cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dubbo Our Lady's Catholic School ️

This is the official telegram channel of DOLC school. You will get latest news, notices and informations of the school through this channel. #WeMakeABetterFuture #Since1933 🌐 - http://www.dubboourladyscs.com ❓️ - @dolcschoolbot

Show more
Advertising posts
712
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ለጥንቃቄ ቴሌግራም ላይ ከተለያዩ ሰዎች አጭር ጹሑፍና ሊንክ እየተላከሎት ነው ? ቴሌግራም ላይ ከተለያዩ ሰዎች ጹሑፍና ሊንክ ያለው መልዕክቶች እየተላኩ ነው። ብዙዎች ይህ ጉዳይ በተደጋጋሚ እየደረሳቸው እንደሆነና የጥንቃቄ መልዕክቱን እንድናስተላልፍ ጠይቀውናል። በመልዕክት የሚላከው ሊንክ ምንድን ነው? በመልዕክቱ አብሮ የሚደርሶት ሊንክ የቴሌግራም አካውንቶን ለመጥለፍ የተዘጋጀ ቴሌግራምን የሚመስል ድረ-ገጽ ነው። ሊንኩን ሲከፍቱት ስልክ ቁጥር አስገብተው ወደ ቴሌግራም እንዲገቡ ይጠይቆቃል። ቁጥሮን አስገብተው የሚመጣው ሌላኛው ገጽ በቴሌግራሞት የተላከሎትን አጭር የማረጋገጫ ቁጥር እንዲያስገቡ የሚጠይቅ ነው። የተላከሎትን የማረጋገጫ ቁጥር ካስገቡ የእርሶን ቴሌግራም በቀጥታ ይህን ወጥመድ ያዘጋጁ ሰዎችም መጠቀም ይጀምራሉ። በዚህም መልዕክቶችን ለሌሎች መላክና እርሶ እንደላኩት አድርገው ማቅረብ ይችላሉ። ይህ ገጽ ልክ ቴሌግራምን እንዲመስል ተደርጎ የተሰራ ሲሆን የሚያስገቡት መረጃ ግን ወደ ቴሌግራም ሳይሆን ይህንን ወደ ሚቆጣጠሩት ሰዎች የሚላክ ነው። ይህ አይነቱ ማጭበርበር ማጥመድ (Phishing) በመባል ይታወቃል። ምን ማድረግ እችላለሁ ? ይህ ችግር ካጋጠሞት ቀጥታ ቴሌግራሞት ላይ Setting ላይ በመግባት #Device የሚለውን በመጫን የእርሶ አካውንት በምን በምን ስልኮች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ማየት ይችላሉ። በዚህም ከእርሶ ቁጥጥር ውጪ ያሉ ስልኮችን በሙሉ ማስወጣትና እርሶ የሚጠቀሙበትን ብቻ ማስቀረት ይችላሉ። ሁለተኛው መንገድ ይህ ችግር ከተመፈጠሩ በፊት የሚያገለግል ሲሆን ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) መጠቀም ድንገት ለእንደዚህ አይነት ችግሮች ብንጋለጥ ተጨማሪ የደኅንነት ማረጋገጫ ይሆነናል። (ስለዚህ ዝርዝር ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ) Via 👋  @TikvahethMagazine
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ። የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡ በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል። ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የRemedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 255 ከ700 ያመጡ ☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 234 ከ700 ያመጡ ☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 218 ከ600 ያመጡ ☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 200 ከ600 ያመጡ ☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 224 ከ700 ያመጡ ☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ ☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 192 ከ600 ያመጡ ☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ ☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ ☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ ☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ ☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ ☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 150 ከ500 ያመጡ ☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 150 ከ500 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል። መረጃውን ትምህርት ሚኒስቴርን ዋቢ በማድረግ ያሰራጨው ኤፍ ቢ ሲ ነው። @tikvahethiopia
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ። በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። Website:  https://result.ethernet.edu.et/ Telegram bot: @moestudentbot @tikvahethiopia
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
Photo unavailableShow in Telegram
ውጤት በምን ይታያል ? " ነገ ጥዋት 12 ሰዓት ላይ በዌብሳይት እና በSMS ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይቻላሉ። " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ @tikvahethiopia
Show all...
👍 6 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ሚኒስትሩን ያስደናገጣቸው ቁጥር ? ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦ " ከዚህ ፈተና አንድ #ሊያስደነግጠን የሚገባ ነገር ከተፈተኑት ጠቅላላ ተማሪዎች ውስጥ 50 ከመቶ የሚሆኑት እና ከዛ በላይ 26 ከመቶ ነው ያገኙት። ከ845 ሺህ ፤ 422,500 ሺህ ተማሪ ከ26 በታች ነው ያገኘው። እንደው ዝም ብሎ አንድ ተማሪ ፈተናውን በግምት ቢሞላ እንኳን ሊያገኘው የሚችለው ውጤት ነው። ለዚህ ነው ከታች ጀምሮ በደንብ አጥርተን መስራት አለብን የምንለው። " ስለ 2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ቁጥሮች ምን ይላሉ ? - በ2015 የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት 845,099 ፤ 50 በመቶና በላይ ያመጡ 27,267 ተማሪዎች (3.2%) ብቻ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ፦ • ከተፈጥሮ ሳይንስ ያለፉ 19,017 ተማሪዎች • ከማህበራዊ ሳይንስ ያለፉ 8,250 ተማሪዎች - በማታ የተፈተኑ 16,541 ያለፉ 12 ተማሪዎች ብቻ - በግል የተፈተኑ 169,502 ያለፉ 498 ተማሪዎች ብቻ - በመደበኛ የተፈተኑ 659,056 ያለፉ 26,757 ተማሪዎች ብቻ - የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ት/ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች #አንድም_ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም / ምንም ተማሪ አላሳለፉም። - በሀገሪቱ ካሉትና የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑት ትምህርት ቤቶች 42.8 በመቶ የሚሆኑት አንድም እንኳን ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም። - 27 ሺህ 267 ተማሪዎች በቀጥታ ፍሬሽ ማን ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 160 ሺህ ገደማ ተማሪ በሬሜዲያል ይገባሉ። #TikvahEthiopia @tikvahethiopia
Show all...
👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ሙሉ_መግለጫ የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ የሰጠው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል። ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጥዋት 12 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተከታትሎ መረጃዎችን ያደርሳል። More - @tikvahuniversity @BirlikEthiopia @tikvahethmagazine @tikvahethiopia
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል " - ትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ  ፈተና ውጤት ነገ ይፋ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም ዙሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ነገ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጿል። @tikvahethiopia
Show all...
👍 2
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" እስካሁን ውጤት አልተገለፀም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እስካሁን #አልተገለፀም ሲል አሳውቋል። ተፈታኞችና መላው የትምህርት ማህበረሰብ #በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል። ከሁለት ሳምንት በፊት በፀጥታና ሌሎች ምክንያቶች ፈተና ሳይወስዱ የቆዩ ተማሪዎች ፈተናቸውን መውሰዳቸው ይታወቃል። የነዚህ ተማሪዎችን ፈተና ውጤት በሐምሌ 2015 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች ጋር አብሮ ይፋ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ከዚህ ቀደም " እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል " የአገልግሎቱ ከፍተኛ ኃላፊ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ @tikvahethiopia
Show all...
👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
#Update የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይገለጻል? የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤትን ቶሎ ለማድረስ በሙሉ አቅም እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡ ፈተናውን የማረም ሥራ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ማንጠግቦሽ አዳምጤ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡ ከመስከረም 07 እስከ 11/2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን ጨምሮ ውጤት ለመግለፅ መታሰቡን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡ "ምናልባትም እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል" ተናግረዋል፡፡ በነሐሴ መጨረሻ በሰጡት መግለጫ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ ይፋ ይደረጋል ብለው እንደነበር አይዘነጋም። በትግራይ ክልል በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለነበሩ ተማሪዎች ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም የመልቀቂያ ፈተናው ይሰጣል መባሉ ይታወቃል። @tikvahuniversity
Show all...
👍 1 1👏 1
Happy New Year for all families Dubbo Our Lady's Catholic School. The school is happy to announce, the opening day of the Academic Year 2016E.C. on tomorrow, Wednesday Sept.13/2023G.C./ረቡዕ መስከረም 02/2016ዓ.ም./። ስለዚህ የዱቦ እ/ቅ/ማ/የካ/ካ/ትም/ት ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎቹን መምጣት ብቻ እየተጠባበቀ ስለሆነ ልክ ከጧቱ 2:00ሰዓት በትም/ት ቤቱ ቅጥር ግብ ተገናኝተን መደበኛ ሥራ መጀመር የትም/ት ቤቱ ማኅበረሰብ ልዩ የሆነ የቀጠሮ ቀን ነው። ሰላም ወሠናይ!!!
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.