en
Feedback
ነፃ ዓለም✨✨✨

ነፃ ዓለም✨✨✨

Open in Telegram

✨አጫጭር ወጎች ✨ልቦለዶች ✨መፃህፍት ✨profile picture ✨የተለያዩ ሰዎች ድንቅ አባባል ✨ግጥሞችን ያገኛሉ። ለሀሳብ ለአስተያየት @netsi2_9

Show more
Ethiopia7 941The category is not specified
2 659
Subscribers
+3324 hours
+1157 days
+13230 days
Posts Archive
ኪዳንሽ ነው መበርቻዬ" ፀሎትሽ ነው መደገፊያዬ " ሞገሴነሽ መድመቂያዬ" አርማዬነሽ መለያዬ..."
ኪዳንሽ ነው መበርቻዬ" ፀሎትሽ ነው መደገፊያዬ " ሞገሴነሽ መድመቂያዬ" አርማዬነሽ መለያዬ..."

ሰላም እንዴት ነህ የሚል ቴክስቷ ገባልኝ.... አይኔ ባለማመን አፈጠጥኩ እሷ ናት። ከስንት ጊዜ በኋላ ዛሬ እንዴት ፃፈልኝ...? ደመና ሳይኖር እንደዘነበ ዝናብ ነው ቴክስቷ ያስገረመኝ። ክብሩ ይስፋ
ሰላም እንዴት ነህ የሚል ቴክስቷ ገባልኝ.... አይኔ ባለማመን አፈጠጥኩ እሷ ናት። ከስንት ጊዜ በኋላ ዛሬ እንዴት ፃፈልኝ...? ደመና ሳይኖር እንደዘነበ ዝናብ ነው ቴክስቷ ያስገረመኝ። ክብሩ ይስፋ ደና ነኝ አንቺስ ብዬ ልፅፍላት አሰብኩ....ግን ወድያው በእሷ የሆንኩት ትዝ አለኝ....ማዕበል እንዳናወጣት መርከብ ሰመጥኩ ተጋጨው ....ስል ነበር.... አውሎ ንፋስ እንደሚያባርራት ብጣሽ ፌስታል ህይወቴ ሲጦዝ ነበር። አልፈልግህም ስትለኝ....አለም በእሷ ድምፅ ያወራችኝ ያህል ራሴን ከአለም ነጥዬ ነበር። ደናነህ ወይ ሲሉኝ ምን ደንነት አለ ያልኩበት ጊዜም ነበር። በእኔ እና በእሷ ተስፋ ከመቁረጥ ራሴን ማጥፋት የተሻለ አማራጭ የመሰለኝ ጊዜም አሳልፌለሁ። ያንን ሁሉ ሳስብ....ምን አገባሽ አሁን ለምን መጣሽ በላት በላት አለኝ። ግን ደግሞ የአሁኑ ማንነቴ ለጠያፍ ቃል ቦታ የለውም። በቃ ደና መሆኔን እኔ አውቃለሁ። ተመልሳ መታ አይደለም ህይወቴን ሽርፍራፊ ደቂቃዎቼን አታባክንብኝም። እሷን በመውቀስም በመክሰስም የማባክነው ትርፍ ሰአት የለኝም። ስለዛ ዝም አልኳት ...!!! ✍ነፂ_ነኝ #ነፃሁኑልኝ ✨✨✨
@NetsaAleme

አመናጨቃት .... የማላውቀው ጋጥወጥነቱን አየሁት....ንዴቱ አካኪ ዘራፍ አለ....የፊቱ ደምስር እስኪደንቀኝ ድረስ ተገታተረ.....ሲናደድ በዚ ልክ ማስፈራቱ አስፈራኝ። እንዲ ሲሆን አይቼው አላውቅ
አመናጨቃት .... የማላውቀው ጋጥወጥነቱን አየሁት....ንዴቱ አካኪ ዘራፍ አለ....የፊቱ ደምስር እስኪደንቀኝ ድረስ ተገታተረ.....ሲናደድ በዚ ልክ ማስፈራቱ አስፈራኝ። እንዲ ሲሆን አይቼው አላውቅም። ስልኩን አውርቶ ሲጨርስ....የኔ ፍቅር በጣም ይቅርታ እሺ ይቺ እብድ የሆነች ልጅ አናዳኝ እኮ ነው በረጅሙ ተነፈሰ። እብድ ያላት እና የመነጫጨካት እኩያ ናችሁ የሚለኝን ታናሽ እህቱን ነው። እሺ ....አልኩት አፌ ላይ የመጣው ቃል እሺ ስለነበር። መታጠቢያ ቤት ደርሼ መጣሁ ብሎ ሄደ። ለብቻዬ ስምሰለሰል ወድያውኑ መጣ....ተረጋግቷል የማቀውን የዘመናት ፍቅረኛዬ ቦታው ተመልሷል። አሁን እንደ በፊቱ ብዙ አልፈራሁትም...አባ ግን በምን አናዳህ ነው...አልኩት እጆቹን እየዳሰስኩ.... ተያት ባክሽ ጉዳዩ Sirius አይደለም...ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽልኝ የኔ ንግስት....ወደ ወደድኩለት እሱነቱ ተመለሰ። እሱነቱ ስል ግን ግራ እየተጋባሁ ነው። እሱ የቱ ነው የቅድሙ ወይስ የአሁኑ....? ከእህቱ ጋር በትንሽ ነገር ከሆነ እንደዛ የጮሀባት እኔስ ላይ ነገ...? እኔ ላይማ ይሄን አያደርግም ብዬ ጥብቅና ልቆምለት አልፈለኩም። እህቱን ያላከበረ እኔንም ከትንሽ ቆይታ በኋላ....? አፈትልኮ ከወጣው ንዴቱ በላይ የማንነቱ መራራቅ አስፈራኝ። የሆነ በማስክ የከለለው ድብቅ ማንነት እንዳለው ስድስተኛው ህዋሴ ደጋግሞ ነገርኝ። የማስመሰል ብቃቱ ምን ያህል እንደሚሄድ ....ከመጠን በላይ ልነጠፍልሽ የሚለኝ አኳኋኑ....የቲያትር መድረክ ላይ የቆመ ተዋናይ እንደሆነ እንዳስብ አስገደደኝ። አስመሳይ እንደሆነ ጠረጠርኩ....ጥርጣሬዬ ወደ ፍርሀት ተቀየረ....ማስኩን ሲያወልቅ ምን እንደሚመስል ሳስብ የበለጠ ፈራሁ። ሸሸሁት...!!! ✍ነፂ_ነኝ #ነፃሁኑልኝ ✨✨✨
@NetsaAleme

አመናጨቃት .... የማላውቀው ጋጥወጥነቱን አየሁት....ንዴቱ አካኪ ዘራፍ አለ....የፊቱ ደምስር እስኪደንቀኝ ድረስ ተገታተረ.....ሲናደድ በዚ ልክ ማስፈራቱ አስፈራኝ። እንዲ ሲሆን አይቼው አላውቅም። ስልኩን አውርቶ ሲጨርስ....የኔ ፍቅር በጣም ይቅርታ እሺ ይቺ እብድ የሆነች ልጅ አናዳኝ እኮ ነው በረጅሙ ተነፈሰ። እብድ ያላት እና የመነጫጨካት እኩያ ናችሁ የሚለኝን ታናሽ እህቱን ነው። እሺ ....አልኩት አፌ ላይ የመጣው ቃል እሺ ስለነበር። መታጠቢያ ቤት ደርሼ መጣሁ ብሎ ሄደ። ለብቻዬ ስምሰለሰል ወድያውኑ መጣ....ተረጋግቷል የማቀውን የዘመናት ፍቅረኛዬ ቦታው ተመልሷል። አሁን እንደ በፊቱ ብዙ አልፈራሁትም...አባ ግን በምን አናዳህ ነው...አልኩት እጆቹን እየዳሰስኩ.... ተያት ባክሽ ጉዳዩ Sirius አይደለም...ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽልኝ የኔ ንግስት....ወደ ወደድኩለት እሱነቱ ተመለሰ። እሱነቱ ስል ግን ግራ እየተጋባሁ ነው። እሱ የቱ ነው የቅድሙ ወይስ የአሁኑ....? ከእህቱ ጋር በትንሽ ነገር ከሆነ እንደዛ የጮሀባት እኔስ ላይ ነገ...? እኔ ላይማ ይሄን አያደርግም ብዬ ጥብቅና ልቆምለት አልፈለኩም። እህቱን ያላከበረ እኔንም ከትንሽ ቆይታ በኋላ....? አፈትልኮ ከወጣው ንዴቱ በላይ የማንነቱ መራራቅ አስፈራኝ። የሆነ በማስክ የከለለው ድብቅ ማንነት እንዳለው ስድስተኛው ህዋሴ ደጋግሞ ነገርኝ። የማስመሰል ብቃቱ ምን ያህል እንደሚሄድ ....ከመጠን በላይ ልነጠፍልሽ የሚለኝ አኳኋኑ....የቲያትር መድረክ ላይ የቆመ ተዋናይ እንደሆነ እንዳስብ አስገደደኝ። አስመሳይ እንደሆነ ጠረጠርኩ....ጥርጣሬዬ ወደ ፍርሀት ተቀየረ....ማስኩን ሲያወልቅ ምን እንደሚመስል ሳስብ የበለጠ ፈራሁ። ሸሸሁት...!!! ✍ነፂ_ነኝ #ነፃሁኑልኝ ✨✨✨
@NetsaAleme

እገልሻለሁ ነው ....ማስፈራሪያው....? መፍራት ላቆመ ሰው ...ማስፈራራት ይቻላል ወይ...?... ትልቁ ፍርሀት የማጣት ፍርሀት ነው። ያንን ደግሞ እንዳላጣቸው በእንብርክኬ የሄድኩላቸውን ነገሮች
እገልሻለሁ ነው ....ማስፈራሪያው....? መፍራት ላቆመ ሰው ...ማስፈራራት ይቻላል ወይ...?... ትልቁ ፍርሀት የማጣት ፍርሀት ነው። ያንን ደግሞ እንዳላጣቸው በእንብርክኬ የሄድኩላቸውን ነገሮች ሁሉ ነጥቆ ፍርሀቴንም ወስዶብኛል። ግን አሁንም እገልሻለሁ ይላል። እገልሻለሁ....አጠፋሻለሁ ማለት ነው አይደል እባክህን ነው የኔ መልስ.... ለልመና የማወጣው የተማፅኖ የመጨረሻው ቃል ውደዱኝ....አፍቅሩኝ ...አክብሩኝ....አንግሱኝ አይደለም...ግደሉኝ ገላግሉኝ ነው። በቁሙ የሞተን ሰው መግደል ተሸክሞ ከሚሄደው ሬሳ ጋር መለያየት እኮ ነው። ሬሳ ፊቴ ለመጨረሻ መጀመርያ ጊዜ ፈገግ አለ። አው ፊቴ ፈካ ....በመንፈስ ከሞትኩ በኋላ ሬሳዬም ስቆ አያውቅም ነበር። አሁን ግን እገልሻለሁ የሚለው የምስራች አስፈገገኝ ህይወትን በማየት የደከሙት እና የቧዘዙተ አይኖቼ ሞትን ለማየት ቸኮሉ አንፀባረቁ። እባክህን አሁን አድርገው....በሽጉጥ ተመቶ በቅፅበት የመሞትን ደስታ ሳስበው ....የአለም የደስታ ጥግ ሆነልኝ። ህይወቴ ፊልም ቢሆን አያጎጎም ነበር ....መጨረሻው ሞት ሲሆን ግን ፍፃሜው አጎጎኝ። ግን ክፉ ነው....ደስታዬን ሲያይ የደገነብኝን ሽጉጥ መለሰው....አልገልሽም አለኝ። መጨረሻዬን መዳረሻዬን ማረፊያዬን ሞቴን ነጠቀኝ። ከበድገን መንፈሴና አካሌ ጋር ተወኝ። ሞቴንም ነጠቀኝ....! ✍ነፂ_ነኝ የሰሞኑን ፁፌ ነፃሁኑልኝ አያስብልም ከወደዳችሁት ግን like አድርጉ❤️
@NetsaAleme

ስሚኝማ የኔ ቆንጆ ብላ ጀመረች...! ማን ያንቺ አደረገኝ...ከበፊቱ በበለጠ በሚንቀለቀል ቁጣ አፍጥጣ ጠየቀቻት...! ለማረጋጋት ያወጣቸው ቃል የባሰ ቦግ ያደረጋት ለምን እንደሆነ አልገባትም....ማ
ስሚኝማ የኔ ቆንጆ ብላ ጀመረች...! ማን ያንቺ አደረገኝ...ከበፊቱ በበለጠ በሚንቀለቀል ቁጣ አፍጥጣ ጠየቀቻት...! ለማረጋጋት ያወጣቸው ቃል የባሰ ቦግ ያደረጋት ለምን እንደሆነ አልገባትም....ማ.ለት.. አለች...ነገሩ ግራ እንደሆነባት የደነገጠው ገጿና ድምጿ ያስታውቃል። የኔ ቆንጆ አልሽኝ እኮ....ማን ያንቺ ቆንጆ አደረገኝ....? አንቺ ማነሽና እኔን ያንቺ አድርገሽ ለምንድነው የጠራሽኝ....." ስሚ እኔ የማንም ሁኜ አላውቅም የማንምም አልሆንም። ወፍ ዘራሽ እንደሆንኩ....ስሞትም ያው ራሱ ወፍ ይበላኛል። የኔ ቆንጆ ትለኛለች ጭራሽ......የማንም አልነበርኩም.....የማንምም አልሆንምም ....በቁጣ ቃል በለሆሳስ ታወራለች.ቦርሳዋን ከወደቀበት ተንገዳግዳ አንስታው ሄደች። እንደዚ አድርጎሽማ ክሰሺው ሲሏት የነበሩት ሁሉ ....ደፍረው አትሂጂ ሊሏት አልቻሉም። ቢሏትም የሚከተላቸውን ያውቃሉ። አሰብኩልሽ አቀረብኩሽ ወደድኩሽ ሲሏት አትወድም። በተቃራኒው ልቧን ለሚከሰክስባት ሰው....ልቧን ማንነቷን አሳልፋ ትሰጣለች። በተከሰከ ብርጭቆ ላይ መራመድ ቀይ ደሟን ማየት የማታውቀው እፎይታን ያለብሳታል። በስቃይ ውስጥ ላደገችው ነፍሷ....ተድላ ደስታን አትፈቅም። እንደለመድነው እንርከስ ትላታለች... መርከስ መተናነስ ህይወቷ ነው ✍ነፂ_ነኝ #ነፃሁኑልኝ ✨
@NetsaAleme

ወደ ኋላ የሚጎትተን ትዝታ ከኖርንበት ጊዜ ቢቀነስ አሁን ስንታመታችን ይሆን...? እድሜ ወደፊት መቁጠር ሆነ እንጂ ሰው ህይወቱ ወደፊት ብቻ አይደለም ብዙ ወደኋላም አለው...!!! ✍ነፂ_ነኝ #ነፃሁ
ወደ ኋላ የሚጎትተን ትዝታ ከኖርንበት ጊዜ ቢቀነስ አሁን ስንታመታችን ይሆን...? እድሜ ወደፊት መቁጠር ሆነ እንጂ ሰው ህይወቱ ወደፊት ብቻ አይደለም ብዙ ወደኋላም አለው...!!! ✍ነፂ_ነኝ #ነፃሁኑልኝ ✨✨✨
@NetsaAleme

ጥያቄ...?
ጥያቄ...?

Repost from እንማር
✅በአንድ በህዝብ በተጨናነቀ ባቡር ውስጥ አባት ከ24 አመት ወጣት ልጃቸው ጋር እየተጓዙ ነበር። ✔️ልጅ በጣም ደስተኛ መሆኑን በሚያሳብቅ ሁኔታ የሚያየው ነገር ሁሉ አስገራሚ ሆኖበታል። በየመሃሉ በደ
✅በአንድ በህዝብ በተጨናነቀ ባቡር ውስጥ አባት ከ24 አመት ወጣት ልጃቸው ጋር እየተጓዙ ነበር። ✔️ልጅ በጣም ደስተኛ መሆኑን በሚያሳብቅ ሁኔታ የሚያየው ነገር ሁሉ አስገራሚ ሆኖበታል። በየመሃሉ በደስታ ተሞልቶ ወደ አባቱም እየዞረ "አባዬ ዛፎቹን ትተናቸው አለፍን" "አባዬ ደመናው አብሮን እየሄደ ነው እየው " "አባዬ ተራራው ሰማዩን ነክቶታል ተመልከተው" በተደጋጋሚ እንደዚህ ያሉ ነገሮችን በደስታ ተሞልቶ ከፍ ባለ ድምፅ ለአባቱ ይነግራቸው ነበር ፡፡ አባት ልጃቸውን በስስት እያዩ የሚላቸውን ቦታ ሁሉ ይመለከቱ ነበር። አባትም በደስታ ትክክል መሆኑን ያረጋግጡለታል፡፡ በባቡሩ ውስጥ የነበሩት ሌሎች ተሳፋሪዎች በወጣቱና በአባቱ ሁኔታ ግራ እንደመጋባት ብለዋል፡፡የወጣቱን የአይምሮ ጤንነት በፅኑ ተጠራጥረዋል፡፡ የወጣቱ ነገረ ስራ ያበሳጫቸው ጤንነቱንም የተጠራጠሩ ጥንዶች ለአባትየው "ሆስፒታል ብትወስደው የተሻለ ነው። የልጅህ አዕምሮ ጤነኛ አይመስለንም "አሉት:: ✅አባትም ጥንዶቹን በአንክሮ እያየ "ከሆስፒታል ነው የምንመጣው፡፡ዛሬ ህክምናውን ጨርሶ ነው የወጣው ፡፡ልጄ ከብዙ አመታት ልፋት በውኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማየት የቻለበት ቀን ነው። ከተወለደ ጀምሮ ማየት የተሳነው ነበረ"አላቸው። *** ለምን እንፈርዳለን? ✈️✈️@Enmare1988 ✈️@Enmare1988

ልጅ ሁነሽ የምተታውቂ አይመስለኝም.... ለራስሽ ስታስቢ ራስሽን ስታስቀድሚው አላውቅሽም.....አንጀትሽ ሲንሰፈሰፍ.....የአይንሽ ውሀ ሙሉውን ፍቅር ሲሆን ነው የማውቅሽ..... አምላክ ገና ከጅማሬው ሲፈጥርሽ ጠባቂ ተንከባካቢ ከለላ መከታ ለኛ ያደረገሽ ይመስለኛል.....ያ ባይሆን የተፈጠርሽው ለእኛ ባይሆን በዚ ልክ ሰውን ሰው እንዴት ይወደዋል። ሞትን ስታስቢ እንኳን የአንቺ አለመኖር የሚያጎልብንን እያሰብሽ ነው ሞትን የምትፈሪው ይሄንን ሳላደርግ ሳይሆን ይሄንን ሳላደርግላቸው እንዳትወስደኝ ነው ፀሎትሽ። ደስታሽ የእኛ ደስታ ነው....ህመማችን ደግሞ ላንቺ የሞት ጣር.....ምን ያህል እንደምትወጂኝ ሳስብ ላንቺ ስል ብቻ መኖር ያጎጎኛል። ሆድሽ ውስጥ የቆየሁባቸው 9 ወራት ምን እንደሚመስሉ አለማስታወሴ ይቆኛል....ሰፍሳፋው አንጀትሽ ውስጥ መተኛት ያንሰፈስፍ ነበር ወይስ ይመቻል ....? ግን በዚ ልክ እንዴት ወደድሽን.....? የኔ እናት ደግሞ ደጋግሞ የመፈጠር እድል ቢሰጠኝ ካንቺ ውጪ ከሌላ እናት መወለድ አልፈልግም...እናትነት ያምርብሻል አልልሽም....። ምክንያቱም አንቺ የሚገልፅሽ ቃል ቢሆን እናት የሚለው ስለሆነ። እናት መሆንን እንደ ጫማ ተጫምተሽው ልክክ አለብሽ ...እንደልብስ ለብሰሽው አማረብሽ ማለት አንቺን እና እናትነትን ሁለት አካል ማድረግ ይሆንብኛል። እናት አንቺ ነሽ....ውስጥሽ ነው...እንደ ልብስ የሚደረብ....እንደጫማ የሚጠለቅ ሳይሆን የተዋሀደሽ ማንነት። ሴት ከመሆንሽ በፊት እናት የሆንሽ  ነው የሚመስለኝ...በቃ ስትፈጠሪ ጀምሮ እናት አርጎ የፈጠረሽ አይነት .... ልብሽን የልጇቿን ሸክም ለመሸከም የምትችል አድርጎ....የብዙ ሰው ችግርን የሚችል ሰፊ ትከሻ ሰቶ ባይፈጥርሽ.... እውን ማን ባንቺ ልክ ይጠነክርል ልል ይዳዳኝና....ፈጣሪ አስችሏት ነው ብዬ ጥንካሬሽን ማድበስበሴ ያሳፍረኛል። ፈጣሪማ ለሁሉም እንደ አቅሙ ችግር ሰቶታል...ግን አቅቶት ስንቱ ተሰበረ ....የኔ ፅኑ አለት ማን እንዳንቺ በጀግንነት ከዚስ ደረሰ። ውድድድድ አደርግሻለሁ እናቴ የኔ ብርሀን😍 ✍ነፂ_ነኝ #ነፃሁኑልኝ ✨✨✨ @NetsaAleme

ሺ ስም ባወጣልሽ የሚመጥንሽ አላገኝም የኔ እናት ስልሽ ግን የሚሰማኝ ስሜት ከምንም ይበልጣል።
ሺ ስም ባወጣልሽ የሚመጥንሽ አላገኝም የኔ እናት ስልሽ ግን የሚሰማኝ ስሜት ከምንም ይበልጣል።

ምን አይነት ፊልም ይወዳሉ?
Anonymous voting

"እንግሊዝኛ እሰማለሁ፣ እረዳለሁ... ግን መናገር ስጀምር ቃላት ይጠፉብኛል!" የሚል የሁልጊዜ ስጋት አለባችሁ? 🤦‍♂️🤦‍♀️ የቃላት እጥረትና የሰዋስው ስህተት ፍርሃት ወደ ኋላ እንዳያስቀራችሁ! እንግሊዝኛን ልክ እንደ አማርኛ ያለ ምንም መቆራረጥ አቀልጥፈው የሚናገሩበትን ብቸኛ አማራጭ አቅርበንላችኋል። 🌟 @ENGLISH_LANGAUGE_CLUB 🌟 ከእኛ ጋር ሲማሩ፡ የአነጋገር ስልትዎን (Accent & Pronunciation) ያሻሽላሉ። በየቀኑ የሚጠፉብዎትን ቃላት (Vocabulary) በቀላሉ ይለምዳሉ። ከስህተት ፍርሃት ነፃ ሆነው መናገር ይለማመዳሉ። አሁኑኑ ይቀላቀሉና የቋንቋ ብቃትዎን ወደ ላቀ ደረጃ ያሳድጉ! 👇👇 ሊንኩን ይጫኑ 👇👇 👉 @ENGLISH_LANGAUGE_CLUB 👈 የለውጥዎ መጀመሪያ!
ነገ ማታ ያበደ Give away 6 ሰወች

የተዋወቅነው ፎቶ ልትነሳ መታ ነው። ቆንጂዬ ናት አብሶ አይኗ ጋር ያለው ጠባሳ ባይኖር...."አጠፋዋለሁ እሺ አልኳት ችዬ ከገላዋ ባላርቀው ከፎቶው እንኳን ላውጣላት ብዬ። ምንኑ ነው አለችኝ ...ድምፅ ውስጥ ይሄ ሁሉ ነገር ይኖራል ወይ እስክል ድረስ ትህትና አክብሮት በተሞላው ድምፅ .... ጠባሳውን ነዋ ማለት እየከበደኝ አይንሽ ጋር.... ....እእእእ ጠባሳዬን ነው እንዴ ተወው እንዲጠፋ አልፈልግም እንዲሁ አንሳኝ ....ማመስገኛዬ ነውና አለችኝ። እኔም ምን አንቀለቀለኝ ብዬ እንደፍላጎቷ አነሷኋት እሷም ሄደች። ከሄደች በኋላ ግን ማመስገኛዬ ያለችው ነገር ጥያቄ ፈጠረብኝ። ፎቶዋን መታ እስክትወስድ እና ጠባሳዋ እንዴት ማመስገኛ ሊሆናት እንደሚችል ለመጠየቅ ጎጎሁ። ጠባሳ ትዝታ ካለውም መጥፎ ትዝታ ነው እንዴት ማመስገኛ ይሆናል ...? አይደርስ የለም ፎቶዋን ልትወስድ መጣች...እኔም ጥያቄን አስከተልኩ ጠባሳሽ እንዴት ማመስገኛ ሆነሽ ግን አልኳት ፎቷዋን ስሰጣት። ....እንዴት መሰለህ ...ጠባሳዬን አየሀው አይኔ አጠገብ ነው። አይኔ አለመጥፋቱ የአይን አምላክ የሚሉት እግዜሩ ጠብቆኝ በተአምር ነው። ታድያ ይሄንን ጠባሳ ባየሁት ቁጥር የእግዚአብሔር ቸርነት ይገርመኛል። አይኔ ቢጠፋ ኑሮ  ....ህይወቴ ምን እንደሚመስል ስለሚያስታውሰኝ ....."እንዳመሰግን ያለኝ እንድቆጥር እና በአምላክ ጠባቂነት እንድተማመን አድርጎኛል አለችኝ። ከድምጿ ደግሞ አነጋገሯ ይበልጣል መሰለኝ ...የልቤ አመታት ስልት ቀየረ ... ከዛን ቀን ጀምሮ ጎደኛሞች ሆንን ....ከዛ best friend ከዛማ የሴትና የወንድ Best friend የለም የሚባለው እውነት ነው መሰለኝ...ፍቅረኛሞች ሆንን....! በቀረቧት ልክ ልቧ ወደራሷ ይጎትታል....እሷ ጋር ሁልግዜም ምስጋና አለ። ለማመስገን ሰበብ ፈላጊ ናት። አይነ ኩሉ ሚስት እንዲኖረኝ በጣም እመኝ ነበር። እሷን ካገኘሁ በኋላ ግን ከአይነ ኩሉ ሚስት በላይ ነገሮችን ኩላ የምታይ ሴት ህይወትን እንደምታስውብ ገብቶኛል። ጠማማዎች እሷ ጋር ይቀናሉ....ሁሉም ለበጎ ነው ብላ ከማሰብ የላቀ እምነት አላት እንደ እምነቷ ይደረግላትል....የምታመሰግነው አምላኳ እለት በእለት ማመስገኛ ደስታን ይጨምርላታል። እሷ ጋር ጎዶሎ የለም ሁሉሙ ሙሉ ሁኖ ነው የሚታያት....ሙላት መትረፍረፍ ውስጥ እንደምትኖር ስለምታምን ምሬት አርባ ክንድ ይርቃታል። ደርቋል ጠውልጓል እኮ ያልኩትን ጉዳይ በፀሎቷ ነፍስ ትዘራበታለች ....አምላኳ ሲተማመኑበት ደስ ስለሚለው ...የእምነት ፀሎቷን መልስ አያቆይባትም....። ብቻ የኔ  አበባ እወዳታለሁ....❤❤❤ ✍ነፂ_ነኝ #ነፃሁኑልኝ ✨✨✨ እኔ የምወደው ፁፌ ነው እናንተ ከወደዳችሁት like ❤️ አድርጉ😍
@NetsaAleme

photo content

ቁምነገር አውርቼ ከየት ሰማሽው ሲሉኝ ካንተ ነው የምላቸው....እግዚአብሔር ከአዳም አጥንት ሄዋንን ሰራት እንደተባለው። የእኔም ማንነት የተሰራው ባንተ ነው። አንተን ሳላውቅህ በፊት ነጭ ወረቀት ነበ
ቁምነገር አውርቼ ከየት ሰማሽው ሲሉኝ ካንተ ነው የምላቸው....እግዚአብሔር ከአዳም አጥንት ሄዋንን ሰራት እንደተባለው። የእኔም ማንነት የተሰራው ባንተ ነው። አንተን ሳላውቅህ በፊት ነጭ ወረቀት ነበርኩ ....ነጭ መሆኔ ግን ካንተ ለመግባባት አላገደኝም ምክንያቱ የእውቀት መጨረሻው ትህትና መኖርያው ካንተ ዘንድ ነውና። ለምጠይቅህ ነገር ሁሉ የምትሰጠኝ ማብራሪያ .... የማወቅ ጉጉቴን ያንረዋል። ምኞቴ አንተን መሆን ወደ መፈለግ ይመጣል። እንዳንተ ነገርን ከስር መሰረቱ መመርመር በቻልኩ እላለሁ። እንዳንተ ወግ አፌላይ ባማረልኝ። እንዳንተ እውቀት እና ትህትና በተስማሙልኝ። ትንሽ ሳውቅ ይሄንን የማያውቅ አለ እኮ ብሎ ልቤ ከመታበይ ቢዘገይልኝ እላለሁ። እመኛለሁ። ብቻ አንተ ህይወቴ ውስጥ ባትኖር የአሁኗ እኔ እኔን መሆኗን እጠራጠራለሁ። ✍ነፂ_ነኝ #ነፃሁኑልኝ ✨✨✨
@NetsaAleme

"እንግሊዝኛ እሰማለሁ፣ እረዳለሁ... ግን መናገር ስጀምር ቃላት ይጠፉብኛል!" የሚል የሁልጊዜ ስጋት አለባችሁ? 🤦‍♂️🤦‍♀️ የቃላት እጥረትና የሰዋስው ስህተት ፍርሃት ወደ ኋላ እንዳያስቀራችሁ! እንግሊዝኛን ልክ እንደ አማርኛ ያለ ምንም መቆራረጥ አቀልጥፈው የሚናገሩበትን ብቸኛ አማራጭ አቅርበንላችኋል። 🌟 @ENGLISH_LANGAUGE_CLUB 🌟 ከእኛ ጋር ሲማሩ፡ የአነጋገር ስልትዎን (Accent & Pronunciation) ያሻሽላሉ። በየቀኑ የሚጠፉብዎትን ቃላት (Vocabulary) በቀላሉ ይለምዳሉ። ከስህተት ፍርሃት ነፃ ሆነው መናገር ይለማመዳሉ። አሁኑኑ ይቀላቀሉና የቋንቋ ብቃትዎን ወደ ላቀ ደረጃ ያሳድጉ! 👇👇 ሊንኩን ይጫኑ 👇👇 👉 @ENGLISH_LANGAUGE_CLUB 👈 የለውጥዎ መጀመሪያ!

ሀሳብ ስጡበት ...
ሀሳብ ስጡበት ...

ህይወትን ለማጣጣም ምላስ ብቻ ሳይሆ ጥሩ ምላስ ያስፈልጋል። አለ አይደል ዝንብሎ ማግበስበስ የለመደ ሆድ ያለው ሰው ምላስ ለመቅመስም ለማጣጣምም አይሆንም ያገኘውን እንደወፍጮ ይፈጫል እንጂ..... ወይም ደግሞ ስራ ረፈደብኝ ብሎ ቢቀርብኝስ እያሉ እንደሚያፋጥኑት ጉርሻ አናት በአናት ትን እንዳይለን እየፈረረን የምንጎርሰው የመሯሯጥ ጉርሻ አይነት ህይወት ጊዜ ይሮጣል እንጂ እኛ አንኖርም። ለዚህ ነው ህይወትን ለማጣጣም ጥሩ ምላስ ያስፈልጋል ያልኩት። ጠዋት ከእንቅልፍ ስንነሳ የቀን ህይወት ይጀመራል። አላርም አስደንብሮ አስበርግጎ የቀሰቀሰው ሰው በላይ በላይ ጉርሻውን ጀመረ በቃ ምላሱን ገደለው። እሰይ ነጋ ብሎ ያልጀመሩት ቀን ጥርቅም ወር አመት እድሜ ይሆናል። እንበላለን አንረካም እንኖራለን ግን አልኖርንም። በእሰይ ነጋ የተጀመረ ቀን ....በረከትን ይቆጥራል ፀሀይ ለእሱ የወጣች ያህል በውበቷ ይማረካል። ትንንሽ ነገሮችን አይንቅም ....እግሮቹ መሬት የሲረግጡ በዘልማድ አይሆንም ስለ ጤንነቱ ያመሰግናል ። ግሩም እና ድንቅ አድርጎ የፈጠረውን አምላክ ማመስገን እንደ ተራራ አይከብደውም። ራሱን እያየ በራሱ ውስጥ አምላኩን ይፈልጋል። ትላንት ያልሰበሩትን የአለም ዱላዎች አስታውሶ አምላኩን ያወድሳል። ለዛሬ መድረሱን ያመሰግንበታል ነገን አንተ ብፈቅድ እያለ ሴለ አቀደው ለአምላክ ይናገራል ...የምኞቱን ቃብድ ፀሎቱን ለአምላክ ያደርሳል። መረጋጋት ከጊዜ መትረፍረፍ አይደለም የሚመጣው....መረጋጋት የሚመጣው ከውስጥ ሰላም ነው። የተዘበራረቀ ማንነት ያለው ሰው ይቸኩላል ይሮጣል ይጣደፋል። ግን አርፋጅ ነው። የቸኮለ አፍሶ ለቀመ እንደሚባለው....ይቸኩላል ይደፋል የደፋውን ሲለቅም ....ሲያማርር ሲነጫነጭ የእድሜው ጥላ ቀስ በቀስ ሲሸሽ ወጣትነት በጎልማሳነት ....ወደ አዛውንትነት ይቀየራል። ከዛማ ከመቼው ኖርኩ ይላል ሳይኖር መኖርያው ያልቃል። ✍ነፂ _ነኝ #ነፃሁኑልኝ✨✨✨ @NetsaAleme

photo content