cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Agape-True Love

True love is God and he gave us his only son Jesus Christ. Throught Jesus Christ we had an eternal life.

Show more
Advertising posts
205
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ትሕትና ✍️Bini Girmachew ኃጢአትህ እየበዛ ሲመጣ የሌሎች ስህተት እየታየህ ይመጣል ፡፡ ጽድቅ በውስጥህ እየተስፋፋ ሲመጣ የራስህ ደካማነት ይታይሃል ፡፡ ትሕትና በአደባባይ እንደ ለበስከው ነጭ ሸማ ነው ፡፡ ታጌጥበታለህ ፡፡ ትዕቢት ግን ያዋርድሃል ፣ የማያውቅህ ሳይቀር አይቶ ይጸየፍሃል ፡፡ ቁመተ ረጅሞች ሲኮሩ ሰማይን የምታይ ይመስልሃል ፡፡ አጭሮች ሲልመጠመጡ መቃብር የገቡ ይመስላል፡፡ የረጅምነት ውበቱ ዝቅ ማለት ነው ፡፡ ትዕቢተኛ ስትሆን ሰዎች እንከን እንዲፈልጉብህ መንገድ ትከፍታለህ ፡፡ ትሕትና ራስን የማወቅ ውጤት ነው ፡፡ ራሱን በትክክል የሚያውቅ ሊታበይና በሌሎች ሊፈርድ በፍጹም አይችሉም ፡፡ ትሕትና የሌሎችን ክብር ማወቅ ነው ፡፡ ማክበር መከበር ነውና ሌሎችን ስናከብር ትሕትና ታስከብረናለች ፡፡ ትሕትና ሁልጊዜ እንደሚማሩ ሁኖ መኖር ነው ፡፡ ትሕትና በጠፋበት ዘመን ሁሉም ሰው አስተማሪ ይሆናል ፡፡ ሁሉም ሰው ቅዱስ ነኝ በማለት ሌሎችን ያጣጥላል ፡፡ ጆሮ ጠፍቶ አፍ ብቻ የበዛበት ዘመን ዘመነ ትዕቢት ነው ፡፡ እገሌ ክፉ ነው ማለት በተዘዋዋሪ እኔ መልካም ነኝ ማለት ነውና ትዕቢት ነው ፡፡ ትሕትና የሰዎችን ትልቅ ድካም አሳንሶ ፣ ትንሽ ብርታታቸውን አጉልቶ ያሳያል ፡፡ ትሕትና እንዳልኖሩ ሁኖ ከሌሎች ልምድን መቅሰም ነው ፡፡ ከፍ ላሉት ዝቅ ማለት ትሕትና አይደለም ፡፡ ከፍ ያሉትማ ግርማቸው በግድ ያሰግዳል ፡፡ ትሕትና ዝቅ ላሉት የምናሳየው ፍቅርና ክብር ነው ፡፡ ለእግረኛ ቅድሚያ ስትሰጥ አንድ ነገር አስብ ፡- “መኪና ለሰው እንጂ ሰው ለመኪና አልተፈጠረም፡፡” እውነተኛ ትሕትና ለሚያንሱን መታዘዝ ነው ፡፡ ሰው እንደዚህ ሁኖ እንደማይቀር ብናስብ ስንት ሕጻናትን ስንት ድሆችን ባከበርን ነበር ፡፡ ትሕትና የልብ መሰበር ያመጣልና ለዝማሬና ለንስሐ ያበቃል ፡፡ አበባ ካልታሸ አይሸትም ፣ ፍራፍሬ ካልተጨመቀ አይጠጣም ፡፡ ሰውም ትሑት ካልሆነ መልኩ አይወጣም ፡፡ ትሕትና ያወቁትን ያለ ትችት ማስተማር እንጂ አላውቅም ማለት አይደለም ፡፡ እያወቁ አላውቅም ማለት ልግመት ፣ ሳያውቁ አውቃለሁ ማለት ራስን አለማወቅ ነው ፡፡ ያወቁትን በትጋት ማስተላለፍ ትሕትና ነው ፡፡ የተማርከው ሌሎችን ደንቆሮ ብሎ ለመሳደብ ሳይሆን በጨለማ ላሉት ብርሃን ለማወጅ ነው ፡፡ የጋን ውስጥ መብራት ከመሆን የሚያድነው ትሕትና ነውና ስታውቅ ትሑት ሁን ፡፡ ፍሬ ያለው ዛፍ ዘንበል ይላል ፡፡ ቀና የሚሉት ዛፎች ግን ፍሬ የሌላቸው ናቸው ፡፡ በእውነት ካወቅህ ያላወቅከው ስለሚበዛብህ ትሑት ትሆናለህ ፡፡ በአንድ ጥቅስ ጫካ የሚገቡ የአቡጊዳ ሽፍቶች ግን ትዕቢተኞች ናቸው ፡፡ “ድምፅና ቁንጫ ባዶ ቤት ይወዳል” ይባላል ፡፡ ቁንጫም እንደ ልቡ ይዘላል ፣ ባዶ አዳራሽም ድምፅን ያስተጋባል ፡፡ ጩኸት ማብዛት የባዶ ቤት ምልክት ነው ፡፡ ባዶ ሰው ከቀድሞ የከፉ የሰባት ኣጋንንት ማደሪያ ይሆናልና እባክህ ባዶ አትሁን ፡፡ ትሕትና የልብ ነው ፡፡ የልብ ያልሆነ ትሕትና የአንገት መሰበር ፣ የጉልበት መሸብረክ ብቻ ነው ፡፡ በልብ እየናቁ በአፍ ማክበር እርሱ ትሕትና ማጣት ነው ፡፡ የወደቀውን ለማንሣት ዝቅ ትላለህ ፣ ወደ ሐኪም ቤት ለማድረስ አህያህን እንደ ደጉ ሳምራዊ ለቀህ እግረኛ ትሆናለህ ፡፡ የስድብ አምሮትህን ለመወጣት “ውሾች” ይላል ቃሉ ፣ የነቀፋ ጥማትህን “ተኩላ” ይላል ወንጌሉ እያልህ ከተወጣኸው ኃጢአትና በቅዱሱ ነገር መበደልህ ነው ፡፡ ውሻ ፣ ተኩላ ያለው ጠባያቸውን ለመግለጥ እንጂ ላንተ ስድብ ለማበደር አይደለም ፡፡ ትሕትና ተፈትኜ አልጨረስኩም ብሎ በራሱ በጣም አይመካም ፡፡ ገና በፈተና ዓለም ያሉ ሰዎችንም በጣም አያመሰግንም ፡፡ እባክህ ወዳጄ ትሑት ሁን ፡፡ የበላይ የበታች ሁሉም ልቡ ጎረምሳ ሁኗልና የሚያስተነፍስ መዓት ሳይመጣ ትሕትናን ገንዘብ እናድርግ ፡፡ ትሕትናን በማጣት ያሳዘንከውን ፈጣሪን በብዙ ትሩፋት አታስደስተውም ፡፡ ትሕትና የእምነት መጀመሪያ ነውና ፡፡ በስተመጨረሻ 1- ከሰው ጋር ንግግር ከመጀመርህ በፊት በማለዳ ጸልይ ። 2- አእምሮህን ሰፊ ለማድረግ ቀኑን በንባብ ጀምር ። 3- ከእንቅልፍ እንደ ተነሣህ የዓለምን ወሬ አትስማ ። 4- ያላለቀው ጉዳይህ የዛሬው ሥራህ ነውና ተደሰትበት ። 5- ንጽሕናህን ጠብቅ ፣ ለራስህ ያለህ ክብር ማሳያ ነውና ። 6- ሁሉም ነገር ከተሳካ የምትሠራው አይኖርህምና ሁሉም ነገር ይሳካ ከማለት ተቆጠብ ። 7- ለትምህርት የዕድሜ ገደብ የለውምና እስክትሞት ተማር ። 8- ለሚወዱህና ለሚያከብሩህ ቅድሚያ ስጥ ። 9- ጉዳይን ከባለቤቱ እንጂ ከሦስተኛ ሰው አትስማ ። 10- በትሕትና ለሚያገለግልህ ክብር ይኑርህ ፣ ምቹ ነገርንም አዘጋጅለት ። 11- ባዶ እጅህን ተወልደሃልና ፣ ባዶ እጅህንም ትሄዳለህና ስለ ንብረት ሕይወትህን በብስጭት አትጉዳ ። 12- መታዘብህ ውስጥህን እንዳይጎዳው ከብልጦች ጋር ጊዜ አታጥፋ ። 👇👇👇👇👇👇👇👇 @agapetruelove
Show all...
ይህንን ዕድል ተጠቅማችሁ ተሸላሚዎች ሁኑ።
Show all...
Show all...
Safaricom Ethiopia

safaricom በኢትዮጵያ ያሉ telegram ተጠቃሚዎችን ዕውቅና ለማግኘት ሽልማቶችን አዘጋጅቷል።የኛን ዕውቅና እያሰፉ ተሸላሚ ይሁኑ🎁

Photo unavailableShow in Telegram
“ራእይህን ማወቅ እና መኖር” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በቅርብ ቀን በገበያ ላይ ይጠብቁ! ከመጽሐፉ መግቢያ ላይ የተወሰደ ሃሳብ ላጋራችሁ፡- የራእይ ጉልበት “ራእይህን እጅግ ግልጽ አድርገህ ከማወቅህ የተነሳ በሕይወትህ ግራ የሚያጋቡህ ሁኔታዎች ትርጉም-የለሽ እንዲሆኑ ማድረግ ትችላለህ" – Anonymous • አንድ ሰው የሚሞተው ጤናው ሲጠፋ ብቻ አይደለም … ራእይ ሲጠፋም ጭምር ነው! • አንድ ሰው የሚከስረው ስራ ሲበላሽ ብቻ አይደለም … የራእዩ ሁኔታ ሲበላሽም ጭምር ነው! • አንድ ሰው ብቸኝነት የሚሰማው ሰው ሲርቀው ብቻ አይደለም … ራእይ ሲርቀውም ጭምር ነው! • አንድ ሰው ተስፋ የሚቆርጠው ሁኔታዎች አልታይ ሲሉት ብቻ አይደለመደ … ራእይ አልታይ ሲለውም ጭምር ነው! • አንድ ሰው ውዳቂ የሚሆነው ስልወደቀ ብቻ አይደለም … ራእዩን ሲጥል ጭምር ነው! . . . እያለ እውነታው ይቀጥላል፡፡ ይህ እውነታ እንደሚያሳየን አንድ ሰው ምንም እንኳን በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሲያልፍ የዚያን ሁኔታ ውጤት መቅመሱ ባይቀርም፣ የመጨረሻውን ውሳኔ ከሚያስላልፉትና በብርታትና በደካማነት መካከል ከሚወስኑት ሁኔታዎች መካከል አንጋፋው ራእይ የመኖሩና ያለመኖሩ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ “ራእይን ማወቅና መኖር” በተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ የምንመለከታቸው እውነታዎች የራእይን ትርጉም ከመገንዝብ አንስተን እንዴት ራእያችንን ማግኘት፣ ማዋቀር፣ መከተልና ወደስኬታማ ጎዳና መግባት እንደምንችል ጥርት ባለ መልኩ ያሳዩናል፡፡
Show all...
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

Repost from Dr. Eyob Mamo
Photo unavailableShow in Telegram
ልዩ ናችሁ! አዎ! ልዩ ናችሁ! እናንተነታችሁ ማንም ሰው ጋር ኖሮ አያውቅም፣ አሁንም የለም፣ ወደፊትም አይኖም! አንድ ሰው በአስገራሚ ሁኔታ ያስቀመጠውን አንድ ሃሳብ ላጋራችሁ፡- “አሉኝ የምትሏቸውን ነገሮች በሙሉ (ገንዝብ፣ ቁሳቁሱ፣ እውቀት፣ ውበት …) ተመልከቷቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ሌሎች ሰዎች ጋር አሉ፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ሌላ ሰው በፍጹም የሌለው አንድና ብቸኛ ነገር እኛነታችን ብቻ ነው፡፡ የቀሩት አሉኝ የምንላቸው ነገሮች በሙሉ ሌሎች ሰዎች ጋር አሉ”፡፡ ስለዚህ ከሁሉም በፊት ራሳችሁን ሁኑ፣ ራሳችሁን ተቀበሉ፣ ራሳችሁን አክብሩ፣ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፣ ራሳችሁን ምሩ፣ ራሳችሁን ይቅር በሉ፣ ከራሳችሁ ጋር ደስተኞች ሁኑ፣ የግል ራእያችሁን ለይታችሁ እወቁና ኑሩት . . . ፡፡ መልካም ቅዳሜ ይሁንላችሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
Show all...
ኢሬቻን የምታከብሩ ወየውላችሁ||ኢሬቻና የማያልቀው ትልቅ መዘዝ||የቄስ ቶሎሳ ጉዲና ጥብቅ ማሳሰቢያ||@ቤተሰብ Beteseb

Welcome to Agape Media#Subscribe​ በማድረግ የደውል ምልክቱን በመጫን በየግዜው የሚለቀቁ አስተማሪ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ Ethiopian Protestant Spiritual YouTube Channel Content Copyright ©2022: #Agape Media Ethiopian Protestant Mezmur, Breaking News, celebrity news, fashion, comedy, Ethiopian music, and news analysis, blogging, information, vine .....all Entertainment. -------- --------- ---------------------- ---------------- ---------- #protesetan_song #new_Worship #Mezmur #share #subscribe #like #share @ebstv worldwide @Abel Birhanu @Yenante Media @Guramayle ጉራማይሌ ዜና @MARSIL TV WORLDWIDE @Apostle Israel Dansa / Jesus Wonderful TV @Prophet Eyu Chufa @PRESENCE TV CHANNEL WORLD WIDE @ESATtv Ethiopia @Miko Mikee @የናንተው መንፈሳዊ tube Ynanetwe @Rakeb Alemayehu @Dagi Show - ዳጊ ሾው @Ethiopia tiya Diy @Minew Shewa Network @Hope Music Ethiopia @Kana Television @Betoch Comedy @Eyoha Entertainment #protestant_worship_song_2021 #Amharicworship #worshipsong #amharicsong #ethiopianSong #WORSHIP #GOSPELSONG #AMHARICWORSHIP #MEZMUR #AMLEKO #ETHIOWORSHIP #ETHIOPIANSONG #AMHARIC #AMHARICMEZMUR #GREATART #EPHRAIMAMARE

ራስህን በሚገባ መምራትን ተለማመድ! 🔰ራሱን የሚገዛ ከተማን ከሚገዛ ይሻላል። 🔰የትልቅ ውጤት ምስጥር ራስህን በየቀን መግዛትና መምራት ነው። 🔰ተስጦ ስላለህ ብቻ ትልቅ ውጤት አታመጣም። 🔰በራስህ ላይ በጎ ተጽኖን አሳድር። ራስህን ስማ! ራስህን ተከተል!ራስህን አክብር! 🔰አንተ ራስህን ካልሰማህ ለምን ሌሎች ይስሙህ?! አንተ ራስህን ካላመንህ ለማን ብለው ሌሎች ይመኑህ?! 🔰መሪነት በራስህ ላይ በጎ ተጽኖን በማሳደር ይጀምራል። አንተ እቅዶችን ዘርዝረህ ስታበቃ በእቅዶችህ የማትመራ ከሆነ ታድያ ለምን ሌሎች እንድታዘዙልህ ትጠብቃለህ። 🔰የሚልዮኖችን ህይወት የሚነካ መሪ መሆን ትፈልጋለህ ? ራስህን ድንቅ በሆነ መንገድ መምራትን ተማሪ! ሰዎች ምክርህን ሳይሆን ምሣለነትህን ነው የሚከተሉት። መልካም   ምሽት ውዶች!! ይቀላቀሉን 🔔👇👇👇          ♨️@agapetruelove          ♨️@agapetruelove          ♨️@agapetruelove
Show all...
#እግዚአብሔርን_መፍራትና_ጥቅሞቹ!! (በመጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ) "እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጠንካራ መታመን አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያ ይኖራል።" (ምሳሌ 14፡26) እግዚአብሔርን መፍራት ትልቅ ጥቅም አለው። ጥቅሙ ወደ ቀጣይ ትውልድም የሚሻገር ነው። ጥቅሙን (ጥቅሞቹን) ከማየታችን በፊት ግን እግዚአብሔርን መፍራት ምንድነው? በማለት ብንጠይቅ መልካም ይሆናል። እግዚአብሔርን መፍራት፣ ሃሳቡ ለእግዚአብሔር ዕውቅና መስጠትን፣ እግዚአብሔርን ማክበርን፣ ማምለክንና ለእርሱ መገዛትን የሚያጠቃልል ነው። እግዚአብሔርን መፍራት የመንፈስን ጥንካሬ የሚገልጥ አቋም እንጂ ደካማነት አይደለም። እግዚአብሔርን መፍራት ለእግዚአብሔር የሚኖረንን ፍቅርም ይገልጣል። የምናፈቅረውን እናከብራለን። የሚፈራው ሰው የእግዚአብሔርን ፍቅርና ርኅራሔም ይለማመዳል። ጥቅሞቹ 1. እግዚአብሔርን መፍራት ከሌሎች ፍርሐቶች ነጻ ያወጣል። በመተማመን፣ በልበ ሙሉነትና በፍጹም በእርጋታ ያኖራል። "ጠንካራ መታመን" የሚለው አገላለጽ ይህንን ያመለክታል። በሌላ ሥፍራ "በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱ ዘንድ ተማምኖ ይኖራል። በትከሻውም መካከል ያድራል።" የሚል እናገኛለን። (ዘዳግም 33:12) በመዝሙር 46:1-2 ላይ ደግሞ "አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው። ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም።" ይላል። እግዚአብሔርን መፍራት ሌሎቹን ፍርሐቶች ያስወግዳል ማለት ነው። 2. እግዚአብሔርን መፍራት ለአስተዋዮች የኑሮ ጥበብም ነው። መጽሐፈ ምሳሌ ለትውልድ የአንዋንዋር ጥበብን የሚያስተምር መጽሐፍ ነው። ጥበቡ ከእግዚአብሔርም ከሰውም የተጣጣመ ግንኙነትን እያስገኘ ያስቀጥላል። መግባባት የመልካም ግንኙነቶች ቁልፍ ነገር ነው። ጠቢብ ሰው ደግሞ ለመግባባት የማይቸገርና የማያስቸግር ይሆናል። ምክንያቱም፣ ፈርሐ እግዚአብሔር ከክፋት እየጠበቀ የልብ ቅንነትን ያስገኛል። ልበ ቅንነት ለመግባባት ያመቻል። ክፋት ግን ማሕበራዊ ግንኙነትን ያናጋል። 3. እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰው እግዚአብሔር ራሱ መጠጊያው ይሆንለታል። መጠለያና የመጠበቂያ ጽኑ ምሽግ ። ከእርሱ የሚበልጥ መታመኛ (መጠጊያ) የትም አይገኝም። መጠጊያነቱም ለትውልድ የሚተርፍ ነው። ትውልዱ በፈርሐ እግዚአብሔር ለመኖር የሚመርጥ ከሆነ ማለት ነው። ፈርሐ እግዚአብሔር ለዘመናት ብዙዎችን እየጠቀመ ይኖራል። በብሉይ ኪዳን ዘመን ጠቅሟል። በአዲስ ኪዳን ዘመንም እጅግ አስፈላጊ የሆነ እሴት ነው። ጌታ ኢየሱስ እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ነበረው። (ኢሳ 11፡2። ዕብ 5፡7) ሐዋርያቱም በትምሕርታቸው ፈርሐ እግዚአብሔርን አካትተዋል። (የሐዋ 9፡31። 2ቆሮ 7፡1። ኤፌ 5፡ 21። ፊልጵ 2፡12። 1ጴጥ 1፡17።ዕብ 12፡28።) ይህን ያደረጉት ጥቅሙን ስላወቁ ነው። ባይጠቅም ኖሮ አይጽፉትም ነበር። ፈርሐ እግዚአብሔርን መለማመድ የምንጀምረው ከቤተ ሰብ መሆን አለበት። በአደባባይ የምንገልጠው ባሕርይ በቤት ውስጥ ያሳደግነውን ነውና። እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት እርስዋ ትመሰገናለች (31፡31)። ኑሯንና ቤትዋን በጥበብ ትመራለች። ለባልዋ መልካምን በማድረግ፣ ልቡን በማሳረፍ፣ ለቤተ ሰብዋ የታታሪነት ምሳሌ በመሆን፣ ንግግርዋን በጥበብ በማሰማት። ለዚህ ሁሉ መሠረቱ እግዚአብሔር መፍራት ነው ለማለት ይቻላል። ሰውየውም ሴትዮዋም በፈርሐ እግዚአብሔር መመራት ይጠበቅባቸዋል። የቤታቸው፣ የትዳራቸው ራስ የሆነውን ጌታ ክርስቶስን መፍራት፣ ማክበርና መታዘዝ ይኖርባቸዋል። ይህን ካደረጉ ጠቢባን ናቸው። ለትውልድ ጭምር የሚተርፍ መታመኛና መደላደያም አግኝተዋል ለማለት እንችላለን። መጪው ዘመን ከፊት ይልቅ እግዚአብሔርን በመፍራት ዝንባሌ የምንመላለስበት፣ ይህንን ጥበብ የምንማርበትና ጥቅሞቹንም የምንቀበልበት ይሁንልን። ከብዙ ሰዎች ልብ በፍጥነት እየጠፋ ያለ ይህ ክቡር እሴት በእኛ ዘንድ በስስት የሚያዝ ይሁንልን። አሜን። መስከረም 8/2015 ዓ.ም
Show all...