en
Feedback
ኡመተ ረሱል

ኡመተ ረሱል

Open in Telegram

የአላህ ሰላም እና እዝነት በናንተ ላይ ይውረድ ውድ የአላህ ባሮች በዚህ #channel ላይ የተለያዩ ♥ ኢስላማዊ አስተምህሮቶች ♥ አስተማሪ ታሪኮች ♥ ቀልዶች እና ♥ ወቅታዊ አሳሳቢ ነገሮችን ወደናንተ እናደርሳለን ፨ ፨ ፨ ለማንኛውም አስተያየት @Ummate_resul_bot ይጠቀሙ

Show more
1 977
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-2930 days
Posts Archive
ይህ ሁለት ገፅታ ያለው ሰው ማን ነው?! እጅግ ልብን የሚያደማ የኢራቁ ፕሮፌሰሩ ታሪክ በተቀዳደደ ልብስና በቆሸሸ ድሪቶ ሰውነቱን ሸፍኖ በኢራቅ ጎዳናዎች ላይ ይዘዋወራል። ግና ምድር ላይ የሚራመድ ሊቅ በሁለት እግሩ የሚጓዝ የአቶሚክ ቦንብ ሳይንቲስትና ፕሮፌሰር ነበር። ኢራቃውያን ተማሪዎች የከበዳቸው የትምህርት ዘርፍ ሲኖር ወደ እሱ በማቅናት ይጠይቁታል። እሱም አስፓልት ዳር በጣቱ ሲጋራውን ይዞ ፀጉሩን እየፈተለ ፈትፍቶ ያስረዳቸዋል። ዶክተር ሃሚድ ኸለፍ አል-ኦካይሊ ይሰኛል። ትውልደ ኢራቃዊ ነው። በኮምፕሌክስ አቶሚክ ቦንብ ዶክተር በኒውክለር ኬሚስትሪም ፕሮፌሰር ነው። የካምብሪጅ ብሪቲሽ ዩኒቨርሲቲ ሌክቸሩ ሃሚድ የቆሸሸውን ልብሱን አጥልቆ ረዥም ፀጉሩ ከመሬት አፈር ጋር ተለውሶ ለሚመለከተው ሁሉ በእጅጉ አግራሞትን ይጭራል። አዋቂው እብድም ይሉታል። ዕድሜ ለአሜሪካ! ሙሉ ቤተሰቦቹን በጅምላ ሲገድሉበት በዓይን በብረቱ ተመልክቷል። ለወሬ ነጋሪነት እንኳ አንድም አላስተረፉለትም። እናት አባቱ ልጆቹ ሚስቱ ፊት ለፊቱ ነበር የወደቁት። ይህን ልብ አድሚ ክስተት እያነባ ሲመለከት ቆይቶ ከህመሙ ጋር እንዲኖር በካቴና ተጠፍሮ ወደ እስር ቤት አቀና። እስር ቤት መኖርያው ሆነ። ዘወትር ጁሙዐ ከሌሎች ቀናቶች በተለየ ሽንት ቤት መቀመጫ ላይ በአፉ ተገልብጦ እርቃኑን ከብረት ጋር ተጠፍሮ የሽንትና የሰገራ ሽታ በአፍ በአፍንጫው እየተጋተ ያሳልፋል። እንደ እንሰሳ አንገቱ ላይ ሰንሰለት ተደርጎ በተከበረ ፊቱ ይጎተታል። መሬት ላይ የወዳደቁ ቆሻሻዎችን በምላሱ እያፀዳ በርካታ ቀንና ለሊቶችን ለረጅም ሰአት እየቆመ አሳለፈ። ትንሽ ከስቃዩ ፋታ ሲያገኝ በሐሳብ ጭልጥ ብሎ ቤተሰቦቹን ያስታውሳል። እናቱ በአሜሪካ ወታደሮች ተጨፍጭፋ ስትገደል ልጆቹ እግሩ ስር እየተወራጩ ሲያነቡ በወታደሮቹ ከስክስ ጫማ እየተረገጡ ሲደፈጠጡና የጥይት እራት ሲሆኑ ያስታውሳል። አዎ መጥፎ ትውስታውና ቶርቸሩ ተደራርቦ በደረሰበት ስቃይ የአዕምሮ በሽተኛ ሆነ። ከእስር ቤት ሲወጣ ቤትና ንብረቱ እንኳ አልተረፈ ሁሉም ተዘርፎ ባዶ ቀረ። አዎ ማንኛውም ሙስሊም በመስቀላዊያኖች እየተሰራች ባለችው በአዲሲቷ የአለም ስርአት ውስጥ ሳይንቲስት የመሆን መብት የለውም። ሰምተን ዓይናችን ሳያነባ በዝምታ ያለፍናቸው ብዙ መሰል ታሪኮች ይኖራሉ። እኛ ብንረሳቸውም አላህ ግን ፈፅሞ የማይረሳቸው በእርግጥም የእርሱ ባሮች አሉ። መገን አላህዬ አቻቻልህኮ። #ሼር #share #join Https://t.me/smithhk

ሩሖች ከስጋ ሳይዋኃዱ፣ ስጋዎች ከአፈርም ከፍትወት ጠብታም ሳይገነቡ፣ ምድርን ሰፋሪዎች ሳይሰፍሯት ምድር ሳትዋቀር በልዕላነ-አለሙ እንዲህ ሆኖ ነበር። በሩሆች መከማቻ ስፍራ ህልቆ መሳፍርት ሩሆች ከሚገኙበት መንፈሰ-አለም ውስጥ አላህ 124 ሺህ ሩሆችን መርጦ ከችሎተ - መለኮት ፊት አቆማቸው። የዙፋኑ ጌታ ችሎቱን ያስደምጥ ጀመር። «እናንተ ነብያት ሆይ! ወደ ምድር ወርዳችሁ ከኔ የሚመጡትን ትዕዛዛት ለባሮቼ ለማስተላለፍ መፃሕፍትን እና ጥበብን በሰጠኋችሁ ግዜ ሙሐመድ የተሰኘው ነብይ በእናንተ ዘመን ቢመጣ በሱ አምናችሁ ልትተባበሩትም ትገደዳላችሁ።» ስፍራው በዝምታ ተውጧል። የዙፋኑም ባለቤት ንግግሩን ቀጥሏል፦«ተስማምታችኋልን....? አሁን ባልኳችሁም በሙሀመድ ጉዳይ ቃል ኪዳንን ያዛችሁን? » «ተስማምተናል፤ ታዛዦች ነን» ብለው ለነቢ ደረሳ ለመሆን እጅ ነሱ። «እንግድያውስ ለመስማማታቹ ማስረጃ ይሆን ዘንድ በነፍሶቻችሁ ላይ መስክሩ፤ እኔም ከመስካሪዎች ነኝ» አለ። «ነገር ግን...» የዙፋኑ ባለቤት ንግግሩን ቀጠለ። «ይህን ቃል ኪዳን ከገባችሁ በኋላ ከእናንተ ውስጥ ሙሀመድን ከመታዘዝ የሚያፈነግጥ ካለ እሱ ወራዳ ይሆናል» ነብያት ቃል ኪዳን ገብተው ሙሀመድንም አልቀው ለመታዘዝ ተስምተው የቃል ኪዳን ስፍራውን ለቀቁ። ምድር ተዋቅራ ነዋርያኑን ማስተናገድ በጀመረችበት ግዜም ነብያቱ በየተራቸው ይተካኩ ጀመር። ሁሉም ነቢያት ያላዩትን ሙሀመድ ሰዐወ ሲናፍቁ የናፍቆት ጥማቸውን ሳይቆርጡም ዱንያን ተሰናበቱ። ከሱ በፊት የነበሩትም ሆኑ ከሱ በኋላ የሚመጡ ህዝቦች ሲናፍቁት የሚኖሩለት ክቡር ስብዕና። ቁጥር ማያካብበው የሰለዋት እና የተብሪካት አይነቶች በመለኮት መአዛ ታውደው እስከ እለተ ቂያማ ድረስ በነቢያቱ ንጉስ ላይ ይሁኑ። #ሼር #share #join Https://t.me/smithhk

ካሜራማኑ ህፃኗ ያለችበት ሁኔታ አሳዝኖት ሊቀርፃት ሲጠጋት እርሷ ደግሞ ሲጠጋት የተራበ መስሏት ከምትበላው ልታካፍለው እጇን ወደርሱ ዘረጋችለት ድህነት ምንኛ አስቀያሚ ነገር ነው ዳሀዎች ምንኛ ንፁህ
ካሜራማኑ ህፃኗ ያለችበት ሁኔታ አሳዝኖት ሊቀርፃት ሲጠጋት እርሷ ደግሞ ሲጠጋት የተራበ መስሏት ከምትበላው ልታካፍለው እጇን ወደርሱ ዘረጋችለት ድህነት ምንኛ አስቀያሚ ነገር ነው ዳሀዎች ምንኛ ንፁህ ልብ አላቸው❤

🏹🏹🏹🏹🏹🏹🏹🏹 አስማእ ቢንት አቡበከር ልጇ አብደላህ በአንድ ዘመቻ ወቅት የጦር መከላከያ ልብስ ደረቱ ላይ ለብሶ ሊሰናበታት መጣ መከላከያውን አይታ አለቀሰችና እንዲህ አለች 《ልጄ ሆይ !!! ሞትን የሚፈልግ ሰው አልፎ ተርፎም ሸሂድ ሆኖ አላህ ዘንድ ይሸመግለናል ብለን የምናስበው ልጃችን ደረቱ ላይ ይህን መሰል መከላከያ እንዴት ይለብሳል?! ወላሂ ይህን ለብሰህ ብትሞት ፈፅሞ አልቀብርህም።》 በእስልምና ታሪክ ውስጥ ሴቶች የተጫወቱት ሚና ቀላል አልነበረም አስማእን መሰል እናቶች ያስፈልጉናል علموا بناتكم كيف يصنعون الرجال #ሼር #share #join Https://t.me/smithhk

ጌታችን ሲያጣቅም እንዲህ ነው😊 አንዱ ቤተሰባችን ዛሬ ዐሹራን ፆሞ ነገር ግን ሁለት ጊዜ ረስቶ (ቁርስና ምሳውን) ድብን አድርጎ በልቷል።😁 ያው ከ8 ሰአት በኋላ ያለውን ፆሟል አላህ ይቀበለው። ደስ የሚለው ማፍጠሪያ ላይ ለማካካስ ውሃ ብቻ ነው የጠጣሁት አለኝ 😁 «ፆመኛ ሆኖ ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ፆሙን ይቀጥል።የመገበውና ያጠጣው አላህ ነውና» (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

عن ابن عباس رضي الله عنهما قال : قدِمَ النبي ﷺ المدينةَ ، فرأى اليهودَ تَصومُ يومَ عاشُوراءَ ، فقال : ((مَا هَذَا؟)) قالوا : هذا يومٌ صالِحٌ ، هذا يومٌ نجَّى اللهُ بَني إسرائيلَ مِن عدُوِّهِم ، فصامَهُ مُوسَى ، قال : ((فَأنَا أحَقُّ بِمُوسَى مِنْكُمْ)) فصَامَهُ وأمرَ بصِيامِهِ. رواه البخاري.

የአሹራ ቀን ➤የአሹራ ቀን ከሙሀረም ወር ቀናት አንዱ ቀን ነው። የሙሀረም ወር ደግሞ ከተከበሩ ቀናት መካከል አንዱ ነው። ➤ከአቢ ሁረይራ በተዘገበው ሀዲስ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል "ከረመዳን በኃላ ታላቁ ፆም የአላህ ወር የሆነው ሙሀረም ነው"። ➤ነብያችን አለይሂ ሰላት ወሰላም ወደ መዲና በመጡ ጊዜ አይሁዶችን የአሹራ ቀንን ሲፆሙ አዩዋቸው ፤ "ለምንድነው የምትፆሙት" ሲሉ ጠየቋቸው እነሱም "ይህ ቀን አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ከጠላታቸው ያዳነበት ቀን ነው ይህን ቀን ሙሳም ፆሞታል" ሲሉ መለሱላቸው። ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እኛ ከናንተ የበለጠ ለሙሳ የተገባን ነን አሉና ያን ቀን ፆሙት፣ሰሀቦችንም አዘዙዋቸው። አብደላህ ኢብኑ አባስ አላህ ስራውን ይውደድለትና እንዲህ ይላል"ነብዩ አለይሂ ሰላት መሰላም የአሹራን ቀን ፆመው ሰሀቦችንም ባዘዟቸው ጊዜ፤ይህ ቀን እኮ የአይሁዶች ቀን ነው ሲሉ ሰሀቦች ጠየቁ፤ የቀጣዩን አመት አላህ ካደረሰን ከሱ በፊት ያለውን(ዘጠነኛውን) እንፆማለን አሉ፤ነገር ግን ቀጣዩ አመት ሳይመጣ ህይወታቸው አለፈ"። ➤በሌላ ሀዲሳቸው ላይ "የአሹራን ቀን መፆም ከሱ በፊት ያለውን የአንድ አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለው" ብለው ተናግረዋል። ➤በጥቅልሉ የሙሀረም ወር የተከበረ ወር እንደመሆኑ መልካም ስራዎችን መጨመር፣ከወንጀሎች የበለጠ መራቅ ተገቢ ነው።በተለየ መልኩ አስረኛውን(አሹራእን) ቀን መፆም በተጨማሪም ከየሁዶች ጋር ላለመመሳሰል ከሱ በፊት ወይም በኃላ እንድ ቀን መጨመር ታላቅ ምንዳ ያለው ስራ ነው። ➤እንግዲ አስረኛው ቀን በአላህ ፍቃድ የሚመጣው ሰኞ ይሆናል # share @smithhk

عن عبدالله بن عمرو رضي الله عنهما ، أنه سمع النبي ﷺ يقول : ((مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلَاةً صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا)) رواه مسلم. «اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ»

photo content

ሰለዋት እናብዛ‼️ 🌴☘🌴☘🌴☘ ምን ያህሎቻችን ነን ጁምዓ ተጠባብቀን በረሱል [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ላይ ሰለዋት የምናወርደው❓❓ ለምንድን ነው ከዚህ ትልቅ ስራ የምንዘናጋው❓❓ 📚እስኪ አላህና መልዕክተኛውን ምን እንደ ሚሉን እንመልከት 👇👇👇 🌴💥🕋🌴💥🕋 قال الله تعالى ﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلّونَ عَلَى النَّبِيِّ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا صَلّوا عَلَيهِ وَسَلِّموا تَسليمًا﴾ [الأحزاب: ٥٦] አላህ እንዲህ ይላል፦ {አላህና መላዒካዎቹ በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ; እናንተ ያመናችሁ ሆይ በእሱ (በነብዩ) ላይ ሰለዋትና ሰላምን አውርዱ} 📖የአላህ መልዕክተኛም እንዲህ ይሉናል👇👇 "أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشرا " و حـسـنه الألباني في السلسلة الصحيحة 1407 {ጁምዓ ቀንና ጁምዓ ሌሊት በእኔ ላይ ሰለዋት አብዙ። በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው በእሱ ላይ አላህ አስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል} "من صلى علي مرة كتب الله له بها عشر حسنات" وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة (٣٣٥٩) {በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው አላህ ለእሱ በዚህ ምክንያት አስር ምንዳ ይፅፍለታል} " من صلى علي من أمتي صلاة مخلصا من قلبه صلى الله عليه بها عشر صلوات ورفعه بها عشر درجات وكتب له بها عشر حسنات ومحا عنه عشر سيئات " وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة ( ٣٣٦٠) {ከኡመቶቼ ውስጥ ከቀልቡ ጥርት አድርጎ በእኔ ላይ ሰለዋት ያወረደ የሆነ ሰው; አላህ በእሷ ምክንያት አስር ሰለዋት ያወርድበታል፣ አስር ደረጃም ከፍ ያደርግለታል፣ አስር ምንዳም ይፅፍለታል፣ አስር ወንጀልም ይሰርዝለታል} " من صلى علي واحدة صلى الله عليه عشرا " رواه أبو داود في سننه (١٥٣٠) وصححه الألباني رحمه الله {በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ በእሱ ላይ አላህ አስር ያወርድበታል} 🌴🌱🌴🌱🌴🌱 "اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد" ✍"ወደ መልካም ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው"‼ #share #Join @smithhk

ያኔ ~ አልቅስ ‼ ▬ ▭▬▭▬▭▬▬▭▱▬ 👉 በነፍስህና በስሜትህ ተበልጠህ ለትናንሽም ሆነ ለትላልቅ ወንጀሎች በቀላሉ እጅ የሰጠህ ቀን። 👉 መልካም ነገርን እያየህ ከመሥራት ስትሰንፍ ፣ መጥፎን ደግሞ መጥፎነቱን እያወቅክ ስትዳፈር። 👉 ለሙዚቃ ፣ ለድራማና ለፊልም ውስጥህ ሲነካ ፡ ለቁርዓን ልብህ ሲደነደን። 👉 ለዱኒያና ለጥቅሞቿ ስትሮጥ እንቅልፍ ስታጣ ለአኺራህ ግድ የለሽ ስትሆን። 👉 ሶላትህ ትርጉም ስታጣብህ ፣ ሩኩዕና ሱጁድ ጎንበስ ቀና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ብቻ ሲሆንብህ። 👉 ከዒባዳህ ጥፍጥና ስታጣ በአምልኮ ተግባርህ እርካታን ከተነፈግክ። 👉 ጊዜህን ባልረባ ነገር ስትጨርስ ፡ ኸይር ሳትጨምር ቀን አልፎ ቀን ከተተካ። 👉 የተውባ በር ሁሌም ክፍት ሆኖ ሳለ ለመግባት ድፍረት ስታጣ። 👉 የዓለማዊው ሕይወት ፍጻሜ መቃረቡን ስታውቅ በበቂ አለመዘጋጀትህን ስትረዳ። 👉 ያኔ አልቅስ ልክ እንደዚህ አይነት መልእክት አይተህ ሼር ሳታደርግ ስትቀር ዝም ብለህ እንደተራ መልእክት አይተኸው ዝም ብለኸው ያለፍክ ቀን በደንብ አልቅስ። #join #share Https://t.me/smithhk

ታሪክ የማይረሳው የኢስላም ታጋይ ዑመር አል ሙኽታር ጣሊያኖች ሊቢያን በግፍ ሲያስተዳድሩ ለበርካታ አመታል ሲታገል ከቆየ በኋላ በጣሊያን የጦር መኮነኖች ተይዞ ፍርድ ቤት ላይ ሲቀርብ ከዳኛው ጋር ያደ
ታሪክ የማይረሳው የኢስላም ታጋይ ዑመር አል ሙኽታር ጣሊያኖች ሊቢያን በግፍ ሲያስተዳድሩ ለበርካታ አመታል ሲታገል ከቆየ በኋላ በጣሊያን የጦር መኮነኖች ተይዞ ፍርድ ቤት ላይ ሲቀርብ ከዳኛው ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ዳኛው፦ የጣሊያንን መስግስት ተዋግተሃል? ዑሙር፦ አዎ ዳኛው፦ የሊቢያ ህዝብ መንግስታችን እንዲዋጋ ቅስቀሳ አድርገሃል? ዑመር፦ አዎ ዳኛው፦ ይህ ተግባርህ ምን አይነት ውሳኔ ሊያስወስንብህ እንደሚችል ታውቃለህ? ዑመር፦ አዎ ዳኛው፦ ያልከውን አምነህ ትቀበላለህ? ዑሙር፦ አዎ ዳኛው፦ የጣሊያንን መንግስት መዋጋት ከጀመርክ ምን ያህል ጊዜ ሆነህ? ዑመር፦ ሃያ (20) አመት ዳኛው፦ በትግልህ ተፀፅተሃል? ዑመር፦ አልተፀፀትኩም! ዳኛው፦ ስቅላት እንደሚፈረድብህ ታውቃለህን? ዑመር፦ አዎ! ዳኛው፦ ፍፃሜህ ይህ መሆኑ እጅግ ያሳዝነኛል ዑመር፦ እኔ ደግሞ ይህ ጎዳና ሒዎቴን የምፈፅምበት መሆኑ ያስደስተኛል ዳኛውም ዑመር ጣሊያንን እየተዋጉ ያሉ ሊቢያኖች ትግላቸውን እንዲያቆሙ ትእዛዝ ከሰጠ ሙሉ ይቅርታ እንደሚደረግለት ለማሳመን ቢሞክርም የዑመር ምላሽ ግን ቀጣዩ ነበር፦ «ከአሏህ በስተቀር በእውነት አምልኮት የሚገባው እንደሌለና ሙሐመድም صلى الله عليه وسلم መልክተኛው መሆናቸውን አንደበቴ ሲመሰክር ስትጠቁም የኖረችው ጠቋሚ እጣት አሁን ስህተትን ልትፅፍ አትችልም!» #share #ሼር #Join Https://t.me/smithhk

﷽ { የጁምዓ ቀን ሱናዎች } 1 ገላን መታጠብ 2 ሽቶ መቀባት (ለወንድ) 3 ጥርስ መፍቂያ መጠቀም 4 የክት ልብስ መልበስ ለወንድ (ነጭ ልብስ) 5 በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ 6 በእግር ወደ መስጂድ
﷽ { የጁምዓ ቀን ሱናዎች } 1 ገላን መታጠብ 2 ሽቶ መቀባት (ለወንድ) 3 ጥርስ መፍቂያ መጠቀም 4 የክት ልብስ መልበስ ለወንድ (ነጭ ልብስ) 5 በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ 6 በእግር ወደ መስጂድ መሄድ 7 መስጂድ ውስጥ የሰዎችን ትከሻ አለመረማመድ 8 ኹጥባ እየተደረገም ቢሆን ተህየቱ መስጂድ መስገድ 9 ኹጥባ ወደ ሚያደርገው ኢመም መዞር እና ኢማሙን እያዩ ኹንባን ማዳመጥ 10 ኹጥባ በሚደረግበት ወቅት ፀጥታን መላበስ 11 ሰደቃ ማብዛት 12 ከሀሙስ ማታ እስከ ጁምዓ ዐስር ድረስ ሱረቱል ካፍ መቅራት 13 ድዓ ማድረግ 14 የአላህ መልክተኛ(ሠ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት ማብዛት https://t.me/smithhk

عن أبي هريرة رضي الله عنه ، عن النبي ﷺ أنه قال : ((إنَّ فِي الجُمُعَةِ لَسَاعَةً لَا يُوَافِقُهَا مُسْلِمٌ يَسْألُ اللهَ فِيهَا خَيْرًا إلَّا أعْطَاهُ إيَّاهُ)) رواه مسلم.

📌ይች #ሃገር_ሶስት/③ቀናት_አሏት 📌 ①🚫ትናንት ኑረነዋል መዝገቡን ይዞ ላይመለስ ሄዷል፤ ②🚫ዛሬ አብሮን ነው አይዘወትርም ፤ ③🚫ነገ ለመኖራችን ዋስትና የለንም ፤ ስለዚህ #ያለንበትን #ጊዜ ጌታችንን በማጥራት በማመስገን እና ምህረት በመጠየቅ እናሳልፍ። ያረብ ያአላህ ማረን🤲🤲 https://t.me/smithhk

😁ለፈገግታ .......ለ ኡዱሂያ ምን አረድክ ያ ቢላል አሉት (ረሱለላህ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ) ዶሮ አላቸው ቢላል (ረዐ)... ሙአዚን ሙአዚንን ያርዳል አሉት ረሱል(ሰዐወ)😁😁 መልካም ዒድ ይሁንላችሁ ❤️ #share #ሼር #Join Https://t.me/smithhk

AnimatedSticker.tgs0.24 KB

AnimatedSticker.tgs0.38 KB

ምርጥ የዐረፋ ቀን ዱዓ —————— በዛሬው የአረፋ ቀን በብዛት መባል ያለበት ዱዓ /ዚክር ﻻَ ﺇِﻟَـﻪَ ﺇِﻻَّ ﺍﻟﻠﻪُ ﻭَﺣْﺪَﻩُ ﻻَ ﺷَﺮِﻳْﻚَ ﻟَﻪُ، ﻟَﻪُ ﺍﻟْﻤُﻠْﻚُ ﻭَﻟَﻪُ ﺍﻟْﺤَﻤْﺪُ، ﻭَﻫُﻮَ ﻋَﻠَﻰ ﻛُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻗَﺪِﻳْﺮٌ ‹ላኢላሀ ኢልለሏሁ ወህደሁ ላ ሸሪከለሁ፣ ለሁል ሙልኩ፣ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር ። › «ከአላህ ውጭ በእዉነት የሚገዙት አምላክ የለም፡፡ እርሱ አንድ ነው ፡፡ ለርሱ አጋር የለውም ፡፡ ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ተገቢነቱ ለረርሱ ብቻ ነው ፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው››!!! #share #ሼር #Join Https://t.me/smithhk

🌹አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ🌹 ወንድም እህቶቼ አደራችሁን ነገ ዱአ ከማድረግ እንዳንሳነፍ ወላሂ በአላህ ይሁንብኝ አላህ ነገ የምትደረግን ዱአ አልመልስም ብሏል ወንጀል ውስጥ የተዘፈቅንም ሰዎች አላህን ምህረት ለምነን በንፁህ ልብ የምንፈልገውን እንለምነው። መረሳት የሌለባቸው ዱአዎች -ጤንነትን -ሪዝቅን - በረካን (በልጅ፣በቤተሰብ፣በገንዘብ) -ሁስነል ኻቲማን(መጨረሻችንን እንዲያሳምርልን) -ቀብራችን በብርሀን እንዲሞላልን -በእኛ እና በአላህ መካከል ያለውን ወንጀል እንዲምረን -ከረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ጋር አላህ ጎረቤት እንዲያደርገን -የአላህን ፊት በማየት የሚገኘውን ጣእም እንድናገኝ -ጀነትን እንዲያስገባን ከጀሀነም እንዲጠብቀን ~~እንዲሁም ለመላው በስቃይ እና በችግር ውስጥ ያሉት ሙስሊም እናት አባቶች፣እህት ወንድሞች በዱአችን እናስታውስ፤ሌሎች ያሉብንን እና የምንፈልጋቸውን ነገሮችም በማብዛት አላህን እንለምን። #የፆሙን ጉዳይም እንዳንዘነጋ ከአስሩ ቀናት በተለየ መልኩ የ9ኛውን ቀን ማለትም የዐረፋን ቀን መፆም ተወዳጅ ነው። ምክንያቱም ነቢዩ - ﷺ -  ስለዐረፋ ቀን ፆም እንዲህ ብለዋል ፦ [ ያለፈውን አመት እና የወደፊቱን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ አላህ ላይ ተስፋ አደርጋለው ] 📒(ሙስሊም ዘግቦታል). በዚህም ቀን ዱአን ማብዛት አስፈላጊ ነው። እኛ ተጠቅመን ሌሎችንም ጠቅመን ምንም ሳንሰራ ሌሎች በሰሩት ተጠቃሚ እንድንሆን ሁላችንም ሼር ወደ ግሩፕ ወደ ቻናል በማድረግ የአጅር ተካፋይ እንሁን ለአላህ ብዬ እወዳችዋለሁ 🌼ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ 🌼 #share #ሼር #join Https://t.me/smithhk