en
Feedback
🫂ሰው ሁን ከሰውም ሰው️️

🫂ሰው ሁን ከሰውም ሰው️️

Open in Telegram

until August 18/2021 ያለ አእምሮ ጤና ምንም ጤና የለም For Any Comment Inbox Me @umbeya

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel 🫂ሰው ሁን ከሰውም ሰው️️

Channel 🫂ሰው ሁን ከሰውም ሰው️️ (@ende_libe1) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 12 601 subscribers, ranking 1 824 in the Psychology category and 2 392 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 12 601 subscribers.

According to the latest data from 30 April, 2025, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 278 over the last 30 days and by 0 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 3.37%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 2.32% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 425 views. Within the first day, a publication typically gains 292 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 18.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
until August 18/2021 ያለ አእምሮ ጤና ምንም ጤና የለም For Any Comment Inbox Me @umbeya

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 18 March, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Psychology category.

12 601
Subscribers
No data24 hours
-117 days
+27830 days
Posts Archive
DSTV ቤት መሄድ ቀረረረረረ የፈለጉትን ጨዋታ በ LIVE STREAM የሚያሳይ ቻናል ተከፈተ 👇 https://t.me/addlist/kap8FWzsuG84YTE0 Add your channel @jowaver
+1
DSTV ቤት መሄድ ቀረረረረረ የፈለጉትን ጨዋታ በ LIVE STREAM የሚያሳይ ቻናል ተከፈተ 👇 https://t.me/addlist/kap8FWzsuG84YTE0 Add your channel @jowaver

በአብላጫ ድምፅ አሪፍ ተከታታይ ታሪክ ወይም ልብወለድ የምናቀርብ ሲሆን፣  ይህ post 50 Like እንደሞላ ይጀመራል። ✍ታዚ

ማዘር ማማሰያ ይዛ ና አልመታህም ስትልህ እና በሱ ልትቀምሽኝ ነው 😳🏃‍♀️😂        #Like ማንን ገደለ😂😂😂😡😡 ✍ታዚ

💎 የዛሬውን ተጠባቂ ጨዋታ ለመመልከት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ live 👉 https://t.me/addlist/kap8FWzsuG84YTE0 Add yours @jowaver
💎 የዛሬውን ተጠባቂ ጨዋታ ለመመልከት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ live 👉  https://t.me/addlist/kap8FWzsuG84YTE0 Add yours  @jowaver

🫶🏻ፍቅር..... 🔮🫀ፍቅር ውስጥ ....መተማመን አለ🥰 🔮🫀ፍቅር ውስጥ....ሀቀኝነት አለ☺️ 🔮🫀ፍቅር ውስጥ ....መፈላለግ አለ😍 🔮🫀ፍቅር ውስጥ ....መኮራረፍ አለ😪 🔮🫀ፍቅር ውስጥ....ይቅር መባባልም አለ🤗 🔮🫀ፍቅር ውስጥ..... ሰላም አለ😇 🔮🫀ፍቅር ውስጥ....ደስታ አለ🙂 🔮🫀ፍቅር ውስጥ ....መነፍፈቅ አለ👩‍❤️‍👨 🔮🫀ፍቅር ውስጥ....ትእግስት አለ😪 🔮🫀ፍቅር ውስጥ....ፍቅር አለ🫶🏻 ግን ፍቅራችን ውስጥ ከነዚ ነገሮች አብዛኞቹ ከሌሉ .....ድሮ ልጅ እያለን የእቃቃ ባልና ሚስት ሆነን እነደምንጫወተው አይነት ጊዜ ነው ምናሳልፈው👉🏽 := የስሜት መፈላለግ 👉🏽, የስሜት ንክኪ ,👉🏽የስሜት ግንኙነት ከዛ መሰለቻቸት 😐🫤መጨረሻው ደሞ መለያየት ከዛ ፍቅር እንዲነው እያሉ ማለቃቀስ 😅.........እና በቃ ስሜትና ፍቅርን እንለይ 😉 🫶🏻ፍቅር ደስ ይላል 🥰ስሙን አታጥፍት 🤨ዋ like ማንን ገደለ ሆሆ ✍ታዚ

ማስተዋል እንደአባቱ ላለመሆን ነበር የጣረው ገፍታ ገፍታ ከተተችው ሰከረ በጠጅ ተሳደበ እንዳባቱ የበደሉትን ሁሉ እረገመ የጊቢዉን በር ወርውሮ ገባ ወደ ዉስጥ ህሊና በሀይል ጮሆ ጠራት ከመኝታ ቤት ዘላ ወጣች አላመነችም ማስተዋል መሆኑን ሰደባት እስኪበቃዉ ወቀሳት መኖር እንጂ ማኖር የማትችዪ እራስ ወዳድ በሰዉ ሽንቁር ስንጥር እየሰነቀርሽ የምታላግጪ አረመኔ ........ መቋቋም አቃታት አንተም ወንድ ሆነህ እኔ ላይ አፍህን ትከፍታለህ አለች እየተመናቀረች ወንድ እንድሆን አይደል ፍላጎትሽ ያውም እንደ አባቴ መቼም አተሆንም ልፍስፍስ ሴታሴት ነህ አላስጨረሳትም ጠረቤዛ ላይ ባለዉ የአበባ ማስቀመጫ ወርውሮ መታት መስታወቱ አናቷ ላይ ፈነዳ ወደኋላ ወደቀች የቲቪ ማስቀመጫዉ ተቀበላት : : : : አቶ ማስተዋል ዘለቀ በተከሰሱበት ሰዉ የመግደል ወንጀል ጥፋተኛ ሆነዉ ስለተገኙ ፍርድ ቤቱ የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል !!!! { አንድ አንድ ታሪክ እንደዚህ ነዉ ትላንት አለማኖሩ ሳያንስ ዛሬንም ነገንም ይቀማል   } ''ከዝምታ ጀርባ ብዙ ንግግር ከማጎንበስ ጀርባ ብዙ ሸክም ከዛሬ በፊት ብዙ ትላንት መኖሩን መረዳት አስፈላጊ ነዉ '' < ዛሬ እንደዚ ያየነዉ ሰዉ ምን አልባት እንደዚ አልነበር ይሆናል የቀየረዉ የለወጠዉ የሆነ ምክኛት ይኖራል  > በስተመጨረሻም 👇👇👇👇 ያለፈ ታሪካቸዉ ጠፍንጎ ያሰራቸዉን ሰዎች አናስጨንቃቸዉ የታሰሩበትን ገመድ ሳይከረክራቸዉ ለመፍታት እንሞክር እንጂ ✍nati

CODE 5 አንገቱን ደፍቶ ሲሰራ ነዉ የምታውቀዉ : : : (ከልጅነቱም ቀና ብሎ ሰዉ ማየት አይችልም) : : : አንድ መስሪያቤት ነዉ የሚሰሩት እሱና እሷ የሁለት አለም ሰዎች ናቸዉ መሳቅ ትወዳለች=አይስቅም ብዙ ታወራለች=አያወራም አጃቢዋ ብዙ ነዉ=ብቸኝነት ጌጡ ነዉ እዛ ድርጅት ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ከማንም ጋር አያወራም አይስቅም አይጫወትም ስራዉን ብቻ ነዉ የሚሰራዉ አቀርቅሮ ገብቶ አቀርቅሮ ይወጣል ህሊና መስሪያ ቤቱን ከተቀላቀለች ቡሀላ ግን ይሄ ነገር አልቀጠለም ህሊና ዝም ያለ ሰው አይደለም ድንጋይ ታናግራለች ቆንጆጆጆ የምትባል ባትሆንም ለክፉ አትሰጥም አቋሟ.....አቋም እንኳ የላትም አጭር ለመባል እራሱ ትንሽ መርዘም አለባት ከምላሷ ግን አጠር ትላለች ማስተዋል ደግሞ ረዘም ብሎ ከመቅጠኑ የተነሳ ጎበጥ ያለ ዠልጋጋ ነዉ የጎበጠዉ ግን አብዝቶ ከማቀርቀር ይመስለኛል ህሊናና ማስተዋል የተግባቡት በስማቸዉ ምክኛት ነዉ ተግባቡ ተግባቡ ተዋወቁ አወሩ ተገናኙ ''ጊዜዉ ይነጉዳል አይደል እንደቀልድ ከተጋባን ሁለት አመት ሆነን'' ''ኧረ ሁለት አይደለም 22ነዉ ሴትዮ''አላት በልቡ ሁሌም ማስተዋል በልቡ እንጂ ቃል አዉጥቶ አይናገርም ቢናገርም የመልስ ምቷን ይፈረዋል በልጅነቱም ፈሪ ነበር መጫወት ይፈራል መደባደብ ይፈራል መዋኘት ይፈራል ጥያቄ መመለስ ይፈራል ሰዉ ማየት ይፈራል በቃ ማስተዋል ፈሪ ሳይሆን ፍርሃት እራሱ ነዉ በትዳሩ ደስተኛ አይደለም ለነገሩ በህይወቱም ደስተኛ አይደለም እንዴት እንዳገባ ሲጠየቅ አግብታኝ ነዉ እንጂ ተጋብተን አይደለም ይላል እራሷ መጣች እራሷ ፍቅረኛዬ ሆነች እራሷ ስለ ትዳር አወራች እራሷ አገባችኝ አንድ ቀን ሰምታኝ አታዉቅም ልትሰማኝም አትፈቅድም እርግጥ እኔ የማላወራ ብመስልም አይኔ ልቤ ብዙ ያወራ ነበር ግን አላስተዋለችም ነዳችኝ ተነዳሁላት አስከተለችኝ ተከተልኳት ይላል ልጅ መዉለድ አይፈልግም አባት መሆን አልችለም ይላል ቤተሰቦቿ ሲመጡ ይጨንቀዋል  ሁሌ ስለጦርነት ማዉራት የማይሰለቹ አደረኩ አደረኩ ማለት የሚወዱ ወታደር ነኝ የሚሉ ግን ከውትድርና ይልቅ ለባልቴት የቀረቡ አባቷ ዘርማንዘር መቁጠር የማይሰለቻቸዉ በወጣትነታቸዉ ህዝብ ቆጠራ የሰሩ የሚመስሉት የእከሌ ዘር ነህ እያሉ የሚያደናቁሩ እናቷ ሁሌ የጀርባዉን ቁስል እየነካካች ምታደማዉ አክስቷ ምቾት አይሰጡትም ምን አልባት እሱ ዘመዶቼ የሚላቸዉ አካላት ስለሌሉት ይሆናል አውዳመት ሲመጣ ይጨንቀዋል ጩህ ጩህ ይለዋል ተኝቶ መዋል ነው የሚፈልገው ''እስኪ እንደ ወንድ እንደ አባወራ ሁን በአውዳመቱ ቤቱን የሀዘን ቤት አታስመስለው''ህሊና ናት ''የምትዪው አይገባኝም'' አባወራነትም ወንድነትም የማያውቀዉ ማስተዋል አንድ አንዴ ባልገባን ባልተረዳነው ነገር ላይ ጎበዝ እንድንሆን ይጠብቁናል መንገድ አያሳዪን ወይ አይመሩን ብቻ መጠበቅ ዝም ብሎ የመጣንበትን ያሳለፍነዉን አያውቁም ግን ሲተቹን አይራሩልንም ህሊናም እንደዚህ ናት ማስተዋልን በዝምታው ወቀሰችው እንጂ ከዝምታው ጀርባ ያለዉን ንግግር አላዳመጠችም ንቃ አትፍዘዝ ትላለች እንጂ ምን እንዳፈዘዘዉ ግድ አይሰጣትም እንዳገባሽኝ ፍቺኝ ብሎ ለምኗታል እኔ ስለ ትዳር አላውቅም ዝም ብዬ እኖር ወደነበረበት መልሺኝ ብሏታል እሷ ግን ሁሌም ልፍስፍስ በራስ መተማመን የሌለው መሆኑንና አቅመቢስነቱን እየነገረች ልታበረታው ትሞክራለች አልገባትም እንጂ እየገደለችው ነበር አንድ ቀን ጠዋት እንደ ባል ሁን አለችው ባል እንዴት እንደሆነ አላውቅም አላት ጎዳና ነው ያደከው አባት የለህም እንዳባትህ ወንድ ሁን አለችው ጥሏት ወጣ አባቱ እንደሚያደርገው የጊቢውን በር በሃይል ዘጋው አባቱ የሚጠጣውን ጠጅ ለመጠጣት ጠጅ ቤት ሄደ አዘዘ ጠጣ ደገመ ደገመ ደጋገመ : : ተቀበል ''ከአባቱ እርሻ ላይ የተኛውን በሬ ነካክተዉ ነካክተው አደረጉት አውሬ'' ድገመዉ 🎶🎶🎶🎶 ደገመለት ጠጁን ጨልጦ ወጣ ጮክ እያለ ይዘፍናል ይጮሀል ይሳደባል ዘለቀ ጋሽ ዘለቀ ና አሁን ወንድ ከሆንክ የተረገመ ዘር በለኝ(አባቱ ነው) ኑ ያሰገደች ቤተሰቦች የነፍሰገዳይ ልጅ በሉኝ(እናቱ ናት አሰገደች) ማስተዋል ከዘለቀና ከአሰገደች ቢወለድም ሁለቱም በራሳቸው አለም ነበር የሚኖሩት እሱን እረስተውት ነበር ዘለቀ መስከር የማይሰለቸው ከስካሩና ከአፉ የሚወጣው ቃል እኩል የሚሸት ነበር ቤቱን ሚስቱን ልጁን የረሳ እየሰከረ ሚስትና ልጆቹን የሚደበድብ ነበር  አሰገደችም ከዱላ ብዛትና ከችግር የተነሳ የደቀቀች ከምትበላበት የማትበላበት ቀን የሚበልጥ ምስኪን ነበረች ግን ምላሷ እረጅም ነበር በሶቷን የምትወጣው ጎረቤቶቿን በመስደብ ነበር ማስተዋል ከትምህርት ሲመለስ ሁሌም የሚጠብቀዉ እናቱ ከጎረቤት ጋር ስትሰዳደብ ወይም ስትደባደብ ነው ለነገ አትልም ትሰድባቸዋለች አይራሩላትም ይመቷታል ቀን እነሱ ማታ ባሏ ይፈራረቁባታል ማስተዋል በዚ የተነሳ ይገለላል ይሰደባል   ከማንም ጋር አይገጥምም ብቻዉን ተወለደ ብቻዉን አደገ ብቻዉን ኖረ ቤተሰቦቹ እያሉም ብቻዉን ነበር ህሊና መታም ብቻዉን ነበር አንድ አንድ ግዜ በሰዉ መከበብ ከብቸኝነት አያስጥልም ዋናው ብቸኝነት እንደውም ያለው ሰው መሀል ነው ሰው መሀል ሆኖ ሰው ማጣትን የመሠለ ህመም የለም ማስተዋል እናቱ የሞተችዉ አይኑ እያየ ነው ልጅ ነበር ምሽት ላይ እራት እየበላ አባቱ ከሩቅ የሰፈሩን ሰው ሁሉ እየተሳደበ መጣ የጊቢዉን  በር ወርዉሮ ወደ ቤት ገባ ሰክሯል አሰገደች  እያፈጠጠች ታየዋለች ወደኔ መጣና አንተ የተረገመ ዘር ልጅ እንደ አንበጣ የኔን ላብ ትበላለህ አለኝና እንጀራዉን በእግሩ ከእጄ ላይ ጠለዘው እናቴ ወገቧን ይዛ አፈር ከሚበላው ልጅህ ቢበላው አይሻልም እህሉን የምትደፋው አለችው አትመልሺልኝ ይሄ አንበጣማ የኛ ዘር አይደለም ብሎ ሊያንቃት ሲል ማስተዋል መሀል ገባና ባልጠነከረ እጆቹ የአባቱን እጆች ለመያዝ ሞከረ (ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ) ዘለቀ አይኑ ፈጠጠ ትንሹ ማስተዋልን በደና ጥፊ ሽዉ አደረገበት ወደ ጎን ወደቀ ማስተዋል አሰገደች ልጄን ተወው አትምታው እያለች ፊቱ መጣች የለመደውን የለመደችውን ጥፊ ሰጣት እሷም ሰነዘረች ዘለቀ አጉረጠረጠ ጭራሽ እጅሽን እኔ ላይ አነሳሽ አነቃት ታገለችው ታገላት ወደቁ ላዪዋ ላይ ተቀምጦ አጣደፋት መጮህ አልፈለገችም ብትጮህም የሚደርስላት የለም ዘለቀ እየደበደባት ስትታገለው አሰገደች ቡና ወቅጣ የጣለችዉን ዘነዘና አነሳና አናቷን መታት አልታገለችዉም አይኗን ገርበብ አድርጋ ዝም አለች ዘለቀ ተፍቶባት ወጣ ማስተዋል እየተጎተተ ወደእናቱ ተጠጋ አልጮኸም አላለቀሰም ዝም አለ ዝም ብቻ : : :ህይወት ላይ ምንም ይፈጠር ምን ህይወት ትቀጥላለች አሰገደች ተቀበረች ዘለቀም ጠፋ ማስተዋል ብቻዉን ዝም እንዳለ አደገ ተመረቀ ስራ ያዘ ሳያዉቅ ሳይረዳ በሆነ ግፊት ትዳር ዉስጥ ገባ የአቅሙን ዛሬን ለመኖር ሞከረ ትላንትናዉ ግን አላኖር አለው መዉጣት ፈለገ የሚረዳዉ አጣ ህሊና እንደ አባትህ ወንድ ሁን አለችዉ የማታዉቀዉን ካርድ መዘዘች

Repost from N/a
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ 🔞🔞ከ18 አመት በላይ ለሆናቹ ONLINE ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ ?

😋የጠበሳ ዘዴዎች ለወንድም ለሴትም 👌🤦‍♀ሴቶች ደፍረዉ የማይናገሩት ግን ከወንዶች🤷‍♂ የሚጠብቋቸዉ 7 ነገሮች❤️❤️ ⬜️⬜️OPEN⬜️⬜️
😋የጠበሳ ዘዴዎች ለወንድም ለሴትም 👌🤦‍♀ሴቶች ደፍረዉ የማይናገሩት ግን ከወንዶች🤷‍♂ የሚጠብቋቸዉ 7 ነገሮች❤️❤️ ⬜️⬜️OPEN⬜️⬜️

የትኛውን ነሽ?? በአንድ ወቅት አንዲት ሴት ልጅ ህይወቷ የተመሰቃቀለ እንደሆነ እና አንዱን ችግር ስትፈታ ሌላ ችግር እንደሚገጥማት፤ መኖር እንደከበዳታ እና ከዚህ በላይ ችግሮቿን መቋቋም እንደማትችል አቤቱታዋን ለአባቷ አቀረበች፡፡ _ አባቷ የምግብ ሰራተኛ ነው፤ እናም ወደ ማብሰያ ክፍል ይዟት ሄደ፡፡ ሶስት ድስቶችን ውሃ ሞልቶ እሳት ላይ ጣዳቸው፡፡ ____ በድስቶቹ ውስጥ ያለው ውሃ መፍላት ሲጀምር  በአንዱ ድስት ውስጥ ድንች፤ በሌላኛው ውስጥ እንቁላል፤ በሶስተኛው ውስጥ ደሞ ቡና ጨመረባቸው እና ከደነው፡፡ እናም ምንም ሳይናገር መጠበቅ ጀመረ፡፡ ልጁ መነጫነጭና ትዕግስት በጎደለው መልኩ ምን ሊያረግ እንደሆነ ለማየት መጠበቅ ጀመረች፡፡ ____ ከ20 ደቂቃ በኀላ እሳቱን አጥፍቶ ድንቹን፣ እንቁላሉን አውጥቶ በአንድ ሰሃን አስቀመጠ፡፡ ቡናውን በሲኒ ቀድቶ አስቀመጠ፡፡ ____ "ልጄ አሁን ምን ይታይሻል? በማለት ጠየቃት፡፡ ልጅ "በቁጣ ስሜት ሁና ድንች፣ እንቁላል፣ ቡና" አለች፡፡ ____ "በደንብ ተመልከች፤ ድንቹን ንኪው" አላት፡፡ እንዳላት አድርጋ ድንቹ ጥንካሬውን እንዳጣ ተገነዘበች፡፡ ____ "እንቁላሉንም ስበሪው" አላት፡፡ ሰበረችው ነገር ግን አስኳሉ ሌላ ጠንካራ እና የሚያቃጥል አካል ሰርቷል፡፡ ____ በስተመጨረሻ ከቡናው ፉት እንድትል አዘዛት፡፡ እሷም ቀምሳ ደስ የሚለው ጣዕሙ የፊቷን ፈገግታ ሲቀይረው ታወቃት፡፡ ____ 👉"አባቴ ይህ ምንድን ነው?" አለች፡፡ አባት ማብራራት ጀመረ፡፡ "ድንቹ፣ እንቁላሉ እንዱሁም የቡናው ዱቄት ሁሉም እኩል የፈላ ውሃ ውስጥ ነው የገቡት፡፡ ነገር ግን ሁሉም ለፈላው ውሃ የሰጡት ምላሽ የተለያየ ነበር፡፡ 👉 ድንቹ በፊት ጠንካራ ነበር፤ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ጥንካሬውን አጥቶ ልፍስፍስ ሆነ፡፡ __ 👉እንቁላሉ በፊት በቀላሉ ከተሰበረ ሜዳ ላይ የሚፈስ ልፍስፍስ አስኳል ነበር፡፡ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ውስጡን አጠንክሮ መጣ፡፡ ____ 👉ከሁሉም የሚገርመው ግን የቡና ዱቄቱ ነው፡፡ በፈላ ውሃ ሲፈተን እራሱ ውሃውን ወደ ጣፋጭን መልካም ጠረን ቀይሮ አዲስ ነገር ፈጠረ፡፡ ____ ✍አንቺ የትኛው ነሽ?" ችግር ሲገጥማችሁ የእናንተ ምላሽ ምንድን ነው? እንደ ድንቹ መልፈስፈስ? ወይስ እንደ እንቁላሉ ውስጥን ማጠንከር? አልያም ችግሩን ለአዲስ ነገር መፍጠሪያ መጠቀም?" ____ ✍በህይወት ውስጥ ነገሮች በአካባቢያችን  ይከናወናሉ፤ ነገሮች በእኛ ላይ ይደርሳሉ፤ ነገር ግን ትልቁና ወሳኙ በእኛ ውስጥ የሚከናወነው ነገር ነው!" የትኛው ነህ? ነሽ?? አስተማሪ ታሪክ ነውና ለወዳጅዎ ያጋሩ ለሃሳብ አስተያየት @umbeya inbox me ✍በኃይሉ ነኝ እወዳችኋለው

DSTV ቤት መሄድ ቀረረረረረ የፈለጉትን ጨዋታ በ LIVE STREAM የሚያሳይ ቻናል ተከፈተ 👇 https://t.me/addlist/kap8FWzsuG84YTE0 Add your channel @jowaver
+1
DSTV ቤት መሄድ ቀረረረረረ የፈለጉትን ጨዋታ በ LIVE STREAM የሚያሳይ ቻናል ተከፈተ 👇 https://t.me/addlist/kap8FWzsuG84YTE0 Add your channel @jowaver

😋የጠበሳ ዘዴዎች ለወንድም ለሴትም 👌🤦‍♀ሴቶች ደፍረዉ የማይናገሩት ግን ከወንዶች🤷‍♂ የሚጠብቋቸዉ 7 ነገሮች❤️❤️ ⬜️⬜️OPEN⬜️⬜️
😋የጠበሳ ዘዴዎች ለወንድም ለሴትም 👌🤦‍♀ሴቶች ደፍረዉ የማይናገሩት ግን ከወንዶች🤷‍♂ የሚጠብቋቸዉ 7 ነገሮች❤️❤️ ⬜️⬜️OPEN⬜️⬜️

እናቴ መርፌ ውስጥ ክር እንዳስገባላት ጠራችኝ። በዚሁ ቅፅበት የአንድ ሰው ምክር ትዝ አለኝ ፦ «እናትህ መርፌ ውስጥ ክር እንድታስገባላት ከጠየቀችህ ተቀብለህ ወዲያውኑ አታስገባው። ይልቁንም ያረጀችና እድሜዋ የገፋ  እንዳይመስላትና  ቀልቧ እንዳይሰበር አውቀህ ታግለህ ታግለህ አስገባው» ብሎ መክሮኝ ነበር ። እኔም ማስገባቱ  ቀላል እንዳልሆነ እየነገርኳት ጥቂት ደቂቃዎችን ታገልኩ ። በድንገት አንድ ጥፊ ፊቴ ላይ አረፈ 👋 «ድሮውንም እውር ያደረገህ ይሄ ሞባይልና ፌስቡክ ነው»  😡 የመከርከኝ ልጅ ግን ሰምጠህ ሙት፣ ፆታው የማይታወቅ ልጅ ይስጥህ። ✍ታዚ

የተወለዱበትን ወር በመምረጥ ኮከቦን ይመልከቱ Wave👉@fox_wave0
የተወለዱበትን ወር በመምረጥ ኮከቦን ይመልከቱ Wave👉@fox_wave0

🎁🎁 ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል 🎁🎁 የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ! በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ

◇🎬አክሽን ◇📺የጦርነት ◇🎬 የጫካ ◇🍿 የወንጀል እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በለው ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። JOIN 🫴🫴🫴🫴
◇🎬አክሽን ◇📺የጦርነት ◇🎬 የጫካ ◇🍿 የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል።  JOIN 🫴🫴🫴🫴🫴 https://t.me/addlist/Suc84KryyXViYWZk

ሰላም የእኔ እህት! ወንድን ልጅ ለትዳር ከምትመርጭባቸው 5 መስፈርቶች አንዱን ተነጋግረናል። እነሆ ቀጣዩ መስፈርት!  (ፅሁፉ በዛ? በኋላ ከሚገጥምሽ ምሬት አይበዛም አንብቢ!) መስፈርት 2• • • ጆሮ! ጆሮ! ጆሮ ! እስከአሁን ሳይንስንም ግራ ያጋባው የብዙ የአበሻ ወንዶች ከባድ ችግር (በተለይ ካገቡ በኋላ)  ምን መሰለሽ? ሚስታቸውን አለመስማት! በቃ ብዙ ወንዶች ሴቶችን አይሰሙም! በተለይ ሚስቶቻቸው በቁም ነገር ሲያወሩ ጆሯቸውን ያዝ ያደርጋቸዋል። አንድ ሺ ጊዜ የነገርሻቸውን ነገር ለአንድ ሺ አንደኛ ጊዜ ስትደግሚው «መቸ ነግረሽኝ ነው?» ይሉሻል። ካላመንሽ አሁን ባልሽን ፈትኝው። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ያወራሽውን ሶስት ነገር አንሽና እንደገና እንዲደግምልሽ ጠይቂው፤ ወይ ከነጭራሹ ረስቶታል፣ አልያም አጣሞና አጠናግሮ ነው የሚያስታውሰው! ከሶስቱ ሁለት በትክክል የሚመልስ ባል ካለ አሁኑ ስልጣኔን እለቃለሁ( ለካ ስልጣን የለኝም) በመጨረሻ ምን ብሎ ሲያማርር ትሰሚዋለሽ? «ሴቶች ጨቅጫቃ ናቸው!» ወንዶች ሳይቀንሱ ሳይጨምሩ የሚያስታውሱት ሌላ ወንድ ጋር የነበረሽን ግንኙነት ነው። ለምሳሌ አንድ ቀን ተሳስተሽ «የበፊት ፍቅረኛየ በእንትን ጎበዝ ነበር » ብትይ (ለምን እንጨት በመፍለጥ  አይሆንም) ዕድሜ ልኩን የተናገርሽበትን ቶን ፣ፊትሽ ላይ ስትናገሪ የነበረውን ስሜት ቀኑን ሰዓቱን አይረሱም። በተረፈ ስለልጆቻችሁ፣ ስለእድር፣ ስለሚያምሽ ነገር፣ ቤት ውስጥ እየተንጠባጠበ ስላስቸገረሽ ቧንቧ፣ ልጅሽ ፊት ላይ ስለወጣው ጭርት ነገር፣ ስለቤታችሁ እድሳት...ስለማህበራዊ ህይወት ፣ ሰውነሽና ስለግል ስሜትሽ አመለካከትና ፍላጎትሽ ስታወሪ ውለሽ ብታድሪ አፍታ ሳይቆይ ይረሳዋል! ሲጀመር ለመስማት ትእግስት ማጣቱን ስለምታይ እያሳደድሽ ነው የምታወሪው። ብቻሽን የሚያስወራ አብግን ባህሪ ነው። አድማጭ በማጣትሽ  ወደዝምታ ውቅያኖስ፣ ወደብቸኝነትና ያለመፈለግ ስሜት  የሚገፈትርሽ ዓመል።  ማንም ባልሽ አስቤዛ ያሟላል? ቤት በጊዜ ይገባል? እንጅ ያዳምጥሻል? አይልሽም። ቁሳዊ ስኬትሽን ነው የሚመለከተው። ምን ዋጋ አለው በጊዜ ቢገባ ከሶፋወቹ እንደአንዱ ግዑዝ ዕቃ ከሆነ?! ስለመብራት ክፍያ ወር ሙሉ አውርተሽው የተቆረጠ ቀን የቱ? ምኑ? መቸ ስለመብራት ነገርሽኝ?  ስለውሃ እንጅ. . .እያለ ዘራፍ ቢል አትገረሚ! ስለውሃም የነገርሽውን በትክክል አያስታውስም😀 ይሄ ፍጥረት የዛሬ ሰባት አመት ማንችስተር ዩናይትድ  ሲጫወት የጨዋታው 23ኛ ደይቃ ከሰባት ሰከንድ ላይ ስለጠፋው መብራት ከነምክንያቱ የዛሬ አርባ ዓመት ያስታውሳል። ጓኞቹ ጋር ያወራውን "ደርቲ ጆክ" ዘላለም አይረሳም። ችግሩ ከሚስት ጋር ነው፤ ጆሮው ወሬ  እየመረጠ ከውስጥ ቀጭ ብሎ ይዘጋል።የሚፈልገውን ይሰማል የማይፈልገውን እየሰማ አይሰማም። ምክንያቱም ቢሰማም ባይሰማም ምንም እንደማይደርስበት ነው እያየ ያደገው። "ስራ ስደክም እውላለሁ ስንቱን ላስታውስ?" ሲልሽ ሸም ይይዝሻል። እሱ ማድረግ ያለበትን ታደርጊያለሽ። ግን የሚሰማሽ ባዶነት፣ የነፍስ ድካም ቀላል አይደለም። ይሄ ቀልድ ይመስልሻል፣ ግን መራር ማህበራዊ ቀውስ ነው። አንች ባል ላይ ብቻ ያለ ነገር አይደለም። የወንዶች ዓለም የራሱን ድንቁርና የሴቶች ችግር እንዲመስል አድርጎ ለማሳየት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ድራማውን፣ ጭውውቱን፣ የቲቶክና የፌስቡክ ቀልዱን ልብ ብለሽ ተመልከች! ሴቶችን (በተለይ ሚስቶችን) ለትዳር ለቤተሰብ ጉዳይ ደጋግመው በመናገራቸው ጨቅጫቃ፣ ብዙ የሚያወሩ፣ ለትንሽ ለትልቁ ነገር የሚጨነቁ፣ ባላቸውን ካልተቆጣጠርን የሚሉ ወዘተ አድርጎ ነው የሚስላቸው። ወንዶችን ደግሞ አለመስማታቸው፣ ግዴለሽነታቸው ወዘተ የዋህነት፣ክፋት የሌለበት አስቂኝ ተደርጎ እንዲታይ ይሰብካል። ለምሳሌ በስንቱ የሚባለውን ገፀባህሪ ተመልከች. . . በዛ ልክ አስቂኝና ተወዳጅ ያደረገው ምኑ ነው? ድንቁርናው፣ ነገር ቶሎ አለመረዳቱና ግዴለሽነቱ ነው። አለመስማት ወንዶች ላይ ውበት እንዲሆን የሚጥር ዓለም ላይ ነሽ! ይሄ ድንቁርና ስንት ትዳር ባፍጢሙ እንደደፋ ፣ስንት ቤት እንዳፈራረሰና ስንት ልጆችን የሰቆቃ ህይዎት እንዲገፉ እንዳደረገ አይነግሩሽም። ስንት ሴቶች የወንዱን ግዴለሽነት ተቀብለው አባትም እናትም ሁነው በየቤቱ ከአቅማቸው በላይ በሆነ ሸክም ጎብጠው እንደሚኖሩ ጓዳው ይቁጠረው! የማይሰማሽ ባል ከባድ ሸክም ነው። አየሽ ከማግባትሽ በፊት እጅሽን እያሻሸ ዓይኖቹን አይኖችሽ ላይ ተክሎ በፈገግታ ፣ በጥሞና የምታወሪውን ሲያዳምጥሽ የገባው መስሎሽ እንዳትሸወጅ! እንደሴት እያየሽ ነው እንጅ እንደሰው እየሰማሽ ላይሆን ይችላል። ስለዚህ ከማግባትሽ በፊት የሰውየሽን ((((የመስማት አቅም))) በደንብ ፈትኝ! የምትነግሪውን ነገር በትክክል መረዳቱን በተዘዋዋሪ መርምሪ። ሳትጋቡ በፊት «ውይ ረስቸው » ማለት ካበዛ አትሳቂለት ምክንያት አትፍጠሪለት አንችም እዚህ ሰው ጋር ትዳሩን ርሽው! ትዳር ውስጥ ከሆንሽና የባልሽ ቸልተኛነት ካስመረረሽ አትጨቃጨቂ፣ አለመስማቱ «የአንተ ነገር» ተብሎ የሚታለፍ ቀልድ እንዳልሆነ ዋጋ  እንደሚያስከፍለው አሳይው። ቤት የለመደው ግዴለሽነት ነው የስራ ሃላፊነት ላይ ሆኖ ህዝብ የሚያሰቃየው። ከስህተታችን በመማር የሚለው በየዓመቱ! ሁሉም ድርጊት ውጤት (Consequence) አለው። ለረሳው ነገር የሚያጣው ነገር ከሌለ ገና ይረሳሻል። በተለይ ብዙሃኑ የአበሻ ወንድ «ውይ እሱኮ አይሆንለት. . .» እየተባለ በእርሱ ሐላፊነት አለመወጣት እናቱን ሲጠገርር፣ በእህቱ ሲጦር የኖረ ነው! ባልሽን ብቻ ሳይሆን ወንድ ልጅሽንም ማዳመጥ እና መረዳት፣ ለተረዳው ነገር ያለምንም ሰበብ ተገቢውን የቃልም ይሁን የድርጊት ምላሽ መስጠት እንዲችል ከወዲሁ አለማምጅው። ጆሮ አልባ ወንድ በስሜትም በአመለካከትም ድብልብል ነው! ከዚህ ስትገፊው ወደዛ ይንከባለላል ከዛ ሲገፉት ወደዚህ! ለራሱ ተድበልብሎ ሕይወትሽን ድካምና ድብልብል ነው የሚያደርገው! አያ ድብልብሌ ይሄን ፅሁፍ እያነበብክ እንደሆነ እናውቃለን ከራስህ ድብልብል ዓለም ውጣ አዳምጥ!! ተመካከር! ሐላፊነትን ተጋራ! በሚስትህና በልጆችህ ፊት ሞገስ የምታገኘው በዚህ ነው። ለምን ተናገረኝ ብለህ ከእኔ ገፅ እየተንከባለልክ ወደቲክቶክ ሂድ አሉህ ደግሞ! ✍ታዚ

ለምንድን ነው? ለምንድን ነው ሰዎች እንደፈለጉ የሚያደርጉኝ? . . . ለምንድን ነው ክልከለ ማድረግ ላለብኝ ነገር እምቢ ማለት የሚያስቸግረኝ? . . . ለምንድን ነው በቀላሉ በሰዎች ቅጥጥርና ጭቆና ስር ስወድቅ ራሴን የማገኘው? . . . ለምንድን ነው ሰዎች ለሚሰማቸው ስሜት እኔ ሃላፊነትን የምወስደው? . . . ለምንድን ነው?   1.  ሁል ጊዜ በሁሉም ሰው መወደድን መፈለግ በሰዎች መወደድን የሚፈልግ ሰው ማንም ሰው እንዳይቀየመው ስለሚፈልግ ለሁሉም ነገር በመስማማት ሳይወድ በግዱ በሰዎች ቁጥጥር ስር ይኖራል፡፡ ሆኖም፣ ሁል ጊዜ፣ በሁሉም ሰው መወደድ ስማይቻል አንደኛችንን ነጻነታችን ማወጅ ይሻለናል፡፡ 2.  የግንዛቤ ጉድለት የግል የቀይ መስመርን አስመልክቶ የተዛባ አመለካከት ወይም ያልበሰለ ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች፣ ያንን ማድረግ ያቅታቸዋል፡፡ ይህ የተዛባ ዝንባሌ፣ ከአስተዳደግ ወይም አንዳንድ የሃይማኖት አስተምህሮቶችን በተሳሳተ መንገድ ከመገንዘብ ሊመጣ ይችላል፡፡ ማንኛውም ግንኙነት የቀይ መስመር፣ ማለትም የሚፈቀደውና የማይፈቀደው ነገር ሊለይ እንደሚገባው ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ 3.  የዝቅተኛነት ስሜት የበታችነት የሚሰማው ሰው የራሱ የሆነ አመለካከት እና አቋም የመያዝ ችግር ስላለበት ሁል ጊዜ የበላዩ እንደሆኑ በሚያስባቸው ሰዎች ቁጥጥር ስር ራሱን ያገኘዋል፡፡ ከሰዎች ጋር ማንልባት ችሎታ ልንለያይ ብንችልም “በሰውነት” ግን እኩል መሆናችንን መቀበል አስፈላጊ ነው፡፡  4.  አለመግባባትን መፍራት አንዳንድ ሰዎች ምንም አይነት እንደፈጠር ስለማይፈልጉና ስለሚፈሩ፣ ትንሽ ኃይለኛነትን የሚያንጸባርቁ ሰዎች ካጋጠሟቸው ቶሎ ብለው የበታችነቱን ስፍራ በመያዝ ይገዛሉ፡፡ በማንኛውም ግንኙነት ውስጥ አለመግባባት ሊፈጠር እንደሚችል አምኖ በመቀበል ሁኔታውን ለእድገት መጠቀም የግድ ነው፡፡ 5.  ሰዎችን ካለልክ ማመን ሁሉን ሰው እንዲሁ በየዋህነት የማመን ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች ማንም ሰው ይጎዳኛል ብለው ስለማያስቡ ለሁሉ ነገር ተሰማሚዎች ሆነው ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ ሰዎችን ማመን መልካም ሆኖ ሳለ፣ ራሳችንን ከመጠበቅ ጋርና ሁሉን በልክ ከማድረግ ጋር መያዝ ተገቢ ነው፡፡ Credit :- D.r Eyob Mamo ✍Tazi

Repost from N/a
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ 🔞🔞ከ18 አመት በላይ ለሆናቹ ONLINE ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ ?