cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የደ/መ/ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የፈለገ ዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት የመዝሙር ንዑስ ክፍል 💚

ይህ ቻናል የመዝሙር ክፍሉን እንቅስቃሴ እና የሰንበት ት/ቤቱን ወቅታዊ መረጃ የምንከታተልበት ነው ።

Show more
Advertising posts
602
Subscribers
+124 hours
+37 days
+2430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰላም የተከበራችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ። የልዑል እግዚአብሔር ፍፁም ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን። ነገ ረብዕ እና ሐሙስ የሐምሌ የቅዱስ ሚካኤል ወረብ ጥናት ስለሚኖር ሁላችንም አባላት በተለመደው የመዝሙር ጥናት ሰዓት እንድትገኙ በልዑል እግዚአብሔር ስም እናሳስባለን። አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ከሁላችን ጋር ይሁን። ሰናይ ቀን !!!
Show all...
ሰላም የተከበራችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ። የልዑል እግዚአብሔር ፍፁም ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን። ነገ የሰርግ አገልግሎት ስለሚኖር ሁላችንም በሰዓቱ ተገኝተን እንድናገለግል ስንል በልዑል እግዚአብሔር ስም እናሳስባለን። ቅዱስ ሚካኤል አገልግሎታችንን ይባርክልን። ሰናይ ምሽት!!!
Show all...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!   በቀጣይ ሦስት ዓመታት ሰንበት ትምህርት ቤታችንን በሥራ አመራርነት የሚያገለግሉ የሥራ አመራር አባላት።
Show all...
👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🤝ሰላም የተወደዳችሁ የማኀበረ አፍቃርያነ ንባብ ቤተሰቦች እንሆ ሰባተኛው ዙር የሶስተኛው ዕጣ ዕቁብ በዛሬው ዕለት  28/10/2016 ዓ.ም በጸሎት በመርሐ ግብር የወጣ ሲሆን ከ12/11/2016 ዓ.ም በወራዊ የጸሎት መርሐ ግብር መጻሕፍት የሚሰጥ ይሆናል። 👉 ለባለ 400 ብር ዕቁብተኞች           1  ገነት ቦጋለ           2  አንተነህ ኃይሌ ለእያንዳንዳቸው የ2000 ብር መጻሕፍት የሚገዛላቸዉ ይሆናል። 👉  ለባለ 200 ብር ዕቁብተኞች           1  አለባቸው ማሬ           2  ቤዛዊት ፍቃዱ           3  አባይነህ አወቀ           4  ዮዲት እንዳለ           5  ሰላም ክብረአብ   ለእያንዳንዳቸው የ1000 ብር  መጻሕፍት የሚገዛላቸዉ ይሆናል። 👉ባለ 100 ብር ዕቁብተኞች ደግሞ          1 ጀምበር መለስ ሲሆኑ ለእያንዳንዳቸው የ500 ብር መጻሕፍት የሚገዛላቸዉ ይሆናል። የመጻሕፍት ዝርዝር ማሳወቂያ ጊዜ 28/10/2016 ዓ.ም እሰከ 07/11/2016 ዓ.ም ይሆናል። የክፍያ ጊዜ:- ከሐምሌ 01 እሰከ ሐምሌ 05 2016 ዓ.ም ጊዜውን ተጠብቆ በሥርዓቱ ለሚከፍል መጨረሻ ላይ ታይቶ ሽልማት የሚሰጥ ይሆናል ወስብሐት ለእግዚአብሔር። 📜 ማንበብ መንፈሳዊ እርካታን ይሰጣል                   ዕቁቡ ይቀጥላል...........ለበለጠ መረጃ የመጻሕፍት ዝርዝር ለማሳወቅ እና ለክፍያ  :- በ0910021824(የአብስራ ጸደቀ) ደውሎ ማግኘት ይችላሉ።
Show all...
#በስመአብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን 🔔🔔🔔የሰንበት መርሃ ግብር 🔔🔔🔔             📆 እሁድ ሰኔ 30 /2016 ዓ.ም            🕰 ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ              ⛪️ በትምህርት ቤቱ አዳራሽ በዕለቱ :➡️ ትምህርተ ወንጌል             ➡️ ስንክሳር             ➡️ ወንጌል ትርጓሜ             ➡️ ኪነጥበብ             ➡️ ዝማሬ      ሁላችሁም ተጋብዛችኋል 🙏🙏 የደ/መ/ቅ/ሚካኤል ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት ት/ት ክፍል እና የሰውሃብት ክትትል
Show all...
ከ_ግንቦት_13_ሰኔ_19_አቴንዳንስ_የተስተካከለ_1.PDF9.30 KB
ደስ ይበለን ======= ደስ ይበለን/2/ አምላክ አለ መሐላችን ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ ገናና ነው አምላክ ስምህ አ.ዝ-----------------------// ምሕረቱን አይተናልና አድርሶናል አምላክ በጤና ይችን ዕድሜ የጨመረልን ለንስኃ ጊዜ የሰጠን አ.ዝ--------------------------// ኃጢአትህን ይታገስሃል በቸርነት አምላክ ያይሃል ደስታ ነው በሰማያት በአንድ ኃጥእ የፅድቅ ሕይወት አ.ዝ-----------------------------// እልል በሉ የጎበኛችሁ በምሕረት ዓይኑ ያያችሁ በችግር ቀን ያሰበን ሁሉ አመስግኑ ዝምም አትበሉ አ.ዝ-------------------------// ድንግል ማርያም ትፀልያለች ኃጥኡን ሰው ማረው እያለች በድንግል ክብር እንኖራለን በጽኑ ፍቅር አንድ እንዲያደርገን
Show all...
አማን በአማን:(4) መድኃኒአለም ተመስገን ለዚህ ፍቅርህ ምን ልክፈልህ:(2) ድብቁን ኃጢአት አንተ ብትገልጸው: ይቅር ብለኸኝ ባትሸፋፍነው: እንደ ሰው በቀል ቢኖር ጌታ: ለኔ ኃጢአትስ የለውም ቦታ: ----- አዝማች ----- በየደቂቃው ኃጢአት ስሰራ: ስሰርቅ ስበድል አንተን ሳልፈራ: አንተ ግን ፊትህ ምንም ቢቀየም: በቁጣህ በትር አልገረፍከኝም: ----- አዝማች ----- ምህረትህን ልከህ አድነኝ ዛሬ: ታክቶኛልና በኃጢአት መኖሬ: አለም በኃጢአት እየሳበችኝ: በጽድቅ ደስታ መኖር አቃተኝ: ----- አዝማች ----- የኃጢአት ጉዞ ጣፋጭ ቢመስልም: ውጤቱ መሮ ፍጹም አይጥምም: እንደ በደሌ ስላልከፈልከኝ: ተመስገን እንጂ ሌላ ምን አለኝ:
Show all...
ሰላም የተከበራችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ የልዑል እግዚአብሔር ፍጹም ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን። እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለመድሀኒአለም ወርሃዊ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን። ዛሬ በሚኖረን የአውደ ምህረት አገልግሎት የሚዘመሩ መዝሙሮች 1. አማን በአማን 2. ደስ ይበለን 3. መድሀኒአለም አዳነን የሚሉት ይሆናል። የምንችል እግዚአብሔር የፈቀደልን መጥተን እናገልግል። አምላከ ቅዱስ ሚካኤል አገልግሎታችንን ይባርክልን በረከቱን ያሳድርብን። ሰናይ ቀን
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.