en
Feedback
Werabe University Student Union

Werabe University Student Union

Open in Telegram

ይህ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት የቴሌግራም ቻናል ሲሆን ማንኛውም አይነት መረጃ የሚለቀቅበት እና የተማሪ ጥያቄ የሚመለስበት ነው።ሁሉም ተማሪ ይህን ቻናል በመቀላቀል እና ለሌሎች በማጋራት መረጃዎች ቶሎ እንዲደርሱ ሃላፊነታችንን እንወጣ።

Show more
270
Subscribers
+124 hours
-27 days
+230 days
Posts Archive
Repost from Werabe University
ታኅሳስ 16፣ 2016 ወራዩ /ዉ /ህ /ግ /ዳ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2015 የመውጫ ፈተና አፈጻጸምና የ2016 የመውጫ ፈተና ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል እንደሀገር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንና የመውጫ ፈተናም የዚሁ ስራ አንዱ አካል መሆኑን ገልጸዋል። የወራቤ ዩኒቨርሲቲም ምሩቃን በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በስራው ዓለም ብቁ፣ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በ2016 የመውጫ ፈተና ውጤት ሁሉንም ተማሪዎች ለማሳለፍ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ በ2015 የመውጫ ፈተና ያስፈተኗቸውን ሁሉንም ተማሪዎች 100% ያሳለፉት የስድስት ፕሮግራሞች ተሞክሮ በሁሉም ፕሮግራሞች ውጤቱ እንዲመዘገብ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች ተማሪዎች በመውጫ ፈተና ውጤታማ እንዲሆኑ በቅንጅት መስራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል። የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መምህርት አለዊያ ሁሰን የ2015 የቅድመ ምሩቃን የመውጫ ፈተናን አፈጻጸምና የ2016 ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን ባለፈው ዓመት በ32 ፕሮግራሞች የተሰጠው የመውጫ ፈተና በተያዘው ዓመት በ41 ፕሮግራሞች እንደሚሰጥ ተናግረዋል። የውይይቱ ተሳታፊ የአካዳሚክ ካውንስል አባላት፣ መምህራንና የተማሪ ተወካዮች ለተማሪዎች ሁሉንአቀፍ ድጋፍ በማድረግ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል።  

ማስታወቂያ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ቤተ-መጽሃፍትና ዶክመንቴሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በSRE DIGITAL ማሽን አገልግሎትና አጠቃቀም ዙሪያ በማሽኑ አቅራቢ ድርጅት ባለሙያዎች እለተ ማክሰኞ በቀን 18/03/2016 ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተማሪ ህብረት ተወካዮች፣ለሠላም ፎረም አባላትና ለብሎክ ማስተር ተወካዮች ስልጠና ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱ አደረጃጀቶች አባል የሆናችሁ ተማሪዎች በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ዲጂታል ላይብራሪ እንድትገኙ አሳስባለሁ፡፡ ከሠላምታ ጋር ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ቤ/ዶ/አ/ዳ

+6
📚 የመጀመሪያ አመት የተፈጥሮ ሳይንስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአብዛሀኛው ግቢ ላይ የሚወስዷቸው የመጀመሪያ ሴሚስተር ኮርሶች ናቸው። ━━━━━━━━━━━━ ❤Join & Share      @Concise_Education ✅️ ❤ Contact & Ads   ❤@Aconcise_bot✅️ ━━━━━━━━━━━━

+9
Anthropology Module.pdf1.63 MB

ሰላም ሰላም እንደት ናችሁ?? ለአድስ ወደ ግቢ ገቢ ተማሪዎች ከዚህ በታች የተለቀቀው የፍሬሽማን ትምህርቶች ናቸው።ወደ ግቢ ስትገቡ አዲስ እንዳይሆንባችሁ አይት አይት አድርጉት። ወደ ቻናሉ ሰው አድድ ማድረግ እንዳይረሳ!! 📚 የመጀመሪያ አመት የተፈጥሮ ሳይንስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአብዛሀኛው ግቢ ላይ የሚወስዷቸው የመጀመሪያ ሴሚስተር ኮርሶች ናቸው። ━━━━━━━━━━━━ https://t.me/wrustudentunion ━━━━━━━━━━━━

ውድ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ነባር እና አዲስ ተመዳቢ ተማሪዎች ይህ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት የቴሌግራም ቻናል ሲሆን ማንኛውም አይነት መረጃ የሚለቀቅበት እና የተማሪ ጥያቄ የሚመለስበት ነው።ሁሉም ተማሪ ይህን ግሩፕ በመቀላቀል መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲዳረስ ሃላፊነታችንን እንወጣ።