Ethiopia Andinet school🇪🇹
Open in Telegram
ይህ ቻናል በዓለም አቀፍ ደርጃ በተከስተው የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ተማሪዋች በወላጅ ድጋፍ ቤት ሆነው የተለያዩ ጥያቄዋችን እንዲሰሩ እና የት/ቤት መልዕክትን ለማስተላለፍ የተዘጋጅ የቴሌግራም ቻናል ነው
Show more402
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Data loading in progress...
Similar Channels
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
June '24
June '24
+10
in 0 channels
May '24
+18
in 0 channels
Get PRO
April '24
+28
in 0 channels
Get PRO
March '24
+20
in 1 channels
Get PRO
February '24
+23
in 0 channels
Get PRO
January '24
+28
in 0 channels
Get PRO
December '23
+384
in 0 channels
| Date | Subscriber Growth | Mentions | Channels | |
| 18 June | +1 | |||
| 17 June | 0 | |||
| 16 June | +1 | |||
| 15 June | 0 | |||
| 14 June | 0 | |||
| 13 June | 0 | |||
| 12 June | 0 | |||
| 11 June | +1 | |||
| 10 June | +1 | |||
| 09 June | +1 | |||
| 08 June | +3 | |||
| 07 June | +1 | |||
| 06 June | 0 | |||
| 05 June | 0 | |||
| 04 June | +1 | |||
| 03 June | 0 | |||
| 02 June | 0 | |||
| 01 June | 0 |
Channel Posts
Repost from Yeka Education
😍የ6ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና😍
✅አዘጋጅ 👉ልደታ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት
✅መንፈቀ አመት👉የመጀመሪያ መንፈቀ አመት
የትምህርት አይነት👉ሁሉም
✅አመት 👉2016
✅ክፍል 👉6ኛ
🥰Share
Our telegram channel
👇👇👇👇👇👇
💛💛💛💛💛💛
https://t.me/dam76
| 2 | ❓❓እንዴት እናጥና🤔❓❓❓
በእነዚህ ምክሮች መሠረት የማስታወስ ችሎታችሁንና የትኩረት አቅማችሁን ታዳብራላችሁ።
📌 1. ቁርስና ጠቃሚ ምግቦች
ሰውነታችን በአግባቡ ሥራውን እንዲሰራ ኃይል ያስፈልገዋል፤ አንጎላችን ደግሞ ትኩረት እንዲኖረውና የማስተዋል አቅማችን እንዲጨምር በቂ የሆነና ያልተቆራረጠ የኃይል አቅርቦት ይፈልጋል።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቁርሳቸውን ተመግበው ወደፈተና የሚገቡ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ። የተመጣጠነ ምግብ ተመግበው ለፈተና የሚቀርቡት ደግሞ የበለጠ የማስታወስና የማስተዋል አቅም ይኖራቸዋል።
ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ፈተና ያለባቸው ተማሪዎች እንደ የገብስ ገንፎ፣ ዳቦ፣ ሩዝና ድንች ያሉ በካርቦሃይድሬት የበለጸጉ ምግቦችን በቁርስ ሰዓት ተመግበው ቢወጡ ይመከራል።
እርጎ፣ እንቁላል፣ አሳ፣ ጎመን፣ ቲማቲምና አቮካዶ ዓይነት ምግቦችም እጅጉን ጠቃሚ ናቸው።
📌 2. በጠዋት ወደ ጥናት መግባት
ሁሌም ቢሆን ነገሮችን አስቀድሞ መጀመርን የመሰለ ነገር የለም። ለፈተናም ቢሆን ጥናት በጠዋት ተነስቶ መጀመር በፈተና ወቅት የተረጋጋ መንፈስ እንዲኖረን ይረዳል።
ጠዋት ላይ ጭንቅላታችን እረፍት አድርጎ በአዲስ መንፈስ ሁሉንም ነገር ስለሚጀምር፤ በዚህ ሰዓት ማጥናት ውጤታማ ያደርጋል። በተለይ ደግሞ የክለሳ ጥናቶችን ለከሰዓት ማሸጋገር ተገቢ አይደለም።
ጠዋት ጥናት የምንጀምርበትና የምናበቃበት ሰዓት ከፈተናው በፊት ባሉት ሁለት ወይም ሦስት ሳምንታት ውስጥ ተመሳሳይ ለማድረግ መሞከርም ውጤታማ ያደርጋል።
📌 3. ምን ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባችሁ ወስኑ
በመጀመሪያ ፈተናው የጽሁፍ ነው ወይስ የተግባር? ወይስ ቃለመጠይቅ ነው የሚለውን መለየት ወሳኝ ነው።
ሁሉም ዓይነት ፈተናዎች የራሳቸው የሆነ የተለያየ አይነት አቀራረብ አላቸው። በምሳሌ አስደግፎ ማብራሪያ መስጠት የሚጠይቅ ዓይነት ፈተና ከሆነ ከዚህ በፊት የተሠሩ ፈተናዎችን እያመሳከሩ ጥቂት ቦታዎች ላይ በትኩረት መዘጋጀት።
ምናልባት ፈተናው ምርጫ አልያም አጭር መልስ የሚፈልግ ዓይነት ከሆነ ቀለል ያለና አጠቃላይ መረጃዎችን ለመያዝ መሞከር።
📌 4. እቅድ ማዘጋጀት
ምናልባት ነገሮችን ቦታ ቦታ ለማስያዝና እቅድ ለማውጣት የምናጠፋው ጊዜ የባከነ መስሎ ሊሰማን ይችላል። ነገር ግን እውነታው በተቃራኒው ነው። ምክንያቱም ምን ማጥናት እንዳለባችሁና መቼ ማጥናት እንዳለባችሁ እቅዳችሁ ይነግራችኋል።
ከዚህ በተጨማሪም ምን ያክል እንደተጓዛችሁ ለመመዝገብና ለመከታተል ይረዳል።
የትኞቹን ማስታወሻ ደብተሮች መቼ መመልከት እንዳለባችሁ፣ የትኞቹን መጻህፍት ለተጨማሪ ማብራሪያ እንደምትጠቀሙ እንዲሁም የፈተና ጥያቄዎችን መቼ መለማመድ እንዳለባችሁ በእቅድ ውስጥ ማስገባት ውጤታማ ያደርጋል።
እዚህ ጋር መርሳት የሌለብን ለእረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴም ቦታ መስጠት እንዳለብን ነው።
📌 5. ከፋፍሎ ማጥናት
የክለሳ ጥናትን ከፋፍሎ ማካሄድን የመሰለ ነገር የለም። አንድ የትምህርት ዓይነት ላይ 10 ሰዓት ሙሉ ከማሳለፍ በየቀኑ አንድ ሰዓት በማጥናት በ10 ቀን መጨረስ ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋል።
ያጠናነውን ነገር ለማስታወስና በቀላሉ ለመሸምደድ ጭንቅላታችን ጊዜ ይፈልጋል። ከፋፍሎ ማጥናት ደግሞ ለዚህ ፍቱን መድሃኒት ነው። ከፋፍሎ ማጥናት እጅግ ውጤታማው መንገድ እንደሆነም በመላው ዓለም የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶች ያለመክታሉ።
📌 6. ራሳችሁን ቶሎ ቶሎ ፈትኑ
የሥነ አዕምሮ ጥናት ባለሙያዎች እንደሚሉት የማስታወስ ችሎታን ለማዳበርና በራስ መተማመናችንን ለመጨመር ራስን መፈተን ውጤታማ ያደርጋል።
ከዚህ በተጨማሪ እየተዘጋጀንበት ያለነውን ጉዳይ በደንብ እንድናውቀው ከማድረጉ በተጨማሪ የረሳናቸው
የረሳናቸው አልያም የዘለልናቸው ርዕሶችን ለመለየት ይረዳናል።
📌 7. መምህር መሆን
ከባዱን የክለሳና ራሳችሁን የመፈተን ሥራውን ካከናወናችሁ በኋላ ጓደኞቻችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ በጭንቅላታችሁ የሚመጣውን ነገር በሙሉ ንገሯቸው። ራሳችሁን በመምህር ቦታ አድርጋችሁ እውቀታችሁን ለማካፈል ሞክሩ።
ምን ያህል እንደምታስታውሱ ለማወቅ ከመርዳቱ በተጨማሪ ጓደኞቻችሁንም ትጠቅሟቸዋላችሁ።
📌 8. ከተንቀሳቃሽ ስልካችሁ ራቅ በሉ
ስልኮች በጣም ብዙ ጥቅም አላቸው። ነገር ግን በጥናት ወቅት ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ነው የሚያመዝነው። በተለይ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያዎችን የምትጠቀሙ ከሆነ።
ብዙ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ብዙ ጊዜያቸውን ስልካቸው ላይ የሚያሳልፉ ተማሪዎች የትምህርት ውጤታቸው ሁሌም ቢሆን ዝቅ ያለ ነው።
ብትችሉ ስልካችሁን አጠገባችሁ እንኳን አታድርጉት።
📌 9. ሙዚቃ መቀነስና በጸጥታ ማንበብ
በጸጥታ ውስጥ ሆነው ጥናታቸውን የሚያከናወኑ ተማሪዎች ሙዚቃ እየሰሙ ከሚያጠኑት ጋር ሲወዳደሩ በእጅጉ የተሻለ የማስታወስና የትኩረት አቅም እንዳለቸው ማረጋገጥ ተችሏል።
📌 10. ቋሚ እረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴ
ውጤታማ የክለሳ ጥናት ማለት እረፍት አልባ ጥናት ማለት አይደለም። በጥናታችን መሀል መሀል ላይ ጥሩ አየር ለማግኘትና ሰውነታችንን ለማፍታታት ወጣ ብሎ እንቅስቃሴ ማድረግ የማስታወስ ችሎታችንን በደንብ ከፍ ያደርገዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሰውነታችን እና ጭንቅላታችን በእጅጉ የተሳሰሩ በመሆናቸው እንቅስቃሴ ስናደርግ የደም ዝውውራችን ይስተካከላል፤ ይህ ደግሞ በቂ ኦክስጅን ወደ ጭንቅላታችን እንዲሄድ ይረዳል።
አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ተዘርዝሮ የማያልቅ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ጭንቀትን መከላከልና በራስ መተማመንን መጨመር ከነዚህ መካከል ይጠቀሳሉ።
📌 11. እንቅልፍ
ከፈተና በፊት ያለችውን ምሽት ጥሩ እንቅልፍ አግኝቶ ማሳለፍ ተገቢ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ነገር ግን ጥሩ እንቅልፍ ፈተናው ሲቃረብ ብቻ ሳይሆን ከሳምንታት በፊት ገና ዋናው ጥናት ሲደረግና ክለሳ በሚደረግበት ወቅትም እጅግ ወሳኝ ነው።
✅በጠዋት ተነስቶ ውጤታማ የክለሳ ጥናት ካደረጉ በኋላ በጊዜ ተኝቶ ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት ሰውነታችንና ጭንቅላታችን በደንብ ተግባብተው እንዲሰሩ ይረዳቸዋል። ሌሊቱን በሙሉ ለማጥናት ሙከራ አታድርጉ ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች። ምክንያቱም ራሳችን ላይ ጫና እያሳደርን ስለሆነ።
👍እስካሁን የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ተግባራዊ ካደረጋችሁ ምንም የሚያሳስባችሁ ነገር ሊኖር አይገባም።
መልካም ፈተና! | 0 |
| 3 | ለተማሪዎች ጠቃሚ የጥናት ምክሮች
1. የክፍለ ጊዜ ማስታወሻ መጠቀም
ሁሉንም የክፍል ክፍለ ጊዜዎች መገኘት፣ ንግግሮቹ በትኩረት መከታተል፣ እና ትርጉም በሚሰጥ መንገድ ማስታወሻ መያዝ ጠቃሚ
2. ከክፍል ጓደኞች ጋር ማጥናት
ጓደኞችን ከማፍራት በተጨማሪ፣ በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥ የጥናት ቡድኖችን መፍጠር አብሮ መስራት ጥሩ የጥናት ልምዶችን ለማዳበር ይረዳል, በቡድን ፕሮጀክቶች ላይ ትብብርን ይጨምራል እና በራስ መተማመንን ይጨምራል. "አብረህ መስራት፣አብረህ ማጥናት፣መረዳዳት እና የተሻለ ለመሆን መገፋፋት ትችላለህ"
3. መምህራችን ነፃ የሚሆንበትን ሰዓቶች መጠቀም
በአንድ ጽንሰ-ሀሳብ ወይም ርዕስ ላይ ችግር ካጋጠመዎት መምህርዎ ሊረዱዎት ይችላሉ። የክፍል ትምህርቱን በተሻለ ለመረዳት፣ ለፈተናዎችዎ እንዴት መዘጋጀት እንደሚችሉ አጋዥ ምክሮችን ለማግኘት መምህዎ ነፃ ሲሆን መወያየት ።
4.ለጥናት ጥሩ ቦታ መምረጥ
አንዳንድ ሰዎች የቤተ መፃህፍት መቼት ሙሉ ዝምታ ይወዳሉ፣ ሌሎች ደግሞ ስራ የበዛበትና ማነቃቂያ ይወዳሉ። አንዳንድ ተማሪዎች በጠረጴዛቸው ላይ መሥራትን ይመርጣሉ፣ ሌሎች ደግሞ ፀሐያማ የሆነ የውጪ ቦታ የበለጠ ምቹ ሆነው ሊያገኙ ይችላሉ።
5. ያንብቡ እና ይከልሱ
የተማርነውን 70% በ24 ሰዓታት ውስጥ እንረሳለን። ከክፍል አንድ ቀን በኋላ አዳዲስ ሀሳቦችን ማየቱ ማቆየት እና ግንዛቤን ለመጨመር ይረዳል - ስለዚህ በእያንዳንዱ ምሽት ፈጣን ግምገማ ጊዜ ይውሰዱ። ከመቀጠልዎ በፊት ምዕራፎችን ወደ ክፍሎች ይከፋፍሏቸው እና በእያንዳንዱ መጨረሻ ላይ ያለውን ጽሑፍ ይከልሱ። ሙሉ ምዕራፎችን እንደገና ማንበብ ሳያስፈልግ በቀላሉ መገምገም እንዲቻል የንባቡን ወሳኝ ገጽታዎች በማጠቃለል ማስታወሻ መያዝ።
6. እቅድ ይጠቀሙ
የክፍል እና የቤት ስራዎችን፣ ፕሮጀክቶችን እና ሌሎችንም ፕሮግራም ማስያዝ፣ ተደራጅቶ ለመቆየት ወሳኝ ነው። ማንኛውንም አስፈላጊ ነገር እንዳይረሱ የጊዜ ገደቦችን፣ ቀኖችን እና ሰአቶችን ለመከታተል እቅድ ይጠቀሙ።
7. ቁሳቁሱን በዓይነ ሕሊናህ ተመልከት
ትምህርቱን በማጣመር እና ቁልፍ ቃላትን እና ፅንሰ-ሀሳቦችን በማስመር ወይም በማድመቅ በክፍል ማስታወሻዎችዎ በጣም አስፈላጊ ክፍሎች ላይ ያተኩሩ። የተወሳሰቡ ፅንሰ-ሀሳቦችን እንዲረዱ የሚያግዙ ምስሎችን ለመፍጠር ወደ ስዕላዊ መግለጫዎች፣ የአእምሮ ካርታዎች ወይም ዝርዝር መግለጫዎች እንደገና ለመቅረጽ ይሞክሩ።
8. ጎበዝ ተማሪዎች እንዲያስረዱህ አድርግ
በተለይም በአንድ ርዕስ ላይ ልዩ ችሎታ ያላቸው ወይም የላቀ ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች እንዲያስረዱህ ጠይቅ። እንድሁም በተለያዩ ድህረ ገፆች የሚያስተምሩ መምህራን ለመረዳት ጣር።
9. በመረዳት ላይ ያተኩሩ
ማስታወስ ማለት እውነታዎችን ለማስታወስ እና ለመድገም መንገዶችን መፈለግ ማለት ነው። መረዳት ትንሽ ጠለቅ ያለ ነው እና አዲስ እውቀትን በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ምን ያህል በጥሩ ሁኔታ መተግበር እንደሚችሉ እና ከሌሎች ፅንሰ-ሀሳቦች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ማወቅን ያመለክታል። የማጠቃለያ ፈተናዎች ብዙውን ጊዜ ማስተዋልን ይፈትኑታል እንጂ ማስታወስን ብቻ አይፈትኑም።
10. በክለሳ ክፍለ ጊዜ መገኘት
በፈተናው ቅርጸት እና በጥያቄዎች ውስጥ ምን ሊካተቱ እንደሚችሉ እንዲሁም በጥናትዎ ወቅት ትኩረት ሊሰጡባቸው የሚገቡ ቁልፍ ርዕሶች ላይ ጠቃሚ መረጃ የሚማሩበት በዚህ ነው።
11. እረፍት ይውሰዱ
አንጎልዎ እና ሰውነትዎ እንዲያድሱ እድል ይስጡት። እንደ ፎርብስ ዘገባ፣ የ25 ደቂቃ የረጅም ጊዜ የጥናት ክፍለ ጊዜዎችን ከአምስት እስከ 10 ደቂቃ ዕረፍት ይውሰዱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወደ አንጎል የደም ፍሰትን ይጨምራል ይህም የበለጠ ጉልበት እና የተሻለ ግንዛቤ ይሰጥዎታል.
12. እራስዎን በደንብ ይንከባከቡ
ጊዜን ለመቆጠብ አላስፈላጊ ምግቦችን መሙላት በጣም ብልጥ ስልት አይደለም. በምትኩ፣ እንደ ትኩስ ፍራፍሬ እና አትክልት ያሉ “የአንጎል ምግቦችን”፣ ከፕሮቲን እና ጤናማ ስብ ጋር ሚዛናዊ በሆነ መልኩ አእምሮዎን ለማቀጣጠል ያቆዩ። ለእንቅልፍም ተመሳሳይ ነው: ከፈተናው በፊት ባለው ምሽት ሳይበዛ እረፍት ለማግኘት እቅድ ያውጡ.
13. እራስዎን ያረጋጉ
በመጨረሻው ሳምንት በሁሉም የፈተና መሰናዶዎ ውስጥ መጨናነቅ ወደ ጭንቀት ሊመራ ይችላል። ትምህርቱን ወደ ርእሶች ይከፋፍሉት እና መረጃን ሙሉ በሙሉ ወደ እውነተኛ ግንዛቤ ለመውሰድ ከፈተናው በፊት ለመመልከት ጥቂት ቁልፍ ሀሳቦችን በማስታወሻ ለይ ይፃፉ ።
14. የፈተነውን ቅርፀት ማወቅ
የተለያዩ ሙከራዋች፣ ሞደል ፈተናዎች የተለያዩ አካሄዶችን ይፈልጋሉ። ብዙ ምርጫ ማለት በትርጉሞች እና ጽንሰ-ሐሳቦች ላይ ማተኮር ማለት ነው. የፅሁፍ ሙከራዎች ስለ ቁሳቁሱ ፅንሰ-ሃሳባዊ ግንዛቤ እንዲያሳዩ ይፈልጋሉ። ስለዚህ ፈተናው እንዴት እንደሚዘጋጁ እንዲያውቁ የፈተናውን ቅርጸት መምህሩን ይጠይቁ።
15. ሌሎችን በማስተማር ተማር
ለክፍል ጓደኛዎ ፅንሰ-ሀሳቦችን ማስረዳት ትምህርቱን እራስዎ በትክክል መረዳትዎን ለማረጋገጥ እና እንዲማሩ ለመርዳት ጥሩ መንገድ ነው። ፅንሰ-ሀሳብን ለማብራራት አዳዲስ መንገዶችን ሲያገኙ፣ መረጃውን ለሌሎች በማቀናበር እየተካኑ ነው።
16. ቃላት መፍጠር
የኮርስዎን ይዘት ወደ አጭር ክፍሎች መከፋፈል እና ምህፃረ ቃላትን ፣ ሀረጎችን ፣ ግጥሞችን ወይም ዘይቤዎችን መፍጠር ጠቃሚ እና አስደሳች - ጽንሰ-ሀሳቦችን ለማስታወስ የምንጠቀምበት ሌላኛው ዘዴ ነው።
17. እውቀትዎን ይፈትሹ
ቅርጸቱን አንዴ ካወቁ፣ ፈተናው ሊሸፍን ይችላል ብለው ባሰቡት መሰረት የልምምድ ፈተና ለመፍጠር ይሞክሩ። ይህ ትምህርቱን በጥልቅ ደረጃ እንዲረዱ እና ግልጽ የመማሪያ ዓላማዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳዎታል። ከዚያ እራስዎን እና የጥናት ቡድንዎን ለመጠየቅ የተግባር ፈተናዎን መጠቀም ይችላሉ። በዚህም ለራስ ፈተና በማዘጋጀት መለማመድ
18. ትምህርት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ከሚያሳድሩ ተማሪዎች እራስን መለየት
ይህም አንዳንድ ተማሪዎች በትምህርታችን ውጤታማ እንዳንሆን በወሬ፣ ዝለን፣ ድብድብ፣ ጫዋታ፣ ልፊያ፣ ፌዝ፣ እና ቀልድ በጥቅሉ ለትምህርት ትኩረት ከማይሰጡ እራሳቸውን ከመቀየር ይልቅ ሌሎችም እንደነሱ እድሆኑ ከሚጥሩ ተማሪዎች ጋር አብረህ እየዘለልክ ጊዜህን ከማጥፋት ተቆጠብ።
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library | 0 |
| 4 | +5 የ8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና
✅አዘጋጅ 👉አራዳ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት
✅መንፈቀ አመት👉የመጀመሪያ መንፈቀ አመት
✅አመት 👉2016
✅ክፍል 👉8ኛ
➡️🤲ለሌሎች ማጋራት አንርሳ🤲🤲
የሌሎች ክፍለ ከተማ ይቀጥላል!!
Our telegram channel
👇👇👇👇👇👇👇
💚💚💚💚💚💚💚
💚💚💚💚💚💚💚
https://t.me/dam76 | 0 |
| 5 | Arada subcity Grade 8 model exam 2016 | 0 |
| 6 | ✅አዲስ የወረደ የትምህርት ካላንደር የለም!❌
✅ክረምት ላይ በተላከው 1 ገጽ(ከላይ ተያይዟል) የትምህርት ካላንደር መሰረት የትምህርት ስራዎች ይቀጥላሉ!! | 0 |
| 7 | ማስታወቂያ ለተማሪ ወላጆች በሙሉ
በ26/04/2016 ዓ.ም ከአጠቃላይ ከመምህራን ጋር የ6ወር ውይይት ስለምናደርግ ትምህርት እስከ 6:30 ብቻ መሆኑን እየገለጽን ወላጆች ልጆች ምሳ ከተመገቡ በኃላ 7:00 ሰዓት ላይ ልጆቻችሁን እንደትወስዱ ት/ቤቱ ያሳውቃል። | 0 |
| 8 | ተማሪ ቢኒያም ሀይለማርያም በክፍለ ከተማ ደረጃ በነገው እለት በኮከበ ጽብሀ ት/ቤት ወረዳውን በመወከል ከ12ቱ ወረዳ ከተወጣጡ የ8ኛ ክፍል ተፎካካሪዎቹ ጋር የጥያቄና መልስ ውድድር ያደርጋል ት/ቤቱም መልካም ውጤትን ይመኛል። | 0 |
| 9 | ከ6ኛ ክፍል እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ጋር በስነ-ምግባር እና በመማር ማስተማር ዙሪያ በ17 እና 18/04/2016 ዓ.ም ገንቢ ውይይት አድርገናል። | 0 |
| 10 | ቴሌግራም ለማይጠቀሙም ጓደኞቻችሁ ሼር አድርጓቸው። የሞዴል ፈተናው ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል በመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት ከተማሩት ብቻ ነው። | 0 |
| 11 | ✅የጥያቄና መልስ ውድድርን በተመለከተ
👉በክፍለ ከተማ ደረጃ የ6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር በ26/4/2016 ይካሄዳል::በመሆኑም የሁለተኛ ደረጃ እና በወረዳ ደረጃ የሚካሄዱ ውድድሮች እስከ 25/4/2016 መጠናቀቅ ይኖርባቸዋል::
✅የሞዴል ፈተና የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተ
👉የ2016 ዓ.ም የ6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል የሞዴል ፈተና በከተማ ደረጃ ከጥር 1-3/5/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል::
✅የሞዴል ፈተና የሚሸፍነውን በተመለከተ
👉የ6ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ከ6ኛ ክፍል የመጀመሪያ ሴሚስተር ብቻ ይሸፍናል
👉የ8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ከ8ኛ ክፍል የመጀመሪያ ሴሚስተር ብቻ ይሸፍናል
👉የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ከ9ኛ-11ኛ በነባሩ/በቀድሞው ስርዓተ ትምህርት እና የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርአተ ትምህርት የመጀመሪያ ወሰነ ት/ት የሚሸፍን ይሆናል::
📙በመሆኑም ይህንን መረጃ መሰረት በማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እና ለተማሪዎችን በቂ መረጃ መስጠት ከሁላችንም ይጠበቃል!!
የየካ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት | 0 |
| 12 | ✅የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ፕሮግራም
✅የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ፕሮግራም
✅የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ፕሮግራም | 0 |
| 13 | No text... | 0 |
| 14 | No text... | 0 |
| 15 | ይፋ ያልተደረገ ነው ማለቴ በደብዳቤ ፎርማል በሆነ በሆነ መንገድ አልተላከም ግን በዚህ ግዜ ነው | 0 |
| 16 | በተማሪ 1ኛ. ኢትዮጵያ አንድነት 2.ብርሃን ጉዞ 3.ልእልት ዘነበወርቅ ። እጅግ በጣም ደስ የሚል ተፎካካሪዎች በመለያ የተሸናነፉ ናቸው። | 0 |
| 17 | የተወዳዳሪ ተማሪ ምርጫ ላይ ለወደፊት ከሚደረጉ ተከታታይነት ያላቸው የጥያቄና መልስ ውድድር በተገቢ መንገድ የተፈተሹ ተማሪዎችን መምረጥ እንዳለብን አስተምሮን ያለፈ ውጤት ነው። | 0 |
| 18 | በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልእልት ዘነበወርቅ ጉድኝት ማእከል በሁ ለቱም ስርአተ ትምህርት በ8ኛ ክፍል በተደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር በተቋም ደረጃ 1ኛ ብርሃንጉዞ 2ኛ.ልእልትዘነበወርቅ 3ኛ.ንጋት ኮከብ 1ኛደረጃ ትምህርትቤት በመሆን ደስ በሚል ፉክክር ተጠናቋል። | 0 |
| 19 | በ8ኛ ክፍል በመጀመሪያ ዙር በተደረገው የጥያቄና መልስ ውድድር የተጠየቁትን ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ በመመለስ ተማሪ ቢኒያም ሀ/ማርያም በግል 1ኛ በመውጣት በግል አሸናፊ ሆኗል። እኛም ይህንን ጀግና ተማሪ እንኳን ደስ አለክ እንላለን። | 0 |
| 20 | +7 Grade 1 Books ። New Curriculum.apk | 0 |
