cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አስኳላ💚💛❤

እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉና ያዝናናሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም አይነት ፅሁፎች ከተለያዩ ቦታዎች እየለቀምኩ አቀርባለሁ። ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለክ። እዚህ የሚለቀቁ ፅሁፎች እኔ የተናገርኳቸው እና የፃፍኳቸው ብቻ አይደሉም። ከመፃፍ፣ከሶሻል ሚዲያ እና ከተለያዩ ሰዎች የሰበሰብኳቸው ጭምር ናቸው። Comment▹ @Meklite21

Show more
Advertising posts
3 031
Subscribers
+424 hours
+477 days
+6530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ጀግናዬ.......!!         ፍቅር በፊት ያስቀመጥካቸውን መስፈርቶች አስጥሎ፣ ለእራስህ የሰጠሀውን ክብር አሳንሶ፣ በማትጠብቀው ሰዓት የማይሆን ሰው ላይ ቢጥልህም ማፍቀርህን ላታቆም ትችል ይሆናል፣ እንደማታገኛት እያወክም ከውስጥህ ለማውጣት ይከብድሃል። ለዘመናት ከአንድ ሰው ውጪ ሌላ መመልከት ያልቻሉ፣ በአንድ ሰው ፍቅር የታሰሩ፣ እራሳቸውን የሰወሩ፣ ማንነታቸውን ያስገዙ ሰዎች አሉ። እራሳቸውን መቆጣጠር ሲኖርባቸው ማንነታቸውን በሙሉ የሚሰማቸው ፍቅር እንዲቆጣጠራቸው ያደርጋሉ፤ ህይወታቸውን ቀምቶ በባዶ እንዲያስቀራቸው፣ በጭንቀት ብዛት ሰውነታቸውን እንዲያሳጣቸው ይፈቅዳሉ። የማያፈቅርህን ሰው ታፈቅራለህ ያምሃል፤ ከልብህ ያፈቀርከው፣ በሙሉ ልብህ ያመንከው ሰው ይከዳሃል ይባስ ትታመማለህ። ነገር ግን ይህን አስብ፣ መዝነህ ያልጀመርከው ፍቅር መዝኖ አይከፍልህም፤ እውነት ስታፈቅር አለመፈቀር፣ መከዳት፣ መገፋት አብሮ ሊመጣ እንደሚችል አስታውስ። ከልብህ ወደህ ብትጎዳ፣ በሰውነትህ አፍቅረህ ብትታመም የእውነት ፍቅርን አይተሃልና ዳግም ምላሹን በመጠበቅ እራስህን አታድክም፣ እራስህን አታሳምም። በምትኩ ለአዲሱ የህይወትህ ምዕራፍ እራስህን አዘጋጅ። ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Tiktok channel👇👇 https://www.tiktok.com/@tamrat624?_t=8kb1090E501&_r=1 Telegram channel 👇👇👇 ➱ https://t.me/Asreseehttps://t.me/Asreseehttps://t.me/Asresee
Show all...
3👍 1
ፈገግ ብትል አፏን ገልባ   የ ዓለም ፅልመት ረገፈች፤ ድንግል ኮከብ ተሽኮርምማ ከጥርሷ ላይ ተደገፈች፤ /ልጅቱ_እንደዚህ ናት ለሰው ደስታ/ ትወጣለች ማልዳ ቀድማ የሳቅ መባ ልታበስር፤ እስከሚመሽ ማን ያውቅና እንባ እንዳለ_ትራሷ ስር፤ ፍካት በቃኝ እግዜርዬ ብርሃን_ፀሃይ አታብራልኝ፤ ከዳመነው ሆዷ ታግባኝ ልቧን  ገልጠህ አራራልኝ፤ ዓይኗን አርገኝ በጭለማ በቀን ሳቋ አታክንፈኝ፤ ከ ጥርሷ ጋር ውል የለኝም ሀዘኗ ነው  የለከፈኝ። /እንባዋ ነው ያስለፈፈኝ/ ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Show all...
3👍 1👏 1
#ነይ_አብረን_እንጠጣ!! ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል ጌሾ ነይ እንጠጣ ውዴ ላለመባል ዋሾ እውነቱን እውነቱን እንድንነጋገር ደጋግመን እንጠጣ ነይ አብረን እንስከር አንቺም የልብሽን እኔም የልቤን ምት በጌሾ በብቅል በሰካራም ድፍረት መደባበቅ ሳይኖር ከማስመሰል ወጥተን ከጠጁ ከጠላው እንጠጣ ደጋግመን!!! እውነት በመናገር ነፃነት እንውጣ ማስመሰል ይገፈፍ ነይ አብረን እንጠጣ         ........የእናቴ ልጅ-(Tame).......... ...       .......        ........... @Meklite21 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Show all...
3👍 1🔥 1
"የዛሬ መቶ ዓመት ማንኛችንም አልነበርንም.....ከመቶ ዓመት በኋላ አንዳችንም አንኖርም። ይህንን ከልባችን ማሰብና አስረግጠን መረዳት ብንችል ትንሽ መተዛዘን፣የተሻለ መተሳሰብ፣ ያለንን ተከፋፍለንና ተረዳድተን አብረን በሠላም መኖር እንችል ይሆን? አገር የጭንቅላታችንን እንጂ የቆዳ ስፋቷን ያህል አይደለችምና ።" .......የእናቴ ልጅ-(Tame).......... ...       .......        ........... @Meklite21 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Show all...
👍 8 7
____________________________ የተገላቢጦሽ ሆኖ ጭካኔ እና እራስ ወዳድነት የጥንካሬ ምልክቶች፤ የዋህነትና፣ ይቅርባይነት የሞኝነት ባህሪ ይመስሉናል። እንደ መልካም ስራ ጥንካሬን የሚፈትን ምን ነገር አለ?? ▸ ይቅርታ መጠየቅ ቀላል አይደለም፤ ተበድሎ ይቅር ማለት ግን ይበልጥ ይከብዳል። በድለን መርሳቱ ላይከብደን ይችላል፤ ተበድለን መርሳት መቻል ግን ጥንካሬን ይሻል። እየተጠሉ መውደድ፤ እየተዋረዱ ክብር መስጠት፤ እየተገፉ አለሁኝ ማለት፤ ጠንካራ ማንነትን ይጠይቃል። ▸ ብዙዎቻችን ደግነትን እንደ ደካማ ጎን አድረገን እናየዋለን። ትዕግስት እንደ ፍርሃት፤ ይቅር ባይነት እንደ ውርደት፤ አክብሮት እንደማስመሰል እየተቆጠረ መልካምነት ከዘመኑ ጋር የማይሄድ ባህሪ እየመሰለን እየሸሸነው ነው። ▸ ዋሽተን ማሳመን ብልጠት፤ እራሳችንን ማስቀደም ብልህንት፤ ሌሎችን ማዋረድ ክብር የሚያስገኝልን እየመሰለን ከሰብዓዊው ማንነታችን ቀስ በቀስ እንሸሻለን። 🔹እውነታው ግን ይቅር እንደማለት፤ ሌሎችን እደማክበር፤ ፍቅር ለሚገባው ፍቅር እንደመስጠት ፈታኝ እና ጥንካሬን የሚጠይቁ ምን ነገሮች አሉ? (ካህሊል ጂብራን) .......የእናቴ ልጅ-(Tame).......... ...       .......        ........... @Meklite21 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Show all...
👏 4 2
ከሰዎች ጠብቀሽ ላታገኚው ትችያለሽ፣ በወዳጆችሽ መባል ፈልገሽ አልተባልሽም ይሆናል፣ የተለየ ቦታ በሰጠሻቸው ሰዎች እንዲሁ የተለየ ስፍራ አልተሰጠሽም ይሆናል፡፡ ነገር ግን አንድ ነገር አስታውሺ የትም ሳትሔጂ፣ ማንንም ሳትመስዪ፣ ከማንም ሳትወዳጂ፣ ማንም ሳይኖርሽ፣ ምንም ሳትጨምሪ እንዲሁ ውብ ነሽ። ውበትሽም የግድ በሰዎች ሊነገርና ሊደነቅ አይገባም። ዛሬ ውብ እንደሆንሽ የነገረሽ ሰው ነገም ውብ ስለመሆንሽ እንደሚመሰክር እርግጠኛ መሆን አትችይም፡፡ አዳማቂ የማይፈልገው ውበትሽ ከትምህርት ደረጃሽ የመጣ አይደለም፣ ከስራሽ የመጣ አይደለም፣ ከቤተሰቦችሽ የመጣ አይደለም፣ ከጓደኞችሽ የመጣ አይደለም፡፡ የውበትሽ ምንጭ የአምላክሽ ልጅ መሆንሽ ነው፤ የውበትሽ መነሻ ሴትነትሽ፣ አንቺነትሽና ጥልቁ ማንነትሽ ነው። ልንገርሸ ውብ ነሽ! እስካከበርሽው ድረስ ሴት በመሆንሽ ብቻ ቆንጆ ነሽ፤ አሁን ያለሽበት ስፍራ በመገኘትሽ ብቻ ብርቱ ነሽ፣ እንዳቅምሽ ስለተንቀሳቀስሽ ብቻ ጠንካራ ሴት ነሽ፡፡ አለም የሚያደንቅልሽን ሳይሆን በአምላክሽ መንፈስ የተቃኘውን ውስጣዊ ውበትን የሚያዩ፣ የስብዕናሽን ጥልቀት የሚመረምሩ፣ እንዲሁ አይተው የሚማረኩብሽ ሰዎች እስኪከቡሽ ድረስ ውበትሽን ለእራስ ተናገሪ፣ ጥንካሬሽን ደጋግመሽ ለእራስሽ መስክሪ። የሚረዱሽን መምረጥ፣ የማይረዱሽንም የመተው ምርጫ አለሽ። ማንም እንዲያምንብሽ ዝቅ ብሎ የመለመን ግዴታ የለብሽም፡፡ አንደኛው ውበትሽ ክብርሽ እንደሆነ አስታውሺ፡፡ ለእራስሽ ብርታትና ሃይል መሆን ትችያለሽ፤ ለእራስሽ የሰጠሽውን ቦታ በመቀየር ብቻ አካባቢሽንና የተሰጠሽን ቦታ መቀየር ትችያለሽ። .......የእናቴ ልጅ-(Tame).......... ...       .......        ........... @Meklite21 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Show all...
7👍 3
📓ርዕስ :- ትዝታሽን ለእኔ ትዝታዬን ለአንቺ 📝ደራሲ :- እሱባለው አበራ 📅ዓ.ም :- 2012 📖የገፅ ብዛት :- 180 💚 https://t.me/Asresee 💛 https://t.me/Asreseehttps://t.me/Asresee
Show all...
❤️እናቴ❤️… ➡እናቱን በሞት የተነጠቀው ህፃን መንደር ዳር ቆሞ ጭቃ እያቦካ ነው። አባቱ ከስራ ሲመለስ አፈርን ከውሀ እየለወሰ ሲያሽ ይመለከተዋል። #ልጄ ሆይ በጭቃ አትጫወት ልብስህ ይቆሽሻል ሰውነትም ይቦካል በል ና አሁን ተነስ ወደ ቤት ግባና ታጠብ #ልጅ አባቴ ሆይ እኛ ከጭቃ እንደተፈጠርን አልነገርከኝም ነበር ? #አባት አዎ ልጄ በሚገባ ከጭቃ ነው የተፈጠርነው #ልጅ እባክህ አባቴ እርዳኝ እና እናቴን እንደገና ልስራ ብሎ ያለቅሳል😭😭       ሁሌም ቢሆን የእናትን ዋጋ የሚያውቁ የሚያስቡት ልክ እንደ ህፃኑ ነው🙏🙏🙏 💚 https://t.me/Asresee 💛 https://t.me/Asreseehttps://t.me/Asresee
Show all...
👍 5 2🥰 2
የሆነ መንደር ውስጥ አንድ ጅል ይኖራል። የመጨረሻ ጅል ከመሆኑ የተነሳ አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም መለየት አይችልም። እና የመንደሩ ነዋሪዎች ይመጡና "አንተ ጅል ና እስቲ ከዚህ ምረጥና ውስድ" ብለው አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም ሲያስቀምጡለት አስሯን ያነሳል። "ይሄ (አምሳውን) ይሻልሃል" ሲሉት "እምቢ ብሎ ያለቅሳል። "አይ ይሄ ጅል … ኑ ጉድ እዩ፤ ኑ ጉድ እዩ" ይሉና አስር ሳንቲም እና አምሳ ሳንቲም ድጋሚ ያስቀምጡለታል። አሁንም አስሯን ያነሳል። ኧረ ይሄ ይሻልሃል ሲሉት "እምቢ፣ እምቢ" ብሎ ያለቅሳል። በኋላ በዚህ ጅል ዘመዶቹ እያፈሩ ሄዱ። አንዱ ዘመዱ መጣና "አንተ ጅል … ሁሌ ባንተ እንዳፈርን እንቅር? ኧረ ተው ግድ የለህም፣ ተው ግድ የለህም። አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም መለየት አቅቶህ አምሳ ሳንቲም ሲሰጡህ በአስር ሳንቲም ታለቅሳለህ? ኧንደው ምናለ አምሳውን ብታነሳ?" ብሎ ሲመክረው። "ጅልስ አንተ ነህ! አምሳውን ያነሳው ቀን እኮ አያስመርጡኝም። ፧ ማነው ጅል? እነሱ ወይስ ጅል ብለው የሚያስቡት? አያችሁ እሱ ብልጥ ጅል ነው፤ እስከ ኖረ ድረስ አስር፣ አስር ሳንቲሟን እየመረጠ የተጃጃለ መስሎ ያጃጅላቸዋል፤ ምክንያቱም አምሳዋ አንዴ ነች፤ አስሯ እስካለ ትቀጥላለች። እንደነሱ ከሆነ አምሳ ሳንቲሟን የብልጠቱ፣ አስር ሳንቲሟን ደግሞ የጅልነቱ መገለጫ አድርገዋታል። ለሱ ግን አስር ሳንቲሟ የብልጠቱ መሰወሪያ፣ መደበቂያ ነች። አምሳዋን የመረጠ ቀን ጅልነቱ ያበቃል፤ ማንም አያስመርጠውማ። ምክንያቱም አውቋል፤ ነቅቷል ይሉታላ። © ዓለማየሁ ገላጋይ ........የእናቴ ልጅ-(Tame).......... ...       .......        ........... @Meklite21 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Show all...
👍 4 4😁 2
....... ...... ጭቃ ውስጥ ሆነህ ጭቃው አበላሸኝ አይይይይ ብትል ፤ ጭቃው አይለቅህም ወጥተህ ካላታጠብክ፤ በጣም ብዙ ሰው ከጭቃው ለመውጣት ከመታገል እዛው ቆሞ ማለቃቀስ ይቀለዋል። ለተበላሹ ነገሮች አብዝቶ መጨነቅና ማሰብ ለቀጣይ እርምጃ እግራችን እንዳይነሳ አጣብቆ ይይዛል እንጂ ማስተካከያ አይሆንም፡፡ ያለፉትን እርግፍ አድርገህ ተዋቸው ለቀጣይ ህይወትህ ራስህን አዘጋጅ በፀፀት ራስህን አትቅጣ። ..........የእናቴ ልጅ(Tame) ...       .......        ........... @Meklite21 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Show all...
10👍 3