cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

እንኳን ደህና መጡ‼ ✔ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞https://t.me/WasuMohammed ✔ ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏

Show more
Advertising posts
204 052Subscribers
-33024 hours
-2 6277 days
+1 62030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አማራ ክልል የደቡብ ጎንደር ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ እንደገለፀው መነሻውን መቀሌ መዳረሻውን ደግሞ ባህር ዳር ያደረገ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ በህገ-ወጥ መንገድ በኮንትሮ-ባንድ ከጫነውን 8,900 ጥይት ጋር በቁጥጥር ሥር መዋሉን አሳውቋል።ሹፌርና ረዳቱ መታሰራቸው ተሰምቷል።
Show all...
👍 8😱 1😢 1
Update የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለጸ። ከሶስት ዓመት በፊት የደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በቢሯቸው ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል ተብሏል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዩንቨርሲቲው አስተዳድር አመራር አባል "ፕሬዝዳንቱ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ. ም ጀምሮ በስራ ላይ አይተናቸው አናውቅም" ሲሉ ለአል ዐይን አማርኛ ዘጋቢ ነግረውታል። "ፕሬዝዳንቱ ንጉስ ታደሰ ከተጠቀሰው ቀን አንስቶ የት እንደሄዱ እና መቼ እንደሚመለሱ አናውቅም" ሲሉም እኝህ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አመራር ነግረውናል። ይሁንና ፕሬዝዳንቱ በቢሮ መታየት ካቆሙ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ባልታወቁ ሀይሎች መታገታቸውን ሰምተናል ሲሉም አክለዋል። የሰማን ሸዋ ዞን ፖሊስ፣ ኮማንድ ፖስት፣ ትምህርት ሚንስቴር እና የደብረብረሀን ከተማ ፖሊስ ስለ ደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።ከቤተሰብም የተገኘ መረጃ የለም። የፌደራል መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት የክልል ልዩ ሀይሎችን "መልሼ አደራጃለሁ" የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው። ግጭቱ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የታወጀው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ ሲሆን ይህ አዋጅ ሊጠናቀቅ ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል ሲል አል ዓይን አማርኛ ዘግቧል። ፕሬዝደንቱ ከወር በፊት ከመኖሪያ ቤታቸው ታግተው እንደተወሰዱ በዚህ ቻናል ላይ መዘገቡ ይታወሳል።
Show all...
👍 22😢 4😁 3 1😱 1
' የሀገር ውስጥ በረራው እንዴት ጨመረ ? ' " ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ በረራ መጨመር የሚገልጸውን መረጃ በእጅ ስልኬ ላይ ደረሶኝ አየሁት። እንዲያው ዝም ብሎ የሀገረ ውስጥ በረራ ጨመረ ብሎ የሚታለፍ መስሎ አልተሰማኝም። በእርግጥ አየር መንገዳችን ገቢ ማግኘቱ እጅግ የሚያስደስት ቢሆንም ሰዎችን በዚህን ያህል ልክ የአየር ትራንስፖርት እንዲጠቀሙ ያደረጋቸው ምንድ ነው ?  ብሎ ጥናት ማድረግ ይገባል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገራችን የየብስ ትራንስፖርት ማድረግ እኔን ጨምሮ ብዙ ሰዎችን የሚያሰጋ ሆኗል። በተለያየ ጊዜ የሚሰማው የእገታ ወንጀል ፣ ጥቃት ሰዎች ቅርብ ከተሞች ሳይቀር በአየር እንዲጓዙ እያደረጋቸው ነው። ለአብነት እኔ ከዚህ ቀደም ለስራ የግል መኪናዬን ይዤ ከከተማ ውጭ እስከ ድሬዳዋ ድረስ እየነዳው ሄጄ እመለስ ነበር ዛሬ ላይ ያን ለማድረግ አልችልም። የሆነ ነገር ብሆንስ ብዬ እፈራለሁ ስለዚህም በየጊዜው የአየር ትኬት መቁረጥ ግድ ብሎኛል። እኔ ስላለኝ ነው ይህ ያደረኩት አቅሙ የማይፈቅድ ደግሞ የግዴታ ሆኖበት የየብስ ይጠቀማል። እኔ እንኳን የማውቀው ብዙ ሰው ተቸግሮም ቢሆን በአየር ትራንስፖርት ለመጠቀም ሲገደድ ብዙ ጊዜ አይቻለሁ። ወደ ሰሜኑ ክፍልም ብንመለከተ ካለው ጸጥታ ጋር በተያየዘ ሰዎች ከየብስ ትራንስፖርት ይልቅ አቅማቸው ባይፈቅድ እንኳን ተቸግረው የአየር ትራንስፖርት ይጠቀማሉ። ስለዚህ የሀገር ውስጥ በረራ ቁጥሩ የመጨመሩ ብቻ ሳይሆን በዚህ ልክ እንዴት ሊጨምር እንደቻለ ምክንያቱ ቢታወቅ ጥሩ ነው ባይ ነኝ። " (Ato Solomon K. Tikvah Family Addis Ababa)
Show all...
👍 63 16😱 6👌 6👏 5🕊 3
ADVERTISMENT ታላቅ የምስራች ከDMC realestate በመሀል ከተማ በለቡ መብራት በሚገኘው  እጅግ ውብ እና ቅንጡ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በ10% ቅድሚያ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት ይሁኑ 65,000 ካሬ ላይ ያረፈ መንደር ከstudio  እስክ 4 መኝታ ድረስ በፈለጉት የካሬ አማራጭ ከምቹ አከፋፈል ጋር ✨50/50 የባንክ አማራጮችን አዘጋጅተናል 👉studio  58 ካሬ 👉ባለ አንድ መኝታ ከ77ካሬ-98ካሬ 👉ባለሁለት መኝታ ከ123ካሬ-155ካሬ 👉ባለሶስት መኝታ ከ146-181ካሬ 👉ባለአራት መኝታ ከ177ካሬ ጀምሮ 👉የልጆች መጫወቻ 👉የመዋኛ ገንዳ 👉ጂም እና ስፓ 👉የኤሌክትሪክ መኪና charge ቦታ ሁለት አመት ባነሰ ጊዜ የቤት ባለቤት ሊያደርግዎ ተዘጋጅቷል፡፡  👉ለጥቂት ቤቶች ብቻ ከ8%-25% ቅናሽ አድርገናል Tip:- ፈጥነው ከመጡ 2ኛ እና 3ኛ floor ላይ መግኘት ይችላሉ ! ታድያ ምን ይጠብቃሉ …አሁኑኑ  ወደ DMC realestate ይደውሉና የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ይሁኑ! …….ያስተውሉ ቀድሞ የመጣ ቀድሞ ይስተናገዳል  እንዲሉ ዛሬ ነገ ሳይሉ አሁንኑ 👉☎️0977019814 እና 0961396467       በመደወል  ይመዝገቡ፡፡
Show all...
👍 3 2👏 2🥰 1
አዲስ አበባ‼ ሀሰተኛ የጋብቻ ሰርተፍኬት እና መታወቂያ በመያዝ አገልግሎት ለማግኘት የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ በየካ ክፍለ ከተማ በሀሰተኛ ማስረጃ አገልግሎት ለማግኘት የሞከሩ አራት ደንበኞች እና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ሁለት ሃሰተኛ ሰነድ ይዘው አገልግሎት ለማግኘት የቀረቡ ተገልጋዮችን ጨምሮ ሌሎች ሁለት በወንጀል ተግባሩ የተጠረጡ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አግልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ተናግረዋል ። አንደኛው ግለሰብ ሃሰተኛ የመታወቂያ እና ያላገባ ህገ ወጥ ማስረጃ በመያዝ ለጽ/ቤቱ ሰራተኛ ጉቦ በመስጠት አገልግሎት ለማግኘት የሞከረ ሲሆን ከዓመታት በፊት ማስረጃውን በሌላ አገናኝ ደላላ ያገኘው መሆኑን ተረጋግጧል፡፡ በመሆኑም ደላላው እና ሁለተኛው ተጠርጣሪ የቂርቆስ ክ/ከተማ ነዋሪነት መልቀቅያን አስመስሎ በማሰራት አገልግሎት ለማግኘት ሙከራ ሲያደርግ ሃሰተኛ ሰነዱን ካዘጋጀው አስመዝጋቢ የቤት ባለቤት ነዋሪ ግለሰብ ጋር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። በአንደኛው ወንጀል የተጠረጠረው የጽ/ቤቱ ሰራተኛ ከዚህ ቀደም በወንጀል ተጠርጥሮ በኤጀንሲው ታግዶ የፖሊስ ምርመራ እየተደረገበት ያለ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ሁለተኛው ድርጊት ሃሰተኛ መልቀቅያ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ነዋሪነት ስም አስመስሎ ለመገልገል ሲቀርብ በማስረጃው ላይ በጽ/ቤቱ ጥርጣሬ በማደሩ የቂርቆስ ክ/ክተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ጋር መረጃ በመለዋወጥ ድርጊቱ ለፖሊስ እንዲተላለፍ በየካ ክ/ከተማ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት መደረጉን አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ጨምረው መናገራቸው ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ዘግቧል። ====================== ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ👇       https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 ማስታወቂያና ጥቆማ 👇መቀበያ https://t.me/wasumohammed
Show all...
👍 35 6😱 4👏 3😁 3🙏 3🤔 1😢 1
ADVERTISMENT አፊያ ሙሀመድ ከፍተኛ የባህል ሕክምና እና ዘመናዊ የዋግምት አገልግሎት   የምንሰጣቸው የባህል ህክምናዎች ➢ ለውጭና ለውስጥ ኪንታሮት ➢ ለማድያት ➢ ለሱኳር በሽታ ➢ለጉበት(ለወፍ በሽታ) ➢ለጨጎራ ህመም ➢ለስፈተወሲብ ➢ለደም ግፊት ➢ለአስም ወይም ሳይነስ ➢ለሚጥል በሺታ ➢ ለእሪህና ቁርጥማት ➢ለራስ ህመም (ማይግሪን) ➢ለቺፌ ና ለጭርት ➢ለቋቁቻና ፎረፎር ➢ለእጢና ለእባጭ ➢ለወገብ ህመም ➢ለመካንነት ለወድም ለሴትም ➢ለጆሮና ለአይን ህመም ➢ለሆድ ህመም ➢ዘመናዊ የዋግምት አገልግሎት በተቋማችን እንሰጣለን። 👉ከኢትዮጵያ ባህላዊ ህክምና አዋቂዎች ማህበር በዘርፉ ህጋዊ የባህል ህክምና ፍቃድ ያለን ነን። አድራሻ:አዲስ አበባ አየር ጤና    ስልክ ቁጥር   📲0927506650                          📲0987133734                          📲0956522222 ቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/+08vmUP_ntvE5NmM0
Show all...
4👍 3👏 3
የኤርትራ ጦር  ከዛላንበሳና አጎራባች ወረዳዎች   ሰዎችን   አግቶ እየወሰደ ነው ተባለ የዛላ  አንበሳ ከተማ ከንቲባ ብርሃነ በርሄ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ከምስራቃዊ ዞን  ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ታግተዉ ተወስደዋል  ብለዋል፡፡ ከዛላ አንበሳ 26 ሰዎች፣ ከጉለም ወረዳ  50  እንዲሁም ከኢሮፕ 28 ሰው በኤርትራ ሰራዊት እንደተወሰደ  ገልፀው በዚህ ሳምንት ደግሞ ቁጥሩ መጨመሩን ተናግረዋል። አሁን ላይ ዛላንበሳ ከተማን ጨምሮ  ምስራቃዊው ዞን ሙሉ በሙሉ በኤርትራ ጦር ቁጥጥር ስር እንደሆነ የሚናገሩት የከተማዋ ከንቲባ ማህብረሰቡም  ብዙ በደል እና ጥቃት እየደረሰበት ነዉ ብለዋል፡፡ የኤርትራ ጦር  የአካባቢዉን ነዋሪዎቹ በአልጀርስ ስምምነት መሰረት  ኤርትራዊ እንደሆኑ በመግለጽ  በኃይል  እንደተቆጣጠረም ሰምተናል፡፡ የፌድራል መንግስት ምንም አይነት ትኩረት አልሰጠንም የሚሉት አቶ ብርሀነ ዳግም ጦርነት አንፈልግም ግን ደግሞ ማንነታችንን እና ህልውናችንን ሊያስከብርልን ይገባል ብወዋል። በከተማዋ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች በጦሩ  ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ ተነስቶ  በከተማው እንዲሁም በአካባቢው ያለው ነዋሪ ለከፋ ችግር እንደተጋለጠም ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከ30ሺ በላይ ነዋሪ ተፈናቅሎ በመቀሌ፤ በአዲግራት እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች በመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኝ አቶ ብርሀነ ነግረውኛል ሲል የዘገበው ኢትዮ ኤፍ ኤም 107·8 ነው፡፡
Show all...
👍 46😢 6 5👏 2😱 2
ADVERTISMENT እናመሰግናለን🙏 አብዝሃኛው የእጣ ሽያጭ እተጠናቀቀ ነው።በቀሩት ጥቂት ቀናት ብቻ ቀሪ የቅይጥ ንግድ ቦታ እጣው በቀረበው ልዩ የቅናሽ ዋጋ እንድትገዙ ተጋብዛችኋል። ቦታው ደሴ ገራዶ ጡንጅትአምባ አደባባይ ላይ የሚገኝ እና  በ3 አቅጣጫ መንገድ የሚያገኘው ነው። አንድ እጣ ለሚገዛ አባል የሚደርሰው፡ አንድ ሱቅ፤ አንድ ባለ ሁለት መኝታ አፓርታማ እና 1 የጋራ ፍሎር ነው። ዋጋ 150 ሽህ ብር ብቻ ነው። ➡ የግንባታ ወጭ በአባላት የጋራ መዋጮ ይሆናል። 🙏የሌለንን ስለማንሸጥ ከእኛ ጋር በመስራት ራስዎን ከአጭበርባሪዎች ይጠበቁ። ለበለጠ መረጃ በማህበሩ ስልኮች:— 0937411111 ወይም 0938411111 ይደውሉ። ታማኝነት መገለጫችን ነው። ዶ/ር አብዱ፣ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት የማልማትና የማከፋፈል ህ/ሽ/ማ
Show all...
👍 6 3😱 1
በሀገራችን 1 ሰው ብቻ በትክክል የሚናገረው ቋንቋ መኖሩ ተነገረ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሰው ብቻ በትክክል የሚናገረው የብራይሌ ማህበረሰብ የሆነው የ "አንጎታ" ቋንቋ መኖሩ ተነገረ። የብራይሌ ማህበረሰብ አንጎታ ቋንቋን የሚናገሩ አምስት ሰዎች አሉ ቢባልም ቋንቋውን በቅጡ የሚያውቀው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ ወርቅነሽ ብሩ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ገልፀዋል። ከ 145 አመታት በፊት የብራይሌ ብሔረሰብ ብዛት 8 ሺህ ያህል እንደነበረ ጥናት ያመለከተ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግን ያሉት የብሄሩ ተወላጆችም ሆነ ቋንቋውን መናገር የሚችሉት አምስት ሰዎች ብቻ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው ሁለት ቋንቋዎች ከመጥፋት ለመታደግ ጥናት እና ምርምር እየተሰራ መኖሩ ሲነገር ከብራይሌ በተጨማሪ ከፍተኛ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል የተባለው ሌላኛው ቋንቋ የባጫ ብሔረሰብ ቋንቋ የሆነው ባጫ ቋንቋ መሆኑን ሸገር በዘገባው አመልክቷል።
Show all...
👍 45😱 6🥰 3👏 2🎉 2 1
ADVERTISMENT ሙራበሃ ባንኩ ከደንበኞች በሚቀርቡለት ጥያቄ መሰረት በሸሪዓ የተፈቀዱ እቃዎችን/ንብረቶችን በመግዛት እና በግዥ ወቅት የወጡ ልዩ ልዩ ወጪዎችንና የባንኩን የትርፍ መጠን በተገዛው እቃ ወይም ንብረት ዋጋ ላይ በመጨመር በሽያጭ ለደንበኞች የማስተላለፍ አገልግሎት ነው። አገልግሎቱን በመጠቀም :— ✔ የሥራ ማስኬጃ ✔ የንብረት/ዕቃ ግዢ ✔ የእርሻ ሥራ ማስኬጃ ✔ የፕሮጀክት ፋይናንሲንግ በባንካችን ማግኘት ይችላሉ፡፡ አገልግሎቱን ለማግኘት በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ!               ጁሙዓ ሙባረክ‼ በአዲስ መንፈስ ለላቀ ከፍታ!    ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ   ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ‼ የሶሻል ሚዲያ ገጾቻችንን Like, Follow እና Share ስለሚያደርጉ እናመሰግናለን! ቲክቶክ፡https://www.tiktok.com/@nibinternationalbank ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/nib.intbank ቴሌግራም ቻናል፡https://bit.ly/3SBzNYd ኢንስታግራም ፡https://www.instagram.com/nib_internationalbank/ ዩቲዩብ: www.youtube.com/@nibinternationalbank6204ps://youtube.com/ ሊንክዲን፡ https://bit.ly/3bJUhgG ዌብ ሳይት፡ www.nibbanksc.com
Show all...
👍 6 4🥰 2🎉 2