en
Feedback
Nathan casting agency

Nathan casting agency

Open in Telegram

The best place to get the best casting jobs Our services -casting models - for music clips - movies - series dramas - fashion shows - television shows Contact: 0920358051

Show more
Ethiopia16 170The category is not specified
408
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
አሰርኩሽ! እኔ ያንቺ አፍቃሪ፣ ፊደል ቆጥሬ የማድር የቆሎ ተማሪ፣ ሌቱን የማልተኛ፣ በፍቅርሽ ታስሬ ያጣሁ ሰሚ ዳኛ፣ በማህሌት በቅዳሴው እያሰላሰልኩሽ፣ ድንገት ከፊደላቱ መሀል አግኝቼሽ ደጋግሜ አነበብኩሽ፣ ከቆራቢዎቹ ተርታ ተሰልፈሽ ሳይሽ፣ ምስጋናዬ! ጨመረ አይን ለዓይን ስንተያይ በልሽ ማደሬ ዓይንሽ መሰከረ።

ባላገር! ያመሳስሉኛል እኔን ከባላገር፣ አንቺን ያገኘሁ እለት አፌም አይናገር።

❤️❤️ @nahita2👍 #join and #share @fkrnahiwot @fkrnahiwot
❤️❤️ @nahita2👍 #join and #share @fkrnahiwot @fkrnahiwot

❤️ኤልያስ ተሾመ❤️ Best performance on Fana Lamrot ("አንቺ የ እንጆሪ ፍሬ")🎤👌👏 🌺🌷🌷🌺

2.35 KB

1.60 KB

❤️​​​​ተወዳጁ #የመጨረሻው ክፍል #ክፍል2⃣1⃣ ኤልሳ ስትሮጥ ሄኖክ ሲከተላት መኪናዋን አቁማበት የነበረው ቦታ ደረሰች ወድያውም አስነስታ ልትሄድ ስትል ሄኖክ ደርሶ ኖሮ እያለከለከ ምን ሆነሻል ኤልሳ አትነግሪኝም ሲል በድጋሚ ጠየቃት ኤልሳም እንባዋ በጉንጮቿ እየወረደ ሄኖኬ ጉድ ሆኛለው ልክ እንደናቴ አባቴንም በኔ ምክንያት ላጣ ነው አለች እሺ ክፈቺልኝ ልግባ ቅድሚያ አለ መደንገጡ እንዳይታወቅበት እየጣረ ኤልሳም አይ ሄኒ ብቻዬን ልሂድ ምናልባት አብረን ሲያየን አባቴ ላይ እርምጃ ሊወስድ ይችላል አለችና በፍጥነት መንዳት ጀመረች ሄኖክ አላስቻለውም በኮንትራት ታክሲ ይከተላት ጀመር ከዛ ኤልሳ አባቷ ያለበት ቤት ደረሰች ግን በሚያሳዝን ሁኔታ አባቷን ሳታገኛቸው ቀረች ቤት ውስጥ ማንም አልነበረም ግን አንድ ነገር ተመለከተች ቤት ውስጥ ደም ተንጠባጥቧል ይሄኔ ኤልሳ እንደ እብድ አደረጋት መጮህና ማልቀስ የጠፋባት መሰላት... ወድያው ሄኖክ በሩን ከፍቶ ገባ እሮጣ ተለጠፈችበት ሁኔታዋ ግን ቅይርይር አለ ሰውነቷ ይንቀጠቀጣል ... አይዞሽ ውዴ ተረጋጊ አለ ሄኖክ እሱም ልክ እንደሷ ደሙን ሲያይ በጣም ደንግጧል ሄኖክ ገብቶ ጥቂት እንደቆዩ ወድያው ፖሊሶች ገቡ ጥቆማ ደርሶን ነበር አሉና ቤቱን መበርበር ጀመሩ ከዛም ወደ ጓሮ ዞሩ የኤልሳ አባት ተዘርረዋል... ኤልሳና ሄኖክ ፊልም የሚተውኑ እስኪመስላቸው ነገሩ ከበዳቸው ከዛም ጓሮ ከገቡት አንዱ ፖሊስ ወደቤት በመግባት አለቃ አንድ ሰውዬ አግኝተናል ግን በህይወት አሉ ምናልባት ከተረፉ እንሞክር አምቡላንስ ይምጣ አለ እ አባቴ ነው እ ንገረኝ ፖሊስ አባቴ ነው እያለች ለማየት ስትጣደፍ ሁለቱን ተጠርጣሪ ወደ ጣብያ ውሰዷቸው ተባለ ... ምክንያቱ ምንም ሳይገባቸው ሄኖክና ኤልሳ ታሰሩ አባቷ መናገር ችለው ካልተናገሩ በርግጠኝነት እስኪጣራ እየተባለ አይፈቱም ኤልሳ የእስር ቤቱን ህይወት አልችል አለች እነዛ ያልተፈቱ እንቆቅልሾቿን ተፈተው እስክታይ ጓጉታ ታነባለች ልጇን ከዛ ሰውዬ ተቀብላ አባቷን እያስታመመች በሷ ምክንያት ያለፈ ስቃዩ ሳያንስ አሁንም የታሰረውን ፍቅረኛዋን ባሏ አድርጋ መካስ ትፈልጋለች በዚ መልኩ አንድ ወር ሊሞላ 6ቀን ቀረው አባቷ ነቅተው ልጄስ ብለው ጠየቁ የሚያስታምማቸው አንድም ዘመድ ባለመኖሩ ጎረቤታቸው አስካለ ከጎናቸው አትጠፋም ..ልጄስ አሏት ደግመው እሷም እምባዋን በነጠላዋ እየሸሸገች ልጅህ ታስራለች እስኪጣራ ብለው አስረዋታል አለች ተይ አስካለ ልጄ ስቃይ ላይ ሆና ዝም አልሽ አሉ የኤልሳ አባት በደከመ ድምፃቸው ወድያው ፖሊሶች ገብተው ... እግዜር ይማሮት አባት አሉ የኤልሳ አባትም አይናቸውን ቡዝዝ አርገው እያፈራረቁ ተመለከቷቸው ፖሊሶቹም ቃል መቀበል ጀመሩ በሰአቱ የኤልሳ ባል ሊገላቸው እንደነበርና .... ደውሎ ድረሽልኝ እንድላት ያረገኝ እሱ ነው አሉ ፖሊሶችም ወድያው ሄኖክንና ኤልሳን እንዲፈቱ ትእዛዝ ሰተው ሰውየውን መፈለግ ጀመሩ ... ከ24 ሰአታት ቡሃላ አገኙት ልጇን መልሶ ወደ እስር ቤት ተወሰደ ... አሁን ሄኖክ ተረጋግቶ ኤልሳን ሚስቱ አርጎ በተማረበት መስክ ስራ ጀምሯል ደስተኛ ቤተሰብ ሆነዋል ልጃቸውን በፍቅርና በስስት ማሳደግ ቀጥለዋል የኤሳ አባትም ደስተኛ ልጃቸው ቤት ህመማቸውን እያስታመሙ ነው። በሰፈሩት ቁና እንዲሉ የኤልሳ የቀድሞ ባልም ፍርዱን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል....... ┈┈✦✿ ተፈፀመ💔 ✿✦┈┈ ይህ አሳዛኝ እና አስተማሪ የሆነውን ተወዳጁ❤️ የተሠኘው አጭር ልብ ወለድ ዛሬ በዚህ መልኩ ተፈፀመ እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለው ዳግም በሌላ ታሪክ እንገናኛለን መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ፡፡ 📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚 📖📖📖📖📖📖 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━

❤️​​​​ተወዳጁ #ተከታታይ ልቦለድ #ክፍል ሃያ ኤልሳ ልትወጣ ስትል ሄኖክ እጇን ያዝ አድርጎ ምንድነው አላት ኤልሳም እየተርበተበተች ባሌ ነው ድምፁ አስፈርቶኛል ምናልባት የሰማው ነገር ይኖራል አለችና ልጇን ና አባይዬ ብላ እጁን ይዛው ወጣች ... ሄኖክም ሁኔታዋ ስላስፈራው ከኋላ ተከተላት እውነትም ባልዋ ውጪ ላይ ይጠብቃት ነበር ገና ሲያያት ከመኪናው ወርዶ እየቀረባት ... አንቺ የድሃ ልጅ እድፍሽን ባጠራልሽ ደሞ ጎረምሳ አማረሽ አለ በሀይለ ቃል እሷም እንዳቀረቀረች አይ አጋጣሚ ነው አለች ፍርሃት በወረረው አንደበት ዝም በይ አለና ያ የሚያሳሳ ጉንጯን በጥፊ አቀላው ቀጥሎም ስሚ ሰው ያገኩሽ እኔ ነኝ አትሸውጅኝ ይሄን ጋጠ ወጥ የማላውቀው ይመስልሻል? አለና ወደ መኪናው ገፈተራት ... በራሴ መኪና እመጣለሁ ስትለው መልስም ሳይሰጣት የራሱ መኪና ውስጥ አስገባት... ሄኖክ ሁኔታቸውን ሲከታተል ትግስቱ ተፈታትኖታል ግን መታገስ ስለነበረበት ዝም አለ ... የሱ የሆኑ ሰዎች ሁሌም ተፈታኝ ናቸው በዚም እድለቢስ እንደሆነ ይሰማዋል... ኤልሳ መኪና ውስጥ ገብታ ከመቀመጧ ንዴቱ ያልበረደለት ባሏ አንቺን ያገባሁ ቀን ምናለ ቢደፋኝ አለ ይሄኔ የኤልሳም ትግስት አልቆ ኖሮ... ታድያ ለምን አፈታኝም ...እ... ምን ያዘህ አለችና መኪናውን ከፍታ ስትወርድ ቀድሟት ወርዶ እገልሻለው አንቺንም አባትሽንም ልቹቸን ነው የማስገባቹ አለ ይሄኔ ሰብለ ቀዝቀዝ አለች ለአባቷ ስትል ምንም መሆን እንዳለባት አስታወሰች .... ሄኖክ ግን አላስቻለውም ወደመኪናው በመቅረብ አንተ ማን የሚሉህ ገዳይ ነህ ባክህ እስቲ ይብቃህ... እድሜ ልክህን በቁም የገደልከን ይብቃህ አለው ሰውየውም በንዴት ጦፎ አንተ ወጠጤ ማንነቴን አታውቅም አለና ሄኖክን በቦክስ መታው ይሄኔ ግን ስብለ ትግስቷ ተሟጦ እየሮጠች ወደ ሄኖክ በመሄድ በቃህ ከዚ ቡሃላ የኔና ያንተ ጉዳይ አብቅቷል ዳግም ጫፉን እንዳትነካው እኔ የበደልኩት ይብቃ ብላ ከሄኖክ ጎን ቆመች ባሏም እሺ ዋጋ ትከፍይበታለሽ ሲል ዝቶ መኪናውን አስነስቶ ሄደ... በቆሙበት ጥቂት ከቆዩ በኋላ ኤልሳ ዋ...ይ ብላ ጮኸች ለካ ልጇን ይዞባት ሄዷል ሄኖክም እሷን ለማረጋጋት ጥረት እያረገ አይዞሽ የኔ ፍቅር ልጃችንን ይመልሳል አለና ወደቤት ይዟት ገባ... ሁለቱም በዝምታ ተዋጡ የማይተዋወቁ ይመስል የሚነጋገሩበት ርእስ አጡ ይሄኔ ነበር የኤልሳ የስልክ ጥሪ ዝምታውን ያደፈረሰው ... ስልኩን አውጥታ ስታየው አባቷ ናቸው ስልኩን አንስታ ገና ምንም ሳትል እንባዋ ይወርድ ጀመር ሄኖክም የደወለውን ሰው ለማወቅ እንደጓጓ አተኩሮ ይመለከታት ነበር ... አባቷ በታፈነ ድምፅ ልጄ ሊገለኝ ነው አሏት ምን አባዬ ብላወጥታ ስትሮጥ ምንድን ነው ኤልሳ ብሎ ሄኖክም ይከተላት ጀመር...... ...........ይቀጥላል…..........✍ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━

#Weeha_Despacito_Mash_up_cover . . . . @fkrnahiwot

#Tsedi_Mash_up_cover_video #kunamiga . . . . . @fkrnahiwot

#Kabila_from_zema_covers #Tigrigna_cover #Kabila_ gebreslasie . . . . @fkrnahiwot

❤️ተወዳጁ #ተከታታይ ልቦለድ #ክፍል አስራ ዘጠኝ ተወዳጁ 🌺ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ ሊፈፀም ሁለት ክፍል ብቻ ቀረው💔 ሄኖክ ሲነቃ ራሱን ያገኘው ሆስፒታል አልጋ ላይ ነበር ካጠገቡ ኤልሳ ነበረች አልጋው ጫፍ አቀርቅራ ታለቅሳለች ሄኖክም እዚ ለምን መጣው? አንቺስ እኔጋ ምን ትሰርያለሽ አለ በሚያሳዝን አንደበት ኤልሳም ይበልጥ እንባዋን መቆጣጠር እየተሳናት የፀሎት አባት ነግረውኝ ነው አለች ከዛም መልስ ሳይሰጣት የሆነው ትዝ አለው ፀሎት በህይወት የለችም! ይህን ሲያስታውስ ከመቅፅበት ብድግ አለ ኤልሳም ደንግጣ የኔ ውድ እዛው ተኛ እስኪሻልህ እባክህ አትነሳ አለች ... ሄኖክም እንባው ሳያቆም በምፀት ፈገግ ብሎ አያትና የተሰካለትን ግልኮስ ነቅሎት ካልጋው ወረደ ይሄኔ ኤልሳ አይሆንም ዶክተር ብላ ጮኸች ወድያው ዶክተሮቹ ገቡና ወደ ፀሎት አባት ተደውሎ እንዲመጡ ተደረገ ... የፀሎት አባት መተው ልክ እንደ ልጃቸው ሲያረጋጉት ለተመለከተ የሱ አባት ነበር የሚመስሉት ሄኖክም ፀሎትን አይኗን ሳላያት ፍቅሬን ሳልገልፅላት አፈር አለበሳችኋት አይደል አባባ እስቲ ንገሩኝ ፀሎትን ለዚ ያበቃኋት አውቄ እንዳልሆነ ገብቷታል ? አለ እንባው ያለማቋረጥ እየወረደ አባትየውም ልጄ ተው በቃ እሷን ፈጣሪ ስለሚወዳት ነው የወሰዳት አይዞህ ደሞ ልጄ አንተንም እንደልጄ እንዳይህ አደራ ብላኛለች አሉ ፀጉሩን አያሻሹ... አይ አባባ ያ ቢሆን ጥላኝ አትሄድም ነበር አለ የፀሎትን አባትና ሄኖክን ተመልክቶ ያላነባ አልነበረም ኤልሳም ይህን ማየት ተስኗት ተነስታ ውጪ ቁጭ አለች... ሁሉም ከተረጋጉ ቡሃላ ዶክተሮቹ ሄኖክን ዳግም እንዳይጨናነቅ አስጠንቅቀውት መውጣት እንደሚችል ገለፁለት ... ኤልሳም በመኪናዋ የፀሎት አባትና ሄኖክን ይዛቸው ሄኖክ የሚኖርበት ቤት ወሰደቻቸው ከዛም ልጇን ከትምህርት ቤት ማውጣት እንዳለባት ገልፃ ብቻቸውን ትታቸው ሄደች ሁለቱም በየራሳቸው የትዝታ ማእበል ይዋኙ ጀመር ... ከዛም የፀሎት አባት ከኪሳቸው አንድ የተጣጠፈ ወረቀት አውጥተው ወደ ሄኖክ እየዘረጉ እንካ ይሄ ልጄ የላከችልህ መልክት ነው አንብበው እናም የኔ ልጅ እኔም እንግዲ እዚ መቆየት አልፈልግም ከዚ ቡሃላ ለነብሴ መኖር እጀምራለው ወደ ትውልድ ቦታዬ አምርቼ ገዳም እገባለው ... አሉ ሄኖክ በቅጡ ያደመጣቸው አይመስልም እየተቻኮለ ወረቀቱን ገልጦ ያነብ ጀመር ሄኖኬ እንደምን አለህ እኔኳ ደና አይደለሁም መሞቴም አይቀርም ግን የኔ ውድ ሁለም ቢሆን ሞቼም ሳይቀር አፈቅርሃለው ይሄን አትርሳ የኔ ውድ በመጨረሻዋ ሰአት ደርሰህ ደስታዬን እጥፍ ድርብ አርገህልኝ ነበር የኔ ውድ ሁሌም ለኔ እንዲ መሆን እራስህን ተጠያቂ ታደርግ እንደነበር አውቃለው ግን ተሳስተሃል አንተ ምንም አላደረክም ወደ ህንድ የመጣሁትም የልብ በሽታዬን ለመታከም ነበር የልብ ህመም የነበረብኝ ደግሞ ገና ልጅ ሆኜ ነው እንጂ ባንተ አይደለም!! ሌላው ውዴ አደራ የምልህ ኤልሳ ታፈቅርሃለች አንተም እንደዛው በዛ ላይ ልጅ አላቹ ስለዚህ አብራቹ ሁኑ እሷን ከዛ አስቀያሚ ትዳር አውጣት!! መላካም ህይወት የኔ ውድ። ይላል ይሄን ተመስጦ እያነበበ እንባው ይወርድ እንደነበር ያስተዋለው ደብዳቤው በስብሶ ሲያየው ነበር ... ከዛም ቀና ብሎ ሲያይ የፀሎት አባት የሉም ... ኤልሳም ልጇን አውጥታ ቀጥታ ወደ ሄኖክ ተመለሰች ገና ገመግባቷ ስልኳ ጠራ ባሏ ነበር አንስታም ወዬ አለች ነይ ውጪ አንቺ ተራ አላት ልቧ ስንጥቅ አለ የልጇን ምሳቃ በቁሟ ለቀቀችው ይሄኔ ትንሹ ልጇና ሄኖክ በሁኔታዋ ደንግጠው ቆሙ እሷ ልጇን አውጥታ ስትሄድ ባሏ ለካ ይከታተላት ነበር...... ...........ይቀጥላል…..........✍ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━

❤️ተወዳጁ #ተከታታይ ልቦለድ #ክፍል አስራ ስምንት 💢ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ ታሪክ ፀሎት ያባቷን ቁጣ ስትሰማ ይበልጥ ውጪ ቆሞ ፀሎት የሚለውን ሰው ለማየት ጓጓች አባቷ ግን በአይናቸው ሄኖክን እንዲሄድ ይነግሩት ጀመር ሄኖክ ትግስቱ ተሟጠጠበትና አባቷን እስኪ እባኮትን አንድ እድል ብቻ ስጡኝና ያበላሸሁትን ላስተካክል ብሎ በሩን ግፍቶ አባቷን ገፍትሯቸው ገባ ፀሎትም ሄኖክን ስታይ እውን አልመስልሽ አላት ደንግጣ ፈዛ ቀረች ይሄኔ ሄኖክ እግሯ ስር ተደፍቶ ይሄ ላንቺ አይገባሽም ፀሎትዬ እያለ ያለቅስ ጀመር ፀሎት ማመን ትስኗት ፈዛ ቀርታለች ከዚ ቡሃላ ላንቺ እኖራለው እንደንግስት አነግስሻለው እንደ እናት እጦርሻለው የኔ ውድ እንደ ልጅ እንከባከብሻለው አለ ከልቡ እንደተፀፀተ እያስታወቀበት... አባትየውም ለሄኖክ ለመጀመርያ ግዜ አዘኑለት እሱ ሲያወራ እሳቸው አይናቸው እምባ አቅርሮ ነበር... ከዛ ቀን ቡሃላ ሄኖክ ስራ ለመቀየር ማፈላለግ ጀመረ በፀሎት ግፊትም ትምህርቱን በማታው መርሃግብር ቀጠለ ሁሌም ከስራና ከትምህርት ውጪ ባሉት ሙሉ ሰአቶቹ ፀሎትን ያዝናናታል እሷም ከሷ ውጪ ደስተኛ የሌለ እስኪመስላት ድረስ ደስታዋ ወሰን አጣ... ኤልሳም አካሏ ባሏ ጋር መንፈሷ ሄኖክ ጋር እንደሆነ ህይወቷን ቀጠለች ... ሄኖክ ትምህርቱን ጨርሶ ተመረቀ ፀሎት ሀኪሞቿ ከግዜ ወደግዜ ተሽሎሽ መራመድ ትችያለሽ ቢሏትም እስካሁን ግን አልቻለችም ስለዚህም ወደ ህንድ አገር ሄዳ እንድትታከም ተደረገ ስትሄድ ሄኖክም ያለችውን በሙሉ አባቷም ቤታቸውን ሳይቀር ሽጠው አልበቃ ብሏቸው ሄኖክ የመጀመርያ ፍቅረኛውን ኤልሳን እንድታግዛቸው ጠይቋት እሷም ያለምንም ማቅማማት ነበር እሺ ያለችው... በዚ መልኩ ፀሎት ከአባቷ ጋር ህንድ ሀገር ሄዳ ህክምና ጀመረች ... ቀናት ተቆጠሩና ወደ ሳምንታት ተቀየሩ ከዛም ወደ ወራት ሄኖክ ቢጠብቅም ሳይደወልለት ቀረ አባቷ ገና የገቡ ቀን ብቻ ነበር መግባታቸውን የተናገሩት ከዛ ግን ድምፃቸው ጠፋ ... ሄኖክም ጠንክሮ እየሰራ ነው ፀሎት ድና መታ አንድ ላይ መኖር የሚጀምሩበት ግዜና ሰርጋቸው ተደግሶ ፀሎት የምትመኘውን ሙሽራ ቀሚስ ለብሳ ማየት ይፈልጋል .... ልክ በስድስተኛው ወር ሄኖክ ከዚ ወዳላከቸው ሆስፒታል አምርቶ መረጃ መጠየቅ ጀመረ ስለፀሎት በጠየቀ ግዜ ሁሉም ደነገጡ ፊታቸው የሀዘን ጥላ አጠላ... የሆነውን መገመት አልፈለገም እስኪሰማ ድረስ ጓጓ መዳን አልቻለችም እናም ከሰሞኑ ትመለሳለች ነበር መልሳቸው ሄኖክ ይሄ ቢያሳዝነውም ይሄን ያህል ወር ያለምንም መፍትሄ የመቆየቷ እንቆቅልሽ ሳይፈታለት ይጠብቅ ጀመር ይህ በሆነ በ4ኛ ቀኑ ሄኖክ ስልኩ ጠራ አንስቶ ሀሎ ከማለቱ ኤርፖርት ተቀበለን አሉ አንድ ትልቅ ሰው በደከመ ድምፅ ሄኖክም ደስታና ድንጋጤ ተቀላቅለውበት የፀሎት አባት ፀሎቴ ደና ናት አለ ግን ምላሽ ሳይሰጠው ስልኩ ተቋረጠ.... ግዜ ሳያጠፋ ኤርፖርት ደረሰ እሱ ከደረሰ ከደቂቃዎች ቡሃላ በቁጥር 10 አካባቢ የሚሆኑ ሰዎች ወይኔ ልጄ እኔ አፈሩን ልብላልሽ እያሉ ጥቁር ለብሰውና ነጠላ ዘቅዝቀው ያለቅሳሉ ሲያያቸው በጣም አሳዘኑት ሰው ሊቀበሉ እንደመጡ ያስታውቃሉ ... እያያቸው በልቡ ሲያሳዝኑ በህይወት ሸኝቶ እሬሳ መቀበል ምን ያህል አለመታደል ነው ይላል ... ልክ ከ1ሰአት ቡሃላ የፀሎት አባት ጥቁር በጥቁር ለብሰው ብቅ አሉ ፀሎት የምትባል ልጅ ባካባቢው አትታይም እሳቸው ብቅ ሲሉ ለቅሶው ይበልጥ ይሰማ ጀመር ግራ ገብቶት ማንን ምን መጠየቅ እንዳለበት አያውቅም ይሄኔ የፀሎት አባትም ከለቀስተኛው ጋር ተደምረው ልጄ ልጄ ሲሉ አንዴ ብቻ ሰማቸው ከዛ እራሱን ስቶ ወደቀ............ .............ይቀጥላል…..........✍━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━

🎶Join @fkrnahiwot

Courage to change

🎶Join @fkrnahiwot

God save me, but..

🎶Join @fkrnahiwot