cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ

Advertising posts
906
Subscribers
+324 hours
+347 days
+6730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🔔የወንድሞቻችን የሐዘን ማጽናኛ በአንድነት መርሐግብር🔔 እንደምን ቆያችሁ ውድ የቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ልጆች? እንደሚታወቀው ባለፋት ሁለት ሳምንታት የግቢ ጉባኤያችን ሁለት ወንድሞቻችን አባላት አርፈዋል በመሆኑም ዛሬ ማለትም ዐርብ 09/09/2016 ዓ.ም በአንድነት መርሐ ግብር ላይ የሐዘን ማጽናኛ ኘሮግራም ግቢ ጉባኤያችን አዘጋጅታለች። መርሐ ግብሩን የሚዋጅ ጸሎት እንዲሁም ግንዛቤ የሚያስጨብጠን ትምህርተ ወንጌልም ተዘጋጅቷል። የጧፍ ማብራት ሥነ-ሥርዓትም የምናከናውነውን ይሆናል። ቦታ፦ ደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ቤተ ክርስቲያን (መሠረተ ወገራም አዳራሽ) ሰዓት፦ 11:45 ሁላችንም በመገኘት የግቢ ጉባኤያችንን አባላት አንድነት እናጠናክር! ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ✨
Show all...
12👍 3
የ2ተኛ ዓመቶች ኮርስ✨ #ኮርስን_በቤተሰብ ዛሬ ማለትም ኀሙስ 08/09/2016 ዓ.ም የሁለተኛ ዓመቶች ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር የተሰኘው አዲስ ኮርስ እንደሚቀጥል እያሳወቅን ሁሉም የሁለተኛ ዓመት ኦርቶዶክስ ተማሪ መገኘት ይችል ዘንድ ሁላችንም በመቀሳቀስ ሀላፊነታችንን እንድንወጣ አደራ እንላለን። ኮርስ፦ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ቦታ፦ ደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ቤተክርስቲያን (መሠረተ ወገራም አዳራሽ) ሰዓት፦ 11:45 ያላወቀውን እያሳወቅን! ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ✨
Show all...
👍 2
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእግዚአብሔር ፍፁም ሰላም እንደምን ዋላችሁ! ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ዛሬ የ4ኛ አመቶች ሐዋርያዊ ተልዕኮ የተሰኘዉ ኮርስ አለ! ቦታ፦ ደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ቤተክርስቲያን (መሠረተ ወገራም አዳራሽ) ሰዓት፦ 11:45 ያላወቀውን እያሳወቅን! ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ✨
Show all...
4
Photo unavailableShow in Telegram
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ? አሜን የእግዚአብሔር ስሙ ዘወትር ፈጽሞ የተመሰገነ ይሁን:: ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ ማክሰኞ ግንቦት 06/ 2016 ዓ.ም የአዲስ ገቢ ተማሪዎች 🙏የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐግብር🙏 ይኖረናል። ሰዓት- 11: 30 ቦታ- በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን 11:00 ላይ ካፌ በር ጋር ተሰባስበን እንሂድ። ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ የሚኪያሄዱ መርሐ ግብራት:- 1. ሕጽበተ እግር 2. የመክፈቻ ጸሎት 3. የበገና መዝሙር 4. የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት 5. ትምህርተ ወንጌል 6. መዝሙር 7. የመዝጊያ ጸሎት ነባር ተማሪዎች ይህንን መልዕክት በማስተላለፍ   አዲስ ተማሪዎችን እንቀበል ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪ እናስተላልፋለን! በሰአቱ ሁላችንም እንገኝ! ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️   ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ
Show all...
5👍 1
✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! 📌ዛሬ መምህሩ መገኘት ስላልቻሉ የ3ኛ አመት ኮርስ አይኖረም :: 🔔እንኳን ከአራቱ ዐበይት ነቢያት አንዱ ለሆነው ለካህኑ ኬልቅዩስ ልጅ ለታላቁ ነቢይ ለቅዱስ ኤርምያስ በአይሁድ እጅ በደንጊያዎች ተወግሮ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። ✝️ግንቦት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ (ከታላላቆቹ ነቢያት አንዱ) ✝️ ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት 2.ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ 3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ 5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ 🔔 "ኢየሩሳሌም ሆይ ነቢያትን የምትገድል : ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር : ዶሮ ጫጩቶቿን ከክንፎቿ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም:: እነሆ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላቹሃል:: እላችሁአለሁና : በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ እንግዲህ ወዲህ አታዩኝም::" (ማቴ. ፳፫፥፴፯-፴፱) ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ
Show all...
👍 5 2
✝️በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ አሜን! የዲ/ን ዮሴፍ ሚኒሊክ አጭር የህይወት ታሪክ ዲ/ን ዮሴፍ ሚኒሊክ ከአባቱ ከአቶ ሚኒሊክ አሰፋ እና ከእናቱ ከወ/ሮ አስቴር ወ/ዮሐንስ ሰኔ 30/1992 ዓ.ም ተወለደ:: 📌 የመዋዕለ ህጻናት ክፍለ ጊዜውን በሚሽን ካቶሊክ 📌 በ8 አመቱ እናቱን በሞት ያጣው ህጻን ዮሴፍ 1_4 ክፍል ያለ ትምህርቱን በባንዲራ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት 📌 ከ 5_10 ግራዝማች ጳውሎስ 1ኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 📌 11ኛና 12ኛ ክፍልን በቢሻው ወ/ዮሐንስ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት የተማረ ሲሆን በ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በ2011 ዓ.ም ወደ አ.አ ዩኒቨርሲቲ ገብቷል:: በሜዲካል ላቦራቶሪ የትምህርት ዘርፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 2015 ዓ.ም በዲግሪ ተመርቋል ። ሁሉን ለመልካም የሚያደርግ እግዚአብሔር ህማም ድካም ወደሌለበት ቤቱ ጠርቶት ፤ ግንቦት 1 የሚወዳት እናቱን የድንግል ማርያምን ልደት አክብሮ ግንቦት 2 /2016 ዓ.ም በተወለደ በ23 ዓመቱ ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል ። ዲያቆን ዮሴፍ ለካህናት ለዲያቆናት ጌጣችን ነው:: ከዮሴፍ ጋር መቀደስ ያጓጓል እድሜው ትንሽ ጸጋው ትልቅ ነው ፤ ትንሹ የማህሌታችን አድማቂ ከበሮ ያዣችችን እርሱ ነው። ያለርሱ አይሆንልም የደስታችን የሳቃችን ምንጭም ነው ጆሲ ። ዲያቆን ዮሴፍ ለደብረምህረት ሰንበት ተማሪዎች መድመቂያቸው ነው። እንደ ዮሴፍ ማን ይዘምራል? ህጻናት ክፍል ሆኖ በቅርብ ባሉ አድባራት ከሰንበት ተማሪዎች ጋር ባቀረባቸው ዝማሬዎች ሊቃውንቱን ሳይቀር ሰንበት ተማሪማ ደብረምህረት ቀረ ያስባለ የሰንበት ተማሪዎች መኩሪያ ነው ዮሴፍ። ሞገድ ሲመታኝ ማዕበሉ ሰባቱ መንጦላእት ወዴት ተጋረዱ ማርያምን ለመውሰድ አንፈራም ዮሴፍ ከዘመራቸው ወዲህ ደፍረን የማንዘምራቸው መዝሙሮች ሆነዋል፤ ማን እንደሱ ሊዘምራቸው ይችላል ። የህይወት ታሪክ ወግ ይዞን የሞተን ሁሉ በበጎ የማንሳት ባህል ተጭኖን ሳይሆን በእግዚአብሔር ፊት የምንመሠክርለት እውነት ነው ዲያቆን ዮሴፍ ትሁት ትሁት አገልጋይ ነበር ፣ ለሁሉ ያጎነብሳል ፣ ከአፉ ክፉ አይወጣም ፣ ከሰው ሁሉ ጋር በፍቅር መኖር ያውቃል ፣ ጆሲ እንደልጅ ከእኩዮቹ እንኳን ተጣልቶ አያውቅም እንዳዋቂ ቢያስታርቅ እንጂ ፤ ታላቆቹን ይመክራል ይቆጣል ፣ በኑሮው ምግባር ያስተምራል፣ ባባቱ ቤት ሲኖር ከአባቱ ትዕዛዝ የወጣበት ቀን የለም ፤ ሁልጊዜ እንደህጻን በመታዘዝ ኖሮ አለፈ እንጂ ። ዲያቆን ዮሴፍ / ገ/መስቀል ሞቱ እስከተሰማበት ቀን ድረስ ከማህሌት ከሰዓታት ከቅዳሴና ከሰርክ ጸሎት ታሞ እንኳን እማይቀር እየወደቀ እየተነሳ እግዘብሔርን ከማገልገል ያልሰነፈ ፤ እንደ ኢዮብ በፈተናም ውስጥ እግዚአብሔርን የማሰብና የመፍራት ምሣሌ ተደርጎ የሚወሰድ ብርቱ ልጃችን ወንድማችን ነበር። አልአዛርም ሞተ ፤ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት እንዲል መጽሐፍ የደጉ ልጃችን የትሁቱ ወንድማችን ነፍስ ከአብርሃም ከይስሐቅ ከያዕቆብ እቅፍ ትረፍ። ወኩሉ ዘሰአልክሙ በጸሎት እንዘ ትትአመኑ ትነስኡ። በሃይማኖት ጸንታችሁ የለመናችሁትን ሁሉ ታገኛላችሁ እንዲል ቅዱስ መጽሐፍ በማቴ ወንጌል እግዚአብሔር የእኛንም የገ/መስቀልንም የልመና ቃል ሰምቶ የክብሩ ቀዳሽ የመንግስቱ ወራሽ ያድርገው። እግዚአብሔር ያጽናን። የቦንጋ ደ/ም/ቅ/ድ/ማርያም እና አ/ገ/መንፈስ ቅዱስ ቤ/ን ሰንበት ት/ቤት
Show all...
48
Photo unavailableShow in Telegram
✨የሥነ ጽሑፍ ውድድር ለጸሐፍያን እነሆ✨ ግቢ ጉባኤያችሁ ጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ በሥነ ጽሑፍ ዘርፎች መወዳደር ለምትፈልጉ አሸላሚ የሆነ የሥነ ጽሑፍ ምሽት አዘጋጅቷል። 💥መወዳደሪያ ሃሳብ💥 በእንተ ቅዱሳን 💥መወዳደሪያ ዘርፎች💥 📝በግጥም፣ 📝ወግ፣ 📝አጭር ድርሰት እና ሌሎችም 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ለመሳተፍ 0924499739 ወይም 0942368775 ይደውሉ:: @Amikalo ወይም @Samfasil 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 📅የመጨረሻ ማስገቢያ ቀን:- ግንቦት 15 እንዳያመልጥም!!!
Show all...
ባሱ 1:15 ላይ ይንቀሳቀሳል የቀረ ተማሪ ካለ ቶሎ ኑ!
Show all...
ባስ መጥቷል የምንሄድ ሰዎች በያኔት በር በኩል እየጠበቀን ነው። ተሰባስበን እንሂድ።
Show all...
✝️የወድማችን የዲያቆን ዮሴፍ ምኒልክ የአስከሬን ሽኝት የምንሄድ ባስ ስለተዘጋጀ በያኔት በኩል ባለዉ በር ላይ ጥዋት 12፡20 ተገናኝተን ጥቁር አንበሳ የምንሄድ ይሆናል ፣ በስዓት እንገኝ ፡፡ ✝️አምላከ ቅዱሳን የወንድማችንን ነፍስ ከቅዱሳኖች ይደምርልን! ገብረ መስቀል እያልን በጸሎታችን ነፍስ ይማር እንበል! "እንግዲህ በህይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የእግዚአብሔር ነን" ሮሜ 14፡8 ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ
Show all...
28👍 2