cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

በፍቅር የዳንስ እና የኪነጥበብ ማሰልጠኛ ማእከል OFFICIAL CHANNEL

በዚህ ቻናል ውስጥ 👉የዳንስ ቪዲዮዎች 👉የተለያዩ በኪነ-ጥበብ ዙሪያ ያሉ ማስተዋወቂያዎች 👉የዳንስ ስልጠና ምዘገባዎች እና የመሳሰሉትን ያገኛሉ። በማዕከላችን ለመመዝገብ 0994090808/0992050313

Show more
Advertising posts
510
Subscribers
+124 hours
+57 days
+1730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አሰደሳች ዜና ለጥበብ አፈቃሪያን በሙሉ ኒሞና የኪነጥበባት ማሰልጠኛ ማዕከል አዳዲሰ እና ነባር የጥበብ አፈቃሪያንን ለማሰልጠን እና ለትልቅ ደርጃ ለማድርሰ በበቁ አሰልጣኞች በምታገዝ በዙ የጥበብ ዝርፎችን በማካተት 1,#በዘምናዊ ዳንሰ እና በባህላዊ 2,በትያትር (ድርሰት አፃፃፈ ዳሪክቲንግ) 3,# በሙዴሊንግ እና በድምፅ ሰልጠናዎችን ለምሰጠት ዝግጅታችንን ጨርሰናል። አሰተውሉ ሰለጠናው ካለቀ በኋላ የሙያ ማርጋገጫ ሰርተፈኬት አና የሰራም እድል የተምቻቸ ነው። አድራሻ :- ጀሞ ለቡ ወረዳ1 ውጣቶች ማ/ማ 0922402077/0994090808ይደዉሉ በጥበብ ይደጉ። ኒምና የኪነጥበባትማማ
Show all...
👆👆👆👆👆 ቅዳሜ መተቹ መመዝገብ መጀመር ይቻላል አድራሻ ጀሞ ለቡ ወረዳ 01 ወጣት ማእከል።
Show all...
👍 1
በድጋሚ አስደሳች ዜና በጀም እና ለቡ አከባቢ ለምትገኙ ለጥበብ አፍቃሪያን በሙሉ በዳንስ በባህላዊ ዉዝዋዜ ቴያትር ሙዚቃ ስለጠና የጀመርን መሆሆኑን አዉቃቹ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን። ሀሙስ ቅዳሜ እሁድ 0994090808/0922402077 ደዉላቹ መመመዝገብ ትችላላቹ ኒምና የኪነ ጥበብ ማሰልጠኛ ማእከል አድራሻ ጀሞ ለቡ ወረዳ 01 ወጣት ማእከል
Show all...
በድጋሚ አስደሳች ዜና በጀም እና ለቡ አከባቢ ለምትገኙ ለጥበብ አፍቃሪያን በሙሉ በዳንስ በባህላዊ ዉዝዋዜ ቴያትር ሙዚቃ ስለጠና የጀመርን መሆሆኑን አዉቃቹ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን። ሀሙስ ቅዳሜ እሁድ 0994090808/0922402077 ደዉላቹ መመመዝገብ ትችላላቹ ኒምና የኪነ ጥበብ ማሰልጠኛ ማእከል አድራሻ ጀሞ ለቡ ወረዳ 01 ወጣት ማእከል
Show all...
👍 4
አስደሳች ዜና ሰበታ ና በዙሪያዋ ላላቹሁ ለጥበብ አፍቃሪያን በሙሉ በዚህ ሳምንት መጨረሻ የክረምትና በቋሚነት በቴያትር በሙዚቃ እና በባህላዊ ዉዝዋዜ እና ዘመናዊ ዉዝዋዜ ስልጠና የምጀምር መሆኑን በደስታ እንገልፃለን ። የተመዘገባቹ እንድትዘጋጁ ልሎቹ ይሄን አዉቃቹ በዚህ ሳምንት ምዝገባ የጀመርን ሲሆን ተመዝገቡ እንላለለን በሌሎች ቅርጫፎች ያላቹሁም እንደዛዉ 0994090808 ይደዉሉልን እናመሰግናለን በፍቅር የኪነ ጥበብ ማሰልጠኛ ማእከል
Show all...
ቻናላችንን 500* ገብቶአል በጣም እናመሰግናለን አሁንም ብዙ ሰዎች እንዲገቡ ቻናላችን jone shrr አድርጉልን እናመሰግናለን።
Show all...
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​🎙◉ ጊልዶ X ዳጊ ዲ   🔊◉ ቀን ሙሉ ✦ ━━━━━━━━━━━━ ✦        @Nahom_Records ✦ ━━━━━━━━━━━━ ✦     ♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️       ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
Show all...
ቀን ሙሉ.mp34.45 MB
🔥 1👏 1
እስቲ ሁሉንም አንቡብልኝ ለሁላቹሁም ይሆናል ለዳንስ እና ለዉዝዋዜ ሳታዉቁ ሃሳብ ልትሰጡና እዛዉ ሙያዉ ላይ ሆናቹሁ ሳይገባቹ ለምትሰሩ ይሁንል አመሰግናለዉ። ሁላቹሁም በዉስጥ አስተያየት ስጡኝ ሌሎች ታላላቅ የዳንስ ጥናቶችና ትምህርቶች ልንሰጥ ዝግጅታችንን ጨርሰናል በቅርብ ቀን ይሄን ለቅምሻ አብሶ በዚህ ሙያ ዉስጥ ያላቹሁ ግን ምንም ያልገባቹን ተጋበዙልኝ ከበፍቅር የዳንስ ቡድን አሰልጣኝ Teda ስለ ውዝዋዜ እጅግ በጣም በጥቂቱ!!! ............................#ውዝዋዜ......................... #ውዝዋዜ በሃገራችን እምብዛም የከፍታው ማማ ላይ ደርሷል፣ በሚደርስበት አቅጣጫ እየተጓዘ ነው ለማለት ባያስደፍርም የሃገርን ገፅታ ከመገንባትና ሃገርን በዓለም ደረጃ ከማስተዋወቅ አንፃር ሲታይ ያለው ፋይዳ እጅግ የላቀ ነው። #ውዝዋዜ የሃገራችንን ባህል፣ ወግ፣ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ የሚከወን ሲሆን ሰላም፣ ፍቅር፣ ደስታ እንዲሁም ሃዘን የሚተላለፍበት የጥበብ ዘርፍ ነው፡፡ ውዝዋዜ ለብቻ ወይም በቡድን በመሆን ስልተ-ምትን በመከተል ከውስጥ የሚመነጭ ጥልቅ ስሜትን የምናስተላልፍበት አንዱ የኪነ-ጥበብ መሳሪያ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር-ብሔረሰቦችና ህዝቦች ውቅር ስትሆን የብሔረሰቡ ነዋሪዎች አይጠገቤና ተወዳጅ ባህላቸውን ከሚያስተላልፉበት መንገድ እና እንደ ትልቅ ባህል ከሚታዩት አንዱና ዋነኛው ውዝዋዜያቸው ነው፡፡ እንዲሁም የጎረቤት ሃገሮችንና የምዕራባውያንን ባህል (ዘመናዊ) በመባል የሚጠቀሰውን ወቅቱን በዋጀ እና ባማረ መልኩ የተደራሲውን የልብ ትርታ በማድመጥ ይከወናል፡፡ ስለሆነም በሃገራችን ላይ ባህላዊና ዘመናዊ ውዝዋዜ በመባል በሁለት ተከፍሎ የሚገኝ ሲሆን በባለሙያው የአረዳድ ደረጃና አፈፃፀም ሊከወን ይችላል፡፡ #ውዝዋዜ፡-እንደ ማህበራዊ መስተጋብር በደረጃው የሁሉንም ኪነ-ጥበባዊ ዘርፎች የሚከውን ምትካዊ እንቅስቃሴ ሲሆን ምዕናባዊ ልህቀት የተሞላበት ፍቅርን ሰባኪ፣ ሰላምን አስፋኝ፣ የትናንትን ምስል ፍንትው አድርጎ በስዕላዊ መግለጫ ታሪክን የሚናገር፣ ባለ ትልቅ አቅም ክሂናዊ ድርሰት፣ ጥኡም ያለው ዜማ፣ የረቀቀ ግጥም፣ ቅኔያዊ ጥበብ የሚዘረፍበት፣ አቅጣጫ ጠቋሚ፣ ነገን አሻግሮ ሚያሳይ፣ በፈጣሪው የተፈጠረ መልእክትን ያዘለ፣ ሁሉንም የሙዚቃ መሳሪያዎች በስልተ-ምታዊ ሁነት በአንድነት አጣምሮ በውስጡ የያዘ ራሱ ሙዚቃ የሆነ የኪነ-ጥበብ ዘውግ በመሆኑ እንደሌሎች የኪነ-ጥበብ ዘርፎች ሁሉ ሰዎች ውስጣቸውን ፈንቅሎ የሚወጣውን የተዘበራረቀ እና አላስፈላጊ ስሜት ወደ ጥሩ መንፈስ በመቀየር አስፈላጊውን ስሜት በውስጣቸው የሚፈጥሩበት ኪነ-ጥበብ ነው፡፡ #ውዝዋዜ ትርጓሜው ለሙዚቃ ወይም ለሙዚቀኛው በደረጃዎቹ የተዘጋጁትን የሙዚቃ ስብስቦች በማዋቀር ሙሉ የሰውነታችንን አካሎች ወደ ስልተ-ምታዊ እንቅስቃሴ በመቀየር የሚከወን ረቂቅ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ነው፡፡ አንድ የውዝዋዜ ባለሙያ እንደ ባለሙያው አፈፃፀም የተወሰነ ቢሆንም የዚህ ሙያ ባለቤት ሲሆን በአካል በመንፈስና በአዕምሮ የተዋቀረ ረቂቅ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ሙያ ባለቤት ሆነ ተብሎ ይታሰባል፡፡ በአካል ስንል፡- ሙሉ አካሉ የዳበረና ሰውነቱን እንደልቡ ማዘዝ የሚችል ቀልጣፋ ሰውነት ስለሚኖረን! በመንፈስ ስንል፡- በመንፈስ ጠንካራ በመሆን የምንከውነውን ሃሳብ በአግባቡ ወደ ውስጣዊ ስሜታችን በማስገባት ደስተኛና ንቁ ስሜትን ስለሚፈልግ! በአዕምሮ ስንል፡- የሙዚቃውን ወይም የያዝነውን ስልተ-ምት ምእናባዊ ሃሳብ በመረዳት ከሰውነታችን ጋር በማዋሃድ የፈጠራ ክህሎታችንን በመጠቀም ለመከወን የጎለበተው አዕምሮአችን ትልቁን ድርሻ ይወስዳል! ስለዚህ አንድ የውዝዋዜ ባለሙያ ንቁ ቀልጣፋና ባለተሰጥኦ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡ በአንድ ወቅት ግሪካዊው ፈላስፋ ስለ ውዝዋዜ (Dance) የሰጠው ትርጓሜ:- “የሰዎችን ገፀ-ባህሪዎች እንዲሁም የሚሰሩትንና የሚሰቃዩትን ለመወከል አላማ ያለው ምት እንቅስቃሴ ነው!”
Show all...
ናሆም መኩሪያ ማሬ ማሬ ምርጥ አዲስ ሙዚቃ ተጋበዙልኝ።🙏👏❤️👍https://t.me/BEFKR28
Show all...
ማሬ ማሬ.mp33.70 MB
🔥 1🥰 1
" እጆቼን ማዘዝ ችዬ እኔን ለማገዝ የሚደክሙትን ሁሉ ከድካማቸዉ ባሳርፋቸዉ  ደስ ይለኝ ነበር " - ጠንካራው የይቅርታ ሰዉ ዳግማዊ አሰፋ (ዳጊ) የህግ ባለሞያና ደራሲ ዳግማዊ አሰፋ ከዓመታት በፊት በሀዋሳ ከተማ በእሱ እና በጓደኛው እጅ ላይ ከነበረ የፍትህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ " ጉቦ አንቀበልም !! " በማለቱ በአንድ ግለሰብ በጥይት ተመቶ መጎዳቱ ይታወሳል። በዚህ አደጋ ጠንካራ የወጣት እጆቹ አልታዘዝልህ ብለዉታል። በአከርካሪዉ ዙሪያ ያሉ ነርቮች መጎዳትም ቆሞ እንዳይሄድ እንቅፋት ሆነዉበታል። በዚህ ምክኒያት በሰው እጅ መብላቱ መልበሱ እና መንቀሳቀሱ ፈተና ቢሆንበትም ዛሬም ተስፋው ከሱ አልፎ ለሰዎች ይደርሳል። ያልተሰበረው መንፈሱ የተሰበሩትን ይጠግናል ፤ ያልወደቀው ምራሉም የወደቁትን ያነሳል። በዚህ ትጋቱ ያልተገታዉ ዳግማዊ ከህመሙ ጋር እየታገለ ስቃዩን እየተሰቃዬም ቢሆን አርፎ መቀመጥን አልወደደም ሁለት መጽሀፍት ለተደራሲያን አብቅቶ ለብዙዎች ህይዎት መቃናት ምክኒያት ሆኗል። በዚህ ዓመትም ሌላ መጽሀፍ ሊያስመርቅ እየሰራ ነው። የቀደሙ ሁለቱ መጽሀፍትም በአፋን ኦሮሞ ታትመዉ ለመዉጣት ጫፍ መድረሳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል። ከምንም በላይ ለሰዎች መትረፍ ሲችል የሰዎችን ድጋፍ ይፈልግ ዘንድ ብርቱ ክንዶቹ ዝለው ስራዎቹን መከወን ያቅታቸው ዘንድ ምክኒያት የሆነውን ሰው " ይቅር ብየሀለሁ " ማለቱ ለትንንሽ ጥፋት ይቅርታ ማድረግ ለከበዳቸዉ ሁሉ ታላቅ ትምህርት የሰጠ ሰው ነው። ጠንካራው ዳግማዊ ከሁለት ዓመት በፊት ውጭ ወጥቶ መታከም ከቻለ መዳን እንደሚችል ሀኪሞች ማብሰራቸውን ተከትሎ በርካታ ወዳጆቹ ተደስተዉ ጎ ፈንድሚ ቢያቋቁሙም ወቅቱ ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ ሀገራችን ችግር ላይ የነበረችበት ወቅት  በመሆኑ እንዳስቆመው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል። " አሁን ላይ  ' ጎፈንድሚውን እንጀምር  ዘንድ ፈቃድህን ብቻ ስጠን 'ላሉኝ ጓደኞቼ ፈቃዴን ሰጥቻለሁ "  ብሏል። ድኖ ለብዙዎች መትረፍ ሲችል ' ሀገሬ ችግር ላይ ናት " ብሎ የዘገየዉ ዳግማዊ ምንም እንኳን ብዙ ችግሮቹን " ወዳጆቼን አላስጨንቅም " ብሎ ቢደብቅም በቶሎ መታከም እንዳለበት ግን አሁን ላይ ብዙ ምልክቶችን አሳይቷል። ይህ ተከትሎም ሁሉም ደጋግ ኢትዮጵያውያን እገዛ እንዲያደርግለት ወዳጆቹ እየተረባረቡ ይገኛሉ። ዳግማዊ ፥ " ' 2 ሺህ የፌስቡክ ጓደኞቻችን ሁለት ሁለት መቶ ሰው ይዘዉ የአንድ ማኪያቶ የሚሆን 57 ብር በማዉጣት ያሳክሙሀል ' ብሎ ወዳጄ መምህር ወሌ ሀሳቡን ጀምሮታል " ብሏል። " ዳግማዊ ገንዘቡ ተሰብስቦልህ ታክመህ ስትድን በእጆችህ ቀድመህ ልትሰራ የምታስበዉ ምንድን ነው ? " በማለት የቲክቫህ ሀዋሳ ቤተሰብ አባል ጥያቄ አቅርቧል። ከረዥም ዝምታ በኋላ ፦ " አይገርምህም አስቤዉ አላዉቅም ... ግን እጆቼን ማዘዝ ችዬ እኔን ለማገዝ የሚደክሙትን ሁሉ ከድካማቸዉ ባሳርፋቸዉ  ደስ ይለኝ ነበር። " ዳግማዊ አሰፋን ማገዝ የምትፈልጉ በሀገር ውስጥ ሆነ በውጭ ያላችሁ ደጋግ ኢትዮጵያዉያን ፦ በጎፈንድሚ 👉 https://gofund.me/d93d0840 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 👉1000310977938 በዳሽን ባንክ 👉 5016527877077 በአቢሲንያ ባንክ 👉 39796821 በኩል ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ። ስልክ እንፈልጋለን ለምትሉም ፦ 0909888857 ላይ መደወል ትችላላችሁ። #TikvahEthiopiaFamilyHawassa @tikvahethiopia
Show all...