Nathan casting agency
Open in Telegram
The best place to get the best casting jobs Our services -casting models - for music clips - movies - series dramas - fashion shows - television shows Contact: 0920358051
Show moreEthiopia16 170The category is not specified
408
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼 🌼 🌼
🌼 🌼 🌼 🌼
🌼🌼🌼 🌼🌼🌼
🌼
🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼 🌼 🌼
🌼 🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼 🌼 🌼
🌼🌼🌼 🌼🌼🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼
, 🌼
🌼
🌼🌼🌼
🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼🌼🌼
🌼 🌼
🌼🌼🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼
🌼🌼🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼
🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼 🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 🌼 🌼 🌼
🌼 🌼 🌼 🌼
🌼🌼🌼 🌼🌼🌼
🌼
🌼🌼
🌼
🌼🌼🌼
🌼
🌼
🌹ውድ ጓደኛዬ እንኳን አደረሰሽ/ክ በጣም እወድሻለሁ/ካለው መልካም አዲስ አመት ብዬካለሁ/ሻለሁ🌹
🌹አድሱ አመት🌹
🌹የሰላም🌹 🌹የጤና🌹
🌹የብልጽግና🌹 🌹የፍቅር🌹
🌹የአንድነት🌹 🌹የደስታ🌹
🌹አመት ይሁንልን🌹
🌹ይህን መልእክት ያደረስኩልሽ/ክ እኔ በጣም የምወድክ/ሽ ወይም የማፈቅርሽ/ህ ጓደኛክ ነኝ አንተም/አንቺም ለምትወጂው/ደው አድርስ/ሺ🌹
🌹ይህን የበዓል መልካም ምኞት መግለጫ ለምትወዱት ሁሉ ሼር አድርጉ
🌹 @fkrnahiwot🌹
🌹 @fkrnahiwot 🌹
በዚህ አጋጣሚ 👆ይህን ድንቅ ቻናል 🌹ይቀላቀሉ🌹
❤️ተወዳጁ
#ተከታታይ ልቦለድ
#ክፍል አስር
💢ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ ታሪክ
ሄኖክ ከዚ በፊትም ሴት ልጅ መመምታት ተከሶ ስለነበር አሁን የሴቶች ዶርም ሲገኝ በቀጥታ እርምጃ ተወሰደበት ሄኖክ ኤልሳን አግኝቶ በቅጡ እንኳ ሳያወራት ከትምህርት ቤት ተባረረ ... ሄኖክ
የሚሄድበት ግራ ገብቶት ባለችው ብር አልጋ እየተከራየ ሁለት ቀን ሆቴል አደረ ከዛ ግን ቁርጡን አውቆ ወደ አዲስ አበባ
መምጣትና ስራ እየስራ መኖር እንዳለበት እራሱን አሳመነ ከዛም ባለፈ የሚረዳው ባይኖርም ግን መማር ግዴታው ነው ምክንያቱም ከማንም በታች መሆን አይፈልግም ... ስለፍቅረኛው ኤልሳም
እጅግ ይጨነቃል... እንዳሰበው ህይወት ቀላል አልሆነችም ምንም ሞያና ዘመድ
ሳይኖረው ጥሩ ስራ ማግኘት ይከብዳል ለዛምያገኘው ስራ ቀንስራ ነበርና በ500 ብር ቤት ተከራይቶ ስራ ጀመረ ሄኖክ በርግጥ ውበቱም ሆነ አቋሙ ውብ ነው ይሁንና ይህን ስራ በጀመረ በሳምንቱ ከከለሩ ጀምሮ ሰውነቱ ተቀየረ እንኳን መማር በዚ ስራ ምግብ አቅርቦ መብላት ከበደው ሁሌም ከስራ ተመልሶ የተከራያት ጎጆ ውስጥ ሲገባ እናቱ እንደሞተችበት ህፃን ባለፈ ትዝታው ስቅስቅ ብሎ ያለቅስና ሲደክመው ያንቀላፋል.... በዚ መልኩ እየኖረ ሳለ አንድ ቀን ቤተክርስቲያን ሊሳለም ሲሄድ
ያጎቱ ሚስት ሀና በጣም ተጎሳቁላ ያገኛታል ይሄኔ በጣም ደንግጦ
ደርቆ ቀረ እሷም አጋጣሚ አይታው ስለነበር ቀርባ ልጄ ብላ ተጠመጠመችበት... ትንሽ ከተላቀሱ ቡሃላ ወደቤት ላድርስሽ ሲል ፍቃዷን ጠየቀ ተስማምታም ሲሄዱ ያ ሲፈነጥዝ ያደገበት ቤት የለም የወሰደችው ከዛ በተቃራኒ ሲያዩት ሊፈርስ የዘመመ ጠባብ
ቤት ነበር በጣም ደንግጦ እናቴ ቤቱስ ሲል ጠየቀ ሀናም እንባ ባቀረሩ አይኖቿ ወደሰማይ አንጋጣ እሱ የስራዬን አይቶ ነጠቀኝ አለች አሁንም እንዳልገባው ለማሳወቅ ማለት? ሲላት "ልጄ አጎትህ መውለድ እንደማልችል ሲያውቅ እላዬ ላይ ሴት ይደርብ ጀመር ከዛም በ2አመት ውስጥ 3 ሴት አስረገዘ ... ከዛ ግን የልጅ
አምሮት ሳይሄን ሴሰኝነት ነው እናም ወደ ቀድሞ ማንነትህ ተመለስ ብለው አላርፍ ብሎ ከየት እንዳመጣው ሳይታወቅ የHIV
ቫይረስ ተጠቂ ሆንን እናም ብዙ ሳይቆይ እንደምታውቀው ሞተ... እኔም በንዴት በሀጥያት ተጨማለኩ ፈጣሪ ግን ልክ ስላልነበርኩ አሁን እየቀጣኝ ነው አንተን ልጄን ነጠቀኝ ቤታችንም የመንግስት
ነበርና ተወረሰ ልጄ ስራም ስለደከምኩ ተቀነስኩ አሁን ሞቴን እየተጠባበኩ ነው!" አለች እንባዋ መንታ መንታ እየወረደ ሄኖክም በህይወቱ እንደዛ ግዜ አዝኖ አያውቅም ቃል ሳይተነፍስ እያለቀሰ
ወጥቶ ሄደ... ከዛ ለደሞዝ ለሀና ቤት ተከራየላት ከቀን ስራ ከሚያገኛት እየቀነሰ
እሷን መርዳት ጀመረ በዛ ኑሮ ትምህርት ቤት ከፍሎ ፍፁም እንደማይሆን አመነ ያዳለፈውን ግዜ ባሰበ ቁጥር ቅስሙ ይሰበራል ሜላት ዶጮ ኤልሳ ሁሉንም አጥቷል ... ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ዶጮና ሄኖክ ተገናኙ ዶጮ ሄኖክን
ሲመለከተው በጣም አዘነ ለምን እኛ ቤት አልሄድክም ሲል ተቆጣው ሄኖክ ግን ማወቅ የፈለገው ስለ ኤልሳ ጤንነት ነበር ... ዶጮን ስለኤልሳ ሲጠይቀው ሌላ ወሬ ያስቀይስበታል ይሄኔ ዶጮ
ስለኤልሳ የማትነግረኝ ለምንድን ነው ወይስ ደና አይደለችም ሲል አፋጠጠው ይሄኔ ዶጮ በጣም እየፈራ ጓደኛዬ የምታፈቅራት ልጅ አሁን ያንተ አይደለችም ከፊዚክስ መምህራችን ጋር የፍቅር
ግንኙነት ጀምራ የግቢውን ተማሪ በሙሉ ጉድ አስብላዋለች አለ ይሄኔ ሄኖክ ሰማይ የወረደበት መስለው.......
............ይቀጥላል…..........✍
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
❤️ተወዳጁ
#ተከታታይ ልቦለድ
# ክፍል ዘጠኝ
💢ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ ታሪክ
ፍቅራቸውም እጥፍ ጨመረ ኤልሳም ሆነች ሄኖክ በተያዩ ቁጥር
ውስጣቸው ይረበሻል ግን ደግሞ ሜላት በየዋህነት ያፈቅረኛል ብላ ለሄኖክ እሷነቷን ሰጥታዋለች እሱ ግን አካሉ እንጂ ልቡ ኤልሳ ጋር ነው ይህ በንዲህ እንዳለ ክረምት ደርሶ ለረፍት ሁሉም ወደ ቤተሰብ ሄደ ሄኖክ ያኔ ቤተሰብ እንደሌለው አስታውሶ በጣም ከፋው እናም እነዶጮ ቤት ሄዱ ... ለሁለት ወር
የሚያፈቅሩትን ሰው አለማግኘት እንደሚያምእና ደሚከብድ መሆኑን የሚያውቀው የደረሰበት ብቻ ነው ሄኖክ ኤልሳን ኤልሳ ሄኖክን ሜላትም ሄኖክን
ሁሉም በየራሱ በናፍቆት ተጎዳ... ይሄኔ ዶጮ አንድ ሀሳብ አቀረበ አንድ ሁለት ሰው ጨምረን ለምን አሪፍ ቦታ ከከተማ ወጣ ብለን አንዝናናም በዛውም ኤልሳንና ሜላትን እንጋብዛቸው አለ ... ሄኖክም በሀሳቡ በደስታ ተስማማ... ኤልሳ ትንሽ ብታቅማማም ተስማማች ከዛም ዶጮ የትምህርት ቤት ሁለት ጓደኞቹን ጨምሮ ወደ ባህር ዳር ሄዱ መዝናናት መቦረቅ ተጀመረ መጥፎ ነገር እንዳይፈጠር ሁሉም በየበኩሉ ጥረት ቢያደርግም ፍቅር ግን የበላይነቱን ማሳየት ጀመረ ...
የመጀመርያው ቀን ምሽት ሜላት ከሄኖክ ጋር ክፍል ያዘች ሄኖክ ግን ከሷ ጋር አላድርም እሷና ኤልሳ እኔና ዶጮ... ሲል አሻፈረኝ አለ ይሄኔ ሜላት ሰክራ ስለነበር ወደ ቤቴ እሄዳለው በቃ ብላ ማስቸገር ጀመረች ማንም ሊያስቆማት አልቻለም ነበርና ኮንትራት ታክሲ ይዘው ዶጮ ሊያደርሳት በመስማማት ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ ሄኖክና ኤልሳ እና የዶጮ ጓደኞች ግን እዛው መዝናናታቸውን ቀጠሉ ... ዶጮ በጣም ቅንና የዋህ ነው ለዛም ነበር ያን ሁሉ ኪሎሜትር ለመዝናናት ከሄደበት ቦታ ተነስቶ አንድ ነገር እንዳትሆን በማሰብ ሊያደርሳት የወሰነው ... በዚ አጋጣሚ ሄኖክና ኤልሳ በድጋሚ ብቻቸውን ተገናኙ ይሄኔ ሳይነጋገሩ ለረጅም ሰአት ባህር ዳርቻ ላይ
ተቀመጡ ንፋስና ቅዝቃዜው እያየለ ሲመጣ ግን ብርዱን ለመሸሽ ወደ ክፍላቸው ሄዱ ማንም ቃል ሳይተነፍስ ተያይዘው አንድ ክፍል ገቡ ፍቅር ካንደበት ይልቅ ድርጊት ነው ይባል የለ ... ሳያስቡት መሳሳም ጀመሩ ... ሲነጋ ሁለቱም አንድ መስለው አንድ አልጋ ላይ
ተኝተዋል ...ከዛ ቀን ቡሃላ ሁለቱም መለያየት እንደማይችሉ አመኑ ፍቅራቸው በድብቅ ቀጠለ... የትምህርት ወቅት ደርሶ ተመልሰው ወደ ካምፓስ ሄዱ አንድ
ቀን ታድያ ከዶጮ ጋር እያጠኑ ማታ ላይ ሄኖክ መልክት ደረሰው ይሄኔ ስልኩን ከፍቶ ሲያይ .... "ሄኖኬ በጣም አዝናለው
ስመረመር የ2ወር እርጉዝ ነሽ ተባልኩ ግን ፍቅሬ መመረቅ ስለምፈልግ ብቻ ላሶርደው ነው ምናልባት ከሞትኩ
አፈቅርሃለው..." ይላል ይህን አንብቦ ሲጨርስ እየሮጠ ቀጥታ የሴቶች ዶርም ሄደ ማንም ሊያስቆመው አልቻለም ነበር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ጥበቆቹ ይዘው ቢሮ ወሰዱትና ከሰሱት......
............ይቀጥላል…..........✍
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
❤️ተወዳጁ
#ተከታታይ ልቦለድ
#ክፍል ስምንት
💢ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ ታሪክ
ሄኖክ ላይ እንደተለጠፈች እንቅልፍ ያዟት
ጠዋት ስትነቃ ሄኖክ እንቅልፍ ይዞት ነበር በመጀመርያ ብትደነግጥም በመሀላቸው ምንም እንዳልተፈጠረ ለመገመት ግን
ጊዜ አሎሰደባትም ከዛም ማታ ለለሆነው ሁሉ ቀስ በቀስ ትዝ አላት አፍና የያዘችውን ፍቅር ተንፍሳለታለች እሱም እንደዛው ከዛም አልፎ ጓደኛዋ ሜላት ስላረገችው ትዝ አላት ይሄኔ በፍጥነት
ተነስታ ጫማዋን አርጋ ልቶጣ ስትል ሄኖክ ነቃ ደና አደርሽ ኤልሲ አለ ማታ ያወሩት ሁሉ እውን መሆኑን ለማረጋገጥ ቸኩሎ እየውልክ ሄኖክ ከንግዲ እኔና አንተ መገናኘት የለብንም ምክንያቱም አሁን
የጓደኛዬ ነህ ገባህ? እሷን መክዳት ደግሞ በፍፁም አልፈልግም! ብላ ጥላው ልቴድ ስትል ከአልጋው ዘሎ በመውረድ ግንኮ እኔ አፈቅርሻለው አንቺም...ሲል ንግግሩን አቋርጣ እኔ ግን አላፈቅርህም አለች አይኖቿ እንባ መቋጠራቸው እንዳይታይ ፊቷን አዙራ ማታ ግን እንደምታፈቅሪኝ ነግረሽኛል ሲል ቀልዴን ነው ብላ አልፋው ወጥታ ሄደች... ከዛ ቀን ቡሃላ ሄኖክ ኤልሳን ለማግኘት እድል አጣ ሜላትም እሱን ብላ እሱ ያለበት አካባቢ ስትሄድ ሊያናግራት አይደለም ፍፁም ሊያያት እንደማይችል ነግሮ ጥሏት ይሄዳል ይህ በንዲህ እንዳለ
አንድ ቀን ሄኖክና ዶጮ የግቢው መናፈሻ ውስጥ ቁጭ ብለው ያወራሉ ይሄኔ ሜላት ሳያስቡት መጥታ ሄኒ ውዴ ለምን ትርቀኛለህ ገና ለገና የከዳችኝን ሴት ለምን መታሻት ብለህ ነው እኔን የምትገፋኝ? አለች ሄኖክም አልከዳችሽም አለ ረጋ ባለ ንግግር ከድታኛለች እቺ የድሃ ልጅ ...ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ ሄኖክ
በንዴት በጥፊ መታት ይሄ ሲሆን ድንገት አንድ መምህር አይቶ ስለነበር ሄኖክ ለአንድ አመት ከትምህርት ቤት ታገደ
ሄኖክ ከትምህርት ቤት እገዳ ሲጣልበት ሜላት ማመን አቃታት ምክንያቱም ትምህርት ቤት ሲሆን ቢያንስ አይኑን የማየት እድል አላት ሄኖክም ቢሆን ይሄን ከሚሰማ ቢሞት ይመርጥ ነበር ምክንያቱም ባሁን ሰአት ከ ትምህርቱ ይልቅ ኤልሳን ማጣቱ ይበልጥ ከብዶታል ለዚም ፈጣሪውን በመማፀን ሜላትን አንድ ነገር እንድታደርግለት ጠየቃት ቢያንስ አልተጣላንም ስንቃለድ ነው
እንድትልለት ... ሜላትም ለራሷ ስትል ይህን ማድረግ እንዳለባት ስለምታምን አንድ ቃል ከገባህልኝ እሺ አለችው እሱም ምን ሲል ጠየቃት ሜላትም ከዚ ቡሃላ የማትርቀኝ ከሆነና እንደቀድሟችን
በፍቅር ከቀጠልን አለችው ሄኖክም አማራጭ ስላልነበረው ተስማማ ...
በግዜው ሜላት ምን እንዳለችና እንዳሳመነቻቸው ባያውቅም ትምህርቱን ግን ቀጠለ ከዛም ሄኖክ ሜላትን ከኤልሳ ጋር ካልታረቃቹ ሲል አስገደዳት ከዛም ታረቁና እንደቀድሞው ጓደኝነታቸው ቀጠለ ሁሌም ግን ኤልሳና ሄኖክ በአይን ይግባባሉ........
............ይቀጥላል…..........✍
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
❤️ተወዳጁ
#ተከታታይ ልቦለድ
#ክፍል ሰባት
💢ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ ታሪክ
ከዛ ጥቂት ተያዩና ነበረ አለች በረጅሙ ተንፍሳ ታድሎ ባውቀው ደስ ይለኛል አለ ይሄኔ ታውቀዋለህ አለች ..እ... አለ ሳታስበው እንደተናገረች እያሳበቀባት ስቀልድ ነው በቃ እንሂድ አለችና መንገድ ጀመረች ይሄኔ በተራው እሱ አስቆማትና ኤልሲ አለ የልቧ ምት የጨመረ መሰላት እጆቿን በእጁ ይዞ ትኩር ብሎ አያት ግን ደፍሮ የማፈቅራት ልጅ አንቺ ነሽ ማለት አቃተው አተኩሮ ሲያያት እሷም አትኩራ ስታየው እነዛ የሚያማምሩ ከንፈሮቿ ልቡ ውስጥ ጠልቀው ገቡ ሊስማት ተጠጋ እሷም ቀረበችው ይሄኔ ሁለቱም ያልጠበቁት ክስተት ተከሰተ ሜላትና ዶጮ ከየት መጡ ሳይባል ድንገት ደረሱ
ሄኖክና ኤልሳ ሊሳሳሙ ሲሉ ሜላት በመድረሷ ሁለቱም ደነገጡ ይሄኔ ሜላት ኤልሳን በጥፊ መታቻት ኤልሳ ግን በስራዋ አፍራ ይሁን ሜላትን አክብራት ግልፅ ባይሆንም አቀርቅራ ዝም አለች
ሄኖክ ግን በሜላት ተናዶ እንዴት ትመቻታለሽ ዳግም አይንሽን ማየት አልፈልግም ብሎ ኤልሳን እየጎተታት ወደ ግቢ ሄደ ሲደርሱ ግን ሰአት አልፎ መግባት አይቻልም ነበር ይሄኔ ኮንትራት ታክሲ ይዞ አልጋ የሚገኝበት ቦታ በመሄድ አልጋ ያዘ ከዛም ኤልሳን ጠዋት መጥቼ እወስድሻለው አላት ኤልሳ ግን ብቻዬን አላድርም ስትል አሻፈረኝ አለች ሄኖክም ስሜት አሳስቷቸው መንገዳቸው እንዳይሰናከል ቢፈራም አትሃድ እያለችው ላለመሄድ ወስኖ አብሯት ሆነ... አልጋው ላይ ተቀምጠው ሁለቱም በየራሳቸው ሀሳብ ሰመጡ ይሄኔ ኤልሳ ታውቃለህ ከሜላት ቀድሜ የማውቅህ እኔ ነኝ ገና
እንዳየውህ ነበር በልቤ ቦታ የሰጠውክ ግን... አለችና ንግግሯን ገታ አድርጋ እንባዋን ጠራረገች... ሄኖክ ይበልጥ በንግግሯ ተስቦ በተመስጦ ያዳምጣት ጀመር እና ግን ለጓደኛዬ ለሜላት
እንዳፈቀርኩህ ባልነግራትም መገመት ነበረባት ግን አንድ ቀን እንደማፈቅርህ እነግራታለው እያልኩ ቀን ስቆጥር አንተ የፍቅር አጋሯ እንድትሆንላት ማፍቅሯን የሚገልፅ ደብዳቤ እንድሰጥህ ላከችኝ ያኔ ለመጀመርያ ግዜ ቅስሜ ተሰበረና እረስቼህ ትምህርቴ ላይ ለማተኮር ለራሴ ቃል ገባሁ... አለች በቁጭት ይሄኔ ሄኖክ
ሳይታወቀው እንባው ይወርድ ኖሯል ... ቅድም ሜላት ስትዘባርቅ ገምቼ ነበር እናም ፈጣሪ እንደሚወደኝ አረጋገጥኩ ኤልሲ ገና እንዳየሁሽ ነበር የተመኘሁሽ ግን መንገዳችን ለየቅል ሆነ እመኚኝ
ዶጮ ይነግርሻል እኔ አንቺን ለማግኘት ነው ሜላትን የቀረብኳት አለ... አቀፈችውና ተላቀሱ የማፈቅራት የልቤ ንግስት አንቺ ነሽ አለ ፀሯን እያሻሻት... ኤልሳም መጠጥ ስላደከማት ከዚ በላይ
አቅም አላገኘችም ሄኖክ ላይ እንደተለጠፈች እንቅልፍ ያዛት...
ጠዋት ስትነቃ.......
..........ይቀጥላል…..........✍
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
❤️ተወዳጁ
#ተከታታይ ልቦለድ
#ክፍል ስድስት
💢ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ ታሪክ
ሄኖክ ከኤልሳ ከነ ምንነቷ ድብን ያለ ፍቅር ይዞታል በተለይ ደግሞ ለልደቱ ያልመጣችበትን ምክንያት ግልፅ በሆነ አማርኛ ስትነግረው በጣም ነበር ያዘነላት ቀናት እያለፉ ሳምንታት ተተኩ ሳምንታትም በወራት ተተኩና አንድ ምሽት ላይ አዲስ ነገር ተፈጠረ ሜላት ወተን ካልተዝናናን ስትል አስቸገረች ኤልሳም ለጓደኛዋ ስትል ተስማማችና ወጡ ኤልሳ የሜላትን ቀሚስ ተውሳ አድርጋ እጅግ በጣም ተውባ ነበር ይሄኔ ዶጮ ወደ ሄኖክ ጠጋ ብሎ "አንተ ለካ ኤልሳን ያየሃት በደንብ ኖሯል ስትለብስ በደምብ አበባ መሰለችኮ" አለ ሄኖክም ምላሹን ቃል ያጣ ይመስል በፈገግታ ብቻ አደረገው.... መጠጥ እያዘዙ ይጠጣሉ ይደንሳሉ ባጠቃላይ ሴቶቹ እራሳቸውን
አለማወቅ ደረጃ ላይ ደረሱ... ይሄኔ ሁሉም የልባቸውን መዘርገፍ ፈለጉ ወንዶቹ ሞቅታ ብቻ ነበር ለግዜው የተሰማቸው በቅድሚያ ሜላት"እኔ ሄኖክን እንዳስበው ትኩረት እንድሰጠው ያረገችኝ
ኤልሲ ናት! ቀድማ የምታውቅህም እሷ ናት ከዛ ስላንተ ማን እንደሚነግራት አላውቅም እየመጣች ታወራልኛለች ከዛ በጣም ተሳብኩና እራሴ መከታተል ጀመርኩ... ከዛማ ተወዳጅ ሆነ አገኘውክ..." ብላ "ካ ካ ካ ..." እረጅም ሳቅ ትስቅና "የግሌ ሆነልኝ ግን በጣም
አፈቅርሃለው" ብላ ሳያስበው ከንፈሩን ስትስመው ኤልሳ በድንገት ፊቷ ቅይርይር ይልና ከመቀመጫዋ ተነስታ በሉ እኔ ልግባ አለች ይሄኔ ዶጮና ሄኖክ ግራ ተጋብተው ተያዩና ዶጮ ሄኖክን ሸኛት
አለው በምልክት... ሄኖክ ኤልሳን እየሸኛት ሳለ ሀይለኛ ብርድ ነበር እናም ጃኬቱን አውልቆ ሲሰጣት ቀና ብላ በስስት ተመለከተችው ይሄኔ ፊቷ ላይ
አንድ ነገር አነበበና ልክ በሆንኩ ብሎ ተመኘ... ኤልሳም መጠጡ ይሁን ስሜቷ አስገድዷት ብቻ መለፍለፍ ጀመረች ... በቅድሚያ ሄኖክን አንድጥያቄ ጠየቀችው... ያኔ ሜላት ወረቀቱን
እንዳደርስልህ ስትልከኝ መልስህ የምታፈቅራት ልጅ እንዳለችህ ነበር ተሳሳትኩ? አለችው አይ ልክ ነሽ አሁንም የማፈቅራት ልጅ አለች አለ ኮስተር ብሎ በጥልቀት ለማሰብ እየጣረ ኤልሳም
ከፊት ለፊቱ መንገድ ዘግታ በማስቆም ቀና ብላ በጨረቃዋ ብርሃን እያየችው የምርህን ነው? እና ሜላትን አትወዳትም? ብላ ጠየቀችው አሁንም ኮስተር ብሎ አላፈቅራትም ግን የዋህነቷ ያሳዝነኛል አለ ... ይሄኔ ዝም አለች አቀርቅራ አንቺስ ግን ፍቅር ይዞሽ ያውቃል አላት ይሄኔ እንደመደንገጥ ብላ ቀና አለች ይሄኔ አይን ለአይን ተፋጠጡ.......
..........ይቀጥላል…..........✍
━━━━━━━✦✿✦━━━━
ለ እናንተ የተፀፈ ደብዳቤ…💌
ብቻዬን በእግረኛ መንገድ ላይ እየተጓዝኩ ነው… መሽቶዋል… ነገር ግን የመንገድ መብራቶች ምሽቱን የመሸ ላለመስመሰለ የተቻላቸውን ያህል በርተዋል…
ይሁን እያለን ብዙ ነገር በህይወታችን ውስጥ ሆኖል…
ባያሆን እያልን የፀለይነው እና የፈራነው ነገር ሆኖዋል… እሚሰማህ በሌለበት ማውራት እና እሚረዳህ በሌለበት ማስረዳት በጣም ከባድ ነው… የምር በጣም
❤️❤️
ማንም ብትሆን የሰው ልጅ እስከሆንክ ድረስ
ትንሽ ነኝ ብለህ አታስብ!
ትናንሽ ቁልፎች ትላልቅ በሮችን
ይከፍታሉ . . . . ትናንሽ ቃላቶች ትላልቅ
ምክሮችን ይሰጣሉ . . . . ትናንሽ ስጦታዎች
ትላልቅ ደስታን ይለግሳሉ።
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
❤️ተወዳጁ
#ተከታታይ ልቦለድ
#ክፍል አምስት
💢ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ ታሪክ
ሄኖክ ልጁን መምታቱን ቀጠለ ይሄን ግዜ በሰከረ አንደበቱ እየተኮላተፈ "...እሺ እሄዳለው ግን ገንዘቤን ትስጠኝ!" አለ
ሄኖክም ቀና ብሎ ለማየት እንኳ የሚጠነቀቅላትን ያጎቱ ሚስት ሀና "ቱ... ልጆችሽ የሚሆኑ ወጣቶችን በገንዘብ እያታለልሽ ያጎቴ አልጋ ላይ ስትማግጪ አታፍሪም?! ለካ ያን ቀን እኔንም የወሲብ ፊልም እንዳይ የጠራሽኝ ልታባልጊኝ ኖሯል! ... ግን ምን አይነት ህሊና ቢስ ነሽ ወይስ አብደሻል?? ካንቺ ጋር በማደጌ አፈርኩ ሰው ሁሉ እናቴ ስለምትመስይው አፈርኩብሽ ... "እያለ ቤቱን ከፍቶ ሊወጣ
ሲል እያለቀሰች "አንተም ትተኸኝ ልትሄድ ነው? እስካሁን የተናገርከኝ ምንም እንኳ ስሜት ቢጎዳ አልተቀየምኩህም ምክንያቱም አንተ በምታውቀው ልክ ነው የምታስበው..." ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ ወጥቶ ሄደ... ሄኖክ ሲቦርቅ ያደገበትን ቤት ለቆ ሲወጣ ምንም አልያዘም ነበር
ተመልሶ ቀጥታ ጓደኛው መስፍን(ዶጮ) ቤት ሄደ ዶጮ ወላጆቹን በሞት ቢያጣም እሱም ሆነ አብረውት የሚኖሩት ታላላቅ ወንድሞቹ ሄኖክን ስለሚወዱት ለጊዜው ከቤት እንደተጣላ ሲነግራቸው በደስታ ነበር አብሯቸው እንዲኖር የፈቀዱለት ሄኖክ የኢንተራንስ ውጤት ምን እንደሚሆን መገመት አይችልም ግን ልክ እንደ ኤልሳ አይነት ውጤት እንዲሆንለት ይመኛል። ቀናት ባለፉ ቁጥርም ሀናን በዛ ሁኔታ ጥሎ መውጣቱ ልክ እንዳልነበር ይሰማዋል ይህ ግን እዲሰማው ያረገው ደግሞ በመጨረሻ የተናገረችው ነበር
"አልተቀየምኩም..." ይሄ ማለት ይሄን እንድታደርግ ያደረጋት አንድ እውነት ይኖራታል ሲል ያስባል ግን ከዚ ቡሃላ አይኗን ደፍሮ ማየት እይችልም ይፈራል...
ከቀናት ቡሃላ የኢንተራንስ ውጤት ወጣ ይሄኔ ሄኖክ ተንጠልጥሎ አለፈ ሌሎቹም በጥሩ ውጤት አለፉ ያን ቀን ሄኖክ ተስፋው ዳግም አንሰራራ እንደ ፈጣሪ ፍቃድ ሆኖም አራቱም ሀዋሳ ዩንቨርስቲ
ተመደቡ ይሄኔ ሄኖክ ክፍለሀገር ላሉት ዘመዶቹ ገንዘብ እንዲልኩለት በመናገር ወቅቱ ሲደርስ ወደ ካምፓስ ገቡ ታድያ
ከመጀመርያ ጀምሮ ከሚላክለት ገንዘብ ይልቅ ሜላት የምትሰጠው ነበር የሚጠቅመው... የካምፓስ ህይወት ከቤተሰብ ቁጥጥር ነፃ ያረጋት ሜላት ሄኖክን እንደልቧ እንድታገኘው አረጋት ሄኖክ ግን አላማው ኤልሳ ስለነበረች ሜላት ብቻዋን ስትቀጥረው መሰናክል ይፈልግና ሳያገኛት ይቀራል። አንድ ቀን ለሊት ፈተና ነበራትና ኤልሳ ሄኖክና ዶጮ ሆነው መናፈሻ ላይ እየተጫወቱ ይስቃሉ ሄኖክ ኤልሳ ጎኑ ካለች ችግሮቹንና ያለፉ ፀፀቶቹን ይረሳና ደስተኛ ይሆናል... በዚ
መሃል ዶጮ ብቻቸውን ጥሏቸው ሄደ ከዛም ትንች ዝምታ ከሰፈነ ቡሃላ "እኔ ምልሽ ኤልሲ" አለ ዝምታውን ለመስበር ያህል "ወዬ" አለች ቀና ብላ እያየችው አስተያየቷ እንኳን ላፈቀራት ከሩቅ ላያት
ልብ ትሰነጥቃለች በውበቷ እየተመሰጠ "ለልደቴ ለምን ቀረሽ?" አለ ኤልሳም በጥያቄው በመገረም "እንዴ ፍቅረኛክ መታልህ የለ እሷን አላስቀረውብህም" አለች እየተቅለሰለሰች ፍቅረኛህ ማለቷ
ውስጡን ቅር እያለው መልሺልኝ አለ ይሄኔ ኤልሳ ትኩር ብላ እያየችው... "ያኔ ቆንጆ ቀሚስ አልነበረኝም ፖርቲ ላይ ብዙ ግዜ
አልገኝም ምክንያቱም እኔ ትምህርት ቤታቹ በነፃ የሚያስተምረኝ ጥሩ ውጤት ስለነበረኝ እድል አግኝቼ እንጂ እንደናንተ የሀብታም ልጅ አይደለሁም"... ብላ እያነባች ጥላው ወደ ዶርም ገባች እሱም በቆመበት እንባው መንታ መንታ መውረድ ጀመረ..............
..........ይቀጥላል…..........✍
❤️ ተወዳጁ
#ተከታታይ ልቦለድ
#ክፍል4⃣
💢ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ ታሪክ
ኤልሳን ለማግኘት ሜላትን መጠቀም እንዳለበት በማመን ከሜላት ጋር ፍቅር ጀመረ ሜላትና ኤልሳ በጣም ስለሚዋደዱ ሁሌም አብረው ናቸው የመጀመርያ ቀንማ ሜላት ሄኖክ የፍቅር ጥያቄዋን እንደተቀበላት ሲነግራት በደስታ የፈነጠዘችው መቼም አይረሳም ኤልሳም ዶጮ ያላትን አስታውሳ ውስጧን ቅር ቢለውም በጓደኛዋ ደስታ ግን መደሰቷ አልቀረም ነበር ... ሄኖክ የውሸት ሜላት የእውነት ፍቅራቸው ጦፈ ሁሌም በመኪና ትሄድ የነበረችው ሜላት ሄኖክን ለማግኘት ስትል በእግሯ ይሸኛት ጀመር የኤልሳ ቤት የሜላትን አልፎ ስለሚርቅ ሜላትን ቤት አስገብተው ኤልሳን ደግሞ ወደ ቤት ይሸኛታል በዛ መሀል ሁሌም
ሜላትን ቤት አስገብተው ብቻቸውን እስኪሆኑ በጣም ይቸኩላል እሷ ደርሳ ስትለየው ደግሞ እንደ ሞት የፈራው ቤቱ መግባት ያስጠላዋል... የኤልሳ ጨዋታና ሳቅ ብቻውን አስታውሶት ሁላ ፈገግ ይሰኛል... በርግጥ መጨረሻቸውን ማሰብ አይፈልግም ምክንያቱም ኤልሳ የጒደኛዋ ፍቅረኛ አፈቀርኩሽ ቢላት እንዴትም እንደማትቀበል ያውቃል ... ወራቶች እያለፉ የኢንተራንስ ፈተና መውሰጃ ግዜ ደረሰ ሄኖክ ግን አስተማሪዎች ግራ እስኪጋቡ ድረስ ጉብዝናው ጠፍቷል እቤቱ ስላለው ችግር ማንም አያውቅም ለጓደኛው እንኳ መናገር ደብሮት አልነገረውም ... ይህ በእንዲህ እንዳለ ፈተናው ተጠናቆ ሁሉም ተለያዩ ኤልሳ ስልክ የላትም ሄኖክና ሜላት ግን ሁሌም ትደውልለትና ያወራሉ በመሀል አልፎ አልፎ ኤልሳም በሌላ ሰው ስልክ ደውላ ሰላም ትለዋለች ምን ምክንያት ፈጥሮ እንደሚያገኛት ግራ ይገባዋል ይሄኔ ለዶጮ ያማክረዋል መለኛው ዶጮም ልደቴ ነው ብለህ እኛ ቤት ማንም ስለሌለ ፖርቲ እናዘጋጅ ይለዋል ይሄኔ ሄኖክ በደስታ አወፈው... በእቅዳቸው መሰረትም ፖርቲ ተዘጋጀ... የሄኖክን የውሸት ልደት ለማክበር ሜላት ውድ ስጦታዎችን ይዛ በግዜ ተገኘች ኤልሳ ግን ቢጠብቃትም የውሃ ሽታ ሆነች በዚ የተበሳጨው ሄኖክ በንዴት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ነበር ዶጮም በኤልሳ መቅረት በጣም ተናዶ ሄኖክን ለማረጋጋት ሞከረ ነገር ግን ሄኖክ መጠጥ የመጀመርያው ስለነበር ሰከረና ቤት ካልሄድኩ ብሎ አስቸገረ ... ይሄኔ ሁሉም ወደየቤታቸው ተበተኑ ዶጮም ሄኖክን ሸኝቶት ተመለሰ... ልክ ሲገባ ያጎቱ ሚስት በግምት 22 ከሚሞላው ልጅ ጋር ስትማግጥ አገኛት ይሄኔ ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል እንዲሉ ሄኖክ ገብቶ የሀናን ሁኔታ ሲያይ የሰሞኑን ሁሉ ንዴቱን መወጣት ጀመረ ይሄኔ ያጎቱ ሚስት ሀና ደንግጣ ተነሳችና ውጣ ስትል ጮኸችበት ሄኖክ ግን ማንንም አልሰማም አብሯት ያለውን ወንድ አንተ ውሻ እኩያህ መሰለችህ ምን ፈልገህ ነው የምትልከሰከሰው ብሎ ይደበደብው ጀመር........
..........ይቀጥላል…..........✍
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
❤️ ተወዳጁ
#ተከታታይ ልቦለድ
#ክፍል 3⃣
💢ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ ታሪክ
ይቅርታ ለዚ ከነበር የፈለግሽኝ አዝናለው በጣም የማፈቅራት ልጅ አለች ስለዚህ አልችልም በያት" አለ ኤልሳም የጓደኛዋ ፍቅር ባለመሳካቱ እያዘነች "እሺ ግን እባክህ ቅረባት ከቻልክ ማለቴ ነው"... ብላ የቆመበት ጥላው ሄደች ህይወት ግን ምን አይነት ግራ ናት የምንወደው ይገፋናል የሚወደንን ግን እንገፋለን... አለ በውስጡ ኤልሳ ለጓደኛዋ ሜላት ስለ ሄኖክ መልስ ነገረቻት ሜላትም እልህ
ቀይ ፊቷን በርበሬ እያስመሰለው ኩራት መሆኑ ነው እኔ ሜላት ያልኩትን ካልሰማ እዚ ትምህርት ቤት አይማራትም ! ስትል ዛተች ከዛን ቀን ጀምሮ ሄኖክ ከኤልሳ ውጪ ማሰብ አቆመ እቤት ሲገባ ያጎቱ ሚስት እንደ ጎረምሳ ሰክራና ወንድ ይዛ መምጣቷን ቀጥላበታለች... ሄኖክ እንደመጀመርያው ትምህርቱ ላይ ማተኮር አቃተው ከቀን ወደቀን ውጤቱ ያሽቆለቁል ጀመር በዚ ሁኔታው ግራ የተጋባው ጓደኛው ዶጮ በ ኤልሳ ምክንያት መሆኑን አልጠረጠረም በዚም ኤልሳን ለማናገር ወስኖ ሄደ ጠርቷት
ስትመጣ ከሜላት ጋር ነበረች ዶጮም ብቻዋን እንደሚልፈጋት ነገራት... ሜላትን ወደክፍል መልሳት አቤት አለችው እሱም ንግግሩን ለመጀመር ጉሮሮውን ጠራርጎ እየውልሽ ጓደኛዬ ባንቺ እተጎዳ ነው እናም... ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ማነው ጓደኛህ አለች ሄኖክ ነዋ አላት ኤልሳም የልቧ መደንገጥ የተሰማ መሰላት ሜላትን አልፈልግሽም ያለ እኔን ቀልደኛ ሁለተኛ እንዳጠራኝ ብላው ሄደች ይሄኔ ሄኖክን ኤልሳ ለማግኘት የግድ ሜላትን መቅረብ እንዳለበት መከረው... አንድ ቀን ምሽት ሄኖክ ተቀምጦ ፊልም እያየ ሳለ ያጎቱ ሚስት ሀና መኝታ ቤቷ ጠራችው እሱም እንደናቱ ስለሚወዳት ሄደ ይሄኔ ግን ያልጠበቀው ነገር ነበር የገጠመው ሀና የወሲብ ፊልም ከፍታ ውስኪ ትጠጣለች ልክ ሲገባ አንገቱን አርቀቅሮ አቤት አላት ና ጥሩ ፍልም እይ አለችው ይሄኔ በድንጋጤ አላበው...ሄኖክ አሳዳጊው ሀናን ሲያውቃት ስርአት የነበራት መልካም ሴት ከመሆንም ባለፈ ጥሩ እናት የነበረች ሴት ናት አጎቱ በህይወት እያለና ገና የሀያዎቹ መጀመርያ ላይ እያለች እንኳ እንደዚ ልቅበጥ አላለችም ነበር ግን አሁን እድሜዋ ወደ 30ዎቹ መጨረሻ ደርሷል
ነገር ግን አስነዋሪ ድርጊት ነው የምታሳየው ... ሄኖክን "ና ፊልም
እንይ" ብላ ያንን የወሲብ ፊልም ስትጋብዘው "አይ የቤት ስራ አለኝ" ብሏት ነበር የወጣው ግን ከዛች ደቂቃ ጀምሮ ይህ ድርጊቷ እረፍት ነሳው ለምን ነበር እንደ ልጇ የምታየውን ገና 20 ዓመት
ያልሞላው ልጅ የወሲብ ፊልም አብሯት እንዲያይ የጋበዘችው? ይሄ የሄኖክ የጭንቅላት ጥያቄ ነበር ግን ምንም መልስ አላገኘም...ሄኖክ ከዛ ቀን ቡሃላ እቤት መግባትና እዛ መኖር አስጠላው በዛ ላይ ደግሞ የኤልሳ ፍቅር ውስጡን ያምሰዋል ጓደኛው በመከረው መሰረት ኤልሳን ለማግኘት......
.........ይቀጥላል…..........✍
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
♥️ተወዳጁ
#ተከታታይ ልቦለድ
#ክፍል 2⃣
💢ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ ታሪክ
ሄኖክ የሀና ሁኔታ ቢረብሸውም ትላንት ደፍራ ልቡን ሰንጥቃ የገባችውን ሴት ለማየት እንደጓጓ ሰአቱ ደረሰ ይሄኔ ቀድሞ እዛ ቦታ የተገኘው እሱ ነበር ነገር ግን የመጣችው ከሩቅ የተመለከታት ሴት ነበረች... ገና ስትጠጋው ሽቶዋ የተማሪ አይመስልም የሀብታም ልጅ ለመሆኗ ወዟ ይናገራል ይሄኔ ሄኖክ ትላንት ያየውን ፈገግታ በማስታወስ የትላንቷ ልጅስ አላት ሜላት እባላለው የማፈቅርህና ደብዳቤ የላኩልህ እኔ ነኝ አለችው ሄኖክም ተናዶ ጥሏት ሄደ.... ሄኖክ በጠይሟ ልጅ የአይን ፍቅር ተለከፏል ጠይሟ ቆንጆ ኤልሳ ትባላለች የሜላት ጓደኛ ናት ሜላት ቆንጆ ዘናጭና የሀብታም ልጅ ብትሆንም "እርጋታዋና ስብእናዋ..." እያለ ሄኖክ የሚያወድሳት ግን ኤልሳን ነው ... ክፍል ገብቶ ተክዞ ሲቀመጥ ጓደኛው ዶጮ ሄኒዬ ችግር አለ ?" ሲል ጠየቀው ሄኖክም አይኑን ከተከለበት ሳይነቅል የገጠመውን ነገረው ዶጮም በዛ ጎርናና ድምፁ ከልቡ ስቆ "ሄኒዬ ቺኳኮ እዚ ግቢ ካሉ ሴቶቻችን ወደር ያልተገኘላት ናት በዛ ላይ አባቷ 6 መኪና አላቸው እና እኛ በሳምንት ልብስ ስንቀይር እሷ በ3 ቀን መኪና ትቀይራለች በዛ ላይ..." እያለ የማይቋረጥ የሚመስለውን ሀተታ ሲቀጥል... "ዶጮ እኔ ግን ለጓደኛዋ የሌለ አዲስ ስሜት ተሰምቶኛል!" አለው ዶጮም ጥቂት በዝምታ ተውጦ ሄኖክን ካስተዋለው ቡሃላ "አይ አይ ተምታቶብህ ነው ወዳጄ ኤልሳኮ ፀጉሯን ካለማበጠሯና ያቺን ቀይ ሲሊፐር ካለመቀየሯ የተነሳ ቅፅል ስሟ ድንቅ ነሽ ነው ምክንያቱም ሁሌም ተመሳሳይ ናት"...አለና ከት ብሎ ሳቀ ይሄኔ ሄኖክ በገዛ ጓደኛው በንዴት እየጋለ "ስማ ላይዋ ባይሽቀረቀርም ማንም ሊደፍረው ያልቻለውን ልቤን ደርምሳ ገብታለች እየውልህ ልታግዘኝ ባትችል እንኳ ዳግም እንደ ተራ ሰው የወረደ ንግግርህን መስማት አልፈልግም!" ብሎ ቦርሳውን አንስቶ ተነስቶ ወደ ላይብረሪ ሄደ... ዶጮ በሄኖክ ድርጊት ደነገጠ ብዙ ሴቶች ሊቀርቡት ሲመኙ እጅ ያልሰጠው ሄኖክ ዛሬ ተቀየረበት... ላይብረሪ ገብቶ የፊዚክስ መፅሃፉን ገለጠ ግን በሀሳብ ጭልጥ ብሏል ... ይሄኔ "ሄኖክ መልሱስ ላክልኝ እንጂ ብላሃለች..." የሚል ንግግር በሹክሹክታ ከጆሮው ሲፀርስ ተሰማው ከሀሳብ ሰመመኑ ብንን እንደማለት
ብሎ ቀና ሲል ያ ውብ ከለሯ ከውብ አይኖቿ ጋር ተደምሮ ልእልት ያመሰላት ቆንጆ ከጎኑ ተቀምጣለች ...ከንፈሮቿ ተገጥመው ልብ ቅርፅ ሰርተው ሲያያቸው ሰአሊ ባረከኝ ብሎ ተመኘ በድጋሚ ከነተጨባረረው ፀጉሯ ስታምር አለ በውስጡ ልጅቷ በዝምታ ሲመለከታት ግራ በመጋባት በቅንድቧ መልስልኛ አይነት ምልክት አሳየችው ሄኖክም ወደ ውጪ እንዲወጡ ምልክት ሰጣትና
ወጡ... "እእእ እየውልሽ ኤልሳ ይቅርታ አርጊልኝና ሳላነበው ጠፋብኝ ግን በቃልሽ ንገሪኝ ምንድን ነው?" አላት ኮስተር ለማለት እየሞከረ ኤልሳም እርጋታዋ ሳይለያት "እሺ እየውልህ ጓደኛዬ ሜላት በጣም ወዳሃለች እናም ተቀራርባቹ አንድ ላይ እንድትሆኑ ትፈልጋለች እባክህ ተረዳት ..." አለች አጠቃቀሟ
እንቅስቃሴዋ ሳይቀር ይማርካል ተመስጦ እያያት እያለ...."እ በላ መልስልኝ ምን ታስባለህ" አለችው......
...........ይቀጥላል…..........✍
