HIDASE FIRE GEN.SEC.SCHOOL (JAIKA.WOLKITE)
Open in Telegram
1 701
Subscribers
-124 hours
-57 days
+2630 days
Posts Archive
ለአዲስና ነባር የት/ቤታችን ተማሪዎች በሙሉ
የምዝገባ ማብቅያ ቀን የቀረው አንድ ቀን ብቻ ቢሆንም እስካሁን ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች መኖራችሁ መረጃችን ያሳያል ።ስለሆነም ከነገ አርብ 29/12/18ዓም ውጪ ምንም አይነት ምዝገባ ስለማይኖር በጠዋቱ መጥታችሁ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን ከነገ በኋላ ክፍል ስለምንደለድል ምንም የምዝገባ ጥያቄ ለት/ቤታችን ተማሪም ይሁን እኛ ት/ቤት የተመደበ ተማሪ የማናስተናግድ በመሆኑ ነገ ቀን ሙሉ ምዝገባ ላይ ስለሆንን መጥታችሁ እንድትመዘገቡ ለመጨረሻ ጊዜ እናስጠነቅቃለን።
ት/ቤቱ!!!
Repost from Ministry of Education Ethiopia
ማስታወቂያ
የ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
Ø የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን ከነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ምርጫችሁን ት/ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ እራሳችሁ በመሙላት እንድታሳውቁ እንገልጻለን።
Ø ማስፈንጠሪያ (Link) https://student.ethernet.edu.et/
ማሳሰቢያ፡-
v የህክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከ6 ወር በታች ህፃን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል።
የትምህርት ሚኒስቴር
Repost from Ministry of Education Ethiopia
ማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር ለተማዘገባችሁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ተማሪዎች በሙሉ፤
ለፈተና መስጫ ማዕከልነት የተመረጡት፤
Ø አዲስ አበባ ዩኒቨርቲ (6 ኪሎ ካምፓስ)
Ø የመነን አዳሪ ት/ቤት
Ø ሚኒኒክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስለሆኑ ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች ዛሬ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም ከ9:00 ጀምሮ በእነዚህ የፈተና መስጫ ማዕከላት ተገኝታችሁ የሙከራ ፈተና እንድትወስዱ እናሳስባለን።
Wowwwwwwwwww የህዳሴ ሰማይ ስር ደማቅ አንፀባራቂዋ ኮከብ……እንዲህ ከፍ ብላ በላቀ ስኬቷ ፀዳል ስታብረቀርቅ ለማየት እጅግ በጣም ነበር የጓጉዋነው…ጥበቃችን ጉጉታችን በከንቱም አልቀረ……በፍካቷ ፈካን…በልዕቀቷም የላቀ ደስታም ተሰማን……የቀለሙ አምላክ የተመሰገነ ይሁን🙏🙏🙏🙏
እንኳን ደስ ያላችሁ የሁላችንም ጭንቀት የነበረው የጀግኒት ውጤት ተስተካክሎ የሚገባትን አግኝታለች
Now the total number of our beloved Students Who are able to pass the 2018 E.C`s ESSLCE and directly join university in the coming year reachs 17. Alhamdulillah🙏🙏🙏🙏
ድካማችን አበበ፡ ፍሬውም ታየልን፣
ለ12ኛ ክፍል፡ ተማሪዎቻችን፣
በፈተናው ውጤት፡ ደስ አሰኛችሁን።
ሌሊትና ቀኑን፡ ሳታርፉ ደክማችሁ፣
ለዚህ ታላቅ ድል፡ በቅታችሁ አየን፣
ለወላጅ ለመምህር፡ ኩራት ሆናችሁን።
ጥረታችሁ ተክሶ፡ ውጤት ሲያበራ፣
የደስታችን ምንጭ፡ ሆነ የጋራ።
ይህስ ገና ጅምር፡ የመንገዱ መግቢያ፣
ለነገው ብሩህ ቀን፡ ታላቅ ማሳያ፤
እንኳን ደስ አላችሁ፡ ለላቀው ስኬት፣
ወደፊት ቀጥሉ፡ ወደ አዲስ ህይወት!
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ🙏🙏🙏
ድካማችን አበበ፡ ፍሬውም ታየልን፣
ለ12ኛ ክፍል፡ ተማሪዎቻችን፣
በፈተናው ውጤት፡ ደስ አሰኛችሁን።
ሌሊትና ቀኑን፡ ሳታርፉ ደክማችሁ፣
ለዚህ ታላቅ ድል፡ በቅታችሁ አየን፣
ለወላጅ ለመምህር፡ ኩራት ሆናችሁን።
ጥረታችሁ ተክሶ፡ ውጤት ሲያበራ፣
የደስታችን ምንጭ፡ ሆነ የጋራ።
ይህስ ገና ጅምር፡ የመንገዱ መግቢያ፣
ለነገው ብሩህ ቀን፡ ታላቅ ማሳያ፤
እንኳን ደስ አላችሁ፡ ለላቀው ስኬት፣
ወደፊት ቀጥሉ፡ ወደ አዲስ ህይወት!
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ🙏🙏🙏
ለDisqualified እና ውጤት 0 ለሆነባችሁ እንዲሁም ውጤት ለማየት ላስቸገራችሁ ተማሪዎች:
🟢በDisqualified እና በ0 ውጤት ዙሪያ: ልክ እንደ ባለፈው ዓመት፣ ምንም ዓይነት ጥፋት ሳትፈጽሙ በስህተት Disqualified ሆነችሁ ወይም 0 መጥቶባችሁ ከሆነ ቅሬታ (Complaint) ማቅረብ ትችላላችሁ። ጉዳዩ ተመርምሮ ስህተት መሆኑ ከተረጋገጠ ይስተካከላል።
🟢 ውጤት ለማየት ላስቸገራችሁ: በአሁኑ ሰዓት በSystem Traffic መጨናነቅ ምክንያት ማየት ካልቻላችሁ አትጨነቁ፤ ሰርቨሩ ትንሽ አየር ሲያገኝ (በተለይ ዘግየት ብሎ በሌሊት) ድጋሚ ሞክሩት።
