cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

SHEMA📖✝

ማርቆስ 12 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ❝²⁹ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ( #Shema o Israel) ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥ ³⁰ አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።❞ #we #proclaim #the #sweet #life #with #God.

Show more
Advertising posts
308Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በጥሞና አድምጡት🎧 🗣ገጣሚ ሕሊና ደሳለኝ ትሁቱ እረኛዬ፣ታጋሹ እረኛዬ ደግ ልብህ ሲያርም የግልገሉን ክፋት በአንዲት እንባ ያጥባል የዘላለም ጥፋት የትናንቱ ብኩን ፣የትናንቱ ትቢያ የቸርነትህ በትር አንግሦ ያጀገነኝ የፍቅርህ ምስክር የምህረትህ ቋንቋ #ደቀ_መዝሙርህ_ነኝ!! °°°°°•♥•°°°°° መልካም ሰንበት ⚜Shabbat Shalom⚜ @Dawitdeva7
Show all...
Repost from SHEMA📖✝
#ምልክት_ያለው_ይድናል “ደሙም ባላችሁበት ቤቶች #ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብፅን አገር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም።” — ዘጸአት 12፥13 ምልክት አለብኝ የእየሱስ ደም 🙌🙌🙌😍😍😍 @Dawitdeva7
Show all...
¯¯¯#ምሥጢር_እነግራችኃለሁ/ I shew you a Myestry/ 💎👇💎 1ኛ ቆሮንቶስ 15 ⁵¹-⁵² #እነሆ፥ #አንድ #ምሥጢር_እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት #በቅጽበተ_ዓይን #እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን። ⁵³ ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና። … ⁵⁸ ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ። @Dawitdeva7
Show all...
" #My_heart_is_yours " Amazing passion song 😍😍😍 Yes Jesus, my heart is yours, take it all🙌🙌 “My beloved is mine, and #I_am_his: he feedeth among the lilies.” — Songs of Solomon 2:16 (KJV) @Dawitdeva7
Show all...
💎👇 "Faith never knows where it is being led, but it loves and knows the One who is leading it. " 👤Oswald Chambers Can you say this to your Lord and saviour Jesus; 👇 " I love the way you hold me, Led me all the time and I will follow, Surrendering all🧎" Amenn 🙌 Have a blessed day! @Dawitdeva7
Show all...
የሕይወት ሥነ ሥርዓት (Discipline of life) 💎💎👇💎💎 5- ሥራህን ተግተህ ሥራ ☑ሥራ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ ነው ። ሥራ ርግማን ሳይሆን በረከት ነው ። አዳም ሲፈጠር ገነትን እንዲያበጃትና እንዲንከባከባትም ነው (ዘፍ. 2 ፡ 15) ። ደግሞም ምድርን ግዛ ተብሎ ሥልጣን ሲሰጠው ትልቅ ሥራ እንደ ተሰጠው ያሳያል ። ምድር ለእርሱ ስጦታው ናትና እንደ ራሱ ገንዘብ አድርጎ መንከባከብ ይገባዋል ። ከበደል በኋላ ግን “በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ” ተባለ (ዘፍ. 3 ፡ 19) ። ይህ ሥራ ርግማን መሆኑን የሚያሳይ ሳይሆን ከበደል በኋላ አዳም ብዙ ልፋት ጥቂት ትርፍ ይገጥመዋል ማለት ነው ። በዚህም ምክንያት እርካታ እያጣ እንደሚመጣ የሚገልጥ ነው ። እያንዳንዱ ሰው ለሚኖርበት ዓለም የሚያደርገው አስተዋጽኦ አለው ። ሰው የሁለት ዓለም ፍጡር ነውና ለምድር ኑሮው መሥራት ፣ ለሰማዩ ኑሮ ማመን አለበት ። ሥራ በረከት ነው ። 📌በአእምሮ ላይ የሚነሣውን የሰይጣንን ፈተና ለማሸነፍ ሥራና ጸሎት ሁለቱ መሣሪያ መሆናቸውን አባቶች ተናግረዋል ። ሥራ የፈታ አእምሮ ለሰይጣን መናገሻ ከተማ ነው ። ነገረኛ ሰዎች ሥራ የማይሠሩ ወይም አጉል ትርፍ የሚያገኙ ወገኖች ናቸው ። በሥራ የተጠመደ ነገርን ይሸሻል ። ንጹሕ አእምሮ ለማግኘት ሥራ መሥራት መልካም ነው ። ተነፋፍቆ ለመገናኘት ሥራ አስፈላጊ ነው ። የሰው ልጆች ያለማቋረጥ ከተያዩ ግንኙነቱ ይደፈርሳል ። በዓለም ላይ በተነሣው የቅርቡ ወረርሽኝ ሰው ሁሉ እቤቱ እስረኛ ሁኖ ነበር ። ብዙ ትዳር ፈርሷል ። ብዙ ግንኙነት ተበላሽቷል ። ወንጀሎች ተፈጽመዋል ። ሰዎች ለአእምሮ ጭንቀት ተዳርገዋል ። እስካሁን ድረስም ጠባሳው እያወከ ይገኛል ። ሥራ በረከት ነው ። አሁንም በቤታቸው ተቀምጠው የሚሠሩ ሰዎችን በተለያየ ዓለም እንሰማለን ። የሰይጣን ትልቁ ውጊያው ሰውና ሰው እንዳይገናኝ ማድረግ ነው ። ሥራ ያገናኛል ። ሥራ ከቤታችን ውጭ ሲሆን ለብሰን እንወጣለን ። ለራሳችን እንክብካቤ እናደርጋለን ። ከሰዎች ጋር በማውራት ብቻ ነጻ አእምሮ እናገኛለን ። አአምሮአችን ትልቅ ኃይል የተሸከመ ነውና ማረፊያ ያገኛል ። ማረፊያ ያላገኘ አእምሮ ዓለምን ለማጥፋት አቅም አለው ። 📌ሥራው አለቃ የሆነለት ሰው ውጤታማ ነው ። ሥራ ብዙ እንቅልፍን የሚጠላ በመሆኑ ሠራተኛ ሰው ማልዶ መነሣት አለበት ። ሥራ አካላዊ ፣ ሥነ ልቡናዊና መንፈሳዊ በረከትን ይሰጣል ። አካላችን የሚጠነክረው በሥራ ነው ። የምድር ተግዳሮትን የሚቋቋሙ ሰዎች ሠራተኛ ሰዎች ናቸው ። የዓለም መንግሥታት ትልቅ ስኬታቸውን የሚለኩት የሥራ ዕድልን በመፍጠራቸው ነው ። በአጭር ቋንቋ እግዚአብሔር ሰነፍ ልጅ የለውምና ሥራን መውደድ ይገባናል ። የሐዋርያው ቃልም ቁርጥ ያለ ነው፡- “ሊሠራ የማይወድ አይብላ ።” (2ተሰ. 3 ፡ 10) ። ስብሰባ ፣ ኮሚቴ ፣ ቃለ ጉባዔ የሚሉ ሰዎች አብዛኛዎቹ ሥራ የማይወዱ ፣ ቁጭ ብለው መነዛነዝ የሚያፈቅሩ ናቸው ። ሕይወትን ቀለል አድርጎ መኖር የሚቻለው በስብሰባ ሳይሆን በሥራ ነው ። ጨካኝ መንግሥታት ሕዝባቸውን በስብሰባ ያደነዝዛሉ ። መሪ የሆኑት ደግሞ ሕዝባቸውን ለሥራ ያነሣሣሉ ። ሕዝብን በሥራ መወጠር ከሁከትም ይጋርዳል ። 📌አዎ ሥራህን በታማኝነት ሥራ ። ጸልየህ ያገኘኸውን ሥራ በትጋት አለመሥራት እግዚአብሔርን ማሳዘን ነው ። ሥራ ታማኝነትና ትጋት ይፈልጋል ። ታማኝነቱ ትጋት ከሌለው ፣ ትጋቱ ታማኝነት ከሌለው አደገኛ ነው ። ሥራህ የሃይማኖትህ ቦታ አይደለም ። በሥራህ ቦታ ሥነ ምግባርን እንጂ አምልኮን ልፈጽም አትበል ። ጉቦን ተጸየፍ ። ደመወዝህ እንዲባረክ ጸልይ ። ጉቦ ያለህንም ይዞት የሚሄድ ፣ ልጆችህንም የሚያሳብድ ነው ። ጉበኞች የብዙዎችን እንባና ደም ተሸክመው ይሄዳሉ ። ሰው ወዶና ፈቅዶ እንጂ ተጨንቆ የሚሰጠን ነገር ርግማን የሚያመጣ ነው ። የሥራ ሰዓትህን አክብር ። ደመወዝህ አነስተኛ በመሆኑ ባለጉዳዩን ማንገላታት አይገባህም ። ባለጉዳይህን ፣ ያንተን ሙያ የሚፈልገውን እግዚአብሔርን እንደምታገለግል አድርገህ አገልግለው ። የሙያህ ባለቤት እግዚአብሔር ነው ። በሙያህ ሰውን አታጉላላ ። አንድ ቀን ይህ አእምሮህ ላይሠራ ይችላል ። እጆችህ ላይሠሩ ይችላሉ ። በሚያልፈው አካልህ የማያልፍ ሥራ ሥራበት ። በሙያ ሰውን ማስደሰት መታደል ነው ። ካንተ የሆነ ምንም ነገር የለም ። 📌ሥራ የምትሠራው አሥራትህንም ለማውጣት ነው ። ባንተ የሥራ ትርፍ የእግዚአብሔር ቤት ይገነባል ። ብዙዎች ወንጌል ይሰማሉ ። ልጆችህ ጠግበው ያድራሉ ። ትዳርህ አይታወክም ። የብዙ ትዳር ሁከትም የገቢ ማነስ ነው ። ሥራ ትልቅና ትንሽ የለውም ። በምድር ላይ የሚያሳፍረው ቆሻሻ መጥረግ ሳይሆን ቆሻሻ ጠባይ መያዝ ነው ። ጌታችን ለእኛ አርአያ ለመሆን አናጢነትን ሠርቷል ። ቅዱሳን ሁሉ ሥራቸውን በትጋት ሲሠሩ ለሰማያዊ ግዳጅ የተጠሩ ናቸው ። ትጉ ሠራተኛ ትጉህ ሐዋርያ ሊሆን ይጠራል ። ትጋት ተወዳጅ ያደርጋል ። ለክብር ለመታጨት ያበቃል ። እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ ይባርክ ! ይቀጥላል ✍ዲያቆን አሸናፊ መኰንን @Dawitdeva7
Show all...
A blessing Worship🔥 “ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም።” — ዕብራውያን 10፥38 Happy Sabath ⚜ Shabat Shalom⚜ @Dawitdeva7
Show all...
#ለትልቅ_ምክንያት_መኖር (Live for the greater cause) “አልሞትም #በሕይወት_እኖራለሁ እንጂ፥ #የእግዚአብሔርንም_ሥራ #እናገራለሁ።” — መዝሙር 118፥17 📌የመኖር ምክንያታችን ስላልሞትን ወይንም እስትንፉሳችን መቀጠሉ ብቻ ከሆነ ቆም ብለን ማሰብ አለብን። 📌 ዳዊት 'አልሞትም ' ያለው ሞትን ስለሚፈራ ወይንም መኖርን ስለሚወድ ሳይሆን ሊኖርለት የተገባ አንድ #ትልቅ_ምክንያት ስላለ ነው ።እርሱም " #የእግዚያብሄርን_ስራ_መናገር " ብሎ በህይወቱ ያወጀው ዓላማው ነው። 📌ለትልቅ ምክንያት የሚኖርን ሰው ጥቂቱ ና ጊዜያዊ መከራ አያስቆመውም። ህይወቱም በትናንሽ አስተሳሰቦች አይያዝም። 📌 የማይገባውን ምህረት፣ፀጋ እና ፍቅር እንደተቀበለ የተረዳ ሰው በህይወት ሳለ ማድረግ የሚገባውን ከማድረግ ወደ ኃላ አይልም። ሁለንተናውን ለሰጠን ጌታ ምናችንን እንከለክለዋለን?? 2ኛ ቆሮ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹³ እብዶች ብንሆን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን፥ ለእናንተ ነው። ¹⁴ ይህን ስለቆረጥን #የክርስቶስ #ፍቅር_ግድ_ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፤ ¹⁵ #በሕይወትም_ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት #ለራሳቸው_እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። ፀጋ ከሁላችን ጋር ይሁንን🙌🙌 ❤️❤️❤️ 🌤🌤 መልካም ሠንበት🌤🌤 ( Shabat shalom ) @Dawitdeva7
Show all...
Wise Counsel of Paul 💎 👇👇👇👇 “ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና #የምትደላደሉ፥ #የማትነቃነቁም፥ #የጌታም_ሥራ_ሁልጊዜ_የሚበዛላችሁ_ሁኑ።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥58 ሰማያዊው ህይወት የገባው ሰው፦ ☑የተደላደለ ነው፤ ምንም ነገር አያስደንቀውም ከጌታው ክብር ውጪ ☑የማይነቃነቅ ነው ፤በምንም አይነት የህይወት ወጀብ ውስጥ ☑የጌታ ስራ ሁሌ የበዛለት ታታሪ ነው፤ ብድራቱን ትኩር ብሎ ይመለከታልና። ፀጋ ይብዛልን!🙌 @Dawitdeva7
Show all...
ጋሽ ገዛኽኝ ሙሴ🎧 ሁሉም እንደዘበት ሊጠፋ ሁሉም እንደዘበት ሊያልፍ ነው በጌታ በእየሱስ የፀና ፅዩን ሊገባ ነው ሊያርፍ ነው!🔥 ••••♥•••• “ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ።” — ሉቃስ 21፥28 @Dawitdeva7
Show all...