en
Feedback
ተመስገን አብይ _ Psychologist

ተመስገን አብይ _ Psychologist

Open in Telegram

Psychologist Behavior Trainer Master of Cermoney (MC) የሚቻለው መቻል ነው! ሰው ማለት መሆን ነው። መሆን ደግሞ መቻል ነው። በዚህች ምድር ላይ ላለመቻል የተፈጠረ ፍጥረት አለ ብዬ አላምንም ለመቻል እንጂ። መቻል የፍጥረታት ሁሉ ባህርይ (በተለይ የእኛ ሰዎች) ነው። ለአስተያየት @Temu1msw

Show more
1 081
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-830 days
Posts Archive
✨ንጋት እና ህይወት✨ 🔗 አመክንዮ የበላቸው ተምሳሌቶች 🤔 ምክንያት ወይንስ ምሳሌ ? 📆 ዘወትር ሰኞ ከ 8:00-10:00 በ ኤፍኤም 97.1 ይከታተሉ ! ማይንድ ሞርኒንግ ( Mind Morning
✨ንጋት እና ህይወት✨    🔗  አመክንዮ የበላቸው ተምሳሌቶች         🤔  ምክንያት ወይንስ ምሳሌ ? 📆 ዘወትር ሰኞ ከ 8:00-10:00   በ ኤፍኤም 97.1  ይከታተሉ ! ማይንድ ሞርኒንግ ( Mind Morning ) Telegram:@mindmorning Facebook :https://www.facebook.com/mindmorning YouTube :https://youtube.com/@mindmorning8895?si=kf-l6KGU52UoetK7

🌘 ከግርዶሽ ጀርባ   🔴 እናንተ ቶሎ ቶሎ ትናደዳላችሁ ወይስ አልፎ አልፎ ነው ቱግ የምትሉት ? 🖍 የተከማቸ ስሜት ካለን 🖍 ነገሮችን መቋቋም ሲያቅተን 🖍 እንዳይፈጠር የምንሰጋው ነገር ካለ 🖍 ሌላ አማራጭ የሌለን ሲመስለን 🌘 እያንዳንዱ ሰው በተለያየ ምክንያት ግርዶሽ አለው! በጥያቄው ራስዎን ይፈትሹ!! ማይንድ ሞርኒንግ የባህሪ ስልጠና ምርምርና ማማከር ከ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በመተባበር  ዘወትር ሰኞ ከ 8:00-10:00 ሰዓት በቀጥታ ይቀርብላችኋል፡፡ የዚህ ፕሮግራም አጋሮች #አማራ_ባንክ #ኮካ_ኮላ @Mindmorning

ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለደመራና ለመስቀል በአል አደረሳችሁ። ተመስገን አብይ Psychologist
+1
ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለደመራና ለመስቀል በአል አደረሳችሁ። ተመስገን አብይ Psychologist

ለእስልምና ተከታዮች በሙሉ እንከኳን ለመዉሊድ አደረሳችሁ
ለእስልምና ተከታዮች በሙሉ እንከኳን ለመዉሊድ አደረሳችሁ

📖 ልጆች በበጋው ወቅት ከሚማሯቸው ትምህርቶች እኩል ለህይወታችው ወሳኝ ከሆኑ ትምህርቶች ውስጥ አንዱ የህይወት ክህሎቶችን መማርና ማዳበር ነው፡፡ 🔊ምዝገባችን ሊጀመር ነው! 🚫 ያሉን ዉስን ቦታዎ
📖 ልጆች በበጋው ወቅት ከሚማሯቸው ትምህርቶች እኩል ለህይወታችው ወሳኝ ከሆኑ ትምህርቶች ውስጥ አንዱ የህይወት ክህሎቶችን መማርና ማዳበር ነው፡፡ 🔊ምዝገባችን ሊጀመር ነው! 🚫 ያሉን ዉስን ቦታዎች ስለሆኑ ፈጥነው ልጅዎን ያስመዝግቡ ! 🔐ልጆች በቅዳሜ ስልጠናችን፦ 📌 በራስ መተማመናቸው ይጨምራል። 📌 እንደሚችሉ ይሰማቸዋል። 📌 ደጋግመው መሞከር ይችላሉ። 📌 አቅማቸው ይጨምራል። 📌 ጀምረው መጨረስ ይችላሉ። 📌 ሃላፊነት መውሰድ የሚችሉ ይሆናሉ። 🗓 ዘወትር ቅዳሜ 3:00-5:30 ሰዓት ለበለጠ ማብራሪያ እና ለመመዝገብ ☎️ +251935 545452 +251970414243 @mindmorning

ራስን አንድም ከራስ አንፃር ደገግሞም በሌሎች አይን ማየት አስፈላጊና ጠቃሚ ነዉ:: ተመስገን አብይ Psychologist
ራስን አንድም ከራስ አንፃር ደገግሞም በሌሎች አይን ማየት አስፈላጊና ጠቃሚ ነዉ:: ተመስገን አብይ Psychologist

ከሰሞኑ አንዱን ቀን ወደቤቴ ልገባ የግቢውን በር በመክፈት ላይ ሳለሁ "አባ አባቴ ወንድሜ" የሚል ድምፅ ሰማሁ:: ወደሰማሁበት አቅጣጫ ዘወር ስል ለካ እኔን ነው:: ልጁ ወጣትና ቆሸሽ ያለ ልብስ የለ
ከሰሞኑ አንዱን ቀን ወደቤቴ ልገባ የግቢውን በር በመክፈት ላይ ሳለሁ "አባ አባቴ ወንድሜ" የሚል ድምፅ ሰማሁ:: ወደሰማሁበት አቅጣጫ ዘወር ስል ለካ እኔን ነው:: ልጁ ወጣትና ቆሸሽ ያለ ልብስ የለበሰ ነው:: ወደ እኔ እየመጣ ድምፁን ከፍ አድርጎ "የሚበላም አይደለም የምፈልገዉ ገንዘብም አይደለም የምፈልገዉ እያለ እየቀባጠረ ቆዬ::" ጊዜዬን እንዳይወሰድብኝ አልኩና ምንድን ነዉ የፈለከዉ? የፈለከዉን ተናገር አልኩት:: ቀልጠፍ አለና "ሱሪ ነዉ የምፈልገዉ ሱሪ ካለህ" አለኝ:: ጠብቀኝ አልኩትና ቤት ገብቼ ከጠበቡኝ ሱሪዎች አንዱን አንስቼ ሰጠሁት:: ደስ ብሎት ስሞኝ መርቆኝ ሄደ:: በኃላ ሳስበዉ ሁለት ነገር ገረመኝ:: የመጀመሪያዉ የሚፈልገዉን በቀጥታ ከመናገር ይልቅ የማይፈልገውን ሲዘረዝር መቆየቱ ነዉ:: ይኸም ሰዎች አይረዱኝም የሚል ፍርሃት መሆኑ ነዉ:: ሁለተኛዉ የሚፈልገዉን ስጠይቀዉ በቀጥታ በአንድ ቃል "ሱሪ" ማለቱ አስገረመኝ:: እኔስ የምፈልገዉን በቀጥታ መግለፅ እችል የሆን...? ራሴን ጠየኩት:: አጋጣሚዉ ስላስገረመኝ ሼር አደረኳችሁ:: ከወደዳችሁት ለሚጠቅማቸዉ ሰዎች ሼር አድርጉት:: ተመስገን አብይ Psychologist

ወሳኔ ቁርጠኝነት ነዉ::
ወሳኔ ቁርጠኝነት ነዉ::

እንዲህም ይታሰባል ለካ......... አንብቡት ለጓደኛዉ "ትናንት ማታ ባለቤቴ አንተ መቼም የማትቀየር ድንጋይ ነህ" አለችኝ:: "በሇላ ሳስበው ግን ልክ ነች" ይለዋል:: እንዴት? አንተ መቼም የማት
እንዲህም ይታሰባል ለካ......... አንብቡት ለጓደኛዉ "ትናንት ማታ ባለቤቴ አንተ መቼም የማትቀየር ድንጋይ ነህ" አለችኝ:: "በሇላ ሳስበው ግን ልክ ነች" ይለዋል:: እንዴት? አንተ መቼም የማትቀየር መሰረት ነህ:: በአቋምህ የፀናህ ነህ:: ታማኝ ነህ ማለቷ ነዉ ሲል ይመልስለታል:: ተመስገን አብይ Psychologist

3 አዕምራችን በተደጋሚ የሚያደርጋቸው ነገሮች፡ 1️⃣ መጠቅለል፡ አንድ ሰው ላይ ያየነውን ነገር ሙሉ የኢትዮጵያ ሰዎች እንደሚያደርጉት አድርጎ ማሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ወጣት ሲሳደቡ የተመለከቱ አ
3 አዕምራችን በተደጋሚ የሚያደርጋቸው ነገሮች፡ 1️⃣ መጠቅለል፡ አንድ ሰው ላይ ያየነውን ነገር ሙሉ የኢትዮጵያ ሰዎች እንደሚያደርጉት አድርጎ ማሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ወጣት ሲሳደቡ የተመለከቱ አዛውንት አይ የዘንድሮ ወጣት እንዲህ ናቸው ቢሉ አዕምሯቸው ጠቅልሎ እንዲያስቡ ሆናል ማለት ነው፡፡ 2️⃣ መሰረዝ፡ ከዚህ በፊት አድርገናቸውየምናውቃቸው ነገሮች ሊሰረዙና ልንረሳቸው እንችላለን፡፡ ይህም ብዙዎቻችን የሚገጥመን ነገር ነው በተለይ ለጅም ግዜ ከሆነው በኋላ፡፡ 3️⃣ ማዛባት፡ የሆነው ጉዳይ ላይ ምናባዊ የሆነ እውነት የሚመሰል ሀሳብ ይጨምራል፡፡ ለምሳሌ ፈጣን የነበረ ጓደኛችንን አሪፍ የማስታወስ ችሎታ አለው ብለን ልናወራ እንችላለን፡፡ በተለይ የልጅነት ታሪካችንን ስናወራ አንዳንዶቹ ያልሆኑ ነገሮች ነገር ግነ ያደረግናቸው የሚመስሉ ናቸው፡፡ በቆይታ ሂደትም እውነት አድርገን እንቀበላቸዋለን፡፡ ተመስገን አብይ Psychologist

የሙሉነት ስሜት ተሰምቷችሁ ያውቃል?
Anonymous voting

ነገሮች ሁሌምእኛ እደጠበቅናቸው አይሆኑም፡፡ መሆንም አይገባቸውም፡፡ ስለዚህ ለሁሉም ዝግጁ መሆን የኛ ስራ መሆን አለበት፡፡ ተመስገን አብይ Psychologist
ነገሮች ሁሌምእኛ እደጠበቅናቸው አይሆኑም፡፡ መሆንም አይገባቸውም፡፡ ስለዚህ ለሁሉም ዝግጁ መሆን የኛ ስራ መሆን አለበት፡፡ ተመስገን አብይ Psychologist

የማትደራደሩበት ነገር ምንድን ነው?
Anonymous voting

ስሜቶቻችንን ለመቀየር ወይም ለመቆጣጠር ከመሞከር ይልቅ በውስጣችን እንዲኖሩ መፍቀድ ነው ያለብን፡፡ ስንፈቅድላቸው አዕምሯችን ይረጋጋል፤ ስሜቶቻችንም ይስተካከላሉ፡፡ ተመስገን አብይ Psychologis
ስሜቶቻችንን ለመቀየር ወይም ለመቆጣጠር ከመሞከር ይልቅ በውስጣችን እንዲኖሩ መፍቀድ ነው ያለብን፡፡ ስንፈቅድላቸው አዕምሯችን ይረጋጋል፤ ስሜቶቻችንም ይስተካከላሉ፡፡ ተመስገን አብይ Psychologist

ሰውን ምን ብላችሁ ትገልፁታላችሁ?
Anonymous voting

ደስታችን ለምን ይቀንሳል? ብዙዎች ደስተኛ መሆን እፈልጋለሁ ነገር ግን አልቻልኩም ይላሉ፡፡ እንዴት ነው ደስተኛ መሆን የምችለው የሚል ጥያቄም በተደጋጋሚ ቀርቦልን ያውቃል፡፡ ቀጥሎ የጻፍንላቸሁ ማንኛ
ደስታችን ለምን ይቀንሳል? ብዙዎች ደስተኛ መሆን እፈልጋለሁ ነገር ግን አልቻልኩም ይላሉ፡፡ እንዴት ነው ደስተኛ መሆን የምችለው የሚል ጥያቄም በተደጋጋሚ ቀርቦልን ያውቃል፡፡ ቀጥሎ የጻፍንላቸሁ ማንኛውም ሰው ደስተኛ ሊያደርገው የሚችለውን መፍትሄ ነው፡፡ ደስተኛ ለመሆን፡ 1️⃣ የግል ጥያቄዎቻችንን መመለስ አለብን፡፡ አንዳንዶቻችን ስለተፈጠርን እንጂ መኖራችን ትርጉም እንዳለው ገብቶን አይደለም የምንኖረው፡፡ ህይወት ለኔ ምንድን ነች? እኔ ምን አይነት ሰው ነኝ? የመጣሁበት መንገድ ምንድን ነው? ምን ተጽዕኖ አደረገብኝ? ወዴትስ ነው የምሄደው? ወዘተ የሚሉትን ጥያቄዎች መልስ መስጠት አለብን፡፡ ደስተኛ የምንሆነው ብዙ ቁሳቁስ ስላከማቸን ሳይሆን የውስጥ ጥያቄዎቻችንን ስንመልስ ብቻ ነው፡፡ 2️⃣ በተግባር የምንኖር ሰዎች መሆን ይገባናል፡፡ ደስታ ከሃሳብ ይልቅ ከተግባር ይቀዳል፡፡ ነገሮችን መሞከር፣ መጋፈጥ፣ ማድረግ መቻል በጣም ደስተኛ እንድንሆን ብሎም ጤናችን የተጠበቀ እንዲሆን ያደርገናል፡፡ ስለዚህ ወሬያችንን ቀነስ እናድርግና በተግባር እንሞክር ከዛም ያደረግነውን እናወራለን፡፡ ተመስገን አብይ Psychologist

መኖርን የሚፈራ ሰው መሞትን ይፈራል፡፡ መኖሩን ትርጉም እየሰጠ ያለ ሰው ደግሞ ሞት ሌላ የመኖር ገፅ መሆኑን ይረዳል፡፡ በየትኛውም ሰዓት በሞት ውስጥ ያለውን ህይወት ለመኖርም ዝግጁ ነው፡፡ በምድር
መኖርን የሚፈራ ሰው መሞትን ይፈራል፡፡ መኖሩን ትርጉም እየሰጠ ያለ ሰው ደግሞ ሞት ሌላ የመኖር ገፅ መሆኑን ይረዳል፡፡ በየትኛውም ሰዓት በሞት ውስጥ ያለውን ህይወት ለመኖርም ዝግጁ ነው፡፡ በምድር ያልተዘጋጀ እንዴት በሰማይ ይዘጋጃል? እንድንኖር ተፈጥረን መኖርን የምንፈራው ለምንድን ነው? ተመስገን አብይ Psychologist

ግጭትን ማስተናገድ መቻል “እኔ ከማንም ሰው ጋር መጣላትም ሆነ መቀያየም አልፈልግም!” ሲሉ የምንሰማቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ከሰዎች ጋር አብረን እስከኖርን ድረስ ደግሞ ከግጭት መራቅ አንችልም፡፡ ግ
ግጭትን ማስተናገድ መቻል “እኔ ከማንም ሰው ጋር መጣላትም ሆነ መቀያየም አልፈልግም!” ሲሉ የምንሰማቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ከሰዎች ጋር አብረን እስከኖርን ድረስ ደግሞ ከግጭት መራቅ አንችልም፡፡ ግጭት እንዳይፈጠር ከመታገል ይልቅ ግጭትን የምናስተናግድበትን አቅም መፍጠር ነው ያለብን፡፡ ግጭት ለምን ያስፈልጋል? 1️⃣ ግንኙነትን ለማደስ ያስፈልጋል፡፡ 2️⃣ ልዩነትን ለማወቅና ለማክበር ያስፈልጋል፡፡ 3️⃣ ያመንበትን ነገር እንድናሳይ እድል ይሰጠናል፡፡ 4️⃣ መተማመንን ይፈጥርልናል፡፡ 5️⃣ አቅማችንን ለመፈተሸ ይረዳናል፡፡ 6️⃣ ሁሌም የሚፈጠር ጉዳይ መሆኑን እንድንረዳ ይጠቅመናል፡፡ ከግጭት ለመሸሽ ከመመሞከር ይልቅ ያመንበትን ነገር ለማሳየት መሞከር የተሻለ ደስታን ይፈጥርልናል፡፡ ግጭት ሁሌም ያለ መልካም ነገር ነው፡፡ ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር አድርጉት! ተመስገን አብይ Psychologist