cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቢል ኢስላሚ ነህያ

በአላህ ፈቃድ ኢስላማዊ፣ኦድዮዎች፣ቪድዮዎች፣ኢስላማዊ ትምህርቶችና ታሪኮች የምናቀርብበት ኢስላማዊ ቻናል ነው። find as on 👉facebook https://bit.ly/2zRqhwt 👉youtube https://bit.ly/2MmQqpq

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
232
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ተክቢር አሏሁ አክበር! የክርስትና መምህራን በጥላቻ ቀን ከሌሊት ኢሥልምናን ያጠለሻሉ፥ የእነርሱ የጥላቻ ዲስኩር እጅ እጅ ያላቸው እና ከጉያቸው የነበሩት የኦርቶዶክስ ምእመናት ወደ ዲኑል ኢሥላም እየመጡ ነው። 15 ልጆች ወደ ዲኑል ኢሥላም በሸሀደተይን ገብተዋል። የእኛ መምህራን የተውሒድን ብርሃን ለሙሥሊሙ እና ሙሥሊም ላልሆነው እያስተማሩ ይገኛሉ እንጂ አሉታዊ ነገር ላይ አይጠመዱም። አሏህ ይህንን ዲን ከፈለገ በከሃዲያንም ቢሆን ያጠናክረዋል፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 212 አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እነሆ ሙሥሊም የሆነች ነፍስ እንጂ ሌላው ጀነትን አይገባትም፥ አላህ ይህንን ዲን ከፈለገ በከሃዲያንም ቢሆን ያጠናክረዋል"። ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﻫُﺮَﻳْﺮَﺓَ، ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﻗَﺎﻝ ﻋﻦ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲّ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﺃﻧﻪ ﻗَﺎﻝَ ﺃَﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﻳَﺪْﺧُﻞُ ﺍﻟْﺠَﻨَّﺔَ ﺇِﻟَّﺎ ﻧَﻔْﺲٌ ﻣُﺴْﻠِﻤَﺔٌ، ﻭَﺃَﻥَّ ﺍﻟﻠﻪَ ﻳُﺆَﻳِّﺪُ ﻫَﺬَﺍ ﺍﻟﺪِّﻳﻦَ ﺑِﺎﻟﺮَّﺟُﻞِ ﺍﻟْﻔَﺎﺟِﺮِ‏ መጪው ዘመን የኢሥላም ነው። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ረመዷን ሙባረክ እርሶ ከቁርዓን ጋር ይተዋወቃሉ? የቂርዓቶ ደረጃንስ ማሻሻል ይፈልጋሉ?እነሆ የምስራች በመላው አለም ለምትገኙ ለቁርዐንና ለሀዲስ ትምህረት ፈላጊዎች በሙሉ አልበራሒን ኦንላይን ቁርአን የቦታ ርቀት ሳይገድባቹ ቁርዐንን ባላቹህበት ቦታ አስተካክሎ ለመቅራት ልዩ የኦንላይን ቁርዐን ፕሮግራም አዘጋጅቷል።በተጨማሪም ለርሶና ለልጆችዎ በመልካም ልዩ ትምህርት ( አኽላቅ፣አዝካር፣ ሲራ እና ሀዲስ) የትም መሄድ ሳይጠበቅባቸው በኦንላይን የዘመኑን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ትምህረት ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል። ፈጥነው ይመዝገቡ እርሶ እኛ ጋር ሲቀሩ ከወጪ ቀሪ የሚገኘው ትርፍ ሙሉ ለሙሉ ኢስላማዊ ስራዎችን ብቻ በመስራት ላይ ላለው አልበራሒን ጀመዓ የሚውል መሆኑ በደስታ እንገልፃለን!ኒያ ካሎት የኸይር ስራ ተቋዳሽም ኖት ስልክ ቁጥር +251912104750 በኢንቦክስ👇👇 @Fozmohmmed ግሩፑን ይቀላቀሉ👇👇👇 https://t.me/+5c5NKMc7F75hNDQ0
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Show all...
አዲስ ዳዕዋ ሚስትህን ማን ብለህ ነው ምትጠራት?//ustaz moahammed ferej

አዳዲስና ወቅታዊ ዳዕዋዎች እንዲደርሷችሁ ሰብስክራይብ ያድርጉ!#like #share #subscribe#bilal_tube #somi_tube_comedy #harun_tube #Zawya_TV #ዛውያ_ቲቪ #africa_tv_channel #Nesiha_TV #አፍሪካ...

╔═══════════╗ የአሊሟ ሴት ገጠመኝ ╚═══════════╝ የሸይኽ ሰኢድ ኢብኑ ሙሰዪብን የዕውቀት ገበታን ያዘወትራል። በረሀውን አቆራርጦ በብርድ በቁሩ፣ በሙቀት በግለቱ አንገቱን ሰበር አድርጎ ጆሮውን ቀስሮ ከማዕዱ ይቋደሳል። አቡ ወዳአ ሲሉም ይጠሩታል። የጀነቱ ጨፌ ከሚቀጠፍበት ሥፍራ ለሁለት ወራት ከራቀ በኋላ ወደ ዒልም ገበታው ዳግም ተመለሰ። ሰላምታን ከኡስታዙ ጋር ተለዋወጠና የናፈቀውን ትምህርት መከታተል ጀመረ። ደርሱ እንዳበቃ በምን ምክንያት እንደቀረ ለምንስ ሳይናገር እንደጠፋሁ ሸይኹ ጠየቁ። ባለቤቴ ሞታብኝ ሀዘን ላይ መቆየቱን አብራርቶ አስረዳቸው። ሰው ከበዛበት ቦታ ገለል አድርገው ወሰዱትና እንዲህ በማለት ጠየቁት፦ "አዲስ ሚስት ለማግባት አላሰብክምን?!" "ለኔ አይነቱ የቲም ሆኖ ላደገ፣ ድሃ ሆኖ ለኖረ ልጁን የሚድር ማን አለ?! ወላሒ አሁን ከሁለት ዲርሃም ሀብትም ሆነ ንብረት የለኝም" በማለት መለሰላቸው። "ልጄን እድርልሀለው" አሉት። ታላለቅ ባለስልጣናት ልጃቸውን ጠይቀው አልድርም ማለታቸውን ያውቃልና ይህን ቃል ሲሰማ ምላሱ ተኮላተፈ። ተንተባተበ። "የችግር ህይወቴን አውቀው ልጅዎን ሊድሩኝኝ?" በማለት በተደናገጠና በተቆራረጠ ድምፅ ጠየቀ። "አዎ! ልጄን እድርልሃለው ኃይማኖቱና ሥነምግባሩ ያማረ ሰው ካገኘን ልጃችንን እንድንድር እስልምና ያዘናልና አንተ ደግሞ በሥነ ምግባርህ ትሁትን አደብ ያለህ መልካም ሰው ነህ" በማለት መለሱለት። ለምስክርነት የሚሆኑ ሁለት ሰዎችን ጠሩና ያለችውን ሁለት ዲርሀም መህር አድርገው ኒካሁ ታሰረ። ከድንጋጤና ከደስታው ብዛት የተነሳ የሚናገረውን ማወቅ ተሳነው። ከተቀመጠበት ብድግ አለ። ቀኑን ፆመኛ ስለነበር መስጂድ ገብቶ የመግሪብ ሰላት ሰገደና ወደ ቤቱ አቀና። ልጅቱን ሳያውቃትና ሳያያት መቀበሉ ገርሞት አንገቱን ነቀነቀ። ትርክቱን ለባለታሪኩ እንተውለት "ቤት እንደገባሁ ፋኖሴን አብርቼ የማፈጥርበትን ዘይትና ዳቦ አቀረብኩ። አንድ ሁለት እንደጎረስኩ የቤቴ በር ተንኳኳ። "ማነው?" በማለት ከበሩ ኋላ የቆመውን ሰው ማንነት ለማጣራት ጠየቅኩ። "ሰዒድ" የሚል ምላሽ ሰማሁ። በአላህ እምላለሁ!ሰዒድ በሚል መጠሪያ የማውቃቸውን ሰዎች ሁሉ ሳስብ ኡስታዜ ሰዒድ ኢብኑ ሙሰዪብ ይሆናል ብዬ ፈፅሞ አላሰብኩም። አርባ ዓመታትን ሙሉ ቤቱ ወይም መስጂድ እንጂ ሌላ ቦታ ታይቶ አይታወቅም። አወለሰፍ እንጂ የሰውን ጀርባ እያየ ሰግዶ አያውቅም። በሩን ከፈትኩ ከፊት ለፊቴ ኡስታዜ ቆሟል። ደነገጥኩ። "ልጁን ለኔ አይነቱ መናጢ ድሃ በመዳሩ ተፀፅቶ ሀሳቡን ሊቀይር ነው የመጣው ብዬ አሰብኩ "ያ አባ ሙሐመድ! እዚህ ድረስ በመምጣት ለምን ደከምከ ሰው ልከህ ብታስጠራኝ እመጣ ነበር" አልኩትና ወደ ቤት እንዲገባ ጋበዝኩት። "ዛሬ መምጣት ያለብኝ እኔ ነኝ። የመጣሁትም ልጄ ሚስትህ ሆናለችና እሷ አባቷ ቤት ብቻዋን አንተም በቤትህ ያለ አጫዋች ስለሷ እያሰብክ ብቻህን መሆንህን ጠልቼ ይዣት መጥቻለሁ" አለና ከጎኑ ወፈቆመችው መልከ መልካም እንስት ዞሮ "ልጄ ሆይ! በአላህ ስምና ረድኤት ወደ ባልሽ ቤት ግቢ" በማለት የአባትነት ትዕዛዙን አስተላለፈ። ከሐያእዋ የተነሳ ወደኔ ስትራመድ ቀሚሷ አደናቅፏት ልትወድቅ ተቃረበች። አባቷን አንኳ በስርአት ሳልሰናበት እየተጣደፍኩ ወደ ውስጥ ዘለቅኩ። ድህነቴ ስላሳፈረኝ የፋኖሱን ብርሃን አደብዝዤ ዳቦና ዘይቱን አልጋ ስር ደበቅኩት። የቤቴ ጣራ ላይ ወጥቼ "ሰዒድ ኢብኑል ሙሰዪብ ልጁን ዳረኝ ቤቴ ድረስም ይዞልኝ መጣ" ብዬ ከፍ ባለ ድምፅ አዋጅ አልኩ። ከጎረቤቶቼ መካከል አንዲት አሮጊት በመስኮት በኩል አንገቷን ብቅ አርጋ እንዲህ አለችን፦ "አንተ ሰው! ለመሆኑ የምትናገረውን ታውቃለህ? ሰዒድ ልጁን ድሮህ ከቶውንም ቤትህ ድረስ ይዞልህ ሊመጣ? እሷ እንኳን ላንተ ለድሃው ለታላቁ መሪ ልጅ ወሊድ ቢን አብዱልመሊክ እምቢ ተብላለች ውበቷስ ቢሆን ላንተ ለደሃውማ አትገባም" "ግቡ ቤቴ ናት ያለችው ተመልከቷት እውነተኛነቴን ታረጋግጣላችሁ" አልኳት። ከአዲሷ ሚስቴ ጋር የጫጉላ ቆይታዬን ጨርሼ ወደ ቀድሞው የዕውቀት ገበታ ዒልምን ለመቋደስ ስነሳ "አንተ የዓይኔ ማረፊያ የቤቴ ሙሶሶ ባሌ ሆይ! አባቴ ጋር ያለው እውቀት ሁሉ እኔም ጋር አለና ቁጭ ብለህ ቅራ" በማለት በጆሮዬ ሹክ አለችኝ። ቁርአንን በቃሎ የሸመደደች። የረሱልን ﷺ‎ ሐዲስ የሐፈዘች የጌታዋን ቃል አክባሪ፣ የተማረችውን ዕውቀት ተግባሪ፣ አላህን ፈሪ የባሏን ሀቅ ጠባቂ መልከ መልካምና እጅግ ቆንጆ እንስት ሆና አገኘኋት። አሚን በሉ ልመርቃችሁ! የእስልምና አኽላቅን የተላበሰች፣ ልጆቻችሁን በጀግንነት አሳድጋ ለቆራጥ አላማ የምታዘጋጅ እንስትን አላህ ይወፍቃችሁ። ሴቶችዬ በኢማን የበለፀገ በተግባር የጎለበተ እንደ ሰላሐዲነል አዩቢ አባት ልጆቻችሁን የሚያንፅ ባል ይስጣችሁ ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ
Show all...
هزاع البلوشي سورة الكهف 🎙ሀዛዕ አልቡሉሽ ሱረቱል ካህፍ🌺 قــال رسول الله ﷺ ‏ ‏أكثروا من الصلاة عليّ ليلة الجمعة و ⁧ #يــوم_الجمعة ⁩ فإن صلاتكم معروضة عليّ حديث صحيح .. ‏ﷺ 🌿 ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ https://t.me/Qidmeia_le_tewhid https://t.me/Qidmeia_le_tewhid
Show all...
هزاع_البلوشي_سورة_الكهف_كاملة___.m4a5.71 MB
ቃላቶች ተሰሳክተው ሊገልፁት የማይችሉት ሃሴት ሄዶ ሄዶ ዛሬ ላይ አረፈ።ዛሬ የምንጊዜም የህይወት ዓላማችን የሆነውን ቁርዓን ተፍሲር (መሰረታዊ ማብራሪያ) አጠር ባለ መልኩ ለ5 ተከታታይ ወራት ኢማም አል ቡኻሪ ኢስላሚክ አሶሴሽን በርቀት አስተምሮ አስመርቆናል።በዚህ ሂደት ላይ የተሳተፉትን ሁሉ አላህ ጀዛቸውን እጥፍ ድርብ አድርጎ በዱንያም በአኺራም ይመንዳቸው።ቀስ በቀስ እንቁላል በግሩ ይሄዳል ነውና እኛም ለትልቁ የቁርዓን ጉዟችን ይህ መንደርደርያ መሰረት ይሆነናል።ለ5 ወራት በሙሉ 10ፈተናዎችን ሙሉ 30ጁዝ ቁርዓንን ማለትም 114 ምዕራፎችን በፅሁፍ እየፃፍን ስናስገባ ነበር። ከብዙ የህይወት ሃላፊነቶች እና ውጣ ውረዶች ጋር ይህንን እቅድ በርቀት ማስኬድ ከባድ ነበር።ፈተና ደርሶ ስንፈተን የነበረበት ጊዜ አሁንም አይኔ ላይ በምናብ ይታየኛል።ወላሂ ይናፍቃል!! የአላህ ቃልን እንደኛ ወይም ከኛ በበለጠ ቅርብ ሆኖ ላየው ሰው ወላሂ ጣፋጭነቱ ልብን ይሰረስራል።የላቀ ጌታችን አነገገሩ የስነ ፅሁፍ ጠበብቶችን በዝረራ ማርኮ ጥሏል። ቁርአንን ለእኛ የሰው ልጆች መግለፁ ከባድ ነው።ስለዚህ አላህ እራሱ ሲገልፀው እንሐልከት።ልዕልናው የላቀው ሃያሉ ጌታችን አላህ ባወረደው ጥበብ በተሞላው መፅሃፉ እንዲህ ብሎ የለ! وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ...... እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡.....42፥52 አላህ ቁርዓንን ሩህ (እስትንፋስ፣መንፈስ)ብሎ የጠራው ልቦች በርሱ ህያው ስለሚሆኑ ነው። የሞቱ ልቦች ህይወት ይዘራሉ። يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَتْكُم مَّوْعِظَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَاءٌ لِّمَا فِي الصُّدُورِ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡ ለዚህ እኔ አንዱ ምስክር ነኝ።ልቤን ዳግም የተወለድኩ ያህል ህያው ሲያረግ ይሰማኛል።ነገሮችን የምመለከትበን የእይታ አቅጣጫ ለውጦልኛል። እኔ ሁሌም ማይረሳኝ የተፍሲር ኦድዮ እያዳመጥኩ የጀነት ወስፍን የሚያብራሩ አንቀጾች ሲመጡ ጥልቅ የሆነ ተመስጦ ውስጥ እገባ ነበር።ልክ ሌላ ዓለም ላይ እንዳለው ይሰማኛል።ኡስታዝ አቡ ያሲር(አብዱል መናን) ልቤን ሰለበው እንዴ ያስብላል።ሌላ ተጨማሪ ወራትን ምነው በድጋሜም ቢሆን ተምሬ ባሳልፍ የሚለው ሃሳብ እስካሁን ከአእምሮዬ ላይ ብቅ ካለ ጀምሮ ሊጠፋ አልቻለም።ብዙ ማለት ይቻላል ግን ቃላቶችን ነባብሬ ስሜቴን ልገልፅ ባለመቻሌ እዚህ ጋር ላቁም። ሁላችሁም ዛሬ በኢማም አል ቡኻሪ ተመራቂ ተማሪ የነበራችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ።አላህ በዚህ በተማርነው ለትልቅ እውቀት እንድንደረደር በር የሚከፍትልን ያርገው።አደራ የምለው ይህ የተፍሲር ትምህርትን ኢማም አል ቡኻሪ ገብታችሁ እንድትማሩ ነው።ወላሂ ከቁርዓን ጋር መተሳሰር እጅግ እጅግ እጅግ እጅግ.... ቃላቶች ከሚገልፁት በላይ ደስ ይላል።ነገሩ ከትግልና ከልፋት ጋር ሲሆን ደግሞ የመጨረሻው ውጤት ይበልጥ ውብ ይሆናል። ይሄ ዋና ቻናላቸው ነው ገብታችሁ መረጃዎችን ታገኛላችሁ፦ https://t.me/ethiobukhari2020 https://t.me/ethiobukhari2020 ለመመዝገብ ዝግጁ የሆነ 🔑
Show all...
ኢማም አል ቡኻሪ ኢስላሚክ አሶሴሽን//Imam al-bukhari islamic association

ኢስላማዊ ዕውቀትን ከምንጩ ! ለበለጠ መረጃ +251930491483

🔑 9
የሳሊም ታሪክ አዲስ የሼኽ ኻሊድ ራሺድ ትርጉም ዳዕዋ//2021 ትርጉም>>በላጭ ሕዝቦች https://youtu.be/WbJ_roA_E34 https://youtu.be/WbJ_roA_E34
Show all...
የሳሊም ታሪክ አዲስ የሼኽ ኻሊድ ራሺድ ትርጉም ዳዕዋ//2021

#በላጭ_ሕዝቦች #ሼር #ላይክ እባክዎ ይህን ስራ ለትርጉም እንደጀማሪነታችን ስለለፋንበት ሌላ የዩቲዩብ ቻናል ላይ አትለጥፉ❗❗ መልካ,አስማማው አህመድ,ሚፍታህ ሁሴን,አብዱሰላም አበራ,አሊ አሚን,ሙአዝ ሀቢብ,somi tv,abu hayder #Halal_Media​ #ድምፃችንይሰማ​ #ፍትህለአክሱምሙስሊሞች​ Fana EBC,#Top5Stunning​ EthiopianArtistsByRank #MaramawitAbate​ #FryatYemsalem​ #ZeriruKebede​ #DanaitMekbeb​ #waziworld​ #mikishow​ #senseletdrama​ #SaronAyelign​ #HuluDaily​ #FryatYemene​ #Seifufantahun​ #seifufantahunonebs​ #Ashurka​ #ashruka​ #ethiopianmovie​ #ashrukaamharic​ #ethiopianewmusic​ #hopeentertainment​ #ashrukachannel​ #calebmeakins​ #ethiopianartist​ #ethiopiancomedy​ #ebs​ #ashrukamedia​ #Akukulu​ #Mikael​ #NahooTv​ #Nahoo​ #ethiopia​ #ethiopian​ #addisneger​ #diretube​ #DrAbiy​ #Abiy​ #SeifuonEBS​ #Seifufantahun​ #NewEthiopianMusic​ #tigrignamusic​ #ebstv​ #JTVEthiopia​ #HopeMusicEthiopia​ #AbyssinyaVine​ #ZEMENTV​ #SundayWithEBS​ #LTVWorld​ #MinewShewaTube​ #ADMASMUSIC​ #EBS​ #Amharictube​ #FanaTelevision​ #EthiopianTV​ #EBC​ #betoch​ #comedy​ #ethiopiancomedy​ #betochcomedy​ #ethiopia​ #amharicfilm​…

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.