cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

✞✟ ኦርቶዶክሳዉያን ✞✟

እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጣቹ ይህ ቻናል የተከፈተው ለኦርቶዶክሳውያን እና ማወቅ ለሚፈልግ ለማንኛውም ሰው ነው ✞መዝሙር ✟ግጥም ✞ኦርቶዶክሳዊ ፎቶ ያገኙበታል

Show more
Advertising posts
522
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-1530 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
Media files
40Loading...
02
Media files
40Loading...
03
አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይሠውርልን:: [  †  ግንቦት ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ] ፩. አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ [ ኢትዮዽያዊ ] ፪. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም [ የ፲፪ [ 12 ]ቱ ሐዋርያት መቃብር ከጌታ የተገለጠላቸው ኢትዮዽያዊ ] ፫. አቡነ ብስጣውሮስ ዘሐይቅ እስጢፋኖስ [ ኢትዮዽያዊ ] ፬. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ታላቁ [ ፯ [7 ] ጊዜ ሙቶ የተነሳ ] ፭. "805,007" ሰማዕታት [ በአንድ ቀን ብቻ የተገደሉ ] ፮. አባ ይስሐቅ ገዳማዊ [   †  ወርኃዊ በዓላት    ] ፩ ፡ ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት ፪ ፡ ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ፫ ፡ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ፬ ፡ አባ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ " በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ:: አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ:: በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ:: ስሜንም አውቁዋልና እጋርደዋለሁ:: ይጠራኛል እመልስለትማለሁ:: በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ:: አድነዋለሁ: አከብረውማለሁ:: ረጅም እድሜን አጠግበዋለሁ:: ማዳኔንም አሳየዋለሁ:: " [መዝ.፺፥፲፫] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
40Loading...
04
🕊 ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞ †  እንኳን አደረሳችሁ  † [ †  ግንቦት ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] †  🕊  አባ ዓቢየ እግዚእ  🕊  † ጐንደር ከተማ ነዋሪ ከሆኑ: ወይም ከተማዋን የሚያውቁዋት ከሆነ አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎ::[እንደ ወትሮው ሁሉ] ከተማዋ ውስጥ ጅብና እባብን የመሠሉ አራዊት ነዋሪውን ሲገድሉ: ወይም ሲያቆስሉ ተመልክተው: ካልሆነም በታሪክ ሰምተው ያውቃሉ? መልስዎ "በጭራሽ አላውቅም" እንደሚሆን እገምታለሁ:: [ምክንያቱም ሆኖ አያውቅማ!] ነገሬን እንዲረዱኝ ሌሎች የሃገራችን ዋና ዋና ከተሞችን ልብ ይበሉልኝ:: እንኳን በሌሊት በቀንም አራዊቱ አይጠፉባቸውም:: "ታዲያ ጐንደር ከተማ ውስጥ ጅብ የማይገባው: እባብና ጊንጥ ሰው የማይገድለው ግን ለምን?" ካሉ በጻድቁ በአባ ዓቢየ እግዚእ ቃል ኪዳን ምክንያት ነው:: [ሁሉም የሃገራችን ከተሞች የተባረኩ መሆናቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው] ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ፲፬ [14]ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን [መረታ] ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ:: አጥምቀው 'ዓቢየ እግዚእ' ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጉመ መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው" ማለት ነው:: ዓቢየ እግዚእ በሕጻንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ:: ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኩሰዋል:: በገዳሙ በጾም: በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን አግኝተዋል:: በጊዜው በ፵ [40] ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር:: ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል:: ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ አባትም ነበሩ:: ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ ስብከታቸው ነው:: አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ:: ቀኑ ነሐሴ ፲ [10] ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ፫ [3] ቀናት ባለመጉደሉ ከ፩ ሺህ [1,000] በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ:: ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ- አማንያን [አሕዛብ] ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ:: ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ:: ይሕን ድንቅ ያዩ ከ፩ ሺህ [1,000] በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል:: ይሕም ዘወትር ነሐሴ ፲ [10] ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው [ጐንደር] ይከበራል:: ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ:: ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች:: ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር:: በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሠል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት:: ይሕንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ:: በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ:: የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም:: በሰማይም እሳትን አያዩም:: ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም::" ብሏቸው አርጓል:: ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል:: ይሔው እኛ ምን ብንከፋ: ጻድቁንም ብንረሳቸው እግዚአብሔር ግን ዛሬም በጻድቁ ምልጃ ከተማዋን ጠብቆ ይኖራል:: ነገን ደግሞ እርሱ ያውቃል:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ [ጎንደር ቀበሌ 09 ኪዳነ ምሕረት] ጻድቁ የጸለዩበት ቦታ ነው:: እንኳን በወርሃዊ በዓላቸው በ፲፱ [19] ይቅርና በዓመታዊ በዓላቸው [ግንቦት ፲፱ [19] ለንግስ የሚመጣው ሰው ቁጥር ያስተዛዝባል:: አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው: ፫ [3] ሙታንን አስነስተው: ብዙ ድውያንን ፈውሰው: ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው: የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው: በ፻፵ [140] ዓመታቸው ግንቦት ፲፱ [19] ቀን አርፈዋል:: የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው:: "ተአምሪሁ ለጻድቅ አቡነ ዓቢየ እግዚእ - - - ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን::" " ከበዙ ተአምራቱ አንዱን " ጻድቁ አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን [መረታ] ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ "አባቴ! የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?" አለቻቸው:: ጻድቁም በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው : በመስቀላቸው ባርከው ሰጧት:: ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና "ልጠጣው" ብላ የተቀበለችውን ማይ [ጸበል] ልትጠመቅበት [ልትጸበልበት] ወሰነች:: ባልንጀራዋንም "በላዬ ላይ አፍሺልኝ" ስትል አዘዘቻት:: ባልንጀራዋም "እሺ" ብላ ልታፈስላት [ልትጸብላት] በፋጋ [ግማሽ ቅል] ያለውን ጸበል አነሳች:: ልታፈሰው ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ ፪ [2] ቱም ደነገጡ:: ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና:: ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ:: ከውጭ ሆነውም "አባ! አባ! የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነ" አሏቸው:: ጻድቁም እንዳላዋቂ "ምን አጠፋችሁ?" ሲሉ ጠየቁ:: "አባታችን! ምንም አላጠፋንም:: ብቻ አፍሺልኝ ብየ ስሰጣት እንዲህ ሆነ" ስትል አንዷ መለሰች:: ጻድቁ ግን በየውሃት "ልጆቼ! ሁሌም : 'ምንም አላጠፋንም' አይባልም:: ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና:: + . . . አንቺም ልጄ ! እኔን ያልሺኝ 'የምጠጣው ጸበል ስጠኝ' ነበር:: ግን ልትጸበይበት ወደድሽ:: ስሕተትሽ ከዚህ ይጀምራል:: [የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና] ¤በዚያ ላይ "አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . . ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም::" [ዮሐ.፰፥፵፬] + . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን 'አጥምቂኝ' አልሻት:: ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ ተለውጦባቹሃል" ብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ:: "እፍ" ሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ ተመለሰ:: ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው ለጻድቁ ሰገዱ:: ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን::
30Loading...
05
Media files
110Loading...
06
Media files
110Loading...
07
                       †                          [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]   🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒                [  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ] [   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ] 🕊                            ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ፤ ነፍስን ይመልሳል ፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፥ ልብንም ደስ ያሰኛል ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ፥ ዓይንንም ያበራል። ❞ [ መዝ . ፲፱ ፥ ፯  ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [ ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞  ] [ ክፍል - ፪ - ]           💖   ድንቅ ትምህርት  💖 [ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] ❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]          †              †               † ▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬                        👇
120Loading...
08
                        †                         🕊  💖     ይ ከ ታ ተ ሉ !     💖  🕊 ከነገ ምሽት ጀምሮ በፍኖተ ሕይወት መርሐግብር [ ያ ለ እ ም ነ ት ! ]      💖    ድንቅ ትምህርት   💖 🕊 በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ  🕊 ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ሊሰማው የሚገባው እጅግ ድንቅ ትምህርት በአነስተኛ Mb መቅረብ ስለሚጀምር ሌሎች ኦርቶዶክሳውያንን Add በማድረግ ትከታተሉ ዘንድ እንጋብዛለን !  💞 †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
120Loading...
09
Media files
130Loading...
10
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [ ከመንፈሳዊ መጻሕፍት ቅኝት ] 🔔 [ የተሀድሶ እንቁራሪት ! ] ሰውየው አንድ ትልቅና ጎድጓዳ ዕቃ አምጥቶ በውኃ ከሞላው በኋላ ያን ውሃ ከእሳት ማንደጃ ላይ ጥዶ እሳቱ በኃይል ለቀቀውና ውኃውም በፍጥነት ፈላ። ትንሽ ቆይቶም አንዲት እንቁራሪት አመጣ እዚያ የፈላ ውኃ ውስጥ ከተታት እንቁራሪቷ ግን ተስፈጥራ ወጣችና ነፍሷን አተረፈች ። በእንቁራሪቷ መትረፍ የተበሳጨው ሰውየው በሌላ ጊዜ በእዚያው ዕቃ ውኃ ሞላና ከማንደጃው ላይ ጥዶ ሲያበቃ እሳቱ ከማቀጣጠሉ በፊት ያችኑ እንቁራሪት ይዞ በቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ጨመራት እንቁራሪቷ እንደ በፊቱ ተስፈንጥራ አልወጣችም ይልቁንም ውኃው ቀዝቃዛ በመሆኑ ተዝናንታ ትዋኝ ጀመረ። ሰውየው እንቁራሪቷን ሳይረብሽ በጥንቃቄ እሳቱ ለኮሰና ቀስ በቀስ መጠኑን እየጨመረ ውሃውን ያፈላው ጀመረ ። ከምድጃው ስር እሳት እየነደደ መሆኑን ያልተረዳችው እንቁራሪት ውኃው ለብ ባለ ቁጥር ደስታዋ እየጨመረ ሄደ ። ሰውየው የእሳቱን ኃይል ቀስ በቀስ እየጨመረ ሲመጣ ውሃው ተፍለቀለቀ የውኃውን ለብታ እና ሞቅ ማለት ያላነቃት ይልቁንም ያስፈነደቃት እንቁራሪት ሳታውቀው ፍልቅልቁ ውሃ አንፍሮ ጣላት። 🔴 በዚህ ዘመን ከቅርብ አመታት ወዲህ በቤተ-ክርስቲያናችን አውደ ምህረቶች በተለይም በጣት የሚቆጠሩትና ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ስርአት ይልቅ በሕገ ወጥ መንገድ ለሚሰበሰበው ገንዘብ ልባቸውን በሰጡ ኃላፊዎች ምክንያት በሚዘጋጁ ጉባዔያት የሚታየው ሁኔታ ለእኛ ለቤተ-ክርስቲያን ልጆች እንቁራሪቷ ሳታውቀው የነፈረችበትን የተፍለቀለቀ ውሃ ይመስላል። ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሾልከው በገቡ የተሃድሶ መናፍቃን የማዘናጊያ ስብከት በዝንጋዔ ምድጃ ተጥለን በኑፋቄ ነፍረን እንዳንገኝ ልንባንንና ልንጠነቀቅ ይገባናል ። ሁሉ ነገር እንቁራሪቷን በመጀመሪያ እንዳጋጠማት አፍጦ ሳይሆን እንደ ሁለተኛው ጊዜ በማዘናጋት ነው እየሆነ ያለው። እናም የተዋሕዶ ልጆች እንንቃ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ምዕመናን በላከው መልዕክቱ እንዲህ ይላል ፦ "ንቁ በሀይማኖት ቁሙ ጎልምሱ ጠንክሩ።" [፩ኛ ቆር.፲፮፥፲፫] ይላልና እንጠንቀቅ ሁላችን። [ ምጥን ቅመም ከተሰኘችው የዲ/ን ምትኩ አበራ መጽሐፍ የተወሰደ ] ይቆየን ! †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
130Loading...
11
                        †                         🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊 ❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም ❞ 🕊 ❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ❞ ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ❝  አመ ይመጽእ ንጉሥ በንጥረ መባርቅት ትሰፍን ሰንበት ርእሰ ኵሎን ዕለታት አሜሃ አልቦ ወርኅ ኢፀሐይ ኢክረምት ወኢሐጋይ ፤ ❞ ትርጉም ፦ [  በመብረቆች ብልጭታ [ ታጅቦ ] ንጉሥ በሚመጣበት ጊዜ ፣ የዕለታት ሁሉ አውራ [ አለቃ ] የሆነችው ሰንበት ለዘለዓለም ትሰጠናለች ፤ ያኔ ጨረቃ የለም ፣ ፀሐይም ቢሆን ክረምትና በጋም ቢሆን አይኖርም።  ] [ ቅዱስ ያሬድ ] 🕊 †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
100Loading...
12
Media files
90Loading...
13
Media files
90Loading...
14
Media files
110Loading...
15
Media files
120Loading...
16
🕊 [ † እንኩዋን ለጥንተ በዓለ ዸራቅሊጦስ [ መንፈስ ቅዱስ ] እና ለጻድቁ አባ ገዐርጊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ] †  🕊  በዓለ ዸራቅሊጦስ  🕊  † ✞ ከዚሕ በፊት እንደተመለከትነው የጌታችን ዓበይት በዓላቱ ፪ [2] ጊዜ [ማለትም ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው] ይከበራሉ:: ዛሬም ከ፩ ሺህ ፱ መቶ ፸፰ [1,978] ዓመታት በፊት አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን እናስባለን:: † ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል - ከልዑል ማዕርጉ ወርዶ: - በማሕጸነ ድንግል ተጸንሶ: - በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: - ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕጻናት አድጐ: - በ30 ዘመኑ ተጠምቆ: - ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ: - በፈቃዱ ሙቶ: - በባሕርይ ስልጣኑ ተነስቶ: - በአርባኛው ቀን ያርጋል:: ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው ነበርና በተነሳ በ፶ [50] ኛው ቀን: በዐረገ በ፲ [10] ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው:: - እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች:: ፻፳ [120] ው ቤተሰብ ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ በአምሳለ እሳት አደረባቸው:: - ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች: አሮጌ ሕሊና የነበራቸው ሐዲሶች ሆኑ:: በአዕምሮ ጐለመሱ: ቁዋንቁዋ ተናገሩ: ምሥጢርም ተረጐሙ:: በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ:: - ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል አርሰዋል:: አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል:: ሳይሳሱም አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል:: "ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ: ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ: ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ::" እንዳለ ደራሲ:: - በዚህ ቀን ፪ [ 2 ] ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ :- ፩. የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት :- - እርሱ ከአብ የሠረጸ: ቅድመ ዓለም የነበረ: በባሕርይ ስልጣኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል የሆነ: የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም አምላካችን ነውና:: ፪. 🕊 ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 🕊 :- - አብ ያሰባት: ወልድ በደሙ የቀደሳት: መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት: አንድም ቤት ናትና:: ዛሬ በጉባዔ ተመስርታለች:: † 🕊 አባ ገዐርጊ 🕊 † በዚችም ዕለት የአባ አብርሃም ጓደኛ የከበረ አባ ገዐርጊ አረፈ።ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገን ነው ወላጆቹ ደጎች ጻድቃን ናቸው።በአደገም ጊዜ የወላጆቹን ከብቶች የሚጠብቅ እረኛ ሆነ።ሁል ጊዜም የምንኵስና ልብስ ይለብስ ዘንድ በልቡ ይመኝ ነበር። ዐሥራ አራት ዓመትም በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ አነሣሳችው በጎቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ። እየተጓዘም ሳለ ከሩቅ የብርሃን ምሰሶ አየ ወደ ወንዝ እስከ ደረሰ ድረስ ወደ ርሱ ሔደ ከዚህም በኃላ ያ የብርሃን ምሰሶ ከእርሱ ተሰወረ። ያንንም ወንዝ በተሻገረ ጊዜ በሽማግሌ አምሳል ሰይጣን ተገለጠለትና ልጄ ሆይ ዕወቅ ስለ አንተ ልብሱን ቀዶ አባትህን አየሁት እርሱም ያዝናል ያለቅሳል ተመልሰህ የአባትህን ልብ ልትአጽናና ይገባሃል።የዱር አውሬ ነጥቆ የበላህ መስሎታልና አለው። አባ ገዐርጊም ደንግጦ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ከዚህም በኃላ የከበረ ወንጌል ከእኔ ሊሆን አይገባውም ደቀ መዝሙሬም ሊሆን አይችልም ብሏል ብሎ አሰበ።ይህንንም በአለ ጊዜ ሰይጣን እንደ ጢስ ሆኖ ተበተነ።አባ ገዐርጊም ሰይጣን እንደ ሆነ አወቀ በዚያን ጊዜም ያ የብርሃን ምሰሶ ደግሞ ተገለጠለት የእግዚአብሔርም መልአክ በመነኵሴ አምሳል አብሮት ተጓዘ ቅዱሱም መልአኩን ተከተለው እርሱም ከአባ አርዮን ገዳም አደረሰው።አባ ገዐርጊም ከአንድ ጻድቅ ሰው መነኵሴ ጋራ በዚያ ዐሥራ አራት ዓመት ወጥሳይቀምስ ወይን ሳይጠጣ የአትክልት ፍሬም ቢሆን በዚህ በዐሥራ አራት ዓመት ያህል ከሚቀመጥ በቀር አልተኛም። ተጋድሎውንም በጨመረ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ሥጋህ እንዳይደክም በመካከለኛ ገድል ተጋደል ብሎሃል ጌታ።ከዚህም በኃላ ሊሠራው የሚገባውን ሥርዓት ሠራለት ።ሁል ጊዜም እስከሚመሽ እንዲጾም ትንሽም እንጀራን እንዲበላ ከአራት ሰዓት እስከ መንፈቀ ሌሊት ስለ ሥጋው ዕረፍት እንዲተኛ በቀረው ሌሊት እስቲነጋ ተግቶ እንዲጸልይ። በዚህም ተጋድሎ ብዙ ዘመናት እየተጋደለ በኖረ ጊዜ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ሊኖር ወዶ በጫካ ውስጥ እየተመላለሰ ሁለት ዓመት ኖረ።ከዚህም በኃላ ጌታ ተገለጾለት ወደ ቦታው እንዲመለስ አዘዘው።ያን ጊዜም አምላካዊት ኃይል ከከበሩ መክሲሞስና ደማቴዎስ ገዳም አደረሰችው እርሷም ለደብሩ አቅራቢያ ናት። ወደ ደብሩም በተመለሰ ጊዜ በዚያን ወቅት አብርሃም ከዓለም ወደዚያ ገዳም መጥቶ ሁለቱም ተገናኙና በአንድነት ተስማምተው የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ወደ ሆነ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሱ።እርሱም ቦታ ሰጥቷቸው በውስጡ ኖሩ ያ ቦታም እስከ ዛሬ ታውቆ ይኖራል ። ያቺም ዋሻ በግቢግ ትባላለች የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐለት የሆነ ጣሪያዋን ሠንጥቆ ወደ እነርሱ የወረዳበት ናት ።እነርሱም ሰገዱለት ሰላምታም ሰጥቷቸው አጽናንቷቸው ከእርሳቸው ዘንድ ዐረገ።በዚያችም ጌታችን በወረደበት መስኮት ብርሃንን አዩ እስከ ዛሬም የተከፈተች ሁና ትኖራለች። እሊህ ቅድሳንም ለመነኰሰኘሳት የሚሆን ብዙ ድርሳናትንና ብዙ ተግሣጻትን ደረሱ።ለአባቶቹ የሚታዘዘውንና የሚገዛውን አመሰገኑት።ከዚህም በኋላ አባ አብርሃም ጥር ሁለት ቀን አረፈ። ከእርሱ በኋላም የከበረ አባ ገዐርጊ በዚች በግንቦት ወር በዐሥራ ስምንት ቀን አረፈ።መላ ዕድሜውም ሰባ ሁለት ዓመት ሆነ።በዓለም ዐሥራ አራት ዓመት በምንኩስና ኃምሳ ስምንት ዓመት ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትሁን አሜን። በዚችም ዕለት የሰማዕት ሲኖዳ መታሰቢያው ነው በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። አምላከ ገዐርጊ ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ለኃጥአን ባሮቹ ያድለን:: [ † ግንቦት ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱሳን ሐዋርያት ወአርድእት ፪. አባ ገዐርጊ ገዳማዊ ፫. ቅዱስ ሲኖዳ ሰማዕት [ †  ወርሐዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ ፪. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት [ረባን] ፫. አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ ፬. ማር ያዕቆብ ግብፃዊ " በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ:: ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው:: እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው:: በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው:: በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው:: መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር :: " [ሐዋ.፪፥፩] (2:1-4) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
110Loading...
17
                       †                          [   "  ሃይማኖቴን አልካድህም ! "    ] ❝ እኛ ክርስቲያኖች የሚደርሱብን መከራዎች እንደወርቅ የምንጠራባቸው እቶኖች ናቸው። ❞             [  ቅዱስ  ዮሐንስ አፈወርቅ ] † አንዲት ቤተ ክርስቲያን !                  አንድ ሲኖዶስ !                  አንድ ፓትርያርክ !                  አንድ የሹመት ሥርዐት ! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖናዊት ናት ! †                      †                      † " የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ ፥ ሰይጣንም በሚኖርበት ፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።" [ ራእ.፪፥፲፫ ]           †             †             † ▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
130Loading...
18
                       †                          [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]   🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒                [  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ] [   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ] 🕊                            ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ፤ ነፍስን ይመልሳል ፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፥ ልብንም ደስ ያሰኛል ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ፥ ዓይንንም ያበራል። የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው ፤ ለዘላለም ይኖራል ፤ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው። ❞ [ መዝ . ፲፱ ፥ ፯  ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [ ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞ ]           💖   ድንቅ ትምህርት  💖 [ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] ❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]          †              †               † ▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬                        👇
130Loading...
19
Media files
110Loading...
20
Media files
110Loading...
21
                        †                         🕊  💖     ይ ከ ታ ተ ሉ !     💖  🕊 ከዛሬ ምሽት ጀምሮ በቅዳሜና እሁድ የድምፀ ተዋሕዶ መርሐግብር [ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ]      💖    ድንቅ ትምህርት   💖 🕊 በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ  🕊 ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ከዚህ ቀደም ትምህርቱ ያመለጣችሁ የተዋሕዶ ልጆች ሕይወት የሚገኝበትን ይህንን ድንቅ መርሐ ግብር በጣም በአነስተኛ Mb ከዛሬ ምሽት ጀምሮ መቅረብ ስለሚጀምር ሌሎች ኦርቶዶክሳውያንን Add በማድረግ ትከታተሉ ዘንድ እንጋብዛለን ! 💞 †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
110Loading...
22
Media files
120Loading...
23
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ እናንት የቤተክርስቲያን ዕንቁዎች የቤተክርስቲያን አምላክ ክብርን ፣ ጸጋንና ረጅም ዕድሜን ያድልልን። እናንተን ለሚመስሉ ሁሉ እንጂ ! ለንጽሕይትና ቅድስት ቤተክርስቲያን በፍጹም ነፍሳችሁ የታመናችሁ እውነተኛ ልጆቿ ሆናችኋልና ! የእኛ ዘመን ግን የከፋ ሆኗል። ዘይቱ ከማድጋው ተሟጦ ያለቀ ይመስላል። ምድሪቱ በመዝሙር ስም በሚዘፍኑ ዕልፎች ተሞልታለች። ባዶ ጩኸት ምድሪቱን ያውካል። ዝላዩና ጭፈራው ወሰኑን አጥቷል። ገንዘብንና ዝናን ሽመታው ከዓለሙ ይልቅ ከፍቷል። ኑፋቄው በአደባባይ በነጻነት ተገልጧል። ወይን ጠጁን ከነ አተላው የምንጠጣ ጎስቋሎች ሆነናል ! "እስከ መጨረሻው የሚጸና እርሱ ይድናል" [ ማቴ.፳፬፥፲፫ ] እግዚአብሔር በምሕረቱ ያስበን ! ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬
150Loading...
24
Media files
130Loading...
25
Media files
90Loading...
26
Media files
80Loading...
27
                        †                         🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊 ❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም ❞ 🕊 ❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ❞ ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ❝ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን ከይዶ መቃብሪሁ ለአዳም ወበትንሣኤሁ ገብረ ለነ ሰላመ ለጻድቃን አብርሃ ፤ ❞ [ የአዳምን መቃብር ረጋግጦ ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ ፣ በትንሣኤውም ለጻድቃን ብርሃን የሚሆን ሰላምን ለእኛ አደረገልን ] 🕊 [    ድጓ ዘፋሲካ     ] †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
150Loading...
28
🕊 [ † እንኳን ለታላቁ የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊  †  ቅዱስ ኤዺፋንዮስ  †   🕊 † ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ጽድቅ ከቅድስና : ድርሰት ከጥብቅና የተሳካለት አባት ነው:: "ኤዺፋንያ" ማለት የመለኮት መገለጥ ሲሆን "ኤዺፋንዮስ" ማለት ደግሞ ምሥጢረ መለኮት የተገለጠለት ማለት ነው:: ቅዱስ ኤዺፋንዮስ የተወለደው ክርስቶስን ከሚጠሉ አይሁዳውያን ቤተሰቦች ቤተ ገብርኤል ውስጥ ነው:: ቤተሰቦቹ ከአንድ አህያ በቀር ምንም የሌላቸው ድሆች ነበሩ:: በዚያ ላይ በልጅነቱ አባቱ በመሞቱ ከእናቱና ከአንዲት እህቱ ጋር በረሃብ ሊያልቁ ሆነ:: ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ በአህያው እንዳይሠራ አህያው ክፉ ነበርና ሊሸጠው ገበያ አወጣው:: ፊላታዎስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ለግዢ ሲደራደሩ አህያው የኤዺፋንዮስን ኩላሊቱን ረግጦት ለሞት አደረሰው:: በዚህ ጊዜ አብሮት ያለው ክርስቲያኑ በትእምርተ መስቀል አማትቦ አዳነው:: በፈንታው ግን አህያው ሞተ:: ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ እያደነቀ ሔደ:: ከቆይታ በኋላ ሀብታም አጎቱ ገንዘቡን አውርሶት በመሞቱ ገና በ፲፮ [ 16 ] ዓመቱ ባለጠጋ ሆነ:: ያቺ ገበያ ላይ ያያት ተአምር ግን በልቡ ውስጥ ትመላለስ ነበር:: አንድ ቀን ደግሞ ሉክያኖስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ሲሔዱ ነዳይ አገኙ:: ባለጠጋው ኤዺፋንዮስ አለፈው:: ያ ድሃ ክርስቲያን ግን የለበሳትን አውልቆ መጸወተው:: በዚሕ ጊዜ መልዐኩ መጥቶ የብርሃን ልብስ ሲያለብሰው ኤዺፋንዮስ ተመለከተ:: ኤዺፋንዮስ ጊዜ አላጠፋም:: ከእህቱ ጋር በክርስቶስ አምኖ ተጠመቀ:: ሃብት ንበረቱን ግማሹን መጸወተ:: በተረፈው ደግሞ መጻሕፍትን ገዝቶ ወደ አባ ኢላርዮን ገዳም ገባ:: በዚያም መናንያኑ እስኪያደንቁት ድረስ በፍጹም ትጋትና ቅድስና ተጋደለ:: በጸሎቱ ዝናም አዘነመ : ድውያንን ፈወሰ : ብዙ ተአምራትንም አደረገ:: እግዚአብሔር ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ሽቶታልና በቆዽሮስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኖ ተሾመ:: ብሉይ ከሐዲስ የወሰነ ሊቅ ነውና ብዙ መጻሕፍትን ተረጎመ:: በሺሕ የሚቆጠሩ ድርሳናትን ደረሰ:: በአፍም በመጽሐፍም ብሎ መናፍቃንንና አይሁድን ምላሽ በማሳጣቱ ቤተ ክርስቲያን "ጠበቃየ" ትለዋለች:: ከደረሳቸው መጻሕፍት መካከል "ሃይማኖተ አበው ዘኤዺፋንዮስ : መጽሐፈ ቅዳሴውና አክሲማሮስ [ስነ ፍጥረት]" ዛሬም በቅርብ ይገኛሉ:: ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ በመልካም እረኝነትና በሚደነቅ ቅድስና ተመላልሶ በ ፬፻፮ [406] ዓ/ም ዐርፏል:: እድሜውም ፺፮ [96] ዓመት ያህል ነበር:: † አምላካችን ከቅዱሱ ሊቅ በረከት ያድለን:: 🕊 [ † ግንቦት ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ [ ዘደሴተ ቆዽሮስ ] ፪. ቅዱስ ኢላርዮን ገዳማዊ ፫. አባ ሉክያኖስ ጻድቅ ፬. ቅዱስ ፊላታዎስ ክርስቲያናዊ [ †  ወርኀዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት [ ቀዳሜ ሰማዕት ] ፪. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ ወልደ ዘብዴዎስ ] ፫. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ ፬. አባ ገሪማ ዘመደራ ፭. አባ ዸላሞን ፈላሢ ፮. አባ ለትጹን የዋህ † " የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል:: እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው:: እኛ ግን የማይጠፋውን:: ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም:: ነፋስን እንደሚጐስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም:: ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጐሰምሁ አስገዛዋለሁ:: " † [፩ቆሮ.፱፥፳፭] (9:25) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
110Loading...
29
Media files
130Loading...
30
Media files
130Loading...
31
        †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ [ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል ! ] " አስማተኛም ፥ መተተኛም ፥ በድግምት የሚጠነቍልም ፥ መናፍስትንም የሚጠራ ፥ ጠንቋይም ፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው ፤ ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል። አንተ ግን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ሁን።" [ ዘዳ.፲፰፥፲፩ ] 🔔 በቤተክርስቲያን ማዕረግ ስም እንደ እንጉዳይ የፈሉ ጠንቋዮች ፣ መተተኞችና አስማተኞች የቤተክርስቲያን መከራዎች ናቸው። እነዚህ የእግዚአብሔር ጠላቶችና የዲያብሎስ አገልጋዮች በእጃቸው ብዙ ደም አለ። በነዚህ የተነሳ ብዙ ምስኪኖች በየጸበሉና በየሆስፒታሉ ይሰቃያሉ። ብዙዎች ሕይወታቸውን ፣ ጤናቸውንና ሰላማቸውን አጥተዋል። ብዙዎችም ሃይማኖታቸውን ክደው ጠፍተዋል። በነሱ ጠንቅ ቤተክርስቲያን ትሰደባለች። ክብረ ክህነት ይደፈራል። ምዕመናናን ንጹሕና እውነተኛ የነፍስ እረኞች ካህናትን እንዲጠሉና እንዲርቁ ይሆናሉ። በነዚህ ግለሰቦች የተነሳ ብዙ የዋሃን ገንዘባቸውን ይጭበረበራሉ። ይታለላሉ። ወደ ልዩ ልዩ አጋንንታዊ አሰራሮች ተስበው ይገባሉ። ስለዚህም በዘመናችን ቤተክርስቲያን በመናፍቃን እንድትሰደብ ፤ ክብረ ክህነትም እንዲደፈር በማድረግ አባቶቻችን ካህናትን ከምዕመናን ለመለየት ሰይጣን ያዘጋጃቸውን እንዲህ ያሉ የዲያብሎስ ሠራዊቶችን ከእኛ ዘንድ እናርቅ ! እንዲህ ያሉት የክፋት ሰራተኞች ለሐሰተኛ አጥማቂያን የገበያ ምንጭ በመሆን እየተመጋገቡ እንደሚሰሩም እናስተውል !          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
130Loading...
32
                        †                         🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊 ❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም ❞ 🕊 ❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ❞ ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ❝ ጻድቃን በእንቲአከ ሐሙ ፣ ሕማሞሙ ትፍሥሕተ ኮኖሙ ክብር ይደልዎሙ ፤ በገድሎሙ ሰማዕት ወበትዕግሥቶሙ ወረሱ መንግሥተ ሰማያት" ትርጉም ፦ ጻድቃን ስለአንተ ታመሙ [ መከራን ተቀበሉ ] መከራቸውም ደስታ ሆነላቸው ፣ ክብር ይገባቸዋል ፣ በተጋድሎአቸው ሰማዕታት ፣ በትዕግስታቸውም መንግሥተ ሰማያትን ወረሱ። ❞ 🕊 [    ድጓ ዘፋሲካ     ] †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
120Loading...
33
Media files
120Loading...
34
Media files
100Loading...
35
Media files
160Loading...
36
- ወንጌላዊ - ሐዋርያ - ሰማዕት ዘእንበለ ደም - አቡቀለምሲስ [ምሥጢራትን ያየ] - ታኦሎጐስ [ነባቤ መለኮት] - ወልደ ነጐድጉዋድ - ደቀ መለኮት ወምሥጢር - ፍቁረ እግዚእ - ርዕሰ ደናግል [የደናግል አለቃ] - ቁጹረ ገጽ - ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ [ከጌታ ጎን የሚቀመጥ] - ንስር ሠራሪ - ልዑለ ስብከት - ምድራዊው መልዐክ - ዓምደ ብርሐን - ሐዋርያ ትንቢት - ቀርነ ቤተ ክርስቲያን - ኮከበ ከዋክብት በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር:: ቅዱስ ዮሐንስን የወደደ ጌታ በፍቅሩ ይጠግነን:: ከእናቱ ፍቅር አድርሶ በሐዋርያው በረከት ያስጊጠን:: [ † ግንቦት ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ [ ስብከቱና ቅዳሴ ቤቱ ] ፪. ቅዱስ ኢያሱ ሲራክ ነቢይና ጠቢብ [ መጽሐፈ ሲራክን የጻፈ ] ፫. ቅድስት እናታችን ዐስበ ሚካኤል [ ኢትዮዽያዊት ] [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. ኪዳነ ምሕረት [የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም] ፪. ቅድስት ኤልሳቤጥ [የመጥምቁ ዮሐንስ እናት] ፫. ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ [የቅ/ላሊበላ ወንድም] ፬. ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ ፭. አባ አቡናፍር ገዳማዊ ፮. አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ ፯. አባ ዳንኤል ጻድቅ " በጌታ ኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ: የእናቱም እህት: የቀለዮዻም ሚስት ማርያም: መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር:: ጌታ ኢየሱስም እናቱን: ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን 'አንቺ ሆይ! እነሆ ልጅሽ' አላት:: ከዚህ በሁዋላ ደቀ መዝሙሩን 'እናትህ እነሁዋት' አለው:: ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት::" [ዮሐ.፲፱፥፳፭] (19:25) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
160Loading...
37
Media files
150Loading...
38
🕊 † በስመ አብ: ወወልድ: ወመንፈስ ቅዱስ: አሐዱ አምላክ † †  ግንቦት ፲፮ [ 16 ] † 🕊 † ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ † 🕊 አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው:: ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ: በገሊላ አካባቢ አድጐ: ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው:: ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል:: ከእርሷ ጋር ለ፲፭ [15] ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ:: ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ:: ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል:: ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ በታናሽ እስያ ለ፯ [7] ቱ አብያተ ክርስቲያናት መስበኩ ይታሰባል:: ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ፸ [70]  ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው:: ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል:: ፫ [3] መልዕክታት: ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል:: ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል:: ከእሳት እስከ ስለት: እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል:: ††† ቅዱሱ በኤፌሶን ††† ይህቺ ኤፌሶን የሚሏት ሃገር መገኛዋ በቀድሞው ታናሽ እስያ [አሁን ቱርክ አካባቢ] ሲሆን ብዙ ሐዋርያት አስተምረውባታል:: ያም ሆኖ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ያመጣች አልነበረችምና ቅዱስ ዮሐንስ ሊሔድ ተነሳ:: ከደቀ መዛሙርቱ መካከልም ቅዱስ አብሮኮሮስን [ከ፸፪] [72]ቱ አርድእት አንዱ ነው] አስከትሎ እየጸለዩ በመርከብ ላይ ተሳፈሩ:: ሐዋርያት አበው መከረኞች ናቸውና ማዕበል ተነሳባቸው:: በጥቂት አፍታም መርከባቸው በማዕበሉ ተበታተነች:: ቅዱስ አብሮኮሮስ በስባሪ ላይ ተሳፍሮ ወደ አንዲት ደሴት ደረሰ:: ከንጹሑ መምሕሩ ቅዱስ ዮሐንስ ተለይቷልና አለቀሰ:: ፍቁረ እግዚእ ግን ያለ ምግብና ውሃ ማዕበለ ባሕር እያማታው ለ፵ [40] ቀናት ቆየ:: እርሱ በፈጣሪው ፍቅር የተመሰጠ ነበርና አለመመገቡ አልጐዳውም:: በ፵ [40] ኛው ቀን ግን ደቀ መዝሙሩ ወዳለበት ደሴት ማዕበሉ አደረሰው:: ፪ [2] ቱ ቅዱሳን ተፈላልገው ተገናኙ:: እጅግም ደስ ብሏቸው ፈጣሪን አመሰገኑ:: አምላካቸው ወደዚህች ደሴት ያመጣቸው በጥበቡ ነውና ሲዘዋወሩ ፪ [2] ነገርን አስተዋሉ:: ፩ኛ የደሴቷ ሁሉም ነዋሪ የሚያመልኩት ጣዖትን ነው:: ፪ኛ አብዛኞቹ የቤተ መንግስት ውላጆች ናቸው:: ሮምና የሚሏት አንዲት ሴት ደግሞ እነዚህን ሁሉ እየመገበች ታስተዳድራለች:: ቅዱሳኑ በቦታው በቀጥታ ትምሕርተ ወንጌልን ቢናገሩ እንደ ማይቀበሏቸው ስለ ተረዱ ሌላ ፈሊጥን አሰቡ:: እንዳሰቡትም ወደ እመቤት ሮምና ቤት ሒደው በባርነት ተቀጠሩ:: ለእርሷም "ድሮ የአባትሽ ባሮች የነበርን ሰዎች ነን" ስላሏት ፪ [2]ቱን ቅዱሳን እሳት አንዳጅና ገንዳ አጣቢ አደረገቻቸው:: ለሰማይ ለምድሩ የከበዱ እነዚህ ቅዱሳን የካዱትን ይመልሱ ዘንድ በባርነት ግፍን ተቀበሉ:: የመከር [የማሳመኛ] ጊዜ ሲደርስም አንዳች አጋጣሚ ተፈጠረ:: ቅዱሳኑ ዮሐንስና አብሮኮሮስ ወደ መታጠቢያ ቤቱ ሲገቡ ሰይጣን በውስጥ ኖሮ ደንግጧልና እወጣለሁ ብሎ ሲሮጥ የንጉሡን ልጅ ረግጦ ገደለው:: ሮምናና የአካባቢው ሰዎች ከበው ሲላቀሱ ቅዱሳኑ ቀረቡ:: ሮምና ግን በቁጣ "ልትሣለቁ ነው የመጣችሁ?" በሚል ቅዱስ ዮሐንስን በጥፊ መታችው:: መላእክት እንኩዋ ቀና ብለው ሊያዩት የሚከብዳቸው ሐዋርያ ይህንን ታገሰ:: በጥፊ ወደ መታችው ሴት ቀረብ ብሎም "አትዘኚ! ልጁ ይነሳል" አላትና ጸለየ:: ወደ ሞተውም ቀረብ ብሎ በጌታችን ስም አስነሳው:: በዚህ ጊዜም ሮምናን ጨምሮ በሥፍራው የነበሩ ሰዎች ለቅዱስ ዮሐንስ ሰገዱ:: እርሱ ግን ሁሉንም አስነስቶ ትምሕርተ ሃይማኖትን: ፍቅረ ክርስቶስን ሰበከላቸው:: በስመ ሥላሴ አጥምቆ: ካህናትን ሹሞ: ቤተ ክርስቲያንም አንጾላቸው ወጥቷል:: በሁዋላም ለሮምናና ለደሴቷ ሰዎች ክታብ [መልዕክትን] ጽፎላቸዋል:: ይህች መልዕክት ዛሬ ፪ [2] ኛዋ የዮሐንስ መልዕክት ተብላ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትታወቃለች:: ቅዱስ ዮሐንስ ቀጥሎ የተጉዋዘው ወደ ኤፌሶን ነው:: በዚህች ከተማ የምትመለክ አርጤምስ [አርጢሞስ] የሚሏት ጣዖት ነበረች:: አርጤምስ ማለት መልክ የነበራት ትዕቢተኛ ሴት ስትሆን አስማተኛ ባሏ ነው እንድትመለክ ያደረጋት:: ቅዱስ ዻውሎስ ብዙ ምዕመናን ከእርሷ እንዲርቁ ማድረግ ችሏል:: ጨርሶ ያጠፋት ግን ቅዱስ ዮሐንስ ነው:: በቦታውም ብዙ ግፍ ደርሶበት: በርካታ ተአምራትን አድርጉዋል:: ቤተ ጣዖቱንም በተአምራት አፍርሶታል:: ††† የፍቅር ሐዋርያ ††† ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን 'የፍቅር ሐዋርያ' ትለዋለች:: ለ፸ [70] ዘመናት በቆየ ስብከቱ ስለ ፍቅር ብዙ አስተምሯል:: ፍቅርንም በተግባር አስተምሯል:: በየደቂቃውም "ደቂቅየ ተፋቀሩ በበይናቲክሙ - ልጆቼ ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" እያለ ይሰብክ ነበር:: በተለይ ደግሞ ከፈጣሪው ክርስቶስ ጋር የነበረው ፍቅር ፍጹም የተለየ ነበር:: በዚህ ምክንያትም ጌታ ባረገ ጊዜ እንዲህ ብሎታል:- "ለፍጡር ከሚገለጥ ምሥጢር ከአንተ የምሠውረው የለኝም" ብሎታል:: ቀጥሎም በንጹሕ አፉ ስሞታል:: ሊቁ :- "ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ: ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ" እንዳለው:: [መልክዐ ኢየሱስ] ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችንም ጋር ልዩ ፍቅር ነበረው:: እርሷ እንደ ልጇ ስትወደው: እርሱ ደግሞ እንደ እናቱ ልቡ እስኪነድ ድረስ ይወዳት ነበር:: እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ ተከትሎ ያገኛት እመቤቱ ናትና:: ከዚያ ሁሉ ጸጋና ማዕረግ የመድረሱ ምሥጢርም ድንግል ናት:: ለ፲፭ [15] ዓመታት በጽላሎተ ረድኤቷ [በረዳትነቷ ጥላ] ተደግፎ አብሯት ሲኖር ብዙ ተምሯል:: ከመላእክትም በላይ ከብሯል:: ከንጽሕናዋ በረከትም ተካፍሏል:: ስለ ድንግል ማርያምም "ነገረ ማርያም" የሚል ድርሰት ሲኖረው "የሰኔ ጐልጐታንም" የጻፈው እርሱ ነው:: ድንግል ባረፈችበት ቀንም ልክ እንደ ልጇ ክርስቶስ እርሷም ስማው: ታቅፋው ዐርፋለች:: ሊቃውንቱ ለዚህ አይደል በንጹሕ ከንፈሮቿ መሳምን [መባረክን] ሲሹ :- "በከመ ሰዓምኪ ርዕሰ ዮሐንስ ቀዳሚ: ስዒሞትየ ማርያም ድግሚ" ያሉት:: ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው ፺ [90] ዓመት በሆነው ጊዜ ተሰውሯል:: ከዚያ አስቀድሞም የዓለምን ፍጻሜ ተመልክቷል:: ዛሬ ያለበትን የየሚያውቅ ቸር ፈጣሪው ነው:: † ይሕች ዕለት ለሐዋርያው ቅዳሴ ቤቱ ናት:: † እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው:-
110Loading...
አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይሠውርልን:: [  †  ግንቦት ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ] ፩. አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ [ ኢትዮዽያዊ ] ፪. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም [ የ፲፪ [ 12 ]ቱ ሐዋርያት መቃብር ከጌታ የተገለጠላቸው ኢትዮዽያዊ ] ፫. አቡነ ብስጣውሮስ ዘሐይቅ እስጢፋኖስ [ ኢትዮዽያዊ ] ፬. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ታላቁ [ ፯ [7 ] ጊዜ ሙቶ የተነሳ ] ፭. "805,007" ሰማዕታት [ በአንድ ቀን ብቻ የተገደሉ ] ፮. አባ ይስሐቅ ገዳማዊ [   †  ወርኃዊ በዓላት    ] ፩ ፡ ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት ፪ ፡ ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ፫ ፡ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ፬ ፡ አባ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ " በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ:: አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ:: በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ:: ስሜንም አውቁዋልና እጋርደዋለሁ:: ይጠራኛል እመልስለትማለሁ:: በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ:: አድነዋለሁ: አከብረውማለሁ:: ረጅም እድሜን አጠግበዋለሁ:: ማዳኔንም አሳየዋለሁ:: " [መዝ.፺፥፲፫] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Show all...
🕊 ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞ †  እንኳን አደረሳችሁ  † [ †  ግንቦት ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] †  🕊  አባ ዓቢየ እግዚእ  🕊  † ጐንደር ከተማ ነዋሪ ከሆኑ: ወይም ከተማዋን የሚያውቁዋት ከሆነ አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎ::[እንደ ወትሮው ሁሉ] ከተማዋ ውስጥ ጅብና እባብን የመሠሉ አራዊት ነዋሪውን ሲገድሉ: ወይም ሲያቆስሉ ተመልክተው: ካልሆነም በታሪክ ሰምተው ያውቃሉ? መልስዎ "በጭራሽ አላውቅም" እንደሚሆን እገምታለሁ:: [ምክንያቱም ሆኖ አያውቅማ!] ነገሬን እንዲረዱኝ ሌሎች የሃገራችን ዋና ዋና ከተሞችን ልብ ይበሉልኝ:: እንኳን በሌሊት በቀንም አራዊቱ አይጠፉባቸውም:: "ታዲያ ጐንደር ከተማ ውስጥ ጅብ የማይገባው: እባብና ጊንጥ ሰው የማይገድለው ግን ለምን?" ካሉ በጻድቁ በአባ ዓቢየ እግዚእ ቃል ኪዳን ምክንያት ነው:: [ሁሉም የሃገራችን ከተሞች የተባረኩ መሆናቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው] ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ፲፬ [14]ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን [መረታ] ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ:: አጥምቀው 'ዓቢየ እግዚእ' ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጉመ መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው" ማለት ነው:: ዓቢየ እግዚእ በሕጻንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ:: ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኩሰዋል:: በገዳሙ በጾም: በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን አግኝተዋል:: በጊዜው በ፵ [40] ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር:: ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል:: ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ አባትም ነበሩ:: ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ ስብከታቸው ነው:: አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ:: ቀኑ ነሐሴ ፲ [10] ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ፫ [3] ቀናት ባለመጉደሉ ከ፩ ሺህ [1,000] በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ:: ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ- አማንያን [አሕዛብ] ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ:: ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ:: ይሕን ድንቅ ያዩ ከ፩ ሺህ [1,000] በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል:: ይሕም ዘወትር ነሐሴ ፲ [10] ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው [ጐንደር] ይከበራል:: ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ:: ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች:: ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር:: በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሠል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት:: ይሕንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ:: በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ:: የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም:: በሰማይም እሳትን አያዩም:: ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም::" ብሏቸው አርጓል:: ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል:: ይሔው እኛ ምን ብንከፋ: ጻድቁንም ብንረሳቸው እግዚአብሔር ግን ዛሬም በጻድቁ ምልጃ ከተማዋን ጠብቆ ይኖራል:: ነገን ደግሞ እርሱ ያውቃል:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ [ጎንደር ቀበሌ 09 ኪዳነ ምሕረት] ጻድቁ የጸለዩበት ቦታ ነው:: እንኳን በወርሃዊ በዓላቸው በ፲፱ [19] ይቅርና በዓመታዊ በዓላቸው [ግንቦት ፲፱ [19] ለንግስ የሚመጣው ሰው ቁጥር ያስተዛዝባል:: አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው: ፫ [3] ሙታንን አስነስተው: ብዙ ድውያንን ፈውሰው: ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው: የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው: በ፻፵ [140] ዓመታቸው ግንቦት ፲፱ [19] ቀን አርፈዋል:: የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው:: "ተአምሪሁ ለጻድቅ አቡነ ዓቢየ እግዚእ - - - ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን::" " ከበዙ ተአምራቱ አንዱን " ጻድቁ አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን [መረታ] ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ "አባቴ! የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?" አለቻቸው:: ጻድቁም በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው : በመስቀላቸው ባርከው ሰጧት:: ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና "ልጠጣው" ብላ የተቀበለችውን ማይ [ጸበል] ልትጠመቅበት [ልትጸበልበት] ወሰነች:: ባልንጀራዋንም "በላዬ ላይ አፍሺልኝ" ስትል አዘዘቻት:: ባልንጀራዋም "እሺ" ብላ ልታፈስላት [ልትጸብላት] በፋጋ [ግማሽ ቅል] ያለውን ጸበል አነሳች:: ልታፈሰው ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ ፪ [2] ቱም ደነገጡ:: ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና:: ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ:: ከውጭ ሆነውም "አባ! አባ! የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነ" አሏቸው:: ጻድቁም እንዳላዋቂ "ምን አጠፋችሁ?" ሲሉ ጠየቁ:: "አባታችን! ምንም አላጠፋንም:: ብቻ አፍሺልኝ ብየ ስሰጣት እንዲህ ሆነ" ስትል አንዷ መለሰች:: ጻድቁ ግን በየውሃት "ልጆቼ! ሁሌም : 'ምንም አላጠፋንም' አይባልም:: ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና:: + . . . አንቺም ልጄ ! እኔን ያልሺኝ 'የምጠጣው ጸበል ስጠኝ' ነበር:: ግን ልትጸበይበት ወደድሽ:: ስሕተትሽ ከዚህ ይጀምራል:: [የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና] ¤በዚያ ላይ "አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . . ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም::" [ዮሐ.፰፥፵፬] + . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን 'አጥምቂኝ' አልሻት:: ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ ተለውጦባቹሃል" ብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ:: "እፍ" ሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ ተመለሰ:: ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው ለጻድቁ ሰገዱ:: ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን::
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram