋር በመሆን የማህበረሰቡን ህይወትና ንብረትን ከአደጋ ለመታደግ በጋራ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል፡፡ የእለቱም ስብሰባ በአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ/ACMAD/ እና በአጋር ፕሮጀክቶች ትግበራ ላይ ያለውን ሂደት እና ስኬቶችን በመገምገም፣ የማእከሉን የሚቀጥለውን ዓመት የሥራ ዕቅድ እና በጀት ገምግሞ በማጽደቅ እንዲሁም ከሌሎች ፕሮጀክቶች እና አጋሮች ጋር በሚኖረው ትብብር ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ አጀንዳዎቹንም በጋራ በማፅደቅ ተጠናቋል፡፡
1290Loading...
09
በአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ 4ኛው የአየር ንብረት አገልግሎቶችና ተዛማጅ መተግበሪያዎች ፕሮግራም /ClimSA/ አህጉራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
1310Loading...
10
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል-አሶሳ ያስገነባው የG+2 ህንፃ አስመረቀ። ////////////////////////////////////// ኢንስቲትዩቱ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል-አሶሳ ከተማ ላይ ያስገነባውን የG+2 ህንፃ የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር የሚንስትሩ አማካሪ፣ የክልሉ የቢሮ ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ.ም አስመረቀ። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርና በዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ኢንስቲትዩቱ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሚቲዎሮሎጂ መረጃ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በሰፊው እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። የእለቱ የክብር እንግዳ በውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር በሚንስትር ድኤታ ማእረግ የሚንስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ኢንስቲትዩቱ በአሶሳ ከተማ ላይ ካስገነባው ህንፃ በተጨማሪ የሚሰጠው መረጃ ከእውነታው ጋር የተቀራረበ እንዲሆን በሰራተኛ አቅም ግንባታ ላይ እያከናወነ ያለውን ስራ አድንቀዋል። በኢንስቲትዩቱ የመሰረታዊ የሚቲዎሮሎጂ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ኃ/ማሪያም ስለ ህንፃው አጠቃላይ ማብራሪያ በመስጠት የምረቃ ፕሮግራሙ ተካሂዷል፡፡
2261Loading...
11
ኢንስቲትዩቱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ክረምት 2016/7 ዓ.ም ወቅት መደበኛና ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት እንደሚኖር ትንበያ ሰጠ /////////////////////////////// የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በቀጣዩ የክረምት ወቅት ክልሉን ጨምሮ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት እንደሚኖራቸው ክልላዊ የበልግ 2016 አመት የአየር ሁኔታ ግምገማና የቀጣይ የክረምት 2016/17 ወቅት የአየር ሁኔታ ትንበያ ይፋ ባደረገበት መድረክ ላይ አስታውቋል። በመድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ፈጠነ ተሾመ ኢንስቲትዩቱ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አስራ አንድ የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት መስጫ ማእከሎች በማደራጀት በእነርሱ አማካኝነት የአየር ሁኔታ ትንበያዎችን በመስጠት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የአየር ሁኔታ ትንበያ መረጃ በድንበር እንደማይሰወሰንና ተቋሙ ለትንበያው ዓለም አቀፍ መረጃዎችንም ጭምር እንደሚጠቀም በመግለፅ የኢንስቲትዩቱን መረጃዎች በአግባቡ በመጠቀም ምርት እና ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር በህይወት እና ንብረት ላይ የሚደርስ ጉዳትን መቀነስ እንደሚያስችልም አብራርተዋል። በመድረኩ አጠቃላይ አገራዊ ትንበያ በኢንስቲትዩቱ የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር በዶ/ር አሳምነው ተሾመ፣ ክልላዊ የበልግ ወቅት ትንበያ ግምገማና ቀጣይ ክረምት ወቅት ትንበያ በአቶ ደጀኔ አያና እንዲሁም የዘርፍ ተኮሩን በአቶ ወንድም አዱኛው ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
1681Loading...
12
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በቤንሻንጉል ጉምዝ የሚቲዎሮሎጂ  አገልግሎት ማእከል ውስጥ ያስገነባውን የG+2 ህንፃ ዛሬ ግንቦት 17 ቀን 2016 በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚንስትሩ አማካሪ በአቶ ሞቱማ መቃሳ እንዲሁም በኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በአቶ ፈጠነ ተሾመ ተመረቀ።
1550Loading...
13
በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማእከል ክልላዊ የበልግ 2016ዓ.ም የአየር ሁኔታ ግምገማና የክረምት 2016/17 ወቅት  የአየር ሁኔታ ትንበያ መድረክ ተጀመረ።
1620Loading...
14
ESAT
2030Loading...
15
H.E. Mr. Fetene Teshome Director of Ethiopian Meteorology Institute and WMO Regional Association I /Africa/ President about the meeting of RA-I 19th Session
2190Loading...
16
አሻም ቲቪ
2991Loading...
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በሚዲያ ኮምዩኒኬሽን ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ሰነድ ተፈራረመ ////////////////////////////////// የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ የሚቲዎሮሎጂ መረጃን ለህብረተሰቡ ከማሰራጨት አንፃር የሚዲያ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያነሱ ሲሆን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት /ኢዜአ/ ደግሞ አንጋፋና በተደራሽነቱም ተመራጭ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ምክትል ስራ አስፈፃሚዋ ቤተልሄም አበባውም የሚቲዎሮሎጂ መረጃ ለህብረተሰቡ እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ ኢዜአ በአገሪቱ ውስጥ ባሉት 38 ቅርንጫፎች በመጠቀም ተደራሽ በማድረግ አገራዊ ግዴታውን እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡
Show all...
እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2024 የሚኖረው የአየር ሁኔታ አዝማሚያ በእርሻ ሥራ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ /////////////////////////////////// በሚቀጥሉት አስር ቀናት በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የእርጥበት ሁኔታ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡ ይህም ሁኔታ አስቀድመው ተዘርተው በተለያየ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ የበልግ ሰብሎች፣ ለቋሚ ተክሎችና ለጓሮ አትክልቶች የውሃ ፍላጎትን ከማሟላት አኳያ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋ፡፡ በተጨማሪም በጁን ወር ለሚዘሩ የመኽር ሰብሎች የማሳ ዝግጅት ለማከናወንም ሆነ የተዘጋጁ ማሳዎችን በሰብል የመሸፈን ተግባራትን ለማከናወን አዎንታዊ ሚና ስለሚኖረው አርሶ አደሮች ይህንኑ መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም የሚያስችል ዝግጅት ከወዲሁ ማከናወን ያስፈልጋል፡፡
Show all...
እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 30/2024 የሚኖረው የአየር ጠባይ ///////////////////////////////////////// በመደበኛው ሁኔታ ወቅታዊው የክረምት ዝናብ ቀደም ብሎ በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የሚጀምር ሲሆን፤ በሂደትም እየተጠናከሩ ከሚሄዱ የክረምት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ጋር ተያይዞ በጁን ወር አብዛኛው የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ያዳርሳል :: በመጪው የጁን ወር ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ላይ አንጻራዊ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው የአሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በተለይም በምዕራብ አጋማሽ ኢትዮጵያ ዝናቡ በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተሻለ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም ላይ አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩ ደመናዎች ላይ በመነሳት ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአጠቃላይ በጁን ወር ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ዞኖች፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ፤አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና ሀረር፤ ከአማራ ክልል ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፤ ከትግራይ ክልል ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ከፋ፣ ሸካ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ፣ አማሮ፣ አሌ፣ ቡርጂ፣ ደራሼ፣ ባስኬቶ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ እና ጌዲዮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ፣ ሃዲያ፣ ጠምባሮ እና የየም ልዩ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል ማዣንግ፣ አኝዋክ፣ የኢታንግ ልዩ ዞን እና ንዌር ዞኖች፣ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Show all...
👍 2
እ.ኤ.አ ጁን 11 እስከ 20/2024 የሚኖረው የአየር ሁኔታ ////////////////////////////////////////// በጁን ሁለተኛው አሥር ቀናት በመደበኛ ሁኔታ በደቡብ ምዕራብ" በምዕራብ" በሰሜን ምዕራብና በመካከለኛው አካባቢዎች ላይ ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች እየተጠናከሩ የሚሄዱ ሲሆን፤ በአንጻሩ በሰሜንና በሰሜን ምሥራቅ ላይ አልፎ አልፎ ከሚኖረው መጠነኛ ዝናብ በስተቀር ደረቅና ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ያመዝናል፡፡ በመጪው የጁን ሁለተኛው አስር ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከቀን ወደ ቀን እየተሻሻሉ ከመሄዳቸውጋር ተያይዞ፤ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Show all...
እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2024 የሚኖረው የአየር ሁኔታ //////////////////////////////// በመደበኛ ሁኔታ የክረምት ዝናብ በጁን በመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት የደቡብ ምዕራብና የምዕራብ የሀገሪቱን አካባቢዎች ጨምሮ ቀስ በቀስ የሰሜን ምዕራብ ክፍሎችን የሚያዳርስበት ጊዜ ነው ። በሚቀጥለው አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በአጠቃላይ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፤ ከአማራ ክልል ማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ፣ ካማሺ፣ መተከል እና የማኦ ኮሞ ልዩ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ከፋ፣ ሸካ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባስኬቶ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ እና ጌዲዮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ፣ ሃዲያ፣ ጠምባሮ እና የየም ልዩ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል ማዣንግ፣ አኝዋክ፣ የኢታንግ ልዩ ዞን እና ንዌር ዞኖች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ስርጭት ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም ከኦሮሚያ ክልል ባሌ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ዞኖች፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ፤አዲስ አበባ፣ ድሬ ዳዋ እና ሃረር ከአማራ ክልል ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፤ ከትግራይ ክልል ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ፣ አማሮ፣ አሌ፣ ቡርጂ፣ ደራሼ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፤ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በሰሜን ምሥራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ላይ ከ35 እስከ 35 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ ትንበያዎች ያመላክታሉ፡፡
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ለሁለት ቀን በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይትና ውሳኔ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ በውጤታማነት ተጠናቀቀ
Show all...
1
በአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ 4ኛው የአየር ንብረት አገልግሎቶችና ተዛማጅ መተግበሪያዎች ፕሮግራም /ClimSA/ አህጉራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሄደ //////////////////////// 4ኛው በአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ የአየር ንብረት አገልግሎቶችና ተዛማጅ መተግበሪያዎች ፕሮግራም /ClimSA/ አህጉራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል ተካሄደ፡፡ ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጀት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ፈጠነ ተሾመ ኢትዮጵያን ለስብሰባቸው በመምረጣቸው በማመስገን አዲስ አበባ ሁለተኛ ቤታቸው እንደሆነና የሚያደርጉት ቆይታም የተሳካ እንዲሆን በመመኘት የአየር ንብረትና ጠባይ ድንበር የማይገድበው መሆኑን በመግለፅ ሁሉም በሳይንሱ ዙሪያ ያሉ ተመራማሪዎች በጋራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ዶ/ር አንድሬ ካምጋ የአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልእክት የአየር ንብረት ለውጥን መዋጋት በአለም አቀፍ፣ በአህጉር፣ በብሔራዊ እና በአካባቢያዊ ደረጃ እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን የገለፁ ሲሆን አያይዘውም ተቋማቸው የአየር ንብረት መረጃን ለግብርና፣ ለውሃ፣ ለጤና እንዲሁም ለአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፅ/ቤት የዳይሬክተሯ ተወካይ ዶ/ር ማሪያ የአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ከአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ ጋር በመሆን የማህበረሰቡን ህይወትና ንብረትን ከአደጋ ለመታደግ በጋራ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል፡፡ የእለቱም ስብሰባ በአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ/ACMAD/ እና በአጋር ፕሮጀክቶች ትግበራ ላይ ያለውን ሂደት እና ስኬቶችን በመገምገም፣ የማእከሉን የሚቀጥለውን ዓመት የሥራ ዕቅድ እና በጀት ገምግሞ በማጽደቅ እንዲሁም ከሌሎች ፕሮጀክቶች እና አጋሮች ጋር በሚኖረው ትብብር ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ አጀንዳዎቹንም በጋራ በማፅደቅ ተጠናቋል፡፡
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ 4ኛው የአየር ንብረት አገልግሎቶችና ተዛማጅ መተግበሪያዎች ፕሮግራም /ClimSA/ አህጉራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
Show all...
👍 1

👍 4