cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Muslim voice in Ethiopia

﴿وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلاً مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحاً وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ﴾ “ወደአላህ ከጠራና መልካምንም ከሰራ ፣ “እኔ ከሙስሊሞች ነን” ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?” (አልፉሲለት፡ 33) https://t.me/+406KOCQMOThlYTJk

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
311
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

«ጁሙዓ ቀን ላይ ዱዓእ ተቀባይነት እንዳለው ነቢያችን ዐለይሂስሰላቱ ወስሰላም ተናግረዋል፤ በዕለቱ ዱዓእ ሙስተጃብ ይሆናል ተብሎ ይበልጥ የሚከጀለው ከዓስር አንስቶ ጸሐይ እስክትጠልቅ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው 💥ሀገራችን አላህ ሰላም እንዲያደርግልን፣ ትክክለኛውን መንገድ እንዲመራን፣ ኸይረኛውን እንዲሾምልን፣ የዲን የዱኒያ ሓጃችንን እንዲያሳካልን አላህን ከልባችን እንማፀን።» أبو عائشه https://t.me/+406KOCQMOThlYTJk
Show all...

Photo unavailableShow in Telegram
በፋርስ ኢምፓየር እና በሮማ ኢምፓየር መካከል የተደረገው ጦርነት ለ700 ዓመታት የዘለቀ ሲሆን በዚህ ጊዜ ከ1,000 በላይ ጦርነቶችን አካሒደዋል። በስተመጨረሻ ኻሊድ ብን አል-ወሊድ رضي الله عنه መጥቶ ሁለቱንም የአለማችን ግዙፍ ኢምፓየሮች በ4 አመታት ውስጥ ብቻ አስወገዳቸው። ◾️ ግዛታቸው ሙሉ ለሙሉ እስኪወድቅ ድረስ ፋርሳውያንን በ15 አውደ ውጊያዎች እንዲሁም ሮማውያንን በ9 አውደ ውጊያዎች ድል ካደረገ በኋላ በምስራቅ ለሺህ ዓመታት የዘለቀውን የሮማውያንን ሕልውና እንዲያከትም አድርጎታል። ◾️ በስተመጨረሻም ፋርሳውያን እና ሮማውያን 200,000 ተዋጊዎችን አስከትለው ኻሊድ ብን አል-ወሊድን አል-ፋርድ በተባለ ቦታ በ12ተኛው አመተ ሂጅራ ለመፋለም ተባበሩ። ነገር ግን ኻሊድ በ15,000 ሙጃሂዶች ብቻ አሸነፋቸው። ሰራዊቱ የኻሊድን ስም ሲሰማ ብቻ ይርበደበድ ነበር..! --------------------- Yahya Ibnu Nuhe
Show all...
05:28
Video unavailableShow in Telegram
የአሏህን ﷻ ቃል በዚህ አይነት ውብ ድምጽ መስማት በእርግጥም መታደል ነው..! የሚቀራው ልጅ የኛው ሀገር ልጅ ነው አሉኝ፤ ቴሌግራም ላይ ኻገኘሁት ቀን ጀምሮ እንደ ሱስ እደጋግመዋለሁ። ዙሪያዎቻችንን እንዲህ በጌታችን ቃላት እያዋዙ ወደ መንገዱ የሚያቃርቡንን ሰዎች ያብዛልን..! ---------------------
Show all...
44.85 MB
ምክር ቢጤ! ወንድ የሆነ እንደሆን አያረግዝ። ወደድኩሽ አፈቀርኩሽ አበድኩልሽ ምናምን ያለሽን ሁሉ አትነጠፊ መዘዙ የአንቺ እንጂ ለወንዱ አይደለም። እሱ ምን አለበት አስረግዞ ሲፈልግ ከቆጥ እንጨት ማውረድ ያክል ቀላል ይመስል የሰው ነፍስ ያክል ነገር አስወርጂው ብሎ ቀጭን ትዛዝ ይሰጥሻል ካልሆነም አድረሻውን አጥፍቶ ይሰወርሻል ከዛስ ጦሱ አንቺ ዘንዳ ነው። ትክክለኛ አፍቃሪሽ ፈላጊሽ ከሆነ ኒካህ ይሰርልሽ አጉል ጤፍ በሚቆላው ምላሱ አያታልሽ። በእርግጥ ሴት ልጅ በትንሽ ነገር ትታለላለች ለዛም ነው በደካማ ጎንሽ ገብቶ ለጥፋት የሚዳርግሽ ግንሳ ጠንካራና አይበገሬ ይሁኚ ከኃላ የሚመጣብሽን መዘዝ አስቢ ከቤተሰብ አንስቶ ሁሉንም ሰው አንቺ ላይ ነው ጣቶቹን የሚቀስሩት ጥፋተኛም ተደርገሽ የምትወሰጂ አንቺው ነው! ምናልባት ከኒካህ በኃላ አልፈልግም ቢልሽ እንኳ ለልጅሽ ህጋዊ ባል አገኘ ማለት ነው። የዝሙት ልጅ አይሆንም። ዝሙት ደግሞ ትልቅ ወንጀል ነው። ስለዚህ ለደቂቃዎች ደስታ ብለሽ ሙሉውን እድሜሽን አታጨልሚ! ከሌሎች ያየሽውና የሰማሽውን ትምህርት ውሰጂ። ከአሏህ በኃላ ስለራስሽ ከማንም በላይ እራስሽ ነው መጠበቅና ለወደፊቱ አሻግረሽ ማሰብ ያለብሽ! ወንድሞች ሆይ እንተዛዘን እንጂ! እንደማታገባት ውስጥህ እያወቀው ለምን በእናት በእህትና በልጅህ ሊደርስ የማትፈልገው ነገር እህቶችህ ላይ ታደርሳለህ? አንዳንድ የሚሰሙ ነገሮች ያሳዝናሉ ያበሳጫሉም ያስተዛዝባሉም። አላህ ማገናዘብን ያድለን! እያልኩ ቀጭን ምክሬ እቋጫለሁ!!! https://t.me/+406KOCQMOThlYTJk
Show all...
«አል-ፋሩቅ» «እስልምናው ለሙስሊሞች ስኬትን የበላይነት፣ ሒጅራው ድልን፣ ኸሊፋነቱ በምድር ላይ ፍትሕን ያነገሰ ታላቅ የስብዕና ምጥቀት ጥግ ድንቅ መሪ በሰው ልጆች ታሪክ አማና የተጣለበትን ሥልጣን የሚመራውን ሕዝብ ችግርና የአኗኗር ዘይቤ በቅርብ ለመከታተል ሲል በሌሊት ጨለማ ብቻውን ከተማይቱን የሚሰልል በየቤቱ የሚዞር ድንቅ ሰው ነው። «ሃያ አንድ ቦታ ተቀዳዶ የተሰፋ ቡትቱ ብጥስጣሽ ጨርቅ የሚለብስ ልብሱን አጥቦ ያችው ብጣሽ እስክትደርቅለት ቅያሬ በማጣቱ ቤት ሚቀመጥ፣ ጫማውን ትራስ አድርጎ ዛፍ ጥላ ሥር የሚተኛ፣ ነገር ግን የዓለምን አንድ ሥስተኛ የሚመራ ሓያል መሪ ፍትሕን በእግሯ ቀጥ አድርጎ በትክክለኛዋ ሚዛን ሰፍሮ በገሃድ ምድር ላይ ያቆማት ድንቅ መሪ ረዲየሏሁ ዐንህ... «ከእኔ በኋላ ነቢይ ቢኖር ኖሮ ዑመር ይሆን ነበር ተብሎ በረሱል(ﷺ) አንደበት የተመሰከረለት ድንቅ መሪ አሏህ ጥበብን የለገሰው ሰይጣን እንኳን የማይቀርበውና በርቀት ሲያየው ደንብሮ የሚሽሸው በሕይወት ሳለ የጀነት መሆኑ በገሃድ የተመሰከረለት ድንቅ የአሏህ ባሪያ ከአሏህ ፍራቻ ለቅሶ ብዛት ጉንጩ ላይ የእንባ ሁለት መስመር ምልክት ያሉበት..... «ግፈኞችን አንገት ያስደፋ፣ ዓለም ላይ ኃያላን የነበሩ ግፈኞችን ሕዝባቸውን ባሪያ ያደረጉ በዝባዥ መዝባሪዎችን ልክ ያስገባ፣ ባዛንታይንን ያንሸረደደ፣ ፐርሺያኖችን ያሽመደመደ፣ ለዱኒያ ጌጥ ምንም ግድ የሌለው ለፍትሕ ሲል ግን የዓለምን ኃያላን የገጠመ ጀግና፣ አልቃሻ የዋሕ ለችግረኞችና ምስኪኖች ሩሕሩሕ ዛሬም ቢኖሩልን የምንናፍቃቸው ድንቅ ኸሊፋ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንህ። ©»رَّضِيَ ٱللَّهُ عَنۡهُمۡ وَرَضُواْ عَنۡهُۚ ذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ } «አላህ የእነሱን ሥራቸውን ወደደ፤ እነርሱም የእርሱን ሽልማቱን ወደዱ፤ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡» (5፣119) AbuMahira https://t.me/+406KOCQMOThlYTJk
Show all...

Photo unavailableShow in Telegram
ተፈቅዷል‼ ========= #Confirmed || ✍ ነገሩ ውስብስብ ሆኖ በተደጋጋሚ የሚደረጉ ሙከራዎች እየከሸፉ ባልተረጋገጡ ዜናዎች በተደጋጋሚ የብዙዎች ቀልብ ተሰብሯል። ለነገ መፈቀዱን ከሰማሁ ብቆይም አሁንም አንዱ የፈቀደውን ሌላው ስለሚከለክል 100% ሳላረጋግጥ ድጋሜ የማንንም ቀልብ መስበር ስለማልሻ ከመናገር ተቆጥቤ ነበር። አሁን ብዙዎች ባደረጉት ጥረት በነገው ዕለት በስቴዲዬም ፕሮግራሙ የሚካሄድ ይሆናል። መጀመሪያውኑ ክፍተቱ የአዘጋጆቹ ቢሆንም ህጉ ሰው ሠራሽ ነውና ያልተሟላውን ዶክመንት አልፎ መንግስት ካመነበት ማመቻቸት እንደሚችል ጠቁሚያለሁ። ይህ ፕሮግራም እንዲፈቀድ በማድግ የተከፉ እንዲደሰቱና በመደናቀፉ የተደሰቱ እንዲከፉ ያደረጋችሁ ሁሉ አላህ ምንዳችሁን ይክፈላችሁ። (… لِلَّهِ الْأَمْرُ مِن قَبْلُ وَمِن بَعْدُ ۚ وَيَوْمَئِذٍ يَفْرَحُ الْمُؤْمِنُونَ) «…ትዕዛዙ በፊትም በኋላም የአላህ ነው፡፡ በዚያ ቀንም ምእመናን ይደሰታሉ፡፡» [አ-ር'ሩም: 4] ነገ ስቴዲዬም ሲገባ ማንም ሰው ትኬት ሊጠይቀን አይገባም። ሁላችንም በነፃ መግባት አለብን። ስቴዲዬሙ ሞልቶ ሁሉም ዙሪያው መሙላት አለበት። የዚህ ፕሮግራም ድምቀት ለሃገር ኩራት ነው። መሰረዙና አለመድመቁ ለሃገር ኃፍረት ነው። ያስፈቀዳችሁና የፈቀዳችሁ በሙሉ እናመሰግናለን። ከልክ ያለፈ ደስታም አያስፈልገውም። አላህ መጨረሻውን የሚያምር ያድርገው። ካሰብነው በላይ ደምቆና አስደስቶን የሚያልፍ ያድርግልን። ክስተቱ ብዙ ነገር የተማርንበት ሆኖ አልፋል። ወዳጅ ጠላትና ብዙ ድብቅ ማንነቶች የተለዩበት ነበር። ለወደፊቱ ጉዞ ብዙ ግብዓት የሚሆኑ ነገሮችን ቀስመንበት አልፈናል። አንድ ነገር ያለ መሰናክል ሲሳካ ከሚሰጠው ደስታ ይልቅ መሰናክሉ ታልፎ የሚገኘው እፎይታ ይበልጥ ጣእም አለው።
Show all...
ተሰርዟል❗️❗️ << በዛሬው ዕለት የዓለምዓቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር መዝጊያ ፕሮግራም በስታድየም ይደረጋል ተብሎ የተገለጸ መሆኑ ይታወቃል:: አንዳንድ ዶክመንቶች በጊዜ ባለማሟላቱ እንዲሁም አዲስ አበባ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት የተቆፋፈረና ምቹ ባለመሆኑ የመዝጊያውን ፕሮግራም ከስታዲየም ውጪ በውስን ሰዎች እንዲደረግ ተወስኗል። ስለዚህም ህዝቡን ይቅርታ እየጠየቀን ከዚህ ጋር የተያያዙ ዝርዝር ጉዳዮችን በቀጣይ ጊዜያት የምናሳውቅ ይሆናል:: ( አዘጋጅ : ዘይድ እብን ሳቢት የቁርአን ማህበር ) >> ❗️የተዋረድነው እንደ ሀገር ነው! ይሄ ህዝብንም እንግዳንም አለማክበር ነው።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ 🇪🇹 በኢብራሂም ተወክላለች‼ =========================== ✍ ዛሬ ከተደረገው ማጣሪያ በኋላ ኢብራሂም ዐብዱ-ር'ረሕማን ኢብራሂም በአላህ ፈቃድ ኢትዮጵያችንን🇪🇹 እንደሚወክል ታውቋል። ኢብራሂም ቢላል ቲቪ በረመዿን ባዘጋጀው ኒብራስ ልዩ የሒፍዝ ውድድር ላይ ከሶማሌ ክልል መጥቶ 1ኛ በመውጣት ያሸነፈ ታዳጊ ሲሆን፤ ሃገራችንን ወክሎ ወደ ዓለም ዓቀፍ የቁርኣን ውድድሩ ገብቷል። መልካም እድል‼ ማንም ቢያሸንፍ ማንም ሁሉም የቁርኣን ህዝብ ነው። ||
Show all...
00:15
Video unavailableShow in Telegram
ስንቅ ለቀልብዎ❤️ 👌 #ቁርኣን
Show all...
1.52 MB
ነብዩን ﷺ የሚመስላቸው ሶሐቢይ ማነው?Anonymous voting
  • ሀ) ዲሕየቱል ከልቢይ ረዲየላሁ ዐንሁ
  • ለ) ሐሰን ብኑ ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁማ
  • ሐ) ጀዕፈር ረዲየላሁ ዐንሁ
  • መ) ዙበይር ረዲየላሁ ዐንሁ
0 votes
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.