cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Elroi Gospel Media

♦️በዚህ ቻናል♦️ ➡️መጽሀፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ➡️መንፈሳዊ ስነ ጽሁፎች ➡️አዳዲስ መዝሙሮች ➡️የመዝሙር ግጥምና ➡️ጥያቄ እና መልስ ይኖሩናል Subscribe 👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UC_tqX7XLUiEcELjZkMZtq0Q Join @elroigospelmedia TikTok https://vm.tiktok @elroigospelmedia_bot 👈For Any Comment

Show more
Advertising posts
1 815
Subscribers
-124 hours
-87 days
-1430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በጎውም መጥፎውም ምግባር ነጋችን ላይ በፍሬ መገለጡ አይቀርምና :- በብዙ ፅናትና ትዕግሥት ከመልካም ስራ ሁሉ ጋር መተባበርና እንዲሁም በማስተዋልና በፀጋው ችሎት ደሞ ከመጥፎው ነገር በመራቅ ስኬታማ ሰዎች ለመሆን እለት እለት በትጋት እንደግ😊🥰 “ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።”   — ማርቆስ 13፥37 መልካም ቀን! @elroigospelmedia📚 @elroigospelmedia📚
Show all...
11
የምወድሽ #እህቴ zare ለአንቺ መልዕክት አለኝ በህይወትሽ ዘመን ሁል ጊዜ ይህን አስቢ👇👇 በመከራና ፈተና በምታልፊበት ጊዜ በመውጣት መውረድ😔 ሁኔታ ሲከብድሽ ያልጠበቅሽው ነገር ድንገት ሲሆን ግራ ሲገባሽ እጅጉን አንድ ነገር አብዝቶ ሲያስጨንቅሽ😫 ይህን አስቢ👉 " እግዚያብሄር ከዚህ ምን ሊያስተምረኝ ፈልጎ ይሆን!" የሚለውን 1⃣ አንዳንድ #ፈተናዎች ግድ #ማስተካከል ያለብንን ባህሪዎቻችንን ሊያስተካክሉ የሚመጡ ናቸው ለዚህ ልብ እንበል 2⃣ አንዳንዶች ደግሞ ወደ እግዚያብሄር ሊያቀርቡን የሚመጡ ናቸው አይምሰልሽ ለእግዚያብሄር ከብዶት አይደለም የአንቺ ችግር ነገር ግን አስተውይ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 #ስታስተውይ መከራሽ ሊቀርፀው የፈለገው ባህሪሽ ይኖራል፣ #ስታስተውይ ይበልጥኑ ወደ እግዚያብሄር ሊያስጠጋሽ ይሆናል🤷‍♂፣ #ስታስተውይ ሁሉም ለበጎ መሆኑ ይገባሻል፣ ስታስተውይ ብርቱ ሴት ሊያደርግሽ ነው💪 የቱንም ያክል ገፍቶ ቢመጣ #ካስተዋልሽ ሊጥልሽ አይደለም ወደ ከፍታ ወደ ህልምሽ ሊያደርስሽ እንጂ☹️ ስለዚህ ንቂ ከአቅምሽ በላይ የተሸከምሽው ነገር የለም ተጋፈጪው💪 በጥበብና ማስተዋል "እግዚያብሄርንም በመፍራት" መንገድ እለፊው ተስፋ አትቁረጪ ሁል ጊዜ ከብርቱ ማዕበል ጀርባ ፍሬ አለና🙏              ደህና እደሩ እህቶቼ❤️ ወንድሞቼም🙈 @elroigospelmedia📚 @elroigospelmedia📚
Show all...
8🙏 4👏 3
ከኢየሱስ ጋር ሲጓዝ የመሸበት(የረፈደበት) የለም😍 በእምነት ፅኑ፤በሙሉ ተስፋ ተከተሉት💜 “እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”   — ኢሳይያስ 40፥31 @elroigospelmedia📚 @elroigospelmedia📚
Show all...
6👍 3
ተፈቅዶልን ዛሬም ስለነቃን ስለሁላችን ጌታ ይመስገን🥰 “እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ።” — መዝሙር 3፥5 መልካም ቀን! @elroigospelmedia📚 @elroigospelmedia📚
Show all...
🙏 9 7👍 1
                   ♦️ሊታረቀኝ ወዶ♦️          Aster Abebe||New Song           ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ           SH R ፨ JOIN ፨ SH R      ♻️ @elroigospelmedia      ♻️ @elroigospelmedia_bot          ✨ለበለጠ ቤተሰብ ይሁኑ✨
Show all...
4👍 2
Show all...
Eyesus Yadnal | ኢየሱስ ያድናል | የሀዋሳ ዲያስፖራ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን "ሀ" መዘምራን

#የዋዜማ መልዕክት በህይወቴ በጣም ከምገረምበት ነገር አንዱ በአል ሲመጣ በአል ነው ብለን ያመንበትን ምክንያት ከማሰብ ይልቅ ስለምንበላው ፣ ስለምንጠጣው ፣ ስለ ልብሳችን መጨነቃችን ነው ። 👉 አዲስ አመት መጣ አዲስ ልብስ ልግዛ ፣ 👉 ገና ነውና ስጦታ ካልተሰጠኝ ፣   👉ፋሲካ ነው ዛሬ በጉን ዶሮውን ልግዛ ሆኗል የኛ ህይወት መብላቱ መጠጣቱ ክፋት ሆኖ ሳይሆን ከርሱ በላይ እግዚአብሔርን እንድናስበው ስለምፈልግ ነው   እንደሚታወቀው ነገ ፋሲካ ነው ዛሬ ዋዜማው ላይ ቆመናል ብዙዎቻችንን ያስጨነቀን ነገር ግን  የሽንኩርት ፣ የዘይት ፣ የዶሮ መወደድ ነው እስቲ ስንቶቻችን ነን ከበአሉ ሽር ጉድ ውጪ በፅሞና ስለተደረገልን ስለተከፈለልን ዋጋ የምናስበው ? 📌 ከምንበላው በግ በላይ የናዝሬቱ ኢየሱስ ለኛ እንደ በግ ታርዶልናል እሱ ነው ሊያሳስበን የሚገባው !!! 📌የተከፈለልኝ ዋጋ ዋጋቢስ አድርጌዋለሁ ወይስ ገብቶኛል ብሎመፈተሹ ተገቢ ነው ።በአል ወር ሲቀረው ጀምረን በወጪ ከምንጨናነቀው በላይ ስለነፍሳችን ፣ ስለመዳናችን እንጨነቅ ። 🌹እንደ ፅጌረዳ ፈክተን ተሽሞንሙነን እየበላን እየጠጣን ብቻ ከምናሳልፈው ይልቅ ምንም ሳይኖረን የተደረገልንን እያሰብን ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት አድርገን ብናሳልፈው እሱ ለእግዚአብሔር ታላቅ ዋጋ አለው ። ይህን ስል መብላቱ መጠጣቱ አያስፈልግም ማለቴ ሳይሆን በምቾታችን ተታለን ቅድሚያ መሰጠት ያለበትን ነገር እየረሳነው ይመስለኛል ።    ከጎረቤት አላንስም ፣ ያስለመድኩት አይቀርም እያልን አጉል መጨናነቅ ውስጥ ከመግባት ባለን ተደስተን ከቻልን አካፍለን እግዚአብሔር እያመሠገንን በአሉን ማሳለፍ ነው ።    ቅድሚያ ትኩረታችን #ኢየሱስ ላይ ይሁን ሌላው ትርፍ ነው ። በሰበብ ባስባቡ አመት ባል በመጣ ቁጥር ልዝናና ፣ ልጨፍር ፣ ልብላ ከማለት ይልቅ ልክ እንደ ወርቃማ እድል ቆጥረነው የምንችል #ቤተክርስቲያን ያልቻልን ቤታችን ወይም ባለንበት ቦታ እግዚአብሔርን  ፣ የተደረገልንን ነገር እያሰብን እናክብረው ማሰብ ብቻ ሳይሆን በቀረውም ዘመናችን የመስቀሉን ስራ እያሰብን በዋጋ ተገዝተናልና ስለዛ እንኑር ። 🙏🙏 መልካም የፋሲካ በአል እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ተመኘሁ 😊 B,T @elroigospelmedia📚 @elroigospelmedia📚
Show all...
5👏 3
ስቅለት/ትንሳኤ_ የአመት በዓል አይደለም🙄🙅 እግዚአብሔር #ለዓለም #አንድያ ልጁን በመስቀል በመግደል ከሞትም #የስቃይ ሞት እንዲሞት በመፍቀድ $ፍቅሩን የገለፀበት፣ በልጁ ስቃይና ህመም የፍቅሩን ዳርቻ #ጥግ ያሳየበት ነው እንጂ ዓመት ጠብቀን ምናከብረው አይደለም🙅 #ዕለት #ዕለት #ልንኖርለት የሚገባ #የማይደበዝዝ #እውነት ነው እንጂ! መልካም የትንሳኤው መታሰቢያ በዓል! @elroigospelmedia📚 @elroigospelmedia📚
Show all...
10
"ክብር ሁሉ ላዳነን ለኢየሱስ ይሁን" ቆላስይስ 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁰ በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው #ደሙ ሰላምን በማድረግ በምድርም ሆነ በሰማይ ያለውን ነገር ሁሉ በእርሱ በኩል ከራሱ ጋር #አስታረቀ። ²¹ ከክፉ ባሕርያችሁ የተነሣ ቀድሞ ከእግዚአብሔር የተለያችሁ በአሳባችሁም ጠላቶች ነበራችሁ። ²² #አሁን_ግን ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ሊያቀርባችሁ፣ በክርስቶስ ሥጋ በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ፤ 🚨#የሰርግ ጊዜ ላይ #መድመቅ ያለበት #ሙሽራው እንጂ ሚዜው አይደለም። ምክንያቱም ፕሮግራሙ የፕሮግራሙ ባለቤት ሙሽሮቹ ስለሆኑ። ስለዚህ ሚዜው ከሙሽራው በላይ ውብ ቢሆን እንኳን የራሱን መልክ አደብዝዞ የሙሽራውን መልክ እንደሚገልጥ እንደዛ በፋሲካ የተሰራ ስራውን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር የምንሰጥበት ነው። #ኢየሱስ አምካክ ሆኖ ሳለ ሰው የሆነበት ምክንያት ሰዎችን ሁሉ ለማዳን ከሀጥያት በእሱ ሞት አማካኝነት ለማዳን ነው። ስለሆነም #የፋሲካ #ድምቀቱ #ኢየሱስ ክርስቶስ ሲከብር ብቻ ነው። ወዳጆች #ኢየሱስ ክርስቶስ ያልደመቀበት ፋሲካ እሱ ፋሲካ ሊባል አይችልም። እውነት ነው #ኢየሱስ ሰው የሆነው በማሪያም ተፀንሶ  ተወልዶ ነው ግን በፋሲካው ጊዜ የሁሉ #ባለቤት እና አስተዋፅኦ ያደረገው #ኢየሱስ ብቻ ነው። 🚨 ክብር ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን‼️ “ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤”   — 2ኛ ቆሮ 5፥14 መልካም ቀን!              @elroigospelmedia       #ጌታ @elroigospelmedia       #ኢየሱስ @elroigospelmedia       #ይወደናል
Show all...
7👍 2