cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኢትዮ_ቅምሻ💚💛❤️

አስተዋይ ሰው ማለት መቼ መናገር እንዴት መናገር ለምን መናገር የት ምን መናገር እንዳለበት የሚያውቅ ነው።

Show more
Advertising posts
371Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የማለዳ ጠቢብ እንዲህ ይጠይቃል..🤔 የመኸር አበቦች በክረምት ሊረግፉ ምነው እንዲህ ማማራቸው? በላያቸው ያሉ ደማቅ ቢራቢሮዎች ከትቢያ በስተቀር ምንድነው ልብሳቸው? የሰው ልጅ ሰውነት ወደ ሞቱ መሰብሰቡ ላይቀር ምንድነው መሽቀርቀር? እንደ ኩራዝ ቋያ በራሱ ነበልባል ራሱን ሊበላ ያብባል የሰው ልጅ ይረግፋል የሰው ልጅ መኸርና ክረምት ያው የራሱ ገላ..... ቴዎድሮ ስካሳሁን__(ቴዲ አፍሮ) @ZHabbesha @ZHabbesha
Show all...
እያንዳንዱ ሰው ከራሱ ጋር ጨዋታ አለበት። ለብቻው የሚቀዝፈው ባህር ለብቻው የሚነቃው ንቃት፣ ለብቻው የሚደማው ጠባሳ አለው። እናም ሰው በወጥመድ የያዝከው ወፍ አደለም። ልክ እንደአንተ ልቡ የሰፋበት መንገደኛ ነው። @ZHabbesha @ZHabbesha
Show all...
ለሞት ህይወት መስጠት.... በብራቅ ጠብመንጃ ለሚረግፍ መንደር፣ ይሰማል ብለህ ነው ጯሂ ቃል መሰደር፣ መልህቅ አይጥልም ቢገፋን ቢከፋን፣ ደም ላይ ይንሳፈፋል ያ ወላዋይ ዙፋን፣ ህይወትን ገንዞ ለሞት ህይወት መስጠት ህዝብ ልብ ውስጥ ከስሞ ስልጣን ላይ መሰንበት፣ ሰምቶ ማደባበስ ቅርሱ በሆነ ሀገር፣ ከባሩድ አይጮህም ሰው ምንም ቢናገር፣ ደንቆሮ ነው ምድሩ ጋራ ሸንተረሩ፣ ሰልቅጦ ዝም ነው ሰው ሲረግፍ ከስሩ፣ ተኳሹ ደንቆሮ ነፍስ መቀለጃ፣ ጆሮውን ሸጦ ነው የገዛው ጠብመንጃ፣ ተንታኙ ይተንትን ገጣሚውም ይግጠም፣ ፎቶ አንሺው ይለጥፍ አስከሬንና ደም፣ ድምፅ እያሳመረ ሌላው ያውርድ ሙሾ፣ በቃል ዘነዘና ይወቀጥ ስነስርዓቱ ይላም እንደጌሾ፣ ለአንድ ሰሞን ንዴት እናግሳ እንደአንበሳ፣ እንኳን የገዳይ ፍርድ የሟች እስኪረሳ፣ እለት እንክሰስው በየቀኑ እንማው፣ እኛ የፈራነውን "ፈረንጅ" እስኪሰማ፣ ዙፋኑ እስኪረጋ ምናለ ብንከፋ፣ ሰው ሞተብን እንጂ "ኢንተርኔት"አልጠፋ ሞት ማለት ዜና ነው እልቂት ማለት ቁጥር፣ ተስፋ መዘናጋት ፍትህ ማለት ሚስጥር፣ ገንፎ ሲቀርብ ነበር ማሰብ ስለስንጥር፣ እስከዛው.... ገዳይ ጥቂት ገድሎ አያገኝም ዝና፣ እልፎች ካልታረዱ ዜና አይደምቅምና፣ መርዶ ሸጦ አዳሪ በሟች ደም ይጠቀም፣ ጥግጋት ያጣ ህዝም እሬሳውን ይልቀም፣ አሌክስ አብረሃም✍✍✍✍ @ZHabbesha @ZHabbesha
Show all...
__እይልኝማ. ........... እንደዚህ ነው የሚያደርጉት በሙላትህ ላይ ማርዘነብ አድናቆታቸውን ከነመልካም ገፅታቸው ይዘው ከተፍ ይላሉ። ያን ሰሞን ፀሐይን በእጅህ ለማስጨበጥ ቀን ከለሊት እንቅልፋቸውን አተው እንቅልፍህን ጊዜህን ይወስዳሉ። አንተም ትፈቅዳለህ መወደድና መደነቅ ይሰማሃል። ቀን ሄዶ ቀን ሲተካ ለእያንዳንዱ አድናቆታቸው አንዳንድ ስድብ ይቸሩሃል። ሁሉም እንደዛ ነው የሚያደርጉት። እውነትህን እስኪጨብጡ አንተነትህን ለማጉደል ከዛ በጉድለትህ ላይ ይዘባበታሉ። የነበረችህን እውነት ያጣህ ሲመስልህ ቅስምህ ይሰበራል ። ካንተ በወሰዷት እውነት ሌላ አንተነትን ይፈጥሩልሃል። ሰላምህ ይታወካል ምናልባትም ሰላምህን ባወኩ ሰዎች አልያም አንተነትህን በገለፅክላቸው በየቱ እንደሆን ሳታውቀው ውስጥህ የሀዘን ረመጥ ውስጥ ይዘፈቃል። ቆይ ግን ህይወታችን እንዲህ ዛሬ ታይተው ነገ በሚሄዱ መንገደኞች መበጥበጡ ፍትሕዊ ነው???___ @ZHabbesha @ZHabbesha
Show all...
"አንዳንድ ትዝታ አለ" ዝምታችን ከዝምታ ገዝፎ በአረምሞ በተዘጋንበት ጊዜ ከዕዝነ ልቦናችን በኩል <<ኡኡኡ>>ብሎ የሚጮህ በዝግታ ካሳለፍነው የእድሜ ዘመን ቅፅበቶቻችን ከሽርፍራፊ የልጅነት ምስላችን በልጦ አልባችን ጥጋጥግ ካንጠለጠልነው ተናፋቂ ትዝታዎች መሃል ምናለ በደገምነው እያልን የምንመኘው ከትላንት ትዝታዎቻችን ጋር ባንቀላፋን ቁጥር ሳንሰለች ደጋግመን የምንኖረው አንዳንድ ትዝታ አለ። እንደ ወይን እያደር ጣዕሙ የሚጨምር። በእንባ በተሞሸርንበት ጊዜ እንኳን'በሀዘን ወህኒ ተወርውረን መረሳት፣ ክፉ አጋጣሚ ፊትለፊታችን ሲጋረጥ የመኖር ጣዕም ሲጎመዝዝ በእቅፉ የሚያስጠልለን አንዳንድ ትዝታ አለ። በዘመን መጎስቆል ባረመምንበት ጊዜ እንደ አዲስ የሚወልደን የማያረጅ የእድሜያችን ሞቃት ምዕራፍ 🦋ያብስራ(ደብተራው) @ZHabbesha @ZHabbesha
Show all...
ሞትን መች ፈርተን እናውቃለን? "እኛ መች ሞትን ፈርተን እናውቃለን? በሞታችን የሚሞቱ በሞታቸው የምንሞት ብዙ ሰዎች አሉ እንጂ እኛ መች ሞትን ፈርተን እናውቃለን ። ይልቅ ሞትን በፍቅር ተሳስበን እንግደለው። ቤት መቀመጥ ያቃተን መራባቸው የሚርበን ሰዎች ስላሉን እንጂ ቤት ጠፍቶን አደለም። ይልቅስ አብረን በር እንዝጋ እኛ እቤት ስንሆን ቀን ዳቦ ፍለጋ አደባባይ በሚሰፍሩት ዱኩማን ላይ ለሚዘንበው መከራ ማን ጥላ ይዘረጋል? ማንስ አቅም ኖሮት የሞት የሲቃ ዜናቸውን ለመስማት ከሳሎን ይቀመጣል? እባካችሁ አብረን በር እንዝጋ፣ አብረን እንሸመጥ፣ አብረን ቁርስ እንብላ አብረን ምሳ እንድገም። አለዚያ ይህም ታሪክ ሆኖ አስተዛዝቦን ያልፋል።ይህን ብለን እንጂ እኛ መች ሞትን ፈርተን እናውቃለን?" @ZHabbesha @ZHabbesha @ZHabbesha @ZHabbesha
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ ድል አደረገች 💚💛❤️ ሀገራችን ኢትዮጵያ ግብፅን በፍፁም የበላይነት ድል አደረገቻት። የዛሬውን ጨዋታ ለማስተናገድ ብቁ ሜዳ አጥታ በሰው ሀገር ማላዊ ከግብፅ አቻዋ ጋር በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ የተፋለመችው ሀገራችን ኢትዮጵያ እጅግ ድንቅ እንቅስቃሴ በማድረግ ግብፅን አሸንፋለች። ሀገራችን ሙሉ ጨዋታውን በከፍተኛ የበላይነት ነው ያጠናቀቀችው። ማላዊያን አንድም የግብፅ ሽንፈት ለሀገራቸው የሚሰጠውን ከምድብ የማለፍ እድልን ታሳቢ አድርገው በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በሜዳ ውስጥ ባሳየችው ድንቅ እንቅስቃሴ ተስበው ከፍተኛ ድጋፍ ሲሰጡ ታይተዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ለሀገሩ እና ለኳስ ያለው ፍቅር ምን ያህል እንደሆነ ይታወቃል የዛሬው ጨዋታ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ተደርጎ ቢሆን አሁን ካለው የበለጠ ድባብ ይኖረው ነበር። @tikvahethiopia
Show all...
መመሪያ ነው🤔 ድሮ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስተሩ አንዲትን የገጠር ቀበሌ ሊጎበኙ ይወርዳሉ። በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላትም😊አብረዋቸው ለዚህ ጉብኝት ይወርዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስተሩም ለጉብኝት የተመረጠችውን የአንዲት እናት ቤት ሲጎበኙ በኑሮዋ ዝቅተኝነትና በድህነቷ ክፉኛ ተነክተው ስቅስቅ ብለው ማልቀስ ይጀምራሉ። ይሄን የተመለከተው የክልሉ አስተዳደርም ማልቀስ ይጀምራል። የክልሉን አይቶ...የዞኑ...የዞኑን አይቶ የወረዳው መላቀስ ሆነ። ቀን በቀን አብሯት የሚኖረው ኑሮዋ ከአብዛኛው የቀበሌው ነዋሪ እንደማይለይ የሚያውቀውም የቀበሌው አስተዳደርም ግራ ገብቶት ወደ ወረዳው አስተዳዳሪ ጠጋ ብሎ የሚያለቅሱበትን ምክናያት ይጠይቀዋል። የቀበሌውም አስተዳዳሪ አንገቱን እንደደፋና ፊቱን በእውሸት እንባ እንደረጠበ በሹክሹክታ እኝዲህ ብሎ መለሰለት👇 "ከላይ የወረደ መመሪያ ነው ዝም ብለህ አልቅስ"😢😢😂😂 @ZHabbesha @ZHabbesha
Show all...
"በመስመሩ መዘበራረቅ ውስጥ ህይወት አለ። መኖር ማለት ትክክለኛ እና ልክ አለመሆን ማለት ነው።ቀጥዩን እርምጃ ለመራመድ የምናነሳው እግራችን ሳይቀር በተዘበራረቁ መስመሮች ቀጥ ብሎ መራመድ ሲችል ህያው ሰው እንባላለን። ውጣ ውረድ በበዛብ አለም ውስጥ መረጋጋት ከድሎት እንጂ ከመኖር አያግድም። ህይወት በዝብርቅርቅ ምቾት መኖርን ታጎናፅፋለች። በመውጣትና በመውረድ በማግኘትና በማጣት በሰላምና በጦርነት መካከል የምንቀኘው የየግላችን የህይወት መስመር አለ" @ZHabbesha @ZHabbesha
Show all...