en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

The Christian News

The Christian News

Open in Telegram

ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት። @TCNEW

Show more
5 243
Subscribers
-324 hours
-57 days
-4730 days
Posts Archive
#እንኳን ተጨማሪ ዘመን ተጨመረሎት 🔥🔥 🎂 🥳 በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ ከ50 ዓመት በላይ በትጋት እና በታማኝነት የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን አገልግለዋል። ፖስተር ፃዲቁ አብዶ #ዛሬ ከተወለ
#እንኳን ተጨማሪ ዘመን ተጨመረሎት 🔥🔥 🎂 🥳 በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ ከ50 ዓመት በላይ በትጋት እና በታማኝነት የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን አገልግለዋል። ፖስተር ፃዲቁ አብዶ #ዛሬ ከተወለዱ በብዙ ምህረት እና በእግዚአብሔር ጥበቃ 70 ዓመት ላይ ደርሰዋል። በድጋሜ እንኳን ተወለዱ 🥳🎂🎂 The Christian News - የክርስቲያን ዜና መልካም ቀሪ የማገልገል ዘመን እንዲጨመርሎት እንመኛለን።

በኢትዮጵያ 52 በመቶ ክርስቲያኖች የዲጂታል መጽሐፍ ቅዱስ ተጠቃሚ ናቸዉ። 🔥🔥🙏🙏 በኢትዮጵያ የመጽሐፍ ቅዱስ ዲጂታል ንባብና የዕለታዊ ተሳትፎ እድገት 52 በመቶ መድረሱ ተዘገበ። Christia
በኢትዮጵያ 52 በመቶ ክርስቲያኖች የዲጂታል መጽሐፍ ቅዱስ ተጠቃሚ ናቸዉ። 🔥🔥🙏🙏 በኢትዮጵያ የመጽሐፍ ቅዱስ ዲጂታል ንባብና የዕለታዊ ተሳትፎ እድገት 52 በመቶ መድረሱ ተዘገበ። Christian Daily International ባወጣው ዘገባ፣ በ2026 በኢትዮጵያ የYouVersion የመጽሐፍ ቅዱስ መተግበሪያዎች ዕለታዊ አጠቃቀም 52 በመቶ እድገት እንዳሳየ ገልጿል። በሰሃራ በታች አፍሪካ የመተግበሪያዎቹ ዕለታዊ አጠቃቀም በአማካይ 63 በመቶ ሲያድግ፣ በዓለም ደረጃ የተመዘገበው እድገት 13 በመቶ መሆኑ ተጠቁሟል። በዚሁ ዘገባ መሠረት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ 18.5 ሚሊዮን ሰዎች በየቀኑ የYouVersion መተግበሪያዎችን ይጠቀማሉ። የዲጂታል መጽሐፍ ቅዱስ አጠቃቀም እድገቱ በኢትዮጵያ የወንጌል ስርጭት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና የክርስቲያናዊ ሚዲያ አገልግሎት ላይ ያለውን እድል እንደገና እንድንመለከት ያነሳሳል። ሆኖም 52 በመቶ የሚለው ቁጥር የመተግበሪያ ዕለታዊ አጠቃቀም እድገትን የሚያመለክት እንጂ የክርስቲያኖች ቁጥር መጨመርን አይወክልም። በዘገባዉ መሰረት ሴኔጋል፦ 72% ፣ ዚምባብዌ፦ 72% ፣ኢትዮጵያ፦ 52% ፣ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ፦ 48%፣ ኡጋንዳ፦ 41% ፣ ናይጄሪያ፦ 37% ፣ ኬንያ፦ 36% እንደሆነ ያሳያል። ምንጭ አድርጊ Christian Daily International ተጠቀምኩኝ። እስቲ ንገሩኝ መፅሐፍ ቅዱስ በስልክ ማንበብ ወይስ በወረቀት ያለዉን ማንበብ የሚመቻችሁ ኮመንት ስጡኝ። በዮሐንስ ግርማ

ኢየሱስን ማወቅ በግል ነው በእከሌ በኩል አይደለም! በZadok Perth International Ministry እየተዘጋጀ በወንድም ተመስገን ነጋሽ በZadok Perth Youtube የሚቀርብ ተከታታይ የመጽሃፍ ቅዱስ ትምህርት Zadok Perth የዩቱብ ቻናል subscribe ያድርጉ።

በሰብዓዊ ክብር፣ በሰላም ግንባታ፣ የዜጎችን የእርስ በእርስ ግንኙነት በማጠናከር፣ እና የጥላቻ ንግግር በመከላከል ላይ የሃይማኖት ተቋማት ሃይማኖታዊ አስተምህሮ እና ተቋማዊ አቋምን አሳወቁ። በዛሬው
በሰብዓዊ ክብር፣ በሰላም ግንባታ፣ የዜጎችን የእርስ በእርስ ግንኙነት በማጠናከር፣ እና የጥላቻ ንግግር በመከላከል ላይ የሃይማኖት ተቋማት ሃይማኖታዊ አስተምህሮ እና ተቋማዊ አቋምን አሳወቁ። በዛሬው እለት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል ቤተዕምነቶች በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በጉባኤው ዋና ጽ/ቤት በተካሄደው መግለጫ ሀሰተኛ መረጃን በመከላከል የሰው ልጅን ሰብዓዊ ክብርን መጠበቅ እንደሚገባ ተጠቁሟል። የሃይማኖት አባቶቹ የሁሉም የሃይማኖት አስተምህሮ ክቡሩን የሰው ልጅ በሰውነቱ ብቻ ያለ ልዩነት እንድናከብር የሚያስተምር እና የሚያዝ ነው ያሉ ሲሆን በሰዎች ላይ ማንኛውንም ጥላቻ እና ጥቃት ማድረስ ፈጣሪ ላይ እንደሚደረግ ጥፋት ስለሚቆጠር አስተውሎት በተሞላበት መንገድ መራመድ፣ ሰዎችን መውደድ እና ቤተ እምነቶች እንደ ራስ መጠበቅ እንደሚያስፈልግም መክረዋል፡፡ ዘመኑ የዲጂታል እንደመኾኑ የቴክኖሎጂ መረቦችን ግጭትን ለመፍጠር እና ለሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ሳይኾን፣ በጎነትን ለማስተማር እና የሕዝብን አንድነት ለመገንባት መጠቀም እንደሚገባም አሳስበዋል። ሴቶች እና ወጣቶች በሰላም ግንባታ ተሳታፊ እንዲኮኑ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው ሀገርን ለመገንባት ተሳትፏቸውን ማሳደግ ብሎም በጎ ተፅዕኖን ማሳደር ከሃይማኖት አባቶች ይጠበቃል ነው ያሉት። ግጭቶች ሲፈጠሩ ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ሥርዓቶችን በመጠቀም ልዩነቶችን መፍታት፣ እርቅ መፍጠር እና ማሸማገል ሃይማኖታዊ አስተምህሮው የሚያዝዘው እና ሁሉም አማኝ ሊተገብረው የሚገባ መኾኑንም አስገንዝበዋል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እና የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን መሪዎች ናቸው።

በአፍሪካ የክርስቲያኖች የደኅንነት ስጋት ቀጥሏል። በአፍሪካ ሁለት አገራት የሚገኙ ክርስቲያኖች በታጣቂዎች ጥቃት፣ በመፈናቀልና በሕይወት ማጣት አደጋ እየተጋፈጡ ነው። በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ም
በአፍሪካ የክርስቲያኖች የደኅንነት ስጋት ቀጥሏል። በአፍሪካ ሁለት አገራት የሚገኙ ክርስቲያኖች በታጣቂዎች ጥቃት፣ በመፈናቀልና በሕይወት ማጣት አደጋ እየተጋፈጡ ነው። በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ክፍል፣ በኢቱሪ ክልል የሚገኙ ማኅበረሰቦች በADF ታጣቂዎች የደኅንነት ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ የOpen Doors ዘገባ ያመለክታል። በናይጄሪያ ደግሞ፣ በቤኑዌ ግዛት በጥቅምት 9 በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን የድርጅቱ ምንጭ ገልጿል። ጥቃቶቹ ከሰው ሕይወት መጥፋት በተጨማሪ የእርሻ ምርት መጥፋት፣ የቤተሰቦችን መፈናቀል፣ የኑሮ መቃወስና የአምልኮ ሕይወት መስተጓጎል አስከትሏል። ከ1 መቶ ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖች እንዳሏት የምትነገረው ናይጄሪያ ለክርስትና አስቸጋሪ ከሆንኑ ሀገራት መካከል የ2026 ሪፖርት 7ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። በተመሳሳይ ከ1 መቶ ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖች የሆኑባት እና 95.5 በመቶ የሃገሪቱን ህዝብ የሚሸፍኑት ኮንጎዎች በበኩላቸው በ29ኛ ስፍራ ተቀምጠዋል። በዮሐንስ ግርማ

“በሕይወት እያለው ብቻ ሳይሆን ወደ ጌታም ከሄድኩም በኋላ ማገልገል እፈልጋለሁ” ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን አንጋፋው የወንጌል አገልጋይ እና ጸሐፊ ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን ይህንን ያሉት በዛሬው አዲሱን
“በሕይወት እያለው ብቻ ሳይሆን ወደ ጌታም ከሄድኩም በኋላ ማገልገል እፈልጋለሁ” ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን አንጋፋው የወንጌል አገልጋይ እና ጸሐፊ ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን ይህንን ያሉት በዛሬው አዲሱን መጽሃፎቻቸውን አስመልክቶ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው። በጥቅምት 14/2019ዓ.ም በወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን የተዘጋጁ ሁለት አዳዲስ መጽሃፊት መመረቃቸውን አስመልክቶ በዛሬው እለት ለሚዲያዎች በሸራተን አዲስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል። በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ወንጌላዊ ያሬድ የመጽሀፍቶቹን መልዕክት እና መጽሀፍቶቹን ለማዘጋጀት ያነሳሳቸውን ሃሳብ እና ተደራሲዎቹን አስመልክቶ መልዕክት ባስተላለፉት ወቅት የስነ-ጽሁፍ አገልግሎት ዘመን ዘለል (ትውልድ ተሻጋሪ) ሆኖ ብዙዎችን የሚጠቅም እንደሆነ ጠቅሰዋል። አክለውም ወደ ጌታ በመጣውበት ወቅት እጅግ ያገዙኝ መጽሀፍት አብዛኛዎቹ ጸሃፊዎች ወደ ጌታ የሄዱ ናቸው ያሉት ወንጌላዊው እኔም ከሄድኩኝ በኋላ ለማገልገል ያለኝ እድል መጽሐፍ ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገር አሻራ ለማኖር እና እውነተኛ ክርስቲያናዊ ሕይወት እንዲኖር ይህንን መጽሐፍ ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። በመድረኩ አቶ ጌቱ ግዛው አገልጋይ እና ጸሐፊ የሆኑትን ወንጌላዊ ያሬድ ባለፉት አራት አስርት አመታት የነበራቸው አገልግሎት እና የሕይወት ጉዞ በዝርዝር አቅርበዋል። የጎልደን ኦይል ሚኒስትሪ መሪ የሆኑት ወንድም ሲቢሉ ቢጃ በበኩላቸው ሚኒስትሪው ከዚህ ቀደም የሰራቸውን ስራዎች ያነሱ ሲሆን ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን ከዚህ ቀደም እፎይታ (ሶስት ክፍል ያለው) ፤ እግዚአብሔርን መምሰል እና ታላቅ ርስት የተሰኙ ከአማርኛ ቋንቋ ውጪ በሌሎች የሃገር ውስጥ ቋንቋዎች የተዘጋጁ መጽሐፍትን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ማበርከታቸውን አንስተዋል።

"ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ አንድ ቀን እዚህ ያለን ሁላችንም እንሞታለን" በቅዳሴ ላይ ሳሉ መስቀል ወድቆባቸው የሞቱት ቄስ የስብከታቸው የመጨረሻ ቃል። ቄሱ በስብከታቸው ምዕመኑ ከእግዚአብሔር እና
"ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ አንድ ቀን እዚህ ያለን ሁላችንም እንሞታለን" በቅዳሴ ላይ ሳሉ መስቀል ወድቆባቸው የሞቱት ቄስ የስብከታቸው የመጨረሻ ቃል። ቄሱ በስብከታቸው ምዕመኑ ከእግዚአብሔር እና በዙሪያው ካሉ ሰዎች ጋር ያለውን ትስስር እንዲያጠናክር መምከራቸውን የቢቢሲ ስፓኒሽ ቋንቋ አልግሎት ቢቢሲ ሙንዶ መዘገቡን ጠቅሶ ቢቢሲ አማረኛ አስነብቧል። "አንዳንድ ጊዜ ብዙ ትርጉም በሌላቸው ነገሮች ላይ የምናጠፋው ጊዜ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ከምናሳልፈው ጊዜ እኩል አይሆንም። ለእግዚአብሔር፣ ለወንድሞቻችን እና እህቶቻችን፣ ለባሎቻችን እና ሚስቶቻችን፣ ለልጆቻችን እና ለቤተሰቦቻችን የምንሰጠው መልካም ጊዜ ከሁሉ የተሻለ ነው" ብለው አክለዋል። ስብከታቸውን ከጨረሱ በኋላ ቄሱ ወደ መሠዊያው ተመልሰው ቀጣይ የቅዳሴውን የምልጃ ክፍል ጀመሩ። ሆኖም አደጋው የተከሰተው ስብከታቸው ከተጠናቀቀ ከሁለት ደቂቃዎች በኋላ ነበር።

እነማን ናችሁ? እግዚአብሔር በቃሉ ይሞግተናል። ዛዶክ ፐርዝ ላይ ገብታችሁ ከወንድማችን ተመስገን ነጋሽ ጋር ቃሉን እንማር። 👇👇👇
እነማን ናችሁ? እግዚአብሔር በቃሉ ይሞግተናል። ዛዶክ ፐርዝ ላይ ገብታችሁ ከወንድማችን ተመስገን ነጋሽ ጋር ቃሉን እንማር። 👇👇👇

ነገ ሁላችንም ቤተ ክርስቲያን ያለ ፍርሃት እና በሰላም እንሂድ! የጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ #ጋምቤላ ከሳምንት በፊት ያጋጠመውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ የአካባቢው መንግስት እግዶችን መጣሉ ይታወሳል።
ነገ ሁላችንም ቤተ ክርስቲያን ያለ ፍርሃት እና በሰላም እንሂድ! የጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ #ጋምቤላ ከሳምንት በፊት ያጋጠመውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ የአካባቢው መንግስት እግዶችን መጣሉ ይታወሳል። በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ፣ የምስራቅ ጋምቤላ ቤተል ሲኖዶስ ፕሬዚደንት የሆኑት ቄስ ግኒግዎ ኦሞድ ምሽቱን በፌስቡክ ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። ቄስ ግኒግዎ ለሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ምዕመናን እና መሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ነገ እሁድ ጥቅምት 8/2018 ዓ.ም. ያለ ፍርሃት እና በሰላም ጌታችንን ተሰብስበን እናምልክ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፌስቡክ ላይ ባሰፈሩት ልጥፍ “"ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? ችግር ነው ወይስ ሥቃይ፣ ወይስ ስደት፣ ወይስ ረሀብ፣ ወይስ ዕራቍትነት፣ ወይስ አደጋ ወይስ ሰይፍ?... ማንም አይለየንም! (ሮሜ 8:35-37).” እና “ጌታ ሰላሙን በምድራችን ላይ ያብዛልን!” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ቄስ ግኒግዎ ኦሞድ የሲኖዶሱ ፕሬዚደንት ሲሆኑ፣ በተጨማሪ የጋምቤላ ክልል ሃይማኖት ተቋማት ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን ያገለግላሉ። በኦቦሌሳ አዶላ

ሁለት ፓስተሮች የሞት ዛቻ (ማስፈራሪያ) እየደረሰባቸው ነው። #SouthSudan በደቡብ ሱዳን ጁባ አቅራቢያ በሚገኘው Gorom የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የሚኖሩ ሁለት የሱዳን ፓስተሮች ከወራት በፊት
ሁለት ፓስተሮች የሞት ዛቻ (ማስፈራሪያ) እየደረሰባቸው ነው። #SouthSudan በደቡብ ሱዳን ጁባ አቅራቢያ በሚገኘው Gorom የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የሚኖሩ ሁለት የሱዳን ፓስተሮች ከወራት በፊት ከተፈጸመ ጥቃት በኋላ የሞት ዛቻ እየደረሰባቸው መሆኑን Morning Star News አስነበበ። ዘገባው እንደገልጸው ፓስተር ድሪጅ ሃሩን በሜይ 2026 በቤተ ክርስቲያናቸው አካባቢ በተፈጸመ ጥቃት እግራቸው ተጎድቷል። ከዚያ በኋላ በሴፕቴምበር 25 ምሽት አንድ አጠራጣሪ ሰው ከቤታቸው ውጭ ለ30 ደቂቃ ያህል ከቆየ በኋላ ፓስተሩ ለፖሊስ ሪፖርት አደረጉ። ፖሊስም ሰውየውን እንዳሰረ ተዘግቧል። ሁለተኛው ፓስተር አዴል ኢድሪስ ይባላሉ። ሁለቱም በዳርፉር ክርስቲያን ምክር ቤት )(Darfur Christian Council) የአመራር ሥራ የሚሳተፉ ሲሆን ከዚህ በፊትም ዛቻ እንደደረሰባቸው ተገልጿል። ከሱዳን ዳርፉር ክልል የተሰደዱ አንዳንድ ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት ጫናና ጥላቻ እንደሚደርስባቸው ዘገባው ይጠቅሳል። በመጠለያው የሚገኙ የቤተክርስቲያን መሪዎችም የክርስቲያኖች ደኅንነት እንዲጠበቅና ለስደተኞቹ የመሠረታዊ አገልግሎት ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ እያቀረቡ ነው። በሌላ በኩል የGorom መጠለያ ከተቋቋመለት አቅም በላይ ሕዝብ ስለያዘ የምግብ፣ የውኃና የጤና አገልግሎት እጥረት አለበት ሲል Morning Star News አስነብቧል። ምንም እንኳን ደቡብ ሱዳን ካሏት ሕዝብ 60 በመቶ የሚሆኑት ክርስቲያኖች ቢሆን በአከባቢው ያለው ጦርነት ለክርስቲያኖች ፈተና እንደሆነ ሌሎች ዘገባዎች ያሳያሉ። በዮሐንስ ግርማ

ስለኔና ስለ አንተ ሰው ተሰቅሏል ☦️ ☦️ ☦️ በZadok Perth International Ministry እየተዘጋጀ በወንድም ተመስገን ነጋሽ በZadok Perth Youtube የሚቀርብ ተከታታይ የመጽሃፍ ቅዱስ ትምህርት Zadok Perth የዩቱብ ቻናል subscribe ያድርጉ።

ከ9 ወር እስር የተፈታው ቻይናዊ ፓስተር የ2026 የላንቶስ የሰብዓዊ መብት ሽልማት ተቀባይ ሆኖ ተመረጠ። በቻይና ለ9ወር ገደማ ታስሮ የቆየው ፓስተር ኤዝራ ጂን (Ezra Jin) የ2026 የላንቶስ
ከ9 ወር እስር የተፈታው ቻይናዊ ፓስተር የ2026 የላንቶስ የሰብዓዊ መብት ሽልማት ተቀባይ ሆኖ ተመረጠ። በቻይና ለ9ወር ገደማ ታስሮ የቆየው ፓስተር ኤዝራ ጂን (Ezra Jin) የ2026 የላንቶስ የሰብዓዊ መብት ሽልማት ተቀባይ ሆኖ መመረጡ ተገለጸ። ሽልማቱን የሚሰጠው የላንቶስ የሰብዓዊ መብትና ፍትሕ ፋውንዴሽን ሲሆን፣ ለፓስተሩ እውቅና የተሰጠው ሃይማኖታዊ ነፃነትን ለመጠበቅ ላደረገው ጥረት ነው። ፓስተር ኤዝራ ጂን በቤጂንግ የሚገኘውን የጽዮን ቤተክርስቲያን (Zion Church) የሚመሩ ሲሆን፣ ቤተክርስቲያኒቱ በቻይና ከሚገኙ ትላልቅ ያልተመዘገቡ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያናት መካከል አንዷ ነች። ፓስተሩ በጥቅምት 2025 ከቤተ ክርስቲያኑ ሌሎች አባላት ጋር በተያያዘ የእስር ዘመቻ ተይዘው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በኋላም በጁላይ 2026 ከእስር ተፈትተዋል። የላንቶስ ፋውንዴሽን እንደገለጸው ፓስተሩ በእስርና በመንግሥታዊ ጫና ውስጥ ቢቆዩም ለሃይማኖት ነፃነት መብት የሚያደርጉትን ጥረት ቀጥለዋል። ከእስር ከተፈቱ በኋላም በቻይና ታስረው የሚገኙ ሌሎች 8 የቤተ ክርስቲያኑ አባላት እንዲፈቱ ዘመቻ እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል። የላንቶስ የሰብዓዊ መብት ሽልማት በአሜሪካዊው ቶም ላንቶስ (Tom Lantos) ስም የተሰየመ ሲሆን ሽልማቱ በዓለም ዙሪያ ለሰብዓዊ መብቶችና ለሰው ክብር ለሚታገሉ ግለሰቦች እውቅና ለመስጠት የሚሰጥ የሽልማት አይነት ነው። የ2026 የሽልማቱ ሥነ-ሥርዓት በፈረንጆቹ ታህሳስ 10 2026 በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚካሄድ ይጠበቃል። የላንቶስ የሰብዓዊ መብት ሽልማትን ከፈረንጆቹ 2009 ጀመሮ የቀድሞዋ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን (Hillary Clinton) ጨምሮ በርካታ የሰብዓዊ መብት ተማጋቾች ሽልማቱን ወስደዋል። በዮሐንስ ግርማ

#መጽሀፍ ማንበብ ለምትወዱ ግብዣ አለን። በቄስ Befkadu Borena ተጽፎ የተዘጋጀው "ዲያቴኬ" የተሰኘው መጽሐፍ የፊታችን ጥቅምት 16 ሰኞ ቀን በሃልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን መሪዎች
#መጽሀፍ ማንበብ ለምትወዱ ግብዣ አለን። በቄስ Befkadu Borena ተጽፎ የተዘጋጀው "ዲያቴኬ" የተሰኘው መጽሐፍ የፊታችን ጥቅምት 16 ሰኞ ቀን በሃልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይመቀቃል። ሁላችሁም ቤተሰቦች በመገኘት አብረን ጌታን እናመስግን እና መጽሐፉን እንድንመርቅ ግብዣችን ነው። ቀን፦ ጥቅምት 16/2019ዓ.ም ቦታ፡ ሀልዎት አማኑኤል ሕብረት ቤ/ክ (ጎርጎርዮስ አደባባይ) አከባቢ ሰዓት፦ 10:30 ከሰዓት

#አዲስ የጎርፍና የመሬት ናዳ አደጋ በኔፓል በድጋሜ ተከሰተ። ከዚህ ቀደም 20 ቤተክርስቲያናት በጎርፍ ተወስደዋል። በኔፓል ጎርካ ወረዳ ጋንዳኪ ወንዝ ላይ በኦክቶበር 11 የተከሰተ ድንገተኛ ጎርፍ በ
#አዲስ የጎርፍና የመሬት ናዳ አደጋ በኔፓል በድጋሜ ተከሰተ። ከዚህ ቀደም 20 ቤተክርስቲያናት በጎርፍ ተወስደዋል። በኔፓል ጎርካ ወረዳ ጋንዳኪ ወንዝ ላይ በኦክቶበር 11 የተከሰተ ድንገተኛ ጎርፍ በርካታ ቤቶችንና ድልድዮችን አውድሟል። አደጋው በመሬት ናዳ የተዘጋው ወንዝ በድንገት መከፈቱ ምክንያት እንደተከሰተ ይገመታል። በትላንትናው እለት በኦክቶበር 12 የወጡ ዘገባዎች ቢያንስ 5 ሰዎች እንደጠፉና ከ300 በላይ ሰዎች ከአደጋው አካባቢ እንደተፈናቀሉ ተዘግቧል። በኔፓል ከዚህ ቀደም በኦገስት 26 በኔፓልና በቻይና ድንበር አካባቢ ከተከሰተው አስከፊ የጎርፍ አደጋ በኋላ ይህ በሀገሪቱ ለ2ኛ ጊዜ የተከሰተ ነው። በChristian Solidarity International ዘገባ መሰረት በዚያ ቀደም በደረሰው አደጋ ቢያንስ 20 ቤተክርስቲያናት ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን ከ80 በላይ ክርስቲያኖች እስካሁን የደረሱበት ያልታወቀ ሲሆን ከ30 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል ተብሏል። በሌላ ዘገባ፣ የኔፓል የክርስቲያን ማኅበረሰቦች አባላት ቤቶች መውደማቸውና ፓስተሮችን ጨምሮ በርካታ ክርስቲያኖች መጥፋታቸው ተገልጿል። የአደጋው ሙሉ የክርስቲያን ተጎጂዎች ቁጥር ግን አሁንም በሙሉ አልተረጋገጠም። በኦገስት 26፣ 2026 የተከሰተው ከፍተኛ የበረዶ ተራራ መደርመስ ያስከተለው ጎርፍ ከ1,400 በላይ ሰዎችን እንደገደለ ይታወሳል። ለዚህ ዘገባ Reuters፣ Associated Press፣ Christian Solidarity International ተጠቅመናል። በዮሐንስ ግርማ

"ቴክኖስቲያን" አዲስ መፅሃፍ በቄስ አሸናፊ ብሩ ጥቅምት 15፡ በካዛንቺስ ዑራኤል መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ በድምቀት ይመረቃ። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
"ቴክኖስቲያን" አዲስ መፅሃፍ በቄስ አሸናፊ ብሩ ጥቅምት 15፡ በካዛንቺስ ዑራኤል መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ በድምቀት ይመረቃ። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

የዩክሬን የወንጌል አማኝ ቤተክርስቲያናት የ2026 የ “Hope Award” ሽልማት አገኙ። በዩክሬን የሚገኙ የወንጌል አማኝ (ፕሮቴስታንት) ቤተክርስቲያናት፣ በሩሲያ–ዩክሬን ጦርነት ወቅት ለሲቪል ሰዎ
የዩክሬን የወንጌል አማኝ ቤተክርስቲያናት የ2026 የ “Hope Award” ሽልማት አገኙ። በዩክሬን የሚገኙ የወንጌል አማኝ (ፕሮቴስታንት) ቤተክርስቲያናት፣ በሩሲያ–ዩክሬን ጦርነት ወቅት ለሲቪል ሰዎች ያደረጉትን የሰብአዊ እርዳታ፣ የእምነት ጽናትና በችግር ውስጥ ያሳዩትን አንድነት በማክበር የ2026 Hope Award (የተስፋ ሽልማት) ተሸልመዋል። ሽልማቱን በአልባኒያ በተካሄደው Hope for Europe 2026 ጉባኤ ላይ የአውሮፓ ወንጌላዉያን ሕብረት (European Evangelical Alliance) አቅርቧል። ሽልማቱን በዩክሬን የፕሮቴስታንት ወንጌላዉያን ቤተክርስቲያናት ምክር ቤት ስም የተቀበሉት ዋና ጸሐፊው ፓስተር ኢጎር ባንዱራ (Igor Bandura) ናቸው። የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ በሚሰማበት ጊዜ የአንዳንድ ቤተክርስቲያናት ምድር ቤቶች ለሲቪል ሰዎች መጠለያ ሆነዋል። የቤተክርስቲያን ሕንፃዎችም ምግብ፣ መድኃኒትና ጀነሬተር ለማከማቸት እና ለማሰራጨት አገልግለዋል። የወጣቶች ቡድኖች በበጎ ፈቃድ እርዳታ ሰጪዎች ሆነው ተንቀሳቅሰዋል። አንዳንድ አማኞችና ፓስተሮችም መሸሽ ያልቻሉ አረጋውያንን፣ በፍርሃት ውስጥ የነበሩ ሰዎችንና የወታደሮችን ቤተሰቦች ለመርዳት ቆይተዋል። በዚህ ዉስጥ አንዳንድ ፓስተሮችም ሕይወታቸውን አጥተዋል። በዚህ ጦርነት ወቅት ባፕቲስት፣ ፔንጤቆስጤ፣ ሉተራን፣ ሪፎርምድ፣ አድቬንቲስትና ሌሎች የፕሮቴስታንት አማኞች በጋራ ለሰዎች እርዳታ በመስጠትና ለሰላም በመጸለይ መተባበራቸው ተገልጿል። በዮሐንስ ግርማ

ሰላም የልጆች መደር 40ኛ አመቱን አከበረ ሰላም የልጆች መንደር ባለፉት 4 አስርት አመታት የብዙዎችን ሂወት ሲለውጥ ቆይቷል። ይሄንንም ጉዞውን በማስመልከት 40 አመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ መር
ሰላም የልጆች መደር 40ኛ አመቱን አከበረ ሰላም የልጆች መንደር ባለፉት 4 አስርት አመታት የብዙዎችን ሂወት ሲለውጥ ቆይቷል። ይሄንንም ጉዞውን በማስመልከት 40 አመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል። በትናንትናው እለት ታላክ የመክፈቻ ፕሮግራም እና ታሪካዊ የኢግዚቢሽን ፕሮግራም፣ ዘላቂ የማህበረሰብ ልማት ላይ ሰፊ ውይይት፣ በሸኖ ከተማ የተገነባውን የልጆች ማቆያ ምርቃት እና ተቋሙን በጽኑ ለማስቀጠል የሚውል የባለ 7 ወለል ህንጻ ግንባታ ይፋ ማድረግ ከተካሄዱት መርሃግብሮች መካከል ነው። በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ ወሰን መንገድ ላይ ከ አራት ሺህ በላይ ሰዎችን ያሳተፈ፣ የ7 ኪ.ሜ የእግር ጉዞ ተካሂዷል። ሰላም የልጆች መንደር በ1979 ዓ.ም በወቅት በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ እርዳታ ከስዊድን አገር ለማምጣት በመጡት እትዬ ጸሃይ ሮሽሊ የተጀመረ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው። ተቋሙ በሺዎች የሚቆጠሩ ልጆችን ከጎዳና በማንሳት እልፎችን ማብቃት የቻለ ነው። በኦቦሌሳ አዶላ

"ጉዞ #መልካም ወጣት በጅማ" "ጉዞ #መልካም #ወጣት" በሚል መሪ ቃል የሚከወነው መረሃ ግብር የመጀመሪያ ጉዙውን በዚህ ሳምንት ጥቅምት 6,7,8 በጅማ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ይካሄዳል። በቀጣይ 10
"ጉዞ #መልካም ወጣት በጅማ" "ጉዞ #መልካም #ወጣት" በሚል መሪ ቃል የሚከወነው መረሃ ግብር የመጀመሪያ ጉዙውን በዚህ ሳምንት ጥቅምት 6,7,8 በጅማ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ይካሄዳል። በቀጣይ 10 ወራት በጅማ፣ ቦንጋ፣ ቡታ ጅራ፣ ባስኬቶ፣ ዳውሮ፣ ጅጅጋ፣ ጊዶሌ፣ ሻኪሶ፣ ሳውላ፣ ቡሌ ሆራ እና ሌሎች ከተሞች ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ጉዞ ያደርጋል። የዚህ ጉዞ ዋና አላማ 15ሺህ ሰዎችን ማስተናገር የሚችለው የአምልኮ አዳራሽ እና የመልካም ወጣት ስልጠና ማዕከል የማጠቃለያ ስራዎች ለመስራት የሚያስችል ገቢ ማሰባሰቢያ እንደሆነ የቤተክርስቲያኒቱ መረጃ ይጠቁማል። በዚህ መሰረት የመጀመሪያ ጉዞ በጅማ በዚህ ሳምንት የሚከናወን ሲሆን የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን መሪ የሆኑት አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ እና ሌሎች ተጋባዥ አገልጋዮች እንደሚያገለግሉ ይጠበቃል። #Christian #newsfeed #NewsUpdate

ለ14.4 ሚሊዮን አፍሪካውያን የሚሆን #አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ተዘጋጀ። የትርጉሙ ተጠቃሚዎች በዋናነት በማላዊ (Malawi)፣ ዛምቢያ (Zambia)፣ ሞዛምቢክ (Mozambique) እና በአካባ
ለ14.4 ሚሊዮን አፍሪካውያን የሚሆን #አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ተዘጋጀ። የትርጉሙ ተጠቃሚዎች በዋናነት በማላዊ (Malawi)፣ ዛምቢያ (Zambia)፣ ሞዛምቢክ (Mozambique) እና በአካባቢው ባሉ ሌሎች አገራት የሚኖሩ የቺቼዋ ቋንቋ ተናጋሪዎች ሲሆን ይህንን ስራ የመሩት Trinitarian Bible Society (TBS) ከFree Grace Evangelistic Association (FGEA) ጋር በመተባበር እንደሆነ ዘገባዎች አስነብበዋል። ፕሮጀክቱ በፈረንጆቹ 2015 ተጀምሮ ለ11 ዓመታት የተካሄደ ሲሆን አዲስ ኪዳን በ2020 ታትሞ ነበር፤ ሙሉ መጽሐፍ ቅዱሱ በጁላይ 28፣ 2026 መጠናቀቁን TBS አስታውቋል። የታተሙ መጽሐፍ ቅዱሶች ከዲሴምበር 2026 ጀምሮ ወደ ማላዊ መድረስ እንደሚጠበቅ TBS የገለጸ ሲሆን ይህ የታተሙ ቅጂዎች መድረሻ የታቀደበት ጊዜ ነው እንጂ ሁሉም ቅጂዎች አስቀድመው ተሰራጭተዋል ማለት አይደለም ሲል አክሏል። TBS እንደገለጸው፣ በቀድሞዎቹ የቺቼዋ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ላይ አንዳንድ የጽሑፍ እና የትርጉም ልዩነቶች ስጋት የነበሩ ሲሆን ድርጅቱ አዲሱን ትርጉም የጀመረው በተለይ ከኪንግ ጀምስ ቨርዥን (KJV) እና ከተቀባይ የግሪክ ጽሑፍ (Received Text) ጋር በማነጻጸር ትርጉሙ ትክክለኛ እንዲሆን በማሰብ እንደሆነ ተናግረዋል። #አሁን ተተርጉሞ የተጠናቀቀ ይህ መጽሀፍ ቅዱስ ከ14 ሚሊዮን በላይ የቋንቋው ተናጋሪዎች እንዳሉ ቢነገርም ሙሉ ትርጉሙን ለማሰራጨት የታቀደው በ2027 መጀመሪያ ላይ ነው። ሕትመት እና ስርጭት እስኪጠናቀቅ ሁሉም ጋር ተደራሽ ይሆናል ማለትም አይደለም። በዋናነት እንደዚህ አይነት ስራዎች ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በሚናገሩትና በሚረዱት ቋንቋ ማንበብ እንዲችሉ ያግዛል። በሀገራችን ውስጥ ያልተተረጎመ ቋንቋ አለ ብላችሁ ታስባላችሁ ?

አልገባም! | ክፍል 2 🏠 🏠 🏠 ዛዶግ ፐርዝ የመጽሃፍ #ቅዱስ ትምህርት ጊዜ በZadok Perth International Ministry እየተዘጋጀ በወንድም ተመስገን ነጋሽ በZadok Perth Youtube የሚቀርብ ተከታታይ የመጽሃፍ ቅዱስ ትምህርት ሙሉ ትምህርቱን ኮሜንት ስር ያገኙታል።