cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የብዕር ጠብታ✍📒📖

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗ ║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣ ╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝ 💚 .....ታማኝነት በጥበብ መፅሐፍ ውስጥ የመጀመሪያው 💛 ምዕራፍ ነው ! ❤️ ✔️•═•••🍃🌺🍃•••═✔️ ለአስተያየት @Yetomah_Bot

Show more
Ethiopia3 666Amharic3 523The category is not specified
Advertising posts
2 142Subscribers
No data24 hours
-117 days
-5330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️ ክፍል 27     ✍ደራሲ - አብላካት በዚህ ንዴቴ ላይ ሌላ ነገር መጨመር ስላል ፈለኩኝ ምንም ሳልናገር ወደ ክፍሌ ገባሁና ጋደም አልኩኝ ማይለፍ የተናገረኝ ነገር ጭንቅላቴ ላይ አየተመላለሰ ውስጤን እረበሸኝ ለካ መጥፎ ቃልን ከሚወዱት ሰው አንደበት ሲሰሙት ህመሙ ይብሳል እሱ ላይ ቅያሜ እንዲኖረኝ አልፈልግም ነበር ምክንያቱም ፍቅሩን ብቻ ማሰብ ስለምፈልግ ነገር ግን ሁሌም እንዳሰብነው ብንንኖር ሀዘን ባልኖረ. እንዲሁ ከእራሴ ጋር እያወራሁ የክፍሌ በር ተንኳኳ እናቴ ነበረች…… "ምነው ቃልዬ ዛሬ ደሞ ሰላምም ሳትይኝ" አለችኝ "ይቅርታ እናቴ ትንሽ ስለደከመኝ ነው" "አይንሽም እንባ አቅሯል በሰላም ነው የኔ ልጅ ? የሆንሽው ነገር አለ ?" "አይ እማ ደህና ነኝ አትጨነቂ ሳርፍበት ይቀለኛል" "እንዳልሽ ልጄ እምታወሪኝ ካለ ግን ንገሪኝ" አለችኝ ሌላ ነገር ልትነግረኝ እንደመጣች ያስታውቃል እኔን ላለማስጨነቅ ነው እንጂ "እማዬ ምንድነው ልትነግሪኝ የፈለግሽ ? ከተኛሁበት እየተነሳሁ ጠየኳት " አዪ ልጄ እሱማ ብር ቸግሮኝ ደሞዝሽ ከደረሰ ብዬ ነበር" አለችኝ አንገቷን አቀርቅራ "እሺ አትጨነቂ ነገ እሰጥሻለው አልኳት አንገቷን እንዳቀረቀርች ከክፍሌ ወጣች የሰው ፊት ማየት ለካ አንገት ያስደፋል ምንም ያህል ያንን ሰው ብታውቁት ብትቀርቡት ያ ሰው ወላጃችሁም ይሁን ጏደኛችሁ ከሰውየው መግዘፍ ወይም ማነስ አልያም እድሜ ሳይሆን ችግሩ ከመጥየቁ ላይ ነው……..ከየት አምጥቼ ልሰጣት እንደሆነ ነገ ያልኳት ፈጣሪ ይወቅልኝ……..እንዲሁ ከራሴ ጋር እየተወያየሁ ሳላስበው እንቅልፍ ወሰደኝ……ጠዋት እንደነቃሁ ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄደ ከቤቴ ወጣሁኝ እንደተለመደው መታጠፊያችን ጋር ስደርስ የማይለፍን መኪና ቆሞ አየሁት ወዲያው መለስ አልኩኝ……..ላናገረው ስለማልፈልግ መንገዴን ቀይሬ ጉዞዬን ቀጠልኩ. ከርቀት ትርሲትን አየጏት. እሷም አይታኝ ፈገግ አለች እረጅም ጊዜ ሆኖኛል ካየጏት እሷ ጋር ስደርስ " ቃልዬ ከረጅም ጊዜ በጏላ ከየት ተገኘሽ ?" ብላ አቀፈችኝ "አለሁ ትርሲትዬ ክላስ ስራ ቢዚ አድርጎኝ ነው "ወይ ቃልዬ እንዲ በቀላሉማ አለቅሽም ወዴት እየሄድሽ ነው ?" "ቤተክርስቲያን ተሳልሜ ልመጣ" "በቃ እንደዛ ከሆነ ስትመለሺ እኔ ጋር ነኝ pls መቅረት አይቻልም" "እሺ እመጣለው" ብያት ሄድኩኝ……….. ይቀጥላል....... ቀጣዩ ክፍል ከ60❤️ በኋላ ይለቀቃል። ✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯        @Ketbeb_Mender         @Ketbeb_Mender  ✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
Show all...

❤️
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️ ክፍል 26     ✍ደራሲ - አብላካት አቶ ሰለሞን እና አቶ እስክንድር ጋር ስንደርስ .....ሁለቱም ተያዩና ቃልኪዳን አለኝ አቶ እስክንድር በመጠራጠር ስሜት ውስጥ ሆኖ.... " አዎ አልተሳሳትኩም ቃል ነሽ" አለኝ..... አቶ ሰለሞንም ቀጠል አድርጎ " ቢረሳ ቢረሳ እንዴት የዳይመንድ ፈርጦች ይረሳሉ ? ከሁሉም በላይ ደሞ ቃል አንቺን አለማስታወስ በእውነቱ ንፉግነት ነው" ብሎ ፈገግ አለ........ምን ቤተክርስቲያን ሳስቀድስ እና ስዘምር ወይ በጎ ነገር ስሰራ እንዳየ ሰው አለማስታወስ ንፉግነት ነው ይላል... ባያስታውሰኝ ነበር እኮ እሚሻለኝ...... በቃ እኛ ሰዎች አሉባልተኛ ሆነን ቀረን ማለት ነው ? .....ምናለ በደህና ነገር ብንተዋወስ .... ማይለፍ ግራ በመጋባት ስሜት ውስጥ ሆኖ አይኑን ከአንዳችን ወደ አንዳችን እያንከባለለ ይቃኘናል... "ምነው ሰላም አትይንም እንዴ ቃል" አለኝ አቶ እስክንድር... "በጣም ይቅርታ ሀሳብ ውስጥ ሆኜ ነው እንዴት ናችሁ ?" ብዬ ተራ በተራ ጨበጥኳቸው "እኛማ ደህና ነን እናንተ የውሀ ሽታ ሆናችሁ ከራችሁ እንጂ... እንደቀልድ ብዙ ወራት ሆናችሁ ወደ ዳይመንድ ከመጣችሁ የቤቱ ድምቀት እናንተ ነበራችሁ" አለ አቶ ሰለሞን "አዎ ረጅም ጊዜ ሆነን ከተያየን..... ደሞም እዚህም ቢሆን ጓደኞችሽን እስካሁን አላየኋቸውም ብቻሽን ነው እንዴ የመጣሽው ?" አለኝ አቶ እስክንድር ቀጠል አድርጎ "ፈራ ተባ እያልኩም ቢሆን መመለሴ ግድ ሆነ...አዎ ከዳይመንድ ከራቅን ረጅም ጊዜ ሆኖናል ወደዛ አካባቢ መተን አናውቅም... ጓደኞቼ ደህና ናቸው ዛሬ ከማይለፍ ጋር ነው የመጣሁት ለዛ ነው" አልኳቸው "በሰላም ከሆነ እሺ..ልጅ ማይለፍ ምነው በዝምታ ተዋጥቅ ? ችግር አለ እንዴ ?" አለ አቶ እስክንድር "በጭራሽ እዚሁ ነኝ ንግግራችሁን ጨርሱ ብዬ ነው" አላቸው ማይለፍ "በቃ እንግዲህ እንገናኛለን ቃልዬ ቁጥርሽ የበፊቱ ነው አይደል ? እደውላለው" አለኝ አቶ እስክንድር "አዎ እሺ እንገናኛለን" አልኳቸው.... ከማለፍ ጋር በዓይን ቻው ተባብለው ወደ መቀመጫቸው ተመለሱ.... እንኳን ከዚህ በላይ አልዘባረቁ ብዬ ፈጣሪዬን እያመሰገንኩ ሳለሁ ማይለፍ... "ከዚህ እንውጣ!" አለኝ በተቆጣ አነጋገር....ብደነግጥም ምንም ሳልናገር ተከትዬው ወጣሁ....መኪናው ውስጥ እንደገባን.... "ዳይመንድ ትሄጂ ነበር ?" አለኝ "እእ አዎ እዛ እሰራ ነበር እና ደሞ ከጓደኞቼ  ጋር እዛው እንዝናና ነበር" "ዳይመንድ ማለት እኮ ሴሰኝነትን ከወንዱ እስከ ሴቱ እንደ ጀብድ እሚቆጥሩበት... የርካሽ ሰዎች መናሀሪያ ነው እንዴት አንቺ እዛ ተገኘሽ...  ደሞስ በዚህ ደረጃ ታዋቂ የሆንሽው በምን ምክንያት ነው  ?" ብሎ በጥያቄ አፋጠጠኝ። መጠየቁ ልክ ሆኖ ሳለ ንግግሩ ትንሽ ከስርዓት የወጣ በመሆኑ ተበሳጨሁ ! "እና እዛ መገኘቴ ርካሽ ለመሆኔ ማረጋገጫ ነው እንዴ ?" "እንደዛ እያልኩኝ ሳይሆን እዛ ቦታ ትገኛለሽ ብዬ አልጠበኩም ሲቀጥል ደግሞ እነ አቶ ሰለሞን ማለት እኮ እንኳን ዳይመንድ የተገኘች ሴት ቀርቶ መንገድ ላይ ፈገግ ያለችላቸውን ሴት ሳይቀር አልጋ ላይ ይዘው ካልወጡ እንቅልፍ እማይወስዳቸው ሴሰኞች ናቸው" .......ንግግሩን ሳይጨርስ አቋረጥኩት "ስለዚህ በተዘዋዋሪ ከእነሱ ጋር ማደሬን እየነገርከኝ ነው ?" "አልወጣኝም ግን ደግሞ ዳይመንድ መሄድሽ ግራ አጋብቶኛል... ጓደኞችሽስ የትኞቹ ናቸው አስተዋውቀሽኝም አሳይተሽኝም አታውቂም የዚህን ያህል የዳይመንድ ፈርጦች እስከመባል ያደረሳችሁ ነገር ምንድነው እውነተኛዋስ ቃልኪዳን ማናት እኔ ያፈቀርኳት ወይስ እነ ሰለሞን ያወሩላት ? መቼስ ዳይመንድ መፅሀፍ ቅዱስ አምብበሽላቸው አደለም የወደዱሽ" ብሎ ንቀት በተሞላበት አነጋገር አፈጠጠብኝ.... ከሱ ያልጠበቁት አወራር ስለሆነ ደርቄ ቀረሁ... "ምነው እውነት ስለሆነ መልስ አጣሽ አደል" አለኝ "ታውቃለህ አሁን አንተ ያልካትን ቃልኪዳን እምሆነው መልስ ከሰጠሁክ ነው ! አንድ ነገር ግን ልንገርህ አንተም ብትሆን ዳይመንድ የሄድከው እና የዚህን ያህል ስለ ዳይመንድ ያወከው ለቅዳሴ ሄደህ አይደለም ! አመሰግናለሁ" ብዬ ከመኪናው ወረድኩኝ.... እያለፈ የነበረ የላዳ ታክሲ አስቁሜ ወደ ቤቴ መሄድ ጀመርኩ.....በዚህ ልክ እንዴት ሰውን መገመት ቀላል ይሆናል ? ሳያዳምጡ ሳይጠይቁ ሳያረጋግጡ መፍረድ ቀላል ነው እንዴ ? ስለ እኔ በቅጡ እንኳን ሳያውቅ እንዴት እንዲህ ይናገረኛል.... በርግጥ ስለዳይመንድ ያወራው ሁሉ ልክ ነው ነገር ግን ዳይመንድ መገኘቴ ብቻ እንዴት የኔን ማንነት ያራክሰዋል ..... ቆይ እስር ቤት የገባ ሁሉ ወንጀለኛ ነው እንዴ ?  ቤተክርስቲያን የሄደ ሁሉ ፃድቅ ነው እንዴ ? ....  ሰው በዋለበት እና በለበሰው ነገር ሊገመገም ይገባል ብዬ አላስብም....በየትኛው ንፁህነታችን ነው በሌሎች ጫማ ውስጥ ተቀምጠን ፍርድ እምንሰጠው....ማንም ይሁን ማንም በህይወቱ ስለሚሆነው እና ሰለሚያደርገው ነገር ሊጠይቀውም ሊፈርድበትም እሚገባው የፈጠረው አምላኩ ብቻ ነው ባይ ነኝ።  ማይለፍ በዚህ ልክ አውርዶ ይመለከተኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ከሚፈርድብኝ ቀድሞ እኔ እንዳስረዳው በአግባቡ ቢጠይቀኝ አንድም ሳላስቀር እነገረው ነበር እሱ ግን ቀድሞ ወነጀለኝ። "የኔ እህት ያልሽኝ ቦታ ደርሰናል" እሚል ድምፅ ከገባሁበት ሀሳብ አነቃኝ "እእ እሺ አመሰግናለሁ"  ሂሳቡን ከፍዬ ስወርድ... "እናት"........ ብሎ መስኮቱን ከፈተና ..... "አንድ ነገር ማለት ፈልጌ ነበር ፍቃድሽ ከሆነ"..... አለኝ በተረጋጋ ድምፅ " እሺ ምንድነው ?" መለስኩለት "ስላንቺ ባላውቅም ያለቀሽበት ምክንያት ባይገባኝም እንባሽ ግን ለእውነተኛነትሽ ምስክር ነው። ለሰዎች ብለሽ እሚያምሩት አይኖችሽን አታድክሚያቸው....ሰላም እደሪ" አለኝ... ንግግሩ በጥቂጡም ቢሆን ፈገግ አስባለኝ። "በጣም አመሰግናለሁ ፈጣሪ ያክብርልኝ ፤ አሜን ሰላም እደር" .....ብዬ ተሰናብቼው ወደ ቤቴ ገባሁ..... ይቀጥላል....... ቀጣዩ ክፍል ከ100❤️ በኋላ ይለቀቃል። ✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯        @Ketbeb_Mender         @Ketbeb_Mender  ✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
Show all...

የ #yohabi ደብዳቤ የማይድን ናፍቆት.... 'የተረሳው ክፍል' "ስትሄድ ያልከኝን መርሳት አቅቶኛል" ✍🏽 : @yohabi_24
Show all...
ደስ የሚል በአል! @ilovvl @ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ
Show all...
"የምሰራች" ዮም:ፍስሀ:ኮነ:በእንተ:ልደቱ:ለክርስቶስ!! ትህትናን፣ፍቅርን የሰውን ዋጋ በበረት በመወለድ:አስተማረን!! ወልድ:ሲወለድ:የሰው:ልጅ የሚፈልገውን: አምላክነት:በእሱ:አገኘ:: ውድ የግጥም ቃና ቤተሰቦች እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰለም አደረሰህን 🙏 መልካም በአል @ilovvll @ilovvll @ilovvll 👈 ቤተሰብ ይሁኑ አብሮነትዎም አይለየን
Show all...
Repost from N/a
🎬 FERA MOVIES GALLERY ቻናላችን ላይ ሚያገኞቸው ፊልሞች፡ 🎞 ኢንግሊዘኛ ፊልሞች በትርጉም፡ 🎞 የህንድ ፊልሞች በትርጉም፡ 🎞 ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም፡ 🎞 የቱርክ ተከታታይ ፊልሞች: 🎞 ANIMATION MOVIES በትርጉም : 🎞 የታዋቂ አክተር ፊልሞች በትርጉም : 🎞  አክሽን ፊልሞች በትርጉም: 🎞 ADVENTURE FILM በትርጉም: 🎞 HD ትርጉም የሌላቸው ፊልሞች፡ 🎞 HD KORIA DRAMA : 🎞 አማርኛ ፊልሞችን እንደወጡ ያገኛሉ፡፡ ሁሉንም አይነት ፊልሞች በቅርብ ቀን በቻናላችን ይጠብቁን። t.me/fera_Movie_Gallery t.me/fera_Movie_Gallery t.me/fera_Movie_Gallery
Show all...
Fera Movie Gallery ™📽️

✌️ You're No.1 Movie Choice✌️

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️ ክፍል 26     ✍ደራሲ - አብላካት አቶ ሰለሞን እና አቶ እስክንድር ጋር ስንደርስ .....ሁለቱም ተያዩና ቃልኪዳን አለኝ አቶ እስክንድር በመጠራጠር ስሜት ውስጥ ሆኖ.... " አዎ አልተሳሳትኩም ቃል ነሽ" አለኝ..... አቶ ሰለሞንም ቀጠል አድርጎ " ቢረሳ ቢረሳ እንዴት የዳይመንድ ፈርጦች ይረሳሉ ? ከሁሉም በላይ ደሞ ቃል አንቺን አለማስታወስ በእውነቱ ንፉግነት ነው" ብሎ ፈገግ አለ........ምን ቤተክርስቲያን ሳስቀድስ እና ስዘምር ወይ በጎ ነገር ስሰራ እንዳየ ሰው አለማስታወስ ንፉግነት ነው ይላል... ባያስታውሰኝ ነበር እኮ እሚሻለኝ...... በቃ እኛ ሰዎች አሉባልተኛ ሆነን ቀረን ማለት ነው ? .....ምናለ በደህና ነገር ብንተዋወስ .... ማይለፍ ግራ በመጋባት ስሜት ውስጥ ሆኖ አይኑን ከአንዳችን ወደ አንዳችን እያንከባለለ ይቃኘናል... "ምነው ሰላም አትይንም እንዴ ቃል" አለኝ አቶ እስክንድር... "በጣም ይቅርታ ሀሳብ ውስጥ ሆኜ ነው እንዴት ናችሁ ?" ብዬ ተራ በተራ ጨበጥኳቸው "እኛማ ደህና ነን እናንተ የውሀ ሽታ ሆናችሁ ከራችሁ እንጂ... እንደቀልድ ብዙ ወራት ሆናችሁ ወደ ዳይመንድ ከመጣችሁ የቤቱ ድምቀት እናንተ ነበራችሁ" አለ አቶ ሰለሞን "አዎ ረጅም ጊዜ ሆነን ከተያየን..... ደሞም እዚህም ቢሆን ጓደኞችሽን እስካሁን አላየኋቸውም ብቻሽን ነው እንዴ የመጣሽው ?" አለኝ አቶ እስክንድር ቀጠል አድርጎ "ፈራ ተባ እያልኩም ቢሆን መመለሴ ግድ ሆነ...አዎ ከዳይመንድ ከራቅን ረጅም ጊዜ ሆኖናል ወደዛ አካባቢ መተን አናውቅም... ጓደኞቼ ደህና ናቸው ዛሬ ከማይለፍ ጋር ነው የመጣሁት ለዛ ነው" አልኳቸው "በሰላም ከሆነ እሺ..ልጅ ማይለፍ ምነው በዝምታ ተዋጥቅ ? ችግር አለ እንዴ ?" አለ አቶ እስክንድር "በጭራሽ እዚሁ ነኝ ንግግራችሁን ጨርሱ ብዬ ነው" አላቸው ማይለፍ "በቃ እንግዲህ እንገናኛለን ቃልዬ ቁጥርሽ የበፊቱ ነው አይደል ? እደውላለው" አለኝ አቶ እስክንድር "አዎ እሺ እንገናኛለን" አልኳቸው.... ከማለፍ ጋር በዓይን ቻው ተባብለው ወደ መቀመጫቸው ተመለሱ.... እንኳን ከዚህ በላይ አልዘባረቁ ብዬ ፈጣሪዬን እያመሰገንኩ ሳለሁ ማይለፍ... "ከዚህ እንውጣ!" አለኝ በተቆጣ አነጋገር....ብደነግጥም ምንም ሳልናገር ተከትዬው ወጣሁ....መኪናው ውስጥ እንደገባን.... "ዳይመንድ ትሄጂ ነበር ?" አለኝ "እእ አዎ እዛ እሰራ ነበር እና ደሞ ከጓደኞቼ  ጋር እዛው እንዝናና ነበር" "ዳይመንድ ማለት እኮ ሴሰኝነትን ከወንዱ እስከ ሴቱ እንደ ጀብድ እሚቆጥሩበት... የርካሽ ሰዎች መናሀሪያ ነው እንዴት አንቺ እዛ ተገኘሽ...  ደሞስ በዚህ ደረጃ ታዋቂ የሆንሽው በምን ምክንያት ነው  ?" ብሎ በጥያቄ አፋጠጠኝ። መጠየቁ ልክ ሆኖ ሳለ ንግግሩ ትንሽ ከስርዓት የወጣ በመሆኑ ተበሳጨሁ ! "እና እዛ መገኘቴ ርካሽ ለመሆኔ ማረጋገጫ ነው እንዴ ?" "እንደዛ እያልኩኝ ሳይሆን እዛ ቦታ ትገኛለሽ ብዬ አልጠበኩም ሲቀጥል ደግሞ እነ አቶ ሰለሞን ማለት እኮ እንኳን ዳይመንድ የተገኘች ሴት ቀርቶ መንገድ ላይ ፈገግ ያለችላቸውን ሴት ሳይቀር አልጋ ላይ ይዘው ካልወጡ እንቅልፍ እማይወስዳቸው ሴሰኞች ናቸው" .......ንግግሩን ሳይጨርስ አቋረጥኩት "ስለዚህ በተዘዋዋሪ ከእነሱ ጋር ማደሬን እየነገርከኝ ነው ?" "አልወጣኝም ግን ደግሞ ዳይመንድ መሄድሽ ግራ አጋብቶኛል... ጓደኞችሽስ የትኞቹ ናቸው አስተዋውቀሽኝም አሳይተሽኝም አታውቂም የዚህን ያህል የዳይመንድ ፈርጦች እስከመባል ያደረሳችሁ ነገር ምንድነው እውነተኛዋስ ቃልኪዳን ማናት እኔ ያፈቀርኳት ወይስ እነ ሰለሞን ያወሩላት ? መቼስ ዳይመንድ መፅሀፍ ቅዱስ አምብበሽላቸው አደለም የወደዱሽ" ብሎ ንቀት በተሞላበት አነጋገር አፈጠጠብኝ.... ከሱ ያልጠበቁት አወራር ስለሆነ ደርቄ ቀረሁ... "ምነው እውነት ስለሆነ መልስ አጣሽ አደል" አለኝ "ታውቃለህ አሁን አንተ ያልካትን ቃልኪዳን እምሆነው መልስ ከሰጠሁክ ነው ! አንድ ነገር ግን ልንገርህ አንተም ብትሆን ዳይመንድ የሄድከው እና የዚህን ያህል ስለ ዳይመንድ ያወከው ለቅዳሴ ሄደህ አይደለም ! አመሰግናለሁ" ብዬ ከመኪናው ወረድኩኝ.... እያለፈ የነበረ የላዳ ታክሲ አስቁሜ ወደ ቤቴ መሄድ ጀመርኩ.....በዚህ ልክ እንዴት ሰውን መገመት ቀላል ይሆናል ? ሳያዳምጡ ሳይጠይቁ ሳያረጋግጡ መፍረድ ቀላል ነው እንዴ ? ስለ እኔ በቅጡ እንኳን ሳያውቅ እንዴት እንዲህ ይናገረኛል.... በርግጥ ስለዳይመንድ ያወራው ሁሉ ልክ ነው ነገር ግን ዳይመንድ መገኘቴ ብቻ እንዴት የኔን ማንነት ያራክሰዋል ..... ቆይ እስር ቤት የገባ ሁሉ ወንጀለኛ ነው እንዴ ?  ቤተክርስቲያን የሄደ ሁሉ ፃድቅ ነው እንዴ ? ....  ሰው በዋለበት እና በለበሰው ነገር ሊገመገም ይገባል ብዬ አላስብም....በየትኛው ንፁህነታችን ነው በሌሎች ጫማ ውስጥ ተቀምጠን ፍርድ እምንሰጠው....ማንም ይሁን ማንም በህይወቱ ስለሚሆነው እና ሰለሚያደርገው ነገር ሊጠይቀውም ሊፈርድበትም እሚገባው የፈጠረው አምላኩ ብቻ ነው ባይ ነኝ።  ማይለፍ በዚህ ልክ አውርዶ ይመለከተኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ከሚፈርድብኝ ቀድሞ እኔ እንዳስረዳው በአግባቡ ቢጠይቀኝ አንድም ሳላስቀር እነገረው ነበር እሱ ግን ቀድሞ ወነጀለኝ። "የኔ እህት ያልሽኝ ቦታ ደርሰናል" እሚል ድምፅ ከገባሁበት ሀሳብ አነቃኝ "እእ እሺ አመሰግናለሁ"  ሂሳቡን ከፍዬ ስወርድ... "እናት"........ ብሎ መስኮቱን ከፈተና ..... "አንድ ነገር ማለት ፈልጌ ነበር ፍቃድሽ ከሆነ"..... አለኝ በተረጋጋ ድምፅ " እሺ ምንድነው ?" መለስኩለት "ስላንቺ ባላውቅም ያለቀሽበት ምክንያት ባይገባኝም እንባሽ ግን ለእውነተኛነትሽ ምስክር ነው። ለሰዎች ብለሽ እሚያምሩት አይኖችሽን አታድክሚያቸው....ሰላም እደሪ" አለኝ... ንግግሩ በጥቂጡም ቢሆን ፈገግ አስባለኝ። "በጣም አመሰግናለሁ ፈጣሪ ያክብርልኝ ፤ አሜን ሰላም እደር" .....ብዬ ተሰናብቼው ወደ ቤቴ ገባሁ..... ይቀጥላል....... ቀጣዩ ክፍል ከ100❤️ በኋላ ይለቀቃል። ለደራሲዋ @A_b_l_a_k_a_t ላይ አስተያየታችሁን ማድረስ ትችላላችሁ🙏 ✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯        @Ketbeb_Mender         @Ketbeb_Mender  ✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
Show all...

❤️
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️ ክፍል 25     ✍ደራሲ - አብላካት "ሰላም ነው ማይለፍ ?" "ፈጣሪ ይመስገን። በሰላም ነው ስልክሽ ዝግ የነበረው ?" "አዎ ትንሽ ደክሞኝ ስለነበር ነው በጣም ይቅርታ" "ይቅርታ እንኳን አያስፈልገውም እንዲሁ ስለጨነቀኝ ነው። ክላስ ወይ ስራ የለም እንዴ ?" "ዛሬ ሁሉትም ጋር መሄድ ስላል ፈለኩኝ ነው" "ምነው በሰላም ?" "አንዳንዴ እረፍት ያስፈልግ የለ" "እሱስ ልክ ነሽ። እና የት ሆነሽ ነው ?" " ከቤተክርስቲያን እየወጣሁ" "ቁርስ አልበላሽማ እሚመችሽ ከሆነ እኔም ስላልበላሁ አብረን እንብላ ?" " እሺ ደስ ይለኛል" "ሰፈራችሁ ያለው ቤተክርስቲያን ነው አደል ?" "አዎ" "እሺ መጣሁኝ" ብሎ ስልኩ ተዘጋ።ሁሉ ነገር ተስተካክሎልኝ ሁሌም አብሬው ደስተኛ ብሆን ምነኛ በታደልኩ...ምን ያደርጋል ህይወት ሁሌ አይሞላም አንዱን ስንል አንዱ እየተደራረበ መፈናፈኛ ያሳጣል....ላጣው አልፈልግም በጣም አፈቅረዋለው... ግን ሁኔታዎች ያስፈሩኛል በዚህ ሰዓት እናቴን በቻልኩት መጠን ልረዳት ይገባኛል ማንም እሚያግዛት የለም ሁሉም መቀበልን እንጂ መስጠትን አይፈልጉም.... የእንጀራ አባቴ እንደ ቤት አባወራነቱ ሰርቶ ቤተሰቡን ማስተዳደር ሲገባው እሱ ግን ከእናቴ ይጠብቃል ጭራሽ አረቄ ቤት ሄጄ እምጠጣበት ብር ስጭኝ ብሎ አፉን ሞልቶ ሲጠይቃት አንቀሽ ግደይው ግደይው እሚል ስሜት ይሰማኛል። ወይ የባልነት ወይ የአባትነት ሀላፊነቱን እማይወጣ ሰው ከሰው ሊቆጠር አይገባውም። ልጆቹም ከየአማን በስተቀር እንደሱ ቀንቱዎች ናቸው እንኳን ለሰው ለራሳቸው እንኳን እማይሆኑ እርባናቢሶች። ስልችት ብሎኛል የሊድያንና የየአማንን ትምህርት ቤት ፣ የመብራት ፣ የውሀ ፣ አስቤዛ ስንቱን ልቻለው የራሴም ወጪዎች አሉብኝ አሁን ትምህርት ተጀምሯል ስንት ነገር ያስፈልገኛል የቀን በቀን የታክሲ ወጪ በምኔ ይሄን ሁሉልሸፍነው ? ከየት ላምጣ ደመወዜ የየአማንን ትምህርት ቤትና የመብራት ብቻ ነው እሚችልልኝ የበፊቱ ስራዬ ይሻል ነበር እሱን ደሞ እድሜ ለእነ ሳቢ መተዌ ግድ ሆነ። አሁን የትምህርታቸውም የመብራት ክፍያም ደርሷል ኧረ ሳያልፍ አይቀርም ማታ ትቻቸው ብገባም ሊድያ ብር ስትላት ሰምቻለው። ስለ ሁሉም እግዚአብሄር ያውቃል በፊት በፊት ሳቢዬ ታግዘኝ ነበር ዛሬ ግን እሷም የለችም። ድንገት ከኋላዬ ማይለፍ መቶ ከገባሁበት ሀሳብ አባነነኝ.... "ምንድነው እንደዚህ በሀሳብ ጭልጥ ማለት ?" "ይቅርታ አላየሁክም ነበር ብዙ ቆየህ ?" "ለነገሩ ተሳልሜ ነው የመጣሁት። ከጨረስሽ እንሂድ" አለኝ "ጨርሻለው" ብዬው ወጣን። "ወደየት እንሂድ ?" "እኔ እንጃ አንተን ደስ ወዳለህ ቦታ" አልኩትና ወደሚያቀው ቁርስ ቤት ሄድን። ያዘዝነው ቁርስ እስከሚመጣ ማይለፍ... "አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ?" አለኝ... "ትችላለህ" "ማለት በሌላ መንገድ አትይው እና እውነት ታፈቅሪኛለሽ ስልሽ እኔ እንዳፈቀርኩሽ ስለነገርኩሽ ነው እሺ ያልሽኝ ወይስ ፈልገሽው ነው ?" "ለምን ጠየከኝ ?" "አለ አደል ደስተኛ የሆንሽ አይመስለኝም ከእኔ ጋር ሆነሽ እንኳን ሀሳብ ሌላ ቦታ ነው ምናልባት ለእኔ አዝነሽ ከሆነ እሺ ያልሽኝ ብዬ አስቤ ነው" አለኝ። በእርግጥ መጠየቁ ልክ ነው እንደ ሁኔታዬ እንለያይ አለማለቱም እሱ ሆኖ ነው... "እዮልህ ማይለፍ ይገባኛል ግን አንተን አለመፈለግ ሳይሆን ያለሁበት ሁኔታ ትክክል ስላል ሆነ ነው ብትረዳኝ ደስ ይለኛል የእውነት አፈቅርሀለው" ብዬ መለስኩለት..... "እንደዛ ከሆን እሺ" አለኝና ያዘዝነውን ቁርስ አብረን በላን። እሱ ስብሰባ ስለነበረው እምትሄጂበት ከሌለሽ ስራ ቦታ አብረን እንሂድ ብሎኝ አብረን ሄድን። እሱ ከስብሰባ እስኪወጣ እዛው መስሪያ ቤት ካሉት ሌሎች ሰራተኞች ጋር ደስ እሚል ጊዜ አሳለፍኩኝ። ስለምን እንደሆነ ባላውቅም ከሁለት ሰዓት በኋላ ከስብሰባ ወጡ። ከተሰብሳቢዎቹ መሀል ከእነ ሳቢ ጋር ለመዝናናት ስንወጣ እምናገኛቸው ቱጃሮችም አሉ...ምነው ባላስተዋልኩኝ እያልኩ አንጋጥቼ ፈጣሪዬን ተማፀንኩት። በእርግጥ ያደረኩት ምንም አይነት አሳፋሪ ተግባር ባይኖርም ግን ደግሞ ስለ አቶ መላኩ እንዲሰማ አልፈልግም..... በእዛ ላይ ለብዙ ሰዎች ዳይመንድ እሚሄዱ ሴቶች ከባለሀብቶቹ ጋር አብረው ተኝተው ገንዘብ ለማግኘት እንድሆነ አድርገው ነው እሚያስቡት። ምናልባት እሱም እንደዛ ካሰበ ለማሳመን ይከብደኛል....ደሞም ከአንዳንዶቹ ጋር ከዳይመንድ ውጪ አብሮ ምሳ እና እራት እስከመብላት ከውጪ እቃ እስከማስመጣት እሚያደርስ ግንኙነት ነበረኝ። እዚህ ካሉት ከአቶ ሰሎሞን እና ከአቶ እስክንድር ጋርም በተለይ ከአቶ እስክንድር ጋር ጥሩ ቀረቤታ ነበረኝ ፤  ለዚህ እንጂ ሌላ አይደለም። ከስብሰባው በኋላ የምሳ ግብዣ ስለነበር ወደዛ እንድንሄድ ጠየቀኝ.....እኔ ይቅርብኝ ብለውም ካልሄድሽ እኔም እቀራለው ብሎ ድርቅ ሲል እያቅማማሁም ቢሆን እሺ ብለው ሄድን። ትልቅ ሆቴል ነበር ግብዣው የለበስኩት ቀሚስም ያን ያህል ደባሪ አልነበረም....ምሳ ተበልቶ ከተጨረሰ በኋላ ነይ ሰዎችን ላስተዋውቅሽ ብሎኝ በእየ ጠረጴዛው እየዞርን ሰላም እያልን አቶ ሰሎሞን እና አቶ እስክንድር ጋር ደረስን...... ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​ይቀጥላል....   ✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯          @Ketbeb_Mender           @Ketbeb_Mender  ✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯

ሰላም እንደምን አላችሁ ውድ የብዕር ጠብታ ቤተሰቦች ቃላችንን አክብረን እዮሪካን መቀጠል ባለመቻላችን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን። ነገር ግን ታሪኩን የወደዱትን እና ከልብ የተከታተሉትን ቤተሰቦች አለማክበር ሳይሆን በሁኔታዎች አለመመቸት እንደሆነ እንድትረዱን በአክብሮት እንጠይቃለን። በመሆኑም እዮሪካ ክፍል 26 ዛሬ ማታ 1:00 ላይ ይለቀቃል። እናመሰግናለን🙏
Show all...