en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

ETHIO CRYPTO ™

ETHIO CRYPTO ™

Open in Telegram

Join us✨ for insightful analysis, expert tips, and exclusive strategies to maximize your returns in the dynamic world of digital assets. we launch projects on how to make money online🌟

Show more
3 571
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-8230 days
Posts Archive
#ትንሳኤ እንኳን አደረሳችሁ ! ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ
#ትንሳኤ እንኳን አደረሳችሁ ! ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን። በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊትና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል። በተጨማሪም ፤ በዓሉን በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በጥቃት፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን ፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን። የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን ! ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን ! መልካም በዓል

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ትንሳኤ እንኳን አደረሳችሁ ! ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ
+1
#ትንሳኤ እንኳን አደረሳችሁ ! ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን። በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊትና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል። በተጨማሪም ፤ በዓሉን በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በጥቃት፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን ፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን። የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን ! ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን ! መልካም በዓል ! #TikvahFamily❤️ @tikvahethiopia

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ጠፍተን ነበር በቅርብ ቀን እንመለሳለን ። እስከዛው የምትፈልጉትን ኮመንት ላይ አስቀምጡልን። @StudeNT-TeXT

የሬሚዳል ፕሮግራምን ለመከታተል የመመዝገቢያ ነጥብ በመንግስት እና በግል ዩኒቨርሲቲዎች ይለያያል? ትምህርት ሚኒስቴር ከ50 በመቶ በታች ያመጡ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የሬሚዳል ፕሮግራምን በተለያዩ አማራጮች እንዲከታተሉ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም። የመቁረጫ ነጥቡ ለታዳጊ እና አርብቶ አደር ባልሆኑ ክልሎች የተፈጥሮ ሳይንስ  ተማሪዎች ለወንድ 263 ከ700 ለሴት ደግሞ 227 ሲሆን ለማህበራዊ ሳይንስ ለወንድ 220 ከ600 እንዲሁም ለሴት 190 ከ600 መሆኑን ማሳወቁም የሚታወስ ነው። በዚህ የሬሚዳል መቁረጫ ነጥብ መሰረት ባደረግነው ምልከታ ከተቀመጠው ነጥብ #በታች ያመጡ ተማሪዎችን የሚመዘግቡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መሆራቸውን አይተናል። ምዝገባውን እያከናወነ ላለው ዩኒቨርሲቲ እና ኮሎጁ ትምህርት ሚኒስቴር ካስቀመጠው ነጥብ በታች ያመጡ ተማሪዎችን ለምን መዘገባችሁ? በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄ መንግሥት ይፋ ያደረገው ለመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች እንጂ ለግል ተቋማት አይደለም ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል። አል ዓይን ይህን ጥያቄ ይዞ ትምህርት ሚኒስቴርን የጠየቀ ሲሆን የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙንኬሽን ሀላፊ ወይዘሮ አመለወርቅ እዝቅኤል፥ "ለሬሚዳል ፕሮግራምም ይሁን ከ50 በመቶ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች መመዝገቢያ ነጥብ ለመንግሥትም ይሁን ለግል ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ ነው" ሲሉ ተናግረዋል ። ከዚህ በፊት የነበረው ለግል እና ለመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የተማሪዎች መመዝገቢያ ነጥብ ይለያይ ነበር ያሉት ሀላፊዋ፥ ከ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በኋላ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን አክለዋል። በዚህም መሰረት ትምህርት ሚኒስቴር ካስቀመጠው የሬሚዳል ፕሮግራም መመዝገቢያ ነጥብ ውጪ የሚመዘግቡ ዩኒቨርስቲዎች እና ኮሌጆች ህግ እየጣሱ መሆኑንና እርምጃም እንደሚወሰድባቸው ነው ያብራሩት።

#MoE በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን አማካይነት ማስተካከል ይችላሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳስውቋል። ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከል የሚችሉት እስከ የካቲት 10/2015 ዓ.ም ድረስ መሆኑ ተመላክቷል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ @student_text

#MoE በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒ
#MoE በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን አማካይነት ማስተካከል ይችላሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳስውቋል። ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከል የሚችሉት እስከ የካቲት 10/2015 ዓ.ም ድረስ መሆኑ ተመላክቷል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ More : @tikvahuniversity @tikvahethiopia

photo content

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የመግቢያ መስፈርቶች 1. አመልካቹ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የወሰደ ብቻ መሆን አለበት። ፈተና (EHEEE) በ2023 ጂሲ 2. የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ውጤት የሚከተለውን መሆን አለበት። ሀ. ለአፋር፣ ቦርና ዞን (ኦሮሚያ) ቤንሻግሉ ጉምዝ፣ ጋምቤላ፣ ሶማሌ፣ ደቡብ ኦሞ ዞን (ደቡብ ክልል)፣ ዋጌህሚራ ዞን (አማራ) እና ምዕራብ ኦሞ ዞን (ኤስኤን.ኤን.ፒ.) ለወንድ 400 እና ከዚያ በላይ ለሴት 375 እና ከዚያ በላይ ለ. ለሁሉም ሌሎች ክልሎች፡- ለወንድ 450 እና ከዚያ በላይ ለሴት 425 እና ከዚያ በላይ 3.  ከ9ኛ -12ኛ ክፍል ያለው የጽሑፍ ግልባጭ አማካኝ ምልክት 80% እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት። 4.  ከ9ኛ -12ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ግልባጭ መሰቀል አለበት። 5. ግልጽ የሆነ የመግቢያ ቁጥር የሚያሳይ የEHEEE ውጤት ያትማል። 6.  የማመልከቻ ክፍያ 100 ብር ተከፍሎ ደረሰኙ መጫን አለበት። 7. ሁሉም አስፈላጊ መረጃዎች ከተሞሉ እና ከተሰቀሉ ማመልከቻው የተሟላ ይሆናል። 8. እባክዎን https://portal.sphmmc.edu.et/Web/የመስመር ላይ ማመልከቻን ይጎብኙ። APPLICATION ተቀባይነት ያለው በመስመር ላይ ብቻ ነው። ወደ ኮሌጅ በአካል አይምጡ። አስተያየት • የጽሁፍ ፈተና 60% ይይዛል እና ሁኔታዊ የፍርድ ፈተናዎችን ይሸፍናል። • ብዙ አነስተኛ ቃለ መጠይቅ (30%) (ለአጭር የተዘረዘሩ አመልካቾች ብቻ) • የአካዳሚክ መዝገቦች 10% (የጽሑፍ ግልባጭ 5% እና EHEEE ውጤት 5%) • የኮሌጁ ከፍተኛው የመቀበል አቅም 65 ተማሪዎች ነው። • ከጠቅላላው ቅበላ 15% ከሚከተሉት ታዳጊ ክልሎች እና ተቀባይነት ይኖረዋል ዞን፡ አፋር፣ ቤንሻንጉል -ጉምዜ፣ ቦረና (ኦሮሚያ)፣ ጋምቤላ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ኦሞ (ደቡብ ክልል)፣ ምዕራብ ኦሞ (ደኢህዴን)፣ ዋጊመራ (አማራ) • የጽሁፍ ፈተና እሁድ ፌብሩዋሪ 26፣ 2023 GC ይካሄዳል • የጽሁፍ ፈተና እና ቃለ መጠይቅ የሚሰጠው በአዲስ አበባ እና በቦታ ብቻ ነው። የፈተና ማእከል በኮሌጁ ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ, Facebook ላይ ይገለጻል እና ቴሌግራም መለያ። • የኮሌጁ የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል አ/ሲ ቁጥር 1000208431068 • ያነጋግሩ፡ - ስልክ፡ +251118965125። • የመስመር ላይ ማመልከቻ ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 14 ይጀምራል እና የመጨረሻው ቀን ረቡዕ፣ ፌብሩዋሪ 22፣ 2023 ከምሽቱ 5 ሰዓት (በአካባቢው በ11 ሰዓት) ነው። @student_text

#የመቁረጫ_ነጥብ የአቅም ማሻሻያ (ረሜዲያል) የመቁረጫ ነጥብ፦ - የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 263 - የተፈጥሮ ሳይን
#የመቁረጫ_ነጥብ የአቅም ማሻሻያ (ረሜዲያል) የመቁረጫ ነጥብ፦ - የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 263 - የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 227 - የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 220 - የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 190 - የታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 210 - የታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 210 - የታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 180 - የታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 180 @stUDenT_TExT

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ያረጋገጠውና ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተላከ አንድ ደብዳቤ ፦ - የ2015 ዓ/ም የ1
+1
#MoE ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ያረጋገጠውና ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተላከ አንድ ደብዳቤ ፦ - የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ነሐሴ አጋማሽ በከፍተኛ ተምህርት ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ታቅዷል። - የ2015 ዓ/ም የመጀመሪያ ዲግሪ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እስከ ሐምሌ 15 /2015 እንዲጠናቀቅ ታሳስቢ ተደርጓል። - የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው በመንግስት የኒቨርስቲዎችና ተቋማት የሚደለደሉትንና በራሳቸው ወጪ በመሸፈን በግል የሬሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን በተመለከተ ፦ • የራሚዲያል ፕሮግራም ለአራት (4) ወራት ከየካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሰጥ ታቅዷል። • የሬሚዲያል ፕሮግራም በተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ በሁለት መስክ ተከፍሎ ከማዕከል በተዘጋጀ ይዘት መሰረት ዩኒቨርስቲዎች ተጨማሪ የሚያክሉትን በማካተት በተዘጋጀው መነሻ መሰረት ፕሮግራሙ እንዲከናወን ታቅዷል። • የሬሚዲያል ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ተማሪዎች ተከታታይ ምዘና እንዲኖራቸው ተደርጎ በየተቋማት የሚሰጠው ምዘና 30 % እና በማዕከል የሚዘጋጀው ፈተና 70% ተመዝነ በድምሩ አማካይና ከዚያ በላይ (50 ከመቶና በላይ) የሚያመጡት በመንግስት ተቋማት ሲከታተሉ የቆዩት በዚያው ተቋም መቀጠል የሚችሉ ሲሆን በራሳቸው ወጪ ሸፍነው ወደ ግል ተቋማት ሄደው መማር ቢፈልጉ መብታቸው የተጠበቀ ይሆናል። (ተጨማሪውን ከደብዳቤው ያንብቡ) @tikvahethiopia

photo content

" ተፈታኞች የቅሬታቸውን ምላሽ ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ አር
+1
" ተፈታኞች የቅሬታቸውን ምላሽ ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት እንደሚያበቃ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል። አገልግሎቱ ፤ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያው ቀን ነገ 11:30 እንደሚያበቃ አውቀው በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አለን የሚሉትን ቅሬታ እንዲያቀርቡ መልዕክት አስተላልፏል። በሌላ በኩል ፤ ቀድመው ቅሬታ ያቀረቡ ተፈታኞች የቅሬታቸውን መልስ www.neaea.gov.et:8081 ድረ ገጽ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን (Registration Number/ID) ብቻ በማስገባት ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ቅሬታዎች ሁሉም ተጣርተው ሲጠናቀቁ በቀጣይ ቀናት የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጾ የቅሬታ ምላሽ ያልደረሳቸው ተፈታኞች በትዕግስት እንዲትጠባበቁ አሳስቧል። በተጨማሪ ባልተሟላ ወይም በተሳሳተ ወይም በሌላ ሰው መለያ ቁጥር ያመለከቱ የስም ዝርዝራቸው ዛሬ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገጽ አድራሻ ላይ እንደሚያሳውቅ የገለፀው አገልግሎቱ ተፈታኞች ቅሬታቸውን በድጋሚ በተስተካከለ መለያ ቁጥራቸው ማመልከት እንደሚችሉ ገልጿል።

MoE ትምህርት ሚኒስቴር፤ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ50% በታች ያመጡና በዩቨርሲቱ የቅበላ አቅም " ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች " በዕጩነት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ነጥብ ከ10 እስከ 15 ቀናት ውስጥ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለፋና ብሮድካስት በሰጡት ቃለ ምልልስ ፤ " ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች " በዕጩነት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ነጥብ በጥቂት ቀናት ለማሳወቅ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፤ " 10 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይሄንን ለህዝቡ ይፋ እናደርጋለን።  በ10 ቀን ውስጥ የትኞቹ ተማሪዎች ዕጩ በመንግስት ተቋማት ሄደው እንደ ስኮላርሺፕ ተማሪ ዶርም ይዘው ምግብ ቀርቦላቸው በቅተው ለሚቀጥለው ዓመት ፌሬሽ ማን የመሆን ዕድል ይሰጣቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ በሌሎች አማራጮች ይማራሉ የሚለውን ጉዳይ ቢገፋ በ10 ቀን ውስጥ ማወቅ አለብን በጣም ቢገፋ በ15 ቀን ውስጥ ማወቅ አለብን " ብለዋል። " ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች " ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ተደርጎ ራሳቸውን የሚያበቃቸውን ትምህርት ተከታትለው በሚቀጥለው ዓመት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በመሆን ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ ነው የትምህርት ሚኒስቴር አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ የታወቀው።

የ866,000 ተማሪዎች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ? ትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች አማራጮች እንዳላቸው አሳውቋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት በሰጡት ቃል ፤ ለተማሪዎች የሚቀርበው አንዱ አማራጭ በመንግስት ውሳኔ በሚወሰን ነጥብ " ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪ " መሆን ነው ብለዋል። ዶ/ር ሳሙኤል፤ " አንድ ዕድል እንሞክርና የተወሰኑ ተማሪዎችን በመንግስት / በመንግስት ተቋማት ዩኒቨርሲቲ እንደገቡ ግን ገና ፍሬሽ ማን እንዳልሆኑ እንድቀበል፤ ሌለው ደግሞ በራሳቸው ከፍለው በግል ተቋማት እንደዚሁ remedial ተከታትለው ካሳኩ ወደ ፍሬሽ ማን የሚገቡበትን እድል እንፍጠርላቸው፤ ሊገቡ ይችሉ የነበሩ በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት 50% ያላሟሉትን እንዳናጣቸው እንደዜጋ እሱን እድል መፍጠር ጥሩ ነው፤ ይሄ ለአንድ ጊዜ የሚሆን የአንድ ጊዜ ውሳኔ ብቻ ሆኖ ማለት ነው። " ሲሉ ተናግረዋል። ትግበራውን በተመለከተም ተማሪዎች የፍሬሽ ማን ዕጩ ተማሪዎች እንደሚሆኑ ነው ያስረዱት። ከ50% በታች ያመጡ ተማሪዎች በግል በመፈተን ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችል ውጤት ማምጣት / በፍላጎት እና ምርጫ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መውሰድ መሆኑ ተመላክቷል። ፋና ቴሌቪዥን

"የተገኘው የፈተና ውጤት ከስርቆትና ከኩረጃ በፀዳ መልኩ በትክክል የተመዘገበ መሆኑን ያመላከተ ነው" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ  ------------------------------------------- ጥር 22/2025ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር)  የትምህርት ሚኒስትሩ  ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ2014ዓም የ12ኛ ክፍል ፈተና የተገኘው የፈተና ውጤት ከስርቆትና ከኩረጃ በፀዳ መልኩ በትክክል የተመዘገበ መሆኑን የሚያመላክት እንደሆነ ገልጸዋል። የዚህ አመት የፈተና ውጤት አንድምታም ለዓመታት ሲንከባለል የቆየ በርካታ ችግሮች መገለጫ እና ተሸፋፍኖ የቆየውን እውነተኛ የትምህርት ስርዓታችን ያለበትን ደረጃ  የሚያሳይ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሩ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የተሰጠው ፈተና ስርቆትን እና ኩረጃን ማስቀረት የተቻለበት እንደሆነ ገልፀው ውጤቱም የዚህ ማሳያ ነው ብለዋል። በተገኘው ውጤት መሰረትም ከ 50 በመቶ በታች ያመጣ ተማሪ ወደ ዩኒቨርስቲ እንደማይገባም ተናግረዋል። በ2014 ዓ.ም በተሰጠው ፈተና በሁለቱም የትምህርት መስክ ፈተናውን ከወሰዱት 896 ሺህ 520 ተማሪዎች ውስጥ 29 ሺህ 909 የሚሆኑት ተማሪዎች 50% እና ከዚያ በላይ ማስመዝገባቸው ተገልጿል። በመሆኑም  በቀጣይ እንደሀገር በትምህርቱ ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሁሉም አካላት ቅንጅት እንደሚፈልግ ገልጸዋል። የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን  አስመልክቶ መግለጫ  መስጠቱ ይታወሳል።

ሁሉንም የ 12ኛ ክፍል Entrance Exam በአንድ ላይ!

#New_updated ሁሉንም የ 12ኛ ክፍል Entrance Exam በአንድ ላይ!  ከ 2006-2014 /15. ሌሎች ጠቃሚ ትምህርታዊ መረጃዎችን የምንለቅበትን የ telegram channel ይቀላቀሉ 👇👇 @Ethio_Education_24 @Ethio_Education_24

MoE የትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ስነ ምግባር ስራ ክፍል የምርምር ስነ ምግባር ግምገማን የተቀላጠፈ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ ያስችላል ያለድን ድረ-ገፅ አዘጋጅቶ ወደ ስራ ማስገባቱን በዛሬው ዕለት አሳውቋቃ። ድረ-ገፁ ተመራማሪው ስራዎቹን ለማመልከት እንዲሁም ገምጋሚው ዶክመንቶቹን አይቶ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷታ። የሚሰሩ የምርምር ስነ ምግባር ስራዎችን በተመለከተ ተገልጋዮች ባሉበት ቦታ ሆነው “NRERB Research Ethics Review Portal በመጠቀም በኦላይን : http://nrerb.ethernet.edu.et ላይ አገልግሎቱን በቀላሉ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። ትምህርት ሚኒስቴር

+9
GRADE 7 PERFORMING AND VISUAL ARTS.pdf5.50 MB

ውጤት እንዴት ነበር? በ comment ግለፁልን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇