cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

The Jubair || The ጁበይር

ሀሳብ አስተያየታቹን በ @thejubair ያድርሱኝ ይህ የ The Jubair official የቴሌግራም ገፅ ነው በቻናላችን አጫጫር ዳዕዋዎችን | ፈጣን መረጃዎችን | አጫጭር የቁረዐን አያቶችን| እንዲሁም ሌሎች እጅግ አስተማሪ ነገሮችን በአላህ ፍቃድ ያገኛሉ . ይህን ሁሉ ቻናላችንን Join በማድረግ ብቻ ሀያ ቢስሚላህ 😊 ሹክረን ;)

Show more
Advertising posts
2 643
Subscribers
No data24 hours
+107 days
-1330 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
ከማረሚያ ቤት ያመለጠው ወንጀለኛ ይፈለጋል! 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 በሆለታ ከተማ የመስጂድ ኢማም የነበሩትን ሸህ አህመድ ሙሀመድን በመግደል የ20 ዓመት እስር ፍርድ ተላልፎበት የነበረው አብዱልአዚዝ መሐመድ ጀማል የተሰኘው ወንጀለኛ ከሸገር ማረሚያ ቤት አመለጠ። በሆለታ ከተማ ታላቅ ዓሊምና ኢማም የነበሩት ሼህ አህመድ ሙሀመድ ሚያዝያ 9 ቀን 2014 ዓ.ል ረመዷን ወር ላይ ለማሰገድ ወደ መስጂድ ሲጓዙ በነበረበት ወቅት በሁለት ጥይት ተደብድበው መገደላቸው ይታወሳል። በግዜው በዋነኝነት ግድያውን ያቀናበረው አቶ አብዱልዓዚዝ ሙሀመድ ጀማል የተባለው ግለሰብ በ ሞያሌ በኩል ሊያመልጥ ሲሞክር በዚሁ የፌስቡክ ገጽ ላይ ባደረግኩት ጥሪ በሻሸምኔ ከተማ ላይ በሻሸመኔ ሙስሊም ጀምዓ መያዙ ይታወሳል። በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በግድያ ወንጀሉ ተከሶ በጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ል. በዋለው ችሎት የ20 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት ተላልፎበት ነበር። ሆኖም የእስር ቅጣቱን በሸገር ማረሚያ ቤት እየፈጸመ እያለ በግንቦት 23 ቀን 2016 ከእስር ቤት በመሰወሩ በተገኘበት እንዲያዝ ያለበትን የሚያውቅና ያየ ሰው እንዲጠቁም ጥሪ ተላልፏል። የተፈላጊው ወንጀለኛ ምስል፣የአፋልጉን ጥሪ ደብዳቤና ተያያዠ መረጃዎች ከስር ተያይዟል።
3180Loading...
02
🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ ۖ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا ۖ وَلَا يَغُرَّنَّكُم بِاللَّهِ الْغَرُورُ እናንተ ሰዎች ሆይ! የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት አታታላችሁ፡፡ አታላዩም (ሰይጣን) በአላህ (መታገስ) አያታላችሁ፡፡ إِنَّ الشَّيْطَانَ لَكُمْ عَدُوٌّ فَاتَّخِذُوهُ عَدُوًّا ۚ إِنَّمَا يَدْعُو حِزْبَهُ لِيَكُونُوا مِنْ أَصْحَابِ السَّعِيرِ ሰይጣን ለናንተ ጠላት ነው፡፡ ስለዚህ ጠላት አድርጋችሁ ያዙት፡፡ ተከታዮቹን የሚጠራው ከእሳት ጓዶች እንዲኾኑ ብቻ ነው፡፡ [ሱረቱል ፋጢር : 5-6] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_22 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
3301Loading...
03
(እንቅልፍ) ⭐ከአላህ ተኣምሮችና ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ታላላቅ ፀጋዎች መካከል አንዱ እንቅልፍ ነው 🔸አላህ የሰላምና የጤና እንቅልፍ የሰጠውን ሰው ማንም ሊነፍገው አይችልም 🔹እንዲህ ዓይነቱን እንቅልፍ እርሱ ለነፈገው ሰው ደግሞ ማንም ሊሰጠው አይችልም! በመሆኑም በፈለጉት ሰዓት ተኝተው በፈለጉት ሰዓት መነሳት ትልቅ ምስጋና የሚያስፈልገው የጌታችን አላህ ኒዕማ ነውና ከልብ الحمد لله ማለት ያስፈልገዋል❗ እንቅልፍ ትንሹ ሞት ነውና በዛው እንደተኙ አለመቅረትና ዳግም ተነስቶ አላህን ለመገዛት መብቃትም ሌላው ተጨማሪ ምስጋና የሚያስፈልገው ፀጋ ነው! ለዚህም ነው ሙስሊሞች ልክ ከእንቅልፋቸው ሲነቁ:- (("الحمد لله الذي أحيانا بعد ما أماتنا")) ( ከገደለን በኋላ ዳግም ህያው ያደረገን ጌታ አላህ ይመስገን) የሚሉት 👉 ሆኖም በዲናችን ሁሉም ነገር ገደብና አደብ(ሥርኣት) አለው 🚩️የእንቅልፍ አደብ(ሥርኣት) እንቅልፍ አደቡ ከተጠበቀ ትንሹም በረካ ይሆናል፣ ለጤናም ተስማሚ ከመሆኑ አልፎ የህሊና ሰላምን ይለግሳል✅ 🚩የእንቅልፍ መጠን- እንቅልፍ ሲበዛ ቀልብ ይደርቃል፣ ከመድረቅም አልፎ ይሞታል❎ የሰውነት መወፈርንና መጫጫንንም ያስከትላል! 🚩ለአኼራችን ስንቅ የምንሰንቅበትን ውድ ጊዜያችንንም ያባክናል፣ ግዴለሽነትንና ስልቹነትንም ያስከትላል ⭐ጥሩ እንቅልፍ ማለት:- አንተ መተኛት ስለፈከግክ የምትተኛው ሳይሆን ሰውንነትህ መተኛት ሲያስፈልው የምትተኛው እንቅልፍ ነው✅ ⭐ጥሩ የእንቅልፍ ሰዓት ማለት- ከዒሻ ሰላት በኋላ የሌሊቱ መጀመሪያ ላይ የሚተኛ እንቅልፍ ነው✅ 🔶በቀኑ ክፍለ-ጊዜ የተወሰነ ሰዓት አረፍ ማለት ሱናና ጠቃሚ ሲሆን፣ ለዚህም የተመረጠው ወቅት የቀኑ መሀል ነው ♦ከሱብሂና ከአስር በኋላ መተኛት ተገቢም ጠቃሚም አይደለም❗ 📎ምናልባት ማታ ያልተኛ ሰው ከሱብሂ በኋላ ጸሐይ እስክትወጣ ጠብቆ ከዛ መተኛት ይችላል! በተቻለው ያህል ሱብሂ እንደተሰገደ ላለመተኛት መሞከር ይኖርበታል! 🚩️ በየትኛውም ሰዓት ሲተኙ ውዱዕ ማድረግ ከእንቅልፍ በፊት የሚደረጉ ዚክሮችን ማለት ፣ፊትን ወደ ቂብላ ማዞር፣በቀኝ ጎን ዞሮ መተኛት፣ እንቅልፍ እስኪወስደን ድረስ ዚክርና ቁርኣንን ማብዛት ተገቢና ከሙእሚኖች ባህሪ ነው❗ 🔑እንቅልፍ ጨርሰው ሲነሱም ፊትን በእጆች ጠረግ ጠረግ ማድረግና ከላይ የተጠቀስውን ዚክር ማለት ሱና ሲሆን ፣እንደባነኑ ከፍራሽ ፈጥኖ መነሳት አይመከርም❗ ወላሁ አዕለም ✍ ኡስታዝ አህመድ ኣደም ዙል-ሒጃ 29/1437ዓ.ሂ 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
2961Loading...
04
ያኔ ድሮ ድሮ አባቶቻችን ስልክን አስረው ሲፈልጉ ብቻ ነበር የሚጠቀሙት..... ዛሬ ግን እሱ በተራው እኛን አስሮ እየተጠቀመብን ይገኛል። አሏህ ሆይ! ከሸሩ ጠብቀን። ያ ረብ ከእዝነትህ አታርቀን! 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
2563Loading...
05
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማንነት መፍትሄው አንድና አንድ ብቻ ነው፦ የምክክር ኮሚሽኑ ከወረዳ እስከ ፌዴራል ድረስ ተሳታፊን የሚለይበትን መስፈርት ይቀይር፣ ህዝበ ሙስሊሙ ቁጥሩን የሚመጥን የተሳታፊ ውክልና ኮታ ይሰጠው። ይህ ካልሆነ ታዋቂ ሰዎቻችንም ቢሳተፉ ዋጋ የለውም። ምክንያቱም ሃሳባቸው ውድቅ ስሚደረግ። ይህን ጉዳይ መጅሊስ በደንብ ያስብበትና ሚዲያዎችን በሙሉ ጠርቶ መግለጫ ያውጣ። ቀነ ገደብ ያስቀምጥና ኮሚሸኑ እስከዛ ቀን ድረስ አሠራሩን ህዝበ ሙስሊሙን ባማከለ መልኩ ካላስተካከለ፤ ከዚህ የምክክር መድረክ ራሱን ማግለሉን ያሳውቅ።         ጊዜ የለንም! ምንም እንኳ ሊያራዝሙለት ቢችሉኝ 3ኛ አመቱ ላይ ስለሆነ እየተጣደፈ ነው። እንፍጠን! 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
2441Loading...
06
ሁሉም ሰው ሃሳቡን ከዚህ የምክክር መድረክ ላይ ማንሳት የለበትም ሃሳብ እና ሴራቸው እኛ ከምናስበው በላይ ነው ያንን ጨቁዋኝ ዘመን ሙስሊሞች ላይ መመለስ ነው እና ሀሳባቸው ይሄ የፖለቲካ ጉዳይ እንዳይመስላችሁ ሙስሊሙን ከሁሉም አይነት ጉዳዮች ማግለል ነው እና ሁላችንም በተቻለን አቅም ለሰዎች ማሳወቅ አለብን ቢያንስ ለ 5 ሰው ያጋሩ #ኢትዮዳዕዋ #ሃገራዊምክክር #ኢትዮሙስሊም #ኢትዮጵያውያንሙስሊሞች #መጅሊስ #ኢስላም
2653Loading...
07
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 يَوْمَئِذٍ تُعْرَضُونَ لَا تَخْفَىٰ مِنكُمْ خَافِيَةٌ በዚያ ቀን ከእናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲኾኑ ትቅቀረባላችሁ፡፡ فَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِيَمِينِهِ فَيَقُولُ هَاؤُمُ اقْرَءُوا كِتَابِيَهْ መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ) «እንኩ፤ መጽሐፌን አንብቡ» ይላል፡፡ إِنِّي ظَنَنتُ أَنِّي مُلَاقٍ حِسَابِيَهْ «እኔ ምርመራየን የምገናኝ መኾኔን አረጋገጥኩ፤» (ተዘጋጀሁም ይላል)፡፡ فَهُوَ فِي عِيشَةٍ رَّاضِيَةٍ እርሱም በተወደደች ኑሮ ውሰጥ ይኾናል፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፡፡ قُطُوفُهَا دَانِيَةٌ ፍሬዎችዋ ቅርቦች የኾኑ፡፡ •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_321 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
2723Loading...
08
በዚህ አመት ሐጅ ላልተሳካለት ~ ኢብኑ ረጀብ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:– ★ በዐረፋ መቆም ላልቻለ ከአላህ ወሰኖች ዘንድ ይቁም። ★ በሙዝደሊፋ ማደር ላልቻለ ወደ አላህ ያቃርበው ዘንድ ለትእዛዙ ይደር። ★ ሀድዩን ሚና ላይ ማረድ ያልቻለ ከምኞቱ ይደርስ ዘንድ ስሜቱን ይረድ። ★እሩቅ በመሆኑ ቤቱ (በይተል ሐራም) መድረስ ያልቻለ የቤቱን ባለቤት ያስብ። ወደሱ ከደም ጋኑ የቀረበ ነውና።" (ለጧኢፉል መዓሪፍ: 633) 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
3201Loading...
09
🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፡፡ ጸጥም በሉ፡፡ ይታዘንላችኋልና፡፡ وَاذْكُر رَّبَّكَ فِي نَفْسِكَ تَضَرُّعًا وَخِيفَةً وَدُونَ الْجَهْرِ مِنَ الْقَوْلِ بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ الْغَافِلِينَ ጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል በጧትም በማታም አውሳው፡፡ ከዘንጊዎቹም አትኹን፡፡ إِنَّ الَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيُسَبِّحُونَهُ وَلَهُ يَسْجُدُونَ ۩ እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት (መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፡፡ ያወድሱታልም፡፡ ለእርሱም ብቻ ይሰግዳሉ፡፡ [ሱረቱል አዕራፍ : 204-206] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_320 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
3263Loading...
10
🤲 ኢላሂ ! በውዴታቸው ቅን  የሆኑ የዲን ወንድሞችን ለግሰን! ዑመር ኢብኑል ኸጣብ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ብለዋል፡- "ከእስልምና ቀጥሎ ከጥሩ ወንድም በላይ ምንም አይነት በላጭ ነገር አንድ ሰው አልተሰጠም።" ቁወቱ አል–ቁሉብ - (178/2) ኢማም አሽ– ሻፊኢይ - አላህ ይዘንላቸውና፡- “የዲን ወንድሞች ጋር መጓዳኘት የሚያክል ደስታ የለም፣ ወንድሞቻችን መለያየት የሚያክል ሐዘን የለም። ሹዐቡል ኢማን - (504/6)) 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
3162Loading...
11
🔴 ብዙዎቻችን በትክክል እየፈፀምነው ሚመስለን የሰላተል ጀናዛ አሰጋገድ ሳይረፍድ እናስተካክል ወዳጆቼ ሳይረፍድ !! እንደው ከአንድ አመት በኋላ ወደ ቲክቶክ በዚህ ቪዲዮ ጎራ ብዬ ነበርና...አልሐምዱሊላህ የቲክቶክ ቤተሰቦቼ አላሳፈሩኝም እስካሁን ከ28 ሺህ ሰው በላይ አይቶታል . ለ1200 ወዳጆቻቸውም ቪድዮውን ሼር በማድረግ ኸይር ነው ያሉትን ነገር ልከውላቸዋል እንግዲ የቴሌግራም ቤተሰቦቼም አያሳፍሩኝም በማለት ወደ እናንተ ብቅ ብያለውና እንደው አታሳፍሩኝስ 😊 ለወዳጅ ዘመዶቻቹ ሼር እያደረጋቹ ባረከላሁ ፊኩም ! እስኪ የቲክቶክ ቤተሰቦችህን እንዘይራቸው ካላቹኝ ይሄው ሊንኩ 👇 https://www.tiktok.com/@thejubair00?_t=8mpWXGPYNza&_r=1 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
3775Loading...
12
እንደው ከአንድ አመት በኋላ ወደ ቲክቶክ ጎራ ብዬ ነበር አልሐምዱሊላህ የቲክቶክ ቤተሰቦቼም አላሳፈሩኝም እስካሁን ከ28 ሺህ ሰው በላይ አይቶታል አልሐምዱሊላህ ለ1200 የሚሆኑ ወዳጆቻቸውም ቪድዮውን ልከውላቸዋል እንግዲ የቴሌግራም ቤተሰቦቼም አያሳፍሩኝም በማለት ወደ እናንተ ብቅ ብያለውና እንደው አታሳፍሩኝስ 😊 ለወዳጅ ዘመዶቻቹ ሼር እያደረጋቹ ባረከላሁ ፊኩም ! 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
10Loading...
13
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 الرَّحْمَٰنُ አል-ረሕማን፤ عَلَّمَ الْقُرْآنَ ቁርኣንን አስተማረ፡፡ خَلَقَ الْإِنسَانَ ሰውን ፈጠረ፡፡ عَلَّمَهُ الْبَيَانَ መናገርን አስተማረው፡፡ الشَّمْسُ وَالْقَمَرُ بِحُسْبَانٍ ፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፡፡ وَالنَّجْمُ وَالشَّجَرُ يَسْجُدَانِ ሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡ وَالسَّمَاءَ رَفَعَهَا وَوَضَعَ الْمِيزَانَ ሰማይንም አጓናት፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡ [ሱረቱ ረህማን : 1-7] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_319 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
3411Loading...
14
🛑👉የደስታ ቁልፍ! ~ የሰው ልጆች በዱንያም በአኺራም የተሳካ፣ አስደሳች እና ያማረ ሕይወት መኖርን ይመኛሉ።  ደስታና ስኬትን ለማግኘትም ገንዘባቸውን፣ ጊዜያቸውንና የህይወታቸውን ውድ ነገር ሳይቀር ይገብራሉ።  ነገር ግን ብዙውን ጊዜ የፈለጉትን ደስታ አያገኙም፤ ቢያገኙም ጊዜያዊ ነው። ምክንያቱም ዘላለማዊ ደስታ በደስታም ሆነ በችግር ውስጥ ያለ ደስታ ሲሆን ይህን የሚያገኘው ደግሞ ሙእሚን ብቻ ነው። ይህን አስመልክቶ ሙስሊምና ሌሎችም በዘገቡት ከሱሐይብ በተወራዉ ሐዲስ ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ይላሉ፦ " عَجَبًا لأمرِ المؤمنِ إِنَّ أمْرَه كُلَّهُ لهُ خَيرٌ وليسَ ذلكَ لأحَدٍ إلا للمُؤْمنِ إِنْ أصَابتهُ سَرَّاءُ شَكَرَ فكانتْ خَيرًا لهُ وإنْ أصَابتهُ ضَرَّاءُ صَبرَ فكانتْ خَيرًا لهُ ". رواهُ مُسْلِمٌ. "የሙዕሚን ነገር ይገርማል፤ የሙዕሚን ሁሉ ነገሩ መልካም ነው ይህ ለማንም አይሆንም  ለሙዕሚን እንጂ። መልካም ነገር ከገጠመው አላህን ያመሰግናል በዚህም መልካም ይሆንለታል። አስቸጋሪ ነገር ቢገጥመው ይታገሳል ይህም መልካም ይሆንለታል።" የዱንያ አዙሪት ከነዚህ ሁለት ነገሮች የማይወጣ መሆኑ የታወቀ ነው! " ተድላና ችግር" ሁለቱም ለሙእሚን መልካም ከሆኑ ታዲያ የሰው ልጆች ደስታና ስኬትን ለማግኘት ሙዕሚን ከመሆን ሌላ ምን አማራጭ አላቸው? 🛑👉ጥያቄው  ደስታን እንዴት ማግኘት እንችላለን? አላህ ዐዘ ወጀል በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፡ قال الله تعالى: (مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِنْ ذَكَرٍ أَوْ أُنْثَى وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُمْ بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ)، النحل ٩٧ "ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን።" (ነህል :97) ﴿ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ طُوبَى لَهُمْ وَحُسْنُ مَآبٍ ﴾ [الرعد: 29]. "እነዚያ ያመኑትና መልካም ሥራዎችን የሠሩት ለእነሱ ደግ ኑሮ መልካም መመለሻም አላቸው።" (ረዕድ :29) 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
4205Loading...
15
🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 إِنَّ السَّاعَةَ لَآتِيَةٌ لَّا رَيْبَ فِيهَا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት፡፡ በእርሷ ጥርጥር የለም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም፡፡ وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡ اللَّهُ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ اللَّيْلَ لِتَسْكُنُوا فِيهِ وَالنَّهَارَ مُبْصِرًا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى النَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَشْكُرُونَ አላህ ያ ለእናንተ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት (ጨለማ) ቀንንም (ልትሠሩበት) የሚያሳይ ያደረገላችሁ ነው፡፡ አላህ በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነውና፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያመሰግኑም፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ لَّا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ (ከእምነት) ወዴት ትመለሳላችሁ፡፡ •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_318 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
3685Loading...
16
ፈገግታ ~ "በወንድምህ ፊት ፈገግ ማለትህ ምፅዋት ነው" ''ፈገግታ የህይወት ማጣፈጫ ቅመም ነው። ''የፈገግተኛ ሰዎች አቃ ፈገግተኛ ካልሆኑት በብዙ አጥፍ የተሻለ ይሸጣል። ''ፈገግታኞች የተጋጋሉ የቁጣ እሳቶችን ያበርዳሉ። "ፈገግተኛ ሰው አብሮ ሲኖር ሰዎች ይደሰቱበታል፣ሲጠፋ ይናፍቁታል። "ፈገግተኛን ሰው ሰዎች ቶሎ ይቀርቡታል። ስለዚህ ፈገግታን እንደ ልብስ ገዝተህም ቢሆን ተላበሰው! 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
3661Loading...
17
ጌታህ የምተወደውን ነገር ሲከለክልህ የተከለከልክበትን ምክንያት አታውቅም #ሲተካህ ቢሆን እንጂ *በማታውቀው ነገር ላይ ብዙ አትበል ለማለት ነው። 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
3752Loading...
18
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 يَا أَبَتِ لَا تَعْبُدِ الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ كَانَ لِلرَّحْمَٰنِ عَصِيًّا «አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አትግገዛ፡፡ ሰይጣን ለአልረሕማን አመጸኛ ነውና፡፡ يَا أَبَتِ إِنِّي أَخَافُ أَن يَمَسَّكَ عَذَابٌ مِّنَ الرَّحْمَٰنِ فَتَكُونَ لِلشَّيْطَانِ وَلِيًّا «አባቴ ሆይ! እኔ ከአልረሕማን ቅጣት ሊያገኝህ ለሰይጣንም ጓደኛ ልትኾን እፈራለሁ፡፡» قَالَ أَرَاغِبٌ أَنتَ عَنْ آلِهَتِي يَا إِبْرَاهِيمُ ۖ لَئِن لَّمْ تَنتَهِ لَأَرْجُمَنَّكَ ۖ وَاهْجُرْنِي مَلِيًّا (አባቱም) «ኢብራሂም ሆይ! አንተ አምላኮቼን ትተህ የምትዞር ነህን ባትከለከል በእርግጥ እወግርሃለሁ፡፡ ረዥም ጊዜንም ተወኝ» አለ፡፡ قَالَ سَلَامٌ عَلَيْكَ ۖ سَأَسْتَغْفِرُ لَكَ رَبِّي ۖ إِنَّهُ كَانَ بِي حَفِيًّا «ደህና ኹን፡፡ ወደፊት ከጌታዬ ምሕረትን እለምንልሃለሁ፡፡ እርሱ ለኔ በጣም ርኅሩኅ ነውና» አለ፡፡ [ ሱረቱል መርየም : 44-47] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_317 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
4164Loading...
19
🔴  ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 قُل لَّن يُصِيبَنَا إِلَّا مَا كَتَبَ اللَّهُ لَنَا هُوَ مَوْلَانَا ۚ وَعَلَى اللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ الْمُؤْمِنُونَ «አላህ ለኛ የጻፈልን (ጥቅም) እንጂ ሌላ አይነካንም፡፡ እርሱ ረዳታችን ነው፡፡ በአላህ ላይም ምእመናን ይመኩ» በላቸው፡፡ [ሱረቱ ተውባ - 51] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_316 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ       ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽታችንን 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
4061Loading...
20
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 أَإِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَامًا أَإِنَّا لَمَدِينُونَ «በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?» (የሚል)፡፡ قَالَ هَلْ أَنتُم مُّطَّلِعُونَ እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡ فَاطَّلَعَ فَرَآهُ فِي سَوَاءِ الْجَحِيمِ ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡ قَالَ تَاللَّهِ إِن كِدتَّ لَتُرْدِينِ ይላል «በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡ وَلَوْلَا نِعْمَةُ رَبِّي لَكُنتُ مِنَ الْمُحْضَرِينَ «የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡» أَفَمَا نَحْنُ بِمَيِّتِينَ (የገነት ሰዎች ይላሉ) «እኛ የምንሞት አይደለንምን? إِلَّا مَوْتَتَنَا الْأُولَىٰ وَمَا نَحْنُ بِمُعَذَّبِينَ «የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?» (ይላሉ)፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ لِمِثْلِ هَٰذَا فَلْيَعْمَلِ الْعَامِلُونَ ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡ [ሱረቱ ሷፋት 53-61] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_315 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ       ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
4965Loading...
21
🔖ቤት ውስጥ መሆን ለሴት ልጅ ራሱን የቻለ ዒባደህ ነው። ተገዳ ወይም አማራጭ አጥታ ካልሆነ በስተቀር ሙስሊም ሴት ወጣ-ገባ ማለት ልታበዛ አይገባም። ከደጋግ ቀደምት ሴቶች መካከል አንዷ የሆኑት ፋጢመህ ቢንቱልዓጣር በህይወታቸው 3 ጊዜ ብቻ እንጂ ከቤት ወጥተው አያውቁም ነበር፤ ⓵- ያገቡ ቀን፣ ⓶- ሐጅ ያደረጉ ቀንና ⓷- የሞቱ ቀን ብቻ!:: 👉አንቺስ እህቴ! በቀን ስንቴ ነው የምትወጪው!? 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
4274Loading...
22
🔴  ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_314 يَوْمَ تَرَى الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ يَسْعَىٰ نُورُهُم بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَبِأَيْمَانِهِم بُشْرَاكُمُ الْيَوْمَ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ምእመናንንና ምእምናትን በስተፊቶቻቸው፣ በቀኞቻቸውም ብርሃናቸው የሚሮጥ ሲኾን በምታያቸው ቀን (ምንዳ አልላቸው)፡፡ ዛሬ ብስራታችሁ በውስጦቻቸው ዘውታሪዎች ስትኾኑ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸው ገነቶች ናቸው (ይባላሉ)፡፡ ይህ እርሱ ታላቁ ዕድል ነው፡፡ [አል-ሐዲድ - 12] •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ       ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
4394Loading...
23
~አብዝተው ኢስቲغፋር ማድረግ . የገራላቸው ሰዎች አላህ ከቅጣቱ  ሊጠብቃቸው የፈለጋቸው ሰዎች ናቸው። : وَمَا كَانَ اللَّهُ مُعَذِّبَهُمْ وَهُمْ يَسْتَغْفِرُونَ «መሓርታን እየጠየቁት አላህ የሚቀጣቸው አይደለም።» ኢስቲግፋር እያበዛን ሀባይቢ ! 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
4012Loading...
24
🔖እህቴ ሆይ !#በሶስት ነገሮች እራስሽን አጠንክረሽ ትውልድ ለመገንባት አቋም ያዢ! ⓵• አሏህን በመፍራት ⓶• በእውቀት ⓷• በአኽላቅ 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
4482Loading...
25
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 هَلْ أَتَىٰ عَلَى الْإِنسَانِ حِينٌ مِّنَ الدَّهْرِ لَمْ يَكُن شَيْئًا مَّذْكُورًا በሰው ላይ የሚታወስ ነገር ሳይኾን ከዘመናት የተወሰነ ጊዜ በእርግጥ አልፎበታል፡፡ إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا እኛ ሰውን (በሕግ ግዳጅ) የምንሞከረው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ ሰሚ ተመልካችም አደረግነው፡፡ [ሱረቱል ኢንሳን 1-2] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_313 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ       ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
5234Loading...
26
~በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ይሉሃል እንዲህ ነው! ( ربي إني لما أنزلت إلي من خير فقير) «ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ»። •እንደ ኢብኑ ዐሹር ተፍሲር፤ከላይ የተጠቀሰችው የቁርአን አንቀፅ ሶስት መልእክትን ይዛለች።እነሱም ምስጋና ውዳሴ እና ዱዓእ ናቸው።እንደሚታወቀው አላህን አመስግኖ እና አወድሶ ዱዓእ ማድረግ ፈጣንና ሰፊ ተቀባይነት አለው።ለዚህም አላህ ለ ነብዩሏህ ሙሳ አስደሳችና ፈጣን ምላሽ ሰጥቶታል። ① ሚስት የለውም ነበር። ሚስት አገኘ። ② መጠለያ ቤት አልነበረውም ከደጉ ሰውዬ ቤት ተጠጋ። ③ ስራ የለውም ነበር ስራ አገኘ። ብዙዎች ግን ይችን አንቀፅ ሲያስታውሱ ሚስትን ብቻ ያስታውሳሉ። እውነታው ግን ነብዩሏህ ሙሳ ከሚስት በተጨማሪ ቤትና ስራም አትርፎበታል። 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
7139Loading...
27
ስራህ ይመስክር! ~ አንዴ ለአንድ መስጅድ ማሰባሰቢያ ተደርጎ ሰዎች ስለሰጡት ገንዘብ ሌሎች እከሌ 50,000ብር ሠጠ፣ እከሌ ደግሞ  80,000 ብር……… እያሉ እያወሩ ከመሃላቸው አንዱ፦ “እኛምኮ ሪያዕ(እዩልኝ) እንዳይሆብን ነው እንጂ 2,900 ብር ሰጥተናል” በማለት ተናገረ። የሰራሃውን ስራ ለማሳየት ብዙ አትንገላታ፤ ዝም ብለህ ህይወት ያለው ተግባርን ፈፅም። ያን ጊዜ ስራህ ራሱ ጮሆ ይናገራልና ለሱ እድሉን ስጠው። የስራህን ቀላልነት በወሬህ ክብደት ለመሙላት ስትሯሯጥ በግልፅ መታወቁን ትዘነጋለህ። መልካም ምሽት 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
4201Loading...
28
🔴  ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُلْهِكُمْ أَمْوَالُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ عَن ذِكْرِ اللَّهِ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ አላህን ከማስታወስ አያታሉዋችሁ፡፡ ይህንንም የሚሠሩ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው፡፡ وَأَنفِقُوا مِن مَّا رَزَقْنَاكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ فَيَقُولَ رَبِّ لَوْلَا أَخَّرْتَنِي إِلَىٰ أَجَلٍ قَرِيبٍ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُن مِّنَ الصَّالِحِينَ አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጐቹም ሰዎች እንድኾን ወደ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ፡፡ وَلَن يُؤَخِّرَ اللَّهُ نَفْسًا إِذَا جَاءَ أَجَلُهَا ۚ وَاللَّهُ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ ማንኛይቱም ነፍስ የሞት ጊዜዋ በመጣበት ጊዜ አላህ በፍጹም አያቆያትም፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ [ሱረቱል ሙናፊቁን 9-11] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_312 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ       ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
5297Loading...
29
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 أَمَّن يُجِيبُ الْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ السُّوءَ وَيَجْعَلُكُمْ خُلَفَاءَ الْأَرْضِ ۗ أَإِلَٰهٌ مَّعَ اللَّهِ ۚ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ ወይም ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደረጋችሁ፤ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን ጥቂትንም አትገሠጹም፡፡ [ሱረቱ ነምል 62] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_311 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ       ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
4053Loading...
30
🔴 ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን       እንጀምር አላህ ፅናቱን ይስጠን ♡ حَتَّىٰ إِذَا اسْتَيْأَسَ الرُّسُلُ وَظَنُّوا أَنَّهُمْ قَدْ كُذِبُوا جَاءَهُمْ نَصْرُنَا فَنُجِّيَ مَن نَّشَاءُ ۖ وَلَا يُرَدُّ بَأْسُنَا عَنِ الْقَوْمِ الْمُجْرِمِينَ መልክተኞቹም ተስፋ በቆረጡና እነርሱ በእርግጥ የተዋሹ መኾናቸውን በተጠራጠሩ ጊዜ እርዳታችን መጣላቸው፡፡ (እኛ) የምንሻውም ሰው እንዲድን ተደረገ፡፡ ቅጣታችንም ከአጋሪዎቹ ሕዝቦች ላይ አይመለስም፡፡ ሱረቱ ዩሱፍ ቁጥር 110 •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_310 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ       ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
4406Loading...
31
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 وَذَكِّرْ فَإِنَّ الذِّكْرَىٰ تَنفَعُ الْمُؤْمِنِينَ ገሥጽም፤ ግሣጼ ምእመናንን ትጠቅማለችና፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ مَا أُرِيدُ مِنْهُم مِّن رِّزْقٍ وَمَا أُرِيدُ أَن يُطْعِمُونِ ከነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም፡፡ ሊመግቡኝም አልሻም፡፡ إِنَّ اللَّهَ هُوَ الرَّزَّاقُ ذُو الْقُوَّةِ الْمَتِينُ አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ኀይል ባለቤት ነው፡፡ [ሱረቱ ዛሪያት 55-58] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_309 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ       ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
4325Loading...
32
✍ ብዕረ ሐኒፍ #3 🔖ሟች እና አልቃሽ ☞የሟችና አልቃሽ አስገራሚ ገፅታ! በበስራ ከተማ ኗሪ የሆነ አላህን በጣም የሚያመልክ ሰው ወደ ሞት እየተቃረበ መጣ። በዙሪያው ያሉ ቤተሰቦቹ ማልቀስ ጀመሩ። ከዛም ይህ ሞት የተጣደው ሰው ለቤተሰቦቹ "ቁጭ አድርጉኝ" አላቸው።  ደግፈው አስቀመጡት። ከዛ ወደ አባቱ ዞረና "አባቴ ለምንድነው ምታለቅሰው?" አለው።  አባትም" አንተን ማጣቴ ካንተ ቡሃላ ብቸኛ መሆኔ ነው ያስለቀሰኝ።" አለው። ወደ እናቱም ዞረና "እናቴ ምንድነው ያስለቀሰሽ?" አላት። እሷም "የልጅ ማጣት መሪር ሀዘን ነው ያስለቀሰኝ።" አለችው። ወደ ሚስቱም ዞረና "ምንድነው የሚያስለቅስሽ?" አላት እሷም "ያንተን መልካም ነገር ስለማጣ ወደ ሌላ ሰው ስለምከጅል ሸክም ስለምሆን።" አለችው። ወደ ልጆቹም ዞረና "ምንድነው የሚያስለቅሳቹ?" አላቸው። እነሱም "ከአንተ በኋላ ወደ የቲምነት፣ ወደ ውርደትና ደጋፊ ወደ ማጣት ስለምንጓዝ" አሉ። ይሁን ሁሉ ከሰማ በኋላ ሟቹ በጣም አለቀሰ። ቤተሰቦቹም  "ለምን ታለቅሳለህ?" አሉት። እሱም "ሁላቹም ለኔ ብላቹህ ሳይሆን ለራሳቹህ ጥቅም ነው የምታለቅሱት። ይህን ስላየሁ አለቅሳለሁ።" አለ። "ከናንተ ውስጥ ለጉዜዬ መርዘም ለስንቄ ማነስ የሚያለቅስልኝ የለም? ከናንተ ውስጥ ከዚህ በኋላ መኝታዬ ለብቻዬ አፈር ለመሆኑ የሚያለቅስ የለም? ከእናንተ ውሰጥ ከዚህ  በኋላ አስደንጋጭ ሂሳብ ስለሚጠብቀኝ የሚያለቅስ ሰው የለም? ከእናንተ ውስጥ የአለማት ጌታ ፊት መቆሜን አስታውሶ የሚያለቅስልኝ የለም? አለና በፊት ለፊቱ ተደፋ።  ቢያንቀሳቅሱትም ህይወቱ አልፋለች። ሞቷል። سَفَري بَعيدٌ وَزادي لَنْ يُبَلِّغَنـي *وَقُوَّتي ضَعُفَتْ والمـوتُ يَطلُبُنـي وَلي بَقايــا ذُنوبٍ لَسْتُ أَعْلَمُها *الله يَعْلَمُهــا في السِّرِ والعَلَنِ. ጉዞዬ ሩቅ ነው ስንቄም አያደርሰኝ ሀይሌም ተዳከመ ሞትም ፈላለገኝ የማላቃት ወንጀል አለች አሰፍስፋ አላህ የሚያውቃት በምስጥር በይፋ ✍ በዐብዱረዛቅ አል–ሐበሺይ 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
45112Loading...
33
🔴  ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 ۞ أَلَمْ يَأْنِ لِلَّذِينَ آمَنُوا أَن تَخْشَعَ قُلُوبُهُمْ لِذِكْرِ اللَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ الْحَقِّ وَلَا يَكُونُوا كَالَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلُ فَطَالَ عَلَيْهِمُ الْأَمَدُ فَقَسَتْ قُلُوبُهُمْ ۖ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ فَاسِقُونَ ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው ልቦቻቸው ሊፈሩ እንደእነዚያም በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ እንደረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁት ላይኾኑ (ጊዜው) አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡ [ሱረቱል ሀዲድ 16] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_308 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ       ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
4427Loading...
34
ስልኮቻቸውን ማስተካከል ሳይችሉና ከመጥፎ ጓደኞቻቸው ተነጥለው ሂዎታቸውን ማስተካክል ሳይችሉ #ሞቱ። ነገ እቶብታለሁ ወደ ጊታየ እመለሳለሁ ብሎ ተኛ መንቃት ግን አልቻለም።ጊዜው ደርሶ በዛው ተወስዷል።#አንተ_የዘነጋሃው ሆይ"ጊዜህ ይሄ አሁን አንተ ያለህበት ነው።ከየትኛውም በላይ ውድ የሆነም ነገር ነው።ካጣሃው በዋጋ አታገኘውም።በስልክም ይሁን በጊዜ ማባከን ያጣሃውን በአካውንትህ ላይ ያስመዘገብከውን ሁሉ ዛሬ ማሰረዝ ትችላልህ።ጌታህን የሚያስቆጣ የሆነን ነገር የመዘገብክበትን save ያደረክበትን ሁሉ አጥፋ።ወዳጅህን አስወድደህ ጌታህን አታስቆጣ።ለአላህ ብለህ በተውከው ሁሉ እርሱ የተሻለን ነገር ይተካሃል።በቃ ያለፈውን ተው መልካሞች ላይ በርታ ለአንተ በሚመሰክሩ መልካም ስራዎች አንጅ በአንተ "ላይ" በሚመሰክሩ ስራዎች ጊዜህንም ሂወትህንም አታጥፋ። አቡ ዑበይዳ 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
4186Loading...
35
የመማር ጌጡ ትህትና ነው ~ መማር ጥሩ ነው። ልብን ሊያሳብጥ ግን አይገባም። አንዳንድ የተማሩ ወንድሞቻችን ግን ከንግግራቸው / ከፅህፈታቸው ውስጥ እብሪት ይንፀባረቃል። የመማር ውበቱ ትህትና ነው። ደግሞም በሆነ ዘርፍ መማር ማለት በሁሉም ዘርፍ ላይ ዳኝነት ያጎናፅፋል ማለት አይደለም። እንዴት ነው በሁሉም ዘርፍ ላይ ዘው ብለው እየገቡ ሂስና ግምገማ የሚሰጠው? አንድ ከፍተኛ አቅም ያለው መካኒክ ሆስፒታል ሲሄድ ተራ ሰው ነው። መኪና ፈታቶ ስለሚገጥም ብቻ ቀዶ ህክምና ይሰጣል ማለት አይደለም። በተማሩት ዘርፍ ላይ የያዙት ትልቅ ስም እያደፋፈራቸው ስህተት ነው መባል እንኳ የሚበዛበት ሃሳብ እየሰነዘሩ ወዳጅ የሚያሳቅቁ ሰዎች አሉ። መሳሳት የትም አለ። ግን አይነት አለው። ከኩራት፣ ከትእቢት፣ ከመታበይ ጋር ሲሆን ያስንቃል። ብዙ ሙስሊም ምሁራን በህዝበ ሙስሊሙ መሀል ስላለ ጉዳይ ሲያነሱ ለራሳቸው ያላቸውን ከፍ ያለ ግምት በተለያየ መልኩ ሲያንፀባርቁት ይታያሉ። ምናልባት ካልተማረ ህዝብ መሀል የሚገኙ ልዩ ክስተቶች አድርገው ራሳቸውን እያዩ ሊሆን ይችላል። አንዳንዴ ግን የምናቀብጣቸው እኛው ነን። በቅጡ ባልገባቸው ነገር ውስጥ ገብተው ሲያቦኩ "ልክ ነህ ዶክተር!" ፣ "ልክ ኖት ፕሮፌሰር"፣ " የተማረ ይግደለኝ"፣ ... እያሉ በቦታውም ያለ ቦታውም አድናቆት መስፈር ማክበር ሳይሆን ማሽቃበጥ ነው። እንዲህ አይነቱ አካሄድ ለምናደንቀውም፣ ለራስም፣ ለህዝብም፣ ... ለማንም አይበጅም። ለማንም! 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
4492Loading...
36
ሀጅ ለማድረግ ለተነሳችሁ ወንድም እህቶች የሐጅ እና ዑምራን ድንጋጌዎች ለመማር የሚረዳ ጠቃሚ አፕሊኬሽን ነው። አውርዳችሁ ተጠቀሙበት። እናም በዱዐቹ አትርሱን 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
4122Loading...
ከማረሚያ ቤት ያመለጠው ወንጀለኛ ይፈለጋል! 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 በሆለታ ከተማ የመስጂድ ኢማም የነበሩትን ሸህ አህመድ ሙሀመድን በመግደል የ20 ዓመት እስር ፍርድ ተላልፎበት የነበረው አብዱልአዚዝ መሐመድ ጀማል የተሰኘው ወንጀለኛ ከሸገር ማረሚያ ቤት አመለጠ። በሆለታ ከተማ ታላቅ ዓሊምና ኢማም የነበሩት ሼህ አህመድ ሙሀመድ ሚያዝያ 9 ቀን 2014 ዓ.ል ረመዷን ወር ላይ ለማሰገድ ወደ መስጂድ ሲጓዙ በነበረበት ወቅት በሁለት ጥይት ተደብድበው መገደላቸው ይታወሳል። በግዜው በዋነኝነት ግድያውን ያቀናበረው አቶ አብዱልዓዚዝ ሙሀመድ ጀማል የተባለው ግለሰብ በ ሞያሌ በኩል ሊያመልጥ ሲሞክር በዚሁ የፌስቡክ ገጽ ላይ ባደረግኩት ጥሪ በሻሸምኔ ከተማ ላይ በሻሸመኔ ሙስሊም ጀምዓ መያዙ ይታወሳል። በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በግድያ ወንጀሉ ተከሶ በጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ል. በዋለው ችሎት የ20 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት ተላልፎበት ነበር። ሆኖም የእስር ቅጣቱን በሸገር ማረሚያ ቤት እየፈጸመ እያለ በግንቦት 23 ቀን 2016 ከእስር ቤት በመሰወሩ በተገኘበት እንዲያዝ ያለበትን የሚያውቅና ያየ ሰው እንዲጠቁም ጥሪ ተላልፏል። የተፈላጊው ወንጀለኛ ምስል፣የአፋልጉን ጥሪ ደብዳቤና ተያያዠ መረጃዎች ከስር ተያይዟል።
Show all...
🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ ۖ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا ۖ وَلَا يَغُرَّنَّكُم بِاللَّهِ الْغَرُورُ እናንተ ሰዎች ሆይ! የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት አታታላችሁ፡፡ አታላዩም (ሰይጣን) በአላህ (መታገስ) አያታላችሁ፡፡ إِنَّ الشَّيْطَانَ لَكُمْ عَدُوٌّ فَاتَّخِذُوهُ عَدُوًّا ۚ إِنَّمَا يَدْعُو حِزْبَهُ لِيَكُونُوا مِنْ أَصْحَابِ السَّعِيرِ ሰይጣን ለናንተ ጠላት ነው፡፡ ስለዚህ ጠላት አድርጋችሁ ያዙት፡፡ ተከታዮቹን የሚጠራው ከእሳት ጓዶች እንዲኾኑ ብቻ ነው፡፡ [ሱረቱል ፋጢር : 5-6] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_22 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
Show all...
3.49 KB
(እንቅልፍ) ⭐ከአላህ ተኣምሮችና ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ታላላቅ ፀጋዎች መካከል አንዱ እንቅልፍ ነው 🔸አላህ የሰላምና የጤና እንቅልፍ የሰጠውን ሰው ማንም ሊነፍገው አይችልም 🔹እንዲህ ዓይነቱን እንቅልፍ እርሱ ለነፈገው ሰው ደግሞ ማንም ሊሰጠው አይችልም! በመሆኑም በፈለጉት ሰዓት ተኝተው በፈለጉት ሰዓት መነሳት ትልቅ ምስጋና የሚያስፈልገው የጌታችን አላህ ኒዕማ ነውና ከልብ الحمد لله ማለት ያስፈልገዋል❗ እንቅልፍ ትንሹ ሞት ነውና በዛው እንደተኙ አለመቅረትና ዳግም ተነስቶ አላህን ለመገዛት መብቃትም ሌላው ተጨማሪ ምስጋና የሚያስፈልገው ፀጋ ነው! ለዚህም ነው ሙስሊሞች ልክ ከእንቅልፋቸው ሲነቁ:- (("الحمد لله الذي أحيانا بعد ما أماتنا")) ( ከገደለን በኋላ ዳግም ህያው ያደረገን ጌታ አላህ ይመስገን) የሚሉት 👉 ሆኖም በዲናችን ሁሉም ነገር ገደብና አደብ(ሥርኣት) አለው 🚩️የእንቅልፍ አደብ(ሥርኣት) እንቅልፍ አደቡ ከተጠበቀ ትንሹም በረካ ይሆናል፣ ለጤናም ተስማሚ ከመሆኑ አልፎ የህሊና ሰላምን ይለግሳል✅ 🚩የእንቅልፍ መጠን- እንቅልፍ ሲበዛ ቀልብ ይደርቃል፣ ከመድረቅም አልፎ ይሞታል❎ የሰውነት መወፈርንና መጫጫንንም ያስከትላል! 🚩ለአኼራችን ስንቅ የምንሰንቅበትን ውድ ጊዜያችንንም ያባክናል፣ ግዴለሽነትንና ስልቹነትንም ያስከትላል ⭐ጥሩ እንቅልፍ ማለት:- አንተ መተኛት ስለፈከግክ የምትተኛው ሳይሆን ሰውንነትህ መተኛት ሲያስፈልው የምትተኛው እንቅልፍ ነው✅ ⭐ጥሩ የእንቅልፍ ሰዓት ማለት- ከዒሻ ሰላት በኋላ የሌሊቱ መጀመሪያ ላይ የሚተኛ እንቅልፍ ነው✅ 🔶በቀኑ ክፍለ-ጊዜ የተወሰነ ሰዓት አረፍ ማለት ሱናና ጠቃሚ ሲሆን፣ ለዚህም የተመረጠው ወቅት የቀኑ መሀል ነው ♦ከሱብሂና ከአስር በኋላ መተኛት ተገቢም ጠቃሚም አይደለም❗ 📎ምናልባት ማታ ያልተኛ ሰው ከሱብሂ በኋላ ጸሐይ እስክትወጣ ጠብቆ ከዛ መተኛት ይችላል! በተቻለው ያህል ሱብሂ እንደተሰገደ ላለመተኛት መሞከር ይኖርበታል! 🚩️ በየትኛውም ሰዓት ሲተኙ ውዱዕ ማድረግ ከእንቅልፍ በፊት የሚደረጉ ዚክሮችን ማለት ፣ፊትን ወደ ቂብላ ማዞር፣በቀኝ ጎን ዞሮ መተኛት፣ እንቅልፍ እስኪወስደን ድረስ ዚክርና ቁርኣንን ማብዛት ተገቢና ከሙእሚኖች ባህሪ ነው❗ 🔑እንቅልፍ ጨርሰው ሲነሱም ፊትን በእጆች ጠረግ ጠረግ ማድረግና ከላይ የተጠቀስውን ዚክር ማለት ሱና ሲሆን ፣እንደባነኑ ከፍራሽ ፈጥኖ መነሳት አይመከርም❗ ወላሁ አዕለም ✍ ኡስታዝ አህመድ ኣደም ዙል-ሒጃ 29/1437ዓ.ሂ 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ያኔ ድሮ ድሮ አባቶቻችን ስልክን አስረው ሲፈልጉ ብቻ ነበር የሚጠቀሙት..... ዛሬ ግን እሱ በተራው እኛን አስሮ እየተጠቀመብን ይገኛል። አሏህ ሆይ! ከሸሩ ጠብቀን። ያ ረብ ከእዝነትህ አታርቀን! 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
Show all...
👍 5
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማንነት መፍትሄው አንድና አንድ ብቻ ነው፦ የምክክር ኮሚሽኑ ከወረዳ እስከ ፌዴራል ድረስ ተሳታፊን የሚለይበትን መስፈርት ይቀይር፣ ህዝበ ሙስሊሙ ቁጥሩን የሚመጥን የተሳታፊ ውክልና ኮታ ይሰጠው። ይህ ካልሆነ ታዋቂ ሰዎቻችንም ቢሳተፉ ዋጋ የለውም። ምክንያቱም ሃሳባቸው ውድቅ ስሚደረግ። ይህን ጉዳይ መጅሊስ በደንብ ያስብበትና ሚዲያዎችን በሙሉ ጠርቶ መግለጫ ያውጣ። ቀነ ገደብ ያስቀምጥና ኮሚሸኑ እስከዛ ቀን ድረስ አሠራሩን ህዝበ ሙስሊሙን ባማከለ መልኩ ካላስተካከለ፤ ከዚህ የምክክር መድረክ ራሱን ማግለሉን ያሳውቅ።         ጊዜ የለንም! ምንም እንኳ ሊያራዝሙለት ቢችሉኝ 3ኛ አመቱ ላይ ስለሆነ እየተጣደፈ ነው። እንፍጠን! 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
Show all...
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማንነት.mp317.12 MB
Photo unavailableShow in Telegram
ሁሉም ሰው ሃሳቡን ከዚህ የምክክር መድረክ ላይ ማንሳት የለበትም ሃሳብ እና ሴራቸው እኛ ከምናስበው በላይ ነው ያንን ጨቁዋኝ ዘመን ሙስሊሞች ላይ መመለስ ነው እና ሀሳባቸው ይሄ የፖለቲካ ጉዳይ እንዳይመስላችሁ ሙስሊሙን ከሁሉም አይነት ጉዳዮች ማግለል ነው እና ሁላችንም በተቻለን አቅም ለሰዎች ማሳወቅ አለብን ቢያንስ ለ 5 ሰው ያጋሩ #ኢትዮዳዕዋ #ሃገራዊምክክር #ኢትዮሙስሊም #ኢትዮጵያውያንሙስሊሞች #መጅሊስ #ኢስላም
Show all...
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 يَوْمَئِذٍ تُعْرَضُونَ لَا تَخْفَىٰ مِنكُمْ خَافِيَةٌ በዚያ ቀን ከእናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲኾኑ ትቅቀረባላችሁ፡፡ فَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِيَمِينِهِ فَيَقُولُ هَاؤُمُ اقْرَءُوا كِتَابِيَهْ መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ) «እንኩ፤ መጽሐፌን አንብቡ» ይላል፡፡ إِنِّي ظَنَنتُ أَنِّي مُلَاقٍ حِسَابِيَهْ «እኔ ምርመራየን የምገናኝ መኾኔን አረጋገጥኩ፤» (ተዘጋጀሁም ይላል)፡፡ فَهُوَ فِي عِيشَةٍ رَّاضِيَةٍ እርሱም በተወደደች ኑሮ ውሰጥ ይኾናል፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፡፡ قُطُوفُهَا دَانِيَةٌ ፍሬዎችዋ ቅርቦች የኾኑ፡፡ •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_321 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
Show all...
4.56 KB
👍 2 1
በዚህ አመት ሐጅ ላልተሳካለት ~ ኢብኑ ረጀብ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:– ★ በዐረፋ መቆም ላልቻለ ከአላህ ወሰኖች ዘንድ ይቁም። ★ በሙዝደሊፋ ማደር ላልቻለ ወደ አላህ ያቃርበው ዘንድ ለትእዛዙ ይደር። ★ ሀድዩን ሚና ላይ ማረድ ያልቻለ ከምኞቱ ይደርስ ዘንድ ስሜቱን ይረድ። ★እሩቅ በመሆኑ ቤቱ (በይተል ሐራም) መድረስ ያልቻለ የቤቱን ባለቤት ያስብ። ወደሱ ከደም ጋኑ የቀረበ ነውና።" (ለጧኢፉል መዓሪፍ: 633) 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
Show all...
🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፡፡ ጸጥም በሉ፡፡ ይታዘንላችኋልና፡፡ وَاذْكُر رَّبَّكَ فِي نَفْسِكَ تَضَرُّعًا وَخِيفَةً وَدُونَ الْجَهْرِ مِنَ الْقَوْلِ بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ الْغَافِلِينَ ጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል በጧትም በማታም አውሳው፡፡ ከዘንጊዎቹም አትኹን፡፡ إِنَّ الَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيُسَبِّحُونَهُ وَلَهُ يَسْجُدُونَ ۩ እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት (መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፡፡ ያወድሱታልም፡፡ ለእርሱም ብቻ ይሰግዳሉ፡፡ [ሱረቱል አዕራፍ : 204-206] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_320 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
Show all...
4.20 KB
🥰 4

👍 6