cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

✞✟ ኦርቶዶክሳዉያን ✞✟

እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጣቹ ይህ ቻናል የተከፈተው ለኦርቶዶክሳውያን እና ማወቅ ለሚፈልግ ለማንኛውም ሰው ነው ✞መዝሙር ✟ግጥም ✞ኦርቶዶክሳዊ ፎቶ ያገኙበታል

Show more
Advertising posts
529
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-1630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

                        †                         🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊 '' ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰይጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም '' 🕊 '' ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። '' †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
Show all...
🕊 [ † እንኳን ለነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤርምያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † †  🕊  ቅዱስ ኤርምያስ  🕊 †    † ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ከዐበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በስድስት መቶ አካባቢ የነበረ ነቢይ ነው:: አባቱ ኬልቅዩ ይባላል:: ከካህናተ እስራኤል አንዱ ነበር:: እግዚአብሔር ኤርምያስን የጠራው ገና በሕፃንነቱ ነበር:: "ከእናትህ ማኅጸን ሳትወጣ መርጬሃለሁ: ቀድሼሃለሁ" ሲልም በገሃድ መስክሮለታል:: [ኤር.፩፥፭] (1:5) ከቅዱሳን ነቢያት እንደ ኤርምያስ የተሰቃየና ያለቀሰ የለም:: ከሰባ ዘመናት በላይ ስለ ወገኖቹ አልቅሷልና ሊቃውንት "ነቢየ ብካይ" [ባለ እንባው ነቢይ] ይሉታል:: ዘመኑ ዘመነ-ኃጢአት [ዘመነ ዐጸባ] ነበር:: እሥራኤላውያን ከመሪዎቻቸው ከነ ሴዴቅያስ ጋር በክፋት ተባብረውም ነበርና ኤርምያስን አልሰሙትም:: ይልቁኑ ክፉ ቦታ ውስጥ አስረው አሰቃዩት:: እግዚአብሔር ግን በኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ አማካኝነት ከመከራው አዳነው:: የተሰበከላቸውን የንስሐ ጥሪ አልሰሙምና ስልምናሦር የሚባል የአሕዛብ ንጉሥ መጥቶ አሥሩን ነገድ ማርኮ በ፯፻፳፪ [722] አሦር [ነነዌ] አወረዳቸው:: በኋላ ደግሞ በኃይለኝነቱ የታወቀው የባቢሎን ንጉሥ ይማርካቸው ዘንድ ወደ ሁለቱ ነገድ ኢየሩሳሌም ደረሰ:: ኤርምያስ ወደ ከተማዋ ዳር ወጥቶ ስለ ኢየሩሳሌምና ስለ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቀሰ:: ከቤተ መቅደስ ንዋያት እኩሉን ለምድር አደራ ሰጣትና ሸሸገችው:: ነቢዩ የተናገረው አይቀርምና ንጉሡ ናቡከደነጾር እኩሉን ገድሎ: እኩሉንም ማርኮ: ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ: የአሕዛብ መዘባበቻ አድርጐ በ፭፻፹፮ [586] ባቢሎን አወረዳቸው:: ቅዱስ ኤርምያስን ግን ትሩፋን [ከመከራው የተረፉት] ይዘውት ወደ ግብጽ ወረዱ እንጂ አልተማረከም:: በዚያም ተአምራትን አድርጐ አራዊትን አጥፍቷቸዋል:: ትንሽ ቆይቶ ግን እውነተኛ አባት : ነቢይ : መምሕርም ነውና ወደ ሕዝቡ [ወደ ባቢሎን] ወረደ:: በዚያም ትንቢትን እየተናገረ : ሕዝቡን ከሰባ ዓመታት በኋላ ወደ ሐገራቸው እንደሚመለሱ እያስተማራቸው በባቢሎን ቆይቷል:: ያለ በደሉም በመከራቸው ተካፋይ ሆኗል:: ሰባው ዘመን ሲፈጸም እግዚአብሔር እንደ ቃል ኪዳኑ በኤርምያስ መሪነት እሥራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: አሁንም ግን ክፋታቸውን ይተው ዘንድ ፈቃደኞች አልነበሩምና ኤርምያስ ገሠጻቸው:: በዚህ ተበሳጭተው ሊወግሩት ሲሉ ጸጋ በዝቶለት : ምሥጢርም ሰፍቶለት ስለ ነገረ ሥጋዌ [ስለ ክርስቶስ የማዳን ሥራ] አምልቶና አጉልቶ ትንቢት ተናገረ:: አንዴ ልቡናቸው ታውሮ ኤርምያስ ነው ብለው ድንጋዩን በድንጋይ ሲወግሩት ውለዋል:: ዘግይቶ ግን ኤርምያስ ራሱን ገለጠላቸው:: ስለ እነርሱ ሲል ሰባ ዘመን ያለቀሰውንና ምትክ የሌለውን አባታቸውን ወግረው ገደሉት:: ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ሃምሳ ሁለት ምዕራፎች ያሉት ሐረገ ትንቢት ተናግሯል / ጽፏል:: ዜና ሕይወቱ ከራሱ የትንቢት መጽሐፍ በተጨማሪ በተረፈ ኤርምያስ : በመጽሐፈ ባሮክ : በገድለ ኤርምያስ : በዜና ብጹዐን : በመጽሐፈ ስንክሳርም ተጽፏል:: † ቸር እግዚአብሔር በኤርምያስ ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿን ከስደትና ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: 🕊 [ † ግንቦት ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ [ከታላላቆቹ ነቢያት አንዱ] [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት ፪. ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ፫. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፬. ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ ፭. ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ † " ኢየሩሳሌም ሆይ ነቢያትን የምትገድል : ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር : ዶሮ ጫጩቶቿን ከክንፎቿ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም:: እነሆ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላቹሃል:: እላችሁአለሁና : በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ እንግዲህ ወዲህ አታዩኝም :: " [ማቴ. ፳፫፥፴፯-፴፱] [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Show all...
                          †                           [     🕊    ዳግሚያ ትንሳኤ !    🕊      ] እንኩዋን ለዳግሚያ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ ! 💖 ✞ እሁድ - ዳግም ትንሣኤ ይባላል ፦ በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ --------------------------------------------- "ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ 'ሰላም ለእናንተ ይሁን' አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን 'ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን' አለው:: ቶማስም 'ጌታዬ አምላኬም' ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም 'ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው' አለው::" [ዮሐ.፳፥፳፮-፳፱] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
Show all...
                        †                         🕊  💖    ዕለተ ሰንበት   💖   🕊 ▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬ †  🕊 ዳግሚያ ትንሳኤ !   🕊  † እንኩዋን ለዳግሚያ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ። ለስም አጠራሩ ጌትነት ይድረሰውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ትንሳኤው በሁዋላ ለደቀ መዛሙርቱ በጉባኤ ፫ [3] ጊዜ ተገልጦላቸዋል :- ፩. በዕለተ ትንሳኤ ምሽት በፍርሃት ሳሉ ፪. ያላመነ ቶማስን ለማሳመን በተነሳ በ ፰ [ 8 ]ኛው ቀን [ ማለትም ዛሬ ] ፫. ከተነሳ ከ ፳፫ [ 23 ] ቀናት በሁዋላ በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ላይ ነው:: ጌታ አርባውን ቀን ለአንዱም: ለሁለቱም በግል ይገለጥላቸው ነበር:: እመቤታችንን ግን ፈጽሞ አይለያትም ነበር:: ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለሳምንት ተለይቷቸው ስለ ነበር በቤተ ክርስቲያን ውዳሴ ማርያም እንጂ መልክዐ ኢየሱስ በማሕበር አይደገምም:: በዚሕች ዕለት ደቀ መዛሙርቱ በጽርሐ ጽዮን ሳሉ ጌታችን "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ብሏቸዋል:: ቶማስንም "ና ዳስሰኝ" ብሎታል:: ሐዋርያው እጁን ከተወጋ ጐኑ ላይ ቢያሳርፍ በመቃጠሉ "ጌታየ አምላኬም" ሲል ጮሆ ምስጢረ ተዋሕዶውን መስክሯል:: ጌታም ቶማስን "እስመ ርኢከኒሁ አመንከኒ" [ማለትም ስላየኸኝ አመንከኝ] ! "ብጹዐንሰ እለ እንዘ ኢይሬእዩኒ የአምኑኒ" [ሳያዩ የሚያምኑ ግን ብጹዐን (ማለትም ንዑዳን ክቡራን) ናቸው ብሎታል:: [ዮሐ.፳፥፳፬] (20:24) ከጌታችን ከትንሳኤው: ከቅዱሱም ሐዋርያ በረከት አይለየን:: ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ 'ሰላም ለእናንተ ይሁን' አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን 'ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን' አለው:: ቶማስም 'ጌታዬ አምላኬም' ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም 'ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው' አለው:: [ዮሐ.፳፥፳፮-፳፱] (20:26-29) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † [  ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
Show all...
                        †                         🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊 '' ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰይጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም '' 🕊 '' ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። '' 💖 [ †  🕊  ክብርት ሰንበት  🕊 † ] " ንጉሥ ከእርሱ ርቀን የነበርን እኛ ቤዛችን በሚሆን በልጁ ሕማም ከእርሱ ምን ያህል ክብር እንዳገኘን ዐወቅህን? ሞት ጠፋ ፣ ዲያብሎስም ድል ተነሣ ፣ ሲዖል ታወከ ፣ በኃጢአት የተፈረደው ፍርድ ተፋቀ ፣ ሰይጣን ያመጣው ስሕተት ጠፋ። እንዳልነበረም ሆነ ገነት ተከፈተ ትንሣኤ ተገለጠ" [ ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ ] --------------------------------------------- " ለክርስቶስ ፡ ይደሉ ፡ ስብሐት ፤ ለዘአብጽሐነ ፡ እስከ፡ ዛቲ ፡ ሰዓት ፤ እግዚኣ ፡ ለሰንበት ፤ አኰቴተ ፡ ነዓርግ ለመንግሥትከ ፡ ወመኑ ፡ መሐሪ ፡ ዘከማከ። ትርጉም ፦ [ እስከዚኽች ሰዓት ለአደረሰን ለክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል፡፡ የሰንበት ጌታዋ ነው፡፡ ለጌትነትህ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ እንዳንተ ያለ ይቅር ባይ ማነው ? ] [ ቅዱስ ያሬድ ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
Show all...