cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopia Meteorology Institute

World-class meteorological services in Ethiopia.

Show more
Advertising posts
405
Subscribers
+524 hours
+117 days
+4030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

04:05
Video unavailableShow in Telegram
ዋልታ አዲስ
Show all...
👍 1
07:06
Video unavailableShow in Telegram
Etv- Afan Oromo
Show all...
ኢንስቲትዩቱ እየሰጠ ያለ ትንበያ በተጨባጭ መሬት ላይ እየተከሰተ ካለው ጋር የቀረበ መሆኑን ተገለፀ ///////////////////////////////////////////////////// የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ደንበኞቹና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የክረምት ወቅት ትንበያ በኢንስቲትዩቱ የሚቲዎሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ ይፋ በተደረገበት መድረክ የመጪው ክረምት 2016/17 በትሮፒካል ፓስፊክ ውቅያኖስ የባህር ወለል ሙቀት ከመደበኛ በታች መሞቅ (ENSO-LA NINA) እንዲሁም የሰሜናዊ ህንድ ውቅያኖስ የባህር ወለል ሙቀት ከመደበኛ በላይ መሞቅ (Positive IOD) ሆኖ ሊቆይ እንደሚችል የሚቲዎሮሎጂ የትንበያ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ ክረምት ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሰሜን፤ ሰሜን ምዕራብ፤ ምዕራብ፤ ደቡብ ምዕራብ፤ መካከለኛው፤ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙ በትንበያው ተመላክቷል፡፡ በተጨማሪም የደቡብ የሀገሪቱ ቆላማ አካባቢዎች ከሚጠበቀዉ Positive IOD ክስተት ጋር በተያያዘ በነሀሴና በመስከረም ወራቶች ዝናብ ሊያገኙ እንደሚችሉ በትንበያው መድረክ ላይ ተጠቁሟል፡፡ ትንበያው በግብርናው በውሃው እንዲሁም በጤናው ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ በባለሙያዎች የቀረበ ሲሆን ተሳታፊዎችም ኢንስቲትዩቱ እየሰጠ ያለ ትንበያ በተጨባጭ መሬት ላይ እየተከሰተ ካለው ጋር የተቀራረበ መሆኑን በመግለፅ ለዚህም ተቋሙ በቴክኖሎጂና በሰው ሃይል እራሱን ማብቃቱ መሆኑን ተገልጿል፡፡
Show all...
የአየር ጠባይ ተጽዕኖ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ጉዳይ መሆኑን ተገለፀ ////////////////////////////////////////////////////////// የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የበልግ ወቅት 2016 ትንበያ በሚገመገምበትና የክረምት 2016/17 ዓ.ም የሚኖረውን የወቅት የአየር ጠባይ ትንበያ ይፋ ለማድረግ ባዘጋጀው መድረክ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚንስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የአየር ጠባይ ተጽዕኖ የሁሉንም ማኅበረሰብ፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትንና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን የሚመለከት ጉዳይ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ኢንስቲትዩቱም ይሄንን ኃላፊነት በዋናነት ወስዶ የሚሠራ ቢሆንም የባለ ድርሻና ተባባሪ አካላት እንዲሁም የደንበኞች ሙሉ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝነት በመኖሩ ከዘርፉ የሚጠበቀውን የአገልግሎት ጥራት፣ መሻሻል በሚገባቸው ደረጃ እንዲሻሻሉ የአገልግሎት ሰጪውና ተጠቃሚው ሴክተሮች ቅንጅት እና ተናቦ መስራት ወሳኝ በመሆኑ የተጀመረውን ብሄራዊ የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕቀፍ (National Framework on Climate Service- NFCS) ተግባራዊነት የሁሉም የፌደራልና የክልል ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡
Show all...
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መልእከት /////////////////////////////////////////// የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ኢንስቲትዩቱ ያዘጋጀው የዛሬው መድረክ የበልግ ወቅት የአየር ሁኔታ ትንበያ ትክክለኛነትና ከወቅቱ የአየር ጠባይ ጋር ተያይዘው የተከሰቱትን መልካም አጋጣሚዎችም ሆነ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን በተመለከተ ግምገማ የሚካሄድበትና በቀጣዩ ክረምት ወቅት፣ ሊኖር የሚችለውን የአየር ሁኔታ አስቀድሞ በመተንበይ ሊፈጠሩ የሚችሉትን ጎጂ ክስተቶች እንዲሁም መልካም የአየር ሁኔታ አስቀድሞ በመተንበይ የሀገራችን ሕዝቦች ተገቢውን ቅድመ-ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል አቅጣጫ የሚጠቁም በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት መሰጠት ይገባል ብለዋል፡፡
Show all...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የበልግ ወቅት ትንበያ ግምገማና የክረምት ወቅት ትንበያ ይፋ የሚያደርግበት መድረክ ተጀመ።
Show all...
👍 2
የክልል ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማእከላት የመጡ ባለሙያዎች አዲሱን የኢንስቲትዩቱን ህንጻ ጎበኙ፡፡ /////////////////////////// ከ11ዱ የክልል የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከላት የተወጣጡ የሚቲዎሮሎጂ ተመራማሪዎች ኢንስቲትዩቱ አዲስ እያስገነባ ያለውን የቦሌ ህንጻ ግንባታ ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱም የክልል ሚቲዎሮሎጂ ማስተባበሪያ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ሄኖክ ሀይሉ የእንኳን ደህና መጣችሁ  ንግግር  ባደረጉበት ወቅት ስለ ህንጻው ጠቅለል ያለ መረጃ ሰጥተዋል፡፡ በመቀጠልም በኢንስቲትዩቱ መሀንዲስ በአቶ ጌታቸው ኃ/ሚካኤል       የህንጻውን ውስጣዊ ይዘት ምን እንደሚመስል ያስጎበኙ ሲሆን ህንፃው ሁለት ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ ስቲዲዮ፣ የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎች የሚሰጥባቸው ክፍሎች፣ደረጃውን የጠበቀ ቤተ መጽሐፍት፣ከ1200 በላይ ሰው የሚይዝ ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያካተተ ህንጻ እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡ በመጨረሻም መንግስት ብዙ ገንዘብ ያፈሰሰበት ይህ ዘመናዊ ህንጻ ተጠናቆ በመስከረም ወር ላይ እንደሚገባ የሚጠበቅ ሲሆን በዋናው መስሪያ ቤትም ሆነ በክልል ማዕከላት የሚገኙ ሰራተኞች ሀገራችን ለሚቲዎሮሎጂ የሰጠችውን ቦታ በመገንዘብ ጠንክረው ለመስራት ዘመኑ በሚፈልገው መጠን እራስን በማብቃት ኃላፊነታችንን መወጣት ያስፈልግል የሚል መልዕክትም ተላልፏል፤ ይህ ህንጻ እዚህ ለማድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅርበት ክትትል እያረጉ የሚገኙትን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመን በሌሉበት አመስግነዋል፡፡
Show all...
👍 3
03:58
Video unavailableShow in Telegram
Addis Media Network about RA-I 19th session.
Show all...
👍 1
03:31
Video unavailableShow in Telegram
NBC- About RA-I 19th Session.
Show all...