cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

" የብዕር ምርኮኛ "✍

«ወደ አላህ ከጠራና መልካምን ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? {ፋሲለት:33}🍁🍁 የእውቀት መዓድ ይቀላቀሉ 👇 https://t.me/joinchat/AAAAAFkQxaW5cGELvPrwRQ

Show more
Advertising posts
946Subscribers
-124 hours
-37 days
-1730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ተፈሲር ሱረቱ ኒሳዕ part 5 ሰዎች በገንዘብ ነክ ጉዳዮች እንዳይጋጩ የእያንዳንዱ ድርሻ ምን መሆን እንዳለበት ዲነል ኢስላም አስቀምጧል ፣ ከላይ የምእራፏ መጀመሪያ ላይ ስለ የቲሞች ይናገር ነበር .. ስለ መህርም ተናግሯል ፣ ውርሻ ላይ ወንድም ሴትም ባለድርሻ እንደሆኑ ተናግሯል ፣ ቀጥሎ ድርሻውን ወደ መመጠን ይገባል .. يُوصِيكُمُ اللّهُ فِي أَوْلَادِكُمْ لِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ الاُنثَيَيْنِ የአንቀፁን መጀመሪያ በጥልቀት ተመልከቱ «ዩሲኩሙሏሁ ፊአውላዲኩም» ይላል «አሏህ በልጆቻችሁ ጉዳይ አደራ ይላችኋል»። እንግዲህ ከወላጆች የበለጠ አሏህ አዛኝ ስለሆነ ወላጆች አደራ አስፈለጋቸው! “የልጆችን ነገር አደራ” ብሎ አርሀሙራሂሚን ጉዳዩን ወደሱ መለሰው። አንድ ሰው ማግኜት ያለበት ከሚመለከተው ሸክምና ሀላፊነት አንፃር ነው ። በወጭ በኩል ሴቶች እንዳይጨነቁ ነው ያደረገው ሸርዑ ሙሉለሙሉ! ለዚህም አንዳንድ ኡለሞች “ማሉል መርአቲ ናሚን” ይላሉ (የሴት ገንዘብ በባህሪው መልማት ብቻ ነው) ካላባከነችው በስተቀር ፥ የራሷንም ወጭ ባሏ ነው መሸፈን ያለበት ። ስጦታም ብታገኝ ፣ ውርስም ብታገኝ ፣ በምንም መልኩ ብታገኝ የሷን ገንዘብ እሷ በፍቃዷ ካላወጣች በስተቀር ሙሉ ለሙሉ የወጭን ሀላፊነት ወንድ አንዲሸከም ነው አሏህ ያደረገው ። አባት ከዛ ባል ከሌሉም ወንድም እንዲወጣ ነው ያደረገው ። እሷ መከራ ማየት የለባትም .. አንተ አገልጋይ ነህ ኸድም ነው በአጭሩ ። ወንዱ ሲያገባ ግን ከፍሎ ነው ፡ ተከፍሎት አይደለም ። በትዳር ሲኖር ሁሉን ወጭ የሚሸፍነው እሱ ነው ፣ የሚሸፍንለት የለም ። ኢንፋቅ የሚባል ነገር እሱን ነው የሚመለከተው ። ይሄ ጠቅለል ያለ መንዙመተል ኢስላም ነው ። አንድ ሰው ወራሽ መሆን የሚችለው ከሶስቱ አንዱ ውስጥ ከሆነ ነው ። አንደኛው መወለድ ነው ( ወላጅ ወይም ልጅ መሆን) ፣ ሌላኛው ጋብቻ ነው ፣ ሌላኛው ደግሞ ወላእ ነው ( ከባርነት ነፃ የወጣ ማለት ነው) ። የጀመረው ከልጅ ነው ፥ ብዙ ጊዜ ወላጆች ቀድመው ነው የሚሄዱትና አልፎ አልፎ ተቃራኒም አለ ግን ኖርማል ከሆነው ነገር ጀመረ ። የዚህ አያ ሰበበ ኑዙል እንዲህ ነው ፦ ሰእድ ኢብኑ ረቢዕ የተባለ ሶሃቢይ ኡሁድ ላይ ሸሂድ ሆነ ፣ ሚስቱ ወደ ረሱል ﷺ መጥታ እነዚህ የሰዕድ 2 ሴት ልጆች ናቸው ፣ አጎታቸው መጥቶ ያለውን ገንዘብ ጥርግርግ አድርጎ ወሰደባቸው (ተመልከቱ የጃሂሊያን ሁኔታ እነዚህን የቲሞች መርዳት ሲገባው የወንድሜ ገንዘብ ነው ብሎ ለሚስቲቱም ሳያስቀር ወሰደ ) እንዴት ይደረግ ብላ ጠየቀች ። ረሱልም በዚህ ጉዳይ የሚፈርደው አሏህ ነው አሉ ፣ ይህ አያ ወረደ .. ፣ የአሏህ መልክተኛ ወደ ልጆቹ አጎት ለሰዕድ ልጆች 2/3ኛውን ስጥ ብለው ላኩበት ። እንግዲህ ወራሾች ወንድና ሴት ልጆች ብቻ ከሆኑ 2/3 ኛው ለወንዱ 1/3ኛው ለሴት ስጡ ፣ ሁለትና ከሁለት በላይ ሴት ካለ ደግሞ 2/3 ኛው ለሴቶቹ ይሰጣቸዋል ፣ አንድ ሴት ብቻ ከሆነች ደግሞ ግማሽ ይሰጣታል አለና የልጆችን በዚህ ጨረሰ ። ወላጆችና የጋብቻውን በቀጣይ እናየዋለን..! https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0
Show all...
🌹ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም🌹

إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ አላህ አሸናፊ መሓሪ ነው፡፡ (📗Al Qura'an 35:28)

https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0

📘 ተጅዊድ ቁርአን የጥበቦች ሁሉ መፍለቂያ ድንቅ እና ታላቅ መለኮታዊ መጽሐፍ ሲሆን ዘላለማዊ ተአምር የሆነ ሙሉ የህይወት መመሪያ ነው። ይህን መለኮታዊ መጽሐፍ እያስተነተን ተረድተነው ለማንበብ ደግሞ ከቁርአን ጋር በሚኖረን ትስስር ልንላበሳቸው የሚገቡ ደንቦችና በስርአት ለማንበብ የሚያስችሉን ህጎች አሉ። ይህም የተጅዊድ ህግ ተብሎ ይጠራል። ለዚህም ነው አሏሁ አዘወጀል "وَرَتِّلِ الْقُرْآنَ تَرْتِيلًا" ያለን። እነዚህን ህግጋቶች ለመረዳት እንሆ በተከታዩ መፅሀፍ በአማርኛ ተዘጋጅቶልናል  ዳውንሎድ በማድረግ እንማማር ! @Islamic_picture_wallpaper @Islamic_picture_wallpaper
Show all...
ተፍሲር ሱረቱ ኒሳዕ ፥ part 4 ከአንቀፅ 7-10 የሱረቱ ኒሳዕ 7ኛው አያ መውረድ ብዙ ነገርን ቀይሯል ፣ በጃሂሊያው ማህበረሰብ ሴት ምንም አይነት ድርሻ አልነበራትም .. ምክንያቱም መውረስ የሚገባው ጠላት የሚመክት እንጂ ፈረስ ያልጋለበ ፣ በሰይፍ ያልመታ ፣ ቀስት ያልወረወረ ሰው እንዴት ብሎ ይወርሳል ይሉ ነበር ። እንደውም ሴቶችን እንደ እቃ በመቁጠርም እነሱም ይወረሱ ነበር - በጃሂሊያ ። ይህ በአረቦች ብቻ ሳይሆን በሩሞችም ፣ በፋርሶችም ዘንድ የነበረ ልማድ ነበር። ከዚህ አያ መውረድ በኋላ ግን መጠኑ ይለያይ እንጂ ሴትም ድርሻ አላት ትወርሳለች አለን ። ባለ ደርሻዎች ሲከፋፈሉ ዙሪያውን የሚታዘቡ ሰዎች ይኖራሉ ። የነሱንም ነገር በ8ኛው አያ ተናገረ ። የሀብታምን ገንዘብ ልጆቹ ፣ እህት ወንድሞቹ ወይም ወላጆቹ ቁጭ ብለው ዳጎስ ያለ ድርሻ ሲያገኙ ጎረቤት ያለ የቲም ቁጭ ብሏል ፣ ሚስኪኖች አይናቸው እየቃበዘ እኛም ቢደርሰን ብለው ይጓጓሉ ። እነዛ ሰዎች እንዳይረሱ ምንም እንኳ መጠኑ ይህን ያህል ነው ባይባልም የተወሰነ ነገር ቀነስ አድርጋችሁ ስጡ «ተገቢ ንግግርም ተናገሯቸውም» አለን ፣ ሁሌም ከአንድ ስራ በኋላ መልካም ንግግርን ጎን ለጎን ነው የሚያስቀምጠው ቁርዐን ልብ በሉ ! ንግግር ተፅኖው ከባድ ነው ፣ ጦር ካቆሰለው ንግግር ያቆሰለው ያስቸግራል አይሽርም ። እንደገና ብዙ ችግሮችን በንግግር መፍታት ይቻላል ። 9ነኛው አያ ደግሞ ውርስ የሚያከፋፍሉ ሰዎች በሆነ ሰበብ ወደ አንድ አካል እንዳያደሉ "ነግ በኔ" ይበሉ አለ። ለልጆቹ ፊውቸር የሚሰጋ ሰው በሌላ ሰው ልጅ ላይ ግፍ መስራት የለበትም። እንዲሁ ወሲያ ላይ ሟች ያልሆነ ኑዛዜ ሲናገር የሰማ እንደሆነ መከልክልም አለበት ፣ አንዳንዴ ወራሾችን መጉዳት የሚፈልግ ሰው ይኖራል ። ለፍቼ ለፍቼ ይሄ መናጢ ልጅ ሊወርሰው ነው አንዴ ገንዘቤን :) "ሰደቃ ነው የማደርገው" ሊል ይችላል፣ ለዛም ነው 1/3 ድረስ እንጂ ከዛ በላይ ሰደቃ መስጠት አይቻልም ። "አሱሉሱ ወሱሉሱ ከሲር" ብለዋል ሀቢባችን ፣ በሌላ ሀዲሳቸው ድግሞ “ወራሾችህን ራሳቸውን የቻሉ አድርገህ ጥለህ መሄድ ድሆች አድርገህ እጃቸውን ወደ ሰው የሚዘረጉ አድርጎ ከመሄድ የተሻለ ነው” ብለዋል ። 10ኛው አያ የየቲም ገንዘብ መብላት እሳት መብላት እንደሆነ ይነግረናል ። ረሱልም “የሁለት ደካማ ሰዎችን (የቲሞች እና ሴቶች) ብር ከመብላት እንድትጠነቀቁ አደራ እላችኋለሁ” ብለዋውናል። https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0
Show all...
🌹ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም🌹

إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ አላህ አሸናፊ መሓሪ ነው፡፡ (📗Al Qura'an 35:28)

https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0

የሴቶች ምዕራፍ ትንታኔ ክፍል ሶስት፥ አንቀፅ ቁጥር ⑥ ትናንት ለሰፊሆች ብር መስጠት ተገቢነት እንደሌለውና እኛ ልንጠብቅላቸው እንደሚገባ ተነጋግረናል ። ታዲያ እስከመቼ ነው የሰፊኾችን ገንዘብ እኛ እየጠበቅን ፣ እኛ እያለማን ፣ እኛ እየተንከባከብን እኛ ወጭ እየሰጠናቸው የምንኖረው? ቢባል ፤ ነፍሳቸውን አውቀው ገንዘባቸውን ማስተዳደር የሚችሉበት አቅም ላይ እስከሚደርሱ ነው ። ለዚህ ብሎ ምን አለ ፦ «ወብተሉል የታማ/የቲሞችን ፈትኗቸው» ማለት ብቃታቸውን ከዚህ በኋላ ብሩ ቢሰጠው ማስተዳደር ይችላል ወይስ አይችሉም? የሚለውን ማለት ነው። "ሀታ ኢዛ በለጙ ኒካህ" ጋብቻ እስከሚደርሱ ድረስ» በሸርዕ ደረጃ የተቀመጡ መስፈርቶች አሉ ፣ እነዛ ሲሟሉ ህፃን ከሚለው ወጥቷል ። ነገር ግን አንዳንዴ አካለ መጠን ደርሰውም የአእምሮ ብስለቱ ገና የሆነ ይኖራል ። ስለዚህ ምን አለ፦ "ፈኢን አነስቱም ሚንሁነ ሩሽደን/ ከፈተናው በኋላ ነፍስ ማወቅን ከታዘባችሁ ፣ ከተገነዘባችሁ «ፈድፈዑ ኢለይሂም አምዋለሁም/ገንዘቦቻቸውን ወደነሱ አስጠጉ»። "ሩሽድ" የሚለው በዲናቸው ላይ ጥሩ መሆናቸውንና በገንዘብ ጥበቃም ላይ ጥንቁቅ መሆናቸውን ስታውቁ ለማለት ነው ። አንዳንዴ ጎረምሳ ሆኖ ገንዘብ ሲሰጠው ወዳልሆነ አቅጣጫ የሚሄድ አለ .. ይሄ ሰው አይሰጠውም። ምክንያቱም አካሉ በስሏል አምሮው አልበሰለም። ቀደም ብሎ ባለው አያ ላይ  “አምዋለኩም/ገንዘባችሁ” እያለ ነበር አሁን ደግሞ “አምዋለሁም/ገንዘባቸው” ይለናል ፣ ያኔ እንደዛ ያለው ከብክነት ለመታደግ ነው ፣ ዛሬ ደግሞ ሰዎቹ ራሳቸውን ስለቻሉ የነሱ ብር ተብሎ ወደ ባለቤቱ ይመለስ በሚል አገላለፅ ገለፀው - የቁርአን አገላለጽ ሁሌም ድንቅ ነው። ለካ አካለ መጠን ሲደርሱ ገንዘባቸው ወደነሱ ይመለሳል። ያ ቀን ሳይደርስ በፊት ለምን ዛሬ ቀንጨብ ፣ ቀንጨብ አላደርግም የሚል ዟሊም እንዳይኖር ደግሞ "ወላ ተዕኩሉሃ ኢስራፈን" አለ በማባከን መልኩ ገንዘባቸውን እንዳትበሉ። "ወቢዳረን አን የክበሩ" ነገ አድጎ ከእጄ ከመውጣቱ በፊት ዛሬ አትበሉ ። እናንተ ባለ አደራ እንጅ ባለ ገንዘብ አይደላችሁም ። እንበልና ገንዘቡን ስንረከብ ልጁ የአንድ አመት ቢሆን አስራ አምሰት አመት በእኔ እጅ ነው ይሄ ገንዘብ ያለው ፣ ብሩን ማልማት አለብኝ ። አሁን ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ ፦ በሱ ገንዘብ ላይ ጉልበቴን ፣ ጊዜዬን ..ሳባክን የራሴን ኑሮ ትቼ እንዴት ነው የሚሆነው? የሚል ጥያቄ እንደሚመጣ ስለሚያውቅ ምን አለ « ወመን ካነ ጘኒየን ፈልየስተዕፊፍ» የየቲም ገንዘብ የሚንከባከብ ሰው ከዛ ከየቲሙ ገንዘብ ውጭ የራሱ የሆነ ገቢ ኖሮት የተብቃቃ የሆነ ሰው ለአሏህ ብሎ ይስራ .. ክፍያ ሳይጠይቅ ። ከዚህ ነገር ይጠንቀቅ ወይም ይራቅ ። ድሃ ከሆነሳ? የየቲሞችን ገንዘብ የሚያለማ ከሆነ የራሱ ስራ ሊቀር ነው ፣ የነሱን ትቶ ወደ ራሱ ስራ ከሄደ የዚህ የየቲም ገንዘብ ሊባክን ነው። እህ ምን ይሁን ታዲያ ? ... ደመወዝ ይመደብለት! «ወመን ካነ ፈቂረን ፈልየእኩል ቢልመዕሩፍ» የሚፈልገውን ያህል ሳይሆን የሚገባውን ያህል ደመወዝ ይመደብለት! ማነው የሚመድብለት? ከተባለ ያው ቤተዘመድ አለ ፣ ፍርድ ቤት ይኖራል ይህን በማስተዳደርህ ይሄ ይገባሀል ብሎ ይመድብለታል ። በዛ መልኩ መጠቀም ይችላል ። አሁንም ሌላ ጥያቄ ፦ ደሃ የሆነ የየቲም አሳዳጊ ይህን የየቲም ብር በደመወዝ መልኩ ከበላ በኋላ ሲያገኝ ይመልሳል ወይስ አይመልስም? በዚህ ላይ ፉቀሃወች ሁለት ቀውል አላቸው። የመጀመሪያው .. አነስ ያለ መጠን የችግሩን ያህል ይመገብ መመለስ አይጠበቅበትም። የላቡ ስለሆነ ሌላ ቦታ ቢሰራ ሊያገኝ የሚችለውን ነው ያገኘው ችግር የለውም የሚሉ አሉ (ሻፊኢያዎች) ምክንያታቸው ደግሞ አያው «ፈልየእኩል ቢልመዕሩፍ» ሲል "ይመልስ" አላለምና ይላሉ ። ሁለተኛው ቀውል ደግሞ የየቲም ገንዘብ በመሰረቱ ክልክል ነውና ለችግር ቢፈቀድለትም ሲያገኝ የመመለስ ግዴታ አለበት ያሉ ኡለሞችም አሉ ። ገንዘባቸውን አስረክቡ ካለ በኋላ አሁን ደግሞ ሲያስረክቡ ሞግዚቶች እንዳይበደሉ መስፈርት አስቀመጠ።ምን አለ «ፈኢዛ ደፈዕቱም ኢለይሂም አምዋለሁም» እናንተ አሳዳጊዎች የቲሞቹ አካለ መጠን ደርሰው ገንዘባቸውን ስታስረክቧቸው ዝም ብላችሁ ጠርታችሁ ና ውሰድ ሳይሆን «ፈአሽሂዱ አለይሂም/አስመስክሩባቸው » አለ ..ገንዘብ ያጨቃጭቃል ፣ የሚያናቁረውም የሚያፋቅረውም እሱ ነው ። ሙሲባ ነው ። ደግሞ ከሱ መብቃቃትም አይቻልም ። ስለዚህ የየቲሞቹን ዘመዶች አስቀምጦ ፦ የተረከብኩት ይሄ ይሄ ነበር ፣ ይህን ያህል ወጭ በማሳደግ ሂደት አውጥቻለሁ ፣ ይሄን ያህል ልማት ለምቷል ፣ በጥቅሉ ዛሬ የቀረለት ደግሞ ይሄ ነው ብሎ በምስክር ፊት ያስረክብ ይላል ። 🛑 ምስክር ከሌለ በኋላ የቲሙ ሊከዳ ይችላል ..ገንዘቤን ሲበላ ኖሮ መጨረሻ ላይ የቀረችውን እንኳ ሳያስረክበኝ ቀረ ሊል ይችላል ። አልያም አሳዳጊው ትንሽ ነገር ወርወር አድርጎ ሌላውን ለራሱ ሊያስቀር ይችላል። ሲረከብም ምስክር መኖር እንዳለበት ሁሉ ወጭዎችም በትክክል መመዝገብ አለባቸው ፣ ሲያስረክብም በምስክር ፊት ቆጥሮ ማስረከብ ይጠበቅበታል።ይሄ ህግ ነው ።በዚህ ህግ የሚኖር ማህበረሰብ ሚጨቃጨቅበት ምንም ሰበብ የለም!! ተቋጥሯል፣ ተደንግጎለታል ። አስመስክረናል ብሎ ደግሞ የሆኑ የሆኑ ነገሮችን ደብቆ ፣ አታሎ የሚሰራ ካለ ደግሞ አብሽር ፣ የሰው ምስክር ባይኖርህ እኔ አለሁ እያለ ነው (ወከፋ ቢሏሂ ሀሲባ /ሂሳብ አድራጊ በአሏህ ይብቃ) ማንኛውንም ነገር አሏህ በመዝገቡ ላይ አስቀምጦታል ስለዚህ ዛሬ አማና ያልተወጣ ሰው ነገ ረቡል አለሚን ይተሳሰበዋል። ከምስክር ሁሉ በላይ ነው አሏህ .. ይሄ ስሜት ልቡ ውስጥ ያለ ሰው ለማጭበርበር ፣ አኼራን ለመሸጥ አይጋለጥም .. ለህጉ ያህል ነገ ላለመጠየቅ ምስክሮችን ያስቀምጣል ፣ ረቡል አለሚን ፊት ደግሞ ላለመጠየቅ የራሱን ጥንቃቄ ያደርጋል ። ተቅዋ ካለ ፣ ህግ ካለ በደል የለም ። በመሰረቱ የየቲም ገንዘብን ወደማስተዳደር ሰፍ ብሎ መግባት አደጋ ነው ፣ እንደውም አፊያ የፈለገ ሰው ከመጀመሪያው ይሄ ነገር ይቅርብኝ ቢል ይሻላል ። እሱ ካልገባ ይጠፋባቸዋል ብሎ ካልሰጋ በስተቀር ..ረሱል ﷺ ለአቡዘር «ኢኒ አራከ ዶዒፋ/ አቡዘር ሆይ እንደው ሳይህ ደከም ያልክ ሰው ነህ (ገራገር ነበሩ) ፣ እኔ ደግሞ ላንተ ለራሴ የምወደውን እወድልሃለሁ (ለራሴ የምመክረውን እመክርሃለሁ እንደማለት ነው) ፦ በሁለት ሰው መካከል አሚር እንዳትሆን (ስልጣንን ሽሻት ማለት ነው) የየቲም ገንዘብ ላይም እንዳትሾም» ብለውታል ፤ መወጣቱ ከባድ ስለሆነ ማለት ነው ። https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0
Show all...
🌹ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም🌹

إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ አላህ አሸናፊ መሓሪ ነው፡፡ (📗Al Qura'an 35:28)

https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0

ሱረቱል ኒሳእ ክፍል ሁለት ይህች ምዕራፍ ወሳኝና አስፈላጊ የሆኑ ገንዘብ ነክ ጉዳዮችን በጥልቀት እና በስፋት ታስቀምጣለች ብለናል። ለዛም ነው በዝርዝር ለማየት የወሰነው وَلَا تُوْتُواْ السُّفَهَاء أَمْوَالَكُمُ «ሱፈሃዕ» የሚለው አስተሳሰቡ ደካማ ፣ ነገሮችን በመልካም ማስተባበር የማይችሉ ፣ አዕምሮው ብቁ ያልሆነ ሰውን ብር ከሰጠነው ነገን ስለማያስቡ .. እጃቸው የገባውንም መጠበቅም ሆነ ማልማት ስለማይችሉ ባልሆነ አቅጣጫ ያባክኑትና ..ገንዘቡም ጠፍቶ እነሱም ተመፅዋቾች እና ጥገኞች ይሆናሉ ። ስለዚህ ሊሰጣቸው አይገባም ነው ። "ሱፈሓዕ" ከየቲሞች አካለ መጠን ያልደረሱና ሩሽድ የሌላቸውን ወይንም ደግሞ ትልቅም ሆኖ አቅሉ ደካማ የሆነን ይመለከታል ፣ ፆታ አይለይም ። ታዲያ እነዚህን ሰዎች ከቤተዘመድ መካከል ገንዘቦቻቸውን የሚያስቀምጥላቸው ፣ በሚያስፈልጋቸው ልክ ወጭ የሚያደርግላቸው ሀላፊ ፣ ወኪል፣ ዋቢ ያፈልጋቸዋል ማለት ነው። ይህን ሲገልፅ በሚገርም መልኩ ነው ያስቀመጠው። አስተውሉ "አምዋለኩም/ገንዘቦቻችሁ" ነው ያለው ፣ ገንዘቡ የነሱ ሆኖ ሳለ ለምን የናንተ አለ ?! ይሄ ዲነል ኢስላም በገንዘብ ላይ ያለውን አጠቃላይ ፍልስፍና የሚገልፅ ነው -በአንድ ተውላጠ ስም "ኩም" በምትለው ዶሚር! ። ገንዘብ የተወሰኑ ሰዎች ንብረት ነው ተብሎ ቢመዘገብም በአጠቃላይ የማህበረሰቡም ጭምር ነው ። የግለሰቦች ብቻ አይደለም ፣ የሚያባክኑትም ከሆነ አጠቃላይ በአካባቢው የሚኖር ሰው ነው የሚጎዳው ። ስለዚህ አባካኞች እንዲያባክኑ ሊፈቀድ አይገባም ማለት ነው ። የኛ ነው ብላችሁ መጠበቅ አለባችሁ እያለን ነው ። ምክንያቱም ገንዘብ ካለ.. ልማት አለ ፣ ስራ አለ ፣ ንግድ አለ ፣ ኪራይ አለ፣ ተቀጥሮ መስራት ይገኛል  ... ቅብብሎሹ ይቀጥላል ። ገንዘብ ደግሞ የሚያድገው ቅብብሎሽ ሲኖር ነው.. አለዛ እየጠፋ ነው የሚሄደው ፣ ለሰፊህ ከሰጠኸው ባልሆነ መልኩ ያውለዋል ። አባካኞች የሰይጣን ወንድሞች ናቸው ይለናል። ቁርዓን ስለ መለገስ ያስተማረውን ያህል ስለ መቆጠብም ያስተምራል ። መቆጠብ ፣ ማልማት፣ መንከባከብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታልና እነዚህ ሰፊሆች ብሩን ካስረከብካቸው በአጭር ጊዜ ውሥጥ ብክንክን ያደርጉትና ዳግም የዚያው የማህበረሰቡ ሸክም ነው የሚሆኑት ። በባልተቤትነት አይን ማየትና መንከባከብ ይጠበቅባችኋል ማለት ነው። أَمْوَالَكُمُ الَّتِي جَعَلَ اللّهُ لَكُمْ قِيَاماً አጠቃላይ ስለ ገንዘብ ሲነግረን መቋቋሚያ አድርጎ የፈጠረላችሁ ይለናል ። በሰዎች መካከል ገንዘብ የሚለው ነገር የተፈጠረው ዱንያ ላይ ቆሞ መኖር እንዲችሉ አሏህ ስለሻ ነው ። ለልብሳቸው ፣ ለቁርሳቸው ፣ ለቤተሰቡ ፣ ለወገኑ እያካፈለ ማህበረሰቡ ቆሞ እንዲቀጥል ነው ። አሶቡል ሀያት ነው / የህይወት የደም ቧንቧ ነው - ገንዘብ ፣ እንደፈለገ መመዝበር የለበትም ። ሲመጣም አግባብነት ባለው መንገድ መከሰብ አለበት ፤ ሲወጣም ጤናማ በሆነ መልኩ ነው መውጣት ያለበት ። وَارْزُقُوهُمْ فِيهَا ገንዘቦቻቸውን ተቆጣጠሩላቸው ፣ አትስጧቸው ሲባል እንዳይበሉ ፣ እንዳይጠጡ ማለት አይደለም! ከገንዘባቸው ላይ እናንተ አቅል ያላችሁ ሞግዚቶች ሪዝቃቸውን ስጧቸው «ወክሱሁም» አልብሷቸው ። ይጠቀሙበት ፣ ይብሉ ፣ ይጠጡ ፣ ይልበሱ የሰው ጥገኛ እነዳይሆኑ ይጠበቅላቸው ። በገዛ ገንዘቤ አንተ ላየ ላይ ተሹመህ እየቆጠርክ ትሰጠኛለህ እንዴ? ብለው እንዳይከፉ ደግሞ ❝« وَقُولُواْ لَهُمْ قَوْلاً مَّعْرُوفًا / ጥሩ የሆነ ቃል ተናገሯቸው❞ አለን ። ግዴለም አንተ ልጅ ነህ ፡ አባትህ የለም የሚጠቅምህን የማውቀው እኔ ነኝ .. ላንተው መስለሃ ነው ቢቀመጥልህ ፣ ቢለማልህ ፣ ቢያድግልህ ነገ ላንተው ነው .. የመሳሰሉ ጥሩ የሆኑ ቃልም ተናገሯቸው ። ሞራልም ይጠበቅ ማለት ነው !! ፣ ገንዘብ ብቻ አይደለም! አያችሁ የኢስላም ተሽሪዕ ጥበቡ ሁሉን ነገር መጥኖ እንደሚሄድ .. ሰው መስጠት ብቻ አያስተካክለውም ። ንግግርም ፣ አቀራረብም የራሱ የሆነ ሚና አለው "ከፍትፍቱ ፊቱ" ይባል የለ ። እያበላህ ግን ክፉ የምትናገረው ወይም ክፉ ፊት የምታሳየው ከሆነ "ምነው በቀረብኝ" ይላል ፣ ለሱ ኸይር እየሰራህ ራሱ ማመናጨቅ መኖር አይገባውም ። ጥሩ በሆነ መልኩ አስተናግዱ ይለናል ... ! ለዛሬ አንዲቱን አያ ( 5ኛዋን) በጥልቀት ለማየት ሞክረናል .. በዚህ መልኩ ይቀጥል... https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0
Show all...
🌹ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም🌹

إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ አላህ አሸናፊ መሓሪ ነው፡፡ (📗Al Qura'an 35:28)

https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0

✓ ተፍሲር ሱረቱ ኒሳዕ ... ሱረቱ አለ ኢምራን የጨረሰው «ያአዩሃለዚነ አመኑ ኢስቢሩ ወሷቢሩ ወራቢጡ “ወተቁሏህ” » በማለት "አማኞችን" በማናገር ነበር ፣ ሱረቱ ኒሳዕ ደግሞ ሲጀምር ይህንኑ የተቅዋ ትዕዛዝ "ለመላ የሰው ዘሮች" በማስተላለፍ ነው «ያአዩሃናሱ ኢተቁ-ረበኩም..» ቁጥሩ ይርቃል እንጂ ዞሮ ዞሮ የሰው ልጅ ሁላ ዘመዳም መሆኑን "ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁ" በማለት ነገረን ፡ በመቀጠል "ዝምድናን ጠብቁ" ይለንና ዘመድ የሌለው እንዳይረሳ ደግሞ ስለ የቲሞች ይነግረናል። ዘመድ ነኝ በሚል የየቲም ብር እንዳይበዘበዝ "ኢነሁ ካነ ሁበን ከቢራ" በማለት የየቲም ገንዘብ መብላት ከሰባቱ ትላልቅ ሀጢአት አንዱ መሆኑን ያስታውሰናል። وَإِنْ خِفْتُمْ أَلاَّ تُقْسِطُواْ فِي الْيَتَامَى ይህን አያ ለመረዳት ለምሳሌ የሚያሳድጋት የቲም ልጅ ለጋብቻ ሀላል የሆነች የአጎትን ልጅ ምናምን ሊያሳድግ ይችላል ፣ መጨረሻ ግን እድሜዋ ሲደርስ ቆንጆ ከሆነች ወይም ለብሯ ብሎ ሌላ ሰው ከሚያገባት እኔ ላግባት ይልና መህሯን ቀነስ አድርጎ ለራሱ ያገባታል ፣ ይሄ አድሎ ነው! ካገባሃት ከሌላ ሚስትህ ጋር እኩል አድርገህ ወይም ደግሞ እሷን የሚመጥን ኑሮ ላይ ማኖር ግዴታ ነው። ይህን ማድረግ አልችልም ካልክ ግን ለገንዘቧ ፣ ለውበቷ ፣ ለዲኗ የሚፈልጋት ይኖራል .. እድሏን ትጠብቅ ፣ ገንዘቧን አስረክብ ! አንተ ማስቀረት አይፈቀድልክም ነው ። "ፈንኪሁ" ሲል ሌላ የተፈቀደላችሁን አግቡ ሁለት ፣ ሶስት ፣ አራት ተፈቅዶላችኋል ። ሺዓዎች "መስና" የሚለውን 2×2 ፡ ሩባዕ የሚለውን 4 ሲባዛ በ4 በማለት ነው የሚፈስሩት ፤ ይህ ግን በቋንቋ ደረጃም ስህተት ነው ። ለምሳሌ ስለ መላኢኮች ክንፍ ሲነግረን "መስና" ሲል እያንዳንዳቸው ሁለት ክንፍ ያላቸው ፣ "ወሱላስ" ሲል አንዱ ሶስት ሌላኛውም ሶስት ያላቸው እንጂ 3 ሲባዛ በ3 ማለት አይደለም ። እስከ 4 ተፈቅዷል ሲባል ታዲያ ፍትህ ሊኖር ግድ ነው ። ፍትህ ሲባል ...በልብሳቸው፣ በመኖሪያቸው ፣ በቀለባቸው፣ በሚደረገው ነገር ሁሉ እኩል ማድረግ አለበት! እዚች ሁለት ቀን ካደረ እዛች ሁለት ቀን ማደር ግዴታው ነው ። ወደ መንገድ ሲሄድም መጀመሪያ እጣ መጣል አለበት ፣ ሁለተኛው ግን የሌላይቱ ይመጣል በዚህ መልኩ ነው የተደነገገው ። በቁሳዊ ነገር እኩል ማድረግ ግድ ነው በተቻለ መጠን .. ነገር ግን ፍቅርን እኩል መክፈል አይቻልም ። አንዷ ዘንድ የሚያገኘውን ሌላዋ ዘንድ ካላገኘ (በባህሪዋ ፣ በውበቷ ፣ በኺድማዋ ...በተለያየ ነገር) ወደ አንዷ ልቡ ሊዘነብል ይችላል፤ ይሄ ከአቅም በላይ የሆነው አፍው ይደረጋል ። ይህን ሲያመለክት እዚሁ ሱራ 129 ላይ «በሴቶች መካከል 100% እኩል ልታደርጉ አትችሉም ጉጉት እንኳ ቢኖራችሁ ታዲያ ሙሉ ለሙሉ እንዳታዘንብሉ ተጠንቀቁ» ብሎናል ። ረሱልም ሁሉንም ነገር ያከፋፍሉና «ሀዛ ቀስሚ ፊማአምሊክ፡ፈላቱአሂዝኒ ፊማ ላአምሊክ/እኔ በምችለው ይሄ ነው የኔ አከፋፈል ፤ በማልችለው አትያዘኝ ፣ አትውቀሰኝ ጌታዬ» ይሉ ነበር ። ይህን ያህል ጥንቃቄ ካደረገ ከዛ ውጭ ያለውን አሏህ አፍው ይላል ማለት ነው ። فَإِنْ خِفْتُمْ أَلاَّ تَعْدِلُواْ فَوَاحِدَةً ❝አለማስተካከልን ብትፈሩ አንዲትን ብቻ አግቡ!❞ ሊኩሊ ሳቂጠቲን ላቂጥ / የወደቀ ሁሉ አንሺ አያጣም እንደሚባለው  ..ሁሉም ሰው ቢጤውን ፈልጎ እራሱን ኢዕፋፍ ማድረግ ያስፈልጋል። መጀመሪያ "መስና " በማለት በሁለት ነው የጀመረው .. ሸሪዓው የሰው ዘር እንዲበዛ ይፈልጋል፣ ነብዩም ﷺ ወላድና ወዳድ አግቡ "ፈኢኒ ኡካሲሩ ቢኩሙል ኡመም" ብለዋል ። ذَلِكَ أَدْنَى أَلاَّ تَعُولُواْ የሚለው ሁለት ትርጉም አለው፦ አንደኛው - ግፍ አንዳትሰሩ ፣ አድሎ ውስጥ አንዳትገቡ በአንድ ተብቃቁ እንደማለት ሲሆን ሁለተኛው ፍች ደግሞ እንዳትደኸዩ ማለትም ይሆናል ፥ ቤተሰብ ሲበዛ ከገቢህ ጋር የማይመጣጠን ከሆነ አቅምህን ያንገዳግዳልና በአንድ ተብቃቃ ተብሎም ይፈሰራል። وَاتُواْ النَّسَاء صَدُقَاتِهِنَّ نِحْلَةً "ሶዱቃ" የሚለው ቃል ሲድቅ ከሚለው ይመሰሰላል ፡ ትዳሩን ሷዲቅ የሚያደርገው መህሩ ነው በማለትም ይፈስሩታል ፣ “ኒህላ” የሚለው ግዴታ ወይም ካንተ በጎ ፈቃደኝነት ማለት ነው። ደስ እያለክ out of love ስጥ እንጂ ምን ይሄን ሸክም ቶሎ ሰጥቼ ልገላገል¡ በሚል መንፈስ አይሁን! ብዙ ሰው መጀመሪያ ላይ መህር ቃል ሲገባ አይፈራም ። ደግሞ መህርን ሙሉ ለሙሉ ዱቤ አድርገነዋል ማህበራችን ውስጥ :) አላያችሁም ለሰርጉ ብዙ ሺዎችን ያወጣና መህር ላይ ሲመጣ ወደፊት የሚከፈል ይላል፣ ወደፊት ስለሆነ ቀላል ይመስለዋል .. አንድ ቀን አብሮ ካደረ ጀምሮ በእርሱ ላይ ዋጂብ ነው። ቢሞት እንኳ ሰው ዞልሞ ነው የሚሞተው ማለት ነው። ደስ እያለው መስጠት ተገቢ ነው ፣ ሀዲያ አንደሚሰጥ ሰው (romantic gift) ያድርገው ነው ሀሳቡ ። እዳ ነው ፣ ሸክም ነው በሚል መሆን የለበትም ። ህይዎቷን ሰጥታካለች ፤ አንተም ህይወትክን ሰጥተካታል ..ገንዘብ ሊያጨቃጭቅ አይገባም ። ባይሆን ሴቷም ይቅርብኝ ካለች ወይም ከሰጣት በኋላ ይህችን ለእንዲህ አድርግባት ብላ ከሰጠችው በፍቃደኝነት ከሆነ ችግር የለውም። فَإِن طِبْنَ لَكُمْ عَن شَيْءٍ مِّنْهُ نَفْسًا فَكُلُوهُ هَنِييًا مَّرِييًا  በፈቃደኝነቷ ከሰጠችህ እኔው ሰጥቼ እኔው ልጠቀምበት? ብለህ አትሳቀቅ ፥ ተጠቀምበት take it, and enjoy it ! በመሰረቱ የሰዎቹ መፈቃቀር ነው እንጂ የሚፈለገው ገንዘቡ አይደለም .. ገንዘቡ ይመጣል ይሄዳል « አልማሉ ዚሉን ዛኢል» ይላሉ .. ብር እንደ ጥላ ነው አሁን ያንዣብባል አሁን ይጠፋል! ይቀጥላል ..! መልካም መስሎ ከታያችሁ ሸር አድርጉት ፣ በጋራ ምንዳ እናግኝ   خيركم من تعلم القرآن وعلمه  https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0
Show all...
ተፍሲር አለ ኢምራን ስድስተኛው part ... وَمُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيَّ مِنَ التَّوْرَاةِ ፦ ረሱል ﷺ "ቁርአኑን የምሺ" ( በምድር ላይ የሚሄድ ቁርአን) እንደሚባሉት ሁሉ ኢሳም "ተውራቱን የምሺ" ( በምድር ላይ የሚሄድ ተውራት) ነበር ። አላህ ተውራትን አስተምሮታል ። ይቀጥልና .. وَلاُِحِلَّ لَكُم بَعْضَ الَّذِي حُرِّمَ عَلَيْكُمْ አስተውሉ አላህ ሀራም ያደረገባችሁ አላላቸውም ። ማን ሀራም እንዳደረገው መጅሁል ነው ፣ ሊቃውንቶች ሀራም ያደረጉትን ማለቱ ነው ይላሉ አንዳንድ ሙፈሲሮች። አሏህ ሀላል ያደረገውን ለቃውንቶቹ ሀራም ያደርጉ ነበር ። የኢስራኢላውያን በሽታ አንዱ ይህ ነበር። ኢሳ አለይሂ ሰላም ከሌሎቹ የበኒ ኢስራኢል ነብዮች ከሚለይበት ነገር አንደኛው የመጨረሻው የበኒ ኢስራኢል ነብይ ነው ፣ ሌላው በነብይነቱ ጭራሽ አላመኑበትም ለምሳሌ ሙሳን ስናይ መልክተኛ መሆኑን እያወቁ ነው የሚያስቸግሩት لِمَ تُوْذُونَنِي وَقَد تَّعْلَمُونَ أَنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُمْ ❝የአላህ መልክተኛ መሆኔን እያወቃችሁ ለምን አዛ ታደርጉኛላችሁ?❞ ይላቸው ነበር ። በኢሳ ጊዜ ሀይል ያላቸው ሮማን ጣኦታውያን ነበሩ ። በነብዩም ጊዜ ሀይል ያላቸው የቁረይሽ ጣኦታውያን ነበሩ ፣ በኢሳ ጊዜ የነበሩት አይሁዶች ከሮማውያን ጋር አሲረው ኢሳን ለመግደል እንደሞከሩት በረሱል ጊዜም የነበሩት አይሁዳውያን ከቁረይሾች ጋር አሲረው ረሱልን ለመግደል ሞክረዋል ። የሁለቱን ነብያት ታሪክ ከሱራው አተራረክ ጋር ስታስተውሉት በጣም ደስ የሚል ግጥምጥሞሽ ታገኛላችሁ ... ለምሳሌ አይሁዶች ኢሳን የገደሉት መስሏቸው ነበር ፣ በዚሁ ሱራ ደግሞ የኡሁድን ዘመቻ ታሪክ እናገኛለን ፣ በዘመቻው ረሱል ﷺ የተገደሉ መስሏቸው ነበር ። የኢሳን ታሪክ ከኡሁድ ጦርነት ጋር አብሮ የነገረን ጥበብ እንደገባችሁ ተስፋ አደርጋለሁ ። ሌላው አሏህ ﷻ ኢሳን ወደ ሰማይ እንደወሰደው ረሱልንም ﷺ  በኢስራዕ ሌሊት ወደ ሰማይ ወስዷቸዋል ። የኢምራን ቤተሰቦችን ታሪክ ሲጀምር አሏህ የኢብራሂምን ቤተሰብ በአለም ላይ እንደመረጠ በመንገር ነበር ። ሲጨርስም ስለ common ground ሰለሆነው ነብይ - ነብዩሏህ ኢብራሂም የሚያወራ ሆኖ እናገኘዋለን ። ... ቁርአን ሚዛናዊ ትችት ነው የሚሰነዝረው ፣ አህለል ኪታቦች ሁሉም አንድ አይነት እንዳልሆኑና መጥፎዎቹ ቢበዙም መልካሞችም እንዳሉ እንዳይረሳ እንዲህ ሲል ይነግረናል ፦ وَمِنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ مَنۡ إِن تَأۡمَنۡهُ بِقِنطَارٍ يُؤَدِّهِۦٓ إِلَيۡكَ ቂንጧር እንግዲህ በጣም የተከማቸ ገንዘብ ነው ። አደራም ሆነ ብድር ብትሰጠው አደራውን ጠብቆ የሚያደርስ አለ ። በተቃራኒው ደግሞ ትንሽ ብር ሰጥተክ ብታምነው የማይመልስ አለ  "ኢላ ማዱምተ አለይሂ ቃኢማ" ማለት ምን መሰላችሁ ... ብሬን አምጣ ፣ መልስልኝ ፣ ስጠኝ እያልክ ጧት ማታ ካልነዘነዝከው የማይመልስ ማለት ነው ። لَيۡسَ عَلَيۡنَا فِى ٱلۡأُمِّيِّـۧنَ سَبِيلٌ ፦ አይሁዶች ከነሱ ውጭ የሆነውን መሀይማን እያሉ ነበር የሚጠሩት .. የተመረጥን ህዝቦች ነን እያሉ አምላክን እንኳ በብሄር ገድበው " የእስራኤል አምላክ " እያሉ ነው የሚጠሩት ። ቁርአን ግን ረቢል ዓለሚን (የአለማት ጌታ) እያለ ነው የሚጠራው ። ቀጥሎ አለማዊ ጥቅምን የመረጡ ሰዎች እጣ ፋንታ ይነግረናል ፦ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَشْتَرُونَ بِعَهْدِ ٱللَّهِ وَأَيْمَٰنِهِمْ ثَمَنًا قَلِيلًا أُو۟لَٰٓئِكَ لَا خَلَٰقَ لَهُمْ فِى ٱلْءَاخِرَةِ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ ٱللَّهُ وَلَا يَنظُرُ إِلَيْهِمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ "አያናግራቸውም" ማለት የእዝነት ፣ የርህራሄ ንግግር አያናግራቸውም ማለት ነው እንጂ የወቀሳማ ያናግራቸዋል ፦ فَلَنَسْـَٔلَنَّ ٱلَّذِينَ أُرْسِلَ إِلَيْهِمْ وَلَنَسْـَٔلَنَّ ٱلْمُرْسَلِينَ "ወላየንዙሩ ኢለይሂም " ማለት ደግሞ በራህመት አይን አይመለከታቸውም ማለት እንጂ ከአሏህ የሚሰወር ነገር የለም ። ማየት እና መመልከትም ይለያያል ።  "ወላ ዩዘኪሂም" ከሀጢአት አያጠራቸውም ። እነዚህ እንግዲህ  አለማዊ ጥቅምን የመረጡ ሰዎች ናቸው ። ረሱልም ﷺ በሀዲሳቸው ሶስት ሰዎች አሏህ አያናግራቸውም ብለውናል ፦ አል ሙስቢል ( ልብሱን ለጉራ መሬት ለመሬት የሚገትት) ፣ ሸቀጡን በውሸት መሀላ የሚሸጥ እና መናን ( የሚመፃደቅ ፥ እንዲህ አድርጌ ፣ እንዲህ ሰርቼ እያለ የራሱን ዝና ሲያወራ የሚውል)  እነዚህ ሰዎች አሏህ አያናግራቸውም ። To be continued .. @islamic_picture_wallpaper @Islamic_picture_wallpaper_Gp
Show all...
የበሽታ ደምን የሚመለከት አጭር ማስታወሻ - የወር አበባን መለየት ሲያስቸግር የሚያግዙ ነጥቦች - = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor
Show all...