cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

The Christian News

ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት። @TCNEW

Show more
Advertising posts
4 856
Subscribers
-224 hours
-17 days
+17830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በ18 አመቴ ሀኪም ትሞታለህ እንጅ አትተርፍም ከሆስፒታል ውጣ አለኝ። #እኔ ደግሞ #ዛሬ በ78 ዓመቴ ኢየሱስ ያድናል እላለሁ! ዶ/ር ቤተ መንግስቱ ስንመለከታቸዉ እረጋ ያሉ በአገልግሎት ከኬኒያ እስከ አሜሪካ ከአሜሪካ እስከ ኢትዮጵያ የጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ምስረታ ቀዳሚ የነበሩ። ዶ / ር ቤተ መንግስቱ በአሁኑ ሰዓት በተልይ "አፍሪካ ተነሺ" በሚል አለም አቀፋዊ ጉባኤ የምትታወቀዉን የቤዛ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን እየመሩ ይገኛሉ።
Show all...
🔥 15👍 5 4👏 1
Show all...
ደም አስተፋኝ ነቢይት ዮዲት ተስፋዬ #berhantube #paradigmshift

አዘጋጅ : #ዮሴፍ መኳንንት contact : +251 946 745 905 በብርሃን ቲዩብ የሚለቀቁ እንደነዚ ያሉ ምስክርነቶች ብዙ ሰዎች ጋር እንዲደርስ Share, Like, Subscriber በማድረግ አብረን ወንጌልን እናገልግል። PARADIGM SHIFT # Love that tested death #christiantube #Testimony #PARADIGM SHIFT #ምስጋና #ሞት #YidenekachewTeka #berekettesfaye #ኢየሱስ_ክርስቶስ #ኢየሱስ #berhan #encounter #new_song, #babi_and_grace #Lawedeleh HagerunየPARADIGM SHIFT ቤተሰቦቻችን፤ በብርሃን ቲዩብ የሚለቀቁ እንደነዚ ያሉ ምስክርነቶች ብዙ ሰዎች ጋር እንዲደርስ ካሰባቹ Share, Like, በማድረግ አብረን ወንጌልን እናገልግል። For more information Ethiopian +251 946 745 905 / +251 924 346 435Telegram: - +251 900 302 057 / +251 924 346 435Whats Up :- +251 946 745 905 @abenezerfikruandtsegadanie62 @ebstvWorldwide @-haddiszema @seifuonebs @marakiweg2023 @ComedianEshetuOFFICIAL @TeddyTadesseOFFICIALChannel @mikurabmedia2572 @yonatanakliluofficial @MARSILTVWORLDWIDE @prophethenokgirmajpstvworl8083 @propheteyuchufaamharic @abelbirhanu3world @MinewShewaTube @daniel64813 @BereketTesfayeOffical @realityshow7187 @FrieDagiFamily

👍 4 2🔥 1👏 1
#ሬማ በድምቀት #ተመረቀ ለዝማሬ አገልግሎት ከፍተኛ አሶተዋፅኦ የሚሰጥ ሬማ ሪከርዲንግ ስቱዲዮ ሚያዚያ 12 ቀን 2016ዓ/ም ተመርቆ ለአገልግሎት በቃ። የስቱዲዮዉ ባለቤት ሙዚቀኛ ዳዊት ወርቁ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ለረዥም አመታት ያገለገለ #ወጣት አገልጋይ ሲሆን ሬማ ሪከርዲንግ ስቱዲዮ ለትርፍ ያልተቋቋመ እና በዋነኝነት ተማሪዎችን እና የዝማሬ ፀጋ ያላቸዉን ለማገልገል የተዘጋጀ መሆኑን ገልፃል። በምረቃ ስነስረአቱ ላይ ስቱዲዮዉን በፀሎት የመረቁት አፖስትል ብስራት ብዙአየን(ጃፒ) “አሁንም ቤተክርስቲያን ለሙዚቀኞች ትኩረት ልትሰጥ ይገባል የቤተክርስቲያን ሙዚቃ የአለምን ሙዚቃ መዋጥ አለበት” ሲሉ ተናግረዋል። The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለወንድማችን ሙዚቀኛ ዳዊት የተሰማን ደስታ እንገልፃለን።
Show all...
👍 27 6🔥 2👏 2🥰 1
#አፍሪካ አፍሪካ ባለፉት 150 አመታት በርካታ ክርስቲያናት ያሉባት አህጉር ሆናለች። በ1900 #ላይ በአለም ካለው #ክርስቲያን 82 በመቶው፣ በሰሜን የአለም ክፍል፣ አውሮፓ እና #አሜሪካ ይገኝ ነበረ። በተቃራኒው ደቡባዊ የአለም ክፍል አፍሪካ፣ እስያና ላቲን አሜሪካ ደግሞ 18 በመቶ ብቻ ነበረ። #አንድ #መቶ አመታትን #ወደ ፊት፣ ሰሜኑ አለም 33 በመቶው #ብቻ ክርስቲያን ሲሆን፣ ደቡቡ የአለም ክፍል ደግሞ 67 በመቶ ክርስቲያን ነው። በጋና አክራ፣ በተካሄደ አለም አቀፍ የክርስቲያኖች ፎረም፣ በአለም ላይ የክርስትና ህዝብ ነክ ቁጥር ትልቅ ለውጥ ማሳየቱ ተነስቷል። ከኤፕሪል 16-20 በነበረው በዚህ ፎረም ከ60 የተለያዩ ሃገራት የተወጣጡ ከ240 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። በዚህ ለውጥ ውስጥ ሴቶች ያላቸው ሚና እጅግ ታላቅ ነው ተብሏል። ወደፊት በተቀመጠ ትንበያ መሰረት ደግሞ በ2050፣ 77 በመቶ ክርስቲያኖች በደቡቡ የአለም ክፍል የሚኖሩ ይሆናል። እነዚህ የአሃዝ ለውጦችና ትንበያዎች ወደፊት የክርስትና ማዕከል የትኛው የአለም ክፍል እንደሚሆን ያሳያል ተብሏል። ለአብነት በአውሮፓና አሜሪካ የክርስትና ቁጥር በፍጥነት እየቀነሰ ሲሆን፣ በተቃራኒው በአፍሪካና እስያ ደግሞ በፍጥነት እያደገ
Show all...
👍 11 4🔥 2🥰 1
ፓስተር ጻድቁ አብዶ አድዋ 00 ስለሚካሄደው ስብሰባ መግለጫ ሰጡ! የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ለ5300 የቤ/ክ መሪዎች ከሚያዝያ15-17 በአድዋ 00 ሙዚየም አዳራሽ ውስጥ ነው ስልጠናው የሚሰጠው። ስልጠናው "የወንጌል ተልዕኮና የእርቅ መንገድ ለኢትዮጵያ ቤ/ክ" በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል። ሮሜ 14ን መሰረት አድርጎ፡ ሰላምና እርቅ፡ ወንጌል ተልዕኮ፡ መንፈሳዊ ስምረት እና ጽኑ አመራርነት ላይ ትኩረት ያደርጋል ብለዋል የህብረቱ ስነ መለኮት መምሪያ ሃላፊ ፓስተር ደረጀ። የስልጠናው ወጪ ከአባል ቤተ እምነት እና ሚኒስትሪዎች በተገኘ ድጋፍ ነው የተሸፈነው። በስፍራው ምዝገባ ያደረጉ ሰዎች ብቻ መገኘት የሚችሉ መሆኑ በመግለጫ ተነስቷል። ህብረቱ በቀጣይ 10 ዓመታት መንፈሳዊ ተሃድሶ፡ መንፈሳዊ መነቃቃትና እርቅና ተሃድሶ የትኩረት አቅጣጫዎቹ ናቸው። ከዚህ ቀደም ህብረቱ መሰል ስልጠና በኤልያና ሆቴልና ሚሊኒየም አዳራሽ መሰጠቱ ይታወሳል።
Show all...
👍 22 5🔥 1
#አስደሳች #ዜና ካህን #የክርስቲያን ባዛር ሊደረግ ነው። በመልህቅ ፕሮዳክሽን እና ኢቨንት አዘጋጅነት "ካህን" የተሰኘ እና ጀማሪ እና መካከለኛ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ #ክርስቲያን ነጋዴዎች የሚሳተፉበት የክርስቲያን ባዛር ሊካሄድ ነው። ሚያዝያ 12/2016ዓ.ም ቅዳሜ በሚደረገው ፕሮግራም ላይ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፤ ታዋቂ የኪነ ጥበብ ሰዎች ፤ ወጣት እና አንጋፋ ዘማሪዎች በክብር እንግድነት ተገኝተው በድምቀት እንደሚከፍቱት አዘጋጆቹ አሳውቀዋል። በመረሃ ግብሩ የክርስቲያን ባዛር የአምልኮ #ጊዜ የተለያዩ ጨዋታዎች የሚዲያ ሽፋን እንዲሁም ለክርስቲያን ቲክቶከሮች ማበረታቻ የሚሰጥበት ጊዜ እንደሚኖር ታውቋል። #ቦታ ብሔራዊ ትያትርን ተሻግሮ በከተማና ልማት አዳራሽ ከማለዳው 2:30 ጀምሮ እስከ ምሽት 2:00ሰዓት ይከወናል። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። ይጎብኙ ፤ ይሸምቱ ፤ አብረውን ያምልኩ።
Show all...
👍 11 7🔥 4🥰 1👏 1
#የወንጌል ዘመቻ ሊካሄድ ነዉ። ጋፕስ አለም አቀፍ አገልግሎት አንጾኪያ የወንጌል እንቅስቃሴ ጋፕስ ያለፉትን 14 ዓመታት የአገልጋዮችን የኑሮ ክፍተት መሙላት፡ የመንፈሳዊ ክፍተት (ማጎልበት፡ ማስተማር) ላይ ሲሰራ ቆይቷል። አንጾኪያ የወንጌል እንቅስቃሴ የ10 ቀናት የወንጌል ዘመቻ በነገው እለት ጀምሮ ከሚያዝያ 9-19 ድረስ ይካሄዳል። ዘመቻው፡ የቡና #ሻይ ሰዓትን ለወንጌል፡ ሙስሊም ኢቫንጀሊዝም፡ የደም ልገሳ፡ የጎዳና ወንጌል፡ #አንድ #ሰው ለኢየሱስ፡ ማህበራዊ ሚድያን ከወንጌል፡ አርትን ለወንጌል፡ በመርዳት ወንጌል መስበክ፡ ሙዚቃን ለወንጌል፡ የርህራሄ አገልግሎት በዘመቻው በየእለቱ የሚሰሩ ስራዎች ናቸው። የጋፕስ ሚኒስትሪ መስራችና መሪ መጋቢ ዳንኤል ዋለልኝ ሁሉም ሰው የተልዕኮ ሰራተኛ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡ በእነዚህ 10 ቀናት ሁሉም #ክርስቲያን አንጾኪያ በሚያደርገው የወንጌል ዘመቻ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል። የክርስቲያን መገናኛ ብዙሃንም በዚህ የወንጌል ዘመቻ በትልቅ ተሳትፎ እንዲሰራ፡ የክርስቲያን ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ዘሪሁን ግርማ ጥሪ አቅርበዋል። አንጾኪያ ሙቭመንት #አዲስ የወንጌል ተኮር አገልግሎት ነው። አላማው በሐዋ ስራ 11 እንደተገለጸው፡ የአንጾኪያ ቤ/ክ የወንጌል አካሄድ መድገም ነው። The Christian News - የክርስቲያን ዜና መግለጫውን በስፍራዉ በመገኘት አሰናዳንላችሁ።
Show all...
18👍 6👏 3🔥 1🥰 1
ብፁዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል በአገልግሎት ላይ ሳሉ ጥቃት ተፈፀመባቸው በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በሚዘዋወር ስብከታቸው የሚታወቁት ብፁዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል በአገልግሎት ላይ ሳሉ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተገለጸ ! በአሦርያውያን ቤተ ክርስቲያን የአውስትራሊያ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በእንግሊዝኛ እና ዐረብኛ ቋንቋዎች በሚያስተላልፉት ስብከት የሚታወቁ ሲሆን በሲድኒ በሚገኝ አንድ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ሳሉ በአንድ ግለሰብ አማካይነት በስለት መወጋታቸው ተገልጿል። የኒው ሳውዝ ዌልስ ፖሊስም ጥቃቱን የፈፀመውን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ተናግሯል። የኒው ሳውዝ ዌልስ የአምቡላንስ አገልግሎት በዕለቱ ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት አራት ሰዎች ቆስለዋል ብሏል። ሊቀ ጳጳሱ የሕክምና እርዳታ ተደርጎላቸው በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል። በዕለቱ በሠላሳዎቹ ውስጥ ከሚገኝ ወጣት በተጨማሪ በከባድ ሁኔታ ወደ ሆስፒታል የተወሰደው በሀምሳዎቹ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሰው መኖሩንና በርካታ ቦታዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ለመገንዘብ ተችሏል። ጥቃቱን የሚያሳየው ቪዲዬ >>>>> https://vm.tiktok.com/ZMMCA7PVT/
Show all...
👍 4 2🔥 1👏 1